tgindex
ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ( Ethio Beteseb Media)

ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ( Ethio Beteseb Media)

Статистика

ይህ ቻናል መንፈሳዊ መልክቶች ፣ ማኅበራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ መረጃዎች የሚተላለፉበት ነውና ቤተሰብ ይሁኑ!!

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
12 242
−14 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
4 101
19 постов
Вовлечённость
33,5%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 21
Упоминаний
5
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 870
1/48двое суток
2 143
1/72трое суток
2 311

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.1 666313

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 авг.1 979581

    "የምንመካከረው በብሔራዊ መግባባት አገርን ለማጽናት  እንጂ የቡድን የበላይነትን ለማንበርና ሌላ አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም!" ©እናት ፓርቲ ካወጣው የአቋም መግለጫ የተወሰደ እናት ፓርቲ ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

  • 11 авг.2 23892

    видео или голосовое, без подписи

  • 11 авг.4 4965412

    ለምን ይዋሻል ..? ❗"ከማንኛውም የግል ጉዳይ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ይገባል " ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ©EOTC TV 👉ዛሬ ይህንን የድምፅ መልእክት ሰማን ፣ ይህ ከእውነት የራቀ የቃላት ዲስኩር ፣ ቃሉ እና ተግባሩ ያልተዛመደ "ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ የሚስብል "፣ ያውም በተወዳጁ ጾመ ፍልሰታ እንዲህ ብሎ መናገሩ እየሰራን ያለነው ፣ ወይም እፈጸምን ያለነው ምዝበራ ማንም አልደረሰበትም ነውን ? ዘይገርም እኮ ነው ? 👉 የቅርብ ቀን ትዝታ ነው እኮ ፣ በቤተክርስቲያን ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያፍለፈው እኩይ ተግባራቸው ፣ የግል ፍላጎታቸውን አስቀድመው ለምን ሥራ አስኪያጅ አልተመረጥኩም በሚል ከሃያ በላይ በጫካ ሄደው የጨረቃ ጳጳስ ሾመው ሲያበቁ ፣ ይህንን ህገወጥ ድርጊት በዋና አስተባባሪነት እና ፊት መሪ በመሆን ሲያከናውኑ ፣ 👉ለቤተክርስቲያን መደፈር ፣ ለብዙዎች ሕልፈተ ሕይወት ፣ ለብዙዎች የእምነቱ ተከታይ አካለ ስንኩል መሆን ፣ ብዙዎች ሀብት ንብረታቸው እንዲዘረፍ ፣ ህፃናት ወላጅ አልባ ሆነው እንዲቀሩ ምክንያት የሆኑ ፣ በዚህ እኩይ ተግባራቸው በወቅቱ ሲኖዶሱ አውግዞ የለያቸው ፣ ከጳጳስ አቶ የተባሉ ፣ ያላንዳች ይቅርታ በመንግሥት ድጋፍ ዘው ብለው ገብተው የተመኙትን ሥልጣ ይዛው ፣ በካድሬ እየተመሩ ዛሬ ቤተክህነቱን እያመሱ እና እየመዘበሩ የሚገኙ አባት ዛሬ ቤተክርስቲያን ናት የጠራችን ፣ የሰበሰበችን ፣ እሷን ልናስቀድም ይገባል ፣ ይህ የዘመናችን ትልቁ ቀልድ ብለን እንለፈው ወይስ እሳቸውም እንደ ብልጽግናው ካድሬ ዲስኩር ሊያሞኙን ነው ። 👉በዚህ ዘመነ መንግስት በርካታ የግፍ እና የጭካኔ ተግባሮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን እንዲሁም ቤተክርስቲያን ላይ ተከናውነዋል ባሳለፍነው ወር ፣የበቁ መናንያን ፣ በጸሎት የሚተጉ አበው ወእማት ፣ ምስባከ ቅዱሳን የሆነ ለዐይን የሚማርክ ፣ ለሕሊና ረፍትን በሚሰጥ ቅዱስ ቦታ ራሳቸውን በገዳም ሰውረው በምናኔ ሕይወት ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳት ብገዳም ውስጥ በግፍ ሲገደሉ ፣ ቤተክርስቲያንን ያስቀደመ ምን ይል ነበር ? እናንተ ግን ሕንፃ ምረቃ ላይ ነበራችሁ ፣ የግል ስሜታችሁን እየፈጸማችሁ ነበር ፣ ከገዳዮች በላይ ሞታችንን እንኳን በተቋም ደረጃ ለመዘገብ በራችሁን የዘጋችሁ ፣ ዛሬ ቤተክርስቲያንን ማስቀደም አለብን ? ለምን ይዋሻል ? 👉 በቅርቡ የሐረር ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪን ፣ ሕንፃው ታድሶ ተመረቀ በታባለበት ማግስት መስተንግዶ አትችልም ብሎ ከቦታው ማንሳት ፣ የግልን ፍላጎት ወይስ ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ነው ፦ 👉በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተሰጡ የግንባታ ፕሮጀክቶች ያለ ሕጋዊ ጨረታ ፣ የነበረውን የቴክኒክ ኮሚቴ አፍርሶ ፣ በባለሞያ የተጠናውን ጥናት ወደ ጎን በመተው በከፍተኛ ቢሊዮን እና ሚሊዮን ለሕንፃ ተቋራጭ ሰጥቶ ፣ በድምሩ ወደ 10 ቢሊዮን ብር የወጣበት የሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር ነው ወይ እየተካሄደ ያለው ? ይህስ የገንዘብ ምዝበራ የግል ስሜትን ያስጠበቀ ወይስ የቤተክርስቲያንን ያስቀደመ ? ለምን ይዋሻል ? 👉 አንድ ተቋራጭ የተሰጠውን የሕንፃ ግንባታ በገባው ውል መሰረት ሳይፈጽም እና ሰርቶ ሳያስረክብ የቢሊዮን ፕሮጀክት አዲስ በድጋሚ እንዲሰጠው መደረጉ የግል ፍላጎትን መፈጸም ወይስ ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ? ለምን ይዋሻል ፣ ይህ አሁን በጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ የሥልጣን ዘመን አልተፈጸመም የሚል በመረጃ ይሞግት ? 👉 በከፍተኛ ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎ ለፊኒሽንግ ሥራ ለሕንፃ ተቋራጭ ተስጥቶ ሥራው ተሰርቶ በደንብ ሳያልቅ ፣ ለታይታ ተመረቀ ተባለ እንጂ ፊኒሽንጉ ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅ በጥድፊያ ለሚዲያ ፍጆታ ተመረቀ ተባለ፣ በተመለመሉ በልቶ አዳሪ ካድሬዎች ፣ ብዙ ተባለ ዛሬ ሕንፃው እንደ ሀውልት ቆሞል ፣ ይህስ ቤተክርስትያንን ያስቀደመ ተግባር ? ለምን ይዋሻል 👉 በአጠቃላይ የእናንተ ቲፎዞ እና ደጋፊ የሆኑ እንዲሁም በብዕር ስም የፌስቡክ አምባሳደር የሆኑ ፣ በጠቅላይ ቤተክህነትም ይሁን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና በሸገር ሀገረ ስብከት አንድ ግለሰብ ሁለት ሦስት ሥራ ተመድበው ከፍተኛ ገንዘብ ሲያካብቱ ፣ ሌላው ሞያው ያልታየለት ፣ ዕድሜ ዘመኑን በቤተክርስቲያን የተማረ አንድ ሥራ አጥቶ ደጅ ጠኚ ፣ አልያም በአዲስ አበባ የአንድ ባለጠጋ ቤት የጥበቃ ሠራተኛ የሆኑ ቤት ይቁጠራቸው ፣ ይህስ የግል ስሜትን ያስጠበቀ ወይስ ቤተክርስቲያንን ያስቀደመ ? ለምን ይዋሻል ? 📌ይቀጥላል ...... ለምን ይዋሻል ? 📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

  • 6 авг.4 02010312

    📌ፍልሰታ ጾም ( ሱባኤ) 📝""አቤቱ የሆነብንን አስብ ተመልከት""                 ሰቆቃ ኤር. ፭፥፩ ♣ በሀገራችን ኢትዮጵያ መቼም በማይረሳ የሀዘን ሰቆቃ ፦ ካህናት ሲገደሉ፤ አብያተክርስቲያን ሲቃጠሉ ፤ ወገኔ እየተገደለ ሀብት ንብረቱ ሲዘርፍ አምላክ ሆይ የሆነብንን አስብ በማለት በዚህ ሱባኤ እንዲህ ብለን እንማፀን ኃይላችን እሱ ነውና ፦፦፦፦ ♣"ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ።" (ሰቆቃው ኤርምያስ ፫: ፵፩) እግዚኦ ማሀረነ እንበል ፦፦ ♣" እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይኔ ሳታቋርጥ ዝም ሳትል እንባ ታፈስሳለች።" (ሰቆቃው ኤርምያስ ፫: ፵፱-፶) እንዳለ ነብዩ በእንባ እንማፀን ወደ ጌታ፦፦ ♣" ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?" (ሰቆቃው ኤርምያስ ፭:፳) መከራውን ከእኛ እንዲያርቅ እንለምን ፦፦ ♣" አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።" (መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ፳፡ ፲፪) በማለት ፍርዱን ለፈጣሪ እንስጥ፦፦ ♣" አቤቱ፥ ማረን አንተን ተማምነናል፤ ጠዋት ጠዋት ክንድ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን።" (ትንቢተ ኢሳይያስ ፴፫: ፪) መታመኛችን እሱ ነውና ዘወትር የምህረት ክንዱን እንዲዘረጋልን ማረን እንበል ፦፦ ♣" ማረን አቤቱ ማረን" (መዝሙረ ዳዊት ፼፳፫: ፫) ዛሬ ዐይናችን ያየነውን ፣ ጃሮአችን የሰማውን የመረረ ሀዘንና መከራ ከእኛ እንዲያርቅ በሱባኤው ማረን አቤቱ ማረን እንበል ፤ የሞቱትን ነፍስ ይማር ፤ የተጎዱትን ጨርሶ ምህረቱን ይላክልን ፣ ለሕዝቡ መጽናናትን ያድልልን፤ ቤተክርስቲያችንን ከክፉ ይጠብቀልን ፤ ሀገራችንን ኢትዮጵያንን ሰላም ያድርግልን፤ ለዘመናት ተዋዶና ተከባብሮ የኖረውን ክርስቲያኑና ሙስሊሙን ለመለያየት እሳት የሚያፍሙትን ልቦና ይስጥልን!!!!  ሱባኤውን በሰላም አስጀምሮ እንዲያስጨርሰን የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁን!!!!                 👉የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት እና ረድኤት በሁላችን ይደርብን ፦ መልካም ሱባዔ🙏      📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

  • 30 июл.4 778541

    видео или голосовое, без подписи

  • 29 июл.4 688341

    📝የፍቅር እጃችንን እንዘርጋ — ለታመመችው እህታችን የተስፋ ብርሃን እንሁን 🙏የተከበራችሁ ቤተሰቦች ፣ 👉አንዲት እህታችን በከባድ ሕመም ምክንያት በአልጋ ላይ ያለች እህታችን  ፣ ወንድሟ ጣሰው ትሑት፣ ቅንና ታማኝ አገልጋይ የሆነው ወንድሟ በፍቅር ከጎኗ ቆሞ እያስታመማት ይገኛል። 👉እርሱም በዚህ በDMV አካባቢ በአብያተክርስቲያኑ እየሄደ በቅንነት የሚያገለግል፣ ትጉህ መልካም ወንድም ነው። 👉ዛሬ ግን የእኛን ጸሎት፣ ፍቅርና ድጋፍ ይፈልጋል። በዚህ ከባድ ወቅት የሕክምናና የተያያዙ ወጪዎችን ለማገዝ GoFundMe ተከፍቷል። “ለችግረኛው የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል።” — ምሳሌ 19፥17 👉በገንዘብ መርዳት የምትችሉ በቻላችሁት መጠን እንድትረዱ፣ መርዳት የማትችሉም በጸሎትና ሊንኩን በማጋራት ከጎናቸው እንድትቆሙ በትሕትና እንጠይቃለን። ትንሽ የምንለው ስጦታ ተሰብስቦ ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል። 👉እግዚአብሔር የታመመችውን እህታችንን በምሕረቱ ይጎብኛት፣ ፈውስንም ይስጣት። ወንድሟንና መላውን ቤተሰብ በኃይሉ ያጽናናቸው። የምትረዱትንም ሁሉ መቶ እጥፍ ይክፈላችሁ። ለመርዳት እባክዎ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፦ 🔗 https://gofund.me/5c48bec8e 🙏 እባክዎ ይርዱ፣ ይጸልዩ፣ ለሌሎችም ያጋሩ።

  • 29 июл.4 1995

    видео или голосовое, без подписи

  • 24 июл.5 771923

    📝የገዳማውያኑ ጥቃት ሥርዓታዊና ጥላቻን ያዘለው ስልት ቀጣይ ምዕራፍ ነው! ©በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ 👉ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ 4:00 ላይ በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን፣ ቦረና ወረዳ የሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዓባይ ቅድስት አርሴማ ገዳም ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ 2(ኹለት) መነኮሳይያት እናቶች ወዲያው ሲገደሉ፣ 14(አሥራ አራቱ) እናቶች ደግሞ ክፉኛ ቆስለው መካነ ሰላምና ደሴ ሆስፒታል ተወስደዋል። በጥላቻና ኾነ ተብሎ በሚመስል መልኩ በተፈጸመው ጥቃት የገዳማውያኑ የዓመት ቀለብ እህልና ጥራጥሬ ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲኾን፣ ተግባር ቤት፣ ማብሰያ እቃዎች፣ የውሐ ማጠራቀሚያ የኮንክሪት ታንከር፣ የውሐ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሙሉ በሙሉ ወድማል። "በገዳሙ ሥርዓት የጠዋት 3:00 ፀሎት አድርሰን ኹሉም ወደተመደበበት ሥራ ሲሠማራ ድሮን የምትባለው ስትዞርና ድምጿን ሰምተናል፣ አይተናታል። እኛ ገዳማውያን ነን መቸም ቴክኖሎጂ ነው ያዩናል ምንም የሚያጠራጥርና የሚያስፈራን ነገር የለም ብለን ሥራችንን ቀጠልን" የሚሉት እማኝ "ነገር ግን እኛ እንዳስብነው አልነበረም ቆይተው ለሥራ በተሰበሰብንበት መዓት አወረዱብን፣ ያን የመሰለ ጭካኔ ለምን ማድረግ እንዳስፈለጋቸው ማሰብም ማለምም ይከብዳል። በተለይ የቆሰሉት ሲታዩ የሞቱት ይሻላል ያስብላል" ይላሉ። 👉ገዳሙ እጅግ ከባድ በረሃ ላይ ያለ ነው። በዙሪያው የሚገኝ ታጣቂም ይኹን ወታደር አናውቅም። እንግዲኽ ገዳሙ የቆመውም በእነዚኹ ወጣት መነኮሳይያት እናቶችች ድካም ነበር። ሠሪው ከተገደለ፣ አካሉ ከጎደለና የዓመት ቀለቡ ከወደመ ቀሪውንም የመግደል ያኽል ነው። ተጠንቶ የተደረገ ይመስላል ይላሉ ሌላው እማኝ። 👉እናት ፓርቲ ይኽ እብሪት የተላበሰ ድርጊት ከድግግሞሹ፣ እያስከተለ ከሚገኘው ጉዳትና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በታጣቂዎች ሽፋን በእምነቱ ተከታዮች፣ አገልጋዮችና ገዳማት ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ተራ ስህተት ሳይኾን ሥርዓታዊና ከጥላቻ የመነጨ ብሎም የአጥፍቶ መጥፋት ተግባር እንደኾነ በጽኑ ያምናል፤ ድርጊቱንም በጽኑ ያወግዛል። ለሞቱት ገዳማውያንም ሐዘኑን እንገልጻለን። ስለኾነም፣ 1. መላው ኢትዮጵያውያን ይኽን የአጥፍቶ ጠፊ የሽብር ድርጊት በአንድነት እንዲያወግዝ እንጠይቃለን። 2. መንግሥት ለድርጊቱ ሙሉ ኃላፊነቱን እንዲወስድና ድርጊቱ ሲፈጸም የሚያሳይ የፎቶና የቪዲዮ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ 3. ሀገርን ከጥቃት ለመጠበቅ የተቋቋሙ ተቋሟት ሕዝብን ጅምላ ጨረሽ ወደመኾን መሸጋገራቸው መላው ሕዝባችንና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያውቀው እና አጥፊው አካል ተጠያቂ እንዲደረግ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡ 4. መላው ኢትዮጵያውያን በዚያ ሐሩር ለሀገርና ሕዝብ የሚፀልዩ ገዳማውያን ቀለባቸው እና የመጠጥ ውሐ በጥቃቱ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ቀሪዎቹ በረሃብና ጥም ከማለቃቸው በፊት እንዲደርስላቸው እንጠይቃለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝባን ይጠብቅ! ©እናት ፓርቲ ሐምሌ ፲፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ           📍  ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

  • 24 июл.3 241293

    📝ሣንባውን ለተሰረቀው ... ሚዲያ ! 👉መነኮሳት ተገድለው ፣ ገዳም በመሳሪያ ተደብድቦ፣ ዘገባው ጳጳስ... እከሌ ከባድ አቀባበል ተደረገላቸው ? ፣ ሪባን ቆረጡ ፣ ሕንፃ መረቁ? ፣ ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ? በነገረችን ላይ ሐዋርያዊ ጉዞ ምንድን ነው ? መልሱን በኮሜንት ላይ ይፃፉ! 👉የሞቱት መነኮሳት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን አይወክሉም ፣ አደጋ የደረሰበትን ገዳም ቤተክህነቱ በመዝገብ አያውቀውም ? 👉መተንፈሻ ሣንባው ለተሰረቀው የቤተክርስቲያን ሚዲያ EOTC የቀረበ ምክረ ሀሳብ እና ተግሳጽ ©በአማን ነጸረ https://www.facebook.com/share/1C3qodYpQc/ 📍 ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

  • 23 июл.4 222575

    በእውነት ልብ ይሰብሯል

  • 23 июл.5 067463

    📝ልብን ይሰብሯል ያየነው  👉ዓለም በቃን ብለው  መልካሙን የሕይወት ጎዳና  መርጠው ከሚታየውም እና  ከሚሰማውም እራሳቸውን  አርቀው በመነኑ መነኮሳይት ላይ የደረሰው የግፍ ግድያና ጭፈጨፋ ለሰማውም ላየውም ልብ ይሰብሯል ፣  👉በዚህ ዘመነ መንግስት በርካታ የግፍ እና የጭካኔ ተግባሮች ተከናውነዋል ፣ ይኽኛው ግን ይለያል ፣የበቁ መናንያን ፣ በጸሎት የሚተጉ አበው ወእማት ፣ ምስባከ ቅዱሳን የሆነ ለዐይን የሚማርክ ፣ ለሕሊና ረፍትን በሚሰጥ ቅዱስ ቦታ  ራሳቸውን በገዳም ሰውረው በምናኔ ሕይወት ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳት በዚህ መጠን ሲገደሉ ፣ ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም ፣ የኦርቶዶክሳውያን ደም ለሁሉ ነገር መስዋዕት አለበት የተባለ ይመስል  በተደጋጋሚ  እንዲህ ዐይነቱ የግፍ በኦርቶዶክሳውያን ላይ መፈጸሙ ልብ ሰባሪ ነው ። 👉 ዛሬ ፍትሕ የሚጠይቅ  የኦርቶዶክሳውያን  አባት መሪ ይህ ለምን ይሆናል ብሎ የሚሞግት ማን ነው? ጉዳዩን ለዓለም ለማሳወቅ የሚጥር የሃይማኖት መሪ የለም? አሁን በሩ ተከፍቷል ፣ ምንም ይፈጠር ምንም የእኛዎቹ ዝምታን መርጠዋል ።    👉ዛሬ ያሉት  ዓላማቸው አንድ እና አንድ ገንዘብ ነው ። ሀሳባቸው  ሥልጣን ላይ እንዴት መቆየት አለብን ነው !!  ለእነዚህ መነኮሳይት ማዘን አበል የለውም !!  አዝነናል ብለው ለቅሶ ለመድረስ ቢያስቡም አበል የሚከፍላቸው የለም !! መግለጫ ቢያወጡም መንግስታችን ያዝንብናል ነው ነገሩ !!    👉ስለዚህ ዛሬ ያሉ የሃይማኖት መሪዎቻችን እንዲህ ዓይትነቱ ልብ ሰባሪ ሀዘን አያስጨንቃቸውም ፣ እነሱ ዛሬ ሕንፃ ሥላሴ ይፈርሳል ፣ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ታደሰ ብለው  በመንግስት በመደበላቸው ካድሬ በከፍተኛ አቀባበል ታጅበው በመብላት በመጠጣት ላይ ናቸው ።  ግን  ይህም ቀን ያልፋል ...  👉 የቤተክርስቲያኑም  ሚዲያ EOTC  https://www.facebook.com/share/1DK2DpSBBd የእነሱን ኮቴ እየተከተለ እዚህ ደርሰዋል ፣ እንዲህ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል  እያለ የተዋበ ፎቶ እያነሳ ይለጥፋል ፣ ግን እኛ ያልገባን የሞቱት ግን ኦርቶዶክሳውያን አይደሉም ፣ አደጋ የደረሰበት  ገዳም ቤተክህነቱ አያውቀውም ? እረ ወገን ምን አይነት ዘመን ላይ ነው የደረስነው ፣ 👉የሞቱት ሰማዕታት በረከታቸው ይደርብን🙏 ይህንን መልእክት ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ፣ ላይክ በማድረግ አድርሱ             📍  ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

  • 22 июл.3 791534

    📝በቁልቢ ገብርኤል ስም ..$$.. ምዝበሯ 👉በቁልቢ ገብርኤል ስም የተበላው ሚሊዮን ገንዘብ  ቀላል አይደለም ፣ የሕዝብ ንብረት ነው።  መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሆነ መንግሥት በትኩረት ሊያዩት ፣ ምርመራም ሊደረግበት ይገባል ። 👉በሁለት ፣ በሦት ወር  የቀለም ቅብ እድሳት ፣ የጉልሏቱን እና የተሰነጠቀውን ዕድሳት ፣ ውጭውን (Waterproof painting) ለማድረግ ፣ ያለ ሕጋዊ ጨረታ በጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁ እና በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሪነት ጥቂት በሚሆኑ የውስጥ ተባባሪዎች  ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደረግ እና  ታደሰ ብለው ነገ ተመረቀ ሊሉን ነው ። 👉ይህ ዕድሳት መደረጉ አስፈላጊ ነው ፣ ቀደም ሲል በብፁ አብነ አብርሃም ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዘመን አንድ ዓመት አልሞላውን የታላቁ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል  ገዳም እንዲታደስ ፣ በደብሩ አባት ያላሰለሰ ጥያቄ ቀርቦ ፣ ብፁዕነታቸውም በባለሞያ አስጠንጠው ፣ በጠቅላይ ቤተክህነቱ የቴክኒክ ኮሚቴ አስመርምረው ለዕድሳቱ የቀረበው ዋጋ 59 ሚሊዮን ብር  አካባቢ ነበር ፣ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ጥናቱ ተሰርዞ ፣ የተመረጠውን የቴክኒክ ኮሚቴ አፍርሶ በማን አለብኝነት ፣ በርካታ ሚሊዮኖችን መዝብሮ እንዲመዘበር ማድረግ ፣ አሳፋሪ ነው ። 👉ይህ ሳያንስ ነገ ሊመረቅ ነው በሚል ሰበብ ለአበል እና ለድግስ በረካታ ሚሊዮን ብር እንደተመደበ የውስጥ  የመረጃ ምንጮቻችን  ፣ አድርሰውናል  ይህ ደግሞ እኛም ከምናውቀው  በድግስ ሰበብ ምን እንደሚሰራ ጠንቅቀን እናውቃለን ። 👉ጥያቄው ዛሬ በዚህ ምርቃት ላይ የምትገኙ  ጳጳሳት  ፣ የተሰራው ሥራ ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ  ይወስዳል ወይ? የሕዝብ እና የሀገር ንብረት በዚህ ልክ ሲመዘበር ፣ ዝም ብሎ ማየት ኅሊና ላለው ስው ባድ ነው ። 👉ከዚህ በፊት ለግንቦቱ ርክበ ካህናት  ሲኖዶስ ተመረቀ የተባለው ሕንፃ ፣ ሙሉ ሕንፃው በባንድሪ  አሸብርቆ ያየነው ዛሬ ሕንፃው አገልግሎት ይሰጣል ወይ ? እባካችሁ ብፁዓን አባቶች ሰው ባያየን እግዚአብሔር ያየናል በሉ❗  ይህው ሕንፃው ተመረቀ የተባለው ወፍ የለም ቦዶ ኦናው ሥራው ሳያልቅ ለታይታ ድራማ ተሰራበት አሁን ቆማል ፣ 👉በዚህ በሕንፃ የግንባታ ሥራ ቢሊዮን ገንዘቦች እየተመዘበሩ ነው ፣ እያንዳንዱን በመረጃ እና ፣ የተቋራጩን ስም እና አሸነፈ የተባለውን የቢሊዮን እና የሚሊዮን ቁማሮች   በቅርቡ  ይፋ እናደርጋለን ።  ጥያቄው ግን ቅዱስ ሲኖዶሱም ሆነ መንግስት እየተዘረፈ ያለውን የሕዝብ እና የሀገር ንብረት ምርመራ እንዲደረግ እንጠይቃለን ። 👉የዛሬው የቁልቢ ገብርኤል ገዳምን ነው የምናየው ፣ ቁልቢ ታቦቱ ሰሚ ነው ፣ አማኙ ስለት ተስሎ ፣በእግሩ ሳይቀር ከመላው ዓለም ደጁን ይረግጣል ፣ ቦታው የፈውስ ቦታ ነው ፣ ብዙዎቻችንን ያሳደገ ፣ ደገኛ መልአክ ነው ፣ በዚህ ቦታ በርካታ ታአምራቶች ተክናውነዋል ፣ ከቤተመቅደሱ እስከ አፍአ ድረስ ሌቦችን ሳይቀር ሲቀጡ እና በቁማቸው ተዋርደው ያለፉም አሉ ፣  የቁልቢው ቅዱስ ገብርኤል  ልዩ ነው ፣ ንግሱ የደመቀ ፣ ታሪካዉ እና ጥንታዊ ቦታ ነው ። 👉ለኦሮምያ ቤተክህነት መመስረት እና ለጨረቃ ጳጳሳት ሹመት ዋንኛ ጥያቄ ሆኖ በወቅቱ የቀረበው ፣" በኦሮሚያ የሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል ገዳም ገቢ ውስጥ  በኦሮሚያ የሚገኙ አብያተክርስትያናት ተጠቃሚ አይደሉም " የሚል ነበር ፣ ዛሬስ ተጠቃሚው ማን ነው ? ግለሰቦች ወይስ ተቋሙ? 👉ቁልቢ ደብረ ኃይል ገዳም ከዋናው መስራባት ተመድቦ የሄደ ፣በወር የማያገኘውን አበል ይዞ ይመጣል አይደለም አሁን ያኔ ፣ ዛሬ ደግሞ የልማት አርበኛ ተብለው በቀጠሯቸው ሚዲያ እና አጫፋሪዎች ከ170 ሚሊዮን ብር የወጪ የተደረገበትን የቀለም ቅብ በሁለት ሦስት ወር ገደብ ተጠናቋ አለቀ የተባለው ሕንፃ ዕድሳት  ሥራ ለመመረቅ የሚጋበዙ ልዑካን ስንት አበል ይከፈላቸዋል? ፣ ወገኔ አሁን መዝናናት ነው ፣ መብላት መጠጣት ነው። 👉 በዓሉ ቅዳሜ ለእሁድ ነው ሠርግ እና ምላሹ ከአዲስ አበባ ድሬደዋ የሚቀበል አለ ፣ ጉዞው በአውሮፕላን ነው ፣ ጨዋታው በሚሊዮኖች  እና በመቶ ሺዎች ነው ፣ ጥያቄአችን ሲኖዶሱ ብሎም መንግስት እጁን ያስገባ፣ ምርመራ ይደረግ  ፣ አሁንም ነገም ድምፃችን❗ ሌላውም ... ይቀጥላል.....?           📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

  • ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ( Ethio Beteseb Media) pinned a photo

  • 22 июл.3 96419

    видео или голосовое, без подписи

  • 18 июл.5 01284

    📝ምን እንማር ...❗ 👉ያከበረህ ሕዝብ እንዳከበርህ እንዲቀጥል 💤 አክብረው ❗ አልያ ግን..... መውደቂያህን ታፋጥነዋለህ ፦ 👉ኮሜዲያ እሸቱ ፣ ካለፈው ስህተቱ ዛሬ ብዙ የተማረ ይመስለናል ፣ ሌሎቻችንም ከዚህ መማር አለብን ፣ 👉" ነጋዴ ሁሌ ደንበኛ ንጉስ ነው ይላል " ይህ አባባል ሳይሆን ሀቅ ነው ፣ በዝሕዝብ የበለጸገ መነሻውን መርሳት የለበትም ፣ ስህተት እንኳን ቢሰራ ላከበረው ሕዝን ሲል በፍጥነት ነገሮች ሳይሰፋፉ ይቅርታን ገንዘብ ማድረግ አለበት ። አሁንም መጀመሪያ ያከበረህን ሕዝብ ድረሱልኝ ብለሀል ፦ ፈጣሪ ይርዳህ🙏 📍 ኢትዮ ቤተሰብ ሚዱያ

  • 18 июл.4 72212

    🙏Message to parents 👉Today, we celebrate more than the completion of a course we celebrate growth in faith and identity. 👉Over the past four weeks, our students discovered who they are: ✨ Created in the image of God. ✝️ Followers of Jesus Christ. ⛪ Faithful members of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. 🎓 Students called to honor God through wisdom, character, and excellence. 👉May the lessons learned continue to guide their hearts, strengthen their faith and inspire them to live with purpose wherever God leads them. 🙏🙏🙏 Congratulations to all our graduates! May God bless your journey and help you shine as the light of Christ in your homes, schools, churches, and communities. "For we are His workmanship, created in Christ Jesus for good works." – Ephesians 2:10

  • 16 июл.4 072212

    https://youtu.be/dV7WTxvTvuw?is=UYwYTc1rzt4P3RBT

  • 15 июл.4 6182

    видео или голосовое, без подписи

  • 15 июл.5 3712

    видео или голосовое, без подписи

ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ( Ethio Beteseb Media) — tgindex