ቅድስት ፌብሮኒያ
Статистикаይህ ቻናል ስለ ሕይወታችን የምንወያይበት ሁላችንም ሀሳብና አስተያየት የምናካፍልበት ነው ፤ እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ይለቀቁበታል።
- Последний пост
- 4 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://www.youtube.com/live/yGdscZuI3SI?si=9lRNZcOHKqhSUCRF
🔻ሁሌም አስታውስ. 💠ሚስትህ አንተን ለመውደድ የመረጠች ብቸኛ ሰው ናት። 💠እናትህ የምትወድህ አንተ ልጇ ስለሆንክ ነው፡፡ 💠 ወንድሞችህና እህቶችህ ይወዱሃል ምክንያቱም አንተ ወንድማቸው ስለሆንህ 💠ልጆችህ አንተ አባታቸው ስለሆንክ ይወዱሃል፡፡ 🛑ሚስትህ ግን – ያለምንም ግዴታ ትወድህ ነበር። 🛑ሌላ ማንም ባያደርግህም በአንተ ታምን ነበር። እሷ ከጎንህ የቆመችው ግዴታ ስላለባት ሳይሆን ስለፈለገች ነው፡፡ 🏵️በዙሪያህ ያለውን ዓለም ለመገንባት የመረጠችውን ሴት ፈጽሞ አትርሳ፡፡ አክብራት፣ ጠብቃት። ምክንያቱም የሴት ፍቅር፣ ንፁህና ታማኝ ሲሆን፣ ወንድ ሊኖረው የሚችለው ጠንካራ መሰረት ነው:: 👇👇👇👇👇👇 #ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን @TnshuaBetechrstian
እመቤታችን የተወለደችበት መታሰቢያ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ከሞቀው ቤታችን ወጥተን ድንኳን በመጣል ወደ ውጭ እንወጣለን የሚያሳዝነው ነገር ግን ድንኳኖቻችን በዝማሬ መድመቅ ሲገባቸው እኛ ግን የልደቷን ባለቤት በማይመጥን መልኩ የዘፈን ዳንኪራ ቦታ እናደርጋቸዋለን። አካባቢያችሁን ቃኝታችሁ እስቲ ንገሩኝ ተወዳጆች ተሳስቻለሁ ? በየመንደሩ በዚህ የተነሳ ድኅነት የሚገኝባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እና ክብሯ ይጎድፋል። በዓላቶቻችን ሁሉ የጌታን ክብር የመግለጥ አባቶቻችን እስከ ሙሉ መንፈሳዊ ሞገሳቸው ቢሰጡንም እኛ ግን የኃጢአት እና የዓለማዊነት ፍላጎታችን መፈጸሚያ የርኩሰት ሜዳ እያደረግናቸው መሆኑ ሲታይ ያሳዝናል። በመምህር አቤል ተፈራ @Slehiwetwe
🌿 በመስቀል ላይም ተቸነከረ ሞተ ተገነዘ ተቀበረ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። የሙታን ትንሣኤያቸው ፈርሰው በስብሰው የነበሩትን የሚያድናቸው በጨለማ ላሉ ብርሃናቸው ፣የተማረኩትን የሚመራቸው ፣ለተጨነቁት አምባ መጠግያቸው እርሱ ነው።( ሃይ.አበው ዘቅዱስ ሄሬኔዎስ 7፥17) 🌿 እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ። ደስ የሚል ብሩህ ጊዜ ይሁንላችሁ። 👇👇👇👇👇 @Slehiwetwe
በጣም በትንሽ ነገርም ቢሆን እንሳተፍ
ሰላም እንዴት ናችሁ የሆነ የበረከት ስራ እንድትሳተፉ ብዬ ነበር እና የምትፈልጉ በውስጥ ምስመር አውሩኝ @Begenayee
ከተማችሁ ልትጠፋ ነው ብንባል የብዙዎቻችን እርምጃ ከተማዋን ጥሎ መውጣት ነው። የነነዌ ሰዎች ግን እግዚአብሔር ጠቡ ከከተማዋ ጋር ሳይሆን ከመጥፎ ሥራቸው ጋር መሆኑን ተረድተው በንስሐ ተመለሱ። እንኳን ለነነዌ ጾም በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ። መልካም የበረከት ጾም ይሁንላችሁ @Slehiwetwe
መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ 11: ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ሉቃ 2፥10 @Slehiwetwe
✝🌷🌿🌷ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል ፤ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው፤ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ ከርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ።🌷🌿🌷✝(ሃይማኖተ አበው ቅ/ኤፍሬም ምዕ፵፯ ÷፪) እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል ይሁንላችው። 🌷ድንግል ስትታቀፍ ፈጣሪዋን ወልዳ፣ 🌷ያኔ ፈረሰና የጠቡ ግድግዳ። 🌷ሰውና መላእክት በኤፍራታ ምድር፣ እያሉ ዘመሩ ስብሐት ለእግዚአብሔር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Slehiwetwe
https://t.me/orthodoxywithorthopraxy
በዚህ ቻነል ርቱዕ እምነት ከርቱዕ ምግባር ጋር በአንድነት ሲዋሀድ የሚገኙትን መንፈሳዊ እሴቶቻችንን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ተደግፈን እንዳስሳቸዋለን።👇👇👇👇
"ውድ ጓደኛዬ እንኳን አደረሰህ! አዲሱ ዓመትህ የበረከት የሰላምና የፍቅር እንዲሆንልህ እመኛለሁ። ከሁሉም በላይ በመጪው ዓመት የጸሎት ህይወትህ ይበልጥ እንዲጠነክር የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት እንድትረዳ እና ከእምነትህ ጋር በተያያዘ ታላቅ ፍሬ እንድታፈራ እመኛለሁ። መልካም የአዲስ ዓመት 👺በዓል!" 👉 @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
ከ 1 ብር ጀምሮ የተቻለንን እንደግፍ🙏።
ተጋዳዩ ሐዋርያና ዘመናችን፤ የተወለደው ክርስቲያናዊ ካልሆኑ ቤተሰቦች ነው። ከአካባቢው ልጆች ጋር በነበረው ቀረቤታ ወደ ክርስትና ተሳበ። ተማረ፤ ተጠመቆም የእግዚአብሔር ልጅነትን አገኘ። በትጋትና በቅልጥፍና አገለገለ። ከዲቁና እስከ ጵጵስናም ደረሰ። በዘመኑ ነገረ ተዋሕዶውን አጣሞ ስሁት ትምህርት ሲያስተምር የነበረውን አርዮስን ከ317 ሌሎች ጳጳሳትና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የጉባዔው ጸሐፊ ሆኖ አወገዘ። ቀጥሎም 20ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ኾኖ በትጋት ማገልገል ጀመረ። አርዮሳዊ ንጉሥ ሲነግሥ ግን እርሱን አባሮ አርዮሳዊ ሊቀ ጳጳሳት በመንበሩ አስቀመጠ። ለአስራ አምስት ዓመታት በእስር፣ በስደት፣ በእንግልት አሳለፈ። ጥፍሩንና የሰውነት ክፍሉን ቢቆራርጡት፥ የቆራረጡትን የአካል ክፍል አሽጎ “እነሆ የሃይማኖት ፍሬ” ብሎ በእምነታቸው ጸንተው እንዲጠብቁ ላከላቸው። በዚህ ሁኔታ የቤተክርስቲያንን እውነተኛ አስተምህሮ ጠብቆ፣ አስጠብቆ ለኛ ትውልድ አሸጋገረልን። ሐዋርያ የተባለው ቅዱስ አትናቴዎስ በዚህች ዕለት (ግንቦት 7) አረፈ። ዛሬም ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ በባለሥልጣናት ተጽእኖ ተሾመው እንደ አርዮስ ሁሉ የክህደት ትምህርትን ያለመሸማቀቅ የሚያስተምሩበት ዘመን ላይ ነን። ያው ከትናንቱ የተለየ ነገር የለም። ያኔ እነ ቅዱስ አትናቴዎስ ታስረው፣ ተጋድለው እዚህ ያደረሷት ቤተክርስቲያን ዛሬም የሚጋደሉላትን ትጋብዛለች። የሚጋደሉ ይጋደሉላታል፤ የሚክዱም ይክዷታል። ነገንም ትቀጥላለች። እንደ አርዮስ አይነት ከሃዲ፣ ከእንደ ሁለተኛው አርዮሳዊው ቆስጠንጢኖስ ጋር እያሴረ፥ እንደ አትናቴዎስ አይነት ሃይማኖተኛ እየፈጠረ ዑደቱ ይቀጥላል። የቅዱስ አትናቴዎስ የተጋድሎውና የጸሎቱ በረከት ከሁላችን ጋር ይኑር! ይቀላቀሉ! 👇👇👇 https://t.me/burukie2014
ነብዩ ኤርምያስና የባቢሎን ምርኮ ነብየ እግዚአብሔር ኤርምያስ በአይሁድ እጅ ተወግሮ በዚህች ዕለት (ሚያዝያ 5) ሰማዕት ኾነ። የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማሩ፣ ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ፥ ንስሐም እንዲገቡ በመንገሩ ወገሩት። እግዚአብሔር፥ በነብዩ በኩል ነግሯቸው አልሰማ ያለውን ሕዝብ ለባቢሎኑ ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው። ሰባ ዓመትም በባርነትም ገዛቸው። በርኩሰቷ እግዚአብሔርን ያሳዘነችው “ታላቂቱ ከተማ” (ባቢሎን) ቅዱስ ቃሉን አልሰማ ያለን ሁሉ ትማርከዋለች። ባቢሎን እንዲህ ተብሎላታል፤ “የአጋንንት ማደሪያ ኾነች፤ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤ አሕዛብ ሁሉ ከዝሙቷ ቁጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነቷ ኃይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” (ራእይ 18፥ 2-3)። ሕዝብ ወደ ባቢሎን በመማረኩ ቅዱሳን ያዝናሉ። ደስታቸውም በባቢሎን ላይ እግዚአብሔር የሚሰጠው ፍርድ ነው። “ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት፥ ነቢያትም ሆይ! በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና” (የዮሐንስ ራእየ 18)። አምላካችን እግዚአብሔር ከቤቱ የራቅነውን፣ የቅዱሳንን ቃል ሁሉ ያቃለልነውን በነብዩ ኤርምያስ ጸሎት ከባቢሎን ምርኮ መልሶ በቤቱ አጽንቶ ያኑረን! ይቀላቀሉ! ቴሌግራም፤ https://t.me/burukie2014 ዩቲዩብ፤ www.youtube.com/@ቤተኦርያ-BeteOria
መልካሟ ደጅ፥ ኦርያ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ልምሾ ኾኖ የተወለደ ሰው ነበር። እግሩ አይቆምለትም፣ ወገቡ አይጸናለትም። ከቦታ ወደ ቦታ የሚያንቀሳቅሰው ሌላ ሰው ነው። ይህ ሰው አንድ ሥራ ብቻ ነበረው። ልመና። ሲነጋ ወስደው ከቤተክርስቲያን ደጅ ላይ ያስቀምጡታል። ከሚገባውና ከሚወጣው ሲለምን ይውላል። ማታ መጥተው፥ ያገኘውን ገንዘብ ተቀብለው፥ ወደ ቤቱ ይወስዱታል። ወደዚህ ቤተክርስቲያን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሁለት ሰዎች ለጸሎት እየገቡ ነው። ሁሉንም እንደሚለምነው ለመናቸው። በትኩረትም ተመለከቱት። ዘልቀው የልቡን ሁሉ ገመና አዩ። ያሰረውን ኃይል፣ የያዘውን ጠላት አስተዋሉ። ቀጥሎም አንደኛው እንዲህ አለው፤ “ወደ እኛ ተመልከት”። የሚሰጡትን ገንዘብ ከእጃቸው ሲፈልግ አየውና “ወርቅና ብር የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ ሂድ” አለው። በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው። ቆመ፣ ዘለለ፣ ሮጠም። እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደቤተ መቅደስ ገባ። ይህ ታሪክ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሦስት የተመዘገበ ነው። “ወደ እኛ ተመልከት” ያለው ቅዱስ ጴጥሮስ ነበር። አብሮትም የነበረው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ነው። “ወደ እኛ ሃይማኖት ግባ” እያሉ፣ ጥሪ እያቀረቡለት ነበር። እርሱም ፊቱን ወደ እምነቱ መልሷል። በዚህም ተፈውሷል። ይህንን ያዩ የአካባቢው ሰዎች ተደንቀዋል፤ ይህ የተሠራው በሰቀሉት በጌታችን ስም በመኾኑ ተጸጽተዋል፤ ሐዋርያቱ ስለ ስሙ ኃይልና ሥልጣን አስተምረዋቸዋል። በዚህም አምነው፣ ንስሐ ገብተው፣ ተጠምቀዋል። ያ የተፈወሰ ሰው የተቀመጠባት ቦታ ኦርያ ትባላለች። ትርጉሟም መልካም ደጅ ማለት ነው። ፈውስ የሚገኝባት፥ ምህረት የሚደረግባት፥ እግዚአብሔር የሚመሰገንባት፥ ወደ እነ ጴጥሮስ ሃይማኖት የመግባት ጥሪ የሚደረግባት ሰናይ ደጅ። ወደድንም ጠላንም በዚህ ዘመን ከሚዲያ አሠራር ተጽእኖ ነጻ መኾን የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተዳደር ይህንን ሁኔታ ተረድቶ እንቅስቃሴ ከጀመረ ገና ጥቂት ጊዜው ነው። የተቀናጀ አሠራርን ከማስፈንና ሚዲያን በአግባቡ ከመጠቀም አንጻር በጣም ብዙ ወደ ኋላ የቀረንበት ነው። በእርግጥ ሚዲያን መልካም ደጅ የማድረግ ሥራ የሁሉም የቤተክርስቲያን ልጆች ኃላፊነት ነው ብለን እናምናለን። ቤተ ኦርያም እንደ አንድ የሚዲያ አማራጭ ቅድስት ቤተክርስቲያን የምትዘክራቸውን ቅዱሳን ትምህርታቸውን፣ ተጋድሏቸውንና ሕይወታቸውን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር እየቃኘች ታቀርባለች። የሚዲያ አማራጮቻችንን ይቀላቀሉ! ቴሌግራም፤ https://t.me/burukie2014 ዩቲዩብ፤ www.youtube.com/@ቤተኦርያ-BeteOria ፌስቡክ፤ https://www.facebook.com/profile.php?id=61574859306729
ቅዱስ አባታችን አባ ሕርያቆስ የእመቤታችንን ቅዳሴ ያደረሰው የልደቷ ዕለት ነበር። ይህም የታወቀው አንድ ጻድቅ ባሕታዊ እመ አምላክን በጠየቃት አንድ ጥያቄ ነው። እንዲህ ሲል፤ “ከ33ቱ በዓላት ማንን ትወጃለሽ?” ክብርት እመ አምላክም፤ ‹‹ኪዳነ ምሕረትን፣ ልደታን፣ አስተርእዮን፣ ፍልሰታን›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከእነዚህ ከአራቱስ ማንን ትወጃለሽ?›› አላት። እመ ብርሃንም፤ ‹‹ከጠባብ ወደ ሰፊ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን የወጣሁበት ነውና ልደቴን እወዳለው፤ ቀድሞ እኔ ሳልወለድ እናትና አባቴን መባችሁን አንቀበልም ብለዋቸው አዝነው ተክዘው ነበር፡፡ የእነርሱ ሃዘን ሃዘኔ ነውና እኔን ከወለዱ በኋላ መባቸውን ተቀብለዋቸው ደስ ብሎዋቸዋል፡፡ የእነርሱ ደስታ ደስታዬ ነውና›› አለችው፡፡ እንኳን ለዚህች እመ አምላክ ከበዓሎቿ ሁሉ አብልጣ ለምትወዳት የልደቷ በዓል፣ አባ ሕርያቆስም ቅዳሴዋን ላደረሰባት ዕለት አደረሰን! ይቀላቀሉ👇👇👇 https://t.me/burukie2014
ሰማዕቱ ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ፤ የአንድ ጫማ ሰፊን ሕይወት ከመለወጥ ጀምሮ በርዕሰ መንበርነት የቤተክርስቲያን አስተዳደርን በእስክንድርያ መሥርቶ የመራው ቅዱስ ማርቆስ በዚህች ዕለት ሰማዕት ኾነ። እናቱ ቤቷን ለሐዋርያት የጸሎት ቤት አድርጋ የሰጠች ናት። አጎቱ በርናባስ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ሰባኪ ነበር። እኒህን የወንጌል አርበኞችም ተከትሎ ጵንፍልያ ወደምትባል ሀገር ሄዶ ነበር። በሐዋርያቱ የሚደርሰውን መከራ ባየ ጊዜ ግን ሸሽቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። ክርስትና በሂደት የሚታደግበት መንገድ ነውና ሐዋርያቱ በእግዚአብሔር ተአምር በሰላም ተመልሰው፥ በመከራው መካከል ተረማምደው ያስመዘገቡትን ድል፣ የለወጡትን ሕይወት በነገሩት ጊዜ አዘነ። እንደገናም አብሮ መሄድ ፈለገ። ቅዱስ በርናባስም አስከትሎት አብሮ ሲሰብክ፣ ሲያስተምርም ቆይቷል። በኋላም በርናባስ ሲሞት ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሀገረ ስብከት (ሮሜ) ሄዶ አብሮት አገልግሏል። እዚያም ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ እየተረጎመለት ዛሬ የምናነበውን የማርቆስ ወንጌልን ጽፏል። በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ ሄዶ ከአንድ ቤተሰብ ጀምሮ ብዙዎችን ወደ እውነተኛዋ ሕይወት መልሷል። የኛና የግብጻውያንንም መንበር በእስክንድርያ መሥርቷል። ብዙዎችን አስተምሮ፣ በክርስትና አጽንቶ ሥራውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፥ እግዚአብሔር ወደ ዘለዓለማዊ መንግሥቱ ሊያሸጋግረው በወደደ ጊዜ በዕለተ ትንሣኤ በከሃድያን እጅ ጣለው። በገመድ አስረውም ብዙ አንገላትተው በዚህች ዕለት (ሚያዝያ 30) ገድለውታል። ሥጋውን ሊያቃጥሉም በሞከሩ ጊዜ እግዚአብሔር በነጎድጓድ፣ በውሽንፍርም በትኗቸዋል። ምእመናንም ክቡር ሥጋውን አንሥተው በክብር አሳርፈውታል። የሰማዕቱ የቅዱስ ማርቆስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! የቴሌግራም ቤታችንን ይቀላቀሉ።👇👇👇 https://t.me/burukie2014
የምስክርነት ዋጋና ሽልማት፤ ሰማዕትነት ላመኑት ምስክር መኾን ማለት ነው። ምስክርነት በአንድ በኩል ዋጋ ያስከፍላል። በሌላ ደግሞ ሽልማት አለው። ሰማያዊ፣ ዘለዓለማዊ ሽልማት። ዋጋውን ከፍሎ ሽልማቱን ለማግኘት ደገሞ ያመኑት ነገር ትክክል መኾን አለበት። ሚያዝያ 28 በዚህች ዕለት ሁለት ቅዱሳን ያመኑበትን ትክክለኛውን ክርስቲያናዊ ሃይማኖታቸውን ትተው በሌላ እንዲያምኑ ተገደው ነበር። የመጀመሪያው አባ ሜልዮስ ይባላል። ኮራሳን ከሚባል ተራራ ላይ ወጥቶ በተጋድሎ ከሚኖርበት የሀገሩ ንጉሥ ሁለት ልጆች ሄደው ለፀሐይና ለእሳት እንዲሰግድ አስገድደውት ነበር። ባልሰማቸውም ጊዜ ከፊትና ከኋላው በወታደሮች ፍላጻዎች ተወግቶ እንዲሞት ኾኖ ሰማዕትነትን ተቀብሏል። ይህ አባት ከመሞቱ በፊት ለገዳዮቹ አንድ ትንቢት ነግሯቸው ነበር። “እኔን በፍላጻ እንዳሰቃያችሁኝ እናንተም እንዲሁ በፍላጻችሁ ትሞታላችሁ” ብሎ። ይህ ቃል ከአንድ ቀን በኋላ ተፈጽሞባቸዋል። ሁለተኛው ደግሞ አባ ብስጣውሮስ ይባላል። ክርስቲያናዊ ሕይወቱ ያስቀናው ጎረቤቱ “ሃይማኖታችንንና ባሕላችንን አይቀበልም” በማለት ለእስላም መኳንንት ከሶታል። እምነቱን እንዲቀይር ብዙ ስጦታዎችን፣ ማታለያዎችን ቢሰጡትም አልተቀበላቸውም። የሚያምነውን ያውቃልና። በሰይፍ አንገቱን ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀብሏል። ዓለም በእምነትህ ከቆምህ ሰይፏን ይዛ ትመጣብሃለች። የምታምነው እውነት መሆኑ ከገባህ አንገትህን ትሰጣታለህ። ካልገባህ ደግሞ እየሳቅህ የክህደት ትምህርቷን ትጋታለህ። አምላከ ቅዱሳን ከስህተት ጠብቆ፣ በእውነተኛዋ ሃይማኖት ያጽናን! ይቀላቀሉ👇👇 https://t.me/burukie2014
ሥልጣንን ለድኆችና ለተቸገሩት፣ ሥልጣንን ለገንዘብ፣ ለግል ጥቅማጥቅም ማካበቻ፣ ከፋ ሲልም ሌላውን ለመጉጃ መሣርያ አድርጎ መጠቀም ለዓለሙ ሰው የተለመደ ነው። ይህንን ዕድል ደግሞ ለበጎ የተጠቀሙ ቅዱሳን አሉ። ቅዱስ ፊቅጦር ከነዚህ ይመደባል። አባቱ የጨካኙ ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ አማካሪዎች አለቃ ነበር። እናቱ ደግሞ ደግ ክርስቲያን ነበረች። ልጇን ክርስቲያናዊ ሕይወትን አስተምራ አሳድጋለች። ሃያ ዓመት በኾነው ጊዜ አባት ከንጉሡ ዘንድ ልጁ ፊቅጦርን ወስዶ አሹሞታል። በማዕረግ ከንጉሡ ሦስተኛውን ደረጃ ተሰጥቶታል። በተሾመም ጊዜ ሥልጣኑን ድኆችን፣ ሕሙማንን፣ እስረኞችን፣ ረዳት የሌላቸውን የሚያግዛቸው ኾነ። በዘመኑ የተገደሉ ክርስቲያኖችን እንኳን አንሥቶ መቅበር የማይቻልበት ሁኔታ ነበር። ይህ ቅዱስ ግን ክርስቲያኖችን አክብሮ ይቀብር ነበር። በክርስቲያናዊ ምግባሩም ጣዖት አምላኪ አባቱ ለንጉሥ ከሶ ባሳሰረው ጊዜ እናቱን ያሳሰባት ነገር እርሱ ይረዳቸው የነበሩ ጠያቂ የሌላቸውን ችግረኞች ሁል ጊዜ እንድትጎበናቸው ነበር። ይህ ቅዱስ በዚህች ዕለት (ሚያዝያ 27) ሰማዕትነትን ተቀብሏል። አምላካችን እግዚአብሔር ሁላችንንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን! ዩቲዩብ ገጽ፤ www.youtube.com/@ቤተኦርያ-BeteOria ፌስቡክ፤ https://www.facebook.com/profile.php?... ቴሌግራም፤ t.me/burukie2014