እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
Статистика“እውነት ለሁሉ” በዓለም ዙርያ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ክርስቲያኖች የተመሠረተ ድረ-ገፅ ሲሆን እስልምናንና ክርስትናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ የኦዲዮና የቪድዮ መረጃዎችንም ያቀርባል፡፡ የበለጠ ለማወቅ http://www.ewnetlehulu.net ይጎብኙ።
- Последний пост
- 30 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 621
- 1/48двое суток
- 3 003
- 1/72трое суток
- 3 239
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በሀገር ውጥ አካውንት የወንድማችን ዳንኤልን የትምህርት ወጪ ማገዝ የምትፈልጉ ወገኖች በዚህ የባንክ አካውንት መርዳት ትችላላችሁ:: 1000784785207 CBE Amanuel Endale
ተወዳጆች በዚህ አገልግሎት ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየውና የእውነት ለሁሉ ዌብሳይት መሥራችና አርታዒ ወንድማችን ዳንኤል የዶክትሬት ትምህርቱን ለማጠናቀቅ የናንተ እርዳታ ያስፈልገዋል። አገልግሎቱን የምትወዱ ሁሉ ከጎኑ እንድትቆሙ በታላቅ ትህትና እንለምናችኋለን። በድርጅት መርዳት የምትችሉና ኦፊሴላዊ ደብዳቤ የምትፈልጉ በውስጥ ብታነጋግሩን ከላኪ ድርጅት ደብዳቤ ማቅረብ እንችላለን። በዚህ የgofundme ገጽ በመግባት የምትችሉትን እንድታደርጉ መልካም ፈቃዳችሁ ይሁን። ከሀገር ውስጥ መርዳት ለምትፈልጉ በውስጥ ወንድማችን ዳንኤልን በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ማነጋገር ትችላላችሁ @danit4all ተባረኩ! https://www.gofundme.com/f/expand-ewnet-lehulus-impact-with-your-help/cl/s?utm_campaign=fp_sharesheet&utm_content=amp20_control&utm_medium=customer&utm_source=copy_link&lang=en_GB
አሕመዲን ጀበል የኢትዮዽያ ሕዝበ ሙስሊም ቆጠራ ተጭበርብሯል ብሎ እያለቃቀሰ ነው። ምን ዓይነት ጥናት ሠርቶ ይሆን? በ1999 ዓ.ም በተካሄደው የኢትዮጵያ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከአጠቃላይ ግምት ውስጥ ወደ 2 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ቁጥር 'እንደጠፋ' እና ከቆጠራው ውጭ እንደ ተደረገ የተነገረው የአማራ ክርስቲያንም በዚህ ልክ አልጮኸም። በወቅቱ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ እንደ ነበሩ የሚታወስ ነው። በራሳቸው ሰው የተመራ ቆጣሪ ኤጀንሲ ለዚያውም ይህን ያሕል ከሞላ ጎደል ክርስቲያን የሆነ ሕዝብ የት እንደ ገባ እንደማይታወቅ በድፍረት አስታውቆ ሳለ ሙስሊሙ እንደ ተጭበረበረ መናገር አሳፋሪ ነው። ወሓቢዝም ምንም ዓይነት ሐፍረትና ይሉኝታ የማያውቅ ጭፍንና ጨለምተኛ ንፅረተ ዓለም ነው። ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት በሀገሪቱ ካለ ይህንን ግለሰብ መርዘኛ ምላሱን እንዲሰበብ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን። ይህ ካልሆነ ግን የኢትዮዽያ ሕዝብ ሳይቆጠር ለዘላለም ሊቀር ነው። ከተቆጠረም እንዲህ ያሉ ማሰብያቸው የተናጋ ግለሰቦች ከፍተኛ ሁከት ሊፈጥሩ ይችላሉ። በሕግ አምላክ!
ChatGPT ተጠቅማ እስልምና እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ የምትሞክረዋን አውስትራሊያዊት ፈረንጅ አወቃችኋት? ሊሊ ጄይ ትባላለች። "ሀይ ቻት ጂፒቲ ከእስልምናና ከከርስትና የቱ ነው እውነት?" ብላ ትጠይቃለች። ማሽኑም "ያለ ምንም ጥርጥር እስልምና!" ብሎ ይመልስላታል። እንደዚያ ብሎ እንዲመልስ አስቀድማ ነግራው ነው ቪድዮ የምትቀዳው። እንዲህ ያሉ ቪድዮዎችዋን ሙስሊሞች በሚሊዮኖች እየተቀባበሉ በኢንተርኔቱ ዓለም ታዋቂ ሆና ነበር። ሴትዮዋ ቅንጡ ኑሮ የምትኖር ሲሆን "ሊሊ ጄይ ፋውንዴሽን" የተሰኘ በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የተራቡ ህፃናትን እንደሚመግብ የሚናገር የእርዳታ ድርጅት ትመራለች። ድርጅቱ ከሙስሊሞች ዘንድ ብዙ ገንዘብ የሚላክለት ሲሆን በየ ጊዜውም እነዚህ ህፃናት እርዳታ ሲቀበሉ የሚያሳዩ ቪድዮዎችን ትለቃለች። ምን እንደ ተከሰተ ገምቱ? አብዛኞቹ የምትለቃቸው ቪድዮዎች በቻት ጂፒቲ የተቀናበሩ እንጂ እውነተኛ አይደሉም! የሙስሊሞች የዋህነት ይገርመኛል። ሃይማኖታቸውን እንደ ተቀበሉ በሚናገሩ እንዲህ ያሉ ብልጣብልጥ ሰዎች ሁሌ ይታለላሉ። እንዲህ ያለውን የዋህነት ከክፋት አልቆጥረውም። የተታለሉት ሃይማኖታቸውንና አምላካቸውን ስለሚወዱ ከቅንነታቸው የተነሳ እንጂ መታለል ፈልገው አይደለም። የአምላኩን ስም ከጠራችሁና ሃይማኖቱን ካሞገሳችሁ እንደ ሙስሊም በፍጥነት የሚታለል ሕዝብ የለም። ዛሬም በሀገራችን የሚገኙ ብዙ ሌቦችና አጭበርባሪዎች እስልምናን የተቀበሉ በመምሰልና ሃይማኖቱን በመከላከል ረገድ ፊታውራሪዎች በመሆን ሙስሊሙን ማሕበረሰብ ያልቡታል። እንዲህ ባሉ ጮሌዎች እንዳይታለል ሕዝባቸውን መጠበቅ የሙስሊም መሪዎች ሚና ቢሆንም እነርሱም በዚህ የተሳሳተ መንገድ ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት ካላቸው ጉጉት የተነሳ የነዚህ ኪስ አውላቂዎች ተባባሪ ሲሆኑ ይታያል። ሙስሊም ወገኖች ንቁ::
እውን ወልድ የሚመጣበትን ቀን አያውቅምን? አዲስ ጽሑፍ በድረገጻችን ላይ ተለቋል። ያንብቡ፤ ለሌሎችም ያጋሩ። https://ewnetlehulu.net/eido-parousia/
በወንድም ሚናስ የተዘጋጀ አዲስና ምሑራዊ ጽሑፍ በድረ ገጻችን ላይ ተለቋል:: ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👇 https://ewnetlehulu.net/the-glory-of-the-son-hebrew-1/
አላህ አይጸልይም የምትሉ ሙስሊሞች እስኪ ይህንን ሐዲስ አንብቡ:: "ነቢዩ እንዲህ አሉ:- በእኔ ላይ አንድ ጊዜ የሚጸልይ ሰው አላህ በእርሱ ላይ አስር ጊዜ ይጸልያል::"
ዕብራውያን 1፥2-10 በማስመልከት ለአንድ ሙስሊሙ ሰባኪ በወንድም ዳንኤል የተሰጠ ግሩም ምላሽ ነው። ማስፈንጠሪያውን በመጫን ያንብቡ ➛ https://ewnetlehulu.net/jesus-made-the-worlds/
እውን የወንጌላት ጸሐፊያን አይታወቁምን? በሚል ርዕስ አዲስ ጽሑፍ በድረ-ገጻችን ላይ ታትሟል:: እንድታነቡ እጋብዛለሁ https://ewnetlehulu.net/gospels-are-not-ananymous/
መንግሥት መሬት ሰጠኝ ብሎ በዚህ ልክ ትከሻ ለመለካካት መሞከር ዋጋ ያስከፍላል:: "ጊዜው የኛ ነው፣ የመንግሥት አካላትም ምንም አያመጡም፣ የኦርቶማራ ዘመን አልፏል፣ እኛ እንደ ፈለግን እንንቀሳቀሳለን እናንተ የትም መሄድ አትችሉም፣ ወዘተ.” የሚሉት ይህ አርጅቶም የማይበስል ህፃን የተናገራቸው ንግግሮች የሙስሊሙን ማሕበረሰብ የሚጠቅሙ አይደሉም:: በምናምናቸው ጉዳዮች በሐሳብ ደረጃ መሟገት አንድ ነገር ነው:: በሃይማኖት ስም ግን እንዲህ ያለ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ፖለቲካ ማስፋፋት የሕግ ተጠያቂነትን ያስከትላል:: "ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግሥት ነው ያልለው" ያለው ያ ጫታም ኮንተ እንደ ገባው አንተም ተመሳሳይ እጣ እንዳይገጥምህ የትዕቢት ምላስህን ብትሰበስብ ይሻልሃል:: ሃይማኖት የግል ነው፤ ሀገር የጋራ ነው::
የመጀመሪያውና ሁለተኛው የሙስሊም ትውልዶች የመስዋዕቱ ልጅ ይስሐቅ እንደ ሆነ ነበር የሚያምኑት:: ኋላ ግን ይህ እውነታ ተክዶ እስማኤል ነው የሚል ትርክት ተፈጠረ:: ለምን ይሆን? ሙስሊሞች ሌሎች ሃይማኖታትን መጻሕፍታቸውን ይለውጣሉ በማለት ይወነጅላሉ:: ነገር ግን እንደ እነርሱ የገዛ መጻሕፍታቸውን የሚለዋውጡና የሚክዱ ሕዝቦች ታይተው አይታወቁም:: ማስረጃዎቹን በሙሉ በዚህ ቪድዮ ውስጥ ታገኛላችሁ:: https://youtu.be/t3AFocmDtiw?si=7GWG2yJCF8gGQBJl
ውይይቱ ለምን ቀረ? (በአጭሩ ከቀደመው ውይይታቸው ውድቀት ሳያገግሙ ሌላ ዱላ ስላልፈለጉ ተሰርዟል😁) እስልምና ለቃሉ በጭራሽ የማይታመን ትውልድ እንደሚፈጥር ስላሳያችሁን እናመሰግናለን ማስታወቂያው ላይ እንደተመለከታችሁት ከሙስሊም ወገኖች ጋር ግንቦት 13 እና 15 ውይይት ነበረን፤ እነሱም ተስማምተው ለአወያዩም ተነግሮት ቀኑን እየጠበቅን ባለንበት የኔን ማስታወቂያ ተከትሎ ኢብራሂም የተባለው ተወያይ ፕሮግራሙ እንደራዘመ በቴሌግራም ቻናሉ አሳወቀ፤ ይህንን ሲያደርግ ግን ከኛ እውቅና ውጪ ነበር። ለዚህም ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ ጠይቆናል (የድምጽ ማስረጃ አለ)። በቀጣይ ተሰብስብን ስለ ውይይቱ በምናወራበት ጊዜ ውይይቱ በተያዘለት ቀን እንዳይካሄድ ሲደረድሩ የነበረውን የምክንያት መአት ብትመለከቱ እናንተ ራሱ ታዝኑላቸዋላችሁ😁 ያም ሆኖ ግን ውይይቶቹ በአንድ ሳምንት ልዩነት እንዲደረጉ ባቀረቡት ሃሳብ ተስማምተን እሺ ባልናቸው ጊዜ አሁንም ለአንድ ወር ካልተራዘመ እንደማይወያዩ አሳወቁን😁 (ለእያንዳንዱ ላወራሁት ነገር ማስረጃ አለን) በህይወቴ ውይይት እንደጦር ሲፈራ ያየሁት Crew እነዚህ ሶስት ሙስሊሞችን ነው። ይገባናል ባለፈው የደረሰው ውርደት ባሁኑ እጥፍ ሆኖ እንዳይደገም በመስጋት ነው የሸሹት፣ ደግሞም አዎ ደፍረው ቢመጡ ኖሮ ነቢያቸውንም ቁርአናቸውንም ክደው በተመለሱ ነበር። እስልምና ለቃሉ በጭራሽ የማይታመን ትውልድ እንደሚፈጥር ስላሳያችሁን እናመሰግናለን
እግዚአብሔርን አባት ብሎ መጥራት ምንኛ መታደል ነው:: ይህንን ጥሩ ስብከት እንድትሰሙ እጋብዛችኋለሁ https://addiskidanvb.com/sermons/our-father-who-art-in-heaven/
ለወንድሞች በሙሉ ይህንን ፖስት የተደረገውን አይታችኋል ? ይህ ማንቂያ ደወል ነው ምንም እንዳልተፈጠረ አይተን ማለፍ አልቻልንም። በዚህ ጊዜ እንደ አስቴር ምላሽ የሚሰጥ የቆረጠ ትውልድ መቀስቀስ እንዳለብን ተሰምቶናል። ስለዚህ ከፊታችን ባለው እሁድ እድሜው ለመምረጥ የደረሰ ማንኛውም የኛ ሰው ሁሉ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ በየቤተክርስቲያናችን መደበኛ አምልኮ ላይ ማስታወቂያ መነገር አለበት። ምክንያቱም ምድራችንን ለክርስቶስ ተቃዋሚ አሳልፈን ልንሰጥ አይገባንም የመምረጥ መብታችንን ሳናባክን ነገሮችን በማስተዋል ማየት አስፈላጊ ነውና ሁላችንም ግን በየቤታችን የምርጫ ካርድ እንውሰድ የምርጫ ካርድ መውሰድ የሚቻለው እስከ እሮብ ማለትም እስከ ሚያዝያ 14 2018 ዓ.ም ብቻ ነውና። ------ ይህ ☝️ ከአንድ ሰው የደረሰኝ መልእክት ነው:: ምን ትላላችሁ?
"በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳይያስ 53:4-5)
ይቺ ጽሑፍ ከተነበበች በኋላ በደንብ ሼር ትደረግ:: የአሕመዲን ጀበልን አረባዊ የፖለቲካ ሸፍጥ የምታጋልጥ ናት https://www.facebook.com/share/p/1AyKikTe17/?mibextid=wwXIfr
አዲስ ጽሑፍ። በእንተ ማቴዎስ 28፡19 – እውን ሰርጎ-ገብ ጽሑፍ ነውን? https://ewnetlehulu.net/matt-28-19-authenticity/
መነበብ ያለበት አዲስ ጥናታዊ ጽሑፍ የማርቆስ ወንጌል 16፡9-20 ትክክለኛነት https://ewnetlehulu.net/the-authenticity-of-mark-16/
ሰይጣን በሙስሊሞች አፍንጫ ውስጥ ያድራል? የሙሐመድ ትምህርት
ስለ ስቅለት እስልምና የማይመልሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች