- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 281
- 1/48двое суток
- 322
- 1/72трое суток
- 347
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
pre Islamic period ጊዜ ነገደ ቁረይሽ በመካ ሐራም ውስጥ ካካተቱዋቸው ጣዖታት ውስጥ ታላቁ አምላክ ሁበል፣ ኢሳፍ፣ ናኢላ በbattle of elephant ጊዜ በAbraha ላይ ለቁረይሾች ድልን የሰጣቸው አላህ የሚባለው ጣኦት ከሶስቱ ሴት አማልክት ጋር ይገኛል። መሐመድ አላህ ብሎ የሚጠራው አምላክ እንደነ ስኮት ጆንሰን እና ሌሎች ምሁራን ጥናት መሠረት ከመሐመድ በፊት የሚኖሩ መድብለ አማልክት አምላኪዎች ዘንድ የሚመለክ ጣኦት እንደነበር ታሪካዊና አርኪዮሎጂያዊ ማስረጃዎችን ያቀርባሉ። መሐመድ ወደ መካ ሲገባ ሁሉን ጣኦታት ካስወገደ በኋላ አላህን ሲያስቀረው እንመለከታለን። ለነገሩ ሁበል በጊዜው ሙሉ ለሙሉ ከእስልምና አልወጣም ነበር፤ አንዳንድ ነገሮችን ለምሳሌ ጧዕፍ ማድረግን፣ በመስጂዶች ሚናራና ጉልላቶቻቸው ላይ የሚጠቀሟቸው የኮከብ እና የጨረቃ ምልክት እና ለአምላካቸው የሚሰግዱበት ትውፊት ከሁበል አምላኪዎች የተኮረጀ እንደሆነ እንመለአታለን። ስለሁበል ከዚህ በፊት የጻፍኩትን መጣጥፍ ይሄንን ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ @Yeshua_Apologetics_Ministry
ኧረ replica እና ዋናውን ጽሑፍ እየለየን 🙆♂️😂
ተወዳጆች በዚህ አገልግሎት ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየውና የእውነት ለሁሉ ዌብሳይት መሥራችና አርታዒ ወንድማችን ዳንኤል የዶክትሬት ትምህርቱን ለማጠናቀቅ የናንተ እርዳታ ያስፈልገዋል። አገልግሎቱን የምትወዱ ሁሉ ከጎኑ እንድትቆሙ በታላቅ ትህትና እንለምናችኋለን። በድርጅት መርዳት የምትችሉና ኦፊሴላዊ ደብዳቤ የምትፈልጉ በውስጥ ብታነጋግሩን ከላኪ ድርጅት ደብዳቤ ማቅረብ እንችላለን። በዚህ የgofundme ገጽ በመግባት የምትችሉትን እንድታደርጉ መልካም ፈቃዳችሁ ይሁን። ከሀገር ውስጥ መርዳት ለምትፈልጉ በውስጥ ወንድማችን ዳንኤልን በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ማነጋገር ትችላላችሁ @danit4all ተባረኩ! https://www.gofundme.com/f/expand-ewnet-lehulus-impact-with-your-help/cl/s?utm_campaign=fp_sharesheet&utm_content=amp20_control&utm_medium=customer&utm_source=copy_link&lang=en_GB
[የስነ-ጽሑፍ ትችትና የመጽሐፍ ቅዱስ ተአማኒነት] ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እስካሁን ድረስ እዚህ ቻናል ላይ በጽሁፍ ስንለቅላችሁና ስንወያይበት የቆየነውን በአዲስ ኪዳን የማኑስክሪፕቶች ታሪክና በጽሑፍ ትችት [Textual Criticism] ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን በአንድ ላይ አቀናጅተን ወጥ በሆነ ትንተና መልክ ያዘጋጀነውን አጭርና መሠረታዊ ጥናት አሁን በPDF ይዘንላችሁ ቀርበናል። ይህ ጽሑፍ በተለይ በአሁኑ ዘመን በአማርኛ ቋንቋ በስፋት የማይገኙ ነገር ግን ለእውነት ፈላጊው እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ታሪካዊና ስነ-ጽሑፋዊ ምላሾችን በውስጡ አካቷል። ይህ የመጀመሪያ ሥራችን እንደመሆኑ መጠን ስህተቶች ካሉም ለመታረምና ለማስተካከል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን። ° Tahrif ወይስ Textual Variant:- በዚህ ጽንሰ-ሐሳብ ላይ ያለውን ሰፊ መሠረታዊ የትርጉም ልዩነት። ° የተቺዎች ምስክርነት:- መጽሐፍ ቅዱስን በጥብቅ የሚተቸው Bart Ehrman ከታዋቂው ምሁር Daniel Wallace ጋር የደረሱበትን አስገራሚ የጋራ ስምምነት። ° በማርቆስ 16፣ በሉቃስ 22፣ በዮሐንስ 5 እና በዮሐንስ 1፥18 ላይ የሚነሱትን የጽሑፍ ልዩነቶችና የምሁራኑን የመጨረሻ ድምዳሜ። ይህ ጥናት መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀትና በምሁራዊ መነጽር መመርመር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ጥሩ መነሻ ሰነድ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን። መልካም ንባብ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ! Faith and philosophy https://t.me/Faithandphilosophy
ዛሬ ከምሽቱ ከ2:30 ጀምሮ ከወንድማችን ጆ @YESHUAapolo ጋር በነገረ ክርስቶስ ላይ ሁለት ባህሪ ወይስ አንድ ባህሪ በሚለውን አባቶች የሚያምኑት የቱን ነው በሚለው ትምህርት ይኖረናል ማንም እንዳይቀር ኦርቶዶክስም ተገኙ ጥያቄ ያላችሁም መጠየቅ ትችላላቹ(https://t.me/afterjesus) @Yeshua_Apologetics_Ministry
የጥንቃቄ መልእክት ይህ ብዙ እንከኖችን የያዘ መጽሐፍ ዛሬ ደግሞ ኢየሱስ ከማሪያም ስጋ አልነሳም የሚል የምንፍቅና ትምህርት አዝሎ ተገኝቷል እና ያ መጽሐፍ በወረቀት ያላችሁ አቃጥሉት pdf ያላቹ አጥፉት አይጠቅምም ኢየሱስ ሰማያዊ ስጋ ነው የሚል ነፍስ መንፈስ እና ስጋ ከድንግል ማሪያም አልወሰደም የሚል ከOnly Jesus ትምህርት ጋር የተጋባ የአጋንንት ትምህርት ነው
እውን ወልድ የሚመጣበትን ቀን አያውቅምን? አዲስ ጽሑፍ በድረገጻችን ላይ ተለቋል። ያንብቡ፤ ለሌሎችም ያጋሩ። https://ewnetlehulu.net/eido-parousia/
እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን!! “አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር፦እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን ይበሉ።” — መዝሙር 40፥16
በወንድም ሚናስ የተዘጋጀ አዲስና ምሑራዊ ጽሑፍ በድረ ገጻችን ላይ ተለቋል:: ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👇 https://ewnetlehulu.net/the-glory-of-the-son-hebrew-1/
ዕብራውያን 1፥2-10 በማስመልከት ለአንድ ሙስሊሙ ሰባኪ በወንድም ዳንኤል የተሰጠ ግሩም ምላሽ ነው። ማስፈንጠሪያውን በመጫን ያንብቡ ➛ https://ewnetlehulu.net/jesus-made-the-worlds/
ለሚሽን አገልግሎት ወደ ደቡብ ኦሞ የሚሄዱ ወገኖች የተለይዩ ልብሶችን ለሚያስፈልጋቸዉ ወገኖች ይዘው ስለሚሄዱ በቤታችሁ የሚገኝ ማንኛውም ልብስ እንድትሰጡን በተለይም የህጻናትን ና የእናቶች ልብሶችን እንድሰጡን ስንል በጌታ ፍቅር እንጠይቃችኋለን 🙏 ለመስጠት ባላችሁበት ሀገር 🙌 #Hawassa 0980404779 . Geni #Shashamne 0916828046. Abdi #Nagele Arsi 0916148697 Gech #Addis.A +251 912766809 Eysu ተባረኩ @revealjesus.
ፍትህ ለአርሲ ኦርቶዶክሶች !!! ፍትህ ለአርሲ ኦርቶዶክሶች !!! ፍትህ ለአርሲ ኦርቶዶክሶች !!! ፍትህ ለአርሲ ኦርቶዶክሶች !!! 😭😭😭😭😭😭😭😭 ጌታ ሆይ እባክህ ተመልከት የንፁሃን ደም መፍሰስ ይብቃ። ለሃገራችንም ሰላም ይሁን።
https://ewnetlehulu.net/gospels-are-not-ananymous/ እውነት ለሁሉ ድኅረ ገጽ ላይም ተለቋል
መንግሥት መሬት ሰጠኝ ብሎ በዚህ ልክ ትከሻ ለመለካካት መሞከር ዋጋ ያስከፍላል:: "ጊዜው የኛ ነው፣ የመንግሥት አካላትም ምንም አያመጡም፣ የኦርቶማራ ዘመን አልፏል፣ እኛ እንደ ፈለግን እንንቀሳቀሳለን እናንተ የትም መሄድ አትችሉም፣ ወዘተ.” የሚሉት ይህ አርጅቶም የማይበስል ህፃን የተናገራቸው ንግግሮች የሙስሊሙን ማሕበረሰብ የሚጠቅሙ አይደሉም:: በምናምናቸው ጉዳዮች በሐሳብ ደረጃ መሟገት አንድ ነገር ነው:: በሃይማኖት ስም ግን እንዲህ ያለ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ፖለቲካ ማስፋፋት የሕግ ተጠያቂነትን ያስከትላል:: "ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግሥት ነው ያልለው" ያለው ያ ጫታም ኮንተ እንደ ገባው አንተም ተመሳሳይ እጣ እንዳይገጥምህ የትዕቢት ምላስህን ብትሰበስብ ይሻልሃል:: ሃይማኖት የግል ነው፤ ሀገር የጋራ ነው::
ለመላው ሙስሊም ወገኖቼ:- የመሲሁ ስቅለት ምልክት ለሆነው ኢብራሒም አንዲያ ልጁን፣ (ይስሀቅን) ለእርድ ላቀረበበት መታሰቢያ፣ ለኢድ-አል-አድሀ-አረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ::" . የዐረፋ በዓል አንድምታ:- ታሪካዊ ዳራ:- የእስልምና እምነት እንደ ሚያስተምረው "ዐረፋ" የሚለው ቃል በዓረቢኛ "አወቀ" ማለት ነው:: ይህም ታሪክ አለው ብለው ያምናሉ:: አደምና ሐዋ ከጀነት ወደ ምድር ከወረዱ በኃላ ለረጅም ዘመናት ተጠፋፍተው ነበር:: በመጠፋፋታቸው ምክንያት፣ ለረጅም ጊዜ ሲፈላለጉ ከቆዩ በኃላ፣ በዙልሂጃ ዘጠነኛው ቀን፣ በሳውዲ ዓረቢያ ባለው በአረፋ ተራራ ላይ ተገናኙ:: ለመጀመሪያ ጊዜ ሲተያዩም "ዐረፍቱከ" … "ዐረፍቱኪ" ተባባሉ:: "አወቅኩህ" … "አወቅኩሽ" ማለታቸው ነው:: በዚህ ምክንያት በዙልሂጃ ዘጠነኛው ቀን የዐረፋ በዓል መከበር ጀመረ:: ሌላኛው አንድምታ:- ኡድ-ሒያ ኢድ-አል-አድሓ-ዐረፋ ኢብራሒም በእርጅና ዘመናቸው ያገኙትን አንዲያ ልጃቸውን መስዋዕት አድርገው ለማቅረብ ወደ ዐረፋ ተራራ ወጡ:: በዚያም ስፍራ ልጃቸውን ለማ-ረድ ቢታገሉም ቢላዋው አላርድ ብሎ ዶመዶመ:: በዚያው ቅፅበት ከወደ ሰማይ ጥሪ መጣላቸው:: የፈጣሪ መላአክም ኢብራሒም ሆይ ታላቅነትህን አስመስክረሃልና እርዱን አቆየው በማለት አወጀ:: በልጁ ምትክም መላአኩ ከገነት ያመጣውን … "በግ" … እንዲያርድና ልጁን ወደ ቤቱ እንዲመልሰው ነገረው:: በዚህ መሠረትም በልጁ ምትክ በጉ ታረደ:: ኢብራሒም ፈጣሪው በግልፅ የታዘዘበትን ያቺ እለት ኢድ-አል-አድሓ በዓል ሆና እንድትከበር ተወሰነ:: ሙስሊም ወዳጆቼ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ከዚህ ሚስጥራዊ እውነታ እርቀው የኢብራሒም ልጅ ለዕርድ ቀረበ ብለው የዕርድ በዓል ዐረፋን እያከበሩ ነው:: ለመሆኑ የኢብራሒም በስተ እርጅና ያገኘው የሚወደውን አንዲያ ልጁን ለዕርድ እንዲያቀርብ የታዘዘው ለምን ይመስላችኃል? እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ ኃጢአት አንዲያ ልጁን ክርስቶስ ኢየሱስን ምትክ አድርጎ እንደሚሰጥ ለማሳየት ነው:: በኢብራሒም "ልጅ" ቦታ ምትክ ሆኖ የታረደው …"በግ"… የክርስቶስ ኢየሱስ ጥላ ነበር:: ሌላው ስለዚህ እውነት ማለትም ኢብራሒም ለመስዋዕት ያቀረበው ማንን ነው? ይስሐቅ ወይስ ኢስማኤል? በዚህ ጉዳይ ቁርኣን በቂ የሆነ የተገለጠ ግንዛቤ የለውም ወይም እውነታው እንዳይገለጥ ተድበስብሶ የቀረ መሆኑን እውን ነው:: ኢብራሒም በስም ያልተጠቀሰ አንድ ልጁን ለመስዋዕት እንዳቀረበ ብቻ ነው ቁርኣን የሚተርከው:: ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡(ሱራ 37:102) ስለዚህ አንቀፅ ሙስሊሞች በተሳሳተ አተረጓጎም በመፍታት ለመስዋዕት የቀረበው እስማኤል ነው የሚል ጉንጭ አልፋ ሂስ ለማቅረብ ሲጥሩ ይስተዋላል እውነታው ግን በቁርኣን ውስጥ ለመስዋዕት የቀረበው ይስሀቅ አልያም እስማኤል ነው። አይልም ቁርኣን የሚለው ለኢብራሒም በስተ እርጅናው ሁለት ልጆች ማለትም እስማኤል የተባለው ልጁ ከቤት ሰራተኛው ሐጅራ ወይም አጋር እንደወለደና ሌላኛው ልጁ ይስሀቅ ከእውነተኛ ሚስቱ ከሣራ መውለዱን በመግለፅ በስም ያልተገለጠ ልጁን ለመስዋዕት ማቅረቡን በመተረክ ለመስዋዕት የቀረበው እውነተኛ አካል ማንነት ከመግለፅ ይቆጠባል:: ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡(ሱራ 11:71) «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡::(ሱራ 14:39) ቁርኣን ለመስዋዕት የቀረበው ልጅ እውነተኛ ማንነት ከመናገር የተቆጠበውና አደባብሶ ያለፈው በዚህ ምክንያት ነው:: እነሆ የተገለጠ እውነት ከመጽሐፍ ቅዱስ:: ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው። አብርሃም ሆይ። አብርሃምም። እነሆ፥ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፥ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሕቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነሥቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ። በሦስተኛውም ቀን አብርሃም ዓይኑን አነሣና ቦታውን ከሩቅ አየ። አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው። አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን። አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ሁለቱም አብረው ሄዱ። ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው። አባቴ ሆይ አለ። እርሱም። እነሆኝ፥ ልጄ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት ነው? አለ። አብርሃምም። ልጄ ሆይ፥ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያውን ሠራ፥ እንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው። አብርሃምም እጁን ዘረጋ፥ ልጁንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና። አብርሃም አብርሃም አለው፤ እርሱም። እነሆኝ አለ። እርሱም። በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ። አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፥ በልጁም ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው።(ዘፍ 22:1-13) ይስሐቅ ለመስዋዕት በቀረበበት ቦታ ሞሪያም ተራራ በአሁኑ አጠራር ጎሎጎታ ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢአት ምትክ ሆኖ ተሰዋልን::" ሙስሊም ወዳጆች በድጋሚ እንኳን ለመስዋዕት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: በዓሉን ስታከብሩ ሀሳባችሁ በመስዋዕቱ ላይ ይሁን:: From አብድል ወሀብ
የመጀመሪያውና ሁለተኛው የሙስሊም ትውልዶች የመስዋዕቱ ልጅ ይስሐቅ እንደ ሆነ ነበር የሚያምኑት:: ኋላ ግን ይህ እውነታ ተክዶ እስማኤል ነው የሚል ትርክት ተፈጠረ:: ለምን ይሆን? ሙስሊሞች ሌሎች ሃይማኖታትን መጻሕፍታቸውን ይለውጣሉ በማለት ይወነጅላሉ:: ነገር ግን እንደ እነርሱ የገዛ መጻሕፍታቸውን የሚለዋውጡና የሚክዱ ሕዝቦች ታይተው አይታወቁም:: ማስረጃዎቹን በሙሉ በዚህ ቪድዮ ውስጥ ታገኛላችሁ:: https://youtu.be/t3AFocmDtiw?si=7GWG2yJCF8gGQBJl
1) ኢየሱስ አምላክ ነው “አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።” — ሮሜ 9፥5 2) ኢየሱስ ጌታ ነው “እናንተ መምህርና #ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።”— ዮሐንስ 13፥13 3) ኢየሱስ ምድርን የመሰረተ ነው “ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት #ምድርን #መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤”— ዕብራውያን 1፥10 4) ኢየሱስ አይለወጥም “እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ #አንተ #ግን #አንተ #ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።” — ዕብራውያን 1፥12 5) ኢየሱስ የአብ ልጅ ነው “ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት #በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤”— ዕብራውያን 1፥2 6) ኢየሱስ ሰው ነው “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤” — ሐዋርያት 2፥22 7) ኢየሱስ መልዕክተኛ ነው “እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር፦ እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት #የላከኝ እውነተኛ ነው፤”— ዮሐንስ 7፥28 8) ኢየሱስ አስታራቂ ነው “እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል #አስታረቃችሁ።” — ቆላስይስ 1፥21-22 9) ኢየሱስ መካከለኛ ነው “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም #መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው #የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 10) ኢየሱስ ሐዋርያ ነው “ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን #ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤” — ዕብራውያን 3፥1 11) ኢየሱስ ሊቀ ካህናት ነው “ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና #ሊቀ #ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤” — ዕብራውያን 3፥1 12) ኢየሱስ መሲሕ ነው “እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ #መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው።” — ዮሐንስ 1፥42 13) ኢየሱስ ነቢይ ነው “ኢየሱስ ግን፦ #ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።” — ማቴዎስ 13፥57 14) ኢየሱስ አስተማሪ ነው “ኢየሱስም መልሶ፦ ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? አለው። ዕውሩም፦ #መምህር ሆይ፥ አይ ዘንድ አለው።” — ማርቆስ 10፥51 15) ኢየሱስ እረኛ ነው “መልካም #እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።” — ዮሐንስ 10፥11 16) ኢየሱስ ወንጌላዊ ነው “የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች #ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።” ሉቃስ 4፥17-19 17) ኢየሱስ ሕይወት ነው “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት #ሕይወትም #ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”— ዮሐንስ 14፥6 18) ኢየሱስ መንገድ ነው “ኢየሱስም፦ #እኔ #መንገድ ና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 19) ኢየሱስ እውነት ነው “ኢየሱስም፦ #እኔ መንገድና #እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 20) ኢየሱስ መላዕክት ሁሉ የሚሰግዱለት ነው “ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ #የእግዚአብሔር #መላእክት #ሁሉም #ለእርሱ #ይስገዱ ይላል።” — ዕብራውያን 1፥6 👉 ኢየሱስ …………
infallibility and inspiration..... kale Jonathan sura
ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ ፡ " #መዳንም #በሌላ #በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ #ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።"(የሐዋርያት ሥራ 4:12) የሰው ልጆች ሁሉ ይድኑበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠ ስም አንድ ብቻ ነው እርሱም ኢየሱስ ነው ወደ እርሱ በመምጣት ከዘላለም ሞት ትረፉ። https://t.me/seleslamenwk https://t.me/seleslamenwk