ኑ እናንብብ
Статистика- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 427
- 1/48двое суток
- 489
- 1/72трое суток
- 527
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አህያው የሚቀመስ ምግብ ፍለጋ በጫካ ውስጥ እየዞረ ሳለ የሞተ አንበሳ ተንጋሎ ያገኛል። የፈጠነም የአንበሳውን ቆዳ በመግፈፍ ይለብሰዋል። ቀጥሎ ወደወንዙ በመውረድ በወንዙ ውሃ መልኩን ሲመለከት ቁጭ አንበሳ ሆኖ አገኘው። ወደዱርም በመሄድ በእንስሳቱ መካከል ቆመ፤ የዱር እንስሳቱም አህያውን ሲመለከቱት አንበሳ መስሏቸው ፈሩት። ይሄኔ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለትና ወደአንበሳ ማህበር አቀና። አንበሶችሁ ጋር እንደደረሰም በጨዋታ መልኩ ተላፋቸው፤ እንደሱም ጉልበት ያለው አንበሳ አልተገኘም። የታገሉት ሁሉ ይወድቃሉ። አንበሳ ጎበዝ ተናካሽ ቢሆንም መራገጥ ላይ እንብዛም ነው። ይሄኛው አንበሳ ግን ሲራገጥ አያምጣው ነው። ስለዚህ አንበሳ መስሎ የመጣውን አህያ በጉልበቱ አማክኝነት በአንበሶች መካከልም እጅግ በጣም የተፈራ ሆነ። ስልጣን ሰጥተውም ንጉስ አደረጉት። ታድያ የንግስናው ወንበር ላይ ሲቀመጥ ስሜቱን መቆጣጠር ስላቃተው በድንገት «ኢ..ሃ ኢ..ሃ» ብሎ አናፋ!። 🤓 ይሄንን ጥንታዊያን የኤዞፕ ተረተኞች እንዲህ ብለው ይጠሩታል «The ass in the Lion's skin» ምን ልላችሁ ነው መሰላችሁ You can wear a lion’s skin, but you can’t hide a donkey’s voice! ሰው ምንም ያህል መልኩን ቢቀይርም ባህሪው እና ንግግሩ ውሎ አድሮ ማንነቱን ማሳበቁ አይቀሬ ነው። @Armemo_offical
‹‹ያየን ሁሉ ተሰናክለን የማናውቅ ይመስለው ዘንድ የተረጋጋና ዝም ብሎ የሚሄድ ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ አያውቁትም። ማንም ምን ያህል እንደደከመን አይገነዘብም። በዝምታ ፈገግ ማለታችንና የተስተካከለ ቁመናችንን ስላዩ ብቻ ምን ያህል የድካም ዝርዝሮችን እንደተሸከምን አያውቁም፤ ቢያውቁም ማንም ስለዛ ጉዳዩ አይደለም። በቃ አይረዱኋችሁም.. ሺህ ማይል እያሰብን የተራመድንበትን ነገር አፍ አውጥተን ብናወራው እነሱ አንድ እርምጃ እራሱ ስላልተራመዱ አይሰማቸውም። በልባችን ውስጥ ቤት ስለሰሩት የለሊት ሃሳቦች ሚሊዮን ጊዜ ብናስረዳ የልባቸውን በር አንዷን ሌሊት እንኳን አያንኳኳም። በዚህ ምክንያት አንድ ሰው ተቀብሎ ባለመኖር እና ሳይቀበሉት በመኖር መካከል ይሞታል›› ―አህመድ ካሊድ ታውፊቅ @Imagination_officially
ራስህን በፀፀት አለንጋ መግረፍህን አቁም። እናንተ "ጸጸት" የምትሉት ነገር አእምሯችሁ ራሱን ቅዱስ ለማድረግ የሚጠቀምበት ሌላኛው የውሸት ጭንብል ነው። "ያኔ ያንን ባላደረግኩት፣ ያንን ስህተት ባልሰራሁት፣ ያንን ሰው ባላስቀየምኩት" እያልክ ትላንት በሞተው ታሪክ ላይ ዛሬህን ትገብራለህ። ያ የአእምሮህ ጨዋታ እንጂ ንቃት አይደለም። ትላንትናን መለወጥ አትችልም፤ ነገር ግን በትላንትናው መቃብር ላይ ቁጭ ብለህ ስታለቅስ፣ አሁን በአጠገብህ እያለፈች ያለችውን ህይወት በገዛ እጅህ ትገድላታለህ። አንድ እውነተኛ ገጠመኝ ልንገራችሁ። አንድ ቀን በህይወቱ በሰራው አንድ ትልቅ ስህተት ምክንያት ለዓመታት ራሱን ሲወቅስ የኖረ፣ ፊቱ ላይ ታላቅ ስቃይ የሚታይበት ሰው ወደ እኔ መጣ። "ከዓመታት በፊት አንድ የቅርብ ጓደኛዬን ከዳሁት። ከዚያ ቀን ጀምሮ ውስጤ ሰላም አጣ። በየቀኑ ራሴን እረግማለሁ። እባክህ ይህንን የውስጤን የጸጸት እሳት እንዴት ላጥፋው?" አለኝ እኔም ትኩር ብዬ አየሁትና ፈገግ አልኩ። "ችግርህ እኮ ያኔ የሰራኸው ስህተት አይደለም፤ ችግርህ ያ የሞተው 'አንተ' ዛሬም በህይወት ያለ መስሎ መታየትህ ላይ ነው። ያኔ ያንን ስህተት የሰራኸው በዚያን ጊዜ በነበረህ የንቃት ደረጃ (Awareness) ልክ ነበረ። ዛሬ ላይ ቆመህ ትላንትናን ስትወቅስ ግን ራስህን እንደ እግዚአብሔር ፍጹም አድርገህ እያሰብክ ነው። ይህ ደግሞ ያንተ 'እኔነት' (Ego) እንጂ መጸጸት አይደለም" አልኩት። ያለፈው ነገር አልፏል፤ ድንጋይ ሆኗል። ድንጋዩን በትከሻህ ላይ ተሸክመህ ብትዞር የሚደክመው ያንተ ትከሻ እንጂ ድንጋዩ አይቀልጥም። የትላንትናውን አስክሬን የመሸከም ውጫዊ እብደታችሁን አቁሙ። ልክ እንደ መኸር ዛፍ ሁኑ። የደረቁ ቅጠሎች ከዛፉ ላይ ሲረግፉ፣ ዛፉ ስለወደቁት ቅጠሎች አያለቅስም፣ አይቆጭም። ቅጠሎቹ መውደቃቸው ተፈጥሮአዊ ነው። ዛፉ ግን ወደ አዲሱ የጸደይ ወቅት ያያል፣ አዳዲስ ቅጠሎችንና አበባዎችን ያበቅላል። ህይወት ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አትፈስም። ያለፈውን ስህተትህን እንደ ትልቅ የትምህርት ቤት መጽሐፍ ተመልከተው እንጂ እንደ ሰንሰለት አታድርገው። ከእሱ ተማር፣ ወደ ህልውናው ዝምታ ተመለስ፣ ከዚያም እራስህን ይቅር በል። አሁን በዚህች ቅጽበት አዲስ ነህ። ከአሮጌው ታሪክህ ነጻ ስትሆን፣ ያኔ እውነተኛውን መለኮታዊ ብርሃንና ውስጣዊ ሰላም ታገኛለህ። ራስህን ፍታው! "ትላንትና የታተመ መጽሐፍ ነው፣ ገጹን ማስተካከል አትችልም። አሁን ግን ንጹህ ነጭ ወረቀት በእጅህ ላይ አለ። በትላንትናው ቀለም የዛሬውን ወረቀት አታቆሽሸው፤ አሁንህን አዲስ አድርገህ ጻፈው።" — ኦሾ @enlighten_ethiopia
"የምንኖረው ቀብር ከሟቹ ይበልጥ ፣ ሰርግ ከፍቅር ይበልጥ በሚያሳስብበት እና ቁሳዊ ነገሮች ከአእምሮ ብስለት ይበልጥ የሚከበርበት ዓለም ውስጥ ነው። ይዘቱን በሚንቅ የማሸጊያ ባህል ውስጥ ነው የምንኖረው።" ኤድዋርዶ ጋሊያኖ @zephilosophy
ሩሲያዊው ጸሃፊ አንቶን ቼኮቭ ስለወደቁ ማህበረሰቦች ተፈጥሮ ሲጠየቅ እንዲህ ሲል መልስ ሰጥቶ ነበር፡- ‹‹በወደቁ ማህበረሰቦች ውስጥ ለእያንዳንዱ ጥበበኛ አእምሮ አንድ ሺህ ሞኞች እና ለእያንዳንዱ አስተዋይ ቃል አንድ ሺህ ደደብ ቃላት አሉ። ብዙሃኑ ሁል ጊዜ ሞኞች ሆነው ይቆያሉ። በዚህም ምክንያታዊውን ሰው ያለማቋረጥ ያሸንፋሉ። በህብረተሰብ ውስጥ ለውይይት ግንባር ቀደም የሆኑ ተራ ርእሶችን ካየንና ተራ ሰዎች ዋናውን መድረክን ከተቆጣጠሩ ለእናንተ የሚያወሩት ከራሳቸው ማኀበረሰብ ያመጡትን ተራ ውድቀት ነው። ለምሳሌ በዘፈኖች ውስጥ ትርጉም የለሽ ቃላት እየተዘፈነ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲጨፍሩ እና ደጋግመው ሲያዳምጡ ይታያሉ። እናም የዘፈኑ ባለቤት ታዋቂ፣ ዝነኛ እና ተወዳጅ ይሆናል። ሰው እንኳን በህብረተሰብ እና በህይወት ጉዳዮች ላይ የራሱ አስተያየት አለው። ጸሃፊዎች እና ደራሲዎች ግን ማንም አያውቃቸውም፤ ከእቁብ ባለመቁጠር ዋጋ እንኳን ሳይሰጣቸው ሲያልፉ ይስተዋላል። አብዛኛው ሰዎች ስካርን ብሎም በከንቱ ወሬ መፍዘዝን ይወዳሉ። አዕምሯችንን እንድንስት የሚያደነዝዝና በማይረባ ነገር የሚያስቀን ሰው ደግሞ ወደ እውነት ከሚነቃንና እውነትን በመናገር ከሚጎዳን ሰው የተሻለ ቦታን ያገኛል። ስለዚህም ነው ዲሞክራሲ እና ሎጂክ ለደናቁርት ማህበረሰቦች የማይመቸው!። ምክንያቱም ብዙሃን አላዋቂዎች የብዙሃኑን እጣ ፈንታ ይወስናሉ!።›› @Armemo_offical
እንኳን አደረሳችሁ! መልካም የትንሳዔ በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
ለፋሲካ ሌሊት የአማርኛ ፊልም https://youtu.be/QmGW3e12suc?si=XaBao6yrG5VMpDzt
ግልብጥ የግርንቢጥ! ተምሮ አስተምሮ አገር ላቀና ሰው ውለታው ቢሠላ ቢከፈል ወረታው ወርቅ አልማዝ ላይክሰው ሽልማት አድናቆት ዝናው ቢቀርበት ለምን ያሸማቁት ክብሩን አሳንሰው? ይብላኝ ለትውልዱ ይብላኝ ለወደፊት ድድብና ልቆ ቅራቅንቦ ገዝፎ ለሚታየው ከፊት። እጅግ ልብ ይሰብራል፦ ጥበብ ዕየናቁ ሐሳብ እየሸሹ ዕውቀት እየገፉ ለቁስ ለአሸንክታብ ለብልጭልጭ ዓለም መጻዒውን ዜጋ ለሞት ሲያሰልፉ። ሕዝብ ወዴት ሔደ ሰው ጠፋ ባገሩ ተው አይበጅም ይሔ ብሎ የሚመክር ''ለልጅ ልጆቻችን መጥፎ አርዓያ አትስሩ''? ካገር በሰፋ ሆድ በመከነ አእምሮ ሥርዓት ሲዘወር በማያይ አዙሮ፥ ዓዋቂ ይናቃል፣ አስተዋይ ይፈራል ዳር ይገፈተራል፣ ጠያቂ ይመታል ተቺ ይወገራል፣ አሳቢ ይገፋል፣ በጥበብ ገበያ ደፋር ግሙን ያራል፤ ፈጠራ ተንቆ ተረት ይከበራል፣ ዕውነት ይነወራል እምነት ለከርስ ያድራል፣ ታዲያ በዚህ ጊዜ እምቢ ባይ ከታጣ ይባስ ይጨልማል ደህና ቀን ላይወጣ!!
የገዛ እራሱን ያገባው ብራዚላዊ ዶክተር መነጋገሪያ ሆኗል [ዜና ፕላስ አዲስ አበባ መጋቢት 24/2018] በብራዚል የሚኖሩ አንድ የ33 ዓመት ጎልማሳ እጮኛቸው የጋብቻ ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጋ ብትለያቸውም፣ አስቀድሞ የተያዘውን የሰርግ ፕሮግራም ሳይሰርዙ እራሳቸውን በማግባት ስነ-ስርዓታቸውን መፈጸማቸው በኢንተርኔት ዓለም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ዶክተር ዲዮጎ ራቤሎ የተባሉት ግለሰብ፣ ከእጮኛቸው ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ግንኙነት የነበራቸው ቢሆንም፣ ከሰርጉ ጥቂት ጊዜ በፊት ግንኙነታቸው መቋረጡ ተገልጿል። ሆኖም ዶክተር ዲዮጎ ለዝግጅቱ የወጣውን ከፍተኛ ወጪና የተያዘውን ቀጠሮ ወደ ጎን በመተው፣ "ደስታ በትዳር ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም" በሚል መሪ ቃል ለየት ያለ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ባለፈው የህዳር ወር መጀመሪያ ላይ በአንድ የባህር ዳርቻ ሪዞርት በተከናወነው በዚህ የሰርግ ስነ-ስርዓት ላይ፦ ዶክተሩ በመስተዋት ፊት ለፊት በመቆም ለራሱ የጋብቻ ቃለ-መሀላ ፈጽሟል። በዝግጅቱ ላይ የቅርብ ጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የታደሙ ሲሆን፣ ደማቅ የደስታ ድግስም ተካሂዷል። ድርጊቱ "ሶሎጋሚ" (Sologamy) ወይም እራስን ማግባት በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ግለሰቡ ለራሳቸው ያላቸውን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ ያደረጉት መሆኑን ተናግረዋል። ዶክተር ዲዮጎ በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ "ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ህይወት መቀጠል አለባት፤ የራሳችን ደስታ ባለቤት ደግሞ እራሳችን ነን" ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ክስተት በብዙዎች ዘንድ በአነቃቂነቱ ሲወደስ፣ ሌሎች ደግሞ ድርጊቱ ለየት ያለ መሆኑን በመግለጽ አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። ምንጭ፦ ኢንዲያን ኤክስፕረስ (Indian Express) እና ትሬንድስ ዴስክ (Trends Desk)
https://www.facebook.com/share/r/1ArA5sGrNj/
የሆነ ጊዜ መንግስት ኦሮሚያ ውስጥ በተደረገ ውጊያ ማረኳቸው ያላቸውን ወጣቶች አቅርቧቸው በቲቪ እየተናገሩ ነው የሰራዊቱ የምርኮኛ አያያዝ እንዴት ነው? "እንደልባችን ገላችንን እየታጠብን፣ ስጋም ዳቦም በቀን እንደፈለግን እየበላን ነው ...ተንከባክበውናል ሌሎችም ከኛ ተምረው እጅ በሰላም ይስጡ" ሕዝቡ በኮሜንት "ተምረናል ...መንግስት እኛንም ይማርከን"👐 አሌክስ አብርሀም
https://youtu.be/fYCeOmhfp6o?si=k5SLTCvyrsgEa_nT
ኤሊቶች እንዴት ነው የሰዎችን አዕምሮ የሚቆጣጠሩት?። የምትጠቋማቸው ሚዲያዎች ከአስፈላጊ ጉዳዮች የሚያደናቅፉ ወጥመዶች ናቸው ብላችሁ ታስባላችሁ?፤ በህይወታችሁ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ውሳኔዎች በጠቅላላ እናንተ ሳታስተውሉ ቀስ በቀስ በላያችሁ ላይ ቤታቸውን እየሰሩ እንደሆነ አስተውላችኋል?። እስቲ ዛሬ አንድ ነገር ላጋራችሁ፦ 1(Distraction strategy–ያለመረጋጋት ስትራቴጂ) «Keeping the public occupied and diverted from important issues» ማህበረሰቦችን በመቆጣጠር ውስጥ ወሳኝ ንጥረ ነገር ያልተገመቱ ክስተቶችን ደጋግሞ መፍጠር መቻል ነው። ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኤሊት የሆኑ ታላላቅ ሰዎች ውሳኔያቸው፣ ለውጥ እና ነውጣቸው ጭምር ቀጣይነት ባለው የዜና እና የሚዲያ አገልግሎት ባርነት ስር ይወድቃል። በዚች ቀላል ምክንያት ያስችላቸዋል። በየቀኑ ሰዎች በማይረቡ ስራዎች እንዲጠመዱ በማድረግ ለማሰብና ለመተንተን ግዜ ባለመስጠት ውስጥ ሌላ አዳዲስ ኢኮኖሚካሊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ደጋግሞ መፍጠር። 2(Create a Problem, Then Offer a Solution –ችግርን ፍጠር ከዛ መፍትሄ ስጥ) «Manufacturing crises to justify pre-planned measures» ይህን እንዲህ ይከፈላል፦ #ችግር_ምላሽ_መፍትሔ የሚባል ስትራቴጂ ሲሆን ሰዎች ወደኛ እንዲመጡ ሳይሆን እኛን ፈልገውን እንዲመጡ የማድረግ ብልሃት ነው። በቀላሉ በእነሱ ላይ ችግር እንፈጥርባቸዋለን እነሱም ለችግሩ መፍትሔ ፍለጋ ላይ ይጠመዳሉ። ይህ ብዙ ግዜ ከመዳኒት ንግድ አኳያ ሜዲኬሽን ላይ ሪሰርቸር የሚያደርጉ ኤሊቶች ብዙ ገንዘብ ለመስራት አስችሏቸዋል። ለምሳሌ ነፃነትን የሚገድቡ ህጎችን በማጽደቅ ደህነታቸውን ስጋትን ውስጥ ማስገባት ብሎም ማህበራዊ መብቶችን በመገደብ የኢኮኖሚ ቀውስን ማስፋፋት መቻል ነው። 3(Gradual Strategy / Strategy of Gradualism–የደረጃ ስትራቴጂ) «Introducing unacceptable changes slowly to make them seem normal» የተበላሸ የአገዛዝ ስርዓትን ለማራመድ ከፈለግን..ከፈጣን ኃይል ይልቅ በማያስተውሉት ደረጃ ቀስ በቀስና ለረጅም ግዜ በተተገበረ መልኩ በሌሎች ላይ መፈጸም ነው። ቀስ በቀስ የተለወጠ ስርዓት ያደነዝዛል ፈጽሞ አገዛዙን አለመቀበል አይቻልም። የሆነ ግዜ ላይ ከዛ ስርዓት ጋር የተዋሃደ ማንነት ሆነው እናገኛቸዋለን። 4(የፕሮክራስቴሽን ስትራቴጂ) «Presenting harsh measures as necessary in the future to soften acceptance» ከባድ ውሳኔዎችን ያለማመንታት እንዲወስዱ «የወደፊቱን አስፈላጊነት» ደጋግሞ መስበክ። ሰው የዛሬን መስዋትነት ለመቀበል የሚደፍረው ነገ የተሻለ ይሆናል በሚል ተስፋ ነው። ያለፈው ወቅት የተኖረና የሚታወቅ ነው፤ ስለዚህ የሰው ልጅን የመቆጣጠርያ መሳርያ ያልተኖረ ግዜ ብቻ ነው። 5(Addressing the Public as Children – ህዝቡን ወደህፃናዊ ባህሪ መለወጥ) «Using simplified, emotional language to weaken critical thinking.» ቀላል፣ ስሜታዊ እና የዋህ ንግግሮች እየበዙ ሲሄዱ የማሰብ አቅም በዛው ልክ እየደከመ ይመጣል። የምንጠቀመው ቃላት የአዕምሮ መዋቅር ስርዓትን ይቀርጻል። 6(Stimulate Emotion Instead of Reason–በሃሳብ ፋንታ ስሜትን መፍጠር) «Appealing to feelings to bypass logical analysis» የስሜት መነቃቃት ሎጂካሊ አስተሳሰብን ያበላሻል። ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ጉጉትን መፍጠር ከእውነታው ይልቅ ምናባዊና ያልተጨበጠ ውጤቶችን ያስከትላል። 7(Keep the Public Ignorant–ሰዎችን አላዋቂ ማድረግ) «Maintaining gaps in knowledge and awareness to prevent understanding» የትምህርት ድክመት፣ የጠቅላላ እውቀት ማነስ እና በማዕረግ መካከል ሰፊ የሆነ የአእምሮ ልዩነት ላይ ያሉ ግለሰቦችን ይህን ድክመታቸውን ደጋግሞ መንገር። 8(ደግነትን እና ትህትናን የያየዘ የሚመስል የጭቃ ውስጥ እሾህ) ከፍተኛ የሆነ የአዕምሮ ማደንዘዣ ልምዶችን ኖርማላይዜሽን በማድረግ ማርኬቲንጉን መቆጣጠር መቻል። ባህላዊና ወግ አዘል ልምዶችን በፌዝና በመዝናናት ፈንታ ቀይሮ ማህበራዊ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ። 9(የጋራ አመፅን ወደግል ጥፋተኝነት መቀየር) አንድን ግለሰብ ውድቀቱ የግል ጉድለቱ እንጂ የአገዛዙ ስርዓት አለመሆኑን ማሳመን መቻል። ልክ እንደ ኒው ኤጅ አይነት «ድሃ የሆንከው የገዛ የአዕምሮ ውቅርህ በስበት ህግ አምጥቶት ነው፤ ስለዚህ ኢኮኖሚካሊ የአገር ውድቀትን መተቸት የለብህም» እንደማለት ያለ። ስለዚህ ይህ ግለሰብ መንግስትን ከመቃወም ይልቅ እራስን ወደመውቀስ ድምዳሜ ይገባል። 10(ግለሰቦችን ከራሳቸው በላይ ማወቅ) ምስጋና ለሳይኮሎጂ ይሁንና በኒውሮባይሎጂ እና በመረጃ ትንተና ስርአቶች የሰውን ልጅ ባህሪ በቀላሉ በትክክል ለመረዳት ተችሏል። አንድ ሰውን ወይም አንድ ማኀበረሰብን ከመገናኘታችን በፊት ደካማና ጠንካራ ጎኑን በማጥናት ካርታውን በቀላሉ ማግኘት የቅድመ ማሸነፍ ብልሃት ነው። እነዚህ ስትራጂዎች በትክክል ቢሰሩም ባይሰሩም ወደ አንድ ነገር ይወስዱናል። እሱም ንቃተ ህሊናችን እንደገና ለማግኘት እራሳችንን መጠየቅ መቻል ነው። «ትኩረቴን የገዛው ማነው?» «በእኔ ማጣት የሚያገኘው ማነው?» አዎን ማስተዋል ወደ ነፃነት የምንወጣበት የመጀመርያው እርምጃ ነው። @Armemo_offical
በ12 ሚሊዮን ተሰራ የተባለው ድልድይ‼️
የስፔን የፓርላማ አባል ኢሬን ሞንቴሮ ለትራምፕ የላኩት መልዕክት፦ "ትራምፕ ሆይ፤ ጦርነት ከፈለግክ የገዛ ልጅህን ላክ። ሂድና በጣም የምትወዳቸውን ሰዎች ወደ ግንባር ስደድ። እኛ ግን ልጆቻችንን፣ ሴት ልጆቻችንንና የምንወዳቸውን ሰዎች እቤት ውስጥ ሆነው በጤና እና በሰላም እንዲኖሩ እንፈልጋለን፤ እንወዳቸዋለን። ከእንግዲህ ጦርነት አንፈልግም፤ ምክንያቱም ጦርነት ነፃነታችንን እንደሚሰርቀንና ማህበረሰባችንም በፍርሃት የተሞላ፣ ራስ ወዳድ እና በቀላሉ የሚጠመዘዝ እንዲሆን እንደሚያደርገው እናውቃለን... ይህ ደግሞ እኩልነትን ያጠፋል። ጦርነት አንፈልግም፤ ምክንያቱም ጦርነት የሚታዘዘው በቅንጡ ቢሮዎች ውስጥ ሆኖ ነው፤ ዋጋውን ግን ሁልጊዜ የሚከፍለው ህዝብ ነው። የሌሎችን ልጆች ለሞት መላክ በጣም ቀላል ነው። ስለዚህ በግልጽ እንናገራለን፦ የእኛ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ ባልደረቦቻችን እና ጓደኞቻችን—እዚህ እቤታቸው ይቆዩ፤ ምክንያቱም ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ሙሉ ህይወት አለ። "
▌የብርሃን ብቸኝነት© መንቃት ጉዞ ነው እንጂ መድረሻ አይደለም። ማታለያዎችን መግፈፍ፣ የማይመቹ እውነቶችን መጋፈጥ እና ጥያቄ ከማይቀርብባቸውን እምነቶች የጋራ ግዴለሽነት ባለፈ መራመድ ነው። ሆኖም ታሪክ አንድ ከባድ እውነት በጆሯችን ያንሻኮሻኩል—ብርሃንን የሚሹ ሁልጊዜ በጥላ ውስጥ በሚቀሩት ይገፋሉ! ብርሃናቸው የእውቀትን፣ የግንዛቤን እና ምናልባትም መንፈሳዊ መሻገርን፣ ዕድገትን የማምጣት ሃይል አለው። ነገር ግን ያ ብርሃናቸው የመገለላቸው ምክንያት ሲሆን ማየት ያማል። ማህበረሰቡ የራሱን ፈጠራ የለመደና የራሱን ውሸት የሚያምን በመሆኑ የእምነቶቹን ክፍተት እና ስህተት የሚያሳዩትን አይወድም። ይልቁንም ይፈራቸዋል፣ ይጠላቸዋል፣ ያፌዝባቸዋል፣ እና ድምፃቸውን ለማፈን ይፈልጋል። ይህንን እውነት በታሪክ ውስጥ በግልጽ ማየት እንችላለን። ሶቅራጥስ ወጣቶችን በማበላሸት ተወገዘ። ጋሊልዮ ዶግማን በመቃወም ተሰደደ። ኒቼ ሀሳቦቹ የተለመደ አስተሳሰብን ያናወጡ እና ያወኩ ናቸው ተብለው ተነቅፏል። እነዚህ አእምሮዎች ብርሃንን ቢያንጸባርቁም ግን በዙሪያቸው ያለው ማህበረሰብ የጨለማነትን ምቾት በመምረጡ ወደ ኋላ ተገፍተዋል።... ዮናታን በጋሻው @zephilosophy
የቃልኪዳን አገር ፥ ኢትዮጵያ... ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመረጠች ናት እንላለን። መለኮታዊ ኪዳን እንዳለን እንናገራለን። በአይናችን ከምናየው መራራ እውነት ይልቅ በምናባችን የሳልነውን ጣፋጭ ተረት እናምናለን።... ቅድስት አገር ኢትዮጵያ እንላለን። ስለየትኛዋ ኢትዮጵያ ነው የምናወራው? ልጅ እያለሁ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር ምርጥ ትመስለኝ ነበር። ጣፋጩን ውሸቴን አምኜ ሀሴት አድርጌያለሁ። እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ እንደሚወደን ሳስብ ደስ ይለኝ ነበረ። ጎምዛዛውን እውነት መቀበል አልፈግም ነበር። ከጣፋጭ ውሸት ጎምዛዛ እውነት ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያን ከአለም የተለየች አድርጎ አይስላትም። በመጽሐፍ ቅዱስ መጠቀስ የቅድስና ምልክት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ፅህፈት ዘመን የነበሩ አገራትን በተለያየ አውድ ተጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ተደጋግማ ብትጠቀስም ፥ እኛ በምኞታችን እንደሳልነው "ከአለም ህዝብ ሁሉ የላቅን" እንደሆንን ለማሳየት አይደለም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቂት ምሳሌ እናንሳ ፥ "... እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላ^ላችሁ" (ይህ ጥቅስ ያለው በትንቢተ ሶፈኒያስ ነው። ምዕራፍ ሁለት ቁጥር 12 ላይ ታገኙታላችሁ) "... የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨ^ነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። (ይህ ደግሞ በዕንባቆም 3፥ 7 ላይ የሚገኝ ምንባብ ነው። ) ትንቢተ ሕዝቄል ምዕራፍ 30 ቁጥር 4 ደግሞ እንዲህ ይላል፥ "... ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገ^ደሉትም በግብፅ ውስጥ ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል" ከሕዝቄል መጽሐፍ አንድ እንጨምር ፥ "... እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ" (ሕዝቄል 20 ፥10) ተጨማሪ ከዜና ካልዕ እንውሰድ "እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ" (2ኛ ዜና 14፥12) ከላይ ያሉት ጥቅሶች ምን ይነግሩናል? እርግጥ መሰረታዊ የሄርሚኒትክስ ሕግ ልንከተል ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ ስናነብ ጥንቃቄ ይፈልጋል። የትንቢት መጽሐፍና የታሪክ መጽሐፍ የሚተረጎሙበት መንገድ አንድ አይደለም። የመዝሙር መጽሐፍትና የሕግ መጽሐፍት የተለያዩ ባህሪያት አላቸው። ይህ ሁሉ ቢሆንም ፥ ለሚያስተውል ሰው ከላይ ለናሙና የተቀመጡ ጥቅሶች ጥሩ ማሳያ ናቸው። ኢትዮጵያ የተለየች አገር ናት ብሎ ማሰብ ጥሩ ነው። አገራት ተረት ያስፈልጋቸዋል። ከማንም የላቅን ነን ብሎ ማሰብ ብሔራዊ ኩራትን ይጨምራል። ለአገር የመስራት ተነሳሽነት ይፈጥራል። ይህ ግን ለእኛ አይሆንም። ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ለምናባዊ ኩራት አይፈቅድም። እንደ አገር አደጋ ውስጥ ነን። በየለቱ ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች ይፈጠራሉ። ብሔራዊ ህልውናችን ፈተና ውስጥ ነው። ስለዚህ ከምናባዊው ነገር ይልቅ መራራውን እውነት እንጋፈጥ። ለኛ የሚያስፈልገን "እግዚአብሔር የሚወደን ልዩ ህዝቦች ነን" የሚል ስብከት አይደለም። ለኛ የሚያስፈልገን "ከማንም አንበልጥም" የሚል መራራ ኪኒን ነው። "ከማንም አንበልጥም። ከፈ^ረሱ አገሮች የተለየ ነገር የለንም። አምላክ ይጠብቀናል የሚለውን መመፃደቅ አቁመን የቤት ስራችንን ካልሰራን የፈረ^ሱት አገሮች እጣ ይገጥመናል" ብሎ ማሰብ ነው የሚጠቅመን ሃሳቤን ሳልጨርስ ፅሁፉ ረዘመብኝ... ለማንኛው ጎምዛዛውን እውነት እንቀበል Via ተስፋኣብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
« በዓለም ላይ ያሉ ፖለቲከኞች በጫካ ውስጥ እንዳሉ፡ ዝንጀሮዎች ናቸው፤ ከተጣሉ አዝመራውን ያበላሻሉ፡ ቢታረቁ አዝመራውን ይበላሉ! - © George Orwell Animal farm 📚 @sebleworkbooks
‹‹ለማወቅ የሚኖርንም ሰው እወዳለሁ . . .የማወቅ ፍላጎቱም በምድር ላይ ታላቅ ሰው ይኖር ዘንድ ምክንያት ሁኗልና . . .ምንም እንኳን በዚያ ሂደት የራሱን ውድቀት እንደሚያፋጥን ባውቅም እውቀትን የሚፈልጋት እሱ ታላቅ ሰው ነው፡፡ከመልካም ስራው በፊት መልካም ቃላት የሚናገርና ከተናገረውም በላይ የሚሰራ ሰው እወዳለሁ . . . ቢያንስ ቃሉን አክባሪ ነውና . . .የቱንም ያህል አምላኩ ቢቀጣው አምላኩን የሚወድ ሰው ደግሞ አከብራለሁ፤ ምክንያቱም አምላኩን የሚወድ ሰው በቁጣው ውስጥም ማለፍ ይችላልና . . . ነፍሱ እየደማች ጥንካሬ ያልተለያትን ሰው እወዳለሁ፣ ድልድዩ የተሰራው ለእንደሱ ዓይነቱ ነውና . . .ከጠቆረው ደመና ዕለት ዕለት ‹ጠብታወች› ወደምድር ይወርዳሉ . . . እነዚህ ጠብታወች ሰዎች ቢሆኑም የሚናገሩት የምስራች ግን የመብረቁን መምጣት ነው . . . እነሆ መብረቁ ደግሞ ታላቅ ሰው ነው . . . ›› ዛራቱስትራ ፍሬድሪክ ኒቼ @zephilosophy
Which one are you?