MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™
Статистикаአስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣ አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣ ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው። @mikreaimro ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል! ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ! 🏠Welcome to your Home! 🏘 Personal Contact: @epha_aschalew Insta: instagra.com/epha_aschalew
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 990
- 1/48двое суток
- 1 134
- 1/72трое суток
- 1 223
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
без подписи
🤓 ከመፅሐፉ የተወሰደ! 5️⃣ አይነት እረፍቶች ያስፈልጉሃል! 1️⃣መንፈሳዊ በመጸለይ፣ በማሰላሰል 2️⃣ ስሜታዊ በመጻፍ፣ ራስን በመንከባከብ 3️⃣ ፈጠራዊ በመሳል፣ በመጻፍ፣ አዲስ ነገር በመሞከር 4️⃣ማህበራዊ ከምትወዳቸው ጋር በመሆን 5️⃣ አዕምሯዊ እረፍት በማድረግ፣ መዝሙር ወይ ሙዚቃ በመስማት 📚 LIMITLESS | ገደብ የለሽ ሁን መጽሐፍ ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
💥📣ለሰው አትዘኑ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/1mRBvJx5BRo?is=vauNWiskYVoZ416R
ሁሉንም ዝጋ! ⚠️‼️‼️⚠️ ለስራ ስትነሳ፣ መራመድ ስትጀምር፣ ሩቅ ማሰብ፣ ትልቅ ማለም ስትጀምር ሊጠልፍህ የሚሰናዳውን፣ ከፊትህ የሚቆመውን፣ የሚያዘናጋህን፣ የሚያሸብርህን እያንዳንዱን ነገር ዝጋው። ፈተናዎችህን ቀንስ፣ ጥረትህን ጨምር፤ መሰናክሎችህን አስወግድ በምትኩ ጥሩ መሻገሪያ ድልድይ አዘጋጅ፤ ግፊቶችህን አርቅ በምትኩ ድንቅ መወጣጫ አሰናዳ። በስሜት ለመጓዝ ማወቅ የሚገባህ የሌሎችን ህልም ሳይሆን የእራስህን ህልም ነው፤ እራስህን ነው፤ ማንነትህን ነው። አንተ ባለህበት ሁሉ የሚረብሽህ ነገር ሁሌም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል። ስራዬ ብለህ ጊዜ ከሰጠሀው፣ ከሰማሀው፣ በጥልቀት ካዳመጥከው ይጥልሃል፤ ተሻግረህ ጥለሀው ካለፍክ ግን እርምጃህን ያስተካክላል፤ መንገድህን ያቃናል። አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉንም ዝጋ! ሁሉንም አስወግዳቸው። ከማይሆኑ አመለካከቶች ጀምሮ፣ የሚረብሹ እየታዎችን ጨምሮ፣ ተስፋ አስቆራጭ ሁነቶችን አካቶ። ወደፊት መጓዝ ከፈለክ ትኩረትህን መሰብሰብ፤ አንድ ነገር ላይ ብቻ ማዋል ይኖርብሃል። የተበተነ ትኩረት ለተበተነ ጥረት ይዳርጋል፤ ያልተጨበጠ፣ የማይታይ እንዲሁ ድካምና ልፋት ብቻ የሆነ አሰልቺ ጉዞ ይሆናል። አሸንፋለሁ ካልክ በዙሪያህ የሚያሰናክሉህን፣ የሚረብሹህን ነገሮች ማስወገድ ተለማመድ። በSocial Media ሱስ ተጠምደህ፣ ካንተ ከማይሻሉ ሰዎች ሃሳብ እየተቀበልክ፣ ህልምና ራዕይ በሌላቸው ሰዎች ተከበህ፣ ችሎታህን የሚያሳንስ፣ አቅምህን የሚገድል ስራ ጀምረህ ትልቁን የስኬት አለም ሳይሆን በትንሹም እራስህ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር አትችልም። አዎ! ሃሳብ ስላለህ ብቻ ሳይሆን በሃሳብህ ዙሪያ የሚያንዣብቡትን አሰናካይ ሃሳቦች ማስወገድ ስትችል ከከፍታው ትደርሳለህ፣ ለስኬቱ ትበቃለህ። በጊዜ እንዳትነሳ ስለሚያደርጉህ፣ ማንበብ እንዳትችል፣ አዳዲስ ሰዎችን እንዳትተዋወቅ፣ ህልምህን እንዳትኖር፣ እቅዶችህን እንዳታሳካ፣ ቤተሰቦችህን እንዳትረዳ፣ ለጓደኞችህ እንዳትደርስ፣ በሃሳብህ ልክ እንዳትጓዝ፣ ለራዕይህ እንዳትፋለም የሚረብሹህ፣ የሚያሰናክሉህ፣ ወደኋላ የሚጎትቱህ ነገሮች ምንድናቸው? የኋላቀርነትህ ምክንያት ችሎታህ ሳይሆን ከባቢህ ሊሆን እንደሚችል አስታውስ፤ ድክመተህ ካንተ ሳይሆን ከጫናዎች ብዛት ሊሆን እንደሚችልም አስተውል። በአለማችን ትልቁ የስኬት ጠላት ትኩረት ማጣት ወይም በብዙ ነገሮች መረበሽ (distraction) ነው። በትልቁ ታስባለህ ነገር ግን ሃሳብህን መኖር አልቻልክም፤ በፈለከው መጠን በንቃት ልታደርገው አልተሰናዳህም፤ ትክክለኛውን ጊዜ እየጠበክ መረበሽህን ቀጥለሃል፤ የተሻለ ነገ እስኪፈጠር በሃሳብህ እየተብሰለሰልክ ነው። እያንዳንዱን የሚረብሹህን መንገዶች ዝጋ፤ ሙሉ ትኩረትህን የአምላክህ ሃይል ላይ፣ እራስህ ላይና ህልምህ ላይ ብቻ አድርግ። በቅርቡ ካንተም በላይ ከባቢህ ተቀይሮ ትመለከተዋለህ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ pinned a photo
💥📣ጨካኝ ሰው ሁኑ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/5R6Qj616fUo?si=uIc01utGibiyVc4J
‼️⚠️በስሜትህ እየተመራህ ነው ወይስ ስሜትህን እየመራህ ነው? አብዛኛውን ጊዜ በህይወታችን፣ በስራችን፣ በገንዘብ አያያዛችን፣ በፍቅር ግንኙነታችን ወይም በትዳር ውስጥ የምንሰራቸው ትልልቅ ስህተቶች የችሎታ ወይም የእውቀት ማነስ ሳይሆኑ የስሜት ቁጥጥር ማጣት (Emotional Control) ውጤቶች ናቸው። 🗣️ በቁጣ ጊዜ የሚነገሩ በጥበብ ያልተመዘኑ እና ግንኙነትን የሚያበላሹ ቃላት 🗣️ በጭንቀት እና በፍርሃት ምክንያት የሚያመልጡ ትልልቅ የህይወት እና የንግድ እድሎች 🗣️ ሰዎችን ላለማስቀየም "አይ" ማለት አቅቶን የምንሸከመው አላስፈላጊ የሰው ጫና 🗣️ በቅጽበታዊ ስሜት ተነዳስተን የምንወስዳቸው እና በኋላ የሚያስቆጩን ውሳኔዎች ይህ ሁሉ የሚያሳየን አንድ ነገር ነው፡ EMOTIONAL INTELLIGENCE (የስሜት ብልህነት) ከሌለን እውቀታችን እና ችሎታችን ብቻውን ሙሉ ስኬታማ ሊያደርገን እንደማችል ነው። ➡️በዚህ ጉዳይ እየተቸገራችሁ ከሆነ በአይነቱ ለየት ያለ የአንድ ለአንድ / የ One to One ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል። ርዕስ "የስሜትህ ጌታ ሁን " 1-on-1 Personal Mentorship ℹ️ ይህ ስልጠና ከብዙ ሰው ጋር በቡድን ከመማር ይልቅ፣ በግል ህይወታቹ፣ ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት፣ በስራ፣ በፍቅር ግንኙነታቹ ወይም በትዳር ህይወታቹ ውስጥ ያሉትን የግል ችግሮች ከእኔ ጋር በግል (1-on-1) ለመፍታት እና የስሜታቹ ጌታ ለመሆን ለምትፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ልዩ የግል ማማከርና ስልጠና ነው! ለ4 ሳምንታት በእኔ እና በእናንተ መካከል ብቻ በሚደረግ ቀጥታ ግንኙነት፣ በነርቭ ሳይንስ | Neuroscience እና በባህሪ ሳይኮሎጂ | Behavioral Psychology የተደገፉ ተጨባጭ የህይወት ክህሎቶችን በተግባር እንለማመዳለን። ℹ️ በዚህ 1-on-1 ስልጠና ውስጥ ምን ታገኛላቹ? ሳምንት 1 (የግል የስሜት ኦዲት): የራሳቹን የተደበቁ የስሜት ቀስቃሾች (Triggers) እና የቆዩ አስተሳሰቦችን በግልፅ መተንተን። ሳምንት 2 (ለናንተ ብቻ የተዘጋጀ መቆጣጠሪያ): በቁጣ፣ በንዴት፣ በችኮላ፣ ራስን በመጠራጠር፣ በብቸኝነት፣ በጭንቀት ወይም በፍርሃት ጊዜ ለናንተ ብቻ በሚመጥን መልኩ አእምሮን ወዲያውኑ የማረጋጋት ቴክኒክ (Custom Regulation)። ሳምንት 3 (የግል ግንኙነቶች እና ተጽዕኖ): በፍቅር፣ በስራ ወይም በቤተሰብ ውስጥ ያሉ የተበላሹ ግንኙነቶችን ማስተካከል እና የሰዎችን ስሜት የማንበብ ጥበብ። ሳምንት 4 (ድንበር ማበጀት): ሰዎችን ሳይጎዱ እና ሳያራቁ በልበ ሙሉነት "አይ" የማለት እና የግል የትግበራ እቅድ (Personal Action Plan) ማዘጋጀት። 🎁 ተጨማሪ የ1-on-1 ጥቅሞች፡ © በየሳምንቱ 1 ሰአት በPrivate Live በቀጥታ የሚደረግ የግል ክፍለ-ጊዜ © በሴሽኖች መካከል በTelegram / WhatsApp የዕለት ተዕለት የትግበራ ድጋፍና ክትትል © ለናንተ ብቻ የተዘጋጁ የግል የትግበራ ማስታወሻዎች (Custom Worksheets) ⚠️ የቦታዎች ብዛት እና ምዝገባ ለእያንዳንዱ ሰልጣኝ ሙሉ ትኩረት ለመስጠት እና ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት በወር የምንቀበለው በጣም ጥቂት ሰዎችን ብቻ ስለሆነ አስቀድማቹ ቦታ ያዙ። 📈 የስልጠናው ቆይታ: 4 ሳምንታት (በጠቅላላው 4 የግል ሴሽኖች) 📍 ቦታ: በTelegram Live/WhatsApp/IMO/ Private Zoom /Google Meet በሚችሉት አማራጭ 🖥 አሁኑኑ ቦታ ለመያዝ እና የቅድመ-ምዝገባ መጠይቁን ለመሙላት አውራኝ: 💎 [@epha_aschalew] 📞 [0963831491]
ሁሉም ይቀናብሃል! ⚠️⚠️‼️⚠️⚠️ አንድን ሰው የተራራው ጫፍ ላይ ብንመለከተው ሁሉም ሰው የሚቀናው የተራራው ጫፍ ላይ በመውጣቱ እንጂ በአወጣጡ አይደለም። እንዴት እዛ ይድረስ? ምንያህል ቀን ይፍጅበት? ስንቴ ወደቀ? ስንቴ ተነሳ? የማንም ጉዳይ አይደለም። ሰው የሚቀናው አስቀድማችሁ ባለፋችሁት ስቃይ ሳይሆን በስተመጨረሻ በምትጎናፀፉት ድል ነው። ብዙ ሰው ደስታችሁን ይመኛል ነገር ግን ከዛ በፊት ምንያህል ጨለማ ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ማወቅም አይፈልግም፤ ብዙ ሰው ስኬታችሁን ይናፍቃል ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን ያደረጋችሁት ከባድ ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ አይደለም። ህይወት በምኞት ብቻ የምትሳካ አይደለችም። ሁሉም በየደረጃው ስራ ይፈልጋል። ህልምን ሲተኙ ብቻ መመልከትና ቆሞ የስኬታማ ሰዎችን ህይወት መመኘት አንድ ናቸው። ሁለቱም በምናብ ወደምንፈልገው ስፍራ ይወስዱን ይሆናል እንጂ በፍፁም በተጨባጭ እዛ አያደርሱንም። ዓለም የህልመኛ እጥረት የለባትም፣ ምድር የባለራዕይ ችግር የለባትም። ዋናው ችግሯ ህልሙን ለማሳካት መሱዓትነት የሚከፍል ሰው ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም ይቀናብሃል! ትንሹም ትልቁም፣ አዋቂውም አላዋቂውም፣ ሰነፉም ብርቱውም አንተ የደረስክበትን ከፍታ ይመኘዋል። ነገር ግን ምኞት ብቻውን ግን ያንተ ስፍራ እንደማያደርሳቸው አልተረዱም። ብዙ ምርጫ ነበረህ ነገር ግን ስኬትን ብቻ መርጠሃል፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ጀምሮ ማቆም፣ ሌላ ነገር መሞከር ትችል ነበር ነገር ግን አላደረከውም። ህልምህን ከደምህ ጋር አስተሳስረሀዋል፣ ውስጥህን በማይበገር ፅኑ ማንነት አንፀሀዋል፣ መንፈስህን እስከ ጥግ አጠንክረሀዋል። ይህን ሁሉ ማደረግ የሚችል ያንተ ቦታ አይደለም አንተ ካለህበት ቦታ የሚበልጥ ቦታ መድረስ ይችላል። የትኛውም የሚያስቀና ህይወት የሚያስቀናው መጨረሻው እንጂ መጀመሪያው አይደለም። ተቀምጦ መመኘት ተነስቶ እንደመስራት ከባድ አይደለምና ብዙዎች ይመኛሉ ጥቂቶች ብዙዎች የሚመኙትን ህይወት ይኖራሉ። አንድ ጠጠር እንኳን ሳይጥሉ የተሳካ ህይወት ለመኖር መሞከር ከንቱ የሀሳብ ድካም ነው። አዎ! አሸናፊዎች ሁሌም ያሸንፋሉ፤ ተሸናፊዎች ሁሌም ይሸነፋሉ። ከዚህ የተለየ ህግ የለም። ማሸነፍ እንደምትችል ከልብህ አምነሃል፣ ለአሸናፊነት የሚያበቃህን ስራ ሰርተሃል፣ መክፈል ያለብህን ዋጋ ከፍለሃል፣ የሚገባህን አሸናፊነት በእጅህ አስገብተሃል። ተሸናፊውም ሽንፈትን መርጧል፣ በቀላሉ ተስፋ ለመቅረት ወስኗል፣ ጀምሮ ማቆምን እጣፋንታው አድርጎታል። ከአዕምሮው ስሜቱ በልጦበታል፣ ከዘላቂው ስኬት ጊዜያው ደስታ ሚዛን ደፍቶበታል፣ ከአላማው ወቅታዊው አጀንዳ ስሜት ሰጥቶታል፣ በእቅድ ሳይሆን በስሜት ይጓዛል፣ ብዙ ይመለከታል ብዙ ያውቃል ነገር ግን ሚዛናዊ ውሳኔ መወሰን አይችልም። ይሔ ሰው አሸናፊነት ከባህር ማዶ እንዳለች ደሴት ርቆታል፣ ምኞት እንጂ እውነታው ሊሆንለት አይችልም። ህይወት ምርጫ ነች ሲባል ቀላል ምርጫ እንዳልሆነች መረዳት ያስፈልጋል። ሰው አዝኖልህ እንዲረዳህ ከፈለክ ምርጫው ያንተ ነው፤ በስራህ ተደስቶም እንዲሸልምህ ከፈለክ ምርጫው ያንተ ነው። "ምንም የለኝም፣ ምን ላድርግ? ሰው የለኝም፣ እንዴት ብቻዬን ልስራ?" ካልክ አሁንም ምርጫህ ነው። "ባለኝ ጀምሬ ላሳይ፣ ብቻዬን የምችለውን አድርጌ ውጤቱን ልመልከት" ካልክም ምርጫው ያንተ ነው። አሸናፊነትን እስከመረጥክ ድረስ ስሜትህን ጥለህ በማይናወጠው አቋምህ እንደምትመራ አስታውስ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
💥📣የተረጋጋ ሰው ሁኑ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/eBYCwptwn3k?si=f-YAsKxhSL1M6DaJ
💥📣 ሰው እንዳይንቃቹ እነዚህን አስወግደሐ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/OHMnxyPupR8
ልባችሁን ተከተሉ! ⚠️⚠️‼️⚠️⚠️ የሁለት ሃሳብ ግጪት መሃል ብትሆኑ፣ ግራመጋባት ፋታ ቢነሳችሁ፣ ምርጫ ቢበዛባችሁ፣ ከዚህም ከዛም ጫናዎች ቢያይሉባችሁ፣ ወደህም ወዲያም ለመሔድ ብትቸገሩ፣ በጭንቀትና ስጋት ካላችሁበት ስፍራ መንቀሳቀስ ቢሳናችሁ ምንም ከማድረጋችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ልባችሁ የሚመራችሁን አቅጣጫ ተመልከቱ፣ ከስሜታችሁ በላይ ሚዛናዊው አዕምሯችሁ ወዳዘነበለበት አዘንብሉ። በህይወት መንገድ ግራ መጋባት፣ አጣብቂኝ መሃል መውደቅ፣ ከቀረቡት አማራጮች የተሻለውን ለመምረጥ መቸገር ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ልባችንን ማዳመጥ የተሻለውን አማራጭ ያቀርብልናል። ሃሳብ ሁሌም አለ፣ ስሜት ዘወትር ይቀያየራል፣ ማንም ይጨነቃል፣ ያወጣል ያወርዳል መጨረሻው ግን ከሁለት አንዱ ነው። ወይም አንዱን ይወስናል ወይም ከሁሉም አማራጮች ሳይሆን ይቀራል። አዎ! ጀግናዬ..! በስሜትህ እየተገዛህና የውስጥ ፍላጎታህን እያዳፈንክ የምትጓዝ ከሆነ፣ ለውጫዊ ጫናዎች እራስህን አሳልፈህ ከሰጠህ፣ ለጊዜያዊ ጥቅም ቅድሚያ ከሰጠህ የአጣብቂኝ ብዛት፣ የሃሳብ ዥረት፣ የጭንቀት መዓትና የግራመጋባት አባዜ ሊለቅህ አይችልም። በስሜታዊነት ከምትፈታው ችግር በላይ የምትፈጥረው ችግር ይበዛል፣ የልብ መሻትህን ወደጎን እያልክ በውጫዊ ተፅዕኖ ብትመራ ትክክል ከምትሆነው በላይ የምትሳሳተው መንገድ ይበዛል። እራስን ማወቅ ከጫናዎች ነፃ ያወጣሃል፣ እራስህን ባወከው ልክም በተግባር ሚዛናዊና የልብ መሻትን ያማከለ ውሳኔ መወሰን ለተሻለው ምርጫ ያበቃሃል። በህይወትህ ውስጥ ያለውን ምርጫ የተባለውን ትልቁን የእግዚአብሔርን ስጦታ በጥንቃቄ ተጠቀም። አዎ! ልባችሁን ተከተሉ፣ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ከስሜታችሁ በላይ ሚዛናዊው የአዕምሮ ሃሳባችሁ ላይ አተኩሩ፣ ለጭንቀትና ለፍረሃት ከሚዳርጓችሁ አማራጮች በላይ ምንም እንኳን የተለየ ዋጋ ቢያስከፍሏችሁም ውስጣዊ ሰላማችሁን የሚያረጋግጡና የሚያረጋጓችሁን አማራጮች ምረጡ። ከምንም በላይ የውስጥ ፍላጎታችሁን አስቀድሙ፣ ከማንም ተፅዕኖ በላይ እራሳችሁን አዳምጡ። ማንም ቢወስንላችሁ ሃላፊነቱን አይወስድላችሁም፣ ማንም ቢመርጥላችሁ ምርጫውን አስታኮ ለሚመጣው አደጋ እራሱን አሳልፎ አይሰጥላችሁም። አጣብቂኝ ውስጥ ብትገቡ፣ ግራ ቢገባችሁ፣ ለውሳኔ ብትቸገሩ ተረጋጉ፣ ከማንም በላይ እራሳችሁን ለማወቅ ሞክሩ፣ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ ፍላጎታችሁን በጥልቀት መርምሩ፣ ለልብ መሻታችሁ ቅድሚያ ስጡ፣ በጥበብ በማስተዋል ህይወታችሁን ምሩ፣ ሰላማዊና አስደሳች ህይወትንም ኑሩ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
💥📣ድብቅ የማጭበርበር ስልቶች? ከእነዚህ ሰዎች ተጠንቀቁ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/b0Z2bvEWHWo?si=aDpJ8GZMnvBDK6sV
በድካምህ አትዘናጋ! ⚠️⚠️‼️‼️⚠️⚠️ ሰውነት ደካማ ነው። የሆነ ጊዜ ሃይሉን ያጣል፣ የቀደመ ተነሳሽነቱ ይመክናል፣ እንደ በፊቱ መነቃቃትና ጠንክሮ መስራት ይሳነዋል። ይሔ ተፈጥሮ ነውና ምንም ብታደርግ ልትቀይረው አትችልም። ነገር ግን መቀየር የምትችለው አንድ ነገር ይኖራል እርሱም በሁነቱ መዘናጋት ማቆም ነው። ለድካምህ እጅ አትስጥ፣ በድብርት አትሸበር፣ በዝለት ውስጥህን አታውክ። ምርጫው የአንተ ነው። ማንም የማይደክም የለም ድካሙን ውጦ፣ ዝለቱን ችሎ፣ ድብርቱን ጥሎ የሚያልፍ ግን በጣም ጥቂት ነው። ወደኋላ መመለስ፣ ራስን ማደስ፣ ስሜትን ማስተካከል የብስለት እንጂ የሞኝነት ምልክት አይደለም። በደከመህ ሰዓት ራስህን ጫና ውስጥ አትክተት ፋታ ውሰድ፣ ራስህን ዳግም አንፅ እንደገናም ወደ ጀመርከው መንገድ ተመለስ። ሁሌም የሚከተሉህ ነገሮች አሉ። እነርሱም የሚረብሹህ ነገሮች ናቸው። አያስፈልጉህም ነገር ግን እንደሚያስፈልጉህ ሌት ከቀን ይከተሉሃል፤ አይጠቅሙህም ነገር ግን ሁሌም እንደሚጠቅሙህ እንድታምን ያደርጉሃል። በሂደት ስሜትህን ያውኩታል፣ ተነሳሽነትህን ይገድሉታል፣ የሃሳብ ውቂያኖስ ውስጥ ይከቱሃል፣ ድካምና ዝለት እንዲቆጣጠሩህ ያደርጉሃል። አዎ! ጀግናዬ..! በድካምህ አትዘናጋ፣ ለዝለትህ አትበገር። ሲመጣ ዘላለም የሚደክምህ ይመስልሃል፣ ስትገናኙ እንደሚቆጣጠርህ ሊያሳይህ ይጥራል። በእርግጥ ግን ያላንተ ፍቃድ እርሱ ምንም አቅም የለውም። የሆነ ጊዜ ሊሰብርህ ይችላል ነገር ግን ሁሌም ሊሰብርህ አይችልም፤ የሆነ ጊዜ ስሜትህን ሊያውከው ይችላል ነገር ግን ሁሌም ሊያውከው አይችልም። ለቀጣዩ ከፍታህ አሁን ዝቅ ማለትህን አትፍራ። ነገሮች በትናንቱ መንገድ አይቀጥሉም። ማግኘት ማጣት፣ መውደቅ መነሳት፣ ማትረፍ መክሰር ያለና የሚኖር ነገር ነው። ተሰብሮ መቅረትን በፍጹም ምርጫህ አታድርግ፣ ለውጣውረዱ መሸነፍን መቼም ምርጫህ አታድርግ። ብርቱ ጦረኞች ተዋግተው እስኪያሸንፉ አያቆሙም፤ ጠንካራ ሰራተኞች የሚፈልጉትን እስኪያገኙ ወደኋላ አይመለሱም። ያንተ ጦርነት ከህይወት ፈተና ጋር ነው፤ ያንተ ግብግብ ከስሜት ውጣውረድህ ጋር ነው። ሳታሸንፍ የሚያቆም ጥረት አይኖርም፤ አላማህን ሳታሳካ የሚታጠፍ እጅ የለም። ፍረሃት ሊያስርህ ቢፈልግ አሻፈረኝ ትለዋለህ፣ ጭንቀት አቅም ሊያሳጣህ ቢሞክር አቅምህን ታሳየዋለህ። አዎ! ከጫናዎች ብዛት ትወድቅ ይሆናል ነገር ግን ዳግም ትነሳለህ፣ በድካምህ ምክንያት ስሜትህ ይረበሽ ይሆናል ነገር ግን እነደገና ወደ ትክክለኛው መንገድ ታገኘዋለህ። ያንተን ምርጫ ብዙዎች አይመርጡትም ምክንያቱም ምርጫህ እጅግ ከባድ ነውና፤ ባንተ መንገድ ብዙዎች አይጓዙበትም ምክንያቱም ምቾት የለውምና። ዝቅ መደረግ ብርቅህ አይደለም፤ በሰዎች እይታ ትንሽ መምሰል አዲስህ አይደለም። የግል ህይወትህ ተቆጣጣሪ አንተ ነህ። ዓለም ቢያብርብህ፣ ሰው ሁሉ በተቃራኒህ ቢቆም ከእውነተኛው ማንነትህ ጋር ከተሰለፍክ ማንም ሊያንቀሳቅስህ አይችልም። አቅም አለህና አቅምህን አውጥተህ ተጠቀም፤ ችሎታው አለህና ለውጤት አብቃው። አውቀቱ አለህ እርሱንም ከጊዜያዊ ሙቀት በላይ ለዘላቂው ውጤት ተጠቀመው። ብዙ ሰው የማያየውን በውስጥህ መመልከት ትችላለህ፣ ብዙዎች የተሰናከሉበት ጊዜያዊ ድካምና ድብርት አያቆምህም። አንተ ስትበረታ ፈተናው ጉልበት ያጣል፣ አንተ ስራህን ስትመርጥ የናቁህ ያፍራሉ። ስራህን ወጥረህ ስራ፣ ለምርጫህ እንደምትገባ አስመስክር፣ እንቅፋቶችህን ሁሉ ጥለህ ማለፍ እንደምትችል አሳይ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
💥📣ዘወትር ከመኝታ በፊትና ቦሃላ አዳምጡት? 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/GcQSKg9d3vg?si=rJ7HAhFpU9AtoHRy
በግድ ውደቁ! ⚠️⚠️💎💎 የዓለም አስተምህሮ እንጂ እውነታው የውድቀትን አስከፊነት አያሳይም። ውድቀት ዘርፈ ብዙ ነው። ለአንዳንዱ በሰዎች ተቀባይነት አለማግኘት ውድቀት ነው፤ ለጥቂቶች የሚፈልገውን ህይወት አለመኖር፣ ለሌላው በገንዘብ በንብረት የተሻለ ሰው አለመሆን ውድቀት ነው። ነገር ግን ብዙዎቹ ውድቀት ባሉት ነገር ከማዘን በቀር የውድቀታቸውን አስፈላጊነት ማሰብ አይፈልጉም። በህይወት አላችሁ ስለዚህ ደጋግማችሁ ትወድቃላችሁ፤ ከሰው ጋር እየኖራችሁ ነው ስለዚህ የሰውን አስከፊ ገፅ ደጋግማችሁ ትመለከታላችሁ፤ አላማችሁን ለማሳካት ወስናችኋል ስለዚህ በየጊዜው መውደቃችሁ አይቀርም። ባትፈልጉም የተሻለ ነገር ይገባችኋልና መፈተናችሁ የግድ ነው፤ ባትዘጋጁበትም ጥሩ ሰው ይገባችኋልና በሆነ ሰው መጎዳታችሁ የግድ ነው። እንደማይሳካላችሁ ተነግሯችኋል እውነት ነው የሆነ ጊዜ አይሳካላችሁ ይሆናል ህይወታችሁ ግን ሙሉ በሙሉ ያለ ስኬት አይጠናቀቅም። ማንም ሰው እጣፈንታው ተወስኖ ወደ ምድር አልመጣም። ቢያሻው ያሳምረዋል፣ ካላሻውም እንዲሁ እያበላሸው ይኖራል። አዎ! አስባችሁ ፈልጋችሁ በግድ ውደቁ፤ በግድ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ። ውድቀታችሁ ግን ለላቀው ከፍታችሁ መዘጋጂያ ይሁናችሁ፣ ዝቅታችሁ ግን ትልቁን የህይወት ትምህርት መማሪያ ይሁናችሁ። ዛሬ ላይሳካ ይችላል፣ ነገ ላይሳካ ይችላል፣ እንዲሁ ከነገወዲያም ላይሳካ ይችላል ነገር ግን ተስፋ ከቆረጣችሁ አንድ ማረጋገጫ አላችሁ እርሱም መቼም እንደማይሳካ ነው፤ በዛሬ ውድቀታችሁ ካቆማችሁ መቼም ያሰባችሁበት ቦታ አትደርሱም። ለብዙዎች ውድቀት የህይወታቸው ፍፃሜ ይመስላቸዋል። ፍፃሜው ግን ውድቀት ሳይሆን ተስፋ ማጣት፣ የነገን ብረሃን መመልከት አለመቻል ነው። "የት ይደርሳል የተባለ ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው" ተብሎ የተተረተው ለእናንተ እንዳልሆነ በተግባር አሳዩ። የት ትደርሳላችሁ ተብሎ ሲጠበቅ በሰው ትቺት ምክንያት ወድቃችሁ አትቅሩ፤ ለስንተ ነገር ስትጠበቁ በትንሽ የአሰራር ህፀፅ ምክንያት ከጥረታችሁ አትገቱ። ለውጥና እድገታችሁን የማይፈልግ በጣም ብዙ አካል አለ፣ ያ ግን የእናንተ ሳይሆን የዛ አካል ፍላጎት ነው። የእናንተ ፍላጎት ያላመነባችሁን ማሳፈር ነው፤ የእናንተ ምርጫ ከናቃችሁ በላይ ደምቆ መታየት ነው፤ የእናንተ ውሳኔ በየቀኑ ጥራታችሁን መጨመር ነው። አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ቀን ሳይሆን በዛሬው ቀን አንድ ቀና ብለህ መራመድ ትጀምራለህ፣ በዛሬው ቀን ውድቀትህን ሽረህ ትመለሳለህ፣ በዛሬው ቀን ተስፋህን አድሰህ በልበሙሉነት ትቆማለህ። የራስ መሰናክል መሆን ዛሬ ያበቃል፣ ራስን ማጣጣል ዛሬ ያበቃል፣ ከራስ ጋር ባላንጣ መሆን ዛሬ ይቋጫል። ከፈጣሪና ካንተ በላይ ያንተ ህይወት ግድ የሚሰጠው አካል እንደሌለ አስተውል። ወድቀህ ብትቀር የብዙዎች መቀለጃ ትሆናለህ፤ ተስፋህን በሰዎች ላይ ብትጥል ባዶህን ትቀራለህ፣ ፍረሃትህን አምነህ ብትቀበል ለህይወትህ የጨለማ ክፍል ትጋለጣለህ። ስኬታማዎች ደፋሮች ናቸው፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የውድቀት አለቆች ናቸው። ለመውደቅ ደፋር ሁን፤ ለራስህ ለመታገል ልብህን አደንድን። ፅኑ ታጋዮች ያሸንፋሉ፣ ከልብ የሚፋለሙም ድልን ይቀዳጃሉ። ከልብህ ከህይወት ጋር ተፋለም፣ ያጠቁህን በስልት አጥቃ፣ ያሸበሩህን በብልጠትም ይሁን በንቀት ጥለሃቸው እለፍ። በፀሎትህ በርታ፣ ከመቼውም በላይ መንፈሰ ጠንካራ ሁን። ለሚገባህ የተሻለ ህይወት ራስህን ግዛ፣ ግዛትህንም አስጠብቅ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
ጠላትህን ሻረው! ፨፨፨////////፨፨፨ ትልቁ ጠላትህ ራስህ ነህ። ውዱን ጊዜህን ዛሬ በአግባቡ ከመኖር ይልቅ ስለነገ አብዝትህ በመጨነቅ እያባከንከው ነው፤ ነገ ቶሎ ውጤት እንዲያመጣልህ የምትሰራው ምንም ነገር የለም፣ አሁን የምትኖረው በግማሽ ነው። አዕምሮህ በብዙ ሀሳቦች ተውጧል፣ ውስጥህ ለመረጋጋት ተቸግሯል፣ ለችግሮችህ መፍትሔ መፈለግ ተስኖሃል። ምክንያቱም ዛሬን መኖር አልቻልክም፣ ባለህ ነገር ማመስገን አልቻልክም፣ በረከቶችህን መቁጠር አልቻልክም፣ አይንህ ሁሌም ጉድፍ ይመለከታል፣ ጆሮህ ሁሌም መዓቱን ይሰማል፣ ውሎህ በሚመርዝህ ስፍራ ነው፣ ለሆነብህ ክፉ ነገር ሌላውን ትወቅሳለህ፣ ላጋጠመህ መልካም ነገር ደግሞ ዋጋውን ለራስህ ትሰጣለህ። ሁሉን እያወቅክ ከራስህ ጋር አታካራ ውስጥ አትግባ። ዛሬም ቢሆን እውነታውን አምነህ እስካልተቀበልክ አንዳች የሚቀየር ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም። ማንም ከሚያውቅህ በላይ ራስህን ታውቃለህ፣ ትኩረትህ ምን ላይ እንደሆነ፣ ተስፋህ ምን እንደሆነ፣ የዛሬው ሁኔታህ የት እንደሚያደርስህ ካንተ በላይ የሚያውቅ የለም። አዎ! ጀግናዬ..! ጠላትህን ሻረው፣ ዛሬን በአግባቡ እንዳትኖር፣ ምናባዊው ዓለም ላይ እንድትንሳፈፍ፣ ያለህን ጥሩ ነገር እንዳታጣጥም የሚያግድህን ውስጣዊ ጠላትህን ሻረው፣ ትኩረት አትስጠው፣ እንዲቆጣጠርህም አትፍቀድለት። አውቀህም ይሁን ሳታውቅ ራስህን በውሱንነት መቅጣትህን አቁም። ልበ ብሩህ ከሆንክ የሚታይህ ብረሃን ነው፣ ውስጥህ የተረጋጋ ከሆነ ማንም ትኩረትህን አይበትነውም። እርግጥ ነው ፈጣሪ ነገን መልካም ያደርገዋል፣ አንተ ግን ለመልካሙ ነገህ ዛሬ ምን እያደረክ ነው? እውነት ነው ወደፊት የሚታይህ ብሩህ ቀን ይመጣል፣ አንተ ግን ዛሬህን ምንያህል ብሩህ ለማድረግ እየጣርክ ነው? የትኛውም በጎ ነገር ስራ ይፈልጋል። ከሀሳብ መዓበል ራሳቸውን የታደጉ፣ ትናንቱን እንደ ትናንት፣ ነገንም እንደ ነገ አምነው ተቀብለው ዛሬ የሚችሉትን ብቻ የሚያደርጉ ሰዎች ምነኛ ጥበበኞች ናቸው? ህይወትስ ምንያህል ገብታቸው ይሆን? ህይወትን በሚገባ ካልተረዳህ እድሜ ቁጥር ብቻ እንደሆነ አስታውስ። አዎ! የሚያውቁትን የሚኖሩ እነርሱ ከፍታቸው ከማንም ይልቃል፣ የያዙትን ይዘው ለወደፊታቸው ጠንክረው የሚሰሩ እነርሱ ብልሆች ናቸው፣ ከውሳኔ በፊት ነገሮችን በጥልቀት የሚመረምሩ፣ ከሀሳባቸው በላይ ለድርጊታቸው ቦታ የሚሰጡት እነርሱ ብልጦች ናቸው። የሚጥልህም የሚያነሳህም ምርጫና ውሳኔህ ነው። ዛሬ ላይ ሆነህ የነገን አስከፊነትና ከብደት ማሰብ ትችላለህ፣ ነገር ግን ዛሬም ይሔን ሀሳብህን የሚቀይረውን ተግባር መፈፀም ካልቻልክ ሀሳብህ ማብቂያ አይኖረውም፣ ደጋግመህ ያሰብከው መጥፎ ሁነትም በፍጥነት ወደ አንተ ሲመጣ ትመለከታለህ። ትናንትና ነገን ተዋቸው፣ ልክ እንደ ብልጦቹ የያዝከውን ይዘህ አልቅስ። ዛሬ ቀላል የመሰሉህ ነገ ላይ ሊከብዱህ እንደሚችሉ አስቀድመህ አስብ። በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ይቀየሩ ዘንድ ራስህን ቀይር፣ አንተ ትቀየር ዘንድም እይታዎችህን፣ አመለካከትህንና የየለት ተግባርህን ቀይር። አንተ ፈልገህ ካላመጣሀው ሀብትም ሆነ ደስታ ኬትም አይመጣም። ሀሳብህን ግታ፣ ስራህ ነፃ እንዲያወጣህ ፍቀድ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
💥📣የረዳቹት ሰው ለምን ይጎዳችኋል? 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/CoJ_OKRxQmw?si=AB3BaLdObISG-Wea
ይቅርታህ አኖረኝ! ➡️➡️➡️🗣️ ከራስ ጋር ንግግር፦ "ደካማ ነኝና ብዙ ስቼያለሁ፣ ልፍስፍስ ነኝና በብዙዎች ላይ ፈርጄያለሁ፣ ወንድሜን ገፍቼያለሁ፣ ባየሁት ቁጥር ፊቴን ቋጥሬበታለሁ፣ ከእራሴ በደል በላይ የእርሱን ደጋግሜ እመለከታለሁ፣ በየቀኑ ወቀሳዬን እሰነዝርበታለሁ፣ በየሰዓቱ በሃሜት ቁም ስቅሉን አወጣዋለሁ። አንደበቴ እንደሚወደው ይነግረዋል የውስጤ ጥላቻ ግን ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛል። በወንድሜ ጨክኜ፣ ውድቀቱን ተመኝቼ ምን እንደማገኝ አላውቅም ነገር ግን በዚሁ ጥላቻ ስመላለስ ከርሜያለሁ። ይህን ግብሬን አንተ እንደማትወደው ባውቅም፣ የነፍሴም ፍቃድ እንዳልሆነ ባውቅም የምሰማው መጥፎ ትርክት፣ የሚነገረኝ የጥላቻ ንግግር ማስተዋል አሳጣኝ፣ በጥራት እንዳላስብ አደረገኝ፣ የዋህነቴን ሰወረው፣ ሀዘኔታዬን አጠፋው። አንዳች ያየውት ሳይኖር፣ ምኑንም ሳልረዳ እንዲሁ ከአጥፊው መንጋ ጋር ለጥፋት እቸኩላለሁ፣ ትንሽ የሳተው ላይ ለመፍረድ እፋጠናለሁ፣ የወደቀውን ከማንሳት በላይ እዛው በወደቀበት እረግጠዋለሁ። ጭካኔዬ ይታወቀኛል ነገር ግን ምክንያቱ ጥላቻ የሚባል በሽታ፣ ዘረኝነት የተባለ ቆሻሻ ትርክት ብቻ ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም። አዎ! አንተ አምላኬ ነህ፣ አንተ ፈጣሪዬ ነህ፣ እያንዳንዱን ስራዬን ታውቃለህ። ፃድቅ መስዬ በሀጥዑ ፈረድኩ፣ ፍፁም መስዬ ያጠፋውን ኮነንኩ፣ የተሻልኩ መስዬ ትሁቱን አዋረድኩ። ፈራጅነቴ ከበደሌ ነፃ ያወጣኝ ይመስል ያየውት ላይ በሙሉ ጣቴን እቀስራለሁ፣ እንከኑን እለቅማለሁ፣ መጥፎን እየመረጥኩ እመለከታለሁ። ይሔ ልማዴ ኬት እንደመጣ አላውቅም ነገር ግን እለት እለት ሳደርገው እገኛለሁ። አንተ አባቴ ቅዱስ እግዚአብሔር የይቅርታ አምላክ ባትሆን፣ የቸርነት ጌታ ባትሆን፣ ለበደሌ ተገቢውን ቅጣት የምቀጣኝ ቢሆን ምን ልሆን እንደምችል ሳስብ እጅጉን ደነግጣለሁ፣ ፍረሃት ይወረኛል፣ ለአፍታም ቢሆን ወደ ቀልቤ እመለሳለሁ። ነገር ግን ይቅርታህ አኖረኝ፣ ርህራሔህ በደሌን ተወልኝ፣ ቸርነትህ በምህረት ጎበኘኝ፣ ትዕግስትህ አንተን እንድፈልግ፣ መንገድህን እንድከተል፣ ወዳንተ እንድቀርብ አደረገኝ። የጥላቻን እሾህ ከውስጤ ንቀልልኝ፣ በወንድሜ ጥፋት እንዳልሳለቅ ጠብቀኝ፣ ከፈራጅነት አንተ ሰውረኝ፣ በቀናው መንገድ አንተ ምራኝ።" አዎ! ጀግናዬ..! ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፣ ተግሳፅም ይሁን ቅጣት ከፈጣሪ ነው። ወንድምህ ቢያጠፋ ፍርዱን የሚሰጠው እርሱ እንጂ አንተ አይደለህም፣ እህትህ መንገድ ብትስጥ እያስተማረ የሚገስፃት እርሱ እንጂ አንተ አይደለህም። ከፍርድ ተጠንቀቅ፣ ጥፋትን ለማጯጯህ አትቸኩል። መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚለው "በወንድምኽም ዐይን ያለውን ጕድፍ ስለ ምን ታያለኽ፥ በዐይንኽ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?" ቀዳሚው የእራስን ክፍተት መሙላት፣ የእራስን ድክመት ማረም እንጂ በሰው ክፍተት ላይ አስተያየት መስጠት፣ ድክመቱንም ማጋነን አይደለም። ማንም ከጥፋትና ከሀጢአት የፀዳ ሰው የለም። የሰውን ጉድፍ ባየን ልክ የእኛውን ምሰሶ የሚያህል በደል መመልከት ይኖርብናል። ፈራጅና አስተያየት መስጠት እንደ አዋቂና እንደ ንፁ በሚያስቆጥርበት በዚህ ግዜ እራስን ከፍርድና ከአስተያየት ሰጪነት መጠበቅ ታላቅነት ነው። የተሸፈነልንን ነውር እናስብ፣ የተከደነልንን በደል እናስብ፣ በአምላካችን ቸርነት እንጂ ማናችንም በስራችን ለዛሬ እንዳልበቃን እንረዳ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
💥📣ተደብቆ መኖር ልመዱ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE 📣 SHARE 🙏🙏 https://youtu.be/rbPQXVFVIyk?si=beo4WcdXRwL-i9f3
አይናችሁን ግለጡ! ⚠️⚠️‼️‼️⚠️⚠️ አንድ ተደጋግሞ የሚነገር ምሳሌ አለ። ምሳሌውም ይሔንን ይላል፦ "ትናንት በመንገዳችሁ ስንት ቀይ መኪና እንደተመለከታችሁ አስታውሱ። ብትመለከቱ እንኳን በእርግጠኝነት ቁጥሩን መናገር አትችሉም። ነገር ግን አስቀድሞ ባያቿቸው መኪና ቁጥር ልክ ሁለት መቶ ብር ይሰጣችኋል ብትባሉስ? በእርግጠኝነት ያያቹትን የመኪና ብዛት ከነቦታው መናገር ትችላላችሁ። በህይወት የሚመጡልን እድሎችም እንደዚህ ናቸው። አይናችሁን ገልጣችሁ በህይወት መንገዳችሁ የሚመጡላችሁን እድልና አጋጣሚዎች መመልከት ካልቻላችሁ ሳታስተውሉ እንዳለፉት ቀይ መኪኖች እያለፉ ይሔዳሉ።" እድሎችን ለመጠቀም ዝግጁ ለሆነና ማስተዋል ለሚችል ሰው ህይወቱ በሙሉ በጥሩ አጋጣሚዎች የተሞላች ነች። አንድ ነገር ሲበላሽባችሁ፣ የፍቅር ወይም የትዳር ህይወታችሁ ክፍተት ሲበዛበት፣ አግኝታችሁ ስታጡ፣ ሳታስቡት ውስብስብ የህይወት መንገድ ውስጥ ስትገቡ አይናችሁን ገልጣችሁ ከዚህ አጋጣሚ ምን መጠቀም እንደምትችሉ በጥልቀት አስቡ። ጨለማ ሲመጣ ብረሃንን የመጠበቅን ፅናት እንደሚያስተምር አስታውሱ። በህይወት ዝቅታ ውስጥ መውደቅም ዳግም እራስን አጠንክሮና አርሞ ለመውጣት እንደሚያዘጋጅ አስተውሉ። አዎ! አይናችሁን ግለጡ! "እኔ እድል የለኝም፣ የነካውት ሁሉ ይበላሻል፣ ገደኛ አይደለውም፣ እድሌ ጠማማ ነው።" ብላችሁ ከመደምደማችሁ በፊት በዙሪያችሁ የሚመጡላችሁን እድሎች መመልከት ስለመቻላችሁ እርግጠኛ ሁኑ። እናንተ መመልከት ካልቻላችሁ ሁሌም እድለቢስ መሆናችሁ አይቀርምና አይናችሁን ግለጡ፣ እድላችሁን ተመልከቱ፣ አጋጣሚዎችን አጢኑ፣ አንድ ነገር ስታጡ ምን ልታገኙ እንደሆነ አስተውሉ፣ አንደኛው በር ሲዘጋባችሁ የትኛው በር ሊከፈትላችሁ እንደሆነ አጢኑ። በህይወት ብዙ ተስፋ አስቆራጭና የውድቀት ጊዜያት ቢኖሩም ተስፋ ቆርጦ፣ እጅ ሰጥቶ፣ በውድቀቱ እያማረሩ መቀመጥ ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አያውቅም። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው "አይን አላችሁ አታዩም፣ ጆሮ አላችሁ አትሰሙም፣ ልብ አላችሁ አታስተውሉም።" ምንምእንኳን እድል ከፊታችን ቢመጣም ማስተዋል ካልቻልን እጣፋንታችን ምሬትና ብስጭት ብቻ ይሆናል። የደፈረሰ መጥራቱ አይቀርም፣ የመጣ መሔዱ አይቀርም፣ መከራም ማለፉ አይቀርም። በዚህ መሐል ግን "እኔ ምን ማትረፍ እችላለሁ?" ብለው የሚጠይቁ ሰዎች ብቻ አጋጣሚዎችን እንደ እድል ይጠቀማሉ። አዎ! ጀግናዬ..! አቀርቅረህ ስትሔድ የምትመለከተው መሬቱን ብቻ ነው፣ ቀና ብለህ አካባቢህን እየቃኘህ ስትሔድ ግን ከምድር በላይ ያሉ ክስተቶችን እያስተዋልክ ከእነርሱም ውስጥ የሚጠቅሙህን እየመረጥክ መጠቀም ትጀምራለህ። በዙሪያህ ምን እየተከናወነ ነው? ረጅሙን ጊዜህን ከነማን ጋር እያሳለፍክ ነው? አብረውህ ካሉ ሰዎች ጋር ምን መስራት ትችላለህ? አንተ ጋር ምን አለ? ከቅርብ ሰዎችስ ምን ማግኘት ትችላለህ? ዓለም በእድል ብትሞላ እንኳን አንተ መመልከት ካልቻልክ ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ህይወት በአጋጣሚዎች የተሞላች ነች፣ አጋጣሚውን እንደ እድል መጠቀም ወይም እየፈሩ ማሳለፍ የእኛ ድርሻ ነው። እድላችሁን አታሳልፉ፣ እድለቢስ እንደሆናችሁ ቢሰማችሁ እንኳን አዲስ ነገር መሞከራችሁን እንዳታቆሙ፣ የተለየ ቦታ መገኘታችሁን እንዳትተው። ወድቆ መቅረትን፣ ተስፋ ቆርጦ መቆምን፣ ተሰብሮ አንገት ደፍቶ መቅረትን በፍፁም የመጨረሻ አማራጫችሁ አድርጋችሁ እንዳትቀበሉ። "ወድቋል፣ አብቅቶለታል፣ ዋጋ የለውም፣ ተስፋው ተማጧል" ባሏችሁ ማግስት እንዴት አፈር ልሳችሁ፣ ክንዳችሁን አጠንክራችሁ በፈጣሪያችሁ እርዳታና በእናንተ ብርታት ቀና ማለት እደምትችሉ አሳዩአቸው። አይናችሁን ግለጡ፣ ሁሌም አጋጣሚዎችን ወደ እድል ለመቀየር ተዘጋጁ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ✍️ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 #SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪