tgindex
በማለዳ ንቁ !

በማለዳ ንቁ !

Статистика
Последний пост
11 апр.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
13 143
−18 за 5 дн.
Сутки
−1
−0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 592
23 постов
Вовлечённость
27,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 11 апр.5 2769614

    አንድ ምእመን በዚህ ዓለም ቃሉን ሲማርና ስጋ ደሙን ሲወስድ፣ የሚያገኘው ከትንሳዔው በፊት ያለውን ክርስቶስን ነው፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ትምርቱና ኪዳኑ ለሞት የታዘዘ ነውና፣ በነዚህ አካልነቱን የተሳሰረው ምእመንም ሞቱን ይካፈላል፡፡ በእውነት ለሚኖረው የክርስትና ኑሮ ለዓለሙ መሞት ነው፡፡ ይኹንና የሞተው እሱ በሞቱ አልቀረም፡፡ ተነስቷል፡፡ ተነሳ ከተባለ መላው አካሉ ነው መቼም የሚነሳው፡፡ ማለት አካሉ በቃሉና በስጋው ደሙ ከተዘራባቸው ኹሉ ውስጥ ነው በትንሳዔው የሚበቅለው፡፡ ስለኾነ ትንሳዔው ቃሉና ቁርባኑ ላላቸው ትንሳዔያቸው ነው፡፡ በእነሱም ውስጥ ይነሳል፡፡ እሱስ ስጋ ደሙን ሲሰጥ እንደዛ አይደል ያለው? ስጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ አይሞትም ፤ቢሞትም እኔ አስነሳዋለኹ አይደል የሚለው? በትንሳዔ ያለው ክርስቶስ ከሞቱ በፊት እንደነበረው ያለው አይደለም፡፡ ይለያል፡፡ አበው እንደሚሉት ሐዲስ ብእሲ (አዲሱ ሰው) ነው፡፡ ከሕጉ በሞት የተፈታ አካል ነውና ያለው አኹን ስልጣን በሰማይ በምድር የተረከበ ነው፡፡ ማለት አኹን አካሉ በአንድ ስጋና ደም ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በተቀበሉት ኹሉ ውስጥ ያለ አካል ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የተቀበሉት ኹሉ አኹን የክርስቶስ አካል ናቸው፡፡ እሱ ግንድ ኾኖ እነሱ ቅርንጫፎች ኾነው በአንድ ዛፍነት የተካተቱ ናቸው፡፡ የአማናዊ ክርስቲያን ትርጉም ይሄው፤ አካሉ፣ ሕብረቱ ያለው ነው ክርስቲያን ማለት፡፡ ከክርስቶስ ጋ የአካል ሕብረት ያለው ደሞ በአካሉ ያለች ልጅነት አለችው፡፡ አኹን እግዚአብሔር አብ ይሄን ምእመን ሲያየው ልጁን ነው የሚያየው፡፡ የኢየሱስ አካልን ነው የሚያየው፡፡ ለተቀበሉት ኹሉ በስሙ ለሚያምኑት የእግዚአብሔር ልጆች ይኾኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው የተባለው በትንሳዔው የኾነ ነው፡፡ ትንሳዔው በአንድ አካል የተገለጠችው የእግዚአብሔር ልጅነት 'ልጆች' ታሰኘን ዘንድ በቃሉና በስጋው ደሙ ተዘርታ በእኛ ልትበዛ የምትበቅል የመንፈስ ፀጋ ናት፡፡ ትንሳዔ ዋናዋ ነገር ናት!

  • 11 апр.4 4122611

    ትንሳዔ የክርስትና ዋና ናት፡፡ ይሄም የኾነው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ካሰበው ሀሳብ የተነሳ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በሥጋ የመገለጥ ማእከላዊ ነጥብ በሱ የኾነች ልጅነቱን ለመስጠት ነው፡፡ አስኳሉ፣ አድራሻው ጉዳይ ልጅነቱን ማግኘት ነው፡፡ ይህች አስቀድማ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀችና ኋላም በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት የተገለጠች የእግዚአብሔር ልጅነት፣ የተሰጠቺው በትንሳዔ በኩል ነው፡፡ መቀበሉን ከታደልን ልጅነት በትንሳዔ ተሰጥታለች፡፡ እንዳነሳው ልጅነት ከመጀመሪያው በወልድ አካል ያለች ምሉዕ እውነት ናት፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ቃሉም ነው፡፡ በኋላ ዘመን በሥጋ ሲገለጽ ከእናቱ ማርያም በልደት በወሰደው አካል ብቅ ብሎ ታይቶናል፡፡ ነገር ግን ይህች ልጅነት አኹንም በእሱ የተለየ አካሉ ተይዛ አለች እንጂ በእኛ ዘንድ አልተገለጸችም፡፡ ስለዚህ ይህችን ልጅነት የማግኛው በር ከኢየሱስ ክርስቶስ አካሉ ጋራ ሕይወት ያለው ሕብረት መፍጠር መቻል ነው፡፡ ከአካሉ ጋ ሕብረት ካለን፣ ወይም ከአካሉ የምንተሳሰርበት አንድነት ካገኘን፣ በእሱ ኾና ያለች ልጅነቱንም እናገኛታለን፡፡ ለምሳሌ አንድ የንጉሥ ልጅ ቢኖርና አባቱ በልጁ በኩል እኛንም ልጆቼ እንዲለን ከፈለግን ምንድነው የምናደርገው? የዚያን ልዑል ሰውነት ሰውነታችን ብናደርግ በሱ ያለች ልጅነቱን አናገኛትምን? ማለት ልክ እንደ ዓይኑ፣ አፍንጫው፣ ጸጉሩ፣ ከአካሉ ብንካተት በጥቅሉ የእሱዉ አካል ነው የምንኾነው፡፡ ለዚህ ነው ክርስቶስ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተ ቅርንጫፎች ናችሁ የሚለው፡፡ ዛፉን ያው በጥቅሉ ስናየው ያው አንድ ዛፍ ነው፡፡ መሰረቱ ግንድ አንድ ኾኖ ብዙ ቅርንጫፎች ቢኖሩት፣ ያው ዛፍ በሙሉዉ ሲታይ አንድ ዛፍ ነው፡፡ እኛ ብዙ ኀዋሳት ቢኖሩንም በሙሉዉ ስንታይ አንድ ሰው፣ አንድ አካል ነን፡፡ ስለዚህ ኀዋሶቻችን ልዩ ልዩ ቢኾኑም እንኳ በአካላችን ውስጥ የሚከናወን የደም ሥርዓትን፣ የነርቭ ሥርዓትን፣ የምግብ ሥርዓትን በአንድ ይጋራሉ፡፡ ተረዳችሁት? ዛፉ በጥቅሉ ክርስትና በምልዓቱ ነው፡፡ በዚያም ውስጥ ያለው ቁልፍ ነገር ልጅነቱን ማግኘት ነው፡፡ የዚህ ታላቅ ዛፍ ግንድ ክርስቶስ ነው፡፡ ከዚህ መሰረት ጋ ታዲያ የአካልነት ሕብረት የፈጠሩ የሰው ልጆች ኹሉ ቅርንጫፎቹ ኾነው ያፈራሉ፡፡ በሱ ያለች ልጅነቱን ልጅነታቸው ያደርጋሉ፡፡ ታዲያ ትንሳዔው እንዴት አድርጋ ልጅነቱን አደለችን? እንደሚታወቀው በሥጋ ሕግ መሰረት አንድ ሰው አካሉን፣ ሕልውናውን ከእናቱ ማሕጸን ነው ይዞ የሚመጣው፡፡ ይህን ልዩ የራሱ የኾነ አካሉን ለሌላ ሰው መስጠት አይችልም፡፡ እንደ ዔሳውና ያዕቆብ እንኳ መንታ ብንኾን በየራሳችን ልዩ አካልና ኅልውና ነው የምንወለድ፡፡ ከእናንተ መሃል አካሉን፣ አእምሮውን ለሌላ ሰው ማካፈል የሚችል አለ? በየራሳችን የተያዝን ነን፡፡ የእግዚአብሔር ልጅም በስጋ ሲገለጥ በራሱ ልዩ አካል ነው የተገለጠው፡፡ አካሉ፣ ልቦናው በሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ በዚያም ውስጥ ያለች ልጅነቱ (ቃልነቱ) ወደእኛ መምጣት አይችልም፡፡ የተፈጥሮ ሕግ ማሕተም ኾኖ ተቀምጧል፡፡ ኹሉም በየራሱ ማንነት፣ አካል እንዲገለጥ የተቀመጠ የተፈጥሮ ሕግ አለ፡፡ ነገር ግን ጳውሎስ እንደሚለው ሕግ የሚሰራው እስከሞት ድረስ ነው፡፡ በትዳር ሕግ ለባሏ የተያዘች ሴት፣ ባሏ ከሞተ በኋላ ሌላ ብታገባ ሕግ ተላለፍሽ ተብላ አትጠይቅም፡፡ (ሮሜ. 7፥2) እርግጥም የትኛው የተፈጥሮ ኾነ የሰው ሕግ በሕጉ ተመክቶ የሚከሰን እስከምንሞት ድረስ ነው፡፡ በሕገ መንግስትም የመጨረሻው ቅጣት ያው ሞት ነው፡፡ ከዚያ በላይ ይሄ ዓለም መኼድ አይችልም፡፡ እንዲኹ የክርስቶስ አካሉ፣ በዚያ ያለች ልጅነቱ እስከ ጊዜ ሞቱ ድረስ በሕጉ መሰረት በእሱ ብቻ የተያዘች ነች፡፡ እግዚአብሔር ደሞ ቀድሞ የዘረጋውን ሥርዓት አይጥስምና በልጁም በኩል ቢኾን ሕጉን አልጣሰም፡፡ ራሱን እንደመካድ ነው የሚኾንበት፡፡ ስለዚህ ለተፈጥሮና ጠቅላላው ለተቀመጡ ሕጎች ጌታ በስጋው ወራት ሲታዘዝ ይታያል፡፡ ለቄሳር የቄሳርን ስጡ እያለ የሰውን እንኳ ሲታዘዝ ቆይቷል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በአስቀድሞዉ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ ቃል ነው፡፡ ቃል በኛ በምሳሌው ዓለምም እንደምናውቀው፣ እንደ አዝርዕት ነው ባሕርዩ፡፡ አንድ ዘር ተዘርቶ ብዙ ፍሬ እንደሚገኝበት፣ አንድ መምህር ብዙ ተማሪዎች ጋ ቃሉን ማስቀመጥ ይችላል፡፡ በወንጌሉም ራሱ ጌታ 'ናሁ ወፅአ ዘይዘርዕ ይዝራዕ፤ እነሆ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ' እያለ ጉባዔውን ነግሮናል፡፡ ዘርም የተባለ ቃል ነው ሲል የራሱ ሕይወት እንደኾነ እዛው ተርጉሞታል፡፡ ስለዚህ የሱ ሞቱ እንደ አዝርዕት መዘራቱ ነበር፡፡ በመኾኑ በስጋ ሞቱ ሞቶ፣ ለሕጉ ተፈቶ በትንሳዔው ተነስቷል፡፡ ሞቱ መዘራቱ ከኾነ ትንሳዔው መብቀሉ ነው፡፡ በእርሻ እንደምናውቀው ደሞ የተዘራ ሲበቅል አንድ ኾኖ አይወጣም፡፡ ይበዛል፡፡ ዮሐ. 12፥24 ቁምነገሩ ልጅነቱን ማግኘቱ ነው ብለናል፡፡ ይኸውም ከአካሉ ጋ ሕብረት በመፍጠር ነው፡፡ በዘሩ ምሳሌ ዘሩ ተዘራ ማለት ከአካሉ ቆርሶ እንደመስጠቱ ነው፡፡ ከአንድ መሶብ እንደመውሰድ ነው፡፡ ይሄ በሁለት መንገድ ኾኗል፤ እየኾነም ነው፡፡ በቃሉና በስጋ ደሙ በኩል፡፡ ፩. ቃሉ ቃሉ ዘር ነው ብለናል፡፡ ይሄ የምትሰሙት ቃል ሕይወትም ነው መንፈስም ነው ይላል፡፡ ሰዎች ልብ እንበል፡፡ ቃል የምንለው የኛን ቋንቋ አይደለም፡፡ እሱ ምሳሌ ነው፡፡ መጽሔት ነው፡፡ የኛ ቃል ሕይወት ያለው ሕይወትን የሚከፍል አይደለም፡፡ በኛ ስጋ ውስጥ የተያዘ ምሳሌ ቃል ነው ያለን፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃልነቱ ሕይወቱ ናት፡፡ ሕይወት ነው፡፡ ሲያነቡት ሳይኾን ሲኖሩት የሚያዉቁት ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ የተማርነው እየኖርን አይደለ? ፍቅርን በኛ ያገኘነው ማፍቀርን ስናየው አይደለ? ቃሉ እንዲያ ነው፡፡ ወንጌሉን፣ መጽሐፍቱን ቁጭ ብሎ ማንበብ አይደለም፡፡ የሕይወት ቃል ነው፡፡ መንፈስ ነው፡፡ የሚሰሙትም በሕይወት ነው፡፡ ፪. ስጋው ደሙ ሐዲስ ኪዳን ተሰርታ የተፈረመቺው በስጋው ደሙ በኩል ነው፡፡ ይህች የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው ብሎ ሰጥቷታል፡፡ አስተዋልን? ከላይ እኮ ብለናል፡፡ ኹሉም ሲወለድ በራሱ አካል፣ በራሱ ሕልውና፣ በራሱ ስጋና ደም ነው የሚገለጠው፡፡ እያንዳንዳችኹ በየራሳችኹ ስጋና ደም ነው ያላችኹት፡፡ ታዲያ ለዚህ ስጋና ደማችን ለምሳሌ የእንስሳትን ስጋና ደም ስንበላና ስንጠጣ አካላቸው በኛ ነው የሚኖረው፡፡ አይደለም? የበላነው አካላችንን ነው የሚኾነው፡፡ በእኛ ያድራል፤ ይኖራል፤ በሕይወት ይሳተፋል፡፡ ይሄው ነው፡፡ ስጋውን የሚበላ፣ ደሙን የሚጠጣ አድርጎ እንደ መልከ ጼዴቅ በኾነች ሥርዓት በሕብስትና በወይኑ አካሉን ሰጠን፡፡ ሰው ቆረበ ማለት የጌታን አካል በውስጡ አኖረ ማለት ነው፡፡ ቃሉም ያንን ነው የሚለው፤ ስጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ እኔ በሱ እኖራለው እሱም በእኔ ይኖራል ይላል፡፡ ፫. ትንሳዔው የዘራነውን ነው እንዲበቅል መቼም የምንጠብቀው፡፡ ያልዘራነው አይበቅልም፡፡ ለዚህ ነው ጳውሎስ ሞቱን በሚመስል ሞት ከተባበርን ትንሳዔውን በሚመስል ትንሳዔ እንተባበራለን የሚለው፡፡ ልብ እናድርግ፡፡ ከላይ ያየናቸው ቃሉ የተሰጠው፣ አካሉ በስንዴና በወይኑ ኪዳን የታደለው ከሞቱ በፊት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ለሞት የታዘዘው ወይም ከመስቀሉ በፊት ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ያስተማረውና ስጋ ደሙን የሰጠው፡፡

  • 21 мар.5 7435523

    ሕይወት እስከቀጠለ ድረስ ትውልዶችም ይቀጥላሉ፡፡ ሥልጣኔዎች ዕድሜያቸውን ስለጨረሱ መወለድ የሚያቆሙ ሰዎች አይኖሩም፡፡ ፍጥረት ይቀጥላል፡፡ ይህ ከኾነ የዘመኑ ሀሳብ እየወደቀ ባለበት አንጻር እየተነሳ ሊመጣም ግድ የሚለው ሥርዓት መኖር ይገባዋል፡፡ ሽግግር በዚህ መካከል አለ፡፡ ልብ እንስጥ፡፡ ልብ እንበል፡፡ ሥልጣኔ የሚነሳው ከሰው ነው ፤ መንፈሳዊ መሠረትም ቢኖረው፡፡ ስለዚህ የሚመጣውም ነገር የሚወጣው ከእኛው ነው፡፡ እሱም ሲቀር እየፈረሰ ያለውን ደሞ መቋቋም የእያንዳንዳችን ነው፡፡ ተጠባቂ ተዓምር የለም፡፡ ምን እናድርግ ስለዚህ? ሦስት ነጥቦችን በአጭሩ፡፡ ፩. ልብን መታዘዝ እውነት በሰው ልብ አለች፡፡ የመገለጧ አድማስና ከፍታ ቢለያይም እኛ ውስጥ አለች፡፡ ስለዚህ ነው ስንዋሽ ኹሌ ውስጣችን የሚያውቅብን፡፡ ከራሱ መደበቅ የሚችል አለ? በኛ ኹሌ እውነታውን ብቻ የሚናገር፣ የሚመራ አለ፡፡ ልቦና እውነተኛው ሀሳባችን ነው፡፡ እሱን መታዘዝ ከውስጣዊ ቀውስ ለመዳን ግድ ይላል፡፡ በተረበሸው መካከልም ሰላም የመኾኛው መንገድ ነው፡፡ አይብራራም፡፡ በቃ ግብር የሚገቡት ነው፡፡ በነገራችን ቂምና እውነት በአንድ ልብ ውስጥ አይኖሩም፡፡ ያለብን ቂም ካለ እንተው፡፡ ፪. ማሕፀኑን መፈለግ አስቀድሞ አላልንም? ሀሳቦች ናቸው ሥርዓት የሚዘረጉት፡፡ አኹን በዙሪያችን ተገንብቶ የምናየው ብዙ ሥርዓት፣ በፅንስ ዘመናቸው የሚወጡና የሚወርዱ ሀሳቦች ነበሩ፡፡ እነሆ ተሻጋሪውን ሀሳብ የሚፈልጉ ብፁዓን ናቸው፤ ያስቀጥሉናልና፡፡ ከክርሰትናው እንግባ፡፡ በፊት በወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስን በወቅቱ ያገኙ ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ ብለን ነበር፡፡ አንደኞቹና የሚበዙት በዚህ ዓለም ሀሳብና ስለዚህ ሥርዓቱ ተወስነው የሚቀሩት ናቸው ብለናል፡፡ በሥጋቸው፣ ለሥጋቸው የሚያገኙቱ ናቸው፡፡ የሚያስፈልጋቸውን ካገኙ በኋላ "በሰላም ወደቤታችሁ ተመለሱ" የሚባሉት ናቸው፡፡ ስለዚህ ክርስቶስን ካገኙት በኋላ ወደቤታቸው ተመልሰዋል፡፡ በተገኙበት ዘመን ሥርዓትና እንደ ግልም በኑሮአቸው ሀሳብ የሚቀጥሉ ናቸው፤ እነዚህ አብዛኛውን የዓለም ሰው የሚወክሉ ናቸው፡፡ አኹን እዚህ የተጻፈው ራሱ አይኾናቸውም፡፡ ምክንያቱም ወደ ቤታቸው የሚኼዱ ናቸዋ፡፡ ወደነበረው ሥርዓት፣ ወደነበረው ሀሳብ የሚመለሱ ናቸው፡፡ 75% የዓለም ሕዝብ ናቸው፡፡ በቃ የሚበሉት ጋ፣ የሚጠጡት ጋ፣ ትዳራቸው ጋ፣ በጥቅሉ በሥጋ መቆየት የሚባለው ጋ ናቸው፡፡ ሁለተኞቹ ደሞ አሉ፡፡ በዋናነት ሐዋሪያት፡፡ በአስኳልነት ድንግል ማርያም፡፡ እነዚህ የሚከተሉቱ ናቸው፡፡ ከብዙሀኑ የወጡት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ወደቤት አይኼዱም፡፡ በኼደበት የሚኼዱቱ ናቸው፡፡ አበው ሐዋሪያትን ሲናገሩ በዋለበት የዋሉ፣ በአደረበት ያደሩ ይሏቸዋል፡፡ እነዚህ ካገኙት በኋላ ወደቤት (ወደነበሩበት) ስለማይመለሱ፣ ከነበረው ነገር ኹሉ እየወጡ እየወጡ የሚኼዱ ናቸው፡፡ ከነበረው ሀሳብ፣ ከነበረው አኗኗር፣ ከነበረው ከዘመኑ ነገር እየወጡ ይኼዳሉ፡፡ ለምሳሌ ማቴዎስ አስቀድሞ ቀራጭ ነበር፡፡ በነበረበት ዘመን ለነበረው የሮማ ሥርዓት ተገዢ ነበረ፡፡ እዛ ውስጥ ይመላለሳል፡፡ ና ተከተለኝ ሲለው፣ ከዚህ ውስጥ ነው የሚጠራው፡፡ ተይዞ ይኖርበት ከነበረው የግልም የማሕበረሰብም ሀሳብ ውስጥ ነው የሚጠራው፡፡ ዘመኑ ካመጣው ሀሳብም ውስጥ ነው ና የሚለው፡፡ ከዚያ ዘመን ሥልጣኔም ጭምር እንደማለት፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመኑ ከመገለጡ በፊት፣ በዘመኑ የነበረው በሮም ሥነ መንግሥት የሚመራው ሥልጣኔ ጊዜው እየጨረሰ መጥቶ ነበረ፡፡ ሮም እየደከማት ሳለ ነው የመጣው፡፡ ስለዚህ ተማሪዎቹን ተከተሉኝ እያለ ሲጠራቸው፣ በኋላ በነሱ በኩል አዲስ ለሚነሳው ሀሳብም ደሞ ነው የሚጠራቸው ማለት ነው፡፡ አስቀድሞ የነበረው ሥልጣኔ ሲወድቅ፣ ክርስትና ቀጣዩን ተረክቦ አዲስ ኾኖ ጀምሯል፡፡ በነዚሁ በተከተሉት ሰዎች ምክንያት፡፡ የምለው ግልጽ ነው? እነዚያ ወደቤታቸው የኼዱቱ ብዙሃኑ፣ በነበረው ሀሳብ መኖር ቀጥለዋል፡፡ ቀድሞ በተዘረጋው ሥርዓት ውስጥ ይመላለሳሉ፡፡ እነ ማቴዎስ ግን እንዲያ አይደለም፡፡ ወደ አዲስ ሥርዓት (ትንሳኤው፣ ዕርገቱ፣ በዓለ ሐምሳ) ሊኼዱ ተከትለውታል፡፡ ከዚያም ተከትለው ከደረሱበት ነጥብ ተነስተው የዓለምን ታሪክ ለውጠውታል፡፡ እነሆ አዲስ ሥልጣኔ፡፡ ያለንበት የአኹኑ ዘመናዊ ዓለም ሥልጣኔ እንኳ የክርስትና መነሳት ከተነሳባቸው ሦስት ተጠቃሽ መስንፈጠሪያዎች መካከል አንዱ ስለመኾኑ አንዘንጋ ፤እዚህም ዳሰነው ነበር፡፡ ነጥቡ ምንድነው? ተከተለኝ የሚለው ያላቸው ናቸው ወደ ተሻጋሪው ሀሳብ የሚኼዱት፡፡ እንደውም በሥልጣን ከተናገርን ዓለም የቀጠለው በክርስቶስ ትንሳኤ ምክንያት ነው፡፡ አዲስ ነገር የሚመግቡን በአንድም በሌላም ትንሳኤውን ያገኙት ናቸው፡፡ ትንሳኤ ለእኛ መገለጥ ማለትም ነው፡፡ የሳይንሱም አብዮት እንኳ ከራሱ አልነቃም፡፡ ዞሮ 'ተከተለኝ' ወሳኝ ጥሪ ነው፡፡ ይሄን የሚሰሙት ርሃብ ያለባቸው ናቸው፡፡ ወደ ውስጥ መጥለቅን የሚነኾልሉበት ናቸው፡፡ ተሰርቶ ከመጣው ጀርባ ሠሪውን የሚያስሱሱቱ ናቸው፡፡ በራሳቸው ለመቆም ጥልቅ መሻቱ ያላቸው ናቸው፡፡ ወደ ሰው፣ ወደ ትውልድ የሚኾንን ነገር ለመስጠት ራሳቸውን ከልብ የሰጡቱ ናቸው፡፡ የቀደመውን ለመተው ድፍረቱ ያላቸው ናቸው፡፡ አስኳሉ ጋ ለመድረስ ናፍቆቱ ያላቸው ናቸው፡፡ ሕያው ነገር፣ እውነት ነገር፣ ጥበብ ነገር፣ መልስ ነገር ለማግኘት መቃተቱ ያላቸው ናቸው፡፡ ቃል የሚወዱ ናቸው፡፡ እኛስ? ፫. ሥጋው ደሙ "ቃሉን ተምረው ሥጋው ደሙን ቢወስዱ ሚሥጢር ያቀብላልና..." ይላል የአበው ትርጓሜ፡፡ የላይኛዎቹ ኹለት ነገሮች ጋ ያለ ሰው፣ የበጉን ማእድ ለአእምሮዉ ብርሃን ይውሰድ፡፡ ትንሳኤ መገለጥ ነው አላልንም? ሥጋው ደሙ የሚነሳው እውነት የሚቀበርበት ነው፡፡ ጳውሎስ እንደነገረን በጥምቀት (በቃሉ፣ በኑሮ) እና በሥጋው ደሙ በኩል ከክርስቶስ ጋ ከተቀበርን፣ እንዲሁ ከክርስቶስ ጋ እንነሳለን፡፡ በኛ የሚነሳው እውነቱ መገለጥ ነው፡፡ ይህም አይብራራም፡፡ ማየትን ያዩበታል እንጂ ምን ያብራሩታል? እንግዲህ ምን እንላለን? የጀመርነውን ጨርሰናል፡፡ አንድ ነገር የምንናገረው፣ አኹን ያለንበት ዓይነተ ብዙ ቀውስ ኹሉን አቀፍ ነው፡፡ ሰዎች እነሱ ብቻ የሚናወጹ አይምሰላቸው፡፡ እርግጥ ውጊያውም ረቂቅ ነው፡፡ ዘመኑ የታደሰ አእምሮ ይፈልጋል፡፡ ተስፋ ባለዋጋ ነው፡፡ ደሞስ የተነቃነቀው ነገር ኹሉ መጽናቱ ካልኾነለት ወልቆ ይለይለታ፡፡ በርታ፡፡ በርቺ፡፡ እንበርታ፡፡ በተሻለው ያቆየን፡፡

  • 21 мар.4 3832815

    የዘመንን እርጅና እንዴት እንለፍ? ይሔ ዓለም የበርካታ ሥልጣኔዎች ድምር ነው፤ ከእነሱ ተሰርቷል፡፡ እነሱም በየዘመናቸው ተነስተው፣ አብበው፣ አፍርተው፣ ጨርሰዋል፡፡ እርግጥ ጥቂቶች አሉ፤ በተለይ መንፈሳዊው ነገር ማእከላቸው፣ ኀይላቸው የኾኑ ሥልጣኔዎች ጨርሰው አይጠፉም፡፡ ይቆያሉ፡፡ ተለውጠው ወይ ተሰውረው ወይም ተወስነው ይቀጥላሉ፡፡ ያለንበት ይህ የዘመናዊው ዓለም ሥልጣኔ እንደጀመረ መጠን ደሞ እየጨረሰም ነው የሚሉ ሀሳቦች ከየአቅጣጫው ይነገራሉ፡፡ በተለያየ ማስረጃና ማስተንተኛ የተለያዩ ሰዎች እንደዚህ ይላሉ፡፡ በእርግጥ እኛም ከውስጡ ነንና (እሱኑ ነንና) ዙሪያውን ስናየው ልናየው የምንችለው ብዙ ነገር አለ፡፡ የታሪክና የማሕበረሰብ ጥናት ባለሙያዎች 'አንድ የዓለም ሥርዓት ውስጣዊ መፍረሶቹ ተሰበስበው መላውን ግንባታ ወደሚጥሉበት ነጥብ በመጨረሻም መድረሳቸው አይቀርም' ይላሉ፡፡ መውደቅ የሚጀመረው ከውስጥ ነው፥ ነው ነገሩ፡፡ ወንጌልም እንደዚያ ትላለች፡፡ የሚያረክሰው ከውስጥ ነው የሚወጣው፡፡ ሌላው ባለሙያዎቹ እንደሚጠቁሙት የመፍረስ ሂደቱ ሥልጣኔው በአንድ ወቅት ተነሥቶባቸውና ተመሥርቶም ዓምድ አድርጎ የቆመባቸውን ምሶሶዎች በመናድ እንደሚከናወን ይገልጻሉ፡፡ ለምሳሌ እንየው፡፡ ያለንበት ዓለም አቀፉ ምዕራብ መራሹ ሥልጣኔ በአጀማመሩና በጉልምስናው የተጠመቀው ከአራት ዋና ዋና አብዮቶች እንደነበረ ከዚህ በፊት ዳሰናል፡፡ በነዚህ አብዮቶችም ውስጥ የተገለጠው ሀሳብና ከዚያም ወጥቶ የተቀረጸው መዋቅር፣ የዚህ ሥልጣኔ ካስማዎች ናቸው፡፡ ከመስፋፋት ዘመን የተገኘው የጥቅልዮሹ አብዮት (Globalization)፣ የሳይንስ አብዮት፣ የአብርሆት ዘመን የአስተሳሰብ አብዮትና የኢንዱስትሪው ዘመን አብዮት የዚህ ዘመናዊው ሥልጣኔ መቆሚያ ናቸው፡፡ ከነዚህ ተሰርቶ ፋፍቷል፡፡ ስለዚህ ወደ ውደቀቱ መገስገስ ጀመረ ከተባለ፣ መብረክረክ የሚጀምሩት እነዚሁ መቆሚያ ጉልበቶቹ ይኾናሉ፡፡ የዚህን እንዴትነት ሰዎች በኑሮም፣ በሚዲያም ጊዜ ሰጥተው ቢፈትሹ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለመጥቀስ ያህል ግን አንዳንዶቹን በገረፍታ ብናወራቸውስ? 1. አልቦ ፍትሕ ዕድገት (Economic Inequality) በተለይ በከተሜው ዓለም የምናውቀው የኢኮኖሚው ሥርዓት፥ ከጥቅልዮሹ፣ ከሳይንሱና ከኢንደስትሪው ከነዚህ 3 አብዮቶች እንደተደራጀ ይታወቃል፡፡ ካፒታሊዝም አእምሮዉ ነው፡፡ እኛም በዚያ ውስጥ ገንዘብን መተሳሰሪያ አድርገን እንኖራለን፡፡ እንሰራለን፡፡  ታዲያ ይሄ ጥልፍልፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት፣ አድሎቱ ለላይኛው እርከን ተቀማጮች ነው፡፡ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ለሥርዓቱ ተጨማቂ ፍራፍሬ ነው፤ ወዙን፣ እውቀቱን፣ ኀይሉን ይገብራል፤ ነገ ተመልሶ እንዲመጣ የሚያረገውን ያህል ይከፈለዋል፡፡ በአጭሩ ድሀው እጅግ ብዙ ነው፤ የዓለምም ሐብት በጥቂቶች ይዘወራል፡፡ ፍሰቱ ፍትሕ አልባ ነው፡፡ ይሔ በሂደት ሕዝቦች ላይ ሥነ ልቡናዊም፣ አካላዊም ድቀት እያመጣ ይታያል፡፡ ለመኾኑ ድህነት ግን ምንድነው? ሐብታምነትስ? በነገራችን 2ቱም ተፈጥሮ ውስጥ የሉም፡፡ 2. የተፈጥሮ ሐብት ብዝበዛ (Environmental degradation) ከላይ የጠቀስነው ግዙፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት፣ ጥሬ ዕቃው ያው ተፈጥሮ ነው፡፡ አለበዚያ ከየት ያመጣል? ወደ ኢንደስትሪዎች ምድጃ የምትጣደው ተፈጥሮ ናት፡፡ ሥርዓቱ ከአግበስባሽነቱ የተነሳ በቃኝ አያውቅም፡፡ ሰንበት የለውም፡፡ ያመርታል፤ ያመርታል፤ ያመርታል፡፡ በዚሁ አንጻር የተፈጥሮንም ሐብት እያወጣ ይጠቀማል፡፡ ገጠሮችን የማከተሙ ሥራ (urbanization) ሚዛን መጠበቂያ የለውም፡፡ ስለዚህ ከአየሩ እስከ አፈሩ ኹሉም ተለውጦአል፡፡ የምንበላውና የምንጠጣው ጭምር፡፡ አስተሳሰባችንም እንዲያው ነው፡፡ እና አከባቢውን ያልጠበቀ፣ ከተፈጥሮ ያልታረቀ ሥልጣኔ ውድቀቱም ከዚያው ዘንድ ይደገስለታል፡፡ 3. ሕይወት አልባ ተቋማት ሀሳቦች ይነሳሉ፤ ከነሱም ዘንድ ሥርዓቶች ይዘረጋሉ፡፡ ተቋማት እነዚህን ሥርዓቶች የሚያስፈጽሙ ቅርጾች ናቸው፡፡ ይኹንና ሥልጣኔ ዕድሜውን ሲጨርስ የተነሳባቸው ሀሳቦች ያረጃሉ፡፡ ያኔ ተቋማት ሥጋቸው ብቻ ይቀራል፡፡ ነፍስ የላቸውም፡፡ ይሔን ከፖለቲካው እስከ ማሕበረሰብ ተቋማት ድረስ ዛሬ ላይ ማየት ነው፡፡ ከሕዝብ ልብ ተለያይተዋል፡፡ የሚገርመው ቤተ እምነታዊ ተቋማትም የዚሁ ገፈት ተቃማሽ ኾነው መታየታቸው ነው፡፡ ይልቁን እንደውም ባይብሱ ነውን? መከዳው በመዋቅር የለም፡፡ 4. የሕልውና ትርጉም መጥፋት ሰው የሚኖርለት ነገር ያሻዋል፡፡ ነፍስ ስላለቺው በእንጀራ ብቻ መኖር አይችልም፡፡ የሕልውና ጥያቄ አለበት፡፡ ምንድነው ሰው መኾን? ይህ ዘመናዊው ሥርዓት፣ ማሰቢያ ልቡ ሳይንስ ነው፡፡ የአብርሆቱ ዘመን አመክንዮአዊነት ደሞ ናላው፡፡ ችግሩ ሳይንስ ወደ ውስጥ ቅጥር አይዘልቅም፡፡ ሥጋን እንጂ ተስፋን አይመረምርም፡፡ ምክንያታዊነትም በበኩሉ ኹሉን አይበይንም፡፡ ሕይወት ከነዚህ ትሰፋለች፡፡ እነ ታማኝነት በሳይንስ አይለኩልንም፡፡ የአብርሆቱ ዘመን የአስተሳሰብ ንቅናቄ እንዳለው ግለሰባዊነት የራሱ ጥቅም ቢኖረውም፥ የጋራ ከተማና የሰውነት ግብም ያስፈልገን ነበረ፡፡ ድብርት፣ ግራ መጋባት፣ መሄጃ ማጣት፣ ባዶነት አኹን ሕዝባዊያን ናቸው፡፡ በመዝናኛ፣ በወሲብ፣ በዐመፃ የምንታገላቸው፡፡ 5. ቴክኖሎጂያዊ ጥገኝነት ቴክኖሎጂ የዘመኑ ሥልጣኔ ትንፋሽ ነው፡፡ ቢቋረጥ ብዙ ነገር ይሞታል፡፡ በኢንደስትሪው አብዮት በኩል ከተፈጥሮ ስንርቅ የተቀበለን ቴክሎኖጂ ነው፡፡ ነገሩ ወደ ሥነ ልቡናችንም ሠርጿል፡፡ አኹን ሥልካችን ሥልክ ብቻ አይደለም፤ ሥራ ቦታ ነው፣ እምነት ቦታ ነው፣ የትዳር ቦታ ነው፣ የዕውቀት ቦታ ነው፡፡ ውስጡ ነን፡፡ ሥጋችን ነው መሬት የረገጠው፤ ስብእናችን ዲጂታሉ ውስጥ ነው፡፡ ትኩረት እየሸጥን አለን፡፡ ስለ መረጃ ጎርፍ፣ ስለ እውነተኛና ሐሰተኛ ዕውቀት መደበላለቅ፣ ስለ በብረት ተገናኝቶ በልብ ስለመለያየት፣ ስለ ሳይበር ጥቃት፣ ስለ AI ሰውን ተኪነት አልዘረዘርንም፡፡ ሌላው የትርምሱ አካል ቢኾንም፡፡ 6. ራእይ ማጣት አንድ ግንባታ ሲጀምር በትጋትና በሕግ ነው የሚጓዘው፡፡ ተፈላጊው ነገር ከተገነባ በኋላ ሌላ የሚገነባ ሀሳብ ከሌለ በዕረፍት ስም እናጠፋለን፡፡ ራእይ ነው ቀጣዩን ነገር የሚያስቀጥለው፡፡ ያለእሱ አንሄድም፡፡ እንቆማለን፡፡ ይሄም የ500 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ሥልጣኔ፣ ከውጥኑ እስከ ከከፍታው በታላቅ ትጋትና ውጥረት ሲገነባ ቆይቷል፡፡ ማፍራት ያለበትን ኹሉ አፍርቷል፡፡ መሠረቱን የጣለው በሳይንስ ነውና በተለይ በሚታየው በኩል ብዙ ነገር ሰርቷል፡፡ ነገር ግን እርጅናው ሲመጣ ቀጥሎ የሚወስደውን ራእይ አልተለመም፡፡ አኹን የዓለምን መንግሥታት ሰብስበን ለመኾኑ ዜጎቻችሁን ወደየት እየመራችሁ ነው ቢባሉ መልስ የላቸውም፡፡ ይሄ ሥልጣኔ የራሱ ከነዓን ጋ ደርሶአል፡፡ ስለዚህ ሙሴው ሞቶአል፡፡ እርግጥም ሕግ ከላይ እስከታች ሞቶአል፡፡ ከትንንሽ እስከ ትልልቅ ድረስ ያሉ ሕግጋት በጠመንጃ ነው የሚጠበቁት፡፡ ወይም በመደለያ፡፡ ይሄ የትም ያለመኼድ ቀንደኛ ምልክት ነው፡፡ ስለዚህ ምን እናድርግ? ብዙ ነገሮችን ስለ ዘመናዊው ዓለም ሥርዓት እየጠወለገ መኼድ ማውራት ይቻላል፡፡ ውስጡ ስላለን እኛም እየሰማነው ነው፡፡ ምን እናድርግ?

  • Live stream finished (56 minutes)

  • Live stream started

  • 20 мар.4 945169

    'ቃል ተምረው ሥጋው ደሙን ቢወስዱ ምሥጢር ይገልጻልና ...' ፕሮግራማችን አሁን ይጀምራል፡፡ ተሳትፎ ሀሳብና ጥያቄ ከአስተያየት መስጪያው በማስቀመጥ አጋሩን፡፡ ሌላው፣ ስለ ቀጣዩ ዘመን ምን እናድርግ? እና የሚቀጥለውን ዘመን እውነታ የተሸከሙ ሰዎች እነማን ናቸው? የሚሉ ጥያቄዎችን ጥቆማ የሚሰጥ ጽሑፍ ከዚሁ ውስጥ ታገኛላችሁ፡፡ እዩትማ፡፡ https://t.me/Bemalda_neku?livestream=82d1f13be7691a4300

  • Live stream scheduled for Mar 20 at 17:00

  • 20 мар.4 829244

    የነገውንና የመጨረሻውን ፕሮግራም በዛሬ ተቀጥሯል፡፡ እያለፍንበት ባለው የዘመን ነውጥ ውስጥ፣ ወይም ያለንበት የዘመናዊው ዓለም ሥልጣኔ በውድቀት ሂደቱ ውስጥ ሳለን እኛ ምን እናድርግ? ማታ 2:00 ላይ እንገናኝ፡፡ የሚቻላችሁ ታደሙን፡፡ https://t.me/Bemalda_neku?livestream=82d1f13be7691a4300

  • 15 мар.6 1064116

    ያረጀው ይህ ዘመንና እኛ

  • Live stream finished (2 hours)

  • 14 мар.6 8012811

    ፕሮግራሙ ጀምሮአል፡፡ ተሳትፎ በአስተያየት መስጪያው መስጠት ይቻላል፡፡ "ሌላም ሁለተኛ መልአክ። አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች እያለ ተከተለው።" (የዮሐንስ ራእይ 14:8) https://t.me/Bemalda_neku?livestream=5cebe85c4a9f1d0886

  • Live stream started

  • 14 мар.6 523397

    ሰውን የሚጥለው ከሰው ውስጥ የሚወጣው ነው፡፡ ማር. 7፥20 ከሰውም ለሚገኘው ሥልጣኔ አካሄዱ እንዲሁ ነው፡፡ አንድ ሥልጣኔ መውደቅ የሚጀምረው ከውስጡ ነው፡፡ ቀጣዩም እንዲሁ መነሳት የሚጀምረው ከውስጥ ነው፡፡ ከእኛ ውስጥ፡፡ የቀጣዩ ዘመን ተስፋ በኛም እጅ ነው፡፡ ዛሬ ስለዚህ ነገር እናወጋለን፡፡ ዘመኑን እንዴት እንለፈው? ማታ ታደሙና፡፡ 1:00፡፡ https://t.me/Bemalda_neku?livestream=5cebe85c4a9f1d0886

  • Live stream scheduled for Mar 14 at 16:00

  • 12 мар.6 087346

    ከዚሁ ጋራ በተገናኘ፣ የዛሬው ዘመን የሥልጣኔ ሞተር እንደኾነ የሚነገርለት እጅግ በዳበረና በተወሳሰበ መንገድ የሚከናወነው ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ሥርዓት፣ ግዙፍ ግንባታውን ከዚያ የኀሠሣ ዘመን ላይ ጀምሮታል፡፡ 1.3.2 የሳይንስ አብዮት - The Scientific Revolution ያለፉትን 300 ዓመታት ዘረፈ ብዙ ለውጦች ያለ ሳይንስ እንዴት ማሰብ ይቻላል? ሳይንስ የዚህ ያለንበት ዘመናዊው ዓለም፣ ማሰቢያ ልብ ነው፡፡  'In the 16th–17th centuries, a new method of understanding reality emerged.' ሳይንስ መልክና ቅርጽ አግኝቶ ከተገለጠበት ከዚህ ክ/ዘመን አስቀድሞ፣ የሰው ልጆች ትውልድ እውነታን የሚመለከትበትና የሚቀበልበት መንገድ ነበረው፡፡ እነዚህ መንገዶቹም በዋናነት ከሃይማኖትና ከባሕል ድምር ዕውቀቶች ውስጥ ይመነጩ ነበር፡፡ የሳይንስ ጅማሬ፣ ይህን የአስተሳሰብ አካሄድ ሥር ነቀል ሊባል በሚችል መልኩ ለውጦታል፡፡ ለውጡ በሂደት ወደ ሥነ መንግሥታት ውቅር እየሰፋና እየሰረገ ሊኼድ ችሏል፡፡ የዛሬው ዘመን ታላላቅ ትሩፋቶች የሚባሉት ቴክሎኖጂ፣ ዘመናዊ ሕክምናና ዘመናዊ ሥርዓተ ትምሕርት የዚህ አብዮት ፍሬዎች ወደመኾን መጥተዋል፡፡ በነገራችን ላይ ሳይንስ ሙሉ ለሙሉ ከመንፈሳዊው ዓለም ተነጥሎ የተነሳና የሚኖር የሚመስላቸው ብዙ የዋህ ሰዎች አሉ፡፡ ይኹንና የሳይንሱ ዓለም ቀደማይ ሊቃውንት የሚባሉትን ሰዎች የጀርባ ሕይወት መፈተሹ ብቻ የሚጠቁመን ነገር አለ፡፡ ኾኖም እንጂ ዝርዝሩ ከዚህ ርዕስ ውጪ ይዞን ስለሚወጣ ወደ ቀጣዩ ነጥብ ይልቁን እንሸጋገር፡፡ 1.3.3 የአብርሆቱ ዘመን (The Enlightenment period) እነሆ 18ኛው ክ/ዘመን፡፡ እነሆ የምክንያት ዘመን፡፡ የሥነ ጥበብ ዘመን፡፡ የተነጥሎሹ ዘመን፡፡ ጥንቱን ከነሶቅራጠስ ጊዜ (axial age) ዘሩን የሚቆጥረው የአስተሳሰብ ዘዬ፣ በፈረንሳዩ የአብርሆት ዘመን አባት በሚሉት ሬኔ ድካርትና መሰሎች በኩል ዘመናዊ ፍልስፍና ተብሎ አኹን የሚመደበውን የአተያይ ባሕል፣ ልክ በዚህ ወቅት ላይ ተወልዷል፡፡ ከሳይንስ መጀመር፣ ከፕሮቴስታንት አብዮትና ከሰብእና ሕዳሴ (Renaissance Humanism) ተጣምሮ እንደተሠራ የሚነገርለት ይህ የአብርሆት ዘመን፣ በሰው ልጆች ታሪክ ወሳኝ ከሚባሉ የአስተሳሰብ ንቅናቄዎችና እጥፋቶች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ዋና ዋና መገለጫዎቹንና አድራሻዎቹን ብቻ እንደሚከተለው እንጥቀስለት፡፡ • በተነጠለ አእምሮና አኗኗር የመገኘት መብት (Individualism which later proceeds liberalism) • ከሃይማኖታዊ ሥርዓቶችና ባሕሎች ተጽዕኖ የመላቀቅ "ነጻነት" (To live in non religious themes) • የሥልጣን መዋቅርና የሥነ መንግሥት ተዋረድ ክፍፍል (The birth of democracy and other poltical systems) • በግለሰቦች መብት፣ ሀሳብና አቅም ላይ ትኩረት መስጠት (focuses on human beings and their potential for achievement) • የጥልቅ ኪነ ጥበብና ተያያዥ ሥራዎች ማየልና የሕትመት መሣሪያዎችን መምጣት ተከትሎ የፈጠራ ውጤቶች መብዛትና መስፋፋት የዛሬው ጊዜ በተለይ "ያደጉ" ሀገራት የሥነ ልቦና ድርጅት፣ በዚህ የአብርሆት ዘመን መንፈስ እንደሚመራ ጥሩ ተመልካች ብቻ መኾን በቂው ይመስላል፡፡ 1.3.4 የኢንደስትሪው አብዮት (The Industrial Revolution) ዛሬ ዙሪያ ገባውን አጥለቅልቆት የምናየው የቴክኖሎጂ ወንዝ፣ ከዚህ በአራተኛ የዘመናዊው ዓለም የግንባታ ሂደትነት ከሚጠቀሰው ክ/ዘመን ውስጥ መንጭቷል፡፡ የዚህ ክ/ጊዜ ልዩ መገለጫዎች ከሚባሉ ለውጦች መካከል መሠረታዊው፦ የከሰል፣ የጋዝና የኤሌክትሪክ በኋላም ኒኩልየር ኃይላትን በሳይንሳዊ ግንዛቤዎች በመጠቀም የተፈጥሮ ሐብቶችን ወደ ሰው ሰራሽ ምርቶች የመቀየር እንቅስቃሴው ነበር፡፡ በመኾኑ ይህንን ሥራ የሚያከናውኑ ፋብሪካዎች በየቦታው እየተተከሉ መምጣታቸውን ተከትሎ፣ በዚያ ዙሪያ ሰዎች ዛሬ ሰፍረው የሚኖሩበትና እኛም አኹን ከፍታውን አግኝቶ የምናውቀው የከተማ ሥርዓት መስፈንጠሪያውን ከዚህ ዘመን ላይ አድርጓል፡፡ ሌላው የኢንተርኔትና የትራንስፖርት ሥራዎች በላቀ እምርታ በዚህ ዘመን ላይ መከሰታቸውን ተከትሎ፣ ኹሉ ነገር በሚያስገርም ፍጥነት ወደ ሚከናወንበት የውክቢያ አኗኗር የሰው ልጆች መግባት ጀምረናል፡፡ ምሁራኑ የሰው ልጆች አእምሮና ሥልጣኔውም ጭምር አልተገማች ፍጥነት ያሳይ የጀመረው ከዚህ የ18ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ጊዜ ጀምሮ ነው ይላሉ፤ human civilization began moving at an unprecedented speed. እንግዲህ ዛሬ የምንኖርበት እጅግ ግዙፍና ውስብስብ ሥልጣኔ፣ በጣም በአጭሩ ትናንቱ ይሄንን ይመስላል፡፡ ነገርየው የታሪክ መረጃ ብቻ የሚመስላቸው ሰዎች አይጠፉም፡፡ ግን አይደለም፡፡ የዛሬው ከዕለት ተዕለት የኑሮ ትንንሽ ዘይቤዎቻችን አንስቶ እስከ ግዙፍ ተቋማዊ አስተሳሰቦቻችን የተቃኘነው በዚህ ትናንት ውስጥ ነው፡፡ የምናስበው፣ የምንበላው፣ የምንማረው፣ ቤተሰብ የምንመሠርተው፣... በአጠቃላይ "ኹሉንም" የመኖር ነገር የምናደርገው በዚህ ውስጥ ነው፡፡ ተወልደን የገባነው እዚህ ሥርዓት ውስጥ ነው፡፡ ምን ከዚህ የወጣ ነገር አለንና? ሐይማኖታዊና ባህላዊ ሀሳቦቻችን ራሱ በዚህ ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ በአእምሮና በሥጋችን ላይ የተቀመጠው ይህ የማይታይ አራት ማዕዘን፣ ልደቱና ዕድገቱ እንደዚህ በታሪክ እንዳየነው ተቀርጾአል፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ደሞ እንዳልነው ነው፡፡ ለኹሉ ጊዜውን ይጠብቅለታል፡፡ ቦ ጊዜ ለኵሉ፡፡ ለመወለድ ጊዜ ነበረው፡፡ ስለዚህ ለመሞትም ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ይኼ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለመወለድ የራሱ ዘመን ነበረው፡፡ በመኾኑ ለመሞትም ደሞ የራሱን ጊዜ እየጠበቀ ነው፡፡ እርግጥ እንደውም ነገረ ሞቱን ጀምሮታል፡፡ የኹሉም የሰው ልጆችን ጥያቄዎች መልስ ይዣለው ይል የነበረው ሥርዓት፣ ቅጠሎቹ የደረቁ ትልቅዬ ዛፍ ኾኖዋል፡፡ ይህ ራሳቸው የሥልጣኔው ባለቤት ነን የሚሉት ወገኖች፣ በራሳቸው መረዳትና ቋንቋ ይናገሩ የጀመሩት እውነታ ነው፡፡ አዎ፡፡ እየወደቀ ባለ ሥርዓት ውስጥ ያለን ዘመነኞች ነን፡፡ እርግጥ በዚሁ ትይዩ እየተነሳም ያለ ነገር አለ፡፡ ስለዚህ የሽግግር ወቅት ላይ ነን፡፡ አድራሻ ባይኖርም እየኼድን ነን፡፡ ጥቂቶች ወዴትነቱን ያውቁታል፡፡ አብዛኞቻችን አናውቀውም፡፡ እና የሽግግር ነውጥ ውጦን እንዲህ አለን፡፡ ኹሉ ነገር እንኳን ነክተነው ሳንነካው እየተናወጸብን ነው፡፡ ረግቶ መቆም አቅቷል፡፡ ከግለ-ሰብእ እስከ ዓለመ-ሰብእ ያሉ መሠረቶች ከሥራቸው ተነቃንቀዋል፡፡ ተቋማት ነፍስ አጥተው ቅርጽ ብቻ ኾነዋል፡፡ መረንነት አደባባይ ነግሧል፡፡ ቆንጆው ነገር ከመታየት ገለል ያለ ይመስላል፡፡ ኦናነት በቤትም፣ በከተማም ይደመጣል፡፡ ቀኖች አለ አቅጣጫ ዝምብለው ይሮጣሉ፡፡ ሕግ ከሕሊና አልወጣልን ብሎአል፡፡ ስለዚህ በጠመንጃና በስንት መደለያ ነው ተገቢውን ነገር የምናደርገው፡፡ ማሕበራዊ ሚዲያ ሀገራችን ኾኗል፡፡ በዚያ ትኩረት ይገዛል፤ ትኩረትም ይሸጣል፡፡ ኹሉ ነገር በንግድ ሀሳብ ይታሰባል፡፡ ሕዝባዊ ምስቅልቅል ውስጥ ነን፡፡ አልሰማነው እንደኾነ እንጂ "ባቢሎን ወደቀች ወደቀች..." እያለ ያለው መልአክ ከፊታችን ሮጦአል፡፡ ቅዳሜ፡፡ ማታ 1:00፡፡ ለቀጣዩ ርእስ እንገናኝ፡፡ አርጅቶ ስላለው ዘመንና ስለእኛ በውስጡ የማለፍ እንዴትነት አውርተን እንጨርሳለን፡፡ ያድርሰን፡፡

  • 12 мар.3 762157

    የዘመናዊው ዓለም ልደቱና ያለንበት እርጅናው መቼም ኹላችንም እስከዛሬ የመጣነውን ነን፡፡ ታሪካችንን ነን፡፡ የማንነታችን ትንታኔ በታሪካችን ውስጥ ነው፡፡ መጽሐፍ እንደሚለው እኛ የትናንት ነን፡፡ ማሕበረሰብእም ከዚህ የተነሳ እሱም የራሱ ትናንት አለው፤ የራሱ ታሪክ አለው፡፡ ስለዚህ በጥቅሉም ሲኬድ 'ዓለም' የምንለው አጠቃላዩ የጋራ ነገራችንም የራሱ ታሪክ አለው፡፡ የዓለም ታሪክ የየዘመናቱ ትውልድ ታሪክ ነው፤ እየተዋለድን በምንቀጥለው ባሕርይ በኩል የምንጽፈው ኑሮ አለ፡፡ አበው የሰው ልጅ በውጪና በውስጥ የተጻፈበት መጽሐፍ ነው ይላሉ በትርጓሜ፡፡ (ራእ. 5) 'ሰው' ሲሉ መላውን የሰውን ዘር ስለኾነ፣ ዓለምም መጽሐፍ ናት ስለዚህ፡፡ ገጾቿ የየዘመናቷ ትውልዶች ናቸው፡፡ ሕይወት እስከቀጠለም ድረስ ይህ እውነታ ይቀጥላል፡፡ ይህ በመጻፍ ሂደት ላይ ያለው አጠቃላይ ታሪካችን፣ ጉዞዉ በመዋለድ ባሕርያችን ላይ ይመካል፡፡ ወይም በሌላ አቀማመጥ፣ እየተዋለድን ስለቀጠልን ነው አጠቃላይ እንደ ሰው የሚነገረው ታሪካችን ቀጥሎ ያለው፡፡ ማንነታችን በመዋለድ የዘር ሕግ እየተተረተረ በታሪክ መገለጹን እስካሁን ቀጥሎአል፡፡ የመዋለድ ሥርዓታችን በባሕርያችን ውስጥ ካሉት አንዱ ከእፅዋት ባሕርይ የተዘረጋ ነው፡፡ ወንጌልን የሚተረጉም መንፈሳዊ ድርሳን ስለዚህ ነገር ሲናገር 'አዳም (የሰው ልጅ) በሦስት ኃይላት ጸና፤ በኃይለ ዘርዕ፣ በኃይለ እንስሳና በኃይለ ንባብ' ይለዋል፡፡ ኃይለ ዘርዕ የሚለው የአዝርዕትን ግብር ነው፤ የመዘራት፣ የመብቀል፣ የማፍራትና የመድረቅ ባሕርያቸውን፡፡ ይህን የባሕርይ ሥርዓት በእኛ ተፈጥሮ ውስጥ ስናየው የመፀነስ፣ የመወለድ፣ በዕድሜ የመቆየትና የመሞት ዑደታችን ኾኖ እናየዋለን፡፡ ትውልድ በዚህ መስመር ይመጣል፤ በዚሁ መስመር ይኼዳል፡፡ በነገራችን በመንፈሳዊው ታሪክ አዳምና ሔዋን የዛፍ ፍሬ በልተው ወደዚህ ዓለም ወረዱ የሚባለው የዚህ እውነታ ቅኔ ነው፡፡ ባሕርያችን ለዚህ ጥልቅ ሀሳብም ላለው ሥርዓት በመተዳደሩ በመዋለድ ሕግ ወደፊት እንቀጥላለን፡፡ ታሪካችንን እየጻፍን እናልፋለን፡፡ በየዘመናቱ ከእኛ የሚገለጡትም ሥልጣኔዎች ከእኛ የተነሳ በዚህ በዛፉ ባሕርይ ይመላለሳሉ፡፡ ይዘራሉ፤ ይበቅላሉ፤ ይለመልማሉ፤ ያፈራሉ፤ ይጠወልጋሉ፤ ደርቀው ይጠፋሉ፤ እንደገና ደግሞ ብቅ ይላሉ፡፡ በዓለም ታሪክ ታላላቅ የሚባሉ ሥልጣኔዎች በጊዜያቸው መጥተው በጊዜያቸው ኼደዋል፡፡ እርግጥ ኼደዋል ሲባል ሙሉ ለሙሉ አይጠፉም፡፡ ቅሪቶቻቸው በአንድም በሌላም ይቀጥላል፡፡ በዘመናቸው የገለጡት ሀሳብና ሥራ ሳይለወጥም ሆነ ተለውጦ ወደ ቀጣዩ ይሻገራል፡፡ ሽምግልና የልጅነትና የወጣትነት ድምር ዕውቀትም እንደኾነው፣ አኹን ያለንበት ሥልጣኔም ካለፉት የጥንትም የቅርብም ሥልጣኔዎች ተሰብስቦ ተሰርቷል፡፡ እ.ኤ.አ ፅንሰቱ በ1500 ዓ.ም እንደተጠነሰሰ የሚታሰበው የዛሬው ዘመን ግዙፍ ሥልጣኔ፣ በአንድ ዓይነተኛ መልኩ ከቀድምቶቹ ይለያል፡፡ በዓለም አቀፋዊነቱ! ኹሉም የጊዜው የሰው ልጅ ሊባል በሚያስደፍር መልኩ በዚህ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓትና ባሕሉ ተጠምቋል፡፡ በቂ ዝርዝሩ የዚህ ሥልጣኔ አንድ ውጤት ከሆነው ከመገናኛው መረብ በሚገባ የሚገኝ ቢኾንም፣ ለመቀንጨብ ያህል እንዲኾን ግን በዙሪያችን እንዲህ ከቦን የምናየው ዓለም አቀፍ ኑሮ አጀማመርና ሥሪቱ እንዴት ነው? የሚለውን በአጭሩ እንየው፡፡ ይጠቅማል፡፡ 1. ፅንስትና ልደት የታሪክ ምሁራን በጋራ እንደሚስማሙት፣ ደርሰን ያለንበት ዘመናዊው ዓለም ከ3 ዋና ዋና የዘመን አብዮቶች መሠረቱን ያነሳል፡፡ እርግጥ በማእከልነት የሚጠቀሰው ሦስተኛው የታሪክ አንጓ ነው፡፡ እኛም እዚህ የምንዳስሰው ሦስተኛውን የዘመን ገጽታ ነው፡፡ ኾኖም ኹለቱን መሠረቶቹን ግን በመጠኑ ጠቃቅሰናቸው እናልፋለን፡፡ እንጀምር፡፡ 1.1 የአክዚያል ዘመን - The axial age (800-200BCE) ካርል ጃስፐርስ (Karl Jaspers) የሚባል አንድ የጀርመን ፈላስፋና የታሪክ መርማሪ፣ ያለንበት ዘመናዊው ዓለም መሠረት ከዚህ ታላቅ የአስተሳሰብ ለውጥ ከተነሳበት የታሪክ ሂደት እንደሚመዘዝ ይሞግታል፡፡ ከክርስቶስ ልደት አስቀድሞ ከ800 እስከ 200 ዓ.ዓ ባለው ዘመን የነበረው ይህ ወቅት፣ በዓለም ታሪክ ውስጥ ታላቅ የሀሳብና የሃይማኖት አብዮት የታየበት ጊዜ ነበረ፡፡ ስማቸው ዛሬ ድረስ በጉልህ የሚነገርላቸው እንደነ ሶቅራጠስ በኋላ አፍላጦን (plato)፣ ቡድሃና ኮንፊሺየስ ከዛ ጊዜ ጀምሮ በአጠቃላዩ የሰው ልጆች የሥነ ዕውቀትና የሞራል እሳቤዎች ላይ ዓይነተኛ ለውጥ ያመጡ ሥራዎቻቸውን በዘመኑ ሊገልጹ ችለዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ዋና ዋናዎቹ የምሥራቁ ዓለም ሃይማኖቶች ማለትም ቡድሂዝም፣ ሂንዱይዝም፣ ኮንፊውሺያኒዝምና ዞራስትሪያኒዝም ልደታቸውን በዚያ ዘመን አግኝተዋል፡፡ ሌላው በነ ሶቅራጠስ በኩል የዛሬው ዘመን ፍልስፍና የሚባለው የአስተሳሰብ ዘዬም መነሻውን በግሪክ አድርጎ በወቅቱ ተጀምሯል፡፡ በተጨማሪም ክርስትናን ጨምሮ የኋላ ዘመን የአብርሃም ሃይማኖቶች መውጪያ የሚባለው የዕብራዊው ዓለም የነብያት ባሕልም ከጊዜው ዋና መልኮች ውሰጥ አንደኛው ነበር፡፡ የዚህ ዘመን ታላቅ የለውጥ ነጥብ ተብሎ የሚጠቀሰው፣ የሰው ልጆች ከላይ ከተጠቀሱት መነሻ እሳቤዎች በኋላ ከንግርታዊና ትውፊታዊ የአስተሳሰብ ክበቦች (mythical tribal thinking) ወጥቶ፣ ግለሰባዊ ንቃተ ሕሊና ላይ ወዳተኮሩ የሞራልና የምክንያታዊነት የአእምሮ መንገዶች መሸጋገሩ ነበር፡፡ የታሪክ ባለሙያዎች ነገሩን እንዲህ ሲሉ በአጭሩ ይገልጹታል - Modern human consciousness began here. 1.2 የክርስትና መነሣትና ያስከተለው አብዮት - The christian-Late Antique Transformation (1-6CE) ከክርስቶስ ልደት በኋላ በተለኮሰው የክርስትና ችቦ የተነሳ፣ ታላቂቱ የሮም ግዛት በ4ተኛው ክ/ዘመን ገደማ ክርስትናን ይፋዊ የመንግሥት ሃይማኖት ማድረጓ የዚህ ዘመን ታላቅ የለውጥ አቅጣጫ ነበረ፡፡ ዛሬ የምናውቀው የምዕራቡ ዓለም የሥነ መንግሥት፣ የአኗኗርና የዕውቀት ባሕል ከዚህ የሽግግር እጥፋት በኋላ ቅርጽና ይዘቱን እያገኘ ሊኼድ ችሏል፡፡ የኛይቱ ሀገር የወቅቱ የአክሱም ዘመነ መንግሥቷ ኢትዮጲያም በ328 ዓ.ም አከባቢ ክርስትናን በዐዋጅ ስለመቀበሏ አንዘነጋም፡፡ 1.3 ዘመናዊው ዓለም አቀፍ ሥርዓት - The Modern Global System (1500-1800CE) ዛሬ የምናውቀውና የምንኖርበት የአስተሳሰብ ሥርዓት መቼ ተወለደ ከተባለ፣ 1500ዓ.ም ተጠቃሹ ዘመን ነው! እነሆ የዛሬው ዘመን ብዙ ነገር፣ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ተጀመረ! የዛሬው ዘመን ዋና የመሠረት ድንጋይ የኾነው ይሄ ጊዜ፣ አራት ታላላቅ የለውጥ ደረጃዎችን አልፎ አኹን ያለበት ጋ ደርሷል፡፡ ተራ በተራ እንያቸው፡፡ 1.3.1 የመስፋፋት ዘመን - The Age of Exploration ከ1500 በፊት፣ የዓለም ትውልዶች በሮቻቸውን ዘግተው እንደሚኖሩ ጎረቤቶች አስቧቸው፡፡ አውሮፓ፣ አፍሪካ፣ የሩቅ ምሥራቁ ዓለምና ሌላውም የዓለም ክፍል በየተነጠለ ስፍራውና ባሕሉ ይኖር ነበር፡፡ ከዚህ ክ/ዘመን ወዲህ ግን የያፌት ልጆች (አውሮፓውያን) የተፈጥሮ ሃብቶችንና ግንኙነቶችን ያስተሳሰሩ ኀሠሣዎቻቸውን በመጀመራቸው፣ ዛሬ ፈፍቶና ከጡዘቱ ወጥቶ የምናውቀው ዓለም አቀፉ ትስስር (Globalization) በዓለም የታሪክ እርሻ ላይ መብቀሉን ጀምሯል፡፡

  • 8 мар.4 566558

    በሌላ አነጋገር፣ በዚህ ዘመን የተገኘን ትውልዶች ብንኾንም፣ ባለፉት ዘመናት የነበሩትን ተቀባብለው እዚህ ያደረሱንን ትውልዶች አናውቃቸውም፡፡ በሥጋ አይደለም፡፡ ነገሩ በሥጋ እንወቅ ብንልስ እንዴት እንችላለን? ሀሳቦቻቸውን ነው የምንለው፡፡ ግን ቀድሞውኑ ፍላጎቱስ ከልብ አለን ይሁን? ለማንኛውም ወደ መጽሐፉ እንመለስና በአብርሃም የነበረቺው ሀሳቡ፣ በኋላ ከፊታቸው በሥጋ ቆሞ የሚያናግራቸው የእውነት ቃልም ነው፡፡ ለዚህ ነው ቃሌ በእናንተ ስለሌለ የአብርሃም ዘር እንጂ ሥራው የላችሁም ይላቸው የነበረው፡፡ ወደ ነጥባችን ዘወር ስንል፣ ይሄ ዘመን ያለፉት ዘመናት ስብስብ ነው፡፡ ተከታትሎ ያለንበት ጋ መጥተናል፡፡ ስለዚህ በዙሪያችን በተለያየ ዘርፍና መልክ የምናያቸው ብዙ ነገሮች የእስከዛሬ ትውልዶች ድምር ውጤቶችም ናቸው፡፡ ያ ብቻ አይደለም ደግሞ፡፡ ስለዘመናት ስናወራ ስለ ሥልጣኔዎች አለማውራት አንችልም፡፡ ምክንያቱም የየዘመናቱ መልኮች እነሱ ስለኾኑ፡፡ ሥልጣኔ ግን ምንድነው? ለአንድ ሰው ዕድሜ ለትውልድ ዘመን እንዳልነው አካሄድ፣ ለአንድ ሰው መክሊት የምንለው በሕዝብ ደረጃ ሲገለጽ ሥልጣኔ ይሰኛል፡፡ ሥልጣኔ የሕዝቦች መክሊት ነው፡፡ ከዚህም የሚጨመሩ ዝርዝር ፍቺዎችም፣ መገለጫዎችም ስላሉት መሻቱ ያላችሁ ልትፈላልጉበት ትችላላችሁ፡፡ እንዳይረዝም ነገሩን እናሳጥረውና፣ አኹን ያለንበት የዘመኑ ሥልጣኔ ሥርዓቱ ዓለም አቀፋዊ መኾኑ እስከዛሬ ከነበሩት በዋናነት ይለየዋል፡፡ ጥንስሱን ከምዕራቡ የዓለም ክፍል ያደረገው፣ ከ16ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ የተወለደው የዚህ ዘመን ሥልጣኔ፣  ዓለምን (ሀገራትን ቢሉም) በሀሳቡና በሥርዓቱ አጥምቆ ወደ አንድ መልክ አካትቷል፡፡ የቴክሎኖጂ አብዮት ዋነኛው መገለጫው ነው፡፡ በሃይማኖት፣ በባህል፣ በሥነ መንግሥታት ውስጥ የራሱን መልኮች በተለያየ ጎዳና አሥርጿል፡፡ እና ቦ ጊዜ ለኩሉ ብለንም የለ? ሥልጣኔም ያው ከጊዜ በታች ነው፡፡ ማለት፡ አንድ ሥልጣኔ የሚጀምርበት፣ የሚፋፋበት፣ ከዚያ የሚወድቅበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ እዚህ ለማለት የምንሞክረው አኹን ታዲያ፣ ከላይ የጠቀስነው በዘመኑ ውስጥ ሰፍኖና ገኖ ያለው አውሮጳ መራሹ ሥልጣኔ ጊዜውን ጨርሷል ነው፡፡ ሰለዚህ እየወደቀ ነው፡፡ በመፍረሱ ዑደት ላይ ነው፡፡ የዚህ ጊዜው ላይ ስለመኾኑ የሚናገሩ ብዙ ከግለሰብ እስከ ዓለም አቀፍ የሕዝብ ግንኙነቶችና ተቋማት ድረስ የሚታዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እነሱን ቀጣይ በሚኖረው ፕሮግራም እናወራቸዋለን፡፡ ብቻ አይደለም፡፡ በዚህ እየፈረሰ ባለ የሥልጣኔ ሥርዓት ውስጥ ሳለን፣ እንዴት እንለፍ የሚለውንም በአቅማችን ለመጨዋወት እንሞክራለን፡፡ ከጠቀመ፡፡ እስቲ ያቆየን፡፡

  • 8 мар.4 5413415

    የአኹን ርዕሳችን ስለ ነገረ ዘመን ነበረ፡፡ ለመኾኑ ዘመን ምንድነው? ለግለሰብ ዕድሜ ያልነው በትውልድ አንቀጽ ሲኾን ዘመን ይባላል፤ ዘመን የትውልድ ዕድሜ ነው፡፡ ያው በነጠላም ዕድሜ ያልነው በስብስብም ዘመን ያልነው፣ ያው ጊዜ የሚባለውን ነው፡፡ ስለዚህ ጊዜ ራሱ ምንድነው? .. ጊዜ የፍጥረት ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ሁሉ የተፈጠረው ነገር ሁሉ በጊዜ ውስጥ ነው ያለው፡፡ በነርሱ ውስጥም ጊዜ ይገኛል፡፡ በፈጣሪና በፍጥረት መካከል ያለው አንዱና ዋናው ድንበር ጊዜ ነው፡፡ ማለት ሁሉ የተፈጠረው ነገር ሁሉ በጊዜ ውስጥ ሲኖር፣ ፈጣሪ ከጊዜም ውጪ ሁኖ ይገኛል፡፡ እንደውም ለራሱ ለጊዜ መኖሪያ ዓለሙ እሱ ነው፡፡ ፍጥረት ሁሉ ግን በጊዜ ሥር ይኖራል፡፡ እዚህ ጋራ 'ጊዜ' ስንል፣ በፀሐይ በጨረቃ በከዋክብት ዑደት የምናሰላውን የቁጥር ዕውቀት ማለት ብቻ አይደለም፡፡ እሱ ዕውቀት የተመሠረበት በተፈጥሮ ውስጥ ያለ፣ ከፍጥረታት ጀርባ የሂደትና ለውጥ ሕግ የኾነ መስመር አለ፡፡ እሱን ነው ጊዜ የምንለው እዚህ፡፡ መጽሐፍ ይላል፡፡ ቦ ጊዜ ለኩሉ፡፡ ለኹሉ የራሱ የኾነ ጊዜ አለው፡፡ ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ " መክ 3:2፡፡ ኹሉ በጊዜ ውስጥ ይኾናል፤ እየኾነም ነው፡፡ ሰውም በጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ጊዜም በሰው ውስጥ አለ፡፡ ስለዚህ ጊዜን ማወቅ ራስን ማወቅም ነው፡፡ የኾነ ከኛ ተነጥሎ ያለን ሩቅ ሀሳብ ማወቅ ማለት አይደለም፡፡ ተፈጥሮን ማወቅ ነው፡፡ ብቻ አይደለም፤ በተፈጥሮና በሥርዓቷ ውስጥ እንዴት እንደምንኖር ማወቅም ነው፡፡ የዚህ ነገር ክብደቱ ይታየን ይኹን? ጊዜ በእኛ ውስጥ ስላለ ነው የአካልና የአእምሮ ለውጦችን የምናከናውነው፡፡ በኛ ውስጥ ካለው የጊዜ እውነት የተነሳ ነው ሥጋዊውም ኾነ ሥነ ልቡናዊ ለውጦች በእኛ የሚታዩት፡፡ ለምሳሌ ሁላችንም በተፈጥሮ በኩል ተጉዘን ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሔዋን እንደርሳለን፡፡ ይሄ በኛ ውስጥ የተቀመጠ ጊዜ ስላለ ያከናወንነው ለውጥ ነው፡፡ እንዲሁ ከላይ መጽሐፍ እንዳለው ለመወለዳችን፣ ለማደጋችን፣ ለማርጀታችን የተሰጠ ራሱን የቻለ የየራሳችን ጊዜ አለን፡፡ እሱ መኖሪያ ዓለማችንም እኮ ነው፡፡ በወንጌል "ብርሃን ሳለላችኹ ተመላለሱ" የተባለው አንድም ይህን የየራሳችንን ጊዜ/ዕድሜ ሲናገረው ነው ይላሉ አበው፤ እውነት ነው፡፡ (ዮሐ. 12፡35) ይሔ ወደ አንድ ልናስተውለው ወደሚያስፈልግ ሀሳብ ቀጥሎ ይመራናል፡፡ ይሔውም ዕድሜ የየራሳችን ዓለም የኾነልን ጊዜ ከኾነ፣ በዚህ የጊዜ መስመር ላይ ተቸርችረው የተቀመጡ በራሳቸው ያሉ አንጓ ሀሳቦችና ሥርዓቶች አሉ የሚለውን ሀሳብ ነው፡፡ እነዚህ በጊዜ ውስጥ ተይዘው የተቀመጡ ሀሳቦች ስላሉ ነው በሂደት እየደርስን ስናገኛቸው የምናስባቸው፣ የምንኖርባቸው፡፡ ለምሳሌ በልጅነት ጊዜ ሳለን የልጅነትን ሀሳብ እናስባለን፡፡ ልብ እናድርግ፡፡ እንደ ልጅነት እናስብ ብለን ተዘጋጅተን አይደለም፤ ራሱ ሀሳቡና አኗኗሩ የሚያገኘን ካለንበት የልጅነት ጊዜ የተነሳ ነው እንጂ፡፡ በአጭሩ እንደ ልጅነት ማሰብንና መኖርን የሰጠን ራሱ የልጅነት ጊዜው ነው፡፡ ከዚያ እንደገና ተጉዘን የወጣትነት ጊዜ ላይ ስንደርስ፣ እንደ ወጣት ማሰብን በራሱ እናገኛለን፡፡ ለዚህ ነው ግሩም ሰው ጳውሎስ "ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።" (1ኛ  ቆሮ. 13:11) የሚለው፡፡ ነጥቡ ምንድነው እዚህ ጋ? ጊዜ በራሱ የሚሰጠን ሀሳብ አለ ነው ነጥቡ፤ ወይም በጊዜ ውስጥ ተይዞ የተቀመጠ ሀሳብ አለ ነው፡፡ በሽምግልና ጊዜ ያለውን ሀሳብና ሥርዓቱን ለማግኘት በዛ ዕድሜ ውስጥ ሰተት ብለን በተፈጥሮ መግባት አለብን፡፡ እንጂ ልጅ ወይም ጎልማሳ ኹነን ሳለ ስለ አዛውንትነት መጽሐፍት ብናነብ፣ መረጃ ብንሰበሰብ፣ እንዴት እንደሚኖሩ ብንለማመድ፣ ... አናመጣውም፡፡ ጊዜው ራሱ ካልሰጠን፣ ውስጡ ያለው የመኾን ሀሳብና ሥርዓት አይመጣም አያችሁት፡፡ ይሄ አሁን በዕድሜ በልጅነት መስለን ስናወራው ቀላል ነገር ይመስላል፡፡ ግን እያንዳንዱ ሀሳባችን፣ የመኖር ሥርዓታችን በዚህ የተያዘ ነው፡፡ በትውልድም ማዕቀፍ ስንናየው፣ ዘመን በራሱ ለትውልዱ የሚሰጠውን ሀሳብ ትውልዱ ካላገኘው፣ ሲቃወስ ነው የሚኖረው፡፡ በማይበቅልበት ቦታ ሲዘራ ነው የሚውለው፡፡ ዝምታንም አይሰማም፤ ንግግርንም አይሰማም፡፡ ዘመኑ በራሱ የተሸከመውን ያላገኘ ትውልድ፣ ከራሱ ተጣልቶ እንደመኖር ነው የሚኾነው፡፡ ልክ በግለሰብ ደረጃ እንዳልነው አንድ ሽማግሌ ሽምግልናው የሰጠውን ሀሳብና ሥርዓት ትቶ በልጅነት ሀሳብ ቢመላለስ፣ አስቀድሞ የተጣላው ከራሱ እንደኾነው ማለት ነው፡፡ በወንጌል አንድ የክርስቶስ ድምፅ እንዲህ ይላል፦ "ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?" (ማቴ. 16:3) ይህ በወቅቱ የተነገረባቸው ትውልዶች፣ ዘመኑን ለይተውትስ ቢኾን ኑሮ ከፊታቸው ቁሞ ያለውን ክርስቶስ ባወቁት ነበረ፡፡ እነርሱ ግን ሊያዘንብ ያለውን ሰማይ ባኮረፈው ደመና በኩል ያውቁታል እንጂ የዘመኑን ገጽ ማንበብ አልተቻላቸውም፡፡ ዛሬም እኛ እንዲኹ ነን፡፡ ዘመኑን ማወቅ በግለሰብ የሥጋ ሀሳቦች ተጠርንቆ ለሚኖር ሰው፣ ሚዛን የማይደፋ ነገር ይመስለዋል፡፡ ይኹንና ግን ኹሉ ነገር በጊዜ ውስጥ ነው ያለውና የሚኾነው፡፡ ትውልድም በራሱ ዘመን ውስጥ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ዘመኑን አላወቀም ማለት ራሱንም አላወቀም እንደማለትምም ነው፡፡ ትውልድ ለዘመኑ ያለውን ሀሳብ መፈለግ አለበት፡፡ እግዚአብሔርንም ተናገር ማለት አለበት ከዕለት ተዕለት የኑሮው ጥያቄዎች ከፍ አድርጎ፡፡ በዚኹ በኩል እንደገና ወደ አንድ ጉዳይ እንሂድ፡፡ ለመኾኑ ይሄ ዘመን ምን ይመስላል? ምንስ ይታይበታል? ብለን እንጠይቅ፡፡ እኛ እስከዛሬ የመጣነውን እንደኾንን ኹሉ፣ የዓለም ታሪክም እስከዛሬ የመጣውን ኹሉ ነው፡፡ የአኹኑን ዘመን፣ የእስከዛሬው ትውልድ ዘመናት ሲቀባበል አድርሶታል፡፡ ነገሩን መጽሐፍ እንደማንበብ እንውሰደው፡፡ አንድን መጽሐፍ እስከ ገጽ 20 አንብበነው ከኾነ፣ ለኛ መጽሐፉ ማለት እዛ ድረስ ያለውን ነው ማለት ነው፡፡ ደረሰን እያነበብነው ያለው ገጽ፣ ካለፉት ገጾች ተነጥሎ የቆመ አይደለም፤ በራሱ ገጽ ላይ የተጻፈበት እንዳለ ሁኖ፣ ከነበሩት 19 ገጾች ጋራ የተያያዘም ነው፡፡ ተረድታችሁታል? ያለንበት ዘመን እስከዛሬ የመጡት ዘመናት ሁሉ ቅጣይ ነው፡፡ እኛ የሰው ልጆች እስከዛሬ ሲፈስ የመጣው ታሪካችን ውጤት ነን፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ ከኾነ፣ ስለ ዓለም የሰው ልጆች ታሪክ በቅጡ ማወቅ፣ በአንድም በሌላም ዛሬ በዙሪያችን ከብቦን ስላለው ነገር ሁሉ ማወቅ ነው፡፡ አሁንም ወደ ክርስቶስ ለማሳያ መለስ እንበልና ነገሩን እንጨብጠው፡፡ በአንድ ንግግሩ ደሞ በዘመኑ የተገለጠበትን የአይሁድ ትውልድ እንዲህ ሲናገረው እንሰማለን ፦ "የአብርሃም ዘር መሆናችሁንስ አውቃለሁ ነገር ግን ቃሌ በእናንተ አይኖርምና ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ።" (ዮሐ. 8:37) ሰዎቹ የአብርሃም ዘሮች ነን ይላሉ፡፡ ናቸውምም፡፡ ግን በሥጋ ነው፡፡ በነፍስ አያውቁትም፡፡ በሌላ አባባል የአብርሃም ዘሩ እንጂ ሀሳቡ (ሥራው) የላቻቸውም፡፡ እንዲሁ በተገኙበት ገጸ ዘመን ያሉ ትውልዶች እንጂ የመጡበትን የዘመናት እውነታዎች አያውቁትም፡፡ ዛሬም ኢትዮጰያውያን እንዲሁ ይመስላሉ፡፡ የአባቶቻችን ልጆች ነን እንላለን፤ የአባቶቻችን ሥራ ግን ከኛ ጋር የለም፡፡

  • 8 мар.3 8671521

    без подписи