ጉባኤ ሐዋርያት
Статистикаእንኳን ወደ ጉባኤ ሐዋርያት በደህና መጣችሁ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት "ሐዋርያት በሰበሰቧት ከሁሉ በላይ በምትሆን በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን" "....እግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ፤” — ቆላስይስ 2፥2
- Последний пост
- 23 сент. 2025 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ቅዱስ እግዚአብሔርን እንኳን ለመታየት አይደለም በአንደበቱ ቢናገር የእውቀቱና የጥበቡን ልክ ማንም ሊደርስበትና ሊረዳው አይችልም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት ቆሞ መከራከር የሚችል አንድም ጻድቅ የለም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገር “ ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን ይችላል? ከእርሱ ጋር ይከራከር ዘንድ ቢወድድ፥ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም።” ተብሎ ተጽፏል።(ኢዮብ 9፥2) ከጌታ ፊት ቆመህ ልትከራከር አትችልም፤ ምክንያቱም እርሱ ከሁሉ በላይ የሆነ ጌታ ነው የተናገረውን የእውቀቱን እና የጥበቡን ልክ ተረድተህ ልትናገር አትችልም ሰማያትን ባጸኑ አንደበቶቹ ቢያናግርህ ችለህ እንዴት ልትመልስ ትችላለህ ወዳጄ? ለጻድቁ ኢዮብ በዐውሎ ነፋስ እግዚአብሔር ተገልጦ ከምደር መሠረት እስከ ሰማይ መስተዋት ከላይ ከአርያም እስከ ታች ገሃነም ጥያቄን ቢጠይቀው "እኔ ወራዳ ሰው ነኝ የምመልስልህ ምንድር ነው? እጄን በአፌ እጭናለው" ብሎ ጻድቁ ተናግሯል፤(ኢዮብ 40፥4) እግዚአብሔር እንኳን መልኩ ቃሉም አይደፈርም እርሱ ኀያል ነው። ጉባኤ ሐዋርያት " መልካም ቀን።
“እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ #የቁርበትን #ልብስ አደረገላቸው፥ #አለበሳቸውም።” — ዘፍጥረት 3፥21 “እግዚአብሔርም እርሱን አለው፦ እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል። እግዚአብሔርም #ቃየንን #ያገኘው ሁሉ #እንዳይገድለው #ምልክት #አደረገለት።” — ዘፍጥረት 4፥15 “እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ #ምድርን #ዳግመኛ ስለ ሰው #አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት #ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና #አልመታም።” — ዘፍጥረት 8፥21 እግዚአብሔር ሁልጊዜ መልካም ነው። ሠናይ ሰንበተ ክርስቲያን ይሁንልን🙏
ጌታ ከጠላት ጋር ስንታገል እንደሚመለከተን ዘወትር ልናስታውስ ይገባል፤ ስለዚህም ከቶ ልንፈራ አይገባንም። ሲኦል ሁሉ በላያችን ቢወድቅ እንኳ ጽኑዓን ልንሆን ይገባል።" የአቶሱ ቅዱስ ሲልዋን እንደ ተናገረው።
ነገር ግን 'ቃልም ሥጋ ሆነ' [ዮሐ. 1:14] የሚለው ኃይለ ቃል፣ እርሱ እንደኛ ሥጋና ደምን ከመካፈሉ በቀር ሌላ ትርጉም ሊኖረው አይችልም፤ ሥጋችንን ገንዘቡ አደረገ፤ ከሴትም ሰው ሆኖ ተወለደ። ይህን ሲያደርግ አምላክ ሆኖ መኖሩን ወይም ከአብ መወለዱን አልተወም፤ ነገር ግን ሥጋን ለራሱ በወሰደ ጊዜ እንኳ የነበረውን ሳይለቅ እንደሆነ ጸንቷል። ይህንን በየትኛውም ስፍራ የቀናች ሃይማኖት አዋጅ ያስተምራል። ይህ የቅዱሳን አባቶች እምነት ነበር፤ በዚህም ምክንያት ቅድስት ድንግልን 'ወላዲተ አምላክ' ብለው ለመጥራት ደፍረዋል። ይህን ያሉት የቃል ባሕርይው ወይም መለኮቱ ከቅድስት ድንግል ተጀመረ ለማለት ያህል አይደለም፤ ነገር ግን ከእርሷ ያ ቅዱስ ሥጋ ከለባዊት ነፍስ ጋር ስለተወለደና ቃልም በአካል ከእርሱ ጋር ስለተዋሐደ እንደ ሥጋ ተወለደ ይባላል። ─────────────── ለንስጥሮስ ከተጻፈው የመጀመሪያ ደብዳቤ [በ430 ዓ.ም.])
ነፍስ በዓመፅ ስትኖር፣ ያ ሞቷ ነው፤ እንደገናም ጻድቅ ስትሆን፣ ራሷ ካልሆነው የሌላ ሕይወት ተካፋይ ትሆናለች፤ ይህም ወደ እግዚአብሔር በመቅረብና ከእርሱ ጋር በመጣበቅ ከእርሱ ዘንድ ትጸድቃለች። እንዲህ ተብሏልና፦ “ለዚያም ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።” (ሮሜ 4:5)። እግዚአብሔርን በመተው ዓመጸኛ ትሆናለች፤ ወደ እርሱ በመምጣት ጻድቅ ትሆናለች። ይህ ነገር፣ ወደ እሳት ሲቀርብ የሚሞቅ፣ ከእሳት ሲርቅ ደግሞ የሚቀዘቅዝ የቀዘቀዘ ነገር አይመስላችሁምን? ወደ ብርሃን ሲቀርብ የሚበራ፣ ከብርሃን ሲርቅ ደግሞ የሚጨልም ጨለማ ነገር? ነፍስ እንዲህ ያለች ነገር ናት፤ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም። ቅዱስ አውግስጢኖስ- "Tractates 19:11 on the Gospel of (John 5:19-21) መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🙏
“አንተሰ አንተ ክመ ወዓመቲከኒ ዘኢየኀልቅ" «አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።» — መዝሙር 102፥27 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 ቸርነቱን ለሚታመኑበት እንደ ሰማይ ጠል ያዘንብላቸዋል ምህረቱ ለዘለዓለም ናት በእርሱ ባይሆን ኖሮ አንዷም ምሽት አታልፍም ነበር ይህች ቀን የቀናት መለዋወጥ ሳትሆን የምሕረቱ ባለጠግነት ውጤት ብቻ ናት ዛሬን በምህረቱ ያሳየን አምላክ በማይመጥኑት ቃላት እናመሰግነዋለን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገንልን። እንኳን ለ2018 ዐዲስ ዐመት በሰላም አደረሰን 🙏
“ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።” — ራእይ 1፥8
እኛስ ኃጢአታችንን ለማስተስረይ በሥጋ እንደ ታመመ እንደ ሞተ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደ ገነዙ ከሙታንም ተለይቶ በእውነት እንደ ተነሣ ከተነሣም በኋላ በእውነት እንደ በላ ወደ ሰማይም እንደ ዐረገ እናምናለን። ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም-ሃይ አበው 52:11 @Apostolic_Council
ክርስትና በሰብእ (በሰው) ቢመሰል ልቡ እና እስትንፋሱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ነው በህልውና የመኖሩ ልኬት ትንፋሹ ነውና የክርስትናም ሕልውና ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! ውድቀተ ዓለምን ለመሻርና ለመደምሰስ በአካላዊ ልብ ኄር (ቸር) በሚሆን አብ የተወጠነው የድኅነተ ዓለም ውጥን በአካላዊ ቃል ወልደ አብ ተፈጸመ ይኸውም የዕብራውያን ጸሐፊ ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን ያለው ነው ይህም መልእክት ማሕየዊ [3] (ሕይወት ሰጪ) የሚሆን መንፈስ ቅዱስ ለዓለሙ ሁሉ ሲገልጠው ይኖራል የእግዚአብሔር ጥበብ ክርስቶስ የሚብራራው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና።[4] የእግዚአብሔር የመጨረሻው መልእክቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለዚህም ነው ታላቅ መደነቅ ይገባል የምንለው። ከቀደመ ጽሑፋችን (ከራድዮን) የተወሰደ።
ከኪሩቤል ወይም ከሱራፌል አንዳች ነገር ለመማር ብትፈልግ፥ የቅድስናውን ምሥጢራዊ ዝማሬ ትሰማለህ፤ እንዲሁም ሰማይና ምድር በክብሩ መሞላታቸውን [ትሰማለህ]። ከፍ ያሉትን ኃይላት ብትመረምርም፥ ብቸኛ ተግባራቸው እግዚአብሔርን ማመስገን መሆኑን ብቻ ታገኛለህ። ───────────────── 𝐉𝐨𝐡𝐧 𝐂𝐡𝐫𝐲𝐬𝐨𝐬𝐭𝐨𝐦, 𝐇𝐨𝐦𝐢𝐥𝐢𝐞𝐬 𝐨𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐆𝐨𝐬𝐩𝐞𝐥 𝐨𝐟 𝐉𝐨𝐡𝐧 15.1 (𝐍𝐏𝐍𝐅1, 14) መልካም ሰንበተ ክርስቲያን ይሁንልን 🙏
« ዳርቻ የለህም፣ ፍጻሜም ይለህም፣ ያገኘህ የለም፣ የሚያገኝህም የለም።የሚያውቅህ የለም አንተን ማየት የሚችል የለም ራስህን አንተ ታውቃለህ። መንግሥትህ አያልቅም ኃይልህም አይሻርም ገናንነትህም አይጨረስም ጌትነትህ አይሠወርም፤ አንተ ከሁሉ የተሠወርህ ነህ፣ ላንተ ግን ሁሉ የተገለጠ ነው፤ጥንት የለህም አንተ ግን ለሁሉ ፍጻሜን ትሰጣለህ። ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቍ 4-6 መልካም ቀን🙏
“እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።” — ዕብራውያን 4፥13 አንድ ጊዜ ላይ፣ ሶርያዊው ኤፍሬም መንገድ ላይ ሳለ አንዲት ዝሙት አዳሪ ሴት፣ ወደ አሳፋሪ ግብር ባትመራው እንኳ፣ ቢያንስ ለማስቆጣት በማባበያ ቃላቶቿ ሞከረች። ምክንያቱም ማንም ሰው ተቆጥቶ አይቶት አያውቅም ነበርና። እርሱም «ተከተይኝ» አላት። እጅግ በሕዝብ የተጨናነቀ ቦታ ሲደርሱ፣ «በዚህ ቦታ፣ ነይ፣ የምትፈልጊውን አድርጊ» አላት። እርሷ ግን ሕዝቡን አይታ፣ «ሳናፍር፣ እንዲህ ባለ ብዙ ሕዝብ ፊት የምንፈልገውን እንዴት ማድረግ እንችላለን?» አለችው። እርሱም መለሰላት፦ «አንቺ በሰው ፊት የምታፍሪ ከሆነ፣ በጨለማ የተሰወረውን ከሚያውቅ ከእግዚአብሔር ፊትማ እንዴት አብልጠን አናፍርም?» እርሷም በኀፍረት ተሸፍና፣ ምንም ሳታገኝ ሄደች። ──────────────── 𝐹𝑟𝑜𝑚 "𝑇ℎ𝑒 𝑆𝑎𝑦𝑖𝑛𝑔 𝑜𝑓 𝐷𝑒𝑠𝑒𝑟𝑡 𝐹𝑎𝑡ℎ𝑒𝑟𝑠" 𝑃𝑎𝑔𝑒 59-60.
የሰንበተ ክርስቲያን ጥዑም ምንባብ፦ "በእንተ መንፈስ ቅዱስ ዘእም ቃለ ባስልዮስ ኤጴስ ቆጶሳት ዘቂሣርያ" በሁሉ ምሉዕ የሆነ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ። ወዳጆቼ ሆይ ማኅየዊ የሚሆን የመንፈስ ቅዱስን ግብር አስተውሉ፤ እርሱ ዓሣ አሥጋሪ የነበረ ዮሐንስን ከፍጥረት አስቀድማ ስለ ነበረች የመለኮት ምሥጢር የሚናገር ነባቤ መለኮት አደረገው። ቀራጭ የነበረ ማቴዎስን ቢያምንበት ወንጌልን የሚጽፍ አደረገው። ቤተክርስቲያንን የሚያሳድድ የነበረ ጳውሎስ ቢያምንበት ዓለምን በወንጌል ያበራ ብርሃነ ዓለም፣ ንዋየ-ኅሩይ(ምርጥ ዕቃ) አደረገው። መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሰጪ ቸር ነውና እርሱ ሲያድርባቸው የደከሙ በቅፅበት ጽኑዓን ይሆናሉ፤ ዐላዋቆች ከጠቢባን የሚልቁ ጠቢባን ይሆናሉ። ተመልከቱ፤ ጳውሎስ እኮ ታማሚ ነበር ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ሲያድርበት በለበሳቸው ልብሶች ለድውያን ፈውስን የሚሰጥ ሆነ፤ ጴጥሮስም ሰውነቱን ታማሚ ነበር ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ባደረበት ጊዜ በመንገድ ሲያልፍ በጥላው ድውያን ይድናሉ። ዮሐንስና ጴጥሮስ ድሆች ነበሩ ብርና ወርቅም አልነበራቸውም ሰውንም ያከብራሉ ከብርና ከወርቅ የምትበልጥ ጤናን ይሰጧቸው ነበር። "በሁሉ ምሉዕ የሆነ አምላክ ፈጣሬ ዓለማት መንፈስ ቅዱስ እንደ መልእክተኛ ታዝዞ ጸጋን የሚሰጥ አይደለም እርሱ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና እንደ ፈቃዱ ጸጋን ይሰጣል እንደ ወደደ ለሁሉ ክብሩን ያድላል በምልዓት በሁሉ ያድራል ጸጋንም ይሰጣል ጸንቶም ይኖራል፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አምናለሁ እታመናለሁም። አሜን። ─────────────── ማስታወሻ፦ ሐሳቡ የተወሰደው ከሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ባስልዮስ ከገጽ 113-114 ቁጥር 34 ጀምሮ ከጥቂት ቃላት ለውጥ ጋር ቀርቧል። መልካም ዕለት ሰንበት ይሁንልን🙏
የማለዳ ምንባብ ሠራዒዬ ቀራፂዬ፣ አምላኬ ሆይ! በሥራ የማልፈጽመውን ነገር የምናገር እንደሆነ፣ ያኔ በከንቱ ከሚያስተጋባው የናስ ጸናጽል የተለየ አይደለሁም (1ኛ ቆሮ. 13:1)፤ የራሴንም የጩኸት ድምፅ የማልሰማ ሆንሁ። አቤቱ፣ ከፊትህ አታርቀኝ፤ አትተውኝም፤ ለመሰናከልም አትዳርገኝ፣ መድኃኒቴ ሆይ። እኔስ ጎስቋላ፣ ድሃና መጻተኛ ነኝና፤ ለአንተም አእላፍ መክሊት ዕዳ ያለብኝ (ማቴ. 18:24)። ነገር ግን [አካላዊ] ቃል ሆይ፣ አሁንም እንደ ቀደመው ቸርነትህ አድርግልኝ! ────────────── 𝗗𝗶𝘃𝗶𝗻𝗲 𝗘𝗿𝗼𝘀 𝑯𝒀𝑴𝑵𝑺 𝑶𝑭 𝑺𝑻 𝑺𝒀𝑴𝑬𝑶𝑵 𝑻𝑯𝑬 𝑵𝑬𝑾 𝑻𝑯𝑬𝑶𝑳𝑶𝑮𝑰𝑨𝑵፦𝐇𝐲𝐦𝐧 2:30
በስካር የተራቈተውን የኖኅን ኀፍረት እንደ ሸፈኑት ወንድማማቾች፤ በክቡር ሥጋው (ሸማ) በዐመጻ የወደቀውን ኀፍረታችንን ሸፈነ፤ እርሱ ግን እንደ ሴም የኋሊት ሊሄድ አልወደደም፤ ሥጋችንን ሳያፍረው የገዛ ገንዘቡ አደረገው በትሕትና ወርዶ የዲያቢሎስ መዘባበቻ የነበርነውን እኛን የክብሩ ነዋያተ ቅድሳት ሊያደርገን ፈቀደ። መፍቀሬ-ሰብእ (ሰውን የወደድክ) ክርስቶስ ሆይ ከጸሐይ መውጪያ እስከ መግቢያዋ ድረስ አኰቴት ላንተ ይገባሃል።
«ፍጹም ሰው» ...ከማርያም አንዳች ነገር ያልነሣ ቢሆን ኖሮ፣ ከምድር የተገኘውን ሥጋ የሚመግቡትን ከምድር የሚገኙ ምግቦችን ከቶ ባልተጠቀመም ነበር። እንደዚሁም ሥጋው የራሱን ምግብ ካልተራበ በቀር፣ እንደ ሙሴና ኤልያስ እነዚያን አርባ ቀናት ጹሞ ባልተራበ ነበር። ደግሞም ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ስለ እርሱ ሲመሰክር፣ “ኢየሱስም ከድካሙ የተነሣ በጉድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ” (ዮሐንስ 4:6) ባላለም ነበር። ዳዊትም አስቀድሞ ስለ እርሱ፣ “በቍስሌ ላይ ኀዘንን ጨመሩ” ብሎ ትንቢት ባልተናገረም ነበር። በአልዓዛርም ላይ ባላለቀሰ፣ ታላቅ የደም ወዝም ባላጠበው ነበር። “ነፍሴ እጅግ አዘነች” (ማቴዎስ 26:38) ባላለም ነበር። ጎኑም በተወጋ ጊዜ ደምና ውኃ ባልፈሰሰም ነበር። ቅዱስ ሄሬኔዎስ። St. Irenaeus, Against Heresies, 3.22.1 መልካም ምሽት🙏
ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፦ምንት ውእቱ ንዴት ዘይከውን ቅድመ እግዚአብሔር ፈድፋደ ፡ ሥጋን ከመዋሐድ በቀር የበለጠ በእግዚአብሔር ዘንድ ምን ድኅነት አለ? እውነት ነው። ──────────────── ምልዐት ውስንነትን ሥፋት ጥበትን ርቀት ግዝፈትን ነደ እሳት ሥጋዊ ደማዊ መሆንን የማይታይ መታየትን የማይዳሰስ መዳሰስን ከመፍቀድ በላይስ ምን አስፈሪ ትሕትና አለ። ለአዳም ሰማይን እንደ ጣራ የወጠረ ጸሐይን እና ጨረቃይ ለአዝማናት ያደረገው ሺህ ዓመት በዐይኑ ፊት እንደ ቀን ለሚያልፍ ለእርሱ በጊዜ ውስጥ ከመግባቱ በላይ ምን መዋረድ አለ። ዐይኖቹ ሳይከደኑ ሕዝቡን የሚጠብቅ ክንዶቹ ሳይታጠፉ የሚሸከም ድካም የማያውቀው እርሱስ ደከመኝ ተጠማሁ ከማለቱ በላይ ፍቅር የት አያለሁ? "ፍቅርስ እንደዚህ ብቻ ነው" እንኳን የውሉዳነ አዳም" የሥጋ ለባሽ እና የነፍሳት ሁሉ አባትና መጋቤ-ዓለማት ሲራብና ሲጠማ ሰማይን ዘርግቶ ምድርን ወለል አድርጎ ለፍጥረት መኖሪያ ያደረገው ሀብታሙ ጌታ ደሀ ሲሆን፣ ነገሥታት እየተንቀጠቀጡ የሚገዙለት ከማይታወቁ ከደሀ ቤተሰብ ያለ ወንድ ዘር ሲወለድ "ከዚህ የሚበልጥስ ፍቅር ለማንም የለውም" እውነት ነው ለእግዚአብሔርማ ሰው ከመሆን በላይ ድህነት ሌላ ምንም የለውም። ይህንን አስቤ ለምን ስል.. ምክንያት በሌላት ንጽሕት ፍቅር መወደድ ብቻ ነው አለቀ።ቅዱስ ሕርያቆስ ፍቅር ኀያል ወልድን ከመንበሩ ሳበው ከዙፋኑም አወረደው እስከሞትም አደረሰው ይል የለምን? ትሑት ነው የትሑታን ሁሉ አባት። ኢየሱስ በደህነቱ ውስጥ ያጣነውን የነፍስ ባለጠግነትን ከስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ በመሄዱ ውስጥ የሞላብን ቅብዝብዝነትን አስወገደ። በጽምዐቱ የደረቀችውን ነፍሳችንን አረካት በረሀቡ እርሱን በማጣት የተራበችውን ልቡናችንን አጠገባት በዕጽ የወደቀውን ፍጥረተ ዓለም በዕጽ ተሰቅሎባት ዓለምን ሁሉ አዳነባት። በጉልበቱ ሳይሆን ደካማ ሆኖ እየተጨነቀ እያለቀሰ ጌታዬ ለዓለም ሁሉ መስፍነ-መሳፍንት ሆነባት። እንደዚህ ያለ ጀግና ከየት ይገኛል? እንደዚህ ነው እግዚአብሔር ያዳነን እንዲህስ ለምን ቢሉ "ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ" ይል የለምን??። ምድርን እንደ ብራና ተወጥራ ባሕሯን ቀለም አድርጌ ቃላትን ከመዛግብትና ከጠቢባን ልሳን እየተዋስኩ ስለዚህ አዳኝ ብጽፍ የከንቱ ከንቱ ነው... ስለወደደን ብቻ አዳነን ስሙ ይመስገን።
አባ እንጦንስ እንዲህ አለ፦ ‘ጠላት በዓለም ላይ የሚዘረጋቸውን ወጥመዶች አየሁ እናም እያቃሰትኩ እንዲህ አልኩ፦ “ከእንዲህ ካሉ ወጥመዶች ማምለጥ የሚችለው ምንድን ነው?” ከዚያም አንድ ድምፅ እንዲህ ሲለኝ ሰማሁ፦ “ትሕትና።”’ 𝐴𝑁𝑇𝐻𝑂𝑁𝑌 𝑇𝐻𝐸 𝐺𝑅𝐸𝐴𝑇 𝐹𝑟𝑜𝑚 "𝑇ℎ𝑒 𝑆𝑎𝑦𝑖𝑛𝑔 𝑜𝑓 𝐷𝑒𝑠𝑒𝑟𝑡 𝐹𝑎𝑡ℎ𝑒𝑟𝑠" 𝑃𝑎𝑔𝑒 1:7 ──────────────── መልካም ምሽት 🙏
ለመማር ቅንዓትን የሚያነሳሳው ቀዳሚው ነገር የመምህሩ ታላቅነት ነው። ከወላዲተ አምላክ (ከእግዚአብሔር እናት) ማን ይበልጣል? ክብር ራሱ ከመረጣት በላይ ክብርት ማን ናት? ከሌላ ሥጋ ጋር ንክኪ ሳይኖራት ሥጋን ከወለደችው በላይ ንጽሕት ማን ናት? ሌላ በጎ ምግባሯንስ ለምን አነሳለሁ? እርስዋ በሥጋዋ ብቻ ሳይሆን በልቦናዋም ጭምር ድንግል ነበረች። ምንም ሽንገላ ቅንነቷን አላጎደፈውም። በልቧ ትሑት፣ በንግግሯ ቁም ነገረኛ፣ በአእምሮዋ ልባም፣ ቃላትን የምትቆጥብ፣ በማንበብም ትጉህ ነበረች። ተስፋዋን ያደረገችው በሀብት ላይ ሳይሆን በድሆች ጸሎት ላይ ነበር። በዓይኖቿ ምንም የተኮሳተረ ነገር፣ በቃላቷ ቅጥ ያጣ ነገር፣ በድርጊቷም ክብር የጎደለው ነገር አልነበረም። የሞኝነት እንቅስቃሴም ሆነ ያልተገታ እርምጃ አልነበራትም። በፍጹም የምትበሳጭ አልነበረችም። በዚህ መንገድ ውጫዊ ገጽታዋ ራሱ የነፍሷ መገለጫ፣ የተወደደውንም ነገር የሚያሳይ ሆነ። በሥርዓት የተደራጀን ቤት ገና በደጃፉ ላይ ሆነን ልናውቀው ይገባናል፤ ገና ከመግባታችን በውስጡ የተደበቀ ጨለማ እንደሌለበት ሊያሳይ ይገባል። በተመሳሳይ መልኩ ነፍሳችን፣ በምንም ዓይነት ሥጋዊ እገዳዎች ሳትገደብ፣ በውስጥ እንደተቀመጠ መብራት ልታበራ ይገባል። –St. Ambrose of Milan, Three Books on Virgins, 2.7 ቅዱስ አምብሮስ 339-397
ስለ አንተ ይህንን ሁሉ ከሰማሁ በኋላ፣ ከሁለት ነገሮች አንዱ እውነት መሆን አለበት ወደሚል ድምዳሜ ደርሻለሁ፦ ወይ አንተ ከሰማይ የወረድክ አምላክ ሆነህ ይህንን ታደርጋለህ፤ ወይም ደግሞ ይህንን የምታደርገው አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ። ስለዚህ፣ ችግሩን ተቀብለህ ወደ እኔ መጥተህ ያለብኝን ደዌ እንድትፈውስልኝ ልጠይቅህ ይህንን ጻፍኩልህ። ምክንያቱም አይሁድ በአንተ ላይ እንደሚያጉረመርሙና ሊጎዱህም እያሴሩ እንደሆነ ሰምቻለሁ። "ወደ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ከተላከው የንጉሥ አብጋር ደብዳቤ"