ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)
СтатистикаMIIDIYAA TUNBII እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ የኢትዮ ቱንቢ ሚድያ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። የቱንቢ ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የሁላችንም ሀገር፣ ባለ ብዙ ፈተና እና ባለ ብዙ ተስፋ ስለ ሆነችው የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው። የመረጃ፣ ማስረጃ፣ የቀጥተኛ ምልከታና መፍትሔ ተኮር ጋዜጠኝነት ቤት።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 13
- Всего постов
- 48
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 282
- 1/48двое суток
- 323
- 1/72трое суток
- 348
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
☝️የሞትከው አንድን ታናሽ ብላቴና ለ መ ግ ደ ል ይህን ያህል ስትደክም ነው! በጥፊ ብቻ የሚሞት ህፃንን እጆቹን የፊጥኝ አስረህ፥ ግንባሩ ላይ አፈ ሙዝ ደቅነህ ፎቶ ስትነሳ በእውነትም ከሰውነት ወጥተህ አረመኔ ጭ ራቅ መሆንህን በግልጽ ታስረዳለህ። ይሄ የሚሆነው በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳውያን ቄራ በሆነችው 'አርሲ' በተባለች ቦታ ነው!!! እንግዲህ እንዲህ ያለውን ጭካኔ ከየት እንደተማራችሁት እናንተው ንገሩን።👇 Megbaru Asmare
ለምን ይዋሻል ..? ❗"ከማንኛውም የግል ጉዳይ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ይገባል " ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ©EOTC TV 👉ዛሬ ይህንን የድምፅ መልእክት ሰማን ፣ ይህ ከእውነት የራቀ የቃላት ዲስኩር ፣ ቃሉ እና ተግባሩ ያልተዛመደ "ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ የሚስብል "፣ ያውም በተወዳጁ ጾመ ፍልሰታ እንዲህ ብሎ መናገሩ እየሰራን ያለነው ፣ ወይም እፈጸምን ያለነው ምዝበራ ማንም አልደረሰበትም ነውን ? ዘይገርም እኮ ነው ? 👉 የቅርብ ቀን ትዝታ ነው እኮ ፣ በቤተክርስቲያን ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያፍለፈው እኩይ ተግባራቸው ፣ የግል ፍላጎታቸውን አስቀድመው ለምን ሥራ አስኪያጅ አልተመረጥኩም በሚል ከሃያ በላይ በጫካ ሄደው የጨረቃ ጳጳስ ሾመው ሲያበቁ ፣ ይህንን ህገወጥ ድርጊት በዋና አስተባባሪነት እና ፊት መሪ በመሆን ሲያከናውኑ ፣ 👉ለቤተክርስቲያን መደፈር ፣ ለብዙዎች ሕልፈተ ሕይወት ፣ ለብዙዎች የእምነቱ ተከታይ አካለ ስንኩል መሆን ፣ ብዙዎች ሀብት ንብረታቸው እንዲዘረፍ ፣ ህፃናት ወላጅ አልባ ሆነው እንዲቀሩ ምክንያት የሆኑ ፣ በዚህ እኩይ ተግባራቸው በወቅቱ ሲኖዶሱ አውግዞ የለያቸው ፣ ከጳጳስ አቶ የተባሉ ፣ ያላንዳች ይቅርታ በመንግሥት ድጋፍ ዘው ብለው ገብተው የተመኙትን ሥልጣ ይዛው ፣ በካድሬ እየተመሩ ዛሬ ቤተክህነቱን እያመሱ እና እየመዘበሩ የሚገኙ አባት ዛሬ ቤተክርስቲያን ናት የጠራችን ፣ የሰበሰበችን ፣ እሷን ልናስቀድም ይገባል ፣ ይህ የዘመናችን ትልቁ ቀልድ ብለን እንለፈው ወይስ እሳቸውም እንደ ብልጽግናው ካድሬ ዲስኩር ሊያሞኙን ነው ። 👉በዚህ ዘመነ መንግስት በርካታ የግፍ እና የጭካኔ ተግባሮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን እንዲሁም ቤተክርስቲያን ላይ ተከናውነዋል ባሳለፍነው ወር ፣የበቁ መናንያን ፣ በጸሎት የሚተጉ አበው ወእማት ፣ ምስባከ ቅዱሳን የሆነ ለዐይን የሚማርክ ፣ ለሕሊና ረፍትን በሚሰጥ ቅዱስ ቦታ ራሳቸውን በገዳም ሰውረው በምናኔ ሕይወት ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳት ብገዳም ውስጥ በግፍ ሲገደሉ ፣ ቤተክርስቲያንን ያስቀደመ ምን ይል ነበር ? እናንተ ግን ሕንፃ ምረቃ ላይ ነበራችሁ ፣ የግል ስሜታችሁን እየፈጸማችሁ ነበር ፣ ከገዳዮች በላይ ሞታችንን እንኳን በተቋም ደረጃ ለመዘገብ በራችሁን የዘጋችሁ ፣ ዛሬ ቤተክርስቲያንን ማስቀደም አለብን ? ለምን ይዋሻል ? 👉 በቅርቡ የሐረር ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪን ፣ ሕንፃው ታድሶ ተመረቀ በታባለበት ማግስት መስተንግዶ አትችልም ብሎ ከቦታው ማንሳት ፣ የግልን ፍላጎት ወይስ ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ነው ፦ 👉በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተሰጡ የግንባታ ፕሮጀክቶች ያለ ሕጋዊ ጨረታ ፣ የነበረውን የቴክኒክ ኮሚቴ አፍርሶ ፣ በባለሞያ የተጠናውን ጥናት ወደ ጎን በመተው በከፍተኛ ቢሊዮን እና ሚሊዮን ለሕንፃ ተቋራጭ ሰጥቶ ፣ በድምሩ ወደ 10 ቢሊዮን ብር የወጣበት የሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር ነው ወይ እየተካሄደ ያለው ? ይህስ የገንዘብ ምዝበራ የግል ስሜትን ያስጠበቀ ወይስ የቤተክርስቲያንን ያስቀደመ ? ለምን ይዋሻል ? 👉 አንድ ተቋራጭ የተሰጠውን የሕንፃ ግንባታ በገባው ውል መሰረት ሳይፈጽም እና ሰርቶ ሳያስረክብ የቢሊዮን ፕሮጀክት አዲስ በድጋሚ እንዲሰጠው መደረጉ የግል ፍላጎትን መፈጸም ወይስ ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ? ለምን ይዋሻል ፣ ይህ አሁን በጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ የሥልጣን ዘመን አልተፈጸመም የሚል በመረጃ ይሞግት ? 👉 በከፍተኛ ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎ ለፊኒሽንግ ሥራ ለሕንፃ ተቋራጭ ተስጥቶ ሥራው ተሰርቶ በደንብ ሳያልቅ ፣ ለታይታ ተመረቀ ተባለ እንጂ ፊኒሽንጉ ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅ በጥድፊያ ለሚዲያ ፍጆታ ተመረቀ ተባለ፣ በተመለመሉ በልቶ አዳሪ ካድሬዎች ፣ ብዙ ተባለ ዛሬ ሕንፃው እንደ ሀውልት ቆሞል ፣ ይህስ ቤተክርስትያንን ያስቀደመ ተግባር ? ለምን ይዋሻል 👉 በአጠቃላይ የእናንተ ቲፎዞ እና ደጋፊ የሆኑ እንዲሁም በብዕር ስም የፌስቡክ አምባሳደር የሆኑ ፣ በጠቅላይ ቤተክህነትም ይሁን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና በሸገር ሀገረ ስብከት አንድ ግለሰብ ሁለት ሦስት ሥራ ተመድበው ከፍተኛ ገንዘብ ሲያካብቱ ፣ ሌላው ሞያው ያልታየለት ፣ ዕድሜ ዘመኑን በቤተክርስቲያን የተማረ አንድ ሥራ አጥቶ ደጅ ጠኚ ፣ አልያም በአዲስ አበባ የአንድ ባለጠጋ ቤት የጥበቃ ሠራተኛ የሆኑ ቤት ይቁጠራቸው ፣ ይህስ የግል ስሜትን ያስጠበቀ ወይስ ቤተክርስቲያንን ያስቀደመ ? ለምን ይዋሻል ? 📌ይቀጥላል ...... ለምን ይዋሻል ? 📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ
ሦስት የሥጋ ቤተሰብ የሆኑ ደቡብ ኮሪያውያን ተጠምቀው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት አገኙ! በሩቅ ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ሥር ባሉ ሁለት ሀገራት አራት ነፍሳት ተጠምቀው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል። በጃፓን የቶኪዮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እና በደቡብ ኮሪያ የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩት አራት ሰዎች ማለትም... አንድ ወጣት ኤርትራዊ ወንድም እና የሥጋ ቤተሰብ የሆኑሦስት የደቡብ ኮሪያ ዜጎች መጠመቃቸውን የሩቅ ምሥራቅ ሀገረ ስብከት አስታውቋል። ሀገረ ስብከቱ ነፍሳትን ወደ እውነተኛው መንጋ ለመቀላቀል በየሀገራቱ ቋንቋዎች የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እና በአገልግሎት ያለመታከት እየሠሩ ያሉትን ካህናትን (ቄሶችን እና ዲያቆናትን)፣ ወንድሞችንና እህቶችን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮችን አመስግኗል። ይህ አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ መቅረቡም ተገልጿል። ግዮን ማለዳ
በአርሲ ተባብሶ የቀጠለው ጅምላ ፍጅት ፩ ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ 02/12/2018 ዓ.ም ለ 03/12/2018ዓ.ም አዳር የ70ዓመት አዛውንት አቶ ጌታቸው ቶሎበል ከእነ ባለቤታቸው ለቀብር በማይመች ሁኔታ ገድለው ጥለው የሄዱ ሲሆን 17ከብቶቻቸውንም ዘርፈው ወስደዋል በዚህ ወረዳ ያለው ኦርቶዶክሳዊ አብዛኛው በአክራሪዎቹ ከበባ ውስጥ ነው ያለው። ራሳቸውንም እንዳይከላከሉ የወረዳው ባለሥልጣናት ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። ይኽ ብቻ አይደለም በጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን ስልታዊ በሆነ መንገድ እያስመቷቸው ነው።ሰሞኑን በ አለንዴ ባዱ ቀበሌ አራት ኦርቶዶክሳውያን ሚሊሾች ተመርጠው ከአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ጋር እንዲዋጉ ተልከው ወዲያውኑ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው የታገቱ ሲሆን ሦስቱ ይኑሩ ይሙት አይታወቅም አንደኛውን ደግሞ እያሰቃዩት ነው።እንዲህ ዓይነት ሴራ መከላከያ ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ጭምር በተደጋጋሚ ሲሠራ ቆይቷል። ፪ በአሰኮ ወረዳ ካራ አሊባር ቀበሌ ከሳምንት በፊት ማለትም ሐምሌ 25/2018ዓ.ም እድሜው የ37 ዓመት የሆነው ጠግዬ ቃልዬ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ በ20 ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።ከወረዳው አመራር ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ አብይ አሕመድ አሊ ድረስ ያሉት " ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ተሰደው የነበሩት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል"የሚል በሐሰት መረጃ ቢያሠራጩም አንድም ወደ ቤቱ የተመለሰ ኦርቶዶክስ የለም። ሕዝባችን የሰቆቃ ኑሮ እየገፋ ነው በ ቤተ መንግሥቱምበ ቤተ ክህነቱም ክህደት ተፈጽሞበታል። ፫ በሔበን አርሲ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል። ሰሞኑን ዘር እየዘሩ ባሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በተከፈተ ጥቃት አንድ ሰው እዚያው ማሳ ላይ እያለ በአቃቂ ሁኔታ ተገድሏል አንደኛው ደግሞ ከእነ በሮቹ ታግቶ የተወሰደ ሲሆን በማግስቱም አምስት ኦርቶዶክሳውያን እገታ ተፈጽሞባቸዋል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ወር ጎልጆታ በተባለ ቦታ ላይ አንድ የ19 ዓመት ዲያቆንና 7 ኦርቶዶክሳውያን ገበሬዎች ተገድለዋል።ታግተው ደብዛቸው የጠፋ ይኑሩ ይሙቱ የማይታወቁ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን አሉ።ብዙ የወረዳው ቀበሌዎች ከኦርቶዶክሳውያን እየጸዱ ነው አሁንም ርስት ጉልታቸውን እየለቀቁ የሚሸሸ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው ይኽ ሁሉ የግፍ ግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ሲፈጸም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ኤልሳዕ በከተማና አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው አከባቢዎች ላይ እየተመላለሱ ዜና እያሠሩ ግጽታቸውን ከማስገምባት ውጭ ፍጅቱን ለማስቆም አንዳች ያደረጉት እንቅስቃሴ የለም።
በአሰቦት ገዳም አንድ መነኮስ ጉዳት ደረሰባቸው ተደጋጋሚ ጥቃት በሚያጋጥመው በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አንድ መነኮስ አባት ባልታወቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ። የገዳሙ አገልጋይ የሆኑት አባ ተክለ ዮሐንስ ደረሰ በእንጨት ለቀማ ላይ እያሉ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 አካባቢ አደጋው እንደደረሰ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት ጽ/ቤት ገልጿል። ታጣቂዎቹ አባ ተክለ ዮሐንስን በአሰቃቂ ሁኔታ ጉሮሯቸውን ወግተው ለመግደል ሲሞክሩ ለማምለጥ የቻሉ ሲሆን ገዳሙም በሕይወትና በሞት መካከል ያሉትን አባት ወደ ህክምና የወሰዱ መሆናቸውን ገልጸው እየደረሰባቸው ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለመከላከል ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን አድርሱልን በማለት ጥሪ አቅርበዋል። የሀገረ ስብከቱም ጽ/ቤት በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ችግር እንዲቀረፍና ገዳማውያኑም በተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖሩና ለሀገር እንዲፀልዩ የመንግስት የፀጥታ አካላት መፍትሄ እንዲሰጥና ክትትል እንዲያደርግ ለሚመለከተው የዞኑ የፀጥታ አካላት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ሪፖርት በማድረግ ክትትል እያደረጉ መሆኑን ገልጿል። ዘገባው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው። #አሰቦትደብረወገግ #ቤተክርስቲያን #ዜና
ጽምዶ እና አዲሱ ነባር ጦርነት #ምክክሩና_ብልጽግና #ጋዜጠኛ_ብሩክ_ይባስ #ዶክተር_ተፈሪ_ኃይለሚካኤል #ዮሴፍ_ከተማ https://www.youtube.com/live/uNLdNdCfN78?si=_oVsVTdAANonALtm
በአርሲ ተባብሶ የቀጠለው ጅምላ ፍጅት ፩ ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ 02/12/2018 ዓ.ም ለ 03/12/2018ዓ.ም አዳር የ70ዓመት አዛውንት አቶ ጌታቸው ቶሎበል ከእነ ባለቤታቸው ለቀብር በማይመች ሁኔታ ገድለው ጥለው የሄዱ ሲሆን 17ከብቶቻቸውንም ዘርፈው ወስደዋል በዚህ ወረዳ ያለው ኦርቶዶክሳዊ አብዛኛው በአክራሪዎቹ ከበባ ውስጥ ነው ያለው። ራሳቸውንም እንዳይከላከሉ የወረዳው ባለሥልጣናት ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። ይኽ ብቻ አይደለም በጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን ስልታዊ በሆነ መንገድ እያስመቷቸው ነው።ሰሞኑን በ አለንዴ ባዱ ቀበሌ አራት ኦርቶዶክሳውያን ሚሊሾች ተመርጠው ከአክራሪ የእስልምና ታጣቂዎች ጋር እንዲዋጉ ተልከው ወዲያውኑ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው የታገቱ ሲሆን ሦስቱ ይኑሩ ይሙት አይታወቅም አንደኛውን ደግሞ እያሰቃዩት ነው።እንዲህ ዓይነት ሴራ መከላከያ ውስጥ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ጭምር በተደጋጋሚ ሲሠራ ቆይቷል። ፪ በአሰኮ ወረዳ ካራ አሊባር ቀበሌ ከሳምንት በፊት ማለትም ሐምሌ 25/2018ዓ.ም እድሜው የ37 ዓመት የሆነው ጠግዬ ቃልዬ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ በ20 ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።ከወረዳው አመራር ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ አብይ አሕመድ አሊ ድረስ ያሉት " ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ተሰደው የነበሩት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል"የሚል በሐሰት መረጃ ቢያሠራጩም አንድም ወደ ቤቱ የተመለሰ ኦርቶዶክስ የለም። ሕዝባችን የሰቆቃ ኑሮ እየገፋ ነው በ ቤተ መንግሥቱምበ ቤተ ክህነቱም ክህደት ተፈጽሞበታል። ፫ በሔበን አርሲ ወረዳ ኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል። ሰሞኑን ዘር እየዘሩ ባሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በተከፈተ ጥቃት አንድ ሰው እዚያው ማሳ ላይ እያለ በአቃቂ ሁኔታ ተገድሏል አንደኛው ደግሞ ከእነ በሮቹ ታግቶ የተወሰደ ሲሆን በማግስቱም አምስት ኦርቶዶክሳውያን እገታ ተፈጽሞባቸዋል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ወር ጎልጆታ በተባለ ቦታ ላይ አንድ የ19 ዓመት ዲያቆንና 7 ኦርቶዶክሳውያን ገበሬዎች ተገድለዋል።ታግተው ደብዛቸው የጠፋ ይኑሩ ይሙቱ የማይታወቁ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን አሉ።ብዙ የወረዳው ቀበሌዎች ከኦርቶዶክሳውያን እየጸዱ ነው አሁንም ርስት ጉልታቸውን እየለቀቁ የሚሸሸ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው ይኽ ሁሉ የግፍ ግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ሲፈጸም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ኤልሳዕ በከተማና አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው አከባቢዎች ላይ እየተመላለሱ ዜና እያሠሩ ግጽታቸውን ከማስገምባት ውጭ ፍጅቱን ለማስቆም አንዳች ያደረጉት እንቅስቃሴ የለም።
ተባብሶ የቀጠለው የኦርቶዶክሳውያን ፍጅት በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ ሬኤ አምባ ቀበሌ ልዩ ስሙ መልከምያ መንደር ትናንት 02/12/2018 ዓ.ም ለ 03/12/2018ዓ.ም አዳር የ70ዓመት አዛውንት አቶ ጌታቸው ቶሎበል ከእነ ባለቤታቸው ለቀብር በማይመች ሁኔታ ገድለው ጥለው የሄዱ ሲሆን 17ከብቶቻቸውንም ዘርፈው ወስደዋል
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ይኽ ሁሉ የግፍ ሲፈጸም ዝም ብላችሁ ያያችሁ የሃይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች በምድርም ሆነ በሰማይ ከፍርድ እንደማታመልጡ እንድታውቁ።
ፎቷቸውን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት፣ ህይወታቸው ገና ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ወጣቶች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። መሀል ላይ ያለው ወጣት ድንጋጤው ይጋባል፣ ሰው ባላጠፋው ጥፋት ሲከሰስ የሚሰማው ስሜት። ሁሉም 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ተረሸኑ፣ አስከሬናቸው እንኳን እንዳይነሳ ለቀናት ተከለከለ። ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው፣ ግዛው ግርማዬ! ነፍስ ይማር! https://www.meseretmedia.org/p/346
የሠላማዊ ትግል በሮችን በሙሉ ዘግቶ የጦርነት በሮች እንዲከፈቱ ሳይታክት የሚሠራ አለ ወይ? በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ ከሰሞኑ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለው የሚያምኑ ሦስት ፖለቲከኞችን ማለትም አቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስኃቅ ወልዳይ እና ጠበቃ አበራ ንጉሥ ለእሥር መዳረግ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የሚያመጣውን አሉታዊ ጫና በማሰብ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል። ትብብራችንም ድርጊቱ እጅግ አስደንጋጭ ክስተት ኾኖ አግኝቶታል። አኹን ከነችግሩ ሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 ን.አ 2 ላይ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው። ይኽ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ያካትታል” ይላል። ከዚኽ ሕገ መንግሥታዊ ቅኝት ባፈነገጠና በሀገራችን ከውዳሴ በስተቀር ምንም የተቃውሞና ትችት ድምጾች እንዳይሰሙ ምክንያት እየፈጠሩ ማሳደድ ባልተጻፈ ሕግና እንደመርኅ ተይዟል ወይ? እንድንል አድርጎናል፤ ሰላማዊ ትግል ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ሌሎች አማራጮች እንዲናኙ የሚሠራ ግራ ኃይል ተፈጥሯል ወይ? ብሎ የሚያስጠረጥርም ሆኖ አግኝተነዋል። ስለኾነም መንግሥት በሩቅና በጠባብ ቀዳዳ ጭልጭል የምትለዋን የፖለቲካ ምኅዳር ብርሃን ከነጭራሹ እንዳጠፋ ክፉኛ መጠንቀቅ አለበት። ያሠራቸውንም የሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮች ያለቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ፣ የዋስትና መብታቸውንም እንዲያከብር እናሳስባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ጾመ_ፍልሰታ_ለማርያም! #እንኳን_አደረሳችሁ!
видео или голосовое, без подписи
በአገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የመንግሥት ባለስልጣናት ያልተገባ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑ ተነገረ‼️ "የዘመሙ አካሄዶች ሲታዩ በጊዜውና በወቅቱ ዕርምት ይደረግባቸዋል" የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን - 250ው ስልታዊ ቡድን አዲስ አበባና ድሬዳዋ የፌዴራል አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል የአገራዊ የምክክር ጉባዔ በአጀንዳ ጭብጦች ላይ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ የተመደቡ አመካካሪዎች፣ምሁራንና ቃለ ጉባዔ ያዦች፣ ተመካካሪዎች የሚያነሱትን ሃሳብ ባለመቀበልና በተለይ የመጡበትን ተቋም መሠረት ያደረገ አቋም በመያዝ፣ ተመካካሪዎች ሐሳብ እንዲቀይሩና የምክክር ሒደቱ እንዲዘገይ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተመካካሪዎች ገለጹ በተለይ መንግሥትን ወክለው የመጡ አመካካሪዎች እንደ የመንግሥት አደረጃጀትና አገር ግንባታ ያሉ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከምክክሩ ሒደት ባፈነገጠ መልኩ የራሳቸውን ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ምንጮች ተናግረዋል። የመንግሥት አደረጃደት አጀንዳን በተመለከተ እንዲያወያዩ በኮሚሽኑ የተመደቡ አመካካሪዎች በዚህ የተነሳ ለቀናቶች ውይይት እንዳይመሩና ማይክ ብቻ እንዲያቀብሉ በማድረግ፣ በእነርሱ ምትክ ደግሞ ከቡድን መሪዎች ተመርጠው ውይይት እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል። ከዚህ አልፎ የኮሚሽኑ አመካካሪዎች ውይይት እንዲመሩ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩን ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ የአጀንዳ ሐሳብ በተለይ የተለያዩ የፓርቲዎችን ወክለው የተገኙ ተመካካሪዎች የአመካካሪዎች አካሄድ በተመለከተ ቅሬታ አቅርበው ሁኔታው ከላይ በተገለጸው መንገድ እንዲመራ መደረጉን ተመካካሪዎቹ ተናግረዋል። በተለይ የተቋማት ግንባታን በተመለከተ፣ “ስለ ተቋም ግንባታ ለእኛ አትነግሩንም፣ የተቋም ግንባታ ምን መሆን እንዳለበት እናውቃለን፣ ተቋሙን የምንመራው እኛ ነን፣ ሪፎርም አድርገናል” ተቋማትን ወክለው የተገኙ ተመካካሪዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት ተቆጥተው ውይይት ጥለው የወጡ ተመካካሪዎች እንደነበሩም አክለዋል። አመካካሪዎች በሙስናና መልካም አስተዳደር አጀንዳ ሥር፣ ንዑስ አጀንዳ በሆነው የሙስና ጉዳዮች፣ በአንዳንድ ቡድኖች ከስምምነት እንዳይደረስና ለውይይት በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል። በዚህ ምክንያት ሐሳብ ተንዛዝቶ ከመግባባት ለመድረስ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29 ቀን ድረስ ውይይት እንዲቀጥል ማስገደዱን አስረድተዋል። የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማን በተመለከተ የፅንሰ ሐሳብ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ በኮሚሽኑ የተመደቡ ምሁራን (Panel of Experts)፣ በተለይ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል አካል ትሁን በሚለው የአጀንዳ ሐሳብ ፅንፍ በያዘ ሁኔታ መከራከራቸውን ጨምረው ገልጸዋል። ሆኖም ይህን አካሄድ የተከተሉ ምሁራን ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ይቅርታ መጠየቀታቸውን ተመካካሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል። በቃለ ጉባዔ ያዥነት የተመደቡ አንዳንድ ባለሙያዎችም የቀረቡ ሐሳቦችን በሙሉ ያለማጠናከርና በፈለጉት መንገድ ብቻ የመሰነድ ችግር እንደተስተዋለባቸው ተናግረዋል። እነዚህ ቃለ ጉባዔ ያዦች የአንዱን ሐሳብ ይዘው የሌላውን የመተው አካሄድ መከተላቸው ተነግሯል። በመሆኑም እንዲህ ያሉ ድርጊቶች አስፈላጊ እንዳልሆኑ፣ የምክክሩም ዓላማ ይህ እንዳልሆነ የገለጹት የመረጃ ምንጮቹ አሁን ያሉ ተቋማት ብቁ፣ ነፃና ገለልተኛ ሆነው የማይሰሩና የሚቀርቡ ጥያቄዎችን የመፍታት ከፍተኛ ችግሮች ስላሉባቸው፣ ውሃው እንዳይደርቅና አሳውም እንዳይሞት መታረምና መስተካከል እንዳለባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል። ኮሚሽኑም እንደዚህ አይነት ጉዳዮችን ጣልቃ ገብቶ በጊዜ እንዲታረሙ ማድረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል። በዚሁ ረገድ የአዲስ አበባ ከተማ የባለቤትነት ጉዳይ ትልቁ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ እንደነበር፣ በዚህም አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት አካልና ዋና መቀመጫ ከተማ እንድትሆን ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል። ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ሌሎች የፌዴራል ከተሞች እንዲኖሩ ሰፊ ምክረሐሳብ መቅረቡን፣ ለዚህም ደቡብ አፍሪካ እንደ ምሳሌ መቅረቧን ተናግረዋል። አዲስ አበባ ከተማ የራሷ የሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የተጠናከረ የፖሊስ ኮሚሽን እንዲኖራትና በከተማዋ ውስጥ የሚሰየሙ የሰፈር ስሞች የአገር አንድነትንና የሁሉንም ማኅበረሰብ ውክልና እንዲኖራቸው ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል፡፡ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ የአዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ ሆኖ እንዲቀጥል ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል። ሆኖም አማርኛ፣ ኦሮሚኛና፣ ትግርኛ፣ አፋርኛና ሶማሊያ የፌዴራል የሥራ ቋንቋዎች ከሆኑ የአዲስ አበባም እንዲሆኑ ሐሳብ መኖሩን ጠቁመዋል። (ሪፖርተር) ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
«ሞዐ ተዋሕዶ» የማነው? ከወቅታዊ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጎልተው ከሚነሱ አጀንዳዎች መካከል አንዱ «ሞዐ ተዋሕዶ» ነው። ስለ ንቅናቄው ግልጽና የጠራ ግንዛቤ ይኖረን ዘንድ በተረዳሁት መጠን የሚከተለውን ምልከታ ማጋራት ወደድሁ። «ሞዐ ተዋሕዶን» በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባቶች ይስተዋላሉ። አንዳንዶች ሆን ብለው በሚመስል ሁኔታ ከዐውዱና ከዓላማው ውጭ የሆነ መረጃ በማሰራጨት፣ ንቅናቄው የፖለቲካ ዓላማ እንዳለው አድርገው በመሳል ብዙዎችን ያሳስታሉ። እንዲያውም «ሞዐ ተዋሕዶ» በአንዳንድ የመንግሥት አካላትም ሆነ በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎች በኩል የሚለጠፍበት አሉታዊ ስም፣ በተግባር ከሚሠራው በጎ ሥራ ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም። ከዚያም አልፎ ስሙን የመምቻ ዱላ በማድረግ፣ ኦርቶዶክሳውያንን ለማሳቀቅ፣ ለማሰር፣ ለማሳደድና ለማጥቃት እንደ ምክንያት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ሆኖም «ሞዐ ተዋሕዶ» ምንም ዓይነት የፖለቲካ ወገንተኝነት የሌለውና ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ሊጋሩት የሚችሉትን ዓላማ ሰንቆ የሚጓዝ ግብረ-ኃይል ነው። ዋና ግቡም ቤተ ክርስቲያንን ከጥቃት፣ ከስደትና ከጥፋት መከላከል ብቻ ነው። አንዳንዶች ሞዐ ተዋሕዶን ከ«ሞአ አንበሳ» ጋር በማመሳሰል ንቅናቄውን ከንጉሣዊ ሥርዓት መመለስ ጋር ለማያያዝ የሚያደርጉት ጥረት ፈጽሞ መሠረት የለውም። የ«ሞዐ ተዋሕዶ» መነሻ ቅዱስ ሲኖዶስ በ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. የምልዓተ ጉባኤው ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ያደረገውን ጥሪ መሠረት ያደረገ ነው። ሲኖዶሱ በምእመናንና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በመመልከት፣ ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በይፋ ተመሠረተ። ሞዐ ተዋሕዶ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚሰነዘሩ መዋቅራዊ፣ አስተዳደራዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጥቃቶችን ለመመከት የሚሠራ የጥብቅና ንቅናቄ (Advocacy Movement) ነው ማለት ይቻላል። ግብረ-ኃይሉ ለዘመናት የነበረውን «የዝምታ ስልት» በመስበር፣ የቤተ ክርስቲያኗን መብትና ድምፅ በግልጽ የሚያሰማበትን ሰላማዊ መንገድ ቀይሷል። ይህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዝምተኛ ተከታይነት ወደ «ንቁ ተሟጋችነት» የተሸጋገሩበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያመላክታል። «ሞዐ ተዋሕዶ» ከምሥረታው ዕለት ጀምሮ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረባቸው ሰባት ዋና ዋና ጥያቄዎችን በማስተጋባት ላይ ይገኛል። እነዚህም በትምህርት፣ በሚዲያና በልማት ስም የሚሰራጩ ጸረ-ኦርቶዶክስ ትረካዎች እንዲቆሙ፣ በመንግሥት መዋቅርና በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸም መዋቅራዊ ማግለል እንዲያበቃ፣ ቤተ ክርስቲያንን በብሔርና በቋንቋ የመከፋፈል ፖለቲካዊ ሴራዎች እንዲገቱ፣ በምእመናን ላይ የሚፈጸሙ አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጥቃቶች እንዲቆሙ፣ በጥፋተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዶ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲሰጥ፣ የተፈናቀሉ ምእመናን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ እንዲሁም «አዲሲቷን ኢትዮጵያ» በመገንባት ሰበብ የሚካሄዱ ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ዘመቻዎች እንዲቆሙና መንግሥት ይፋዊ የይቅርታ መግለጫ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ናቸው። በአጠቃላይ፣ መገንዘብ እንደቻልሁት ሞዐ ተዋሕዶ በየትኛውም ዓይነት የፖለቲካ አሰላለፍ ያልወገነ፣ ዋና ዓላማውና ትኩረቱ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻና ብቻ የሆነ ንቅናቄ ነው። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የታሪክ እውነታ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን ተነጣጥለው ስለማይቆሙ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አወንታዊ አስተዋጽኦ ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም። ሁሉም ኢትዮጵያውያን በፍቅርና በመከባበር የሚኖሩባት፣ ፍትሕ፣ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ሀገር እንድትገነባ እንደቀደምት አያቶቹ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል። እንደ እኔ መረዳት፣ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ-ብዙ ጥቃት ለመከላከል ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበት የትብብር መረብ በመሆኑ «ሞዐ ተዋሕዶ» የማንም ሳይሆን የሁሉም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በህልውና አደጋ ውስጥ የምትገኝ በመሆኗና ይህንን ሰፊና መዋቅራዊ ፈተና ለመመከት ይመጥናል ተብሎ የሚታመን ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ባለመኖሩ፣ እንደ «ሞዐ ተዋሕዶ» ያሉ ንቅናቄዎችን መደገፍ፣ ማበረታትና ማሳደግ ከመላው ኦርቶዶክሳውያን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ዶ/ር)