- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 21
- Всего постов
- 37
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 4 301
- 1/48двое суток
- 5 013
- 1/72трое суток
- 5 406
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
ጊዜው የመሪዎች ነው! “ልክ ሕይወትን እንዴት መኖር እንዳለብኝ ያወቅሁ ሲመስለኝ ህይወት ትለወጣለች” - Hugh Prather የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትንበያዎች ሃርቫርድ የተሰኘው ታዋቂ ዩኒቨርስቲ ለውጥን አስመልክቶ ሶስት እውነታዎችን እንደተነበየ ይታወቃል፡፡ አሁን በተሰማራንበት ወይም ለመሰማራት ባሰብንበት የስራ ወይም የንግድ ዘርፍ ውስጥ፣ በመጪው ጥቂት አመታት ውስጥ . . . 1. ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በርካታ ለውጦች ይከሰታሉ፡፡ 2. ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ የጋለ ውድድርና ፉክክር ይከሰታል፡፡ 3. ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በርካታ የእድል በሮች ይከፈታሉ፤ ሆኖም እነዚህ እድሎች አሁን ከምናደርጋቸው ነገሮች እጅግ የተለዩ ናቸው፡፡ ከዚህ ፈጣን ሂደት ጋር አብሮ ለመራመድ የሚያስችለን ብቸኛ ክህሎት የአመራር ክህሎት ነው፡፡ 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ ይህንን ክህሎታችሁን የሚያዳብር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁና ተጠቀሙበት፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
ካልመራችሁ ኋላ ቀር ትሆናላችሁ! ራሳችሁን በጥበብ ካልመራችሁ ራሳቸውን የሚመሩ ሰዎች በመሻሻል አልፈዋችሁ ሲሄዱ እናንተ ግን ወደ ኋላ ትቀራላችሁ! ሰዎችን በመልካም ተጽእኖ ካልመራችሁ በሰዎች ላይ ተጽእኖ በማምጣት የሚመሩ ሰዎች አልፈዋችሁ ሲሄዱ እናንተ ግን ወደ ኋላ ትቀራላችሁ! ስራችሁን በተሳካለት መልኩ ካልመራችሁ ስራቸውን በብቃት የሚመሩ ሰዎች በመበልጸግ አልፈዋችሁ ሲሄዱ እናንተ ግን ወደ ኋላ ትቀራላችሁ! በእነዚህ ሶስት ወሳኝ የአመራር ዘርፎች ልቃችሁ በመሄድ ከኋላ ቀርነት እንድትድኑ የሚደግፋችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷል፡፡ የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
የ2018 ዓመትን የመደምደሚያ ስልጠና! የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
ከልክ በላይ መስጠት (Over-giving) በአጭሩ ሲገለጽ፣ ከልክ በላይ የመስጠት መነሻው ፍቅርን ለመግዛት መሞከር ነው፡፡ እንዳብራራው ይፈቀድልኝ፡፡ ከልክ በላይ መስጠት ማለት አንድ ሰው ጤናማና አስፈላጊ ከሆነው በላይ ያለማቋረጥ መስጠት ነው። ይህም ሁልጊዜ ከእውነተኛ ፍቅር የሚመነጭ ላይሆን ይችላል፤ አንዳንዴ ሰውዬው በውስጡ ሳያውቀው፦ “በቂ ከሰጠሁ ምናልባት ይወዱኛል።” “በቂ መስዋእትነት ከከፈልኩኝ ምናልባት አይተውኝም።” “ሁሉን ካደረግኩላቸው ምናልባት የተሸለ ዋጋ ይሰጡኛል።” “ባይመቸኝ እንኳን ሁልጊዜ ከተገኘሁላቸው ይቀበሉኛል።” ብሎ ከልክ በላይ የሚሰጥ ሊሆን ይችላል። ከልክ በላይ መስጠት የሚታይባቸው መንገዶች 1. ጊዜ የራሳችን ሃላፊነት እያለብን እና አንዳንዴም ማረፍ እንዳለብን እወቅን ሁልጊዜ ለሌላ ሰው መገኘት። 2. ገንዘብ ከአቅማችን ገንዘብ ማውጣት፣ መክፈል ወይም ሰዎችን በገንዘብ መርዳት። 3. ትኩረት ሰዎችን ሁልጊዜ መጠየቅ፣ መከታተል፣ ችግራቸውን መፍታት፣ ማዳመጥ እና ሰዎቹን የሕይወታችን ማዕከል ማድረግ። 4. አገልግሎት ሰዎች ዋጋችንን እንዲያውቁልን በሚል እሳቤ ሁሉንም ነገር ለእነሱ ማድረግና ማለቂያ የሌለው አገልጋይ መሆን። 5. ስሜት የሌላው ሰው ችግር ሁሉ ከአቅማችን በላይ ቢሆን እንኳን መሸከም፣ በሂደቱም የራሳችንን ፍላጎትና ደህንነት እስክንጥል መድረስ። እዚህ ላይ ማስታወስ ያለብን፣ ችግሩ መስጠት አይደለም። መስጠት መልካም ነው። ችግሩ ግን ጤናማ ባልሆነ ተስፋ እና የማይሆን ነገር በመጠባበቅ በመስጠት ለስሜት ቀውስ መዳረግ ሲከሰት ነው። ስለዚህ በመስጠት የአንድን ሰው ፍቅር ወይም ተቀባይነት ለማረጋገጥ ስንል ሁል ጊዜ ከልክ በላይ ስንሰጥ ራስን ወደ መተው (self-abandonment) ደረጃ ልንደርስ እንችላለን። ከልክ በላይ መስጠት ብዙ ጊዜ ይህንን ሂደት ይከተላል፦ የተቀባይነትና የመወደድ ጥማት → ያንን ለማግኘት ከልክ በላይ መስጠት → በተስፋ መጠበቅ → የጠበቁትን ባለማግኘት መበሳጨት → መራራ እና ቂመኛ መሆን → የስሜት ዝለት → ራስን ከሰዎች ማግለል፡፡ 1. ወደ ጤናማ መስጠት መሸጋገር አንድን ሰው ስለምንወደው ወይም ስለምናከብረው እንስጥ፤ ነገር ግን ዋጋችንን ለማረጋገጥና ከሰውው ምላሽ ለማግኘት አንስጥ፡፡ 2. በፍቅርና ባለመተማመን መካከል መለየት ፍቅር ይሰጣል፤ አለመተማመን ግን ከልክ በላይ ይሰጣል። ፍቅር በነፃ ይሰጣል፤ አለመተማመን ግን ለመቀበል ሲል ይሰጣል። የምትሰጡትን ለማን እንደምትሰጡ፣ ለምን እንደምትሰጡና ምን ጠብቃችሁ እንደምትሰጡ በሚገባ ለዩ፡፡ ሰዎች እንዲቀበሏችሁ ብላችሁ አትስጡ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ከልክ በላይ መስጠት (Over-giving)
ያደግንበት ቤት እና ሕብረተሰብ አብዛኛዎቻችን ሁሉም ነገር ተነግሮንና በራሳችን አንድን ነገር አስበን እንድናደርግ ሳንበረታታ ነው ያደግነው፡፡ ይህ የአስተዳደግ አጉል ተጽእኖ አስበን፣ አቅደንና ወስነን ራሳችንን እንዳንመራ ይገታናል፡፡ ራሳችንን መምራት ካልቻል ደግሞ በሌሎች ሰዎች ላይ መልካም ተጽእኖ በማምጣት የመምራት ጉዳይ የማይታሰብ ነው፡፡ በተጨማሪም በተሰማራንበት ስራ ወይም ንግድ መስክ ውስጥም በእቅድ እና በስልት የተሞላ አመራር መለማመድ ስቸግረናል፡፡ በእነዚህ እውነታዎች ላይ ወደ ተሻለ ደረጃ እንድናድግ የሚረዳን ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አሁኑኑ ተመዝገቡ፡፡ የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
ሰዎችን የመቆጣጠር አድካሚነት! በሰዎች ሕይወት ጣልቃ የመግባትና ሁሉንም ነገር የመቆጣጠር ዝንባሌ ካላችሁ ጊዜያችን ካባከናችሁ በኋላ ልትቆጣጠሯቸው እንደማትችሉ ትደርሱበታላችሁ፡፡ ለአብነት ያህል . . . • የሰዎችን ሕይወት ለመቆጣጠር ስትሞክሩ ሰዎች ከእናንተ ውጪ ሕይወትን የመኖርን ብልሃትና ብርታት እያዳበሩ ይሄዳሉ፡፡ • የሰዎችን ምርጫና ውሳኔ ለመቆጣጠር ስትሞክሩ ሰዎች ከእናንተ ውጪ የመምረጥና የመወሰን ብልሃትና ብርታት እያዳበሩ ይሄዳሉ፡፡ • የሰዎችን ገንዘብ ለመቆጣጠር ስትሞክሩ ሰዎቹ ከእናንተ ውጪ ገንዘብ የማግኘትን ብልሃትና ብርታት መፈላለግ ይጀምራሉ፡፡ ሰዎች እንድትቆጣጠሯቸው የሚፈቅዱላችሁ አማራጭ እንዳላቸው እስከሚባንኑ እና ያንንም አማራጭ የመውሰድ አቅም እስከሚያዳብሩ ድረስ ነው፡፡ እናንተን አስመልክቶ ግን ትርፉ ድካም ነው! እንደ ቅርበታችሁ ደረጃ ሰዎችን የመምከር፣ የማገዝና አቅጣጫ የማሳየት አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሰዎችን እስከወዲያኛው መቆጣጠር እንደማትችሉ አስታውሱ፡፡ ሰዎችን ካለአግባብ አትቆጣጠሩ፡፡ ሰዎች ፍላጎታቸውንና ማንነታቸውን እንዲኖሩ ፍቀዱላቸው፡፡ የተሳሳተ ፍላጎትና ተግባር ውስጥ ስታገኟቸው ደግሞ ላላችሁ የግንኙነት ጥልቀት የሚመጥንን አቀራረብ አዳብሩ፡፡ በማያገባችሁ አትግቡ፡፡ በሚያገባችሁ ስትገቡ ደግሞ ሰዎቹን በማይጨቁን መልኩ አድርጉት፡፡ ይህንን ካላደረጋችሁ ሰዎቹን የመቆጣጠር አቅማችሁንም ሆነ ሰዎቹን ጭምር ወደማጣት ትሄዳላችሁ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የ2018 ዓመትን የመደምደሚያ ስልጠና! የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
የምሽቱ በኢኮኖሚ የማደግ ጥያቄ የኑሮአችን ሁኔታ ባለበት መቆም እንደሌለበትና በየእለቱ የአኗኗራችን ሁኔታ በጥራትም ሆነ በብዛት ማደግ እንዳለበት ሁላችንም የምንስማማበት እውነታ ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ ግን ብዙ ሰዎች ከምኞት ባለፈ መልኩ ሲራመዱበት አይታዩም፡፡ አንድ ቀን ከእንቅልፋችን ስንነሳ የገንዘብ ብቃታችን ጨምሮ አንነሳም፡፡ በገንዘብ ብቃት የማደጋችንን ጉዳይ የሚወስኑ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ፡፡ የኢኮኖሚ ደረጃችንን ለማሳደግ ወሳኝ በሆኑት በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ “የአንድን ነገር ጥያቄ” ጠይቅ፡- 💲 አሁን ካለሁበት የትምህርት ደረጃ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለማደግ ማድረግ ያለብኝ አንድ ነገር ምንድን ነው? 💲 አሁን የተሰማራሁበትን የስራ ወይም የንግድ ሁኔታ ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ማድረግ ያለብኝ አንድ ነገር ምንድን ነው? 💲 አሁን ያለሁበትን የገቢ ምንጬን ለመጨመርና ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ማድረግ ያለብኝ አንድ ነገር ምንድን ነው? እስቲ ወደ መኝታ ከመሄዳችሁ በፊት እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስና ወደ ተግባር ለመለወጥ አስቡ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የ2018 ዓመትን የመደምደሚያ ስልጠና! የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
የከባዱ ጊዜ ምስጢር! "አስቸጋሪ ጊዜያት አይዘልቁም፤ ጠንካራ ሰዎች ግን ይዘልቃሉ" – Unknow source ከባዱ ጊዜ ሰውን ከሚከተሉት ነገሮች ጋር ያስተዋውቁታል 1. ከእውነተኛ ጥንካሬው ጋር አስቸጋሪ ጊዜያት ከዚህ በፊት በውስጣችን እንዳለ ያላወቅነውን ድፍረትና የመቋቋም ኃይል ይገልጣሉ። 2. ከእውነተኛው የሰዎች ባህሪ ጋር በስኬት ጊዜ ብቻ ሳይሆን በአስቸጋሪ ወቅቶችም አብረውን የሚቆሙትን ይለይልናል። 3. ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች ጋር ከባዱ ጊዜ በሕይወታችን በእውነት አስፈላጊ የሆነውንና ያልሆነውን ለይቶ ያሳየናል። 4. ከተደበቁ ድክመቶቹ ጋር ፈተናዎች እድገትና ብስለት የሚያስፈልጋቸውን የሕይወት ክፍሎቻችን አጋልጠው ያሳዩናል። 5. ያልተገለጠ የፈጠራ ችሎታው ጋር ችግር ሲገድበን በአዲስ መንገድ እንድናስብና ፈጠራ እንድናመጣ ያደርገናል። በሕይወታችሁ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ስታልፉ፣ ራሳችሁን ለማወቅና ለውጥ ለማምጣት ተጠቀሙበት እንጂ አትዳከሙበት፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የ2018 ዓመትን የመደምደሚያ ስልጠና! የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
እኔ ራሴን እንደ መሪ ባየው፣ ራሴን እከተል ነበር? አመራር የሚጀምረው ራስን ከመምራት ነው። ሌሎች እንዲከተሉን ከመጠየቃችን በፊት፣ የእኛ ባህሪ፣ ውሳኔ፣ ራስን መግዛት፣ ታማኝነት እና ምሳሌነት ሊከተሉ የሚገባ ናቸውን በታማኝነት ራሳችንን መጠየቅ አለብን። “ራሴን እከተል ነበር?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ መመልከት ያለብን ሰውን ለመከተል የሚያስችሉትን ባህሪያትና አመለካከቶች በራሳችን ውስጥ የማግኘታችንን ሁኔታ ነው። በራሳችን ውስጥ መመልከት ያሉብን የመሪነት ባህሪያት 🌟 ታማኝነት (Integrity) — ማንም ባያየኝም የምናገረውን እና የምሠራውን አንድ አደርጋለሁ? 🌟 ራስን መግዛት (Self-Discipline) — ራሴን፣ ጊዜዬን፣ ስሜቴን እና ልማዶቼን መቆጣጠር እችላለሁ? 🌟 ኃላፊነት (Responsibility) — ለስህተቶቼ ኃላፊነት እወስዳለሁ ወይስ ሌሎችን እወቅሳለሁ? 🌟 ወጥነት (Consistency) — በግል ሕይወቴም ሆነ በሰው ፊት ተመሳሳይ ሰው ነኝ? 🌟 ስሜታዊ ብስለት (Emotional Maturity) — ስሜቴ ውሳኔዎቼን እንዳይቆጣጠር ስሜቴን መምራት እችላለሁ? 🌟 ራዕይ (Vision) — ወዴት እንደምሄድ አውቃለሁ? ለሌሎችስ ትርጉም ያለው አቅጣጫ መስጠት እችላለሁ? 🌟ጥበብ የተሞላበት ውሳኔ መስጠት (Decision-Making) — ውሳኔዎቼን በማሰብና በጥበብ ነው የምወስነው ወይስ በስሜት ብቻ? በጫና ጊዜ የሚገለጥ ባህሪ (Character Under Pressure) — ነገሮች እንደፈለግሁት በማይሆኑበት ጊዜዓይነት ባህሪይ እገልጣለሁ? ራሳችሁን ከመምራት ተነስታችሁ ሰዎችን በመልካም ተጽእኖ ለመምራት እና እንዲሁም ስራችሁን በስኬታማነት ለማከናወን የሚረዳችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷልና አያምልጣችሁ፡፡ ለመረጃው የተያያዘውን poster ይመልከቱ!
የማንነታችን ወሳኝነት! “ወደ እናንተ የምትስቡት የምትፈልጉትን ሳይሆን የሆናችሁት ነው” ይባላል፡፡ ይህ ማለት የሰው ባህሪ፣ አስተሳሰብ፣ እሴቶች፣ ልምዶችና ከሌሎች ጋር የሚኖረው ተግባቦት ብዙ ጊዜ ወደ ሕይወቱ በሚመጡት ሰዎች፣ ግንኙነቶችና ዕድሎች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል ማለት ነው። ይህ ማለት በሕይወታችን የሚመጡት ነገሮች በአብዛኛው መነሻቸው የእኛ ማንነት እንደሆነ ጠቋሚ ነው፡፡ ምንም እንኳን ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ሁኔታዎች፣ ኢ-ፍትሐዊነት፣ አጋጣሚዎችና የሌሎች ሰዎች ውሳኔዎች ቢኖሩም፣ ነገር ግን የማንነታችን ጉዳይ ወደ እኛ የሚሳበውን ከመወሰኑ በተጨማሪ በሰዎች ምክንያት የሚመጡትን ነገሮች የመቆጣጠራችንን ሁኔታም ይነካል። ለምሳሌ፣ ታማኝ፣ ሰው አክባሪ እና እውነተኛና ከሆንን፣ እነዚህን እሴቶች የሚያከብሩ ሰዎችን የመሳብና ጤናማ ግንኙነት የመገንባት ዕድላችን ይጨምራል። ስለዚህ ጤናማ ግንኙነትን መፈለግ ብቻ አይበቃም፤ ጤናማ ግንኙነትን ሊገነባና ሊጠብቅ የሚችል ሰው መሆንም ያስፈልጋል። የሰዎችና የሁኔታዎች ጉዳይ ከማሳሰቡ ይልቅ መልካም ማንነት የመገንባታችሁ ጉዳይ ያሳስባችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የ2018 ዓመትን የመደምደሚያ ስልጠና! የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
የበቀል ወጥመድ አንድ ሰው ሲጎዳን በቶሎ የሚመጣው ስሜት ያንን ሰው መበቀል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የበቀል ስሜት ብዙ ጊዜ ትክክለኛ ምላሽ ይመስለናል፤ ምክንያቱም እፎይታ፣ ፍትሕ ወይም እርካታ እንደሚያመጣልን እናስባለን። እውነታው ግን በቀል ከምንበቀልበት ሰው ይልቅ ሂደቱ የሚጎዳ እኛንው ነው፡ 1. በቀል ካለፈው ጉዳት ጋር አስሮ ያቆየናል በቀልን የመፈለግ ዝንባሌ አእምሯችሁን ስለሚይዘው ከጎዳችሁ ሰው ውጪ ማሰብ እንዳትችሉ ያስራችኋል። ስለሆነም፣ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ሁልጊዜ ያንኑ ጉዳት እያሰባችሁ ትኖራላችሁ። 2. በቀል የመበቃቀል ዑደት ይፈጥራል እናንተ የተበቀላችሁት ሰው መልሶ እናንተን ሊበቀል ከፈለገ፣ ሁኔታው በዚያ መልክ ስለሚቀጥል አንድ የበቀል እርምጃ ሌላ የበቀል እርምጃን ይወልዳል። ከመፍትሔ ይልቅ ግጭትን ያባብሳል። 3. በቀል ሰላምን ይሰርቃል ብዙ ሰዎች ከተበቀሉ በኋላም የልብ ሰላም እንዳላገኙ ይናገራሉ። በቀል ለጊዜው እርካታ ሊሰጥ ይችላል፤ ነገር ግን ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን አያመጣም። 4. በቀል ፈውስን ያዘገያል በሰዎች ጉዳት ከመጣባችሁ ቁስል መዳን የምትምሩት ቁስሉን የሚያባብሰውን የበቀል እርምጃ ተወት አድርጋችሁ ራሳችሁን ማከም ላይ ስታተኩሩ ነው፡፡ የተሻለው አማራጭ ከበቀል ይልቅ፦ 🌠 ፍትሕን መፈለግ፡፡ 🌠 ከሁኔታው በመማር ለሰዎች ጤናማ ድንበሮችን (የግል መስመር) ማስቀመጥ። 🌠 ይቅር በማለት የልብን ቋጠሮ መፍታት። 🌠 ኃይልን በፈውስና በግል እድገት ላይ ማተኮር። በቀል እንዲህ ይላል፦ "እኔን እንዳሰቃየኸኝ አንተም እንደኔ እንድትሠቃይ እፈልጋለሁ።" ይቅርታ እንዲህ ይላል፦ "ያደረግክብኝ ነገር ሕይወቴን እንዲቆጣጠረው በፍጹም አልፈቅድም።" የበቀል ተቃራኒው የተፈጸመውን ክፋት እንዳልነበረ ማስመሰል አይደለም። ይልቁንም ከምሬት ይልቅ ነፃነትን እና ከበቀል ይልቅ ጥበብን መምረጥ ነው፡፡ ሰዎች ባደረጉባችሁ በደል ምክንያት በፍጹም ራሳችሁን ከማሳደግና ዓላማችሁን ከመከታተል ጎዳና አትውጡ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የበቀል ወጥመድ
የ2018 ዓመትን የመደምደሚያ ስልጠና! የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) ገለጻ:- 💡 ራስን መምራት (Leading Self) - ራሳችሁን የመምራት ጥበብ ካላዳበራችሁ ስሜታችሁ፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ይመሯችኋል፡፡ 💡 ሰዎችን መምራት (Leading Others) - ሰዎችን የመምራትን ብቃት ካላደበራችሁ ያላችሁ ተጽእኖ እየወረደ ይሄዳል፡፡ 💡 ስራን መምራት (Leading Work) - ስራችሁን የመምራት ክህሎት ካላዳበራችሁ ስኬታማነታችሁ እየደከመ ይሄዳል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!
የነሃሴውን ንባብ አሁንም መቀላቀል እንችላለን ወይ? ለምትሉ። መልሱ አዎን ትችላላችሁ የሚል ነው።
ዝም ብላችሁ እደጉ! ይህንን አባባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ፦ “ዛፍ ያረጁ ቅርንጫፎቹ እንዲወድቁ ኃይሉን አያባክንም። የደረቁ ቅጠሎቹን በማየት አይበሳጭም፤ ወይም ምን ማስወገድ እንዳለበት ለማግኘት ራሱን አያጨናነቅም። ዝም ብሎ ማደጉን ሲቀጥል መርገፍ ያለበት ይረግፋል፡፡" ዛፉ እያደገ፣ እየበረታና እየተጠናከረ ሲሄድ፣ ያረጁ፣ የማይጠቅሙና ሕይወት ሌላቸው ነገሮች በሙሉ ቀስ በቀስ ይደርቃሉ፤ በመጨረሻም በራሳቸው ይወድቃሉ። አዲሱ እድገት አሮጌውን በተፈጥሮ ይተካል። የዛፉ ትኩረት አንድን ነገር በማስወገድ ላይ ሳይሆን ራሱን በማሳደግ ላይ ነው። የእኛም ሕይወት ይህንን መርህ ቢከተል ፍሬያማነታችን የበዛ ይሆናል፡፡ ብዙ ጊዜ ድክመቶቻችንን፣ መጥፎ ልማዶቻችንን፣ አሉታዊ አስተሳሰቦቻችንን፣ ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶቻችንን ወይም የሚያሳምሙንን ትውስታዎች ለማስወገድ ብዙ ጉልበት እናጠፋለን። ራስን መመርመር ጠቃሚ ቢሆንም፣ ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው አሮጌውን በመዋጋት ብቻ አይደለም፤ አዲሱን በማሳደግ ነው። ❇️ በጥበብ ስናድግ፣ አለማወቅ ቀስ በቀስ ይጠፋል። ❇️ ጥሩ ልማዶች ስናዳብር፣ አጥፊ ልማዶች ኃይላቸውን ያጣሉ። ❇️ አእምሯችንን በእውነት ስንሞላ፣ ውሸት እየደከመ ይሄዳል። ❇️ ጤናማ ግንኙነቶችን ስንገነባ፣ ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች ተጽእኖአቸውን ያጣሉ። ❇️ የሕይወት ዓላማችንን ስናገኝ፣ የሚያዘናጉ ነገሮች ማራኪነታቸውን ያጣሉ። “ምን ላስወግድ?” ከማለት ይልቅ፣ “እንዴት ማደጌን ልቀጥል?” ብለን መጠየቅ ይሻላል። ብዙ ጊዜ የሁለተኛው ጥያቄ መልስ፣ የመጀመሪያውን ጥያቄ ይፈታል። ጨለማ ብርሃን ባለበት ቦታ መቆየት እንደማይችል ሁሉ፣ ጤናማ እድገት በቀጣይነት በሚኖርበት ሕይወት ውስጥ ጤናማ ያልሆኑ ልማዶችም ለመቆየት ይቸገራሉ። ዝም ብላችሁ ራሳችሁን አሳድጉ!!! ሰልጥኑ! አንብቡ! በስሜት ብልህነት እደጉ! የቀረው ነገር በራሱ እየረገፈ ይሄዳል! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/