መልህቅ
Статистика"ይህም ተስፋ እንደነፍስ መልሕቅ አለን!" ዕብ 6:19 Youtube: https://www.youtube.com/@zanchorr Tiktok: https://www.tiktok.com/@zanchorr ቻነሉና ግሩፑ የሚመሩባቸውን የአዲስ ኪዳን መርሆች ከቀጣዮቹ ክፍሎች ማግኘት ትችላላችሁ። Titus 2 : 2, 6 - 8 1 Peter 3: 8 - 12 James 3: 13 - 18
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 573
- 1/48двое суток
- 656
- 1/72трое суток
- 708
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የምታምኑትን ነገር Infallible የሆነ አካል ካልነገራቹ እውነት መሆኑን ልታውቁ ትችላላችሁ ግን እርግጠኛ ልቶኑበት አትችሉም… 😁 ይህን አንተ የምትለውን እርግጠኛነት (which is absolute certainity) አንፈልገውም ፤ አያስፈልገንምም! እውነትን ማወቅ ከቻልን (which necessarily requires a moral certainity to be justified) በቂ ነው።
ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ በሸለቆ ቢሆን በተራራ አመቺ ነው ደስ ያሰኛል እርካታን ይሰጣል
እግዚአብሄር እያለ ለምን እፈራለሁ ? አምናንም ካቻምናንም ክንዱን አይቻለሁ!
ስለ ልሳን የማውቀው ነገር የለም። አለምም ፤ የለምም የሚል የተደመደመ አቋም የለኝም። የነብይና የሐዋርያ ሹመት የለም። ትንቢት ፤ ፈውስ ፤ አጋንንት ማስወጣት እና በየትኛውም ጉዳይ ላይ በግልም ቢሆን በጋራ ፀልዮ መልስ ማግኘት አሉ። ነገር ግን እነዚህም በአይነትና ተከታታይነታቸው ከሐዋርያትና ከነብያት ዘመን አንፃር ያነሱ ናቸው። የግድም መጠበቅ ያለባቸው አይደሉም። እኛ ሳናቋርጥ በነገሮቻችን ውሰጥ ሁሉ እንጠይቃለን ፤ እግዚአብሄር ግን እንደፈቀደ ይሰራል።
без подписи
አፕሮች ላይ እንለያያለን።
መጠየቅ ያለበት እንደውም የተለየ ነገር ያረገው ወይም ልዩነቱን ያመጣው ነው እንጂ ባለበት የዘለቀው ሰው አይደለምኮ። ሁለቱም ተመሳሳይ status ላይ ከሆኑና በዚህም ትክክል በሆነ state እንዲዘልቁ በቂ ፀጋ ቀርቦላቸው ይህ state እንዲለወጥ የተለየ ነገር ያደረገው የካደው ሰው ነው። ስለዚሀ እሱ ነው ምን ጎሎበት ነውና ነው የካደው ተብሎ መጠየቅ ያለበት። ምንም አይኖርምና የሱ በእግጥም ተአምር ይሆናል። እኛም ማብራሪያ አንሰጥበትም። ነገር ግን የጠፋው ሰውዬ በለወጠው status እና ባመጣው difference የፀናው ሰውዬ የሆነ የተለየ ነገር አድርጎ አልያ ሆኖለት ነው ማለት non sense ነው።
ከConversion በኋላ Synergy አለ ማለት ሰውየው እግዚአብሄርን ማድመጥ ፤ መረዳት ፤ መውደድ ፤ ማመን ፤ መከተል ይችላል ማለት ነው። ፎርሙላው እምነትህ የሚጠበቀው በመንፈስቅዱስ ብቻ ነው ሲል እያነፃፀረ ያለው ከስራህ ጋር ነው። በስራህ አይደለም የምትጠብቀው ይላል። ይህ ማለት በአጭሩ እምነትህ የሚጠበቀው እግዜር በሚያቀርብልህ ፀጋ እየጠነከረና እያደገ ሲሄድ ስለሆነ Efficient Cause-ኡ እግዜር ነው እየተባለ ነው። የአንተ ሀላፊነት ከላይ እንዳልኩት ይህንን የሚያፀና ፀጋውን ባስቀመጠበትና በሚሰጥበት ቦታ መቅረብና መቀበል ብቻ ነው። ይህን ለመቃወም አያይ በስራዬ ጠብቀዋለሀው ብለህ ማለት አለብህ። ስራህ በእግዜር የማመንህና በእርሱም ፀጋን የመቀበልህ ውጤት (ፍሬ) እና ማስረጃ ከሆነ እንዴት ነው መልሶ የእምነትህ ማዝለቂያ Efficient Cause የሚሆነው ?
አዎ ይመስለኛል እና ይችላሉ ግን ቢያንስ ከዌስተርኑ አማራጭ ማብራሪያዎች የሚወጡ አይስለኝም። እስከማውቀው የኢስተርኑን EED መቀበል የሚችሉ አይመሰለኝም። ግን እርግጠኛ አይደለሁም።
ተገቢ አይደለም።
በጣም General የሆነው መልስ በተቻለ መጠን ፀጋውን ከማገኝበት ቦታ ራሴን ላለማራቅ መጣር ነው። በወንድሞች ህብረት ውሰጥ መገኘት እና ቅዱስ ቁርባንን ያለማቋረጥ መውሰድ የመጀመሪያው ትልቁ መንገድ ነው። ሰው የዋለበትን ስለሚስል በዛ ውስጥ በመገኘት ውስጥ ብቻ ሀይል አገኛለሁ። በግል ደግሞ ያው የምታውቃቸውን መፀለይ ፤ ቃል ማንበብ ማሰላሰል የሚባሉትን ልጠቅስልህ እችላለሁ። ነገር ግን ችግሩ እነዚህን ራሱ ማረግ የምንደክምበትና ምንዝልበት ጊዜ አለ እና ያኔ የሚረዳኝ ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በዛው ድካም ውሰጥንኳ ሆኜ የክርስቶስን ፍቅር ፤ የእግዚአብሄርን ምህረት በተደጋጋሚ ማሰብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ መዝሙር ነው። መዝሙር ማዳመጥም ሆነ መዘመር የእግዚአብሄርን ምህረት እንዳስብ የሚረዳኝ ነው ፤ ይበልጡንም ደግሞ ወደፀሎት የሚስበኝም ነው። ብዙ መዝሙሮችን እከፍትና እሰክነካና እስኪያንበረክከኝ ድረስ እየቀያየርሁ አዳምጣለሁ። ይብዛም ይነስም የገባው ነውና የሚወጣው የሆነ ጊዜ ላይ ሲመልሰኝ አገኘዋለሁ። አንዴ ከተንበረከኩ በኋላ ግን ብዙ ድካሜን ጠርጎልኝ ስለሚሄድና አቅም ስለሚሰጠኝ በተቻለ አቅም ተመሳሳይ ሪትም ይዤ ለመቀጠል እጥራለሁ። ይህ እንግዲ በግል ላለ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። እዚህ ላይ ከላይ ያልኩት ህብረት ሲታከልበት እና በዛም ህብረት ውስጥ በአገልግሎትና ሀላፊነቶች ራስህን ስታስጠምድ የተሻለ ለመመላለስ ይረዳሀል። ያው ነገሩን በጣም Mechanical ማረግም አልፈልግም ምክንያቱም ሁሌ ለሁሉም እንደዛ ይሰራል ማለት አይደለም። ቢያንስ ግን መጨረሻ ላይ የሚያቆመን የእግዚአብሔር ፀጋ መሆኑን አውቃለሁ። ፀጋው ለበሽተኞችንጂ ለፍፁማን የቀረበ አይደለምና በጣም በደከመን ሰአት ወደፀጋው ለመቅረብና ወደጌታ ለመሸሽ እንደውም በጣም ትክክለኛው ሰአት ነው።
የወጀቡ አዛዥ የተራራው ሰሪ የሸለቆው ጌታ ለጨለማው መሪ የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ አንተ ነህ የእኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ https://youtu.be/FCGExvNywx0?si=C5844lAbY-jdvOwZ
ከአንድ ድምፀ ጥዑም ዲያቆን ጋር የነበረኝ አጭር ቆይታ .. የቱ ገዳም ገብተህ ነው እንዳትሉኝ 😅
ያልከው ሁሉ እውነት ሆኖ ሳለ still ግን ፀጋው Resistable መሆኑን አንጥልም ለዛም ነው መካድ possible የሆነው። የቅድሙ ሰው ነህ ደግመህ የጠየከኝ ብዬ ስለማስብ ከሱ ጋር በተገናኘ ይህን የማለት ምንም ስህተቱ አይታየኝም። መጥፋት እዲቻል ግዴታ ለመዳን የተለየ የሚቆጠር መልካም ነገር ግድ ይላል የሚለው ቅድመ እሳቤ አመክኗዊ ያልሆነና ያልተሞገተለት ሀሳብ ነው።
ያው GodLogic እና እፎይ
ምንም ባለማድረጋቸው። በተሰጣቸው እምነት ስለዘለቁ። እምነት essentially ባለመቻል እና በሚችለው አካል ላይ በመደገፍ (trust) የሚተረጎም ነው። የሆነ እንደ መልካም ስራ የሚመዘን የሚቆጠር ነገር አይደለም። ከእግዜር ከራሱ የተቀበልነው ፤ በቃሉና በቅዱሳት ምስጢራቱ በራሱ ፀጋ የሚጠነክርና የሚዘልቅ ነው።
ሙሉ የዕብራውያን መፅሀፍ መሸሸጊያዬ ነው። የወንጌላቱን የመጨረሻ 4, 5 ምዕራፎች ዝም ብሎ መደጋገምም እንደዛው። ወደ ዕብራውያን 7:22-26 ²² እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል። ²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ ²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ²⁶ ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤
እርግጥ ነው መስቀሉ የእግዚአብሄር ultimate self revelation ነው። በእርሱም ፍቅሩና ፅድቁ ተገልጠዋል። ይህ ግን ሌሎቹ የእግዚአብሄር ባህሪያት ላይ ባለን መረዳት ላይ ለውጥን የሚያመጣ ነገር አለው ብዬ አላስብም። ለምሳሌ መስቀሉ የገለጠው ፍቅሩ Simplicityው ላይ ያለህን መረዳት እንዴት ሊነካው ይችላል ? ምናልባት ጥያቄህን አልተረዳሁት ይሆናል።
ያው GodLogic እና እፎይ
ልዩነቱ የሚጠፉት ሰዎች Active Rejection ብቻ ነው።