AASTU-ECSF
СтатистикаEvangelical Christian Students' Fellowship at AASTU CBE: 1000656422959 Daniel Kebede and/or Samuel Tesfaye Telebirr: 0931106178 Daniel Kebede Stay tuned via: @galleryaastuecsfBot @souceoflifeBot @AASTU_Anony_Counseling_bot @i4u_contact_bot
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 26
- Всего постов
- 163
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 315
- 1/48двое суток
- 360
- 1/72трое суток
- 389
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#Last_Message ዳዊት ግን በእግዚአብሔር አምላኩ በረታ "ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተማራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር በረታ።" - 1 ሳሙኤል 30:6 የአማሌቅ ሰዎች ጺቅላግን አቃጥለው የዳዊትንና የሰራዊቱን ሚስቶችና ልጆች በሙሉ ማርከው ወስደው ነበር። በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ማልቀስ እስከሚያቅታቸው ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። በተጨነቀውና ተስፋ በቆረጠው ሕዝብ ዘንድም ዳዊት ሊወገር ተቃረበ። በሰው በኩል ምንም ተስፋ በሌለበትና በጨለማ ሰዓት ውስጥ ግን፡- 👉 “ዳዊት ግን በእግዚአብሔር አምላኩ በረታ” ዓለም በዙሪያችን ስትፈርስ፣ አብረውን ያሉት እንኳን ተስፋ ቆርጠው በላያችን ላይ ሲነሱ፣ በሰው ጥበብ ወይም በራሳችን ጉልበት ልንቆም አንችልም። ዳዊት በችግሩ ላይ ሳለ ወደ ጠራው አምላክ ተመለከተ፤ በእግዚአብሔርም በረታ። 👉 እግዚአብሔርንም በኤፉድ ጠይቆ “ተከተላቸው፤ ፈጽመህ ታገኛቸዋለህ፣ የተወሰደውንም ሁሉ ታድናለህ” የሚል የምስራች ሰማ። በራሱ ጥበብ ሳይሆን በእግዚአብሔር መሪነት ሄዶ የተወሰደበትን ሁሉ በድል አድራጊነት አስመለሰ! ዛሬ በሕይወታችን ተስፋ የሚያስቆርጥ፣ የተስፋችን ከተማ የተቃጠለ የሚመስልበትና ሰዎች ሁሉ የዞሩብን የሚመስልበት ሁኔታ ውስጥ እንሆን ይሆናል። ነገር ግን በሰዎች ተስፋ መቁረጥ መካከል እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር አምላካችን እንበርታ! በጨለማ ውስጥ በእግዚአብሔር መበርታት፣ እርሱን መጠየቅ እና የታጣውን ሁሉ በድል ማስመለስ ይሁንልን። አሜን! 🤲 መልካም አዳር ይሁንላችሁ ተባረኩ!!!!! #እግዚአብሔርን_መፈለግ #በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
#Winners 🥇Hana Debela Wollega University (Welcome😊) 4th Year Public Administration and Development Management Department 🥈 Seble Simon From AAU (Welcome😊) 3rd Year Law Student 🥉Ebisa Abera 2nd Year Engineering #እግዚአብሔርን_መፈለግ #በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
#ማስታወቅያ 📌እንደሚታወቀው በክረምት ውስጥ 1ኛ እና 2ተኛ ሳሙኤል መፅሐፍን ለመጨረስ አስበን ቆርጠን ተነስተናል ፤ ስለሆነም ቀጣይ ሳምንት 2ኛ ሳሙኤልን ከምዕ 4-9 አንብበን እንድንገናኝ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን። 📌 ክረምቱ ገብቶ በአካል ቢያራርቀንም ግን ለsmall group ቤተሰቦቻቹ እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ መደወል መጠያየቅ እንዳትረሱ ፤ መያያዛችሁን እንዳትተዉ አደራ አደራ እንላለን፡፡😊 📌በየሳምንቱ እንደምናደርገው ላልተደረሱ ህዝቦች መጸለያችሁን አትዘንጉ። 📌በመጨረሻም የትኛውም ዓይነት የጸሎት ርዕስ ያላችሁ ሰዎች በሙሉ ከስር ባለው Fellowshipኡ የTelegram Account መላክ ትችላላችሁ። 👉🏼@aastuecsfcontact👈🏻 #እግዚአብሔርን_መፈለግ #በመመለስ #በፅድቅ_ኑሮ #በመታመን Follow AASTU ECSF On : Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
#Book_Club 📚 ያልተንኳኩ በሮች ✍️ በጳውሎስ ፍቃዱ የፍቅር እውነተኛነት የሚታወቅበት መንገድም አለ - ተግባር! እንኳን እግዚእብሔር፣ እኛ እንኳ እርስ በርስ “በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በእንደበት እንዋደድ” ተብለናል (1ዮሐ. 3÷18)፡፡ በእርግጥ እግዚያብሔር የልመናችንን ቃል ሰምቶልናልና እኛም በተራችን፣ “እንወድሃለን!” ልንለው እንችላለን:: ሆኖም እንደ እምነትና ትዕግሥት ሁሉ ፍቅርም ይፈተናል:: “እግዚአብሔርን እንወደዋለን” ብለን ስለ ተናገርንና ስለ ዘመርን አይደለም እርሱን መውደዳችን የሚረጋገጠው፡፡ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ" ብሏልና እግዚእብሔርን መውደዳችን ትእዛዛቱን በደስታ በመፈጸማችን ይገለጣል፤ ይረጋገጣል:: ይህ መፅሀፍ "ያልተንኳኩ በሮች" ብሎ የሰየማቸውን የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት በግልፅ በእግዚአብሔር ቃል መነፅር በማየት ይሞግታል። እንድታነቡት እና እንድትማሩበት እንጋብዛለን። Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
#Book_Club የአሸናፊዎቹን ዝርዝር እስክናሳውቅ ድረስ በየሳምንቱ እንደምናደርገው ብታነቡት የሚጠቅምና የምትማሩበትን መፅሃፍ የምንልክላችሁ ይሆናል።
#Answers 1.ለ 2.ሀ 3.ሐ 4.ለ 5.መ 6.ሐ 7.ለ 8.ለ 9.ሀ
❌ ሰዓት አልቋል ❌
1.1ኛ ሳሙኤል 28:6 ላይ ሳዖል ወደ መናፍስጥ ጠሪዋ ሄዶ እንዲጠይቅ ያሰበበት ምንን ያሳያል? ሀ) እግዚአብሔርን መታዘዙን ለ) እምነቱ መጎደሉንና የእግዚአብሔርን መመሪያ መፈለግ ማቆሙን ሐ) የሕዝቡን ፍላጎት ማሟላቱን መ) የወደፊቱን ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት እንዳለው 2.1ኛ ሳሙኤል 29:3 ላይ ንጉሥ አኪስ (አንኩስ) ዳዊት ላይ "ምንም አልተገኘበትም" (አላገኘሁበትም) ያለው ለምንድን ነው? ሀ) ዳዊት ከእርሱ ጋር በነበረበት ጊዜ ሁሉ በታማኝነትና በጥሩ ጠባይ ስላገለገለው ለ) ዳዊት ብዙ ስጦታዎችን ስለሰጠው ሐ) ዳዊት የፊልስጥኤማውያን ሰላይ ስለነበር መ) ዳዊት በጣም ደካማ ስለነበር 3. 1ኛ ሳሙኤል 30:6 ላይ ሕዝቡ ልጆቻቸው በመወሰዳቸው ምክንያት ሊወግሩት ሲሉ የዳዊት ምላሽ ምን ነበር?ሀ) ከሕዝቡ ጋር መከራከርና መጣላት ጀመረ ለ) በጠላቶቹ ላይ ወዲያውኑ ጦር አወጀ ሐ) በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ (በረታ) መ) ተስፋ በመቁረጥ ማልቀስ ብቻ ነበር 4. በመጽሐፈ ሳሙኤል "እንደ ዱር ሚዳቆ ፈጣን" ታይቶ የተጠቀሰው ሰው ስም ማን ይባላል? ሀ) ሳዖል ለ) አሳኤል ሐ) ዮናታን መ) አበኔር 5.ሊቀ ካህናቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ይጠቀምበት የነበረው "ኡሪም" የሚለው ቃል ትርጉም ምንድን ነው? ሀ) እውነት እና ፍርድ ለ) የከበረ ዕንቁ ሐ) ቅዱስ ዘይት መ) ብርሃናት 6. ከሳዖል ሞት በኋላ የሳዖልን ቤትና የእስራኤልን ሠራዊት ይመራ የነበረው ማነው? ሀ) ኢዮአብ ለ) ሜምቦሴቴ ሐ) አበኔር መ) ሰሎሞን 7. ሳዖልንና ልጆቹን ከቤተ-ሳን ቅጥር አውርደው የቀበሩት የየት አካባቢ (ከተማ) ሰዎች ናቸው? ሀ) የኬብሮን ሰዎች ለ) የኢያቤስ ገለአድ ሰዎች ሐ) የቤተልሔም ሰዎች መ) የኢየሩሳሌም ሰዎች 8. 2ኛ ሳሙኤል 2:4 ላይ ዳዊት ለመጀመሪያ ጊዜ የይሁዳ ቤት ንጉሥ ሆኖ የተቀባው በየትኛው ከተማ ነው? ሀ) ኢየሩሳሌም ለ) ኬብሮን ሐ) ቤተልሔም መ) ሰማሪያ 9. 2ኛ ሳሙኤል 3:27 ላይ የሳዖል የጦር አዛዥ የነበረው አበኔር በኢዮአብ እጅ ተንኮል የተገደለው የትኛው ከተማ በር ላይ ነው? ሀ) በኬብሮን ለ) በኢየሩሳሌም ሐ) በጌቴ መ) በሴሎ 10. ከዛሬው ቃል ምን ተማራችሁ? Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
በመቀጠል ሁላችንም በጉጉት ወደምንጠብቀው እና ወደሚያሸልመው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ነው የምንሄደው 🤩 የጨዋታው ህጎች 1) መቼም ቢሆን የምትልኩትን መልስ Edit ማድረግ በፍጹም አይቻልም።🙅🏻 2)መልሳችሁን የምትልኩት @aastuecsfcontact ላይ ብቻ ሲሆን ከዚያ ውጪ Group ላይም ሆነ በሌላ ስፍራ መላክ ከጨዋታው ውጪ ያደርጋል። 3)Time Up ከተባለ በኋላ መልስ መላክ ዋጋ የለውም። 4) ተስፋ በመቁረጥ አለመሞከር አይቻልም።😁 5) ያላችሁ 15 ደቂቃ ብቻ ነው መልካም እድል 🙌🏻 መስማማታቹን በReaction ካላሳወቃቹን ጥያቄውን አንለቀውም 😁 Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
ቦርኬት ጌታ ይባርክህ ከዚህ በላይ የቃሉን ፍቺ ጌታ ያብራልህ። 🙏🙏🙏
#Sermon Borket Beyene 4th Year Electromechanical Engineering
#Sermon 📖 ከጌታ ቃል የምንማርበት ጊዜ ስለሆነ ለመማር በተዘጋጀ ልብ ሆነን ከቃሉ እንማራለን። 🙏
#የመባ_ጊዜ 💰 አሁን ደግሞ ለህብረታችን አገልግሎት የሚውል የምንችለውን ያህል መባችንን እና የፍቅር ስጦታችንን በልግስና ደስ እያለን የምንሰጥ ይሆናል። 🙏🙏 Click to Copy👇👇👇 CBE 1000656422959 Daniel Kebede and/or Samuel Tesfaye Telebirr: 0931106178 Daniel Kebede Telegram | YouTube | Instagram | TikTok | CounselingBot | I4UBot
#Card_Number 89055663798033 -ቀድሞ የሞላ ሰዉ group ላይ Screenshot ይላክልን, መልካም እድል!!😊 Telegram | YouTube | Instagram | TikTok
#card_Gift አሁን የስጦታ ሰዓታችን ደርሷል🥳 -ስጦታችን የሚሆነው Card ሲሆን አሁን የምንለቅላችሁ ይሆናል:: ስለዚህ አሸናፊው የሚሆነው ቀድሞ ቁጥሩን ቀድሞ የሞላ ነው። መልካም እድል! Telegram | YouTube | Instagram | TikTok
Voice message
#worship Nathnael ayele 3rd year Arc
አሁን ደግሞ በዝማሬ ጌታችንን እናመልካለን።
ማሂ ተባረኪልን! እስቲ እግዚአብሔር ይባርክሽ እንበላት🙏🤚
#prayer Mahder Samson 4th year Software Prayers team