tgindex
ተዋሕዶን እንወቅ።

ተዋሕዶን እንወቅ።

Статистика

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኲሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድኅነነ እምዕለት እኪት ወባልሐነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ጸሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማዕታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 367
+1 за 2 дн.
Сутки
+2
+0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
505
26 постов
Вовлечённость
21,3%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 26
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
117
1/48двое суток
134
1/72трое суток
144

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 3 авг.421113

    ለጥቂት ደቂቃ አቁመው ያንብቡት፤ ሕይወትን የሚቀይር ጥሪ ነው! 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የሀገሬ ልጆች፣ እኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ። ዛሬ ይህንን መልእክት የምጽፍላችሁ ችግሬን ለሰው ከመናገር እና ከመለመን ይልቅ እግዚአብሔር በሰጠኝ እውቀት ሰርቼ አባቴን ለመደገፍ እና ትምህርቴን ላለማቋረጥ በመታገል ላይ ስለሆንኩ ነው። አባቴ በጽኑ ታሞ አልጋ ላይ በመውደቁ ምክንያት ስራ አቁሟል። እኔ ደግሞ ትምህርቴን ማቋረጥም ሆነ የሰውን እጅ ማየት አልፈለግሁም። ይልቁንም እግዚአብሔር በሰጠኝ ጥልቅ የግእዝ ቋንቋ እውቀት ሰዎችን ማስተማር እና በዚያውም አባቴን መርዳት እንደምችል አመንኩ። ✨ የትምህርቱ አላማ፡ ለእናንተ፡ ታሪካችንን፣ ጥንታዊ እውቀታችንን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችንን በምርምርና በጥልቀት ለመረዳት እንዲችሉ የግእዝን ቋንቋ ሰዋስው (Grammar)፣ ንባብ እና ንግግር (Speaking) በጥራት ማስተማር። ለእኔ፡ ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን የህክምና ወጪ በመሸፈን አባቴን መታደግ እና የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን ሳይቋረጥ መቀጠል። 📚 የምናስተምረው ትምህርት፡ ሙሉ የግእዝ ሰዋስው (Grammar) የንባብ ስልቶችና ልምምድ (Reading) የንግግር እና የቃላት ጥናት (Speaking) 💰 ክፍያ፡ መማር ለሚፈልጉ ሁሉ ቀላል እንዲሆን በጣም አነስተኛ ክፍያ ነው በወር 200 ብር ብቻ። ወዳጆቼ! እኔ በእግዚአብሔር ስም፣ ስለ ድንግል ማርያም ብዬ የምጠይቃችሁ ትልቅ ትብብር አለ፡ ራሳችሁ መማር ካልቻላችሁ እንኳን ሊንኩን ለሌሎች ማጋራት (Share ማድረግ)። መማር የሚፈልጉ ወዳጆቻችሁን፣ ቤተሰቦቻችሁን ወይም ልጆቻችሁን በመጠቆም ተማሪ እንድታፈሩልኝ። በስራዬ አግዙኝ፤ ከመለመን እና ከመቸገር ታደጉኝ! 📌 ለመመዝገብ እና ትምህርቱን ለመቀላቀል፡ 🔗 የቴሌግራም ሊንክ፡ https://t.me/HiyawLissan 📞 ስልክ ቁጥር፡ 0943910036 (እባካችሁ ይህን መልእክት ለሌሎች በማጋራት የታመመውን አባቴን እንድታክም እና ትምህርቴን እንድቀጥል በጎ ፈቃዳችሁ ይሁን!)

  • 2 авг.3755из Applied_CHRISTIANITY

    ✉️ "" ተሸክሞህ ይሄዳል ! "" JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 1 авг.36423из Applied_CHRISTIANITY

    ✝ ወደ ክርስቶስ መገስገስ የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡፡ ስለ ምድር አውቀህ ስለ ሰማይ ዝንጉ ከሆንህ ፣ ስለሚጠፋው እንቅልፍ አጥተህ ስለማይጠፋው ከደነዘዝህ በእውነት ከንቱ ነህ ፡፡ የሚያውቀህን አምላክ ትተህ የማያውቁህን ዝነኞች ስታስስ መዋል ፣ ገና ፈሳሽ ሳለህ ሳትረጋ ያወቀህን ጌታ ገሸሽ ብለህ የካዱህን ስታስብ መኖር ፣ ወላጆችህ ሳያዩህ በዓይነ ምሕረት ያየህን እግዚአብሔር አለማየት ፣ ዓለም ሳይፈጠር የመረጠህን ምርጫህ አለማድረግ በእውነት ከንቱ ነው ፡፡ "ደስታ የሌለው እውቀት ፣ ዕረፍት የሌለው ጥበብ እግዚአብሔርን ማወቅ የሌለበት ነው ፡፡" JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 31 июл.3622из Applied_CHRISTIANITY

    ሰላም ለእናንተ ይሁን ? እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ዛሬ ምሽት 3፡00 ሰዓት ትምህር ይኖረናል ። በመዘግየታችን ይቅርታ እንጠይቃለን !ለሌሎች በማጋራት አገልግሎቱን እንደግፍ ። - ለመሆኑ ከመማርና ከአገልግሎት የቱ ይበልጣል ? የቱስ ይቀድማል ? የቱስ ይጠቅማል ? በዋናነት ወደ ቤተ ክርስቲያን የምንመጣው ለአገልግሎት ወይስ ለትምህርት ? Join Live Stream - https://t.me/Applied_CHRISTIANITY?livestream

  • 30 июл.3731из Applied_CHRISTIANITY

    ✝ "" እስቲ ልሞክረው ፣ ምን ያደርጋል ብለን የገባንበት ኃጢአት ብዙ ነው ። JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 29 июл.41943из Applied_CHRISTIANITY

    "የማያልፈው ምንድነው? ከተባለ መልሱ ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት ነው ።"

  • 29 июл.463из Amlake_Birhan

    አምላከ ብርሀን በኦሮምኛ መጥታለች @Waaqa_Ifaa በየቀኑ ከቤተክርስቲያንን አምልኮ መፃህፍት ቀንጭበን ወደናንተ እናደርሳለን ፤ ቤተክርስቲያን እንዴት ባለ ፍቅር ሙሽራዋን እንደምታልከው አብረን እናያለን። አልጫ ህይወታችንን በአምልኮ ጣዕም እናጣፍጥ ዘንድ እንጋብዛለን ፤ ለኦሮምኛ ተናጋሪዎች Share በማድረግ ተባበሩን

  • 25 июл.634153из SSC_KIdme_Gibi_Gubae

    አቤል ይባላል የግቢ ጉባኤያችን አባልና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። አሁን ግን እንደምትመለከቱት አደጋ አጋጥሞት የእኛን እርዳታ ይፈልጋልና የምንችለውን ያህል ከላይ በተጠቀሱት አካውንቶች በመላክ እናግዘው። ማጋራትም እርዳታ ነውና ይህን ፖስት ለምናውቃቸው ሰዎች በማድረስ እነርሱም እንዲያግዙ እናድርግ

  • 25 июл.52432из Applied_CHRISTIANITY

    እንኳን አደረሳችሁ 🕊 የ3 ዓመቱ ሕፃን የእናቱን የእምነት ጉድለት በጸሎት አራቀላት በእጁም ይዟት ወደ ሕይወት መራት እናቱም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ ፤ ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው ። ከፍላቱ የተነሣ እንደ ነጎድጎድ የሚያስፈራ የነበረው እንደ ማለዳ ውርጭ ቀዘቀዘላቸው ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና ። JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 24 июл.50722из Applied_CHRISTIANITY

    "" ለምን ተኝተሃል ? "" /ዮና 1÷6/ ( ዝክረ ቅዱስ ዮናስ ነቢይ ) [ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ] JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 19 июл.67264из Applied_CHRISTIANITY

    ✝ እግዚአብሔር የሌለበት ! እግዚአብሔርን ማወቅ መሠረት መሆኑን ረስተህ ችላ አልከው ። ዛሬ ሁሉን ጨብጠህ ደስታ የምታጣው መሠረት የሌለው ቤት ስለሠራህ ነው ። እግዚአብሔርን ነፍገህ ለልጅህ ምድራዊ እውቀትን ብቻ ሰጠኸው ፣ ልጅህን ግን አጣኸው ። ያንተ ስም እንዳይሰደብ ብቻ ልጅህን በሥነ ሥርዓት አስጨነቅኸው ፣ ነጻ ሲወጣ ግን የታመቀ ኃጢአቱን በሁሉ ፊት አፈነዳው ። እግዚአብሔርን ማወቅና ማፍቀር ብታስተምረው ልጅህ እስከ ሞትህ ድረስ ያንተ ይሆን ነበር ። ከእግዚአብሔር ነጥሎ ልጅን ከእውቀት ጋር ብቻ መሸሸግ የሚያፈስ ጣራ ውስጥ እንደ ማስጠለል ነው ። ዛሬ እግዚአብሔርን ማወቅ ከትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲወጣ ተደረገ ። ለራሱ ጌታ መሆን አቅቶት ይኸው ትውልድ ወደቀ ። ስለ እግዚአብሔር መናገር ፈሪ ፣ አፈረ ። ቤተ ክርስቲያን ትውልድ ማሰሪያ ነው ፣ ሃይማኖትም አደንዛዥ ዕፅ ነው ተባለ ፣ ይኸው አሁን በምድር ላይ ካሉ አራዊቶች በጥቂት የሚለዩ ልጆችን አፈራን ። እግዚአብሔር ማወቅ ፀሐይ ነው ፣ ምድራዊ እውቀት ግን የቀን ሻማ ነው ። አለባበስህ ተስተካክሎ ኑሮህ ከተዘባረቀ ፣ ሥልጣኔ ገብቶህ የሕይወት ውል ከጠፋህ ፣ ብዙ ደርጅቶችን እያስተዳደርህ ቤትህ ከሸፈተብህ ፣ አገር እየገዛህ መንፈስህ ካመጸብህ መፍትሔው እግዚአብሔርን አሁንም አሁንም ማወቅ ብቻ ነው ። እግዚአብሔርን ማወቅ በራሱ ደስታ አይሆንህም ፣ በእግዚአብሔር እንደ ታወቅህ ስታውቅ ግን ለዘላለም እረፍት ይሰማሀል ። ወዳጄ ዝም ብለህ ተማር ! - .....እንዴት #አደራችሁ ? - .....እንዴት #አረፈዳችሁ ? - .....እንዴት #ዋላችሁ ? - .....እንዴት #አመሻችሁ ? JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 18 июл.561151из Applied_CHRISTIANITY

    ምናልባት . . . "አቤቱ ፡ ወደ ፡ ፈተና ፡ አታግባን ፡ ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ አድነን ፡ እንጂ ፡ መንግሥት ፡ የአንተ ፡ ናትና ፡ ኃይል ፣ ክብር ፣ ምስጋና ፡ ለዘለዓለሙ ።" አሜን ፫ JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 17 июл.5002из Applied_CHRISTIANITY

    ✝ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ! "" ለመሆኑ ! በኃጢአት ለመውደቃችን ፣ ከቤተ ክርስቲያን (ከአገልግሎት) ለመራቃችን እና ለግድ የለሽነታችን ተጠያቂው ማን ነው ? "" ዛሬ ማታ 3፡00 ሰዓት ይጠብቁን ! JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 12 июл.66234из Applied_CHRISTIANITY

    ✥ ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ አማርኛ እንገልጠዋለን? ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው? የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ? ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም ። ቅዱስ ዻውሎስ ከነገደ ብንያም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር ። ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው ። ይህ የሆነው በ42 ዓ.ም ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር ። ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ ፣ ጨው ሆኖ አጣፈጠ ። ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ ። ስለ ወንጌል ተደበደበ ፣ ታሠረ ፣ በእሳት ተቃጠለ ። በድንጋይ ተወገረ በጦር ተወጋ ። ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ ። በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ ። ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ ። እርሱን የመሰሉ ፣ እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል ። ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል ። ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው ማለት ነው ። « ወስብሐት ለእግዚአብሔር » - .....እንዴት #አደራችሁ ? - .....እንዴት #አረፈዳችሁ ? - .....እንዴት #ዋላችሁ ? - .....እንዴት #አመሻችሁ ? JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 12 июл.45713из Applied_CHRISTIANITY

    እንኳን አደረሳችሁ 🕊 ✝ ሐምሌ 5 ቀን ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዕረፍታቸው ነው ። ✝ ✥ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው ። ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው ። በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ ፣ ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው ። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ ፣ በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል ። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል ። (ማቴ 16÷17 ፣ ዮሐ 21÷15) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል ። ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል ። ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል ። በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል ። አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል ። እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል ። የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ ። ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ.ም የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው ። "እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም" አላቸው ። እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል ። በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል ። በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ ነበር ። JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 11 июл.51365из Applied_CHRISTIANITY

    ✝ ጌታ ሆይ አስተምረኝ ! ✥ ክፍል 1 ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ መላልሶ ከሚለምነው ልመና አንዱ " አስተምረኝ " የሚል ነው ። " አቤቱ መንገድህን አስተምረኝ ፧ ፍለጋህንም አስተምረኝ ። በእውነትህ ምራኝ አስተምረኝም ።" /መዝ 24÷1-7/ እውቀትን በተፈጥሮ ፣ በልምድ ፣ በትምህርት ፣ በጉዳት እናገኛል ። እግዚአብሔር አእምሮን የፈጠረው እንድናውቅ ስለፈለገ ነው ። መማርን መጥላት አእምሮ የተባለው ትልቅ መሣሪያ ያለ ሥራ እንዲሆን ማድረግ ነው ። ጡንቻ ያለ ሥራ እንደሚሟሽሽ አእምሮም ያለ እውቀት እየሟሸሸ ይመጣል ። ሰዎች መልካሙን ነገር ለማወቅ ካልፈለጉ በክፉ እውቀት እየሰለጠኑ ይመጣሉ ። መልካሙን ማወቅ ክፉውን በተግባር ላለማወቅ ይረዳል ። ቀናችንን አዲስና የሚያስደስት ማድረግ የምንችለው ትላንት የማናውቀውን ዛሬ ማወቅ ፣ መማር ስንጀምር ነው ። ሰው መኖሩን የሚወደው በአዲስ እውቀት ቀኑን እስከ ጀመረ ድረስ ነው ። የዓለማችን ትልልቅ ፈላስፎችና አዋቂዎች እንኳ አእምሮአቸውን ከመቶ ሁለት እጅ ብቻ ተጠቅመዋል ይባላል ። ተመልከት አእምሮ ብዙ ያልተሰራበት መሣሪያ ነው ። ዛሬ በእፍኝ እውቀት አእምሮአችን የሞላ የሚመስለን በጣም የምንገርም ሰዎች አለን ። መማር ስለ መረጃ ሳይሆን ስለ መፍትሔ የሚያስብ ነው ። መፍትሔው ያለው ደግሞ ችግሩን በደንብ በማወቅ ውስጥ ነው ። አዋቂ ሰው ሁሉን እንዳላወቀ ይገባዋል ። ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመማር ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃል ። ..... ይቀጥላል - .....እንዴት #አደራችሁ ? - .....እንዴት #አረፈዳችሁ ? - .....እንዴት #ዋላችሁ ? - .....እንዴት #አመሻችሁ ? JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 5 июл.71056из Applied_CHRISTIANITY

    ራእየ ኒፎን ገጽ 59 የይቅርታ ፏፏቴ የርኅራኄ ባለጠጋ የሆንክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ! ፊትህን ከእኔ አትመልስ፤ ማረኝ፤ ይቅርም በለኝ ፡፡ ጌታ ሆይ “አላውቅህም አትበለኝ !' ጌታ ሆይ እስከዛሬ የት ነበርክ?' ብለህም አትቆጣብኝ ፡፡ በኃጢአት የቆሸሽሁ ፧ በበደል እንደ ጢስ የጠቆርሁ ፤ ሕግህን በመተላለፍ የበሰበስሁ ፤ ፍቅርህን በመርሳት የተዋረድሁ ፤ በርኵሰት የሽተትሁ ፤ በዲያብሎስ ምክር የጠፋሁ ፤ ሰዎች በሚሠሩት አስነዋሪ ሥራም ዋነኛ የሆንኩ የማልጠቅም ትቢያና ጉድፍ ልጅህን አትናቀኝ ፤ ከፊትህም አፍሬ አልመለስ ፡፡ መምህሬ ሆይ ! ከእኔ አትራቅ ፤ ራራልኝ ፤ አድነኝም ፡፡ ሰው ወዳጅ ሆይ “አንተ የኃጢአተኛን በንስሐ ከክፉ መንገዱ መመለሱን እንጂ መጥፋቱን እንደማትሻ' አውቃለሁና ተመልሰህ እስክትረዳኝና ምሕረትህን እስካገኝ አላርፍም ፡፡" - .....እንዴት #አደራችሁ ? - .....እንዴት #አረፈዳችሁ ? - .....እንዴት #ዋላችሁ ? - .....እንዴት #አመሻችሁ ? JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 1 июл.75072из Applied_CHRISTIANITY

    📖 ራእየ ኒፎን 2013 ዓ.ም ከገጽ 222 - 228 “በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሳለን ዘወትር ከምሥጢራት ሊካፈል ወደ ቤተ ክርስቲያን በመገሥገስ የሚተጋ ለጽድቁ ሥራ የሚጋደል አንድ ወጣት ወደ አባታቸን ቀርቦ “አባቴ ሆይ የዘለዓለም ሕይወት እንዳገኝ ምን ላድርግ?” ሲል ጠየቀው ፡፡ “ልጄ ንጹሕ ነፍስ ያለችህ ኾነህ ሳለህ በኃጢአት ከተበላሸ አንድ ሽማግሌ ምን የሚጠቅም ነገር አለና ትጠይቀኛለህ?” አለው ፡፡ “ምክንያቱም አባቴ የእግዚአብሔር ቃል “አባትህን ጠይቅ ይነግርሃል” ይላልና ፤ ከአንተ የሚጠቅመኝን ቃል ለመስማት ጠየቅሁህ ፡፡ እባክህ የማልጠቅም ከኾንሁ ከእኔ ፊትህን አትመልስብኝ ፡፡” “ለመመንኮስ አስበሃል ወይስ ለሰው ሁሉ የተፈቀደውን ሕይወት በመኖር ፈጣሪህን ደስ ለማሰኘት ነው ምኞትህ? በማለት ወጣቱን ጠየቀው ፡፡ “አባቴ ለጊዜው በዚህ እየኖርሁ ለየትኛው ሕይወት የተገባሁ እንደ ኾንሁ ራሴን መፈተን እፈልጋለሁ ፡፡ ከዚያ የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደምትመራኝ እሄዳለሁ ፡፡” አለው ፡፡ እንግዲያውስ ልጄ በሰዎች መካከል የምትኖር ከኾነ በእነዚህ ነገሮች ዙሪያ ጥንቃቄ ልታደርግ ይገባሃል ፡፡ በማንም ላይ ትችትን አትሰንዝር ፤ በማንም አትሳለቅ ፤ ለመቆጣት አትቸኩል ፤ ማንንም አትናቅ ፣ እገሌና እገሌ በቅድስና ይኖራሉ ፤ እገሌና እገሌ ደግሞ በኃጢአት ተውጠዋል ብለህ ከመናገር ተጠንቀቅ ፡፡ ምክንያቱም “በማንም አትፍረድ” ማለት ይህ ነውና ፡፡ ሁሉንም ሰው በተመሳሳይ ሐሳብ በእኩል ወዳጅነት በንጹሕ ልቡና ተመልከት ፡፡ እንደ ክርስቶስ አድርገህ ተቀበላቸው ፡፡ በሰዎች ላይ የሚፈርድን ሰው ጆሮህን ከፍተህ አትስማው ፡፡ የበለጠ ግን በሚሰጠው ሐሳብ ተስማምተህ ደስተኛ እንዳትኾን ተጠንቀቅ ፤ አፍህንም ጠብቅ ፡፡ በሌላ አነጋገር ለመናገር የዘገየህ ለጸሎት ግን የምትፋጠን ኹን ፡፡ ምንም እንኳ እያደረገ ያለው ስሕተት ቢኾንም በሌሎች ሲፈርድ የሰማኸውን ሰውም በሕሊናህ እንዳትፈርድበት ተጠንቀቅ ፡፡ ከዚያ ይልቅ የራስህን ድክመት እያሰብክ በራስህ ላይ የምትፈርድ ኹን ፡፡” አለው ፡፡ “አባቴ አኹን የነገርከኝ ዘወትር ሳያቋርጡ በተጋድሎ ለሚኖሩ ነው ፡፡ የማልጠቅም እኔ እግዚአብሔርን እንዴት ደስ ማሰኘት እችላለሁ? በማለት የመከረውን ሁሉ በደንብ ከሰማ በኋላ ጠየቀው ፡፡ “ልጄ በብዙ ምኞትና የሥጋ ፈቃድ ለሚቃጠል ወጣት ንጽሕናንና ትሕትናን ከያዘ ተስፋ ያለው ነው ፡፡ በጸጋ እያደገ እስኪሄድም ጌታ እግዚአብሔር ከዚያ በላይ አይጠብቅበትም ፡፡ ስለዚህ ወጣትነትህን በንጽሕናና በትሕትና አስጊጠው ፡፡ ራስህን በትሕትና ከሁሉ በታች አዋርድ ፡፡ ይህን ካደረግህ በእውነት ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ይኖርሃል ፡፡ በሕሊናህም በቅድስና ታላላቅ ቅዱሳን የደረሱበት ከፍታ ላይ እንደ ወጣህ አታስብ ፡፡ ይልቅስ ነፍሴ ሆይ በእግዚአብሔር ፊት የሚያቀርብሽ ምንም መልካም ሥራ የለሽም ፡፡ ዕለት ዕለት በክፋት ከአጋንንት እንኳ እየባስሽ ሄደሻል ፡፡ በፍርድ ቀን የሚጠብቅሽ ቅጣት ምን ያህል ይኾን? ወዮልሽ! በማለት ራስህን ውቀስ ፡፡ ጸሎት ስትጸልይም በዓለም ካሉት ኃጢአተኞች ሁሉ የከፋው ሰው ጸሎት እንደ ኾነ ቊጠር ፡፡ … አንድ ሰው ሲበድልህ ካየህ ስለ እርሱ ራስህን ውቀስ ፡፡ አንተን ሰው ቢሰድብህ፣ ቢተችህ፣ ቢሳለቅብህ፣ ፈጽሞ ቢያዋርድህ እንኳ በሕሊናህ ራስህን አዋርደህ በሕይወት እንኳ ለመቆየት የማይገባህ መኾንህን እመን ፡፡ ይቅርታና ድኅነት የሚመጡት እነዚህን ተከትሎ ነው ፡፡” አለው ፡፡ - .....እንዴት #አደራችሁ ? - .....እንዴት #አረፈዳችሁ ? - .....እንዴት #ዋላችሁ ? - .....እንዴት #አመሻችሁ ? JOIN @Applied_CHRISTIANITY

  • 26 июн.7033из Applied_CHRISTIANITY

    ✝ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ! (በዋናነት ለ12ተኛ ክፍል ተፈታኞች የተዘጋጀ) ነገ ማታ 3፡00 ሰዓት ይጠብቁን ! JOIN @Applied_CHRISTIANITY

ተዋሕዶን እንወቅ። — tgindex