ʏɪʟɪᴋᴀʟ ᴏʀᴛʜᴏᴅᴏx
Статистика"የእግዚአብሔር ቃል ለነፍስ ምግብ ነው!" በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የጠበቁ፡- 📖 አጫጭር የቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት 🕊 ዕለታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክቶች 🎶 ነፍስን የሚያርሱ መዝሙራት ይቀርባሉ። እውነትን እንወቅ፤ በእውነት እንኑር! 👇 ይቀላቀሉን 👇 @YilikalOrthodox
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 65
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 190
- 1/48двое суток
- 217
- 1/72трое суток
- 234
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#በጾመ_ፍልሰታ_በሥራ_ምክንያት_ቅዳሴ_ማስቀደስ_አልቻልኩም_ምን_ላድርግ ? እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ብዙዎች የሚናፍቋትን የእመቤታችን ክብር የምትገልጠውን ጾመ ፍልሰታን መጾም ከጀመርን 8ተኛ ቀናችን ላይ ደርሰናል ያም ማለት ግማሽ ብለናል ማለት ነው ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን። በዚህ የጾም ሳምንት አብዛኛው ክርስቲያን ከህጻናት ጀምሮ በቤተክርስቲያን በመገኝት የውዳሴ ማርያም ትርኋሜን በማዳመጥ እንዲሁም ቅዳሴ በማስቀደስ በሱባኤ በጸሎት እያሳለፉ ይገኛሉ። ነገር ግን እኛስ በሥራና በተለያዩ ምክንያቶች ማስቀደስ አልቻልንም ምን በማድረግ ከእመቤታችን በረከት እንሳተፍ ካላችሁኝ መልሱን እንሆ! በቤተክርስቲያይ ሙሉ ቀን በሚባል ደረጃ ሌሊት በኪዳን ፣ ቀን በውዳሴ ማርያም ትርኋሜ ፣ ከሰዓት በቅዳሴ ፣ ማታ በምሕላና ጉባኤ እያሳለፍን ነው ስለዚህ እንድም ክርስቲያን ከበረከቱ ላለመሳተፍ ምንም ምክንያት ሊያቀርብ አይገባም። ስለዚህ ቀኑን ሙሉ በሥራ የምንጠመድ ክርስቲያኖች ሌሊት በመነሳት ኪዳን በማድረስ ጠዋት ወደ ሥራ መኋዝ ወይም ማታ ከሥራ መልስ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ምሕላ እና ጉባኤ መሳተፍ እንዲሁም ወደ ቤት ከተመለስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በማድረስ የቀሩትን 8 ቀናት ያለ ቸልተኝነትና ያለመዘናጋት እናሳልፍ አደራ እስከ አሁን ከምኑም ያልተገኛችሁ ክርስቲያኖች ስለ እመቤታችን ፍቅር ስትሉ ወይ ከሌሊቱ ወይ ከማታው ተሳተፉ! አደራ። [ ✍ ወልደ ሚካኤል ] ከተወደደች እመቤታችን ረድኤት፤ በረከት፤ ፍቅር አይለየን! @YilikalOrthodox
"As soon as the Virgin Mary heard that Elizabeth was with child in her old age, she travelled the mountains of Judea to visit Elizabeth. She did not say, 'I am the mother of the Lord; Elizabeth should be the one to visit me'- but no- 'I will go to her,' and not only that but she remained to serve Elizabeth for the three months till she gave birth to John" + Pope Shenouda + @YilikalOrthodox
እናንተ የክርስቲያን ወገኖች ሆይ፤ በዚህች ቀን እንደተሰበሰባችሁ እንዲሁ ክብርት በምትሆን በደብረ ጽዮንና በሰማይ ባላች ነጻ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ይሰብስባችሁ። ይህንም የማርያምን የምስጋናዋን ቃል እንደሰማችሁ የሕፃናትን የምስጋና ቃል ይልቁንም ከጣዕሙ ብዛት የተነሣ አጥንትን የሚያለመልም የመላእክትንም ምስጋና እንዲሁ ያሰማችሁ ። የእሳት ነበልባል ድንኳኖች ወደ ተተከሉበት፤ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳለበት ያገባችሁ! [📔ቅዳሴ ማርያም] ከተወደደች እመቤታችን ረድኤት፤ በረከት፤ ፍቅር አይለየን!!! መልካም የጌታ ቀን! @YilikalOrthodox
እንኳን ለጾመ ማርያም አደረሳችሁ እንደምታውቁት በዚህ ጾም ሌሊቱን ሙሉ ሰአታት በተባለው የቅዱስ አባ ጊዎርጊስ ዘጋስጫ ምስጋና እግዚአብሔርን እያመሰገንን እናድራለን ። ሰአታቱ ብዙ ቦታ ከማታ 4 ሰአት እስከ ጠዋት 11 ነው በዋነኝነት ካህናት እና ዲያቆናት ናቸው የሚቆሙት ፤ ሲነጋ ደግሞ መሪጌቶች ስብሐተ ነግህ ያደርሳሉ ፤ ከዛ ረፈድ ሲል የመጽሐፍ መምህራን ውዳሴ ማርያም ይተረጉማሉ ... ከዛ ወደ ቅዳሴ እና በተቻለን አቅም ሌሊት በሰአታት ቀን በቅዳሴ ለመትጋት እንሞክር ። ከተወደደች እመቤታችን ረድኤት፤ በረከት፤ ፍቅር አይለየን ። © አምላከ ብርሃን @YilikalOrthodox
ምክረ አሃው : የወንድም ምክር ጸሎት መጸለይ ከበደኝ ፣ እንደምንም ብዬ ለጸሎት ስቆም መመሰጥ አልቻልኩም ፣ ሃሳቤ ብትንትን ይላል እና ወዘተ 😁 ለምንል ሰዎች ወልደ አማኑኤል የተባለ ወዳጄ እንዲህ ብሏል :- 🗣 “ Well እንግዲህ input ታችንን ማስተካከል አለብን.. ለምሳሌ ቀኑን ሙሉ Tiktok scroll እያደረግን ( ከአለማዊ እስከ አጫጭር መንፈሳዊ ጉዳዮችን ) አእምሮችን ውስጥ እያጨቅን ውለን ማታ በተረጋጋ መንፈስ ለጸሎት መቆም ከባድ ነው። ስለዚህ ወደ ውስጥ የሚገባው ነገር የሚወጣውን የሚወስን ስለሆነ Digital ፋስቲንግ (ጾም ) ያስፈልገናል። ዓይናችን እና ጆሮአችን የነፍሳችን መስኮቶች ናቸው። ቢያንስ ለጸሎት ከመቆም በፊት ከአንድ ወይም ከሁለት ሰዓት አስቀድሞ ስልካችንን ዘግተን አእምሮአችንን ማሳረፍ አለብን። መንፈሳዊ መመሰጥ (Concentration) የሚጀምረው ለጸሎት ስንቆም ሳይሆን፣ ቀኑን ሙሉ አእምሯችንን ከምንመግበው ምግብ ነው። ጤናማ Input ካለን፣ ጤናማ Output ( ጸሎት )ይኖረናልና። ” እውነቱን ነው....ቃለ ሕይወት ያሰማልን! መልካም የጌታ ቀን! 🤍 @YilikalOrthodox
“እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና 🥹 እኛ እንወደዋለን።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥19 @YilikalOrthodox
“እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና 🥹 እኛ እንወደዋለን።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥19 @YilikalOrthodox
+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++ ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው « ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ » እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም « ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ » ላሏቸው አባ ተጠምቀ « እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል? ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር » ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው « ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ » እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም😔😢። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ😣😢። ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ7 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ « ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው» ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ « ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን » ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ። አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ። የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!! (*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።) ✍ ዲያቆን አቤል ካሳሁን ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም የጻፈው @YilikalOrthodox
እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል አደረሳችሁ!!! በእግዚአብሔር ፊት በባለሟልነት የሚቆም መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሁላችንንም በያለንበት ይጠብቀን! ምልጃው አይለየን! @YilikalOrhodox
ቀሲስ ወንድወሰን በላይ Wondwosen Belay – ባንተ ልኑር ቸር አባቴ bante len...
በፍጹም ትህትና የተሞሉ ጸሎቶች 1. የመቶ አለቃው ጸሎት “ጌታ ሆይ፥ በቤቴ ጣራ ከታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል።” - ማቴዎስ 8፥8 2. የቀራጩ ጸሎት “ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን፦ አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።” - ሉቃስ 18፥13 3. በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ጸሎት "ወንበዴውም ኢየሱስን፦ ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።" - ሉቃስ 23፥42 ይርዳን! @YilikalOrthodox
⁴ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። ⁵ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ⁶ በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥…
⁴ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። ⁵ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ⁶ በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል። ⁷ በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ⁸ ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። 📔ዮሐ 15፥4-8 በ'ርሱ እንድንኖር እርሱ ይርዳን! @YilikalOrthodox
ኪዳንሽ ነው መበርቻዬ | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ @YilikalOrthodox
"... ይሁበነ ዝናመ በጊዜሁ ፤ ወይሁበነ እክለ በረከት ፤ ያርኁ ክረምተ ይገብር ምህረተ ፤ ከሢቶ አይኖ ሰፊሖ የማኖ ይፌኑ ሣህሎ ... " መዝሙር ዘቅዱስ ያሬድ ❤ "... በጊዜው ዝናምን ይሰጠናል ፤ የበረከት ምግብን ይሰጠናል ፤ ክረምትን ይከፍታል ምህረትን ያደርጋል ፤ የቸርነት አይኑን ከፍቶ የበረከት እጁን ዘርግቶ ምህረቱን ይልክልናል ..." @amlake_birhan
1ኛ ጴጥሮስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። ²⁵ እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል። ✍ ቅዱስ ሐዋርያ ጴጥሮስ @𝗬𝗶𝗹𝗶𝗸𝗮𝗹𝗢𝗿𝘁𝗵𝗼𝗱𝗼𝘅
አቤቱ ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ መዓትህ የራቀ ምሕረትህም እውነትህም የበዛ። ✨ [ መዝ 86፥ 15] ✨ @YilikalOrthodox
የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር “ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነው ለሁሉ ” 🗣 ዘማሪ ዲያቆን ዮሐንስ አየለ መልካም የጌታ ቀን! @YilikalOrthodox
የኔ ጌታ ፍቅሩ ችሎኝ ሰፊው ክንዱ አሻገረኝ ለውለታው ከእንባ በላይ የሚያረካው ምን ቃል አለኝ! 🥰 ያየህብኝን ያላሳየህብኝ 🤍🙏🏻 @YilikalOrthodox
እሱ ስለኛ ሲል ብዙ መከራ ተቀብሏል🩶። እኛስ? 🤔 🗣 መምህር ያረጋል አበጋዝ @𝗬𝗶𝗹𝗶𝗸𝗮𝗹𝗢𝗿𝘁𝗵𝗼𝗱𝗼𝘅