tgindex
ሰማዐያዊ

ሰማዐያዊ

Статистика

መጽሐፈ ሰማዐያዊ👉🏾 https://semaayawi.com/ የግል እገዛ ለማግኘት👉🏾 @pharetz

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 681
−2 за 4 дн.
Сутки
+1
+0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 085
20 постов
Вовлечённость
23,2%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
588
1/48двое суток
673
1/72трое суток
726

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.4543110

    የማትፈልገዉ የሕይወት አጋጣሚ ገጥሞክ ያልተፈለገ አሉታዊ ስሜት ዉስጥ ከገባክ ይኼን መምሪያ ተከተል። አየክ ብዙኋኑ ያልተፈለገ ስሜት ሲገጥመዉ ይሸሸዋል ወይ ወደ አዎንታዊ ለመቀየር ይታገላል። ኹለቱም ካለክበት ኹኔታ ለመዉጣት አያግዙም እንደዉም ያብሱታል። መሸሽ ነገሩ ከኔ በላይ ነዉ በማለትክ የተደበክ ይምሰልክ እንጂ በኅቡ አእምሮክ ዉስጥ ኩነቱ ተደብቆ ከዠርባ ሕይወትክን ነዉ የሚመራዉ። ለዚነዉ በዚኽ አጋጣሚ ሰዎች ትላንት ወይ ከዓመታት በፊት ያጋጠማቸዉን እያጉተነተኑ በጠቈረ ስሜት የሚቆዮት። አንድ ለ አንድ እገዛ ስሰጥ ከምንፈታቸዉ ነገሮች ዉስጥ አንዱ ይኼ ነዉ። የአእምሮ ገደብ ብለን እንጠራዋለን። ከአሉታዊዉ ወደ አዎታዊ ልመለስ ካልክም የማይሆን ነዉ። ለምን? በቅድሚያ ወደ አልቦ መመለስ ስለሚገባ። ከመደበኛ ወይም አልቦ ስሜት ወደ አሉታዊ እንደወረድክ ኩሉ፥ ስሜቱን ለማጥፋት አትገልፍጥ፤ እሱ መፍትሔ አይኾንክም ወደ አልቦ ተመለስ። ከዛም ነዉ ወደ አዎታዊ ለመዉጣት ዐቅም የምታገኘዉ። አሁን በደንብ አንብብ፦ መፍትሔዉ ስሜቱ እንዲበላክ መፍቀድ ነዉ። አሉታዊ ኹኔታ ሲያጋጥም አለመሸሽ ወይም ለመቀየር አለመታገል። እንዲጎርስክ ፍቀድ ሰዉነት በራሱ አትኖ ወደ አልቦ ይመልስካል። ያኔም አንተ ለእዉነታ ምላሽ መስጠት እየተዉክ እዉነታ ላንተ መገዛት ይዠምራል።

  • “ምግብን እንደመዳኃኒት የማትወስድ ከኾነ መድኃኒትን እንደምግብ ትወስደዋለህ” ይኽን ያለዉን ሰዉ ባላስታዉሰዉም ወርቅ የሆነ ነሀር ጠቈሞን አልፉል። ምግብ የስሜት መወጣጫ ሳይኾን ኀይል ለማደሻ መዋል ያለበት ግብኣት ነዉ። በዘመናችን መልከ ጥፉ፥ ደካማና ከግብ የራቅን የሆነዉ ለምግብ ስለምንኖር ነዉ። ኩሉ በፈጣሪዉ አምሳያ ዉብ ሆኖ ተፈጥሮ ሳለ ገበሎ መስሎ ቅርጹን ያጣዉ ለሥጋ ባሕርይዉ በመገዛቱ ነዉ። ቀጣይ ሲርብክ/ሲርብሽ ሱስ ነዉ ወይስ የእዉነት ሰዉነቴ ምግብ አስፈልጎት ነዉ በማለት እራሳችኹን ጠይቈ። የተቀነባበረና ተፈጥሮኣዊ ያልሆኑ ምግቦችን መጠቀም፥ ኀይል መታደስ የነበረበትን አካል ያለዉን ተፈጥሮኣዊ ዐቅም በማሳጣት የባስ እንዲንኮታኮት ነዉ የሚያደርገዉ። ንቃት በሐሳብ ብቻ ሳይኾን በተፈጥሮ የተሠጠንን ሥልጣን በመገንዘብ የሚጎለብት ነዉ።

  • እርግት በማለት እዉነታ ለናንተ እንዲገዛ አድርጉ። አእምሮ (አንጎል በሥራ ላይ) በዉጥረት እና በጭንቀት ዉስጥ ከኾነ ፊቱ የቀረበን መልካም ዕድል ሳይገነዘብ ነገሮችን ኩሉ ከችግር በማምለጥ ኩነት ዉስጥ ሆኖ ያስተናግዳል። አንድ ለ አንድ አብረዉኝ ለሚሠሩ ከፍተኛ የሥራ ፈጣሪዎች የምላቸዉ አንድ ነገር አለ፥ እሱም “ለም መሬት ሁኑ ነዉ”። ለም መሬት የተዘራን ዘር በጥሩ ኹኔታ እንዲበዛ አድርጎ ሰብል እንደሚያደርስ ኩሉ፤ እርግትና ጽንት ስትሉ የአንጎል የሥራ ሂደት ከዉጥረትና ከጭንቀት “ቤት” ወጥቶ ወደ አልፍና ጤት የተረጋጋ፤ የኅቡ አእምሮንም ደጃፍ የተከፈተ እንዲኾን ያስችለዋል። ኅቡ አእእምሮ (ዉስጠ አእምሮ) ከ90% በላይ የሚኾነዉን እዉነታችኹን ከዠርባ በመኾን እየመራ የሚገኝ ነዉ። በዐጭሩ የእዉነታ ማሕፀን ነዉ። ታዲያ በቀጣይነት በተዝናኖት ዉስጥ ሰዉ ሲቆይ ያልተፈለጉ ከዠርባ በዉስጠ አእምሮ ዉስጥ ሆነዉ ሲመሩ የነበሩ መርሐ ግብሮችን በመሰረዝ ዐዲስ መርሐ ግብርን ለማተምም ይቀላል። የማስበዉ ነገር ለምን አእምሮዬ ዉስጥ ጠብ አይልም ካላችሁ ተዝናኖት ዉስጥ ሆናችሁ ማሰብ ባለመቻላችሁ የተፈጠረ እና ዉስጠ አእምሮ ዝግ በኾነበት ሰዓት በግድ ለመጫን እየጣራችሁ በመኾኑ ነዉ። በቀን ዉስጥ 20-30 ደቂቃ ምንም ያለማድረጊያ ጊዜ ለራሳችሁ ስጡት፤ ይኽ በተፈጥሮ ተዝናኖት ዉስጥ እንድትገቡ ያግዛል። ጸሎት እና አርምሞ ከአርምሞ የጠለቀዉ ተመስጦ “ጽማዌ” ደግሞ የበለጠ በዚኽ መገኘት ዉስጥ እንድትቆዮ ይረዳል።

  • ስበት በኹለት ተቃራኒ ዋልታዎች መኻከል የሚፈጠር ኀይል ነዉ። በወንዴ እና በሴቴ (ብእሲ እና ብእሲት) ይወከላል። ወንዴ በሰሜን ወይ በምሥራቅ፤ ሴቴ በደቡብ ወይ በምዕራብ። የሰዉ አካሉ ሰሜን እና ደቡብ ዋልታ ያለዉ በኤሌክትሪከመግነጢስ ክበብ ዉስጥ ኀይል እየመገበና እየተመገበ የሚገኝ ሕይወት ያለዉ ተንቀሳቃሽ ፍጥረት ነዉ። ሰሜን ብቻዉን (ዐናት፥ አብ፥ ሰማይ) ለስበት አይዉልም፤ ደቡብ ብቻዉን (አካል፥ ወልድ፥ ምድር) ለስበት አይዉልም። ስበት (ከፍተኛ የንዝረት እርግብግብታ ያለዉ መገለጥ) አብ እና ወልድ፥ ሰማይ እና ምድር፥ ዐናት እና አካል ሲጣመሩ የሚፈጠር ነዉ። በዕዉቀት ብቻ መጥነን ሰሜን ቀድሞ ስበትን ያበላሻል። በምድራዊ ምኖት (ምግብ፥ ፍትወት፥ ሥልጣን) መመራት ደቡብ ቀድሞ ስበትን ያበላሻል። ሰዎች ሳቢ፥ ማራኪ፥ ደስ የሚል ቆሌ የሚኖራቸዉ በሰሜን እና በደቡብ ዋልታቸዉ መኻከል ለፍተኛ መጓተት ተፈጥሮ ልባቸዉ የተደጋገመ የኀይል ኅትመትን ወይም ዝዉተራን በማሳደሩ ነዉ። እዉነታ፣ ሰዎች፣ አጋጣሚ፣ የሥራ ዕድል ሌላም ሌላም ሰዋዊ በጎ ልምምዶች ወደናንተ እንዲሳቡ የሚያደርገዉ 50 ሰዓት የሰዎችን ማስተማሪያ ስላያችሁ ወይ 1000 መጽሐፍት ስላነበባችሁ ወይ እኔ የምሠራዉን ስለተመለከታችሁ ሳይኾን ሰሜን እና ደቡብ በማዕከላዊ ነጥብ (ልብ) ላይ ሲያድሩ ነዉ። ከዉጪ ቀነስ እያደረጋችሁ ለዉሳጣዊ ዓለማችሁ ቦታ ስጡት፥ ለዉጡንም ለራሳችሁ ኑሩት።

  • ከሙሉ ዐቅምክ የተቈጠብከዉ በካርበን 666 (Carbon: electron - 6, proton - 6, neutron - 6) መሠረት በሆነዉ አካልክ ነገሮችን ለመተርጎም ስለምትሞክር ነዉ። የፈጣሪ ጠልሰም ሆነክ ሳለ ለምን እጥረትን ታቀሸባብላለክ? ለፈጣሪ የሚከብደዉ የለም፤ ኩሉ የበታቹ ነዉ። ሰልፍክ ከሱ ጋር እንጂ ከሥጋ ጋር አይኹን። ፍጥጫዉን አንተ ከነገሮች ጋር ሳይኾን የሱ መገኘት ከነገሮች ጋር ይኹን። የመነሻ ኀይል እያለ መነሻክ ከቊራሽ ኀይል አታድርግ።

  • ብዙ በመሥራት ሰበብ ከዉስጥ ያለዉን ባዶነት ለመሙላት አትሞክር። ሥራ ከመሆን ከቀደመዉ ዉጤቱ አናሳ ነዉ። ከኩሉ ተግባር ዠርባ እየመራዉ የሚገኝ ዝዉተራ አለ። የአንዳንዶች ማጣት፥ መጉደል፥ እልቂት፥ መቈጠብ ሲኾን የአንዳንዶች መትረፍረፍ፥ ምላት፥ በብዙ ማጨድ ነዉ። ታዲያ ጎዶሎ ዝዉተራ ኖሮት አንድ ሰዉ የፈለገ ብዙ ቢጥር ተግባር ዉጤት ፈጣሪ ሳይኾን በዉስጥ የነበረዉን ዝዉተራ መዝጊያ ነጥብ በመኾኑ፥ ያዉ ጎዶሎነት ዝቅተኛ ዉጤትን ያስከትላል። ከተግባር በፊት ተግባሩን የሚከዉነዉ የዉስጥ ማንነት ከየት እየተነሳ እንደኾነ እራስክን ጠይቅ። ብዙ ስለሠራክ ሳይኾን ብዙ ዝዉተራ ስላለክ ነዉ በዓለም ላይ የመከሩን የምታጭደዉ። ዝዉተራ ከፊት ተግባር ከኋላ። (መግለጥ)

  • አንድ ዐናት አለን፥ እሱም ክበብ ቅርጽ አለዉ። ዐናት የከፍተኛ ንቃተ ኅሊና ማደሪያ ነዉ። ክበብም ቀጣይነት ያለዉ የመንፈስ ዉክልና ነዉ። ኹለት እግሮች አሉን፥ እነሱም የተከፋፈለዉን የዝቅተኛ ልኬቶች ምልከታ ይወክላሉ። የላይኛዉ የሰዉነት ክፍል በገነት፤ የታችኛዉ በገሃንም ይነጻጸራሉ። ገነት እና ገሃንም ንቃተ ኅሊና ያደረበት የልኬት ደረጃ ነዉ በዚኽ አንድምታ። ሰዉ በበላይ ባለዉ የከፍተኛ የንቃት ማደሪያ በኾነዉ ዐናት እና ልብ ሲመራ በገነት ይዉላል። እንዲኹ ይኼዉ ሰዉ በታችኛዉ ባለዉ የምግብ፣ የፍትወት እና ምድራዊ ኀይል ሲመራ በገሃንም ይዉላል። (ዮሐ 13፥14) ላይ መምህራቸዉ እግራቸዉን ሲያጥብ፥ ምድራዊ ንቃተ ኅሊናን ከፍተኛዉ ማንነት ሲያጸዳ ይወክላል። ሰዉም እራሱንና በከባቢዉ የሚገኙ ወዳጆቹን ከወረዱበት ንቃት በማጠብ ወደ ከፍታ ይመልሳል።

  • እኔ ንጹሕ ንቃተ ኅሊና እንጂ ስም፥ ቦታ፥ የሕይወት ልምምድ፥ ትዉስታ አይደለም። ብዙ ጊዜ “እኔ” ስንል የምንጠቈመዉ በሦስተኛዉ ልኬት ዉስጥ የገነባነዉን የቅብዐ-መልክ (Ego) ነዉ። እኔ ግን የአጽናፈ ዓለማዊ መታወቂያ የኾነችዉ ነፍስ መጠሪያ ነዉ። ትክክለኛ እኔ ሸፍኖት የሚገኝ የተወረሱ ቅርፊቶች ወድቀዉ ከመሐል የሚገኝ ንጹሕ ግንዛቤ ወይም አስኳል ነዉ።

  • 9 авг.9784637

    1. ፀጥ ያለ ቦታ ዐይንን ጨፍኖ መቀመጥ። 2. ሐሳቦች ቢበታተኑም በእርጋታ ወደ አሁን መመለስ። 3. ሰዉነት መነሳት ወይም መንቀሳቀስ ቢፈልግ እዛዉ የተቀመጠበት እንዲቈይ ማድረግ። 4. ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ሰዉነት ተዝናኖት ዉስጥ ይገባል፥ የአንጎል ሞገድም ወደ አልፍ ብሎም ወደ ጤት ይወርዳል፥ ይኽም ዉስጠ አእምሮ ዉስጥ ዐዲስ መርሐ ግብር ለመጫን ምቹ ያደርገዋል። (እዚኽ ለመድረስ እንደየ ሰዉ ይለያያል፥ 20፣30፣50 ደቂቃ ቢፈጅም ሰዉነት እስኪዝናና መጠበቅ) 5. መግለጥ የተፈለገዉን እዉነታ በዐጭር ተንቀሳቃሽ ምስል እየደጋገሙ ማጫወት፥ የቅርብ ወዳጅ ወይም ቤተሰብ እዉነታዉ ሲገለጥ የሚያሳዮትን መልካም ምላሽ (መታቀፍ፣ መሞገስ ኾኖ ሊቀርብ ይችላል) ይኽ መግለጥ የተፈለገዉ እዉነታ ስሜት በአካል ላይ ስለሚፈጥር ወደ መኾን ያሻግራል። 6. በሰዉነት ላይ የተፈጠረዉ ስሜት መታተሙን ሲሰማ ወይም መደበኛ ኾኖ ሲተን ወደ ሦስተኛዉ ልኬት ተመልሶ ሰዋዊ ቈይታን መቀጠል። 7. ይኽን ልምምድ እንደ አስፈላጊነቱ በቀን ዉስጥ ደጋግሞ ማድረግ ይመከራል ዐዲሱ ዝዉተራ በሰዉነት ታትሞ መደበኛ እስኪኾን፤ የቀኑ መዠመሪያ ማድረግም ዐዲሱን ዝዉተራ ተላብሶ የቀን ዉሎን ለመቀጠል ዕድል ያመቻቻል።

  • ሰማዐያዊ pinned «የመግለጥ ጣቢያ እንደጠፋ በዉስጥ መልእክት እያደረሳችኹኝ ነዉ። ከዚኽ በፊት ጣቢያዉ ዉስጥ ሆናችሁ ወደ ስልካችሁ ያላወረዳችኹት ካላችሁ ጠይቁ በግል እልካለዉ።»

  • 9 авг.950223

    የመግለጥ ጣቢያ እንደጠፋ በዉስጥ መልእክት እያደረሳችኹኝ ነዉ። ከዚኽ በፊት ጣቢያዉ ዉስጥ ሆናችሁ ወደ ስልካችሁ ያላወረዳችኹት ካላችሁ ጠይቁ በግል እልካለዉ።

  • 9 авг.987285

    ዉዱ መገበያያ ትኩረት ነዉ። ምን ላይ እያዋልከዉ ትገኛለክ?

  • 8 авг.1 184467

    ትዕቢት ዉድቀትን ትቀድማለች..

  • 7 авг.1 321536

    ሰዉ መሆን ማለት ሰዉ የመኾን ልምምድ ነዉ።

  • 5 авг.1 6656218

    አሁን የምልክን/የምልሽን በጥሞና አንብበክ ከተረዳከዉ የብዙ ዓመት ልፋትን ትቀንሳለክ/ትቀንሻለሽ። ሰዎች የግል ሕይወታቸዉን አሳምሮ ለመፍጠር በሚያደርጉት ልምምድ ዉስጥ በእንግልጥ አጠራሩ “Manifestation” ብዙ ነገር አወሳሳበዉ በመመልከት መኖር ከሚገባቸዉ መደበኛ እዉነታ ሲዘገዮ እመለከታለዉ። ስለዚኽ ጉዳይ ማሕበራዊ ገጾች በሙሉ የራሳቸዉን ሐሳብ ሰጥተዉ ተመልክታችሁ ይኾናል.. ወይ እኔ መግለጥ ብዬ ያዘጋጀኹትን መጽሐፍ አድምጠሽ ይኾናል.. ወይ ከኔ ጋር አንድ ለ አንድ ሥልጠና በመዉሰድ የተለያዮ መንገዶች ተጉዛችሁ ይኾናል.. በዐጭሩ እንካችሁ። መግለጥ ተኣምር አይደለም። ሰዉ መኖር የሚገባዉን እዉነታ እራሱን ለም መሬት በማድረግ ብዙ ፍሬ እንዲያፈራ ማድረግ ነዉ። አሁን ቀጥዬ የምልክን/የምልሽን ማስታወስ ከቻላችሁ ደግሞ በዚኽ ዘርፍ ምንም መመራመር ሳይጠበቅባችሁ የመላ ፍሬ ታያላችሁ። መግለጥ ሦስተኛዉ ልኬት ዉስጥ የሚገኝ እዉነታን ስለመቀየር ሳይኾን እራስን ስለመቀየር ነዉ። ማረጋገጫዉን ከምድር መጠበቅ አቈሞ ለራስ መስጠት። (ደግመክ አንብበዉ) አለቀ ጨዋታዉን የሚታየዉን ተጽዕኖ ለማሳደር የሚደረግ ጥረትን አቈሞ ማረጋገጫዉን በዉጪ መመልከት ሳያስፈልግ በቀጣይነት በተፈለገ የስሜት ደረጃ ላይ መቈየት ነዉ። በል ከዚኽ በኋላ ብዙ መጽሐፍ ስላነበብክ ወይ እኔ የምለዉን ስለተከተልክ ሳይኾን ስለራስክ አድርገዉ። ኩሉን አቈምና እኔ የምሠራዉንም መመልከት ሊኾን ይችላል እራስክን አጥና፣ መኖር የምትፈልገዉን እዉነታ ስትኖር እገባበታለዉ የምትለዉን ስሜት ለብሰከዉ ቆይ። ሌላዉ ኩሉ ትርፍ ነዉ።

  • 4 авг.1 499223

    ምዕናብ ከሚታየዉ ዓለም ባሻገር የዉስጥ ዐይን የሚመለከተዉ እዉነታ ነዉ። ምዕናብ በማይታየዉ መገኛ ላይ የሚገኝ ጠጣር የመሆን ዕድል ያለዉ የማይዳሰስ እዉነታ ነዉ። ሦስተኛዉ ዐይን ወይም የዉስጥ ዐይን፣ የመዠመሪያዉ ዐይን፣ የአእምሮ ዐይን ይህን በማይታየዉ መገኛ ላይ ያለን እዉነታ ተመልካች ነዉ።

  • 4 авг.1 481222

    ሦተኛዉ ዐይን፣ የዉስጥ ዐይን፣ የመዠመሪያዉ ዐይን፣ የአእምሮ ዐይን ተአምር አይደለም። የማሰብ ችሎታ መላቅ ምልክት ነዉ። እራስን እና ተፈጥሮን፤ ተፈጥሮንም ያስገኘዉ ፈጣሪ መሐል ልዩነት ሳይሆን አንድነት እንዳለ መገንዘብ፣ መመልከት ነዉ።

  • 3 авг.1 6073012

    የሰጠከዉ ሳይኾን ያልሰጠከዉ ነዉ የሚወሰድብክ። መስጠት ያለን ኀይል ማዘዋወር ነዉ፤ ዞሮም ለራስ ይገባል። አለመስጠት ኀይልን መገደብ ነዉ፤ ዞሮ እንዳይመጣ ይገድባል። “ላለዉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለዉ ግን ያዉ ያለዉ እንኳ ይወሰድበታል” (ማቴ 13:12)። እንዳለዉ በዝዉተራ ደረጃ ያወቀ ይሰጣል። እንደሌለዉ በዝዉተራ ደረጃ ያመነ ይቈጠባል። ማግኘት እና ማጣት አካላዊ አይደሉም፤ አካላዊዉን እየመሩ የሚገኙ የዝዉተራ ደረጃዎች ናቸዉ። ሕይወትን ከጎዶሎ ተነስተክ ስትመለከታት እሷም አጉድላ ትመለከትካለች። ከምላት ስትመለከታት ደግሞ በኹኔታ፣ በአጋጣሚና በሰዎች እየሞላች ትመለከትካለች። ስለ ኪስክ ሳይኾን ስለዝዉተራክ ሙላት ተጨነቅ። በዝዉተራ ደረጃ ሲኖርክም ስላለክ የበለጠ ስለሚሰጥክ።

  • 3 авг.1 231206

    ነፍስክን አላዘልካትም ነፍስክ ናት ያዘለችክ። ትክክለኛ ማንነት ሥጋ አይደለም፥ የአጽናፈ ዓለም መታወቂያ ነፍስ እንጂ። ሥጋክን ለማዳን አትሞክር እሱን ግደለዉ። ነፍስክንም ለማዳት አትጣር እሷን ልቀቃት። “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል” (ማቴ 16:25)። ነፍስክንም ለማዳን አትሞክር ግን ልቀቃት፤ በራሷ መገኛዋን ታዉቃለችና።

  • 1 авг.1 563294

    ሐሳብ እፈጥራለዉ አይባልም፥ እቀበላለሁ ነዉ የሚባለዉ። ለምን? በምንገኝበት ዝዉተራ ልክ የሐሳብ ሞገዶችን እንደ ጣቢያ እየተቀበልን ስለምንተረጉም። የተሻለ ሐሳብ (የፈጠራና የተለያዮ ልምምዶች) ለመቀበል የተሻለ ዝዉተራ ላይ መገኘት ነዉ። የሰዉ ዝዉተራዉ የሚገኝበት ኩነት፤ የሚኖረዉንም እዉነታ ይወስናል። እሱም ከሐሳብ የዠመር ነዉ።