tgindex
ሎጎስ-Logos🔔

ሎጎስ-Logos🔔

Статистика

🅞🅡🅣🅗🅞🅓🅞🅧=ክርስቲያን // ሰለ እምነታችን እንወቅ //  “ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” (1ኛ ጴጥሮስ 3፥15)//

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
430
+1 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,23%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
407
25 постов
Вовлечённость
94,7%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
111
1/48двое суток
127
1/72трое суток
137

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ለማንኛውም ሉተራውያን መካነ ኢየሱስ አማኞች ወደ ቅዱሳን አንፀልይም ቢሉም ቅዱሳን በሰማይ ለቤተክርስቲያን እንደሚፀልዩ ያምናሉ 🙌 ጴንጢያንስ መጀመሪያ ከእነሱ ጋር ጨርሱ 🤝 ሎጎስ-Logos

  • ይሄ ነገር ግድ ነው መሰለኝ ወንዶች አስቡበት በ ፌሚኒዝም ምክንያት የወንድን ልጅ ክብር የሚነካ ነገር አሁን ላይ እየተለመደ ነው ። የሴትን ልጅ መብት ማስከበርና ደህንነቷን ማስጠበቅ ማለት እኮ ወንድን ልጅ ማንቋሸሽ ማለት አይደለም! ሎጎስ-Logos

  • እኛ የእግዚአብሔር የባህሪ ልጆች አንባልም! የአብ የባህሪው ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ብቻ ነው🙏 እንደዛ የሚሉ ፕሮዎች ሰላየው ነው 🙈 ሎጎስ-Logos

  • ☦️በዚህ አመት በተለይ አሁን ላይ በጣም ፍቅር እያደረብኝ የመጣው ሰለ ዘሚካኤላውያን ማወቅ ነው። አንዳንድ ከማነባቸው መፅሀፍቶች ላይ ሰለነሱ አቋም ሲፃፍ ከማየት ውጪ ሰለነሱ በጥልቀት በደንብ አላነበብኩም። ብቻ ዘሚካኤል በአፄ ዘርአ ያእቆብ ዘመን የነበረ ሊቅ ነው ከዛ የሱን ሀሳብ የሚያንሸራሽሩና በሱ ስራ ያሉ ዘሚካኤላውያን አሉ እና ጥቂት ምልከታቸውን ከአንዳንድ ምንጮች ስንመለከት ጥሩ መረዳት እንዳላቸው አለመገንዘብ አይቻልም!። እስቲ ሰለነሱ በደንብ የማወቅ ፍቅሩ አድሮብኛል የምትጠቁሙኝ መፅሀፍ ካላ ንገሩኝ 🥰 📚ለዛሬ ሳሙኤል ፍቃዱ በምጽአተ ክርስቶስ በሚለው መፅሀፍ ከሺህ አመት መንግስት ጋር ስማቸው የሚነሳውን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን እና ሌሎችንም አንስተው ከፃፉት ጥቂቱን ከታች ላስቀምጥ ከገፅ 141 የተወሰደውን። 📄.......ከመጽሐፈ ምሥጢር- “የደብረ ጽዮን ምሳ የለም ስለሚሉት በመዝሙር በረከትን እምቢ ያላት ከእርሱ ትርቃለች (መዝ 108 (109): 17) እንዳለ በአንድ ሺህ ዓመቱ ምሳ ተሳትፎ እንደሌላቸው የኢየሱስ ክርስቶስን እጅ (መትቼ) ምያለሁ" የሚል ንባብ አለ፡፡ በተለይ ዘሚካኤላውያን የሺህ ዓመቱን ንግሥና የደብረ ጽዮንን ማዕድ ይቃወሙ ነበር፡፡ አፄ ዘርአ ያዕቆብ ጉዳዩን አስመልክቶ በመጽሐፉ እንደ ነገረን የዘሚካኤላውያን አስተምህሮ ይህ ነበር፡- “አሁን ካለንበት ከዘመነ ሥጋዌ በስተቀር የቅዱሳን የሺህ ዓመት ንግሥና የለም፤ ማዕዱም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ እንዲሁም ደብረ ጽዮን ተብላ ልትጠራ የሚገባት የእግዚአብሔር ማዕድ (ሥጋሁ ወደሙ) የሚሠዋባት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡" ይህ የዘሚካኤላውያን አስተያየት በራእይ 20፡ 4-6 ትርጓሜ ከሰፈረው የቤተ ክርስቲያናችን አተረጓጎም ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ እንዲሁ ገማልያል የተባለው ምሁርም እንደ ዘሚካኤላውያን ሁሉ ምሳሐ ደብረ ጽዮን የሚባል ነገር የለም የሚል አቋም ያራምድ ነበር።.............. 🔗እያለ ይቀጥላል🙈 በአኰቴተ ቁርባን ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስም ሰለነሱ በዚህም እርስም በሌላም ያስቀምጣሉ። ሎጎስ-Logos

  • ⛪መጽሐፈ ዲድስቅልያ ምእራፍ አራት 62 (፷፪) ሰው ፡ ሆይ ፡ ዕወቅ ፣አስተውልም ። በዚህ ፡ ዓለም ፡ ብትበድል ፡ ኀጢአትንም ፡ ብትሠራ ፡ ንስሐም ፡ ባትገባ ፡ ድኅነት ፡ አይኖርህም ። እንግዲህ ፡ በሕይወት ፡ ሳለህ ፡ ንስሐ ፡ ግባ ። ዳዊት ፡ በሞት ፡ የሚያስብህ : የለምና ፣ ፡ በሲኦልም ፡ የሚያምንህ ፡ ማን ፡ ነው? ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ተናገረ ፡ ከሞት ፡ በኋላ ፡ ንስሐ ፡ የለምና ። ሎጎስ-Logos

  • 9 авг.257282

    ሰላም ምርጦች 😍 😀በተለያየ ምክንያት እስከ ዛሬ በንስሀ ያልተመለሳቹ ለዘላለም ህይወት የሚሆነውን ቅዱስ ቁርባን ያልጀመራቹ ካላቹ እንደምንም ወደዚህ መንገድ ለመግባት ሞክሩ እግዚአብሔር ደሞ ያግዛችኋል🥰 😀የጀመራቹ በዛ ህይወት ያላቹ ደሞ ሌሎቹን የመመለስ ሀላፊነት አለባቹ ሰለዚህ ጓደኞቻቹሁን ቤተሰቦቻችሁን በንስሀ እየተመላለሱ ቅዱስ ሥጋና ደሙን እንዲወስዱ አጉዟቸው🙏 እዚህ ነገር ላይ (ቅዱስ ቁርባን ያልጀመራቹ) ማማከር የምትፈልጉት ነገር ካለ አለሁኝ በዚህ አውሩኝ 🌐@Eyobmekonenz ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን በቤቱ ያፅናን🙏 ⚙ምሳሌ 28፥13 ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል። ሎጎስ-Logos

  • 8 авг.256153

    ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህንን እንደማታምን አድርገው የሚያወሩ ሰዎች ግን👊

  • 3 авг.445181

    📝ቅዱስ ሙሴ ፀሊም {St. Moses the Black} 🔗ሃጢያአቴ እጅግ ብዙ ነው እግዚአብሔር ይቅር አይለኝም ለምትሉ ከሃጢያት ወደ ቅድስና የመጡ አባቶችን ታሪክ አንብቡ አንዱ ቅዱስ ሙሴ ፀሊም ነው። ለንስሃ ህይወት የንስሃ ህይወታቸውን እንመልከት 🔖ከአለማዊ ሂወት አሳዳጅ ገዳይ ዘራፊ ከመሆነ በንስሀ የተመለሰው እግዚአብሔር የረዳው ቅዱስ አባታችን ነው ። ''ቀማኛው ወይም ጥቁሩ የተባለው ሙሴ፡ በኒትሪያ (Nitria) በሽፍታነት ይኖር የነበረ ነፃ የወጣ ባሪያ ነበር። በዕድሜው መገባደጃ ላይ መነኮሰ፤ በአባ እሲዶሮስም (Isidore the Priest) ስልጠና አገኘ። ካህን ሆኖ ተሾመ፤ የአስቄጥስ (Scetis) ታላላቅ አባቶችም አንዱ ሆነ። በቅዱስ መቃርስ ምክር ወደ ጴጥራ (Petra) አቀና፤ በዚያም ከአራት/ከሰባት ሌሎች ጋር በአረማውያን በበርበር ወራሪዎች እጅ በሰማዕትነት አለፈ'' 🔗(The Sayings of the DESERT FATHERS page 138) 📚የሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ሥራው ከጸሎቱ ጋር የማይጣጣም ከሆነ፣ ድካሙ በከንቱ ነው። ዲያብሎስ ሰውን በአንድ ጊዜ አይጥለውም (አያጠፋውም)፤ ይልቁንም ‘ነገ፣ ነገ’ እያለ በጆሮው ይሹከሹካል። በዚህም ልብ ተሸንግሎ ይተኛል (ይዘናጋል)፤ ነፍስም ዘላለማዊነትን ትረሳለች። ብልህ ሰው ግን ‘ዛሬ የመዳን ቀን ነው’ ይላል፤ ጊዜ እያለውም ንስሐ ለመግባት ይነሳል። 🔗ስንክሳር ዘወርሀ ሰኔ 24 ላይ ታሪኩን ታገኛላቹ ሎጎስ-Logos

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 2 авг.6051318

    በጌታ ይሄ መዝሞር🥹❤️ የልቤን ሁሉ የውስጤን ሁሉ የመረከመረከው በማዕበሉ የቀና መንገድ ያሳየኸኝ እምላኬ ሁሌ ተናገረኝ ሎጎስ-Logos

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🔗አንዱ ሉተራን ወንድማችን ከሳምንታት በፊት የኢትዮጲያ ሊቃውንቶች እግዚአብሔር እጅ እግር አለው ሲሉ ግዘፍ ነው ማለታቸው አይደለም Concrete reality ወይም ቀዋሚ አካልን ለመግለጽ {አካላዊ ፍጹምነታቸውን ለመግለጽ ነው ከእግር ጥፍር እስከ እራስ ጸጉር} የሚሉት ብሎ በጥሩ ሁኔታ ሚዛናዊ ሆኖ ሲያስረዳ ነበር እኛም አመስግነናል ሰለመረዳቱ። ያስገረመኝ ግን ሉተር እራሱ እዚህ ነገር ላይ ተመሳሳይ መረዳት ያለው ይመስላል ከላይ እንደምታዩት ትርጉሙን ከስር ላስቀምጠው ። 📄የፓፓ አዋጅ አንትሮፖሞርፋይቶችን (Anthropomorphites) እግዚአብሔርን ልክ እንደ ሰው አድርገው ስለሚናገሩ፣ እና ለእርሱ አይኖች፣ ጆሮዎች፣ ክንዶች፣ ወዘተ በመስጠታቸው ይኮንናቸዋል። ነገር ግን ይህ ውግዘት ፍትሃዊ አይደለም። በእርግጥም ሰዎች በሰዎች መካከል ሆኖ ከዚህ ውጪ ስለ እግዚአብሔር እንዴት ሊናገሩ ይችላሉ? እግዚአብሔርን በዚህ መልኩ ማሰብ መናፍቅነት ከሆነ፣ እንግዲህ እግዚአብሔርን በዚህ የህፃንነትዘይቤ በሚያስቡ እና በሚናገሩ ህፃናት ሁሉ መዳን ላይ ፍርድ ተሰጥቷል ማለት ነው። ነገር ግን ህፃናቱን ትተን እንኳ፦ እጅግ የተማረውን ምሁር አምጡልኝ — እርሱ ራሱ ስለ እግዚአብሔር እንዴት ሌላ መንገድ አስተምሮ ይናገራል? 27 ኤፒፋንዩስ (Epiphanius) በፓናሪዮን (Panarion) መጽሐፉ ምዕራፍ 70 ላይ "ኦዲያንስ" (Audians) የተባለኑ ማህበር ይጠቅሳል። እነርሱም ከባድ የሆነውን የአንትሮፖሞርፊዝም (Anthropomorphism) መልክ በማስተማር ተከሰው ነበር። ......እግዚአብሔር ድሆችን የሚመለከትባቸው ዓይኖች አሉት፤ የሚጸልዩትን የሚሰማባቸው ጆሮዎች አሉት፣ ወዘተ ብለው በመናገራቸው ጥፋተኛ ተብለዋል። ይህ የተፈጥሮ ህዋሳችን የእግዚአብሔርን መንፈሳዊ ፍሬ ነገር እንዴት ሊረዳው ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስም ጭምር በየትኛውም ስፍራ ይህንኑ የንግግር ዘይቤ ይጠቀማል። ስለዚህ እነርሱ ያለ ፍትህ ተወግዘዋል።......... ሎጎስ-Logos

  • видео или голосовое, без подписи

  • ቁርአን አልተበረዘም ከምትሉ መሀመድ ድንግል ሆኖ ነው የሞተው ብትሉ ይቀላል 💣 ሎጎስ-Logos

  • hy🙄

  • ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደነጐድጓድ አቤቱ አምላካችን ቤተ ክርስቲያንህ ትማልድሃለች ትሰግድልህማለች፣ ሙሽራህም ታከብርሃለች ሕዝብህም ይገዙልሃል❤ ☦️ ሎጎስ-Logos

  • 📝John Chrysostom Homily 6 on Philippians «በመጨረሻም፣ ወልድ የተለየ ባሕርይ (substance) አለው ብሎ በሚያምነው በአርዮስ ላይ ምን እንላለን? ንገሩኝ እስቲ፣form of a servant? ‹የባሪያን መልክ ያዘ› የሚለው ምን ማለት ነው? ይህም ማለት ሰው ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ ‹በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር›፣form of God እርሱ እግዚአብሔር ነበር። አንድ ‹መልክ› እና ሌላ ‹መልክ› ተሰይመዋልና one form and another form is named አንደኛው እውነት ከሆነ፣ ሌላኛውም እውነት ነው። ‹የባሪያ መልክ› ማለት በባሕርይ ሰው ማለት ነው፣ ስለዚህ ‹የእግዚአብሔር መልክ› ማለት በባሕርይ {by nature} እግዚአብሔር ማለት ነው።» «የባሪያ መልክ እውነተኛ መልክ {true form} እንደሆነና ከዚያም ያነሰ እንዳልሆነ ተናግሬአለሁ። ስለዚህ የእግዚአብሔርም መልክ ፍጹም ነው፣ ከዚህም አያንስም{ Therefore the form of God also is perfect, and no less.} ለምን ‹በእግዚአብሔር መልክ ተፈጠረ›{being made in the form of God} ሳይሆን ‹በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር› {being in the form of God?} ይላል? ይህ ‹እኔ የሆንኩ እኔ ነኝ {«ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ}› {I am that I am} ከሚለው አባባል ጋር ተመሳሳይ ነው። (ዘጸአት 3፡14)። ሎጎስ-Logos

ሎጎስ-Logos🔔 — tgindex