አፖሎጊያ
Статистика- Последний пост
- 5 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 690
- 1/48двое суток
- 790
- 1/72трое суток
- 852
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሰላም ቤተሰብ እንደምታዩት የቻላሉን ኮሜንት ሴክሽን አጥፍቻለሁ። ባለፈው ቲክቶክ ላይ እንደነገርኳችሁ ከሚዲያ ላልተወሰነ ጊዜ የምርቅበት ሰዓቴ ነው (በተለይ ከቲክቶክ)። ስለዚህ እኔ በሌለሁበት ኮሜንት ላይ እንዳታጡኝ ስል ቆልፍያለሁ። ሁኔታዎች ሲመቻቹ ቪዲዮዎች አንዳንዴ Youtube ላይ የምለቅላችሁ ይሆናል (ቻናሉን ሰብስክራብ ያደረጋችሁ ታዩታላችሁ)። ማለት መታለፍ የሌለባቸው ርዕሶች ሲሆኑ። ከወራት በፊት ነገረ መለኮት ኮርሶችን በመካከለኛ ደረጃ ለማጥናት የተመዘገባችሁ ሀገር ውስጥም ውጭም ያላችሁ ሰዎች እንደተለመደው ቅድመ ክፍያ በመጨረስ የትምህርቶችን ሊንክ እኔን ቀጥታ @Aman808080 ላይ በማናገር መቀበል እና ትምህርቱን መከታተል ትችላላችሁ። ትምህርቶቹን ማግኘት የምትችሉት እኔ በምልክላችሁ ሊንክ ነው። በኦንላይን ሰርተፍኬት ያልተቀበላችሁ የአምና ተማሪዎች በውስጥ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ። በነበረን የዋትስአፕ ግሩፕ ወይም አዲስ ከፍተን የምንሰባሰብ ይሆናል። የነገረ ክርስቶስ (Christology እና ታሪካዊ ነገረ መለኮት (Historical Theology). ትምህርቶች ቪዱዮዎችን ጭኜ ጨርሻለሁ። አምና ስትማሩ የነበራችሁ ኮርሶቹን ስለጨረስን በዚህ እንደ አዲስ መመዝገብ ትችላላችሁ! በ48 ሰዓት ውስጥ ምዝገባው ይጠናቀቃል! የእጅ ስልክ ስለማልይዝ ከዚያ በኋላ የሚመጡ መልዕክቶችን የማልመልስ ይሆናል። ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
https://youtu.be/S_CtWOYWcbw 🤔🤔🤔
без подписи
ሁለቱም ችግር ናቸው ግን የስህተታቸውን ጥልቀት እንገምግም ከተባለ ካልቪኒስቶች ከአርመንያን ይልቅ መንፍቀዋል ያስብለናል ብዬ አስባለሁ
እቺ ጀለስ ወንድማችን ነች (እንደምወደው ይታወቃል)፣ ከአርሚኒያን አንፃር ካልቪኒስቶች መንፍቀዋል የሚል አቋም አለው ነገር፣ አንድ የፈለገውን ርዕስ ቢመርጥ ሙግት ልገጥም ዝግጁ ነኝ 🤭
ይህ ካቶሊክ አቃቤ እምነት ስለ ቅድመ ውሳኔ ቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደምታምን እንዲህ ጥንቅቅ አድርጎ አስቀምጦታል 00:00 - 00:09: ትላንትና ካቶሊኮች ቅድመ ውሳኔን (predestination) የቤተክርስቲያን የማይሳሳት ትምህርት አድርገው እንደሚያምኑ የሚያብራራ ቪዲዮ ሰርቼ ነበር። ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች አልተስማሙብኝም። 00:09 - 00:24: ሰዎች ሰዎችን እያሳሳትኩ እንደሆነ ተከሰስኩ። ይህ የይገባኛል ጥያቄ ከካቶሊክ ትምህርት አንፃር ፍጹም ሀሰተኛ እንደሆነ ነግረውኛል። አሁንም ትክክል ነኝ፤ ይህ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የማይሳሳት ትምህርት ነው። 00:25 - 00:35: ፖፕ አድሪያን አንደኛ በዴንዚገር 596 ላይ እግዚአብሔር ክፉ ወይም ክፉ ስራዎችን እንዳዘጋጀ በግልጽ ይናገራል፣ ነገር ግን ለፍትህ እና ለዘላለማዊ ቅጣት ሰዎችን አዘጋጅቷል። 00:36 - 00:47: ይህ ከቅዱስ ቶማስ አኩዊናስ ጋር በትክክል ይስማማል፤ እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ኃጢአት እንዲገቡ አያደርግም፣ ነገር ግን አስፈላጊውን ጸጋ ባለመስጠት ያንን ኃጢአት ለማሸነፍ የማይቻል ያደርግባቸዋል። 00:48 - 01:10: እንደ ቅዱስ አግስቲን እና የቫለንስ ሲኖዶስ ገለጻ እግዚአብሔር በሁሉም ቦታዎች ለሁሉም ነገሮች የተወሰነ የቅድመ ውሳኔ መመሪያ ሰጥቷል። 01:11 - 01:34: ስለዚህ ፈጣን ማጠቃለያ እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ኃጢአት እንዲገቡ አያደርግም፣ እና ማንም ወደ ሲኦል አይሄድም የሚለው የእርሱ ቀዳሚ ፈቃድ ነው። ሆኖም ግን, የእርሱ ተከታይ ፈቃድ ብዙ ሰዎች ወደ ሲኦል እንደሚሄዱ ይወስናል። 01:35 - 01:50: አኩዊናስ እንዳለው መነጠቅ ወይም ውድቅ መደረግ (reprobation) ከቅድመ ውሳኔ በምክንያትነት ይለያል። እግዚአብሔር አንዳንዶችን ውድቅ ያደርጋል፣ ነገር ግን ሰዎችን ወደ ሰማይ ከማቀድ ይለያል። 01:51 - 02:21: እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ሰማይ ሲወስን ኃጢአታቸውን እንዲያሸንፉ ጸጋን ይሰጣቸዋል። ነገር ግን ውድቅ ሲያደርጋቸው ኃጢአት እንዲሰሩ ይፈቅድላቸዋል ጸጋን ግን አይሰጣቸውም። 02:22 - 02:39: ይህ ማለት እግዚአብሔር በዕጣ ፈንታቸው ላይ ምንም ድርሻ የለውም ማለት አይደለም፤ እግዚአብሔር እውነተኛ መለኮታዊ እቅድ አለው። 02:40 - 02:55: ይህ በቀጥታ ከሮሜ መጽሐፍ የተወሰደ ነው፤ እግዚአብሔር ለምህረት ለሚገባው ምህረት ያደርጋል የፈለገውንም ያደነድናል። ካቶሊክ ከሆኑ ይህንን የማይሳሳት ትምህርት መካድ አይችሉም። እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
без подписи
без подписи
“ጋብቻ ከእግዚአብሔር የተሰጠ መለኮታዊ እና ሉዓላዊ ጥሪ ነው፤ ይህ የሚሆነው ከእግዚአብሔር ሴቶች ልጆች አንዲቷን ለመጥቀም ሲባል ሕይወትዎን አሳልፈው እንዲሰጡ ነው።” (ፖል ዎሸር) “ሁሉንም ቅድመ-ሁኔታዎች ከሚያሟላ ሰው ጋር ቢጋቡ ኖሮ፣ ቅድመ-ሁኔታ የሌለውን ፍቅር እንዴት ሊማሩ ይችላሉ? በጭራሽ በማይበድልዎት ሰው ቢጋቡ ኖሮ፤ መቼም አስቸጋሪ ካልሆነብዎት ሰው ጋር ቢጋቡ ኖሮ፤ በጭራሽ ኃጢአት በማይሠራብዎት ሰው ጋር ቢጋቡ ኖሮ፤ ኃጢአቱን ለመቀበል ወይም ይቅርታ ለመጠየቅ መቼም ቢሆን ዘግይቶ በማያውቅ ሰው ጋር ቢጋቡ ኖሮ፤ ምሕረትን፣ ትዕግሥትን፣ ረጅም ታጋሽነትን እና ከልብ የመነጨ ሐዘኔታን እንዴት ሊማሩ ይችላሉ? ሁልጊዜ መልካም የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ለሚገባው ሰው ቢጋቡ ኖሮ፤ በማይገባው ሰው ላይ ሞገስዎን በማፍሰስ ጸጋን እንዴት ሊማሩ ይችላሉ? ይህንን አስተውለዋል? የጋብቻ ዋና ዓላማ በጋብቻችሁ በኩል ሁለታችሁም ወደኢየሱስ ክርስቶስ መልክ እንድትመሰሉ ነው። ጋብቻ ከሁሉ የላቀ የቅድስና መሣሪያ ነው። ቅድመ-ሁኔታዎችን ሁሉ የማሟላትን ሰው ያገባችሁት ቅድመ-ሁኔታ የሌለውን ፍቅር እንዲማሩ ነው። ምሕረት የሚፈልግ ሰውን ያገባችሁት እርስዎም ምሕረት መስጠትን እንዲማሩ ነው። ማይገባውን ሰው ያገባችሁት፣ ምንም ተገቢውን ምላሽ በማይሰጥ ሰው ላይ ራስዎን በልግስና ማፍሰስን እንዲማሩና በዚህም የምንሰግደውን ጌታ እንድንመስል ነው። ለጸጋው ጌታን ታመልካላችሁ፤ ነገር ግን ሚስትዎ የጸጋ ተጠቃሚ እንዳትሆን በሚያስችል መንገድ እንድትኖር ትፈልጋላችሁ። ለቅድመ-ሁኔታ አልባ ፍቅር ጌታን ታመልካላችሁ፤ ነገር ግን የራስዎ ሚስት ቅድመ-ሁኔታዎቹን ሳታሟላ ስትቀር ትናደዳላችሁ። እኛ የምናመልከውን ጌታ እንመስላለን! እዩት፣ ለቅድመ-ሁኔታ አልባ ፍቅር፣ ለጸጋና ለምሕረት ጌታን እናመልካለን፤ ነገር ግን እነዚያኑ ነገሮች ለሌሎች መስጠት አንፈልግም። ሚስቴ የፍላጎቶቼን ሁሉ አሟልታ፣ የጉጉቶቼንም ሁሉ አርክታ፣ እኔም ብዙም መስዋዕትነት ሳልከፍል ወይም ብዙም ሳልታገስ ስኖር ክርስቶስን የምንመስለው በዚያን ጊዜ ነው? ወይስ አጥብቆ መሥራት ባለብን፣ ጥልቅ ፍለጋ ማድረግ ባለብን አስቸጋሪ ቀናት ውስጥ ክርስቶስን እንመስላለን? አብዛኛውን ጊዜ የምንቸገረው በራሳችን ውድቀት ፍሬ ማፍራት የተነሳ መሆኑን መገንዘብ ባለብን ጊዜ? እነዚያ ቀናት ክርስቶስ የጠራንንና ያደረገንን እንድንሆንና እንድንሠራ በእርሱ ኃይል ላይ ምን ያህል ጥገኛ እንደሆንን መገንዘብ የሚገባን ቀናት ናቸው! ጠንክሩ! በርቱ!” ፖል ዎሸር
እኛ የነገረ መለኮት ዲፕሎማ ሳንማር ወንድማችን ዳኒ እውነት ለሁሉ PHDኡን ሊጨርስ ነው🥰 እናም የዶክትሬት ትምህርቱን ለመጨረስ የሆነ የገንዘብ እርዳታ አስፈልጎታል። ለዚህ የሁላችንም ትብብር ይፈልጋል። ምናልባት ዳኒ እውነት ለሁሉን ለማታውቁ ወዳጆች ዳኒ በእቀበተ እምነት አገልግሎት ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየና የእውነት ለሁሉ ዌብሳይት መሥራችና አርታዒ ወንድማችን ነው። እስልምናና ሌሎች የኑፋቄ ትምህርቶችን በመመከት የሚታወቅ አመለ ሸጋ ወንድማችን ነው። በዚህም ሁለት አማራጮችን ተከትላችሁ እርዳታችሁን ለወንድማችን ማድረስ ትችላላችሁ... ውጪ ላላችሁ ወዳጆቻችን በዚህ የgofundme ገጽ በመግባት የምትችሉትን እንድታደርጉ በፍቅር እንጠይቃችኋለን.... https://gofund.me/e6a849d69 ሃገር ውስጥ ላላችሁ ወዳጆች ደግሞ በዚህ በጓደኛው አካውንት ልትረዱት ትችላላችሁ፤ 1000784785207 አማኑኤል እንዳለ በውስጥ ወንድማችን ዳንኤልን በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ማነጋገር ትችላላችሁ @danit4all ተባረኩ....
https://youtu.be/x-4dpFjyKbY?si=zMRQT0a9t_LKbdb6 መንፈስ ቅዱስ 🥺 what a devotional song... ይደመጥ 😊
https://youtu.be/SugNHx-eM7M ክፍል ሁለት ተለቋል
https://youtu.be/PaASATiid7M
ማስተርስ እና ዶክትሬት ቤትህ ድረስ ሲላክልህ 😁
እቺን እዩዋትማ እስቲ... ዩትዩብ ላይም ለቅቂያለሁ ተመልከቱ! ቪዲዮውን እስከ መጨረሻ እዩት አለዚያ አይወጣም፣ ላይክ ሪፖስት ኮፒ ሊንክ አይረሳ 🙏 ቲክቶክ: https://vt.tiktok.com/ZSXp2dWPc/ ዩትዩብ: https://youtu.be/Pd3xyKhH6jE?si=x6Gy9T_uFldDoKPl
без подписи
ከሰሞኑ ውዝግብ ያስነሳው የሙሉ ወንጌል እምነት አቋም ማሳያ ተደርጎ የቀረበው መፅሐፍ ይሄ ነው! በተደጋጋሚ እየተጠየኩ ስለሆነ እዚሁ ላስቀምጥላችሁ እስቲ!
ስልክህ infinix ሆኖ... የቤት ኪራይ እንዳለፈብህ ስታውቅ፣ ብድርም እንዳለብህ ትዝ ሲልህ 😭
እኔና ፓስተሬ ... እስቲ ባርኩን 😎
3. የሰው ዘር ተካፋይ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ለምን ሰው እንደሆነ ሲገልጽ፡- "ስለዚህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ እንደዚሁ በሥጋና በደም ተካፈለ..." (ዕብራውያን 2፡14) ይላል። ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ከሰው ልጆች ጋር በአንድ ተፈጥሮ (ሥጋ እና ደም) መካፈሉን በግልጽ ያሳያል። ጽሑፉ ግን "ሥጋውን ከማርያም አልወረሰም" በማለት ከዚህ ጥቅስ ጋር ይጋጫል። 4. ከሴት የተወለደ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ "ከሴት የተወለደ" መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል (ገላትያ 4፡4)። ይህም ማለት በተፈጥሮ ሂደት ከማርያም ተፈጥሮን በመካፈል መወለዱን ያሳያል። ጽሑፉ ግን የኢየሱስን ልደት ከማርያም ተፈጥሮ ውጭ በማድረግ፣ "ከአንደኛው ሰው ወደ ሌላው እንደማይተላለፍ" በመግለጽ የባዮሎጂ እና መንፈሳዊ ዝምድናውን ይክዳል። ይህ ፅሑፍ የያዛቸው ምንፍቅናዎች የሚከተሉት ናቸው። 1. ቫለንቲኒያኒዝም (Valentinianism) ይህ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበረው የኖስቲሲዝም (Gnosticism) እምነት ውስጥ ይነገር የነበረ የስህተት አቋም ነው። የቫለንቲኒያኖች ትምህርት፣ "ክርስቶስ ሥጋውን ከድንግል ማርያም አልወሰደም" የሚል ነው። እንደ እነሱ እምነት፣ ክርስቶስ "ከማርያም እንደ ውሃ በቧንቧ ውስጥ እንዳለፈ" እንጂ ከእሷ ምንም ነገር እንዳልወሰደ ያስተምሩ ነበር። ይህ ደግሞ ጭልጥ ያለ የ Only Jesus ምንፍቅና እምነት ነው። መፅሐፉ ላይ "ሥጋውን፣ ነፍሱንና መንፈሱን ከማርያም እንዳልወረሰ" በማለት የሚያቀርበው ክርክር፣ ከዚህ የቫለንቲኒያኖች አስተምህሮ ጋር ፍጹም ተመሳሳይነት አለው። ይህ አመለካከት ድንግል ማርያምን እንደ "መተላለፊያ" እንጂ እንደ "እናት" (ሥጋን የሰጠች) አድርጎ አይመለከትም። 2. ዶኬቲዝም (Docetism) ይህ ከግሪክ ቃል "ዶኬይን" (dokein) የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "መታየት" ወይም "መሰል" ወይም "መምሰል" ማለት ነው። የዶኬቲዝም ተከታዮች ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ የሰው ሥጋ አልነበረውም፣ ሥጋው "የሚታይ እንጂ እውነተኛ አይደለም" ብለው ያምኑ ነበር። በመፅሐፉፉ ላይ "ኢየሱስ የተገኘው ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ብቻ ነው" የሚለው አባባል፣ የክርስቶስን ሥጋዊ ተፈጥሮ (Human Nature) ከሰው ዘር ጋር ያለውን ተፈጥሯዊ ግንኙነት ውድቅ ያደርገዋል። ክርስቶስ የሰው ሥጋና ደም ከሌለው፣ ያን ጊዜ እውነተኛ ሰው መሆኑ ይጠራጠራል፤ ይህም የዶኬቲዝም መሠረታዊ ግብ ነው። በርግጥ ይህ የሙሉ ወንጌል እምነት ማሳያ ተደርጎ የተጻፈው መጽሐፍ በሙላት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የተዘጋጀ ሳይሆን አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ሀላፊነት ተሰጥቷቸው በራሳቸው የእውቀት ደረጃ ያዘጋጁት እንጂ ጥልቅ የሆነ ትንተና የተሰጠው ፍተሻም የተደረገበት አይመስልም። እኔ በዚህች ቤተ ክርስቲያን ተወልዶ እንዳደገ የደህንነት ትምህርት ከእርሷ እንደተማረ ሰው እንዲህ አልነበረም የተማርኩት። ጤነኛ አቢያተ ክርስቲያናት እንዲሁም ከተሐድሶ የሚነሱ የፕሮቴስታንት ትራዲሽኖች በፍፁም እንዲህ አይነት ትምህርት ኖሯቸው አያቅም አሁንም የላቸው። ስለዚህ ይህ መጽሐፍ በአስቸካይ እርማት ሊደረግበት ለምዕመኖቿም ልታሳውቅ ይገባል። አማን ሻሎም!