ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን
Статистикаእኛስ በትዳር ከእግዚአብሔር ጋር እንተባበራለን። ትንሿ ቤተክርስቲያንን እናይ፣እናውቅ እና እንወድ ዘንድ እንማማራለን። @LovableFamily
- Последний пост
- 23 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 47
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 278
- 1/48двое суток
- 1 464
- 1/72трое суток
- 1 579
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። መጽሐፈ መክብብ 4፥9 #ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TinshuaBetechrstian
https://www.youtube.com/live/yGdscZuI3SI?si=9lRNZcOHKqhSUCRF
🔻ሁሌም አስታውስ. 💠ሚስትህ አንተን ለመውደድ የመረጠች ብቸኛ ሰው ናት። 💠እናትህ የምትወድህ አንተ ልጇ ስለሆንክ ነው፡፡ 💠 ወንድሞችህና እህቶችህ ይወዱሃል ምክንያቱም አንተ ወንድማቸው ስለሆንህ 💠ልጆችህ አንተ አባታቸው ስለሆንክ ይወዱሃል፡፡ 🛑ሚስትህ ግን – ያለምንም ግዴታ ትወድህ ነበር። 🛑ሌላ ማንም ባያደርግህም በአንተ ታምን ነበር። እሷ ከጎንህ የቆመችው ግዴታ ስላለባት ሳይሆን ስለፈለገች ነው፡፡ 🏵️በዙሪያህ ያለውን ዓለም ለመገንባት የመረጠችውን ሴት ፈጽሞ አትርሳ፡፡ አክብራት፣ ጠብቃት። ምክንያቱም የሴት ፍቅር፣ ንፁህና ታማኝ ሲሆን፣ ወንድ ሊኖረው የሚችለው ጠንካራ መሰረት ነው:: 👇👇👇👇👇👇 #ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን @TnshuaBetechrstian
ቤተሰብ ምንም #ዴሞክራሲያዊ የሆነ የአኗኗር ፈለግን የሚከተል ቢሆንም( በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ መታዘዝን የሚከተል ቢሆንም) ወይም ሁለቱም ባለስልጣናት ቢሆኑም (እኩል ክብር ያላቸው ቢሆኑም) ቤተሰብን የመምራት ኃላፊነትን #የግድ #አንዱ #አካል #መያዝ ይኖርበታል።ያለበዚያ በቤተሰቡ መካከል #ሰላም ሊሰፍን አይችልም።ይህ በአካል ላይ የሚታየው የአገዛዝ ሥርዓት ሁሉም የሚቀበለው ነው።ይበልጡኑ #ባሎች #መንፈሳውያን በሆኑ መጠን የቤቱም ሰላም እንዲሁ ተጠብቆ ሊኖር ይችላል። 👇👇👇👇👇👇 #ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን @TnshuaBetechrstian
የፍቅር ዳርቻው እስከምን ድረስ ነው? ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንዴት እንደወደዳት መረዳት ትፈልጋለህን? አንተም ሚስትህን #ምክንያቶችን ሳታበዛ እንዲሁ #ውደዳት።የነፍሷን ድኅነት ብቻ ፈልግ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ማለትም እኛን ሲወደን ከእኛ በጎነት የተነሳ አልነበረም፤ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊም " እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን" ብሎ እንደተናገረው ፤ሊቁ ደግሞ ምን ብሎ እንደሚመክረን እንስማ።" ከባሪያ ጋር እንደምትኖር ከሚስት ጋር መኖር ለባል የሚፈጥርለት ደስታ ምን አይነት ደስታ ነው?" ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሚስትህ ለአንተ እንደምትገዛ ሚስትህ ለአንተ እንድትገዛልህ ትፈልጋለህ?ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን እንዳደረገላት አንተም እንዲሁ ለሚስትህ አድርግላት።ሕይዎትህን ስለ እርሷ አሳልፈህ መስጠት ካለብህ ስለርሷ ሕይዎትህን አሳልፈህ ስጥ፤መከራም መቀበል ካለብህ መከራን ለመቀበል አትሰቀቅ። #የትዳር #አንድምታ #ቅዱስ #ዮሐንስ #አፈወርቅ እንዳስተማረው። #ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TnshuaBetechrstian
እመቤታችን የተወለደችበት መታሰቢያ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ከሞቀው ቤታችን ወጥተን ድንኳን በመጣል ወደ ውጭ እንወጣለን የሚያሳዝነው ነገር ግን ድንኳኖቻችን በዝማሬ መድመቅ ሲገባቸው እኛ ግን የልደቷን ባለቤት በማይመጥን መልኩ የዘፈን ዳንኪራ ቦታ እናደርጋቸዋለን። አካባቢያችሁን ቃኝታችሁ እስቲ ንገሩኝ ተወዳጆች ተሳስቻለሁ ? በየመንደሩ በዚህ የተነሳ ድኅነት የሚገኝባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እና ክብሯ ይጎድፋል። በዓላቶቻችን ሁሉ የጌታን ክብር የመግለጥ አባቶቻችን እስከ ሙሉ መንፈሳዊ ሞገሳቸው ቢሰጡንም እኛ ግን የኃጢአት እና የዓለማዊነት ፍላጎታችን መፈጸሚያ የርኩሰት ሜዳ እያደረግናቸው መሆኑ ሲታይ ያሳዝናል። በመምህር አቤል ተፈራ @TnshuaBetechrstian
ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: " ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) " የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው❤❤ @TnshuaBetechrstian
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ። ወደ ገላትያ 4፥7 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Tnshuabetechrstian
ሞትን ይገድለው ዘንድ ሞተ ። የሞቱትን ያድናቸው ዘንድ ሞተ ። የተቀበሩት ያስነሳቸው ዘንድ ተቀበረ ። አሁን ግን ከመቃብር ተነሥቷል፤መቃብር አልቻለውምና። (ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ) እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ጌታ በሚወደው መልኩ በዓሉን እናክብር የኔ ውዶች መልካም በዓል🙏። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TnshuaBetechrstian
የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘን የድልና የሰላም ዝማሬ እያዜምን 'ሆሳዕና በአርያም' የምንልበት ታላቅ ቀን ደረሰ። ይህ በዓል ላንተ/ላንቺ የድል የከፍታና የአዲስ ተስፋ መጀመሪያ ይሁንላችሁ። ልባችሁ እንደ ዘንባባው የለመለመ መንገዳችሁም በብርሃን የተሞላ እንዲሆን እመኛለሁ። እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🌿✨ @TnshuaBetechrstian
እመ አምላክ የመረቀችው ኒቆዲሞስ! ሀብት የሞላለት ነው። እውቀቱም ከጥቂት ልሂቃን መሐል። የሚያዝዝ፣ የሚናዝዝበት ሥልጣንም አለው። ቀኑ በሥራ የተያዘ ነው። ተጨማሪ ትምህርት ላለመማር በቂ ሰበብ አለው። ግን አላሳበበም። “ጊዜ የለኝም” አላለም። ይልቁንም በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በዘመኑ እውነተኛ መምህር ፍለጋ ሄደ። ይህ የእውቀት ገበሬ እውነተኛውን የባሕርይ መምህር በሌሊት አገኘው። አድናቆቱንም ገለጸለት። እውነተኛው መምህርም ልብ የሚመረምር ነውና አድናቆቱን ትቶ ስለጎደለው ነገረው። የአይሁድ መምህር ኾኖ ሳለ እንደገና ካልተወለደ በቀር ከእግዚአብሔር መንግሥት ቦታ እንደሌለው ነገረው። ይህ ነገር ረቀቀበት። “ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?” እያለ እየደጋገመ ጠየቀ። በመጨረሻም ትምህርቱ ሕይወቱን ለወጠውና ጌታችንን እስከ መስቀል፣ እስከ መቃብርም ድረስ ተከተለው። ከቅዱስ ዮሐንስ በቀር ሐዋርያቱ በሸሹበት በዚያ የመከራ ቀን መለኮት ያልተለየውን ቅዱስ ሥጋውን ከአይሁድ የሸንጎ አለቃው ዮሴፍ ጋር ኾኖ ከጲላጦስ ተቀብሎ፣ ሽቱ ቀብቶ፣ ገንዞ፣ ወደ መቃብር ወሰደ። እመ አምላክም እንዲህ ስትል ከዮሴፍ ጋር መርቃዋለች፤ ዮሴፍ ኾይ የሰማይ ጠል ምግብህ ይኹን፤ ኒቆዲሞስ ኾይ አየር ያለምልምህ፤ እናንተ ከመስቀል ላይ አውርዳችሁ የቀበራችሁት ለልጄ በጎነትን አድርጋችኋልና። ግብረ ሕማማት ገጽ 993። እንኳን ለኒቆዲሞስ አደረሰን! 🔻ይቀላቀሉን👇 @burukie2014
ወዳንቺ ከመምጣት! የልቤ መደደር፣ የኃጢአቴ ቁልል፣ የምእመኑ ሽሙጥ፣ የካህናቱ ጥል፣ ከኹሉም አቅጣጫ ቢደፈጥጡኝም፣ ወደ አንቺ ከመምጣት አይከለክሉኝም! ልብን የሚያሳሳ፣ ኃጢአትን የሚገድል፣ ሽሙጥን የሚያርቅ፣ ራሱን የሚያድል፣ እስትንፋስ ሰጭ ልጅሽ ያወጣኛል በድል! 🔻ይቀላቀሉን👇 @burukie2014
የመገፋት ፍሬ! የሚፋቀሩ ባልና ሚስት ናቸው። ክፉዎች በተንኮል ባልዋለችበት ሚስትን ከባሏ ዘንድ ከሰሷት። ባልም አመናቸው። ሚስቱንም በባሕር መካከል በሳጥን ቆልፎ ጣላት። የእግዚአብሔር መላእክት በተአምር አውጥተው ሀገረ ሮሐ አደረሷት። የሐገሪቱ ንጉሥም ተቀብሎ ለ6 ወራት ተንከበክቦ አኖራት። ቀጥሎም በጋብቻ ወንድ ልጅን ወለዱ። ይህቺ ሴት በተንኮል ስትካድና ስትጠላ ወደ ባሕርም ስትጣል የተመለከተላት አንድም ሰው አልነበረም። አምላኳ ግን አልተዋትም። የንጉሥ ሚስት አደረጋት። ወንድ ልጅንም ወለደች። አድጎም በአባቱ ቦታ ነገሠ። እርሷም ከጥልቁ ያወጣትን አልረሳችውም። በጸሎት ዘወትር በሙሉ ልቧ አገለገለችው። በዚህ ጊዜ ያ ተልኮ ያዳናት መልአክ ደግሞ መጣ። በኢየሩሳሌም የተቀበረውን መስቀሉንም መርምራ ፈልጋ እንድታወጣ፣ አብያተ ክርስቲያናትንም እንድታንጽ የእግዚአብሔር ፈቃዱ መኾኑን አሳወቃት። ለልጇም ነገረችው። ሠራዊት አዝዞ ላካት። በማይመረመር ጥበቡ ከ300 ዓመታት በላይ በጎልጎታ ተራራ ላይ የቆሻሻ መከመሪያ ኾኖ የነበረውን ቅዱሱን መስቀል አገኘችው፤ ፈተነችውም። ሙትን አስነሣ። እግዚአብሔር የመገፋቷን ፍሬ ሰጣት። ፍሬውም ለትውልዶች የሚተርፍ በረከትን አመጣ። እግዚአብሔር ጥበቡ ረቂቅ ነው፤ አይመረመርም። የዚህችን ሴት ግፍ ወደ ዘለዓለማዊ ደስታ ቀየረ! ደስታውም ትውልዶችን ተሸጋግሮ ከኛ ደረሰ። ደግሞም ይህን ክቡር፣ ኃያል፣ ቅዱስ መድኃኒት (መስቀሉን) ግፍ ሲሠራባት ለኖረችው፣ እየተሠራባትም ላለችው ሴት (ኢትዮጵያ) ሰጣት። እንኳን መስቀሉ ለተገኘበት በዓል አደረሰን! በመከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፥ ይጐስቍሉም፤ በእኔ ላይ ነገርን የሚያበዙ እፍረትንና ጕስቍልናን ይልበሱ። (መዝ 34፥ 26) ገጻችንን ይወዳጁ 👇👇👇 @burukie2014
ክፉ ትምህርትን እንዳትማርብህ ባጠገብህ የምትተኛ ሚስትህን አታስቀናት። መጽሐፈ ሲራክ 9፥1 @TnshuaBetechrstian
“ነፍሴ ሆይ፣ ምሕረትስ ቅርብ ናት። ባለመድኃኒትም የራቀ አይደለም። አንቺ ወደእርሱ ትሄጅ ዘንድ የምትመኪበት፣ መድኃኒትሽን ተስፋ የምታደርጊበትስ አለን?» ገድለ ማርያም እንተ እፍረት ም. 2፥ 20።
"ከልጆቼ ጋር ስንጫዎት ሁሌም የምነግራቸዉ"የበላይነትም የበታችነትም አይሰማችሁ፤የበላይነት ሲሰማችሁ ሌሎችን ትጎዳላችሁ ፤ የበታችነት ሲሰማችሁ ራሳችሁን ትጎዳላችሁ። So, live your own version of life." የአንድ እናት ግሩም ምክር 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TnshuaBetechrstian
#ባለፀጋ #ስትሆን መዝሙር 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TinshuaBetechrstian
ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና። እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም። የዮሐንስ ራዕይ 3፥1-3 #ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TnshuaBetechrstian
☝️እየገባችሁ ተማሩ Subscribe እና like አድርጉ🙏።
https://youtu.be/zDAwBjx1-iU?si=oUN0jGPdFhGVxwT-