Esleman Abay የዓባይ ልጅ
СтатистикаI Blog about global news analysis specially on the issue of Nile river Horn of Africa and the multipolar world affairs.
- Последний пост
- 22:14
- Последнее чтение
- 00:19
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 42
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 400
- 1/48двое суток
- 1 604
- 1/72трое суток
- 1 730
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Egyptian proverb: They asked the Pharaoh “what made you a tyrant?”. He said, "no one stopped me". Kudos to the pro Cairo echo chambers
የደብረፅዮን ህወሃት ወደ ኩርሙክ ግንባር ለአል ቡርሀን ተሰልፎ የ RSF ሀይሎችን እንዲዋጋ ከ TPLF hardliner ቡድን ትግራይ የተላከው ኢትዮጵያዊ ታዳጊ በሄሜቲ የፈጣን ድጋፍ RSF ሀይሎች ቁጥጥር ስር ሆኗል 💔
без подписи
🚨 ህወሃት ጦርነት ከፈተ ከሰሞኑ ከባድ መሳሪያዎችና ተጨማሪ ታጣቂዎቹን ሲያስጠጋ የነበረው የ ህወሃት hardliner ቡድን ዛሬ ማምሻውን በራያ እና አፋር በኩል ጦርነት መጀመሩ ተሰምቷል። (የሀገር ውስጡ) ፅምዶ ሰብሳቢ የሆነውና የ ህውሃት አክራሪው ክንፍ 33 እና 44 በተባሉ አርሚዎቹ አማካኝነት ተኩስ የከፈተባቸው ቀጠናዎች 👇🏾 ➤ዓዲጉደም ➤ደቡብ ወጀራት ➤ኮንካ ➤ጎነቕ ➤ቶንሳ ➤ንፋሮ መጋለ በተባሉ ቀጠናዎች ሲሆን ከዓዲ ቀይሕ ወደ ገራርሳ እና ቶንሳ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በትግራይ ሰላም ሰራዊት ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። 'የትግራይ ሰላም ሰራዊት' ወይም TPF በሚል ስያሜ የተደራጀው ታጣቂ ሀይልም ወደ መቀሌ ለመግባት ዝግጅቴን ጨርሻለሁ ማለቱን ከሳምንት በፊት አሳውቆ ነበር። ፍትህ ለትግራይ እና ለኤርትራ ህዝብ ውድቀት ለህውሃትና ለሻዕቢያ ድል ለኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት 🇪🇹 ነሃሴ 1 ቀን፣ 2018 አ/ም
በዚህ የህወሃት አለቆች የሚመራው የትግራይ ክልል አስተዳደር ባወጣው መግለጫው፣ የፌደራል መንግሥት በምዕራብ ትግራይ “ግልጽ ወታደራዊ ጥቃት” መክፈቱን አስፍሯል። በአንፃሩ በዛሬው ቅዳሜ እለት፣ በሸረሪና የተፈጠረው ውጊያ ከሰሞኑ በተከታታይ ሲወጡ የነበሩትን የህወሀቱን የጦርነት ዝግጅት እና ነጋሪት የሚጎስሙ መረጃዎችን ተከትሎ የተከሰተ ሆኖ ነው የተገኘው። ስለ ግጭቱ የህወኃት ቡድን መግለጫ በማውጣት ቀዳሚ ሆኖ ተስተውሏል - በመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ መረጃ የለም። ቀደም ባሉ ጊዜያት ከፌደራል መንግስት በኩል ተደጋጋሚ የሰላም አማራጭ ጥሪ መደረጉ፣ በምላሹ hard liner የተሰኘው የህወሀት ቡድን ችላ በማለት ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ታጣቂ ሀይሎች ጋር በመስማማት ለጦርነት ሲንቀሳቀስ እንደነበር የሚታወስ ነው። . . ከታች ያለው መረጃ ደግሞ የአርሚ 70 አባል የሆነው የፃፈው ነው:- "አንድ የአርሚ 70 አባል የሆነ የቤተሰቤ አባል ከሱዳን ወሰን ሸረሪና አካባቢ ደውሎልኝ ነበር። ዛሬ ማታ ሑመራ እንገባለን፤ ተዘጋጁ የሚል ትዕዛዝ ወርዶልናል። ሙሉ ሌሊት ስንጓዝ አድረናል። ሲነጋ አካባቢ የመጣበት ቦታ የማይታወቅ፣ ከሰማይ ሲወርድ ምንም ድምፅ የሌለውና መሬት ላይ ሲያርፍ ብቻ ድምፅ የሚያሰማ ተኩስ ይፈነዳ ጀመር። ሩቅ ሆነን ስናያቸው የነበሩ የመካናይዝድ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ማለት ይቻላል ተቃጥለው እሳት ሲነድ ብቻ ይታያል። እግረኛ የሆንነው ደግሞ የመካናይዝድ ተሽከርካሪዎች እየጠፋ እንደሆነ ስለተረዳን ሁላችንም ተበታትነናል። ከእኛ ጋር አንድ የሬዲዮ ኦፕሬተር እና የሬዲዮ መገናኛ የያዘ አለ፤ ነገር ግን ከኃላፊዎች የደረሳቸው ምንም ዓይነት መረጃ የለም። ለኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እጃችንን እንዳንሰጥ በፊታችን የሚታይ ሠራዊት የለም። ጨንቆናል! . . ተጨማሪ 👇🏾 - የጥቃቱ መነሻና ቦታ፡ አካባቢውን በኃይል ለመቆጣጠር በማሰብ፣ በሱዳን በኩል የተደራጁ የ'ሳምሪ' ታጣቂ ኃይሎች ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከፍተዋል። ታጣቂዎቹ ጦርነቱን የጀመሩት በሱዳን ድንበር በኩል በ'ሸረሪና' እና በወልቃይት ጠገዴ ዞን፣ ቃብትያ ሁመራ ወረዳ ስር በምትተዳደረው የበረከት ከተማ አቅጣጫ ድንበር ጥሰው በመግባት ነው። - የውጊያው ሁኔታ፡ በበረከት ከተማ እና በሸረሪና አቅጣጫ ጥቃቱን የጀመሩት ከሱዳን ሰርገው የገቡት ታጣቂዎች ('አርሚ 70') በቀላል መሳሪያዎች ትንኮሳ የከፈቱ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መጠነ ሰፊ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። - በድሮንና በመድፍ የታገዘ አፀፋ፡ አሁን ላይ ከሁመራ ወደ በረከት ከተማ እና ሸረሪና አቅጣጫ ከፍተኛ የሆነ የመድፍ ድብደባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በሰማይ ላይም የድሮን እንቅስቃሴ በግልፅ እየታየ ነው። የከባድ መሳሪያው (መድፍ) ተኩስ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ርቀት ላይ በምትገኘው ሁመራ ከተማ ውስጥ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እያነዘረ እንደሚገኝ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል። - የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ፡ በበረከት እና ሸረሪና አቅጣጫ የተጀመረውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በአካባቢው ከፍተኛ ወታደራዊ ውጥረት ያንዣበበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከፈተበትን ይህንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ለመመከት እና ለመደምሰስ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አረጋግጠዋል። - በድምፅ አልባ መሳሪያ (መሬት ላይ ሲደርስ ብቻ የሚፈነዳ መሳሪያ) በርካታ የአርሚ 70 ታጣቂዎች ላይ ሞት እና ጉዳት ማድረሱን ምንጮች ጠቁመዋል። - የታጣቂዎቹ የውጊያ አላማ በዛሬው እለት ሁመራን ለመቆጣጠር ከአክራሪ hard liner ህወሀት አለቆቻቸው የተሰጣቸው እቅድ መሰረት ነው።
ሸረሪና ላይ ግጭት መከሰቱን አሜሪካ “አክራሪ ህወሃት” ስትል የፈረጀችው ቡድን አሳወቀ በትግራይ ክልል በአሜሪካ አክራሪ ህወሃትነት (hard liner) ተብለው የተፈረጁት አመራሮች ግጭቱ የተፈጠረበትን “ምዕራብ ትግራይ” ነው ሲሉ በመግለጫቸው አሳውቀዋል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በቀይ ባህር እና በባቢል መንደብ የባህር መስመር ላይ በሁቲ ታጣቂዎች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመግታትና የመርከቦች እንቅስቃሴ ደህንነት ለማስከበር፣ የአካባቢውንና የዓለም አቀፍ ሀገራትን ያካተተ አዲስ የባህር ላይ የደህንነት ጥምረት (Maritime Security Coalition) ለመመስረት ውይይት መጀመሩን የሮይተርስ ዘገባ ያመላክታል:: ምንም እንኳን የሳዑዲ ዓለም አቀፍ ኮሙዩኒኬሽን ማዕከል በይፋ አስተያየት ከመስጠት ቢቆጠብም፣ ጥምረቱ በምዕራባውያን ከሚመሩት ወታደራዊ ህብረቶች ባሻገር የቀይ ባህር ዳርቻ እና የክልሉ ሀገራትን ያቀፈ ሁለገብ መድረክ ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ይነገራል:: የጥምረቱ ጂኦፖለቲካዊ አንድምታ ከጥምረቱን ከሚቀላቀሉ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ባላት ዘብ የመቆም ታሪክ፣ በወታደራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ግዝፈቷ ሳቢያ የጥምረቱ ዋና ተሳታፊ እንድትሆን መደላድል ይፈጥራል:: ሳዑዲ አረቢያና ቀጣናዊ አጋሮቿ የኢትዮጵያን አቅም እንዲፈልጉ ከሚያደርጋቸው ጉዳይ አንፃር ኢትዮጵያ በዚያ መጠን ፍላጎት የማሳየት ጉዳይ ዝቅተኛ ነው - ምናልባት ለኢትዮጵያ አጓጊ ሊሆን የሚችለው ከባህር በር ጉዳይዋ ጋር የተጣጣመ ስትሩቴጂ ከሪያድ ይሁንታውን ይዞ የተገኘ እንደሆነ ነው። ይህ አሞነእኛ እንቅስቃሴ በቅርቡ የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) አዛዥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢ የማይታለፍ የደህንነት እና የምስራቅ አፍሪካ የማዕዘን ድንጋይ (Anchor State) መሆኗን ገልጸው ከተናገሩት ይፋዊ እውቅና ጋር ይገናኛል:: የኢትዮጵያ በዚህ ጥምረት ውስጥ መካተት ከአሜሪካ (AFRICOM)፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) እና እስራኤል የቀይ ባህር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም ሲሆን፣ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማግለልና ለመክበብ (Anti-Ethiopia Encirclement) የምታደርገውን የቆየ የዲፕሎማሲ ሴራ ሙሉ በሙሉ ያከሽፈዋል:: ይህም ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ ላይ ያላትን ተፅዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ የቀጣናው የማይታለፍ ኃይል መሆኗን የሚያረጋግጥ ትልቅ የዕድል ደጅ ይከፍትላታል:: የሁቲ ታጣቂዎች በሳዑዲ የነዳጅ ማጓጓዣ መርከቦችና ወደቦች ላይ ያሳዩትን ተደጋጋሚ ስጋት ተከትሎ፣ ሪያድ የቀይ ባህርን ደህንነት በብቸኝነት ማስበቅ ከባድ መሆኑን በመረዳት የቀጣናውን ሀገራት ያቀፈ የጋራ መከላከያ መዋቅር ለመገንባት መገደዷን ያሳያል:: የዚህ ጥምረት መመሥረት በቀይ ባህርና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚታዩ የኃይል ሚዛኖችን የመቀየር አቅም ያለው ሲሆን፣ የሳዑዲ አረቢያ ተነሳሽነትም ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን መልሳ ለማጠናከር የምታደርገውን ጥረት ያሳያል::
ሳዑዲ አረቢያ በቀይ ባህር አዲስ የባህር ላይ ጥምረት ለመመስረት እንቅስቃሴ ጀመረች 📌 ኢትዮጵያ በሳዑዲው ጥምረት ውስጥ የምታበረክተው ከፍተኛ ሚና ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል
“የቀይ ባሕር ጉዳይ ዳርቻውን ለተቆናጠጡ አገራት ብቻ ነው ከተባለ፣ በዓባይ ውሃ የመጠቀም ብቸኛ አዛዦችም ለወንዙ ውሃ የሚያበረክቱት ብቻ ናቸው” — አሜሪካዊው አምባሳደር በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ቲቦር ናጊ፣ ግብፅ እና ኤርትራ በቀይ ባሕር እና በናይል ወንዝ ጉዳይ ላይ የሚያንፀባርቁትን ጎዶሎ አቋም የሚነቅፍ አተያይ በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል። ግብፅ እና ኤርትራ “የቀይ ባሕር መብትና ስለ ቀይ ባህር ጉዳይ የመናገር ስልጣን የባሕር ዳርቻውን ተቆናጥጠው ለሚገኙ አገራት ብቻ” ነው” የሚለውን አቋም በማስተጋባት፣ ኢትዮጵያን ከቀጠናው የጂኦፖለቲካ ውይይት ለማግለል እንደሚሞክሩ ጠቁመዋል። አምባሳደሩ ይህንኑ አመክንዮ ወደ ናይል ወንዝ ፍሰት እና የአጠቃቀም ስልጣን ጋር በማዛመድ፣ ኢትዮጵያ ከ85 በመቶ በላይ የሆነውን የዓባይ ውኃ የምታበረክት ሀገር በመሆኗ፣ የወንዙን አጠቃቀም የመወሰን ህጋዊ የመብት ባለቤትነቷ አሳማኝ መሆኑን አንፀባርቀዋል። አስተያየታቸው ግብፅ በቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች (1929 እና 1959) ላይ ተመርኩዛ የምታንፀባርቀውን ለብቻዋ የመጠቀም አቋሟ ለትብብር አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን የሚጠቁም ነው። የአምባሳደር ናጊ አስተያየት ከሌሎች አለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር የሚስማማ ሲሆን፣ የአለም ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ሀብት ህጎች የሚያስቀምጡት “ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም” መርህ ከዚህ አመክንዮ ጋር ይጣጣማል። ኢትዮጵያ በናይል ተፋሰስ ካሉ 11 አገራት መካከል እስከ 88% የውኃ አስተዋፅዖ እንዳላት የማይካድ ሳይንሳዊ እውነታ ነው። ተንታኞች እንደሚገልጹት፣ ግብፅ በቀይ ባሕር ላይ የባሕር ዳርቻ ርዝመቷ 2,450 ኪሎሜትር ሲሆን፣ ኤርትራ 1,200 ኪሎሜትር የባህር ዳርቻ አላት። ኢትዮጵያ ግን ቀጥተኛ የባሕር ዳርቻዋን የተነጠቀች ሲሆን፣ ከ125 ሚሊዮን በላይ ለሚገመተው ህዝቧ የባሕር በር ማግኘት ህልውናዊ ጉዳይ ነው። የግብፅ የናይል ውኃ ድርሻ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ከህዳሴ ግድቧ በፊት ከራሷ ወንዝ 0.5% ያህሉን ብቻ ነበር ትጠቀም የነበረው። “So if as Egypt🇪🇬 & Eritrea🇪🇷 say only “littoral states” have anything to say about Red Sea, then logically only nations which put water into the Nile, can determine its use,” - Ambassador Tibor Nagy, American diplomat & former Ambassador to Ethiopia🇪🇹
“የቀይ ባሕር ጉዳይ ዳርቻውን ለተቆናጠጡ አገራት ብቻ ነው ከተባለ፣ በዓባይ ውሃ የመጠቀም ብቸኛ አዛዦችም ለወንዙ ውሃ የሚያበረክቱት ብቻ ናቸው” — አሜሪካዊው አምባሳደር “So if as Egypt🇪🇬 & Eritrea🇪🇷 say only “littoral states” have anything to say about Red Sea, then logically only nations which put water into the Nile, can determine its use,” - Ambassador Tibor Nagy, American diplomat & former Ambassador to Ethiopia🇪🇹
MV ጊቤ ከሆርሙዝ ሰርጥ ወደ ቤቷ እየተመለሰች ነው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት ሳቢያ በሆርሙዝ ሰርጥ ለወራት ተይዛ የነበረችው የኢትዮጵያ ንብረት የሆነችው የጭነት መርከብ MV ጊቤ፣ ከነጭነቷ ወደ አገሯ ጉዞ መጀመሯን የሳተላይት መረጃዎች አረጋገጡ። የዚህች መርከብ በሰላም መለቀቅ ለኢትዮጵያ የወጪና ገቢ ንግድ ትልቅ እፎይታ ነው። 🇪🇹 MV ጊቤ በ347 ዓለም አቀፍ የወደብ መዳረሻዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከሚያውለበልቡ መርከቦቻችን መካከል አንዷ ናት። MV ጊቤ በአሁኑ ወቅት በኦማን ገልፍ አካባቢ የምትገኝ እና ወደ ጅቡቲ በመጓዝ ላይ ስትሆን፣ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ በ11.3 ኖት ፍጥነት እየተጓዘች ሲሆን እ.አ.አ ሰኔ 28 ከምሽቱ 2:00 (20:00) አካባቢ ወደ መዳረሻዋ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል።
የሚሥ ፀዳለ ድምፅ ማራኩ መሆኑን ገና ዛሬ(June 2026) ተረዳሁኝ…..። በዚህ ውብ ድምፅ ላይ የአቋም ወጥነት፣ እና ልባዊ ሐቀኝነት ቢጨመርበት ምን ያህል አማላይ መሆን ትችል እንደነበር ሳስብ ቁጭት ይመዘምዘኛል —- ለአብነትም:- እስከዛሬዋ ምሽት ድረስ “ሁሉን ቻይ” ነህ ስትለው የነበረውን የደብረፅዮን ክንፍ እንደዛሬው በቅፅበት አርገፍግፋ በመጣል “ህወሃት ምንም አይደለም” የሚል የሽምጠጣ ባህርይ ባይኖርባት…፣ እንዲሁም፣ ህወሃትን ካራገፈችበት ደቂቃ አንስታ ከመቅፅበት ከ “ደፂ-first” አቋሟ ተወንጭፉ “ስለ ግብፅ ጉልበተኝነት እና ገንዘባምነት”፣ “ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም”፣ “ክቡርነት”” ስትጀማምር ፍጥነቷ በሰውኛ የፍጥነት መለኪያ አይደለም በሀይፐርሶኒክ ሚሳይሎች የ (match 5, match 6,..match 27…) አሀዶች ደረጃ በሚመደብ ሽምጠጣ ላይ ባልመለከታት ኖር ምን ያህል አወንታዊ ነገር ትፈጥር እንደነበር አሰብኩት …ነበርርር ባይሆን…። ስለ ዓባይ ድምፅ የሆኑ (እኔን መሰል) ዜጎችን ‘የብልፅግና ዲጂታል ሚሊሺዎች’ በሚላ ተቀፅላ ስትጠራን ወላሂ ለኢትየጵያ(130 ሚሊዮን) ህዝብ ያላት ንቀት … ብቻ ብዙ ብዙ ለመፃፍ የሚገፋፋ ነበር፣ ይህ በዚህ ይቅር፣ ነገር ግን ከ state department ምን ምን ሲበጀትላት እንደቆየች (በግሌ) በማስረጃ ማሳመን እችላለሁኝ፣ ….እንዲህ አይነቱን አይንን በጨው የታጠበ ክህደት ዝም ለማለት በጭራሽ ትእግስት አይኖረኝም። አንድ ነገር ብቻ አስደስቶኛል፣ ክብርት ፀዳለ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተውረገረገች፣ በመቶ ሺዎች ዶላር የተቀበለችበትብ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት እየረገመች፣ እየተቆላጨች፣ እየወቀሰች እንዲሁም ህወሃትን “የትም የሚወረወር ምንም ረብ የሌለው ቡድን” በማለት እየጠራች፣ በአንፃሩ ስለ ዓባይ ውሃ ያገባኛል፣ ከሚል ሐበሻዊ ወኔ ጊን ለጎን እንደገና ደሞ “ግድቡ መመረቁም “አልተረጋገጠም” የሚል እየቀላቀለች “የአምታታው በከተማ” ድራማ መጀመሯን ስመለከት፣ አልሀምዱሊላህ አልኩኝ። እንኳንም በህይወት ቆየሁኝ፣ እንኳንም (አንቺም) በህይወት ቆየሽ፣ እኔም ይህን የዛሬውን “ልውጠተ - ፀዳለ” እንኳን ለመታዘብ በቃሁኝ፣ በእግረ መንገድም ‘ኢትየጵያ ሁሌም intact’ የመሆኗን እውነታም ለማረጋገጥ (ተጨማሪ) መልካም አጋጣሚ ሆነኝ…። በመጨረሻም፣ በመጨረሻም…..እንደው ሌላው እሺ ይቅር፣ አንቺ ከተናገርሺውና፣ የአሉላ አባ ነጋ ቀዬ ትግራይ “የአለም የሃይል አሰላለፍ የተደረመሰባት…” ከምትይን፣ ምን አለበት ትንሽ ምላስሽን አድጦሽ፣ ቲኒሽ ተሳስተሽ “ኢትዬጵያ የትላንቷ የሁለተኛው የአለም ጦርነት ዋዜማ ባሩድ” እንዲሁም የዚህ ዘመን የ multi polar world ጮራ መውጫ አድማስ ነሽ” ስትይይ በሰማሁሽ ስል በቀናነት ተመኝቼ ነበር። ነገር ግን “once Tsedale always Tsedale” አይነት የተባነነባት አነብናቢ ሆነሽ ስመለከትሽ ድጋሚ ቁጭት ውስጤን መ ዘ መ ዘ ው … #የዓባይልጅ Esleman Abay
без подписи
без подписи
без подписи
የሚሥ ፀዳለ ድምፅ ማራኩ መሆኑን ገና ዛሬ(June 2026) ተረዳሁኝ…..
በፈረንሳይ የቡድን 7 G7 ስብሰባ ላይ ዶናልድ ትራምፕ ከግብጹ ፕሬዝዳንት ኤል-ሲሲ ጋር ዛሬባደረገው ውይይት ወቅት የሰጠው መግለጫ ለኢትዮጵያ እንደ ማስጠንቀቂያ ደወል ሆኖ የተሰማበት ነው። በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ትራምፕ ለግብጹ መሪ ያላቸውን ልዩ ወገንተኝነት ሳይደብቁ እየሳቁና እየቀለዱ። "ግንኙነታችን ለረጅም ጊዜ በጣም ጠንካራ ነበር። በአንድ ሆቲል ውስጥ አገኘሁት… ፍቅር ያዘን፣ (እኔ) ፍቅር ያዘኝ… [ፈገግ እያለ] በመካከላችን ትልቅ የመግባባት ኬሚስትሪ አለ። በጣም ድንቅ ግንኙነት ነው።" ካሉ በኋላ ነበር፣ ይህ የነሱ የግል "የፍቅር ግንኙነት" በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ በሚኖራቸው አቋም ላይ ሙሉ በሙሉ ተጽዕኖ የማሳደሩ አይቀሪነት በግልፅ የተነገረው። ትራምፕ ሆዬ የግብጽን የሐሰት ትርክት ሙሉ በሙሉ ተላብሶ፣ የኢትዮጵያን የመልማት ሉአላዊ መብት በመናቅ ገዙፉን እና የአሜሪካ ኩባንያዎች ጭምር ኮረንቲ እያገኙበት የሚገኘውን ግድብ "ትንሽዬ የግድብ ፕሮጀክት" በማለት አሳንሰው ሲገልፁት ነው የተደመጡት። ሲቀጥሉም፣ ግብጽ በኢትዮጵያ "በጣም፣ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተበድላለች" ይህ ግድብ "ለግብጽ ከባባድ ችግሮች እየፈጠረባት ነው" በማለት ለሲሲ ደግሞ ተከታዩን ቃል ገብተውለታል፦ "እኔ ያንን (የ 2020) ስምምነት ቋጭቸው ነበር... ግን ወደዚሁ ወደ ግድቡ ጉዳይ እንደገና እንመለስበታለን። መፍታት እንችል እንደሆነ እናያለን።" ካለው በኋላ “እሺ?!” እያለ በማባበል እየተመለከተ “አብሽር” ይለዋል። ይህ የትራምፕ ንግግር አሜሪካ ስለ ህድቡ ጉዳይ ገለልተኛ አደራዳሪነቷ ማክተሙን ያረጓግጣል። አሜሪካዊው የሲአይኤ ሰው እና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ከፍተኛ ተንታኝ ካሜሮን ሁድሰን ሳይቀር Cameron Hudson) ማስጠንቀቂያ ሲሰጡበት ተስተውለዋል። ሁድሰን በአስተያየታቸው "እኔ በኢትዮጵያ ቦታ ብሆን ኖሮ፣ ከዚህ የትራምፕ ንግግር በኋላ በፍጹም አሜሪካ በምትገኝበት በማንኛውም የድርድር ጠረጴዛ ላይ አልቀመጥም ነበር።" ሲሉ ትዊተር ላይ ፅፈዋል። በአጭሩ፣ ኢትዮጵያ በአሜሪካም ሆነ በትራምፕ በሚመራ የድርድር ጠረጴዛ ላይ መቀመጥ የለባትም። ምክንያቱም:— —የድርድር ውሳኔው አስቀድሞ የተዘጋጀና የተፃፈ ስለሆነ። ትራምፕ አበክረው "ኢትዮጵያ ግብጽን በድላታለች"፣ "ትልቅ ችግር እየፈጠረችባት ነው" በማለት አስቀድመው ፍርዳቸውን ሰጥተዋል። —ከአለም አቀፍ ህግ ይልቅ "የግል ፍቅር" በትራምፕ ቅድሚያ ተሰጥቶታል። የአንድ ልዕለ-ኃያል ሀገር የውጭ ፖሊሲዋ ከአለም አቀፍ የውሃ ህግ ይልቅ በግል መግባባት እና በግለሰቦች ስሜት ላይ ሲመሰረት፣ ፍትሃዊነት ድራሹ ይጠፋል። —የትራምፕ የማስገደድ እና ግድብን በሀይል የማጥቃት የቀደመ ታሪክ በራሱ የማይዘነጋ ነው። በመጀመሪያው የስልጣን ዘመን ወቅት ኢትዮጵያ በአሜሪካ የተዘጋጀውንና ለግብጽ ያደላውን ስምምነት በምክንያት ስትቃወም፣ የትራምፕ አስተዳደር በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እርዳታ ማገዱ እና ትራምፕ "ግብጽ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች" ብሎ በይፋ መናገሩ፣ አሁን አሁን ደሞ "ወደ ግድእቡ ጉዳይ እንመለሳለን" ሲል ያንንኑ ጥቃት በድጋሚ ከመጫር ውጭ ሌላ ውጤት ሊኖረው አይችልም። ⚠️ዳኛው የከሳሽህ ጋር የቅርብ ጓደኛ በሆነበት፣ ውሳኔውንም አስቀድሞ ባሳወቀበት እና ለተከሳሽ (ኢትዪጵያ) ያለውን ንቀት በይፋ እየተናገረ ባለበት፣ ሲቀጥልም "ከከሳሽህ ጋር ፍቅር ይዞኛል" ብሎም በሚቀልድበት የፍርድ አደባባይ ላይ ዘው ብለህ ገብተህ ፍትህን አገኛለሁ ማለት አይታሰብም። ከጂ7 (G7) የተደመጠው የአሜሪካ መግለጫ ለአኢትዮጵያ ግልጽ እና ግልፅ ነው — ዋሽንግተን ከአሁን በኋላ የግድቡ አደራዳሪ አይደለችም—አሜሪካ ራሷ የግብፁ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አካል እና አስፈጻሚ ናት! የህዳሴ ግድባችንን እና የውሃ ሉዓላዊነታችንን ለማስከበር ከነጩ የትራምፕ ቤት ውጪ ሌሎች አማራጮችን ብቻ ማማተር የግድ ይላል። #የዓባይልጅ #Ethiopia #GERD #NileRiver
የትራምፕና አል ሲሲ "የፍቅር እና የግድብ ጉዳይ"
ኤፍሬም ስብሓትና ጴጥሮስ ሰለሞን አሁን የፖሊት ቢሮ አባሎች ቀደም ሲል በ1966 ዓ.ም. በመንካዕ ንቅናቄ ውስጥ የተሣተፉ ከፍተኛ የሆነ የክሕደት ተግባር የፈጸሙ ግለሰቦች ስለሆኑ፣ በኢሳያስ ላይ ለመነሳት የማይችሉ ደካሞች ናቸው፡፡ በተመሳሳይ ሆኔታ ሌሎችም በዛ ያሉ የማዕከላዊ ኮሚቴው አባሎች በኢሳያስ ጉዳቸው የሚታወቅባቸው ስለሆነ፣ መሣሪያዎች እንዲሆኑ ኢሳያስ መርጥዋቸዋል፡፡ - በአሁኑ ጊዜ የሻዕቢያ መሪዎች ከፍተኛ በሆነ የፖለቲካና የወታደራዊ ውጥረት ላይ ይገኛሉ፡፡ ተገንጣዮቹ በተለመደ የማወናበጃ ዘዴያቸው ተስፈንጣሪ መሰል መፈክሮቻውን ከማነብነብ በስተቀር ጭልጥ ብለው ቀድሞ ከመሠረቷቸው ኢምፔሪያሊስቶች ጉያ ተወሽቀዋል፡፡ የሻዕቢያ መሪዎች በተለይ ተለዋዋጭ ታክቲኮችን በመቀየስ በየቀኑ አቋማቸውን ይለዋውጣሉ፡፡ “ታክቲክና እስትራቴጂ” ሳይንሳዊ ትርጉምና ዲያሌክታዊ አንድነት ያላቸው ጽንሰ ሐሳቦች ሲሆኑ፣ የሻዕቢያ መሪዎች ግን በተለይ ታክቲክን እንደ ላስቲክ እንደፈለጉትና እንዳሻቸው ሲስቡትና ሲጠመዝዙት ቆይተዋል፡፡ ከዑስማን ሳልሕ ሳበ ጋር ከ1965 እስከ 1968 ዓ.ም. የነበረው ግንኙነት ከአድሃሪ ጋር የሚደረግ ልዩ ታክቲክ ነው በማለት ሳያመነቱ አወሩ፡፡ በ1974 ዓ.ም. ደግሞ በሳውዲ ኢሳያስ በሰጠው ቃለ መጠየቅ “እኔም ሆንኩኝ ድርጅቱ ማርክሲስቶች አይደለንም” በማለት የሰጠው መልስ የሳውዲን መንግሥት ለማስደሰት የተደረገ ታክቲክ ነው ተባለ፡፡ የአሁኑ አዲስ ታክቲክ ደግሞ ከኢራቅ የባዓስ ፓርቲ ጋር ግንኙነት በመፍጠር በኤርትራ ካሉት ተገንጣይ ቡድኖች አንዱ ከሆነውና በዑስማን ዓጀብ ከሚመራው ድርጅት መካከል የባዓስ ፓርቲ ተከታይ “ከሕዝባዊ ኃይልታት ሐርነት ማዕከላይ ባይቶ” አንድነት መፍጠር ነው ሲል አቋሙን እንደእስስት ይለዋውጣል፡፡ ለመሆኑ በአፍሪቃ ቀንድ ኢምፔሪያሊዝም ማረፊያ እንደአጣች አውሮፕላን ተጨንቆ ሲባዝን ተገንጣይ ቡድኖች ማረፊያ ሜዳ ለመስጠት የሚፍጨረጨሩበት ምክንያት ምን ይሆን? ይህ በቀጥታ የኢምፐሪያሊዝም አሻንጉሊት መሆናቸውን አያስረዳንም? የታክቲክስ ትርጉም ይህን ያህል ሊዛባ ይችላል? -እንግዲያውስ ታክቲክ ይህን ከመሰለ ተገንጣዮቹ ነገ ከእስራኤልና ከደቡብ አፍሪካ ጋር የሚፈጥሩትን ግኑኝነት ሕጋዊ አይሉት ይሆን? -የሻዕቢያ ጉድ ሀ እና ፐ ተብሎ ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ጊዜው ይርዘም ይጠር እንጂ ዕውነት እውነትነቷን ሳታረጋግጥ ተድበስብሳ ትቀራለች ማለት ዘበት ነውና የተገንጣዮች ፀረ ሕዝብነት ራቁቱን ቀርቷል፡፡
ደግሞ የግንባሩ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆኖ እንዲሠራ በመስማማት ጀብሃን ለመቋቋም በአንድነት ተነሱ፡፡ - የእርስ በርሱ ውጊያም እየከረረ በመሄዱ ጀብሃ ከዚህ በፊት በቀላሉ ያስመዘግባቸው የነበሩት ድሎች ሊገኙ አልቻሉም፡፡ በእርስ በርሱ ውጊያ ውስጥ ሻዕቢያ ምልምል አባሎችን ከደጋው ክፍል በብዛት ያገኝ ስለነበር፣ እየተጠናከረ መጣ፡፡ ሻዕቢያ በዑስማን ሳልሕ ሳበ እስከ አፍንጫው ድረስ ታጠቀ፡፡ የአንድነቱ ግንባር ጀብሃን መቋቋም በመቻሉ የጀብሃ አደገኛነት እየመነመነ ስለሄደ ለጊዜው ታፍኖ የነበረው ሁለተኛ ቅራኔ ማለትም የሥልጣንና የጎሳ ቅራኔ ብቅ ብቅ ይል ጀመር፡፡ ከአንድነት ግንባር ውስጥ በቀይ ባሕር ተወላጆችና በማሪያ ልጆች (የዑብል አባሎች) መካከል ቅራኔ ስለተፈጠረ በ1966 “ዑበል” ከሻዕቢያ ተገንጥሎ ወደ ባርካ ሲጓዝ በጀብሃ ተደመሰሰ፡፡ በዚህም የዑበል የእንቅስቃሴ ታሪክ አከተመ፡፡ የተቀሩት የአንድነት ግንባር አባሎች ማለትም ሕዝባዊ ኃይልና “ሰልፊ ነጻነት” በስምምነት ሂደት ላይ እንዳሉ በ1966 ዓ.ም. የ“መንካዕ” እንቅስቃሴ ተነሣ፡፡ ይህ የ“መንካዕ” እንቅስቃሴ የአንድነትን ሂደት በማሰናከል በኢሳያስ ቡድን ውስጥ አስጊ ሆኔታን ፈጠረ፡፡ 6- “የመንካዕ” እንቅስቃሴ አሥራ አንድ የሚሆኑ ዲሞክራሲ አዘል ጥያቄዎችን የአንድነቱ ግንባር መሪዎች ለነበሩት ለእነ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ሰለሞን ወ/ማርያም፣ አሥመሮም እንዳ/ጊዮርጊስ፣ መስፍን ሐጎስና ተወልደ ኢዮብ አቀረበ፡፡ ከጥያቄዎቹም መካከል፤ 1- ሰፊው ሕዝብ በመሪዎቹ እንዳይገፋ 2- የብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፕሮግራም አዋጅ እንዲታወጅ 3- የድርጅቱ ጉባኤ ተደርጎ መሪዎቹ በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲመረጡ 4- በድርጅቱ የሰፈነው ወታደራዊ አምባገነንነት እንዲጠፋ 5- ኢሳያስ አፈወርቂ በሞኖፖል የያዛቸውን ኃላፊነቶች እንዲያከፋፍል 6- የፀጥታው ክፍል “በእሥረኞች” ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች የሚፈጽም ስለሆነ፣ ርህራሄ የሰፈነበት ፍርድ እንዲሰጥ የሚሉ ይገኙበታል፡፡ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ አባሎች በሙሉ እንቅስቃሴውን ሲደግፉ ኢሳያስ ግን ባህርዩና ዓላማው ስለማይፈቅድለት እንቅስቃሴውን ለብቻው ተቃወመው፡፡ የመንካዕ እንቅስቃሴ መሪዎችም፣ የድርጅቱን ሥልጣን ለአሥር ቀናት ያህል ይዘው ኃይላቸውን ማጠናከር ጀመሩ፡፡ ኢሳያስና ጓደኞቹ መንካዕን ፊት ለፊት በፖለቲካ መመከት ስላልቻሉ አድኃሪ በሆነው የከፋፍለህ ግዛ ስልት ተጠቅመው ሐማሴን፣ አካለጉዛይ፣ ሠራየ በማለት እርስ በርስ ካነካከሱ በኋላ የተጀመረውን ንቅናቄ ሊያፍረከርኩት በቁ፡፡ የመንካዕን እንቅስቃሴ በጉልህ ሲመሩ ይታዩ የነበሩት አብዛኞቹ የአካለጉዛይ ልጆች በመሆናቸው የመንካዕ እንቅስቃሴ በሐማሴንና በአካለጉዛይ ተወላጆች መካከል እንደተነሳ ቅራኔ ሆኖ ተገመተ፡፡ ሆኖም ያልነቃ ሠራዊት የአድኃሪያን መሣሪያ ከመሆን ስለማያልፍ፣ ብዙዎቹም የሐማሴን ልጆች ስለነበሩ፣ የኃይል ሚዛን ወደ ኢሳያስና ሰለሞን ወ/ማርያም አዘነበለ፡፡ ከኃላፊነት ወርዶና ተባሮ በየጥላ ሥር ይውል የነበረው ኢሳያስ አፈወርቂም በሥልጣን ወንበሩ ላይ ተመልሶ ተቀመጠ፡፡ ወዲያውኑ የመንካዕ እንቅስቃሴ መሪዎች በሙሉ ከታሰሩ በኋላ እንቅስቃሴው የአካለጉዛይ ተወላጆች ብቻ ነው ተብሎ እንዲወራ ተደረገ፡፡ ከመንካዕ እንቅስቃሴ መሪዎች መካከል ታስረው የነበሩ የሐማሴን ተወላጆች የሆኑት ጴጥሮስ ሰለሞንና ስብሃት ኤፍሬምም (አሁን የሻዕቢያ የፖሊት ቢሮ አባሎች) ከእስር ቤት ወጥተው ከሠራዊቱ ፊት ቀርበው እንቅስቃሴው የአካለጉዛይ ልጆች እንቅስቃሴ መሆኑን ከዋናዎቹ የመንካዕ መሪዎች እንደተገለጸላቸው በማስመሰል እንዲገልጹ አደረጓቸው፡፡ የተቀሩት የመንካዕ መሪዎች እንደታሰሩ ቀሩ፤ ብዙዎችም ለምሳሌ እንደ ተወልደ፣ ኢዮብ፣ ሙሴ ተስፋሚካኤል፣ ብጻይ ጎይትኦም፣ ዮሐንስ ስብሃቱና ሌሎችም መሪዎችና ካድሬዎች እንዲገደሉ ተደረገ፡፡ እነ ኢሳያስ አፈወርቂ ከጥላቻቸው ብዛት የተነሳ ከመንካዕ ቡድን አባሎች የሰበሰብዋቸው ተራማጅ መጽሐፍት፣ በተለይ ጎይትኦም በትግርኛ ተርጉሟቸው የነበሩትን ጽሑፎች፣ ሁሉ አንድም ሳያሰቀሩ አቃጠልዋቸው፡፡ ከዚያ በኋላ በድርጅቱ ውስጥ ፍጹም የሆነ ወታደራዊ አምባገነንነት በመስፈኑ ማንም ተራ አባል ባለበት ቡድን መንቀሳቀስ፣ መጻፍ፣ ወይም ኃለፊዎችን ማረም የማይችልበት ወጥመድ ውስጥ ገባ፡፡ ማንኛውም የዚህ ቡድን አመራር ተቃዋሚ በእስር ቤት እንዲማቅቅና በሞት እንዲቀጣ ማድረግ ጀመረ፡፡ “መንካዕ፣ የኢትዮጵያ ሰላይ፣ የሲ.አይ.ኤ. ሰላይ ነው” በሚል ሰበብ ብዙ ዲሞክራቲክ ኤለመንቶችና ምሁራን ያለፍትሕ ተገደሉ፡፡ ምንም ዓይነት ተቃውሞ ማቅረብ አስፈሪ በመሆኑ በድርጅቱ ውስጥ መጠራጠርና ፍርሃት ገነነ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በተራ ወሬና በአሉባልታ አማካይነት የኢሳያስ “ጀግንነት” ይነዛ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ደግሞ ተቃውሞ ሊያቀርብ የሚችለውን ምሁር ከተቀሩት የገበሬና የሠራተኛው ክፍል ጋር በማጣላት ሠራዊቱ ተከፋፍሎና እርስ በርስ ተፈራርቶ እንዲኖር ስለተደረገ የኢሳያስ ገናናነት ብቅ ይል ጀመር፡፡ በሥልጣን ሊወዳደረው የሚችል በብዙ መንገድ ስለጠፋ በርሱና በተከታዮቹ ማለትም በሌሎች መሪዎች መካከል ያለው የሥልጣን ልዩነት ሰማይና መሬት ሆነ፡፡ እስከ 1969 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ የቀድሞዎቹ መሪዎች በሙሉ የእርስ በርስ ድክመታቸውን ስለሚተዋወቁ ለኢሳያስ የሚታዘዙ አልነበሩም፡፡ እነዚህን ሁሉ አስወግዶ ብዙ ደካማ ጎን ያላቸውን መሪዎች ሥልጣን ማስጨበጡ ኢሳያስ ላለው አምባገነናዊ አመራር አመቺ ሆኔታን ለመፍጠርና ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የመጀመሪያ ጉባኤ በ1970 ዓ.ም. እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡ በ1970 ዓ.ም. የድርጅቱ የመጀመሪያ ጉባኤ ተደረገ፡፡ ጉባኤው ያለምንም ተቃውሞ እንዲከናወን ስለተፈለገ ተቃውሞ ሊኖር እንደማይችል ተደርጎ ተዘጋጀ፡፡ ጉባኤው እና ድርጅቱም ኢሳያስ በፈለገው ዓይነት ተዋቀረ፡፡ በዚሁ መሠረት የድርጅቱ ሥልጣን በሙሉ ምክትል ዋና ፀሐፊ ሆኖ ለተመረጠው ለኢሳያስ እንዲሰጠው ተደረገ፡፡ በዚሁ ጉባኤ ላይ የተቋቋመው ማዕከላዊ ኮሚቴ 37 አባሎችን ይይዛል፡፡ ኢሳያስ ተንኮሉን አይተውምና ለራሱ ዓላማ እንዲያመቸው ከ37ቱ አባሎች መሐል አስራ ዘጠኙ ደገኞች ሲሆኑ፤ አስራ ስምንቱ ደግሞ የቀይ ባሕር ተወላጆች እንዲሆኑ አደረገ፡፡ በመሆኑም ኢሳያስ በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ከፍተኛ ድምጽ አለው ማለት ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሌለበት ጊዜ ሥራውን የሚያካሄዱ 13 አባሎች ያሉት ፖሊት ቢሮ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎች መሐል ተመርጠው ተቋቁሟል፡፡ ከነዚህም ሰባቱ ደገኞች ሲሆኑ፣ ስድስቱ ደግሞ የቀይ ባሕር ተወላጆች ናቸው፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎች የተመረጡት ችሎታ ኖሯቸው ሳይሆን፣ ከዚህ ቀደም ደካማ ጎን ስላላቸው ታዛዥ ሆነው እንዲያገለግሉ ሆን ተብሎ በኢሳያስ የተመረጡ ቡችሎቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፤ 1. ተክለ ዓንዶም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የብርጌድ 76 የፖለቲካ ኮሚሳር በ1962 ዓ.ም. ከጀብሃ በማምለጥ ለኢትዮጵያ መንግሥት እጁን ሰጠ፡፡ በ1964 ዓ.ም. ደግሞ የኢሳያስ ቡድን ከተቀላቀለ በኋላ ተመልሶ ለመንግሥት እጁን ሰጠ፡፡ እንደገናም በ1966 ዓ.ም. ወደ ሻዕቢያ ተመልሶ በመግባት የመገንጠል እንቅስቃሴውን እስከአሁን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ሰው ይህንን የመሰለ ድርጊት ፈጽሞ ኢሳያስን መቃወም አይችልም፡፡ 2. እስጢፋኖስ ሥዩምና፣ ዓንደጊዮርጊስ የኢኮኖሚና የሬድዮ ክፍል ኃላፊዎች ናቸው፡፡ ሁለቱም በ1969 ዓ.ም. ሻዕቢያን የተቀላቀሉ እና ለጉባኤው አዲስ በመሆናቸው ማን ምን እንደሆነ ለመናገር የማይችሉ ዱዳዎች ናቸው፡፡ 3.