ራዕየ ማርያም ✝
Статистикаበኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 91
- 1/48двое суток
- 104
- 1/72трое суток
- 112
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የጸጋ ስግደት ኪዳነ ምሕረት የሃይማኖት ምስክር 3X ኪዳነ ምሕረት የቅቡጻን ተስፋ 3X ኪዳነ ምሕረት የረድኤት ደንጊያ 3X ድንግል ማርያም የመለኮት ማኅደር ድንግል ማርያም የመልአክት እህት ድንግል ማርያም የመሃይማን እናት ድንግል ማርያም የነቢያት ጌጽ ድንግል ማርያም የሐዋሪያት አክሊል ድንግል ማርያም የሰማዕታት ሽልማት ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያ ድንግል ማርያም የካህናተ ሰማይ እጣን ድንግል ማርያም የቅዱሳን ልዕልና ወላዲተ አምላክ ነባቢት ገነት ወላዲተ አምላክ የሕግ ታቦት ወላዲተ አምላክ የወይን ሃረግ ደስ ይበልሽ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ ሙሽራ ሆይ ደስ ይበልሽ ሙዳይ ሽቱ ሆይ ደስ ይበልሽ የመድኃኒት ቀንድ ሆይ ደስ ይበልሽ የብርሃን ድንኳን ሆይ ደስ ይበልሽ ንጽሕት መጋረጃ ሆይ ደስ ይበልሽ ቤተልሄማዊት መሶብ ሆይ ደስ ይበልሽ የወርቅ መርከብ ሆይ ደስ ይበልሽ ሁለተኛ ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ የምሕረት ደመና ሆይ ደስ ይበልሽ የክብር ምንጭ ሆይ ደስ ይበልሽ ዕጸ ጳጦሰ ሆይ የአዳም ተስፋ ምስጋና ላንቺ የያዕቆብ መሰላል ምስጋና ላንቺ የዳዊት መሰንቆ ምስጋና ላንቺ የአሮን በትር ምስጋና ላንቺ የአሚናዳብ ሠረገላ ምስጋና ላንቺ የጌዴዎን ብዝት ግምጃ ምስጋና ላንቺ የሕዝቅኤል ደጃፍ ምስጋና ላንቺ የቀርሜሎስ መሠዊያ ምስጋና ላንቺ @raiye_mariyam
እግዚአብሔር የሌለበት ሃብት ልክ እንዳገጠጠ አውሬ ያስፈራል። እርሱ የሌለበት ትዳር ሆድን ብቻ የሚሞላ እንጂ ሕሊናን አይሞላም። ኑሮም ተበልቶ እንዳለቀ አጥንት ወይም የበቆሎ ቆሮቆንዳ ብናገላብጠው ለጥጋብ የሚሆን አንድም ነገር የለውም። ያለ እግዚአብሔር የተደሰቱ እያረሩ ይስቃሉ። ያለ እግዚአብሔርም ያዘኑ መጽናናትን አያገኙም። ያለ እግዚአብሔር የተመራመሩ የተማሩ ባለጌዎች ይሆናሉ። የሰው ልጅ የኑሮ ማትረፊያው የሰላሙ መሠረት የእርካታው ምንጭ እግዚአብሔር ነው። "እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።" ትንቢተ ኢሳይያስ 22:22 መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ @raiye_mariyam
እሾህ ባይወጋን ባንቆስል መልካም ነበረ።ያቆሰለን ካለ ግን በቁስላችን ላይ መድኃኒት ልናደርግበት ይገባል። ኃጢአት ባንሰራ መልካም ነበረ። ከሰራንም ግን ፈጣሪ ይቅር ይለን ዘንድ እንጸጸት ንሥሓ እንግባ። ክፉ ሰው መንገዱን፥ ዓመፀኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ፥ እርሱም ይምረዋል፤ ይቅርታውንም ያበዛለታል።" — ኢሳይያስ 55፥7 “እላችኋለሁ፥ አይደለም፤ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ።” — ሉቃስ 13፥3 👉 በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወድደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ። @raiye_mariyam
"ቤተ ክርስቲያንን በድንጋይና በእንጨት ከመገንባት ይልቅ፣ ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፍና በእምነት ማጽናት የሚበልጥ ሥራ ነው።" ብዙዎች እብነ በረድ በመደርደር፣ ጣራውን በወርቅ በማስጌጥና መሠዊያውን በዕንቁ በማንቆጥቆጥ ላይ ይጠመዳሉ። ይህ መጥፎ አይደለም፤ ነገር ግን የክርስቶስ እውነተኛ አገልጋዮች ምርጫ ሊሆን የሚገባው የሰዎችን ልብ በእምነት ማነጽና ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፍ ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው ያሸበረቁ ሕንፃዎችን ሳይሆን፣ በቅድስና የተሰሩ ንጹሕ (ነፍሳትን) ልቦችን ነው።" (ትምህርተ አበው) “እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።” — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥5 “ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።” — ያዕቆብ 5፥20 👉 በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወድደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ። @raiye_mariyam
አንተ ሰው እትጥልም☦️ @raiye_mariyam
☦️ @raiye_mariyam
ሰንበተ ሰንበታት በዓመት ውስጥ አራት ሰንበተ ሰንበታት አሉ ። እነዚህ ቀናት የሚሰሉት የዓመቱን 365 ቀናት ለ4 በመክፈል (91 ቀናት በመቁጠር) ነው። - የ2018 ዓ.ም የሰንበተ ሰንበታት ቀናት መስከረም 1 ቀን ሐሙስ ስለዋለ፣ በዚህ ዓመት የሚውሉባቸው ቀናት እንደሚከተለው ይሆናሉ፡ 1ኛው ሰንበተ ሰንበታት መስከረም 4 2ኛው ሰንበተ ሰንበታት ታኅሣሥ 5 3ኛው ሰንበተ ሰንበታት መጋቢት 6 4ኛው ሰንበተ ሰንበታት ሰኔ 7 ይሆናል ። በሌላ ቀላል ዘዴም ማወቅ ይቻላል ይኸውም መስከረም ፣ ታህሳስ ፣ መጋቢት ፣ ሰኔ በእነዚህ 4 ወራት የመጀመሪያው እሁድ ሰንበተ ሰንበታት ይሆናል። የእነዚህ የ4ቱ ዕለታት ማሳረጊያ ደግሞ ጳጕሜን 3 ናት። -> በእነዚህ ዕለታት ርኆተ ሰማይ የሚሆንባቸው በመሆናቸው የዚህ ዓመት 4ኛው ሰንበተ ሰንበታት ሰኔ 7 ስለሆነ ከወትሮው በተለየ መልኩ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት፣ ምህረትን የምንለምንበት እና ለራሳችንና ለሀገራችን ሰላም የምንጸልይበት ታላቅ ዕለት ነው። ጸሎታችንና ምልጃችን በፊቱ ይድረስ! ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ ነገ ወርኃዊ የአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ወርኃዊ በዓል እና ሰንበተ ሰንበታት በአንድ ላይ ስለሆነ ከሌላው ጊዜ አብልጠን ከኪዳን ጀምሮ በሥርዓተ ቅዳሴው እንድንካፈል የተዘጋጀን ቅዱስ ስጋው እና ክቡር ደሙን እንድንቀበል ጸሎት የሚያርግበት ዕለት በመሆኑ ካስለመድነው ጸሎት ጨምረን ብንጸልይ እጅጉን እንጠቀምበታለን። @raiye_mariyam
ጌታዬ ሆይ ዛሬ በሕማማትህ ጎዳና ላይ ሳለህ ለካ ትርበህ ነበር። የዓለምን ረሃብ ልታስታግስ የመጣህ የሕይወት እንጀራ አንተ ስትራብ፣ ያቺ በለስ ግን አሳፈረችህ። ጌታ ሆይ፣ ዛሬም ረሃብህ አላበቃም፤ አንተ ዛሬም በእኔ ሕይወት ውስጥ ፍቅርን ትርባለህ፣ ቅድስናን ትራባለህ፣ ምጽዋትንና ትሕትናን ትራባለህ። እኔ ግን እንደ በለስዋ ነኝ— በሩቁ ለሚያየኝ "ክርስቲያን" የምባል ለምለም ቅጠል ያለኝ፣ ስትቀርበኝ ግን ለረሃብህ ማስታገሻ የሚሆን አንዲት ፍሬ የሌለኝ ባዶ ነኝ። ጌታዬ ሆይ፤ ያቺን በለስ "ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ" ብለህ ስትረግማት፣ ውስጤ በመንቀጥቀጥ ተሞላ። ያ የርግማን ቃል ለእሷ ሳይሆን ለእኔ እንደሆነ አውቃለሁ። እኔም በዓመታት መከታተል፣ በጸጋህ ዝናብ መርጠብ፣ በምክርህ መኮትኮት ነበረብኝ። ነገር ግን ዘመኑ አልፎ ዘመን ሲተካ እኔው በነበርኩበት የኃጢአት ቅርፊት ውስጥ ደርቄ ቀረሁ። ጌታ ሆይ፣ በለስዋን የረገምካት የዛፍ ጠላት ስለሆንክ አይደለም፤ "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" የሚለውን ቃልህንም እንዳልሰማሁ ሆኜ፣ የሕይወቴን ጭማቂ በከንቱነት ስላፈሰስኩት መገሰጽህ ነው። ጌታ ሆይ፤ አንተ ስለ እኔ ቍስልን ስትታገሥ፣ እኔ ግን ስለ አንተ አንዲትን ጾም መታገሥ አቃተኝ። አንተ ራቁትህን በመስቀል ላይ ስትሰቀል፣ እኔ በምድራዊ ጌጥና በከንቱ ውዳሴ ቅጠል ራሴን እሸፍናለሁ። ያቺ በለስ በቃልህ ብቻ ደረቀች፤ እኔ ግን ስንት ቃልህ እየተነገረኝ፣ ስንት ማስጠንቀቂያ እያየሁ፣ በኃጢአት ረግረግ ውስጥ ለምለም መስዬ መኖሬን ቀጠልኩ። ጌታ ሆይ፣ ከዚህ የግብዝነት ሕይወት አውጣኝ። መድኃኔዓለም ሆይ፤ እባክህ አትርገመኝ! ይልቁንም ያንን የርግማን ቃል ወደ እኔ ሳይሆን፣ በውስጤ ላለው ለዚያ ለማያፈራ የኃጢአት ግንድ ስጠው። ትዕቢቴ ይድረቅ፣ ምቀኝነቴ ይርገፍ፣ ክፉ ምኞቴ እንደ በለስዋ ቅጠል ይረግፍ። በሥጋዬ ላይ የምታየውን የሕመም ጩኸት ሳይሆን፣ በነፍሴ ላይ ያለውን የኃጢአት ደዌ ተመልከት። ሕማምህን ሳስብ የገዛ ኃጢአቴ እንዲያመኝ አድርገኝ። ችንካሩ በእጆችህ ላይ ብቻ ሳይሆን በደነዘዘው ሕሊናዬ ላይ እንዲሰማኝ አድርገኝ። ከኢዩኤል ሃብታሙ @raiye_mariyam
“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም (በኃጢአት ..በዝሙት..በአመንዝራ ... በአምልኮ ጣዖት ) በባርነት ቀንበር አትያዙ።” — ገላትያ 5፥1 “ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13 👉በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወደውንም ሥራ ብቻ ስሩ ።
видео или голосовое, без подписи
#_የመጀመሪያው_የዐብይ_ጾም_የንስሐና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ! ❤ #_በጎሮ_ኪዳነ_ምህረት_ቤተ_ክርስቲያን! ❤ #_እሑድ_የካቲት_15_ጠዋት_2_ሰዓት! ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም #_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ! "ጥሩ ውኃንም እረጭባችኃለሁ እናንተም ትጠራላችሁ" ሕዝቅ 36፥25 "የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም" ❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው? ❤ #_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን? ❤ #_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን? #_የነፍስ_ጉዳይ_ነውና_ሳትቸኩሉ_በደንብ_አንብቡት! ተወዳጆች ሆይ የዐብይ ጾምን የመጀመሪያው የንስሐ፣ የቄደር ጥሞቀት እና የጠበል ጥምቀት መርሃ ግብር አዘጋጅተናል። ስለዚህ እሑድ የካቲት 15 ጠዋት 2 ሰዓት ከቅዳሴ መልስ በጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን፣ የመጀመሪያውን የዐብይ ጾም የንስሐ የመስጠት እና የቄደር ጥምቀት እንዲሁም የመደበኛ የጠበል የጥምቀት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ፣ ጠበል ተጠመቁ። የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር። ❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው? ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣ ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣ ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን። ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል። በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል። ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ የካቲት 15 ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ። የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ። የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም። የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። ስለዚህ እሑድ የካቲት 15 ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ። ❤ #_ማሳሰቢያ :- ሴቶች ቀለል ያለ የመጠመቅያ ልብስ ልበሱ ወይም ያዙ! ❤ ወንዶችም ቀለል ያለ መጠመቂያ ወይም ቱታ ልበሱ ወይም ያዙ! ❤ #_የቦታው_አድራሻ_እና_የትራንስፖርት_መምጫው ፦ ❤ ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፤ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፓልቱ አጠገብ በስተ ግራ በኩል ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች። ❤ ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍራችሁ፣ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከመገናኛ 113 ቁጥር ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከፒያሳ ከእሳት አደጋው ዝቅ ብሎ ኮዬ ፈጬ በሚለው 131 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያኑ ጋር ይወርዳሉ! ❤ ከሜክሲኮ ሸበሌ ጋር 29 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያና ትገኛለች! ❤ ከሲኤምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፖልቱ ጫፍ ትገኛለች! ❤ ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ሳትደርሱ ወርዳችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በስተቀኝ አስፖልቱ ዳር ትገኛለች፡፡ የካቲት 10-6-2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
ዘወረደ የምስጢረ ሥጋዌ ትምህርት ነው ፡፡ ዘወረደ ስንል አምላክ መጣ ፤ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ፤ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ማለታችን ነው ፡፡ ዘወረደ በአምላክ ትህትና ክብረ አዳም የሚነገርበት ነው ፡፡ አምላክ ሰው በመሆኑ ሰው አምላክ ሆነ ፤ ከበረ ፤ ገነነ ፤ ነገሠ ፡፡ ሕያው አምላክ ክርስቶስ በቅድስት ሞቱ ሟቹን አዳም ዘላለማዊ ሕያው አደረገው ፡፡ አምላክ ወልደ አምላክ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሞቶ ለአዳም ያለውን ታላቅ ፍቅር ገለጸ ፡፡ የተጣላውን አዳምን በፈቃዱ ታረቀው ፡፡ ጠላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ፥ ይልቁንም ከታረቅን በኃላ በሕይወቱ እንድናለን ፡፡ ሮሜ. 5 ፥ 10:፡ በዚህም ትህትናን ፍቅርን አስተማረን ፡፡ 👉በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ።
видео или голосовое, без подписи
#_ንስሐ_የቄደር_የጠበል_ጥምቀት_አገልግሎት! #_እሑድ_ጥር_17_በጎሮ_ኩዳነ_ምህረት_ቤተ_ክርስቲያን #_ጠዋት_2_ሰዓት_ከቅዳሴ_መልስ ሼር በማድረግ ለሌሎች አዳርሱ! ❤ #_የቦታው_አድራሻ_እና_የትራንስፖርት_መምጫው ፦ ❤ ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፤ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፓልቱ አጠገብ በስተ ግራ በኩል ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች። ❤ ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍራችሁ፣ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከመገናኛ 113 ቁጥር ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከፒያሳ ከእሳት አደጋው ዝቅ ብሎ ኮዬ ፈጬ በሚለው 131 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያኑ ጋር ይወርዳሉ! ❤ ከሜክሲኮ ሸበሌ ጋር 29 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያና ትገኛለች! ❤ ከሲኤምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፖልቱ ጫፍ ትገኛለች! ❤ ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ሳትደርሱ ወርዳችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በስተቀኝ አስፖልቱ ዳር ትገኛለች፡፡ አርብ ጥር 16-5-2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
видео или голосовое, без подписи
#_አርብ_ቅዳሜ_እና_እሑድ_አገልግሎት_አለ! #_በተከታታይ_ጥር_15_ጥር_16_እና_ጥር_17 ሼር በማድረግ ለሌሎች አዳርሱ! ❤ #_የቦታው_አድራሻ_እና_የትራንስፖርት_መምጫው ፦ ❤ ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፤ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፓልቱ አጠገብ በስተ ግራ በኩል ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች። ❤ ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍራችሁ፣ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከመገናኛ 113 ቁጥር ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከፒያሳ ከእሳት አደጋው ዝቅ ብሎ ኮዬ ፈጬ በሚለው 131 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያኑ ጋር ይወርዳሉ! ❤ ከሜክሲኮ ሸበሌ ጋር 29 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያና ትገኛለች! ❤ ከሲኤምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፖልቱ ጫፍ ትገኛለች! ❤ ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ሳትደርሱ ወርዳችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በስተቀኝ አስፖልቱ ዳር ትገኛለች፡፡ አርብ ጥር 14-5-2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
видео или голосовое, без подписи
❤ #_የንስሐና_የቄደር_ጥምቀት_የጸበል_ጥምቀት_ጥሪ! ❤ #_በጎሮ_ኪዳነ_ምህረት_ቤተ_ክርስቲያን! ❤ #_እሑድ_ጥር_17_ጠዋት_2_ሰዓት! ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም #_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ! "ጥሩ ውኃንም እረጭባችኃለሁ እናንተም ትጠራላችሁ" ሕዝቅ 36፥25 "የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም" ❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው? ❤ #_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን? ❤ #_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን? #_የነፍስ_ጉዳይ_ነውና_ሳትቸኩሉ_በደንብ_አንብቡት! ተወዳጆች ሆይ እሑድ ጥር 17 ጠዋት 2 ሰዓት ከቅዳሴ መልስ በጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የፆመ ነብያት የመጨረሻው ንስሐ የመስጠት እና የቄደር ጥምቀት እንዲሁም የመደበኛ የጸበል የጥምቀት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር። ❤ #_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው? ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣ ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣ ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን። ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል። በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል። ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ ጥር 17 ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ። የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ። የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም። የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። ስለዚህ እሑድ ጥር 17 ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ። ❤ #_ማሳሰቢያ :- ሴቶች ቀለል ያለ የመጠመቅያ ልብስ ልበሱ ወይም ያዙ! ❤ ወንዶችም ቀለል ያለ መጠመቂያ ወይም ቱታ ልበሱ ወይም ያዙ! ❤ #_የቦታው_አድራሻ_እና_የትራንስፖርት_መምጫው ፦ ❤ ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፤ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፓልቱ አጠገብ በስተ ግራ በኩል ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች። ❤ ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍራችሁ፣ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከመገናኛ 113 ቁጥር ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያኗ ትገኛለች! ❤ ከፒያሳ ከእሳት አደጋው ዝቅ ብሎ ኮዬ ፈጬ በሚለው 131 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያኑ ጋር ይወርዳሉ! ❤ ከሜክሲኮ ሸበሌ ጋር 29 ቁጥር ባስ ይዘው ጎሮ አደባባይ ወርደው ትንሽ ዝቅ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያና ትገኛለች! ❤ ከሲኤምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ወደ ኮዬ በሚወስደው አስፖልት ትንሽ ዝቅ እንዳላችሁ አስፖልቱ ጫፍ ትገኛለች! ❤ ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ሳትደርሱ ወርዳችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በስተቀኝ አስፖልቱ ዳር ትገኛለች፡፡ ሐሙስ ጥር14-5-2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
👉 ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ። 👉 ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ 👉 ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ። #በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ጊዜ_ያልቃል። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ይወስዷታል። (ቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ) “ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።” — ማቴዎስ 24፥44 👉 በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ።
видео или голосовое, без подписи