ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
Статистикаየወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ሚድያ 👇ተከታዮቹን ገጾች ይቀላቀሉ 👇 Telegram https://t.me/wku_gg_media TikTok tiktok.com/@wku_gg Instagram https://www.instagram.com/wku_gbi_gubae YouTube https://www.youtube.com/@Wku_gg የፎቶ ማኅደራችን @wku_gg_gallerystore ለአስትያይቶ @wkugg_bot
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 660
- 1/48двое суток
- 756
- 1/72трое суток
- 815
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
❝ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ — ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም። በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ❞ — ቅዳሴ ማርያም ድንግል ዘርዕ ዘይወጽእ እምስካበ ተዓዳዌ ሕግ ይከውን ለቅጥቃጤ ወለሙስና ባለው ፈቃድ የተጸነሽ አይደለሽም። አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ። ❝ክቡር አውስቦ በኵለሄ ወለምስካቦሙኒ አልቦ ስዕበት❞ ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡ [አንድም]: ❝እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ ወበዓመፃ ወለደተኒ እምየ❞ እንዲል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት (መዝ. ፶)፡ በልተው ጠጥተው በሚያደርጉት ፈቲው ጽነት የተጸነሽ አይደለሽም። ለአብርሃም ❝ብዝኁ ወተባዝኁ ... ❞ ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ [ታሪክ ... ] የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታ በጥሪቃ ይባላሉ። ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ ብዕላቸውም የወርቅ የብር የፈረስ የበቅሎ የሴት ባሪያ የወንድ ባሪያ ነው። ከወርቁ ብዛት የተነሣ እንደ አምባር እንደ ቀለበት እያሰሩ ከበሬው ከላሙ ቀንድ ያደርጉት ነበር። ይህን ያህል አቅርንተ ወርቅ ይህን ያህል አቅርንተ ብሩር ተብሎ ይቆጠር ነበር እንጂ የቀረው አይቈጠርም ነበር። ከእለታት ባንዳቸው ከቤተ መዛግብት ገብቶ የገንዘቡን ብዛት አይቶ ቴክታ :- ❝እኔ መካን አንች መካን ይህ ሁሉ ገንዘብ ለማን ይሆናል?❞ አላት፤ እርሷም :- ❝እግዚአብሔር እንጂ ከኔ ባይሰጥህ ወይ ከሌላ ይሰጥህ ይሆናል አግብተህ አትወልድምን?❞ አለችው። እርሱ ግን:- ❝ይህንስ እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል❞ አላት። በዚህ ጊዜ አዘኑ ወዲያው ራዕይ አይተዋል። ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ እንቦሳይቱ ሌላ እንቦላ እየወለደች እስከ ፮ ስትደርስ ፮ተኛዪቱ ጨረቃን - ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ህልም ፈቺ) አለና ሂደው ነገሩት። ❝ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ። የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል።❞ አላቸው። ❝እንግዲህ ጊዜ ይተርጕመው።❞ ብለውት ሄዱ። ከዚህ በኋላ ጸነሰች። ወለደች። ስሟን ❝ሄኤሜን❞ አለቻት ረከብኩ ስእለትየ፣ ረከብኩ ተምኔትየ ማለት ነው (ስእለቴን፣ ልመናዬን፣ የልቤን መሻት አገኘሁ እንደማለት)። ሄኤሜን ዴርዴን ዴርዴ ቶናን ቶና ሲካርን። ሲካር ሄርሜላን ሄርሜላ ሐናን ወለደች። ሐና አካለ መጠን ስታደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት። ምክነት ወርዶ እንደ አያቶቿ ሁናለች ብዕሉ (ሀብቱ) ግን በመጠን ሁኗል። ከጎረቤቷ በዝሙት የምትኖር አንዲት ሴት ነበረች ሐና :- ❝ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እስማለሁ ብዬ ነበር ነገር ግን የምለብሰው ልብስ የለኝም❞ አለቻት። እርሷም :- ❝ልብስማ የኔ ካንድ ሁለት ሶስት ልብስ ያለልሽ አይደለም ያንን ለብሰሽ አትሔጅም?❞ አለቻት። ❝ያንቺ ልብስ የተሰበሰበ በዓስበ ደነስ በአስበ ዝመት ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ንጹሐ ባሕርይ ነውና ንጹሕ ነገር ይወዳል። ይህን ለብሼ ብለምነው ምን ይሰማኛል ብዬ ነዋ❞ አለቻት። ❝ሐና እኔ በምን ምክንት ልጅ ነሳት እያልሁ ሳዝንልሽ እኖር ነበር ላካ እንደ ደንጊያ አድርቆ ያስቀረሽ ይህ ክፋትሽ ነው❞ አለቻት በዚህ አዝናለች። [አንድም]: ሁለቱ ሁሉ መሥዋዕት እናቀርባለን ብለው ከቤተ መቅደስ ሄዱ። ሊቀ ካህናቱ ሮቤል ይባል ነበር፡፡ ❝ወኢይትዌከፍ መሥዋዕቶሙ ለመካናት እንጂ ይላል አናንተማ ብዝኁ ወተባዝኁ ብሎ ለአዳም የነገረውን ያስቀረባችሁ ርጉማን አይደላችሁምን? ቢጠላችሁ ነው እንጂ ቢወዳችሁማ ልጅ ይሰጣችሁ አልነበረምን መሥዋዕታችሁን አልቀበልም❞ ብሏቸው በዚህም እጅግ አምርረው እያዘኑ ተመልሰዋል። [አንድም]: ከአዕሩገ እስራኤል የወለዱ ሰዎች የሚመገቡት ተረፈ መሥዋዕት ነበር። ያንን ነስቷቸው እያዘኑ ሊመለሱ ከዛፍ ስር ተቀምጠው አርጋብ (ርግቦች) ከልጆቻቸው ጋራ ሲጫወቱ፤ ዕፅዋት አብበው አፍርተው አይታ :- ❝አርጋብን በባሕርያቸው እንዲራቡ፥ ዕፀዋትን እንዲያብቡ እንዲያፈሩ የምታደርግ የኔ ተፈጥሮዬ ከደንጊያ ይሆን? ልጅ የነሣኸኝ?❞ ብላ አዘነች። ከቤታቸው ሂደው :- ❝ወንድ ልጅ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር አንጣፊ ጋራጅ ሁኖ ይኖራል፤ ሴት ብንወልድ እንጨት ሰብራ ውሀ ቀድታ ትርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ትኑር❞ ብለው ብፅዓት ገብተዋል። የሐምሌ አመ ፴ ዕለት እርስዋ ለእርሱ:- ❝ጸምር ሲያስታጥቁህ መቋ ሚያህ አፍርታ ፍጥረት ሁሉ ሲመገባት አየሁ❞ ብላ፤ እርሱ ደግሞ ለእርሷ :- ❝ጸዓዳ ርግብ ፯ቱን ሰማያት ሰጥቃ መጥታ በራስሽ ላይ ስታርፍ፥ በቀኝ ጆሮሽ ገብታ በማኅፀንሽ ስታድር አየሁ❞ ብሎ ያዩትን ራዕይ ተጨዋውተዋል። አሁንም በሀገራቸው መፈክረ ሕልም አለና ሂደው ነገሩት። አሁንም እንደተለመደው በድጋሚ ❝ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ❞ አላቸው። ግራ ተጋብተው ❝አንተስ አልፈታኸውም ጊዜ ይፍታው❞ ብለው ተመልሰዋል። በዛሬው ዕለት በነሐሴ በ፯ት ቀን መልአክ መጥቶ :- ❝ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ❞ ብሏቸው በብሥራተ መልአክ በፈቃደ አምላክ እመቤታችን ተጸነሰች። በተጸነሰችም ጊዜ ብዙ ተአምራት ተደርጓል። በርሴባ የምትባል አክስት ነበረቻት አንድ ዐይና ነች። ሐና ፡ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኘሽ መሰለኝ ጡትሽ ጠቍሯል፥ ከንፈርሽ አርሯል ብላ ማኅፀኗን ዳስሳ ዐይኗን ብታሸው በርቶላታል፤ ይህንን አብነት አድርገው ሕሙማን ሁሉ ማኅፀኗን እየዳሰሱ የሚፈወሱ ሁነዋል። ዳግመኛም ሳምናስ የሚባል ያጎቷ ልጅ ነበር ሞተ፤ ትወደው ነበርና ያልጋውን ሸንኮር ይዛ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ተነሥቶ:- ❝ሰላም ለኪ ኦ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ❞ ብሎ ከመፈክረ ሕልም ሳይፈታ የቀረውን የሕልም ክፍል ተርጕሞላታል። ከዚህ በኋላ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ከነዚህ ወገን የሚሆኑ ዳዊት ሰሎሞን አርባ አርባ ዘመን እንደ ሰም አቅልጠው እንደ ገል ቀጥቅጠው ገዙን ደግሞ ከዚህች የተወለደ እንደምን ያደርገን ይሆን ብለው በጠላትነት ተነሱባቸው። መልአክ ኢያቄምን ❝አድባረ ሊባኖስ ይዘሃት ሂድ!❞ ብሎት አድባረ ሊባኖስ ሂዳ ወልዳታለች። ❝እምሊባኖስ ትወጽእ መርዓት❞ ያሰኘውም ይህ ነው። እንኳን ለእመ ምሕረት፥ ለእመቤታችን በዓለ ጽንሰት አደረሳችሁ ምእመናን። በረከቷ፣ ረድኤቷ እንዲሁም የታመነ ጽኑ ኪዳኗ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን። ዲ/ን ኃይለራጉኤል
ዛሬ ማታ 2:00 በ ጭራሽ አይቀርም share በማድረግ ለሁል እናዳርስ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት መከታተል ትችላላችሁ! 👉Link👈 መልካም የ ሱባኤ እና የ ፆም ጊዜ ይሁንልን!! የ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ጉባኤ!!
እንኳን ለጾመ ማርያም አደረሳችሁ እንደምታውቁት በዚህ ጾም ሌሊቱን ሙሉ ሰአታት በተባለው የቅዱስ አባ ጊዎርጊስ ዘጋስጫ ምስጋና እግዚአብሔርን እያመሰገንን እናድራለን ። ሰአታቱ ብዙ ቦታ ከማታ 4 ሰአት እስከ ጠዋት 11 ነው በዋነኝነት ካህናት እና ዲያቆናት ናቸው የሚቆሙት ፤ ሲነጋ ደግሞ መሪጌቶች ስብሐተ ነግህ ያደርሳሉ ፤ ከዛ ረፈድ ሲል የመጽሐፍ መምህራን ውዳሴ ማርያም ይተረጉማሉ ... ከዛ ወደ ቅዳሴ እና በተቻለን አቅም ሌሊት በሰአታት ቀን በቅዳሴ ለመትጋት እንሞክር ። ከተወደደች እመቤታችን ረድኤት፤ በረከት፤ ፍቅር አይለየን ።
ፍልሰታን እንዴት እንጹም ??? እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለተወዳጇ ተናፋቂዋ ልጅነታችንን ለምታስታውሰን ጾመ ማርያም 🥰 እንግዲህ ፍልሰታ በቤተክርስቲያናችን እንዲጾሙ ከተደነገጉ 7ቱ አጽዋማት መኻል አንዱ ነው፥ እናም ይህችን 16 የጾም ቀናት እንዴት እናሳልፍ ? ፩- ህዋሳትን ማጾም፦ ዓይናችንን በፈቃዳችን ክፉ ከማየት መከልከል፥ ጆሯችንን በፈቃዳችን ክፉ ከመስማት መከልከል፥ አፍንጫችንን በፈቃዳችን ፍላጎት ቀስቃሽ የሆኑ ሽታዎችን ከማሽተት መከልከል፥ እግራችንን በፈቃዳችን ወዳልተገባ ቦታ ከመሄድ መከልከል እና እጃችንንም በፈቃዳችን ያልተገባ ነገር ከመንካት በመከልከል ማለት ነው። ፪- ከቅዳሴ መሳተፍ እና ቅዳሴውን ማጣጣም፦ ቅዳሴ ሰማይና ምድር በአምልኮት ተባብረው አንድ የሚሆኑበት ነው። በመሆኑም የምንችል በፍልሰታ ወቅት ያለውን ቅዳሴ በመሳተፍ እጥፍ ድርብ በረከትን መቀበል እንችላለን። ፫-ንስሐ በመግባት፦ ንስሐ አባት የሌለን በመያዝ፥ ያለን ደግሞ ንስሐ አባቶቻችንን በማግኘት የእመቤታችንን አማላጅነት እየለመንን ንስሐን እንግባ። ይህ የጾሙን ጊዜ በበለጠ ፍቀር እና መንፈሳዊነት እንድናሳልፍ ትልቅ ጉልበት ይሰጠናል። ፬-ከቅዱስ ቁርባን በመሳተፍ፦ በክርስትና ሕይወት ውስጥ መጾሙ፥ መጸለዩ፥ ንስሐ መግባቱ፥ በጎ ምግባራትን ማድረጉ ሁሉ የሚመሰገን ቢሆንም ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ከሌለበት ግን ትልቅ ኪሳራ ነው። በመሆኑም የፍልሰታ ጾምን ከመጾም እና በቅዳሴ ከመሳተፍ ባለፈ ንስሃ በመግባት እና ቀኖናችንን በመፈጸም ከቅዱስ ቁርባኑ መቀበል ይኖርብናል። ፭- መንፈሳዊ መጽሐፍትን ማንበብ ልምድ ማድረግ፦ የንባብ ልምድን ለማዳበር ከሚመከሩ ወቅቶች መካከል አንዱ የጾም ወቅት ነው። በጾም ጊዜ አሳባችን ስለሚሰበሰብ፤ በአጠቃላይም መረጋጋት ስለሚኖረን ለማንበብ አመቺ ይሆንልናል። በተለይም ደግሞ በጾም ወቅት መንፈሳዊ እውቀትን የሚያስታጥቁ፥ በክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባርም የሚያንጹ መጻሕፍትን የምናነብ ከሆነ ከጾሙ ጋር በጥሩ ኅብረት ይሄድልናል። በዚህ የፍልሰታ ጾም ደግሞ ከነገረ ማርያም ጋር የተያያዙ መጻሕፍትን ማንበብ የበለጠ በረከት ይኖረዋል። የበረከት ጾም ያድርግልን🤲🙏 📍የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ 📍
⚡️ቀን 2 ⚡️ "እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" (፪ኛ ቆሮ. ፱፥፯) የነገውን ትውልድ በጽኑ መሠረት ላይ ለመቅረጽ የተጀመረው በጎ ሥራ ይቀጥላል!!🙌 የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤያችንን በዘላቂነትና በጥንካሬ ለመገንባት የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ በቀጥታ ስርጭት (Telegram Live chat) ሊጀምር ጥቂት ሰዓታት ብቻ…
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ pinned a photo
⚡️ቀን 2 ⚡️ "እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" (፪ኛ ቆሮ. ፱፥፯) የነገውን ትውልድ በጽኑ መሠረት ላይ ለመቅረጽ የተጀመረው በጎ ሥራ ይቀጥላል!!🙌 የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤያችንን በዘላቂነትና በጥንካሬ ለመገንባት የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ በቀጥታ ስርጭት (Telegram Live chat) ሊጀምር ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል። 📍https://t.me/+X1GFq-XUSRZmYjc0 👉የባንክ አካውንት::- 1000467682028 " 🏦 Eotc m/k/w/m/ wku wana gibi gubae እርስዎም ይሳተፉ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የዚህ ቅዱስ አገልግሎት በረከት ተካፋይ ይሁኑ!!
ሰዓታት ብቻ ቀሩት!! ከሰዓታት በኃላ የሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ዝግጅታችንን ጨርሰን እናንተን ብቻ እየጠበቅን ስለሆነ የቀጥታ ስርጭቱ ላይ ሁላችንምም እንድንገኝ ስለ እናት ግቢ ጉባኤ ባለውላታዬ ናት የምትሉ ሁሉ ተገኝታችሁ መርሐግብር ላይ እንድትሳተፉ እና የበኩላችሁን ሁሉ እድታደርጉ በግቢ ጉባኤ ስም እናሳስባለን Live chat መርሐግብሩ የት ነው የሚካሔደው?? በግቢ ጉባኤ ዋናው…
ሰዓታት ብቻ ቀሩት!! ከሰዓታት በኃላ የሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ዝግጅታችንን ጨርሰን እናንተን ብቻ እየጠበቅን ስለሆነ የቀጥታ ስርጭቱ ላይ ሁላችንምም እንድንገኝ ስለ እናት ግቢ ጉባኤ ባለውላታዬ ናት የምትሉ ሁሉ ተገኝታችሁ መርሐግብር ላይ እንድትሳተፉ እና የበኩላችሁን ሁሉ እድታደርጉ በግቢ ጉባኤ ስም እናሳስባለን Live chat መርሐግብሩ የት ነው የሚካሔደው?? በግቢ ጉባኤ ዋናው ቻናል❌ በወ/ግ/ጉ/ጉባኤ የገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ✅ 🔗 የቴሌግራም ሊንክ፦ https://t.me/+X1GFq-XUSRZmYjc0 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ ዛሬ ማታ 2:00 ላይ ላይቭ እንገናኝ!! የቅዱሳኑ አምላክ ከሁላችንም ጋር ይሁን 🤲🙏🙏
የእግዚአብሔር ፍቅር ሲገባን ያለፍንበት እና ያባከነው ጊዜ ይቆጨናል! በከንቱ ጨዋታ፣ በዘፈን፣ በጊዜያዊ ደስታና በዓለማዊ ሁካታ ውስጥ የጨረስናቸውን ሰዓታትና ቀናት ስናስባቸው 'ምነው ያን ሁሉ ጊዜ 'ለክርስቶስ በሰጠሁት፤ ምነው በሚያቃጥል ፍቅሩ ውስጥ በጊዜ በተመላለስኩ' የሚያስብ ጥልቅ ቁጭት ይፈጠራል። ወዳጆቼ ዓለም የምትሰጠን ደስታ ለጥቂት ደቂቃዎች ስሜትን የሚያሞቅ፣ ነገር ግን ከኋላው ባዶነትን የሚያስቀር ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ግን የውስጥን የተጠማው ነፍሳችንን የሚያረካ፣ እውነተኛ ሰላምን የሚሰጥና የማያልፍ ሀብት ነው። ያለፈውን ጊዜ ልንመልሰው አንችልም፤ ዛሬ ግን በጌታ ፍቅር ውስጥ አዲስ ሕይወት የመጀመር ሙሉ ዕድል በእጃችን አለ። ዛሬን ለእግዚአብሔር እንስጥ! 🙏
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ pinned a photo
✨✨ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር✨✨✨ በቅድሚያ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያቀረብን እንደሚታወቀው የግቢ ጉባኤያችን አገልግሎት ማስኬጃ አደራሽ በዝናብ አደጋ መጎዳቱ ይታወቃል እና ጥገና ለማድረግ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ መቆየታችን ይታወሳል። ስለሆነም ከላይ በልጥፍ ፎቶው ላይ በተገለጸው ቀንና በተያዘለት ሰዓት በማ|ቅ|ወልቂጤ ማዕከል ጽ/ቤት ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ግቢ ጉባኤ እንዲሁም አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና ብዙ እህትና ወንድሞቻችን በተገኙበት በonline የመጀመርያው ምዕራፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር የምናከናውን ሲሆን እስከዛ ድረስ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃውን በማሰራጨት እና እህት ወንድሞቻችን ቀጠሮ በማስያዝ የሁላችንም መሠረታዊ ክንውን ሊሆን ይገባል። በዚህ ዕለት ለቀጥታ ስርጭቱ(live challenge)ሁላችንም ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች በተለይም የግቢ ጉባኤ እና የድኅረ ግቢ ጉባኤ ልጆች መርሐግብራችንን በማመቻቸት ጥሩ internet access (Wi-Fi ወይም data በመሙላት) እኛም በመዘጋጀት እና ያልሰሙትን በማሰማት የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ ስንል በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ስለ ጽዮን(ግቢ ጉባኤ) ዝም አልልም ስለ ኢየሩሳሌምም(ግቢ ጉባኤ) ጸጥ አልልም ጽድቋ እንደ ጸዳል መዳኗም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።ትን ኢሳ 62:1 ✝✝✝ የማኅበረ ቅዱሳን ወልቂጤ ማዕከል ጽ/ቤት ፣ የወልቂጤ ዩንቨርስቲ ግቢ ጉባኤ እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ግቢ ጉባኤ በአንድነት በመተባበር ✝ ኢንኅድግ ማኅበርነ(መሰባሰባችንን አንተው) ▶ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/wku_dihre_gg 🏷ለሐሳብ አስተያየትዎ @Dihre_gg_bot ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 📍ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ📍
☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️ "እናቴ ሆይ ነፍሴ በአንቺ ዘንድ ትክበር። ስለ ቸርነትሽ እናቴ ነሽ ፤ ስለ ንግሥትነትሽም እመቤቴ ነሽ ፤ ስለ ልጅሽ የመድኃኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ ፤ እንደ ወደቅሁ እቀር ዘንድ አትርሽኝ" ✨አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ✨ 🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜
ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በነገደ መላእክት ላይ ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ ሁለተኛ ሆኖ የተሾመ አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ነው። ዲያብሎስ በመላእክት መካከል ሽብር በፈጠረ ጊዜ ❝ንቁም በበ ህላዌነ እስክ ንረክቦ ለእግዚእነ — የፈጠረንን እስክናገኝ ድረስ በያለንበት እንጽና❞ ብሎ ዓለመ መላእክትን ስላረጋጋ መልአከ ሰላም - የሰላም መልአክ ይባላል። ሊቀ መላእክትነቱን ኤጲፋንዮስ አክሲማሮስ በሚል ድርስቱ «አርባብ» ለሚባሉ መላእክት አለቃቸው ሲያደርገው፤ ነቢዩ ሄኖክ ደግሞ:- ❝በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው❞ ሲል ይገልጠዋል - (ሄኖ I፥፲፬)። ሹመቱም በየትኞቹ እንደ ሆነ ሲገልጥ:- ❝ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ገብርኤል በእባቦች ላይ በገነትና በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ነው❞ ይላል (ሄኖ ፮÷፯)። ቅዱስ ገብርኤል በእባቦች ላይ መሾሙ ከዘንዶ ጀምሮ ልዩ ልዩ የእባብ ዓይነት ሁሉ ስውን እየነደፈ ገድሎ እንዳይጨርስ በእግዚአብሔር ቸርነት ከሰው እስከ እንስሳት ለመጠበቅ ነው:: ዳግመኛም አጋንንት በክፉ መርዛቸው ውኃውን እንዳይመርዙት ጠባቂ መልአክ ሁኖ በውኃዎችም ላይ የተሾመ ነው:: «በገነት ላይ የተሾመ» የሚለውን የትርጓሜ መምህራን በገነት ባሉ ዕፀዋት ላይ የተሾመ ማለት ነው ብለው ተርጉመዋል:: «በኪሩቤል ላይ» የሚለውን ቅዱስ ሚካኤል በሱራፌል ላይ እንደ ተሾመ ቅዱስ ገብርኤልም በኪሩቤል ላይ ተሹሟል ብለው ተርጉመዋል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በግዕዝ መዝገበ ቃላቸው ❝አርባብ የኪሩቤል ስም ጌቶች፥ አለቆች ማለት ነው❞ ብለዋል። ሰሎሞንም በመኃልይ መጽሐፉ ❝ወንበር ዲበ ሳሬል ወዲበ አርባዕቱ አርባብ - በሱራፌል ላይ፥ በኪሩቤልም ላይ ተቀመጥ❞ — (መኃ ፪÷፲፯) ያለውን የትርጓሜ ሊቃውንት ሱራፌልን፣ ኪሩቤልን ይዘህ ተራዳኝ አለ:: ሳሬል ያለው ሱራፌልን ሲሆን፤ አርባብ ያለው ደግሞ ኪሩቤልን ነው፤ ሱራፌል ነገደ ሚካኤል ሲሆኑ ኪሩቤል ነገደ ገብርኤል ናቸው ብለው ተርጕመዋል፡፡ እግዚአብሔርን ፀንሳ እንደምትወልድ ለድንግል ስለ አበሠራት ገብርኤል ማለት ❝አምላክ ወሰብእ - ሰው የሆነ አምላክ የእግዚአብሔር ልጅ❞ ማለት ነው፡፡ ❝ወገጹ ለራብዓይ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ይመስል - አራተኛውም የእግዚአብሔር ልጅን ይመስላል❞ እንዳለ (ትን. ዳን ፫፥፳፭)። ናቡከደነፆር አራተኛው የእግዚአብሔር ልጅ ይመስላል ያለውን ቅዱስ ያሬድ ደግሞ:- ❝ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር ወዲበ ርእሱኒ አክሊል ጽሑፍ በትእምርተ መስቀል — ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፤ በራሱም ላይ የመስቀል ምልክት ያለበት አክሊል አለ❞ ብሎ ገልጾታል - (ድጓ ዘሚካኤል) የመልክአ ገብርኤል ደራሲም በሰላም ለዝክረ ስምከ ላይ «ገብርኤል» ስለሚለው ስም ሲገልጽ:- ❝ሰላም ለዝክረ ስምከ፥ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር — ገብርኤል ሆይ፦ ተመራምሮ ለማይደረስበት ለስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል❞ ብሏል። ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድም በድጓው፦ ❝ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላእክ ሥጋዌ ቃል ለድንግል ይስብክ — ገብርኤል ማለት ሰው የሆነ አምላክ፥ የቃል ሰው መሆንን ለድንግል ምሥራችን ይነግራት ዘንድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ አገልጋይ❞ ማለት ነው ብሏል (ድጓ ገጽ ፻፸) ዙፋኑን ከሚሸከሙ ኪሩቤል ጋር እንደ አንዱ ሆኖ እንደሚቆጠርም ❝ገብርኤል ሆይ የአንበሳ የገጸ ላሕምና የንስር ሥነ ገጽ ካላቸው ኪሩቤል ጋር የእግዚአብሔርን ዙፋን ተሸክመህ በከበረ ሰው አምሳል ሕዝቅኤል ያየህ ከኪሩቤል አንዱ አንተ ነህ❞ ብሏል፡፡ ነገር ግን እዚህ ጋ ማስተዋል ያለብን "ገብርኤል ኪሩብ ጸዋሬ ዐቢይ መንበር" ማለት እንደ ቅኔ ምሳሌያዊ ምስጋና እንጂ ቀጥታ ገብርኤል ኪሩብ ሁኖ ዙፋኑን ይሸከማል ማለትም አይደለም፡፡ ሕዝቅኤልም ያየው የበፍታ ልብስ በለበሰና የሰንፔር መታጠቂያ በታጠቀ ሰው አምሳል ሁኖ በኢየሩሳሌም ከተማ ስለሚሠራው ኃጢአት በሚያለቅሱ ሰዎች ላይ ኃጢአተኞች ከእግዚአብሔር በታዘዙ መላእክት ሲጠፉ አብረው እንዳይጠፉ በግንባራቸው ላይ ምልክት የሚያደርግበት የቀለም ቀንድ ይዞ ነው እንጂ የጌታን ዙፋን ተሸክሞ አይደለም (ሕዝ፱÷፩-፱)። ዳግመኛም አንዱ ኪሩብ ከኪሩቤል መካከል ካለው እሳት ወስዶ በእጁ ሲሰጠው አይቷል (ሕዝ ፲÷፮) ሠለስቱ ደቂቅን ከሚነድ እሳት ያወጣቸው ይኸው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው:: ቅዱስ ገብርኤል ክርስቲያኖችን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት በአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው ታማኝ መልአክም ነው፡፡ ሐምሌ ፲፱ ቀንም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ የተቀበሉበት፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ ከእቶን እሳት ያዳናቸው ዕለት ነው። የ፫ ዓመት ሕፃን የእናቱ የእምነት ጉድለት በጸሎት አራቀላት። በእጁም ይዟት ወደ ሕይወት መራት። እናቱም ❝ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ፤ ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት❞ አለችው። ከፍላቱ የተነሣ እንደነጎድጓድ የሚያስፈራ የነበረው እንደ ማለዳ ውርጭ ቀዘቀዘላቸው ከእግዚአብሔር የታዘዘ የታመነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። ❝በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል❞ — አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ =================================== ❝ሰላም ለቂርቆስ እንተ ኢፈርሆ ለነድ፥ ዘይደምፅ ከመ ነጎድጓድ፥ እንበይነ አድምዐ ሎቱ ኪዳነ ምሕረት እምወልድ፥ ኢይምጻእ ሞተ ላሕም ወላዕለ ሰብእ ብድብድ፥ ኀበ ተሐንፀ በስሙ ማኅፈድ።❞ =================================== የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት፤ የህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በረከታቸውና ቃል ኪዳናቸው በእውነት ለዘለዓለሙ ይጠብቀን። እንኳን አደረሰን። ዲ/ን ኃይለራጉኤል
видео или голосовое, без подписи
ሐምሌ 26 የማይቀርበት ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ እንደተዘጋጀ ያውቃሉ?በመናገሻ ተራራ አናት ላይ የሚገኘው ታላቁን ገዳም በጋራ ልንጎበኝ ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርተውናል። ከመንፈሳዊ ሥፍራነቱ ባሻገር የተፈጥሮ ውበት የሚታይበት፣የሀገርን ታሪክን ሰንዶ የያዘው ታላቁ የመናገሻ አምባ ማርያም ገዳምን ለመጎብኘት አሁኑኑ ፈጥነው ይመዝገቡ!! ▬ሐምሌ 26 (ደርሶ መልስ ጉዞ)▬ ✅ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ ◇ለግቢ ጉባኤ አባላት=400ብር ◇ለድኅረ ግቢ ጉባኤ አባላት=800ብር 📃ለመመዝገብ 0900189371 ሰሎሞን 0916810445 ፍቅረማርያም [ 1000727641797 Genzeb kebede & selemon ] ◆screenshot በ @bay4r ላኩልን! የግቢ ጉባኤ አባላት የሆናችሁ በተለይ ደግሞ አዲስ አበባ የምትገኙ ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ ለመሔድ ያሰባችሁ ፈጥናችሁ በመመዝገብ የበረከቱ ተካይ እንድትሆኑ በፍቅረ እግዚአብሔር እናሳስባለን🙏 ⚡️ኢንኅድግ ማኅበርነ(መሰባሰባችንን አንተው)⚡️ ▮የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ድኅረ ግቢ ጉባኤ ማኅበረ ሚካኤል @wkugg_bot ሐሳብዎን ይጻፉልን @wku_gg_media ተከታተሉን ▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬ 📍የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ📍
" ክርስቲያን መሆንህን በቃላትህ ብቻ ሳይሆን በኑሮህና በባህርይህ አስመስክር። ሰዎች የአንተን ደግነት ፣ ትህትናና ፍቅር ሲያዩ አንተን ሳይሆን በውስጥህ ያለውን ክርስቶስን ያመሰግናሉ። ያንተ ሕይወት ሰዎች የሚያነቡት ሕያው መጽሐፍ ነውና ገጾቹ በቅድስና የተሞሉ ይሁኑ። " [✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ] ✨✨ ሰናይ ዕለተ ረዕቡ ✨✨ ▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬ 📍የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ 📍
📍ምክረ አበው 📍 ንብ የምትሞተው መቼ ነው ? የብልህ ሰው መገለጫው ይኼ ነውና ኹል ጊዜ የምታመሰግኑ ኹኑ፡፡ ክፉ ደረሰባችሁን? ይህስ እናንተ ከፈቀዳችሁ ክፉ አይደለም፡፡ ኹል ጊዜ አመስግኑ፤ ክፉ የኾነባችሁም መልካም ይኾንላችኋል፡፡ ከተወደደው ኢዮብ ጋር ኾናችሁ “የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይኹን" እያላችሁ አመስግኑ ኢዮ.1:21:: እስኪ ንገሩኝ! ደረሰብኝ የምትሉት ክፉ ነገር ምንድን ነው? በሽታ ነውን? ታዲያ ይኼ'ኮ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥጋችን መዋቲና ለስቃይ የተጋለጠ ነውና፡፡ “ሀብት ንብረት ማግኘት አለብኝ" የሚል መሻት ነውን? ታዲያ ይኼ'ኮ ማግኘት የሚቻል ነው፤ ካገኙት በኋላ ግን መልሶ የሚጠፋና በዚህ ዓለም ብቻ የሚቀር ነው፡፡ ከወንድሞች የሚደርስ ሐሜትና የሐሰት ክስ ነውን? ታዲያ ተጐጂዎቹ'ኮ የሚያሙንና በሐሰት የሚከሱን ሰዎች እንጂ እኛው አይደለንም፡፡ “ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች” እንዲል ተጐጂዎቹ ይህን ኃጢአት የሚሠሩት እንጂ እኛው አይደለንም ሕዝ 18፡4)፡፡ ተጐጂው ምንም በደል ሳይኖርበት ክፉ የሚደርስበት ሰው ሳይኾን ክፉ የሚያደርሰው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ሙት ሰው ልትቈጡ አይገባም፤ ከዚያ ይልቅ ከሞት ይድን ዘንድ ልትጸልዩለት ይገባል እንጂ፡፡ ንብ የምትሞተው መቼ ነው ? ሌላውን ስትናደፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህች ፍጥረት በወንድሞቻችን ላይ ልንቈጣ እንደማይገባ ያስተምረናል፡፡ የምንቈጣ (የምንናደፍ) ከኾነ ግን ቀድመን የምንሞተው እኛው ነን፡፡ ስንቈጣቸው የጎዳናቸው ይመስለን ይኾናል፤ ነገር ግን እንደዚያች ንብ ተጐጂዎቹ እኛው ነን፡፡ ✍️ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✨✨✨ ሠናይ ምሽት ✨✨✨ ▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬ 📍የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ 📍
видео или голосовое, без подписи