ቤተ ቅዱስ ሚካኤል
Статистикаለእኛ በ አባታችን ቤት መሆን መልካም ነው ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት @Natnael_E @NAWI21 ይላኩልን 👇👇የYoutube Channel ይቀላቀላሉ👇👇 https://youtube.com/channel/UCqIww_vrxOATvuc5K_EDf1A?sub_confirmation=1
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 29
- Всего постов
- 36
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Видео
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 210
- 1/48двое суток
- 240
- 1/72трое суток
- 259
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #ነሐሴ ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን #ለአባታች_ለአቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል (በዚች ቀን አባታችን እስትፋሰ ክርስቶስ ከሰማይ የወረደውን የቊርባን ኅብስት ተቀብለው ያቀበሉበት ነው ብሎ ገድላቸው ይናገራል)ና ስጥኑፍ ከሚባል አገር ለሆኑ ለሰማዕቱ ለካህኑ #አባ_ኦር ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ጳጳስ_አባ_ጲላጦስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ✝ ✝ ✝ ❤ ስጥኑፍ ከሚባል አገር የሆነ የከበረ #ቄስ_አባ_ኦሪ፦ ይህ ቅዱስ ብዙ ርኅራኄ ያለው በሥጋው በነፍሱም ንጹሕ የሆነ ነው ብዙ ጊዜም አምላካዊ ራእይን ያያል። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት። ❤ ከዚህም በኋላ የአባ ኦሪ ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ ተሰማ ወደርሱም አስቀርቦ "ለአማልክት ዕጣን አቅርብ" አለው እርሱም "ለረከሱና ለተሠሩ አማልክት አልሠዋም" ብሎ እምቢ አለው። መኰንኑም ተቆጥቶ በብዙ ሥራ አስፈራራው ቅዱስ ኦሪም ሥቃዩን ምንም ምን አልፈራውም ጹኑ ሥቃይንም አሠቃየው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ አገር ላከው በዚያም ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃይተው በወህኒ ቤት ጣሉት። በዚያም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ በሽተኞችን ፈወሳቸው ። ዜናውም በተሰማ ጊዜ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ከየአገሩ ብዙዎች ሰዎች ወደርሱ መጥተው አዳናቸው። ይህንንም መኰንኑ ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ። ❤ ከዚህም በኋላ የከበረ ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ ገንዘው ወደ ሀገሩ ስጥኑፍም ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በማመንም ለሚመጡ በሽተኞች ሁሉ ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ ኦሪ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 9 ስንክሳር። ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 1፥12-24፣ 2ኛ ዮሐ 1፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 15፥19-25። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
видео или голосовое, без подписи
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #ነሐሴ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #ለካህኑ_ቅዱስ_አልዓዛርና_ለሚስቱ #ቅድስት_ለሰሎሜ ለሰባቱ ልጆቻቸው #አንኤም፣ #አንጦኒኃስ_ዖዝያ_አልዓዛር_አስዮና_ስሙና #መርካሎት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_አሞን ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ✝ ✝ ✝ ❤ #ካህኑ_ቅዱስ_አልዓዛርና_ሚስቱ_ሰሎሜ ሰባቱ ልጆቻቸው #አንኤም_አንጦኒኃስ_ዖዝያ_አልዓዛር፣ #አስዮና_ስሙና_መርካሎስ፦ ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት። ❤ የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው። ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኰል እንዲገባ አደረጉት። ❤ በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የእሊም ቅዱሳንም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ። ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ። ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ"። መዝ 57፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥24-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 7፥12-26። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #ነሐሴ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከሰባቱ ከዋክብትን አንዱ ለሆኑት ሁለት ድንጋዮችን በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ጣና ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ በመሔድ ታላቁ ገዳም ደጋ እስጢፋኖስን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን። ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ_ዘጣና፡- ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኵስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ "ዓቃቤ ሰዓት" እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡ የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ ❤ ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡ ❤ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ "ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ" ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ "ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት (ገንፎ)" ብለው በመናገር ምላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡ ❤ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ❤ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ ❤ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ከአቡነ ኂሩተ አምላክ ረድኤት በረከትን እግዚአብሔር አምላክ ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
видео или голосовое, без подписи
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #ነሐሴ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #ለሐዋርያት_አለቃ_ለቅዱስ_ጴጥሮስ የሕያው እግዚብሔር ልጅ ብሎ ለመሰከረበትና ሥልጣነ ክህነት (የመንግሥተ ሰማያትን ምክፈቻ ቊልፍ) ለተቀበለበት በዐልና እግዚአብሔር ለሚወድ ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ #ለቅዱስ_ናዖድ_ለዕረፍት በዐል (8ሺህ ዘመን አታሳየኝ ብሎ ሲፀልዩ 8ሺህ ሳይገባ 1500ዓ.ም ያረፉት)፣ ለራኄል ልጅ #ለቅዱስ_ዮሴፍ ልደትና ለእስክድርያ ሃያ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጢሞቴዎስ ለዕረፍት መታሰቢያ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ቀን #የሐዋርያት_አለቃ_የከበረ_ሐዋርያ_ቅዱስ_ጴጥሮስ በዓል ነው። በዚች ቀን ጌታችን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እርሱ እንደሆነ በሐዋርያት መካከል ታምኗልና። ❤ በከበረ ወንጌል እንተባለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፊሊጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል" ብሎ ጠየቃቸው እርሱ ልብን ኵላሊትን የሚመረምር ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን። ❤ ያን ጊዜ ሐዋርያት ተጠራጣሪዎች ስለነበሩ ሰለዚህ ያሰቡትን በልባቸው ያለውን እንዲናገሩ ከከተማ ውጪ አወጣቸው። ከእርሷቸውም ኤልያስ እንደሆነ የሚያስቡ አሉ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆነ የሚሉም ነበሩ። ቅዱስ ጴጥሮስም በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ "ለምን እንዲህ ታስባላችሁ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው እንጂ" አላቸው። ስዚህም የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖት በመካከላቸው ይገልጥ ዘንድና ግልጥ ሊያደርግ ወደ ውጪ አወጣቸው። ❤ እንዲሁም በጠየቃቸው ጊዜ "ኤልያስ እንደሆንክ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆንክ ሰዎች ይናገራሉ" በማለት እነርሱ የልባቸውን ተናገሩት። ቅዱስ ጴጥሮስ ግን "አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ" ብሎ በእውነት ምስክ ሆነ። ❤ ስለዚህም ጌታችን አመሰገነው የመንግሥተ ሰማያትንም ቊልፍ ሰጠው ከዚያች ቀን ወዲህ የሐዋርያት ሁሉ አለቃ ሆነ በእርሱም የሊቃነ ጳጳሳት፣ የኤጲስቆጶሳት፣ የቀሳውስትና ዲያቆናት ሹመት ተሰጠ። የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ተባለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጌቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለሁላችን ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ጢሞቴዎስ፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ለእስክንድርያ ሃያ ስድስተኛ ነው። ይህም በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን መርጦት ተጋዳይ የነበረ አባ ዲዮስቆሮስ በደሴተ ጋግራ ከዐረፈ በኋላ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ። ❤ ይህም አባት ጢሞቴዎስ ብዙ መከራ ደርሶበታል ንጉሥ መርቅያን በእስክንድርያ አገር ሌላ መናፍቅ ሊቀ ጳጳሳት ሾሞ አባት ጢሞቴዎስን አስቀድሞ አባ የዲዮስቆሮስ ተሰዶባት ወደ ነበረች ደሴተ ጋግራ አጋዘው። መርቅያንም ከሞተ በኋላ የእስክንድርያ ሰዎች ተነስተው መርቅያን የሾመውን ሊቀ ጳጳሳት ገደሉት አባ የዲዮስቆሮስ እንደ አዘዘ አባ ጢሞቴዎስ መልሰው ሾሙት። ❤ ከዚህም በኋላ የመርቅያን ልጅ ሊዮን ነገሠ ያን ጊዜ አባ ጢሞቴዎስ ሁለተኛ ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዘው በዚያም ዐሥር ዓመት ኖረ ሊዮን እስከ ሞተ ድረስ ከእርሱም ኋላ ዘይኑን ነገሰ። ያን ጊዜም አባ ጢሞቴዎስን ወደ መንበረ ሲመቱ በታላቅ ክብር መለሰው ሕዝቡንም እያስተማራቸውና እየመከራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ኖረ። ❤ በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ መንበር ሃያ ሁለት ዓመት ኖረ እግዘብሔርንም አገልግሎ ነሐሴ 7 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ በጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 7 ስንክሳር። ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ዕብል_ለጴጥሮስ_ሥዩም። ላዕለ ሐዋርያት ኄራን ካህናተ ኵሉ ዓለም። ሶበ ለክርስቶስ አምኖ ከመ ወልደ አምላክ ዮም። ኢከሠተ ለከ ይቤሎ ዘሥጋ ወደም። እንበለ አቡየ ዘሀሎ እምቅድም"። ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለዮሴፍ_ዘተሠይጠ_ወኮነ_ገብረ ወተሞቅሐ ሠለስተ ዓመተ"። ትርጉም፦ በወንድሞቹ ተሸጦ አገልጋይ ለኾነ፤ ሦስት ዓመታት ለታሰረ ለዮሴፍ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 7።
видео или голосовое, без подписи
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #ነሐሴ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታች_ለቅድስት #ድንግል_ማርያም_ለፅንሰቷ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። ✝ ✝ ✝ ❤ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእት አለቃ #ቅዱስ_ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ #ጻድቅ_ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_የድንግል_ማርያምን_ፅንሰቷን ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው። ❤ ይህም ጻድቅ ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤልም ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደረጉ ስለትን ተሳሉ። የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው "ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎች ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላቸውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች። ❤ በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት አመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ በቅዱስ ኢያቄምና በቅድስት ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ለምንጭ፦ የነሐሴ 7 ስንክሳር። ✝ ✝ ✝ ✝ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን። ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ"። መዝ 86፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 1፥1-17። ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ። ወዘመሀርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኩያት።" መዝ 93፥12-13 ወይም መዝ 84፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 9፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 2፥6-18 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥13-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የእመቤታችን የፅንሰት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
видео или голосовое, без подписи
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #ነሐሴ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን #ጌታችን_ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ላወጣላት #ከ36_ቅዱሳት_አንስት አንዷ ለሆነችው ለእናታች #ለቅድስት_መግደላዊት_ማርያም_ለዕረፍት በዐል መታሰቢያና #ከቂሳርያና_ከቀጰዶቅያ አገር ለሆነች ለከበረች #ለቅድስት_ኢየሉጣ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰበው፦ #ከአባ_ሲኖዳ_ረድእ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዊፃ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅድስት_መግደላዊት_ማርያም፦ ይችም ቅድስት ጌታችን ሰባት አጋንንትን ከእርሷ ያወጣላት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስን ተከትላ ያገለገለችው በመከራውም ጊዜ ከባልንጀሮቿ ጋራ የነበረች እስከ ቀበሩትም ድረስ ያልተለየች እናት ነች። ❤ በእሑድ ሰንበትም ገና ጨለማ ሳለ በማለዳ ማርያም ወደ መቃብር ገሥግሣ ሔደች ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተገለባብጦ መልአክም በላዩ ተቀምጦ አየችው ከእርሷም ጋራ ጓደኛዋ ማርያም አለች። መልአኩም "እናንተስ አትፍሩ ጌታ ኢየሱስን እንድትሹት አውቃለሁና ግን ከዚህ የለም እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል" አላቸው ። ለእርሷም ዳግመኛ ተገልጾላት "ሒደሽ ለወንድሞቼ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባቴታችሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ እንደማርግ ንገሪያቸው" አላት። ወደ ሐዋርያትም መጥታ የመድኃኒታችንን መነሣቱን እንዳየችውና ንገሪ እንዳላትም አበሠረቻቸው። ❤ ከዕርገቱም በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለቻቸው ኖረች። በኃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቼ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ አለ ብሎ ኢዩኤል ትንቢት እንደ ተናገረ ያንን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ተቀብላለች። ❤ ከዚህም በኋላ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን ሰበከች ብዙዎች ሴቶችንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት መልሳ አስገባቻቸው። ሴቶችን ስለ ማስተማርም ሐዋርያት ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት ከአይሁድም በመገረፍ በመጐሳቈል ብዙ መከራ ደረሰባት። ተጋድሎዋንም ፈጽማ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ። እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በቅድስት መግደላዊት ማርያም በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ከቂሳርያና_ከቀጰዶቅያ አገር የሆነች #ቅድስት_ኢየሉጣ፦ ይቺም ቅድስት ከወላጆቿ ብዙ ገንዘብ ወረሰች ከታጋዮችንም አንዱ በግፍ ተነስቶ ጥሪቷን ሁሉ ወንዶች ሴቶች ባሮቿን ለዳኛ መማለጃ በመስጠት ነጠቃት። ❤ ይህም ዐመፀኛ እንደምትከሰውና ሐሰቱንም እንደምትገልጥበት በአወቀ ጊዜ ወደ ቂሳርያው ገዢ ሒዶ ክርስቲያን እንደ ሆነች ወነጀላት። በልቧም እንዲህ አለች "የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ አይደለምን እነሆ እርሱን ነጠቁኝ የሰማይ ድልብን ገንዘብ ካደረግሁ ማንም ከእኔ ነጥቆ ሊወስድብኝ አይችልም"። ❤ ያን ጊዜም ወደ መኰንኑ ቀረበች በፊቱም ቁማ እንዲህ አለች "እኔ ክርስቲያዊት ነኝ ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ"። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ወደ እሳትም ውስጥ እንዲወረውሩዋት አዘዘ ነፍሷንም ነሐሴ 6 ቀን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች። ❤ ነገር ግን እሳቱ አልነካትም ምንም ምን አላቃጠላትም ከውኃ ውስጥ እንደሚወጣም ከእሳት ውስጥ አወጧት። ስለ ገንዘቧና ስለ ጥሪቷም የማያልፍ የሰማይ መንግሥትን ወረሰች። ቅዱስ ባስልዮስም ብዙ ወድሷታል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን። ✝ ✝ ✝ ❤ #የአባ_ሲኖዳ_ረድእ_ቅዱስ_አባ_ዊፃ፦ እርሱም ከእግዚአብሔር ብዙ ምሥጢራትን የሰማ የአባ ሲኖዳንም ገድል እንደ አየና እደንሰማ የጻፈ ነው። መልካም አካሔዱንም እንዴት እንደፈጸመ ከእርሱ ከአባ ሲኖዳ ሰማ እግዚአብሔርም አገልግሎ ነሐሴ 6 ቀን በሰላም ዐረፈ። እግዚአብሔር በአባ ዊፃ ጸሎቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 6 ስንክሳር። ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለኢየሉጣ_እንበይነ_ምግባር_ሠናይ። በውስተ እቶን ዘእብዋእ በውዴተ ብእሲ እኩይ። እንዘ ኢሀሎ ላዕሌሃ አሠረ ዋዕይ። ወጽአት እምእሳት ከመ ዘወጽአ እማይ። አምሳለ ፍቱን ወርቅ ወብሩር ጽሩይ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ_ነሐሴ 6። ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ። ወለገጽኪ ይትመሀለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሴቦን"። መዝ 44፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥10-22፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማር 16፥9-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
видео или голосовое, без подписи
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #ነሐሴ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ዓሣ ከሰማይ ለሚዘንብላቸው ለመናኔ መንግሥት #አቡነ_ኢዮስያስ_ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን። ✝ ✝ ✝ ❤ #መናኔ_መንግሥት_አቡነ_ኢዮስያስ፡- ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የንጉሥ ዓምደ ጽዮን ልጅ ናቸው፡፡ ጥር 6 ቀን ሲወለዱ ቅዱሳን መላእክት ከበዋቸው ታይተዋል፡፡የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በዓለም ነግሠው መኖርን ንቀው በመመነን በመጀመሪያ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ገቡ፡፡ አቡነ ኢዮስያስ በሐይቅ ገዳም ለ14 ዓመታት በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በዚያም ብሉይንና ሐዲስን፣ መጽሐፈ መነኰሳትንና መጽሐፈ ሊቃውንትን አጠናቀው ተምረዋል፡፡ በኋላም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ትግራይ ደብረ በንኰል ገዳም ሄዱ፡፡ በደብረ በንኰልም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በታላቁ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ መነኰሱ፡፡ ቆብ የተቀበሉት ግን ከአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡ ❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ሰባት ዓመት ከእሳቸው ጋር ካቆዩአቸው በኋላ አቡነ ኢዮስያስን ወንጌልን ዞረው እንዲሰብኩና ገዳም እንዲገድሙ በማዘዝ መርቀው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አቡነ ኢዮስያስም ወደ አዱዋ አውራጃ ዛሬ በስማቸው ወደተጠራው ገዳም ሄደው በቦታው ላይ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ገዳሙንም ከገደሙት በኋላ በርካታ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ ያፈለቁት ጠበል በፈዋሽነቱ የታወቀ ነው፡፡ በየዓመቱ በዕረፍታቸው ዕለት ነሐሴ 6 ቀን ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ ይዘንባል፡፡ ይህ አሁንም ድረስ በየዓመቱ ነሐሴ 6 ቀን በግልጽ እየታየ ይገኛል፡፡ ❤ አቡነ ኢዮስያስን ከሃዲያን የሆኑ አረማውያን ቢያስቸግሯቸው ጻድቁም በጸሎት ቢያመለክቱ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ነጭ የንብ መንጋ መጥቶ አረማውያኑን አንጥፍቶላቸዋል፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው አራት ሙታንን በአንድ ጊዜ ከሞት ያስነሡ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በገዳማቸው ውስጥ በበዓላቸው ቀን ገድላቸው ሲነበብ አጋንንት ከሰው ልቡና እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉ፡፡ ❤ ጻድቁን እንደ ረድእ ሆኖ የሚያገለግላቸው አንበሳ ነበራቸው፡፡ ወደ ገዳማቸው መጥቶ መካነ ዐፅማቸውን የተሳለመውን እስከ 14 ትውልድ ድረስ እንደሚምርላቸው ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ልጁን በስማቸው የሰየመ ቢኖር የሰይጣንን ፊት ፈጽሞ እንደማያይ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከአቡነ ኢዮስያስ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
በካንሰር ህመም ምክንያት ሙሉ የግራ እጇን ላጣችው ለኤልሮኢ እጃችንን እንዘርጋላት። ወጣት ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመት የሜኔጅመንት ተማሪ የነበረች ሲሆን፣ በደረሰባት ድንገተኛ የአጥንት ካንሰር (Bone Cancer) በሽታ ምክንያት ትምህርቷን ለማቋረጥ ተገዳለች። ካንሰሩ በተገኘበት ወቅት በነበረው ህክምና የግራ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲቆረጥ ቢደረግም፣ ኤልሮይ ግን ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን ስትከታተል ቆይታለች። ሆኖም ግን፣ አሁን ላይ በሽታው ወደ ሳንባዋ በመዛመቱና የፅኑ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአዲስ አበባ በሚገኘው Heal Venture Medical and Surgical Center በፅኑ ህክምና ክፍል (ICU) ውስጥ ነች። የሆስፒታል ውሎዋ ብቻ በቀን እስከ 50,000 ብር የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ወጪ ለቤተሰቧ ብቻውን ለመሸፈን ከአቅም በላይ ሆኗል። ወጣት ኤልሮይ ወደ የቀደመ ህይወቷና ህልሟ ለመመለስ የሁላችንንም የርህራሄና የደግነት እጅ ትሻለች። የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች : ራሔል አረጋይ 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000487578828 2. ቴሌብር (Telebirr): 0911179293 3. አዋሽ ባንክ (Awash Bank): 013471629151800 ለበለጠ መረጃ እና በአካል ተገኝቶ ለመጠየቅ፦ 0938859859 0911179293 አንድ ትንሽ እርዳታ ለኤልሮኢ ቅዱስ ትልቅ ተስፋ ነው!" በገንዘብ መርዳት ባንችል እንኳ፣ ይህንን መልዕክት SHARE በማድረግ ለብዙዎች እንዲደርስ ማድረግ ትልቅ የህይወት አድን አስተዋፅኦ አለው። አንድ ልብ ሆነን ኤልሮኢ ተስፋ እንሁን! ፈጣሪ ኤልሮኢን ይማርልን፣ ደግነታችሁንም ይባርክ! Via እድል 🙏🙏🙏 ጉርሻ page
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи