Orthodox Patristic Writings
Статистикаhttps://t.me/panorientalorthodox6 የቻናላችን ሀሳብ የመስጫ እና የመወያያ ግሩፕ ይህ ነው።
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 556
- 1/48двое суток
- 637
- 1/72трое суток
- 687
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Oriental Orthodox Unveiled (1).pdf
без подписи
без подписи
https://youtu.be/Oh2wexpc_No?si=NndFOB_j0LC9ZgO_
https://youtu.be/Oh2wexpc_No?si=NndFOB_j0LC9ZgO_
без подписи
አቤል ይባላል የግቢ ጉባኤያችን አባልና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው። አሁን ግን እንደምትመለከቱት አደጋ አጋጥሞት የእኛን እርዳታ ይፈልጋልና የምንችለውን ያህል ከላይ በተጠቀሱት አካውንቶች በመላክ እናግዘው። ማጋራትም እርዳታ ነውና ይህን ፖስት ለምናውቃቸው ሰዎች በማድረስ እነርሱም እንዲያግዙ እናድርግ
በቃ እያነበባችሁ ተኙ😁 የተዋሕዶ አርበኛ ቅዱስ ሳዊሮስ ምልጃ ይርዳን
ማጣቀሻዎች 1.St.Peter Of Iberia (በቅብጦች ስንክሳር ኪያኽ 1(በእኛ ታህሣሥ 1) ላይ ኣል-ሮሀዊያ( ኤል-ራሀ) ተብሎ ሲጠራ የተወለደባትን አካባቢ ለመጥቀስ የተወሰደ ቃል ነው። ግእዙም ከአረበኛው ጋር በመወራረስ ይመስላል ሮሀዊ ያለው። 2.Letter 6፡Against Those who say that men converts from Diphysitism should be re-anointed 3.ዝኒ ከማሁ 4.ዝኒ ከማሁ 5.ዝኒ ከማሁ 6.ቅዱስ ሳዊሮስ ምንፍቅናን እና በሽታን በአንጻራዊነት ነው የሚያስቀምጣቸው ምንአልባትም ከዮልያኖስ ምንፍቅና በተነሳ ይመስላል። የኬልቄዶንንም ጉባኤ የቤተክርስቲያን በሽታ ይለዋል፣ጌታ በምድር እያለ ከትንሣኤው በፊት እንከን-አልባ ህመሞች (Blameless Passion) እንደነበረው ኹሉ፣ለቅዱስ ሳዊሮስም ቤተክርስቲያን በምንፍቅና እንዲህ ያሉ ህመሞች አሉባት ይህንን ቅዱስ ሳዊሮስን ያጠናው Yonatan Moss እንዳህ ይገልጠዋል "በሌላ በኩል፣ የኬልቄዶንን ጉባኤ ላልተቀበለው (Anti-Chalcedonian) ለሳዊሮስ፣ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ሆና ባለችበት ሁኔታ እንኳ፣ የተወሰነ ደረጃ ሕመም፣ ድክመት ወይም ሙስና (Corruption) ሊገጥማት እንደሚችል ተደርጎ ሊታሰብ ይችላል። እንዲህ ዓይነቱን ሕመም ማከም ማለት ብልቶችን ከአካል ላይ ቆርጦ መጣል ሳይሆን፣ መላውን አካል በአንድነት በመፈወስ አንድነቱንና ሙሉነቱን (Integrity) መጠበቅ ማለት ነው።" In/corruptible Bodies Christology, Society And Authority In Late Antiquit፡Page 48 በአንጻሩ አብዛኛው ተገንጣዮች ዮልዮሳውያን በመኾናቸው ምንአልባት በአንጻረ ዮልዮሳዊነት የተቃኘ የነገረ-ቤተክርስቲያን ይኖራቸው ይኾናልም። 7.Novatus 8.Photinus 9.Paul of Samosata 10.Letter 6፡Against Those who say that men converts forom Diphysitism should be re-anointed 11.Iain R.Torrance፡Christology After Chalcedon፡Severus of Antioch And Sergius The Monophysite፡Page 10 12. Letter 34 13. ዝኒከማሁ 15. ይህ መጠሪያ ሥራቸውን ከሐዋርያት የሚስቡትን እና የጥንቷ ቤተክርስቲያን አካል ነን የሚሉትን የኦሬንታል ኦርቶዶክስ፣የምስራቅ ኦሮቶዶክስ፣የካቶሊክ እና የምስራቅ ሶርያ አብያተክርስቲያንን የሚወክል ነው። 14.የእውነታ(Truth) ዲበ-አካላዊ አረዳድ ስንመለከት ፍጹማዊ እውነት(Ultimately True) ሲኾን ምንም እንከን እና ሀሰት የሌለበት ነው፣እውነት ግን ሀሰት ሊቀላቀልበት ይችላል። 16. Andrew N.A Youssef፡Oriental Orthodox Unveiled፡Page፡78 17.ምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን 18.Andrew N.A Youssef፡Oriental Orthodox Unveiled፡Page 74 19.Diana Tsaghikian፡Grigor Tatevatsi And The Sacraments Of Intiation፡Page 168 20.Pastoral Agreement እንደ Economia of the Church ማለትም በግለሰቦች ብቻ የሚደረግ እና በአስቸጋሪ እና ባልተለመዱ ጊዜያት ለሞት እና ለሌሎች ችግሮች እንደመፍትሔ የቀረበ ስምምነት ሲኾን፣ለምሳሌ አንድ ሶርያዊ ኦርቶዶክስ የካቶሊክ አማኞች ብቻ ያሉበት አገር ቢኼድ እና በጽኑ ቢታመም ካቶሊኮች ጋር የመቁረብ ፍቃድ አለው እንደማለት ነው። ይህ ግን ግለሰባዊ ነው። 21.H.H.Paulos Mar Gregorios፡Eucharistic Hospitality. @pan_oriental_orthodox6
ከዚህ የምንረዳው በቤተክርስቲያን በኅብረት እንጂ በግል የሚወሰን መተዳደሪያ ቀኖና የለም ቅዱስ ሳዊሮስ ከቀደሙት እና ከእርሱ ዘመነኛ ከነበረው ከቅዱስ ጴጥሮስ ሮሀዊ ጋር የነበረው ሀሳብ አንድ ነበር፣ለዚህ ምሳሌ በሁለቱም ደብዳቤዎቹ በ6 ኛው ደብዳቤው እና በ34 ኛ ደብዳቤ ኬልቄዶንን በመቃወም ከሚቀድመው ከቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእስክንድርያ ጋር ተመሳሳይ አቋም ማራመዱ ነው። በእርግጥ ቅዱስ ጴጥሮስ ሮሀዊን ባይጠቅሰውም፣ቅዱስ ጴጥሮስ ሮሀዊም ቢሆን ከቅዱስ ሳዊሮስ ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ የሚያራምድ አባት ነው። ቅዱስ ጢሞቴዎስ ከኬልቄዶን ለሚመለሱ ሰዎች ዳግም-ጥምቀት ኾነ ዳግም-ቅብአተ ሜሮን አለመፈጸሙን፣ነገርግን ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ የኬልቄዶንን አንቀጸ-ሃይማኖት በመካድ (By Confession) ወደ ኅብረት እንደሚመለሱ እንዲሁም በፕሮቶርዮስ ኬልቄዶናዊ ክህነትን የተሾሙ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመለሱ ዳግም-መካን(Re-ordination) እንደማያስፈልጋቸው ጭምር ቅዱስ ጢሞቴዎስ ያምናል። ቅዱስ ሳዊሮስ ቴዎዶጦሳውያንን የተቃወመበት ምክንያት አዲስ ቀኖና በመፍጠራቸው እና ከቀደሙትን አበው የተለየ አካሄድ በመፍጠራቸው ነበር። የጆፓውን ቴዎዶጦስ ስሁትነት ከማሳየት እና፣በቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ እንደለሌው ከማሳየቱም ባለፈ ቅዱስ ሳዊሮስ "ዳግም ቅብአተ ሜሮንን" እንደ ህገወጥ እና "በራሱ(በቴዎዶጦስ) የተፈጠረ" ትምህርት ነው ይለዋል¹² ከቴዎዶጦሳውያን ጋር እና ከቴዎዶጦስ ክህነት የተቀበሉ ሰዎች ጭምር የንስሀ ቀኖና ይሰጣቸው ዘንድ ሲያዝም እናያለን¹³ ከዚህ የምንረዳው የቴዎዶጦስ ትምህርት ከቤተክርስቲያን ውጪ እና ሰው ሠራሽ መኾኑን እንዲሁም፣ለቤተክርስቲያን አንድነት እጅጉን መሠናክል የኾነ መኾኑን እና ቅዱስ ሳዊሮስ ከቴዎዶጦሳውያን ጋር ጭምር የተዋጋ አርበኛ መኾኑን ነው። የኬልቄዶናውያን ክህነት ወደ ኅብረት ሲመለሱ የሚሠራ እና ከጥምቀታቸው ጋር ህጋዊ ኾኖ ቤተክርስቲያን ጋር እንደሚሠራ አክሎ ይናገራል። ለጥምቀት የንስጥሮሳውያንን ጉዳይ እንዳነሳው ከክህነቱም ጋር ያያይዘዋል። ይህ ማለት ከኬልቄዶናውያን ጋር የምስጢራት ኅብረት አለን ማለት ነው? በፍፁም! ቅዱስ ሳዊሮስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ህመም የማከም ዓላማ ነበረው እንጂ እውነታን ከእውነት እየቀላቀለ አልነበረም። ለዚያም ነው ኬልቄዶናውያን በንስሀ እና ኬልቄዶናዊ አንቀጸ-ሃይማኖትን በመካድ ወደ ቤተክርስቲያን እውነታ(Truthfulness) የመምጣትን እና የማደግን ነገር አጽንቶ ለኬልቄዶናውያን የተናገረው። ለቅዱስ ሳዊሮስ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት፣ ኬልቄዶናውያን የታመሙ የቤተክርስቲያን አካላት አድርጎ ተመልክቷቸዋል፣ የመንፈስቅዱስ መግቦት በሚስጢራቶቻቸው በኩል እንዳለም ያምናል። ለዚያም ነው ወደ እርሱ ሲመጡ በነጻ የሚቀበላቸው። ስለዚህም ነው ቅዱስ ሳዊሮስ ለቤተክርስቲያን አንድነት የተጋ እና ለቤተክርስቲያን የተሰጠውን እውነታ(Truth)¹⁴ ባለመቀላቀል ረገድ የአብያተክርስቲያናት የእርስ በእርስ ግንኙነት (Ecumenical dialogue) ላይ መሠረት የጣለ አባት ነው ልንል የምንችለው። አንድም ቤተክርስቲያናችን አሁን ከሐዋርያውያን አብያተክርስቲያናት (Apostolic Churches)¹⁵ ጋር የሚኖራት ግንኙነትን የሚገመግም እና የምስጢራቶቻቸውን ህጋዊነት እና ህገወጥነት የሚወስን ኾኖም ይታያል።¹⁶ ከቅዱስ ሳዊሮስ በኋላ ያለውን ጉዳይ ስናይ በመካከለኛው የኮፕት ቀኖናዎች ላይ የቢዛንታይን ምስራቅ ኬልቄዶናውያን¹⁷ ልክ እንደ ቅዱስ ሳዊሮስ በአንቀጸ ሃይማኖት በኩል የመቀበል ልማድ የነበረ ሲኾን¹⁸ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ታቴቫዊ ስለ ጥምቀት ሲናገር የቅዱስ ሳዊሮስን አካሄድ ቢሄድም ንስጥሮሳውያን ዳግም-ጥምቀት ያስፈልጋቸዋል በሚለው ልዩነት አላቸው። "በሥላሴ ስም ለተጠመቁ ዳግም-ጥምቀት አይደረግም፣ነገርግን አርዮሳውያን፣ መቅዶንዮሳውያን እና ንስጥሮሳውያን የሆኑና የሥላሴን አንድነት የሚክዱ በቅድስት ሥላሴ ስም መጠመቅ አለባቸው።"¹⁹ ነገርግን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ታቴቫዊ ኬልቄዶናውያንን ከዳግም ጥምቀት የሚያስፈልጋቸው አካላት ጋር አለመጨመሩ ግን፣ምንአልባት በወቅቱ የነበረችውን የአርመን ቤተክርስቲያን ስርአት የሚያሳይ ይመስላል። ለዚያውም ቅዱሱ ካቶሊኮችንም፣ቢዛንታይኖችንም የሚያውቅ ኾኖ ሳለ ኬልቄዶናውያንን ከዝርዝሩ ውጪ ማድረጉ የእነርሱን ምስጢረ ጥምቀት ህጋዊነት የሚቀበል ነው ልንል እንችላለን። ከዚህ ባለፈ ግን አሁን ላይ በጥምቀት ባሉ ምስጢራት ላይ ኬልቄዶናውያንን መቀበል ላይ ሳዊሮሳዊ አቋም አለ ለማለት የሚያበቃን አይመስለኝም። ባለንበት ዘመን በሶርያእና ህንድ ማላንካራ አብያተክርስቲያን እና ከካቶሊካውያን ጋር መግቦታዊ ስምምነት (Pastoral Agreement)²⁰ ያደረጉ ሲኾን ይህ ማለት ግን በምልአት የተደረገ የምስጢራት ኅብረት (Full Inter-Church Sacremental Communion) ባይኾንም ነገርግን በግለሰቦች የሚካሄድ በቀኖናዊ ስልጣን የሚካሄድ እንጁ የምስጢራት አካፋይነትን እና መቀበልን የሚያሳይ አይደለም።²¹ ነገርግን በኦርየንታል ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በኬልቄዶናውያን ግንኙነቶች የምስጢራትን እውቅና የመሰጣጠት አንዱ ደረጃ ብለን ልንጠቅሰው እንችላለን። @pan_oriental_orthodox6
የቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንፆኪያ እሳቤ በኬልቄዶናውያን ምስጢራት ላይ፡ ለአሁናዊ የቤተክርስቲያን አንድነት ያለው አበርክቶ ከጉባኤ ኬልቄዶን በኋላ በኢ-ኬልቄዶናውያን መካከል ተገንጣዊነትን እና አዲስ መዋቅር ፈጣሪ የኾኑ (Separatist) በጆፓ ጳጳስ በቴዎዶጦስ የሚመሩ፣በንጉሥ ዜይኑን (Emperor Zeno) ሄኖቲኮን የሚመሩ ሄኖቲካውያን (Henotist) እንዲሁም እንደ ቅዱስ ሳዊሮስ ሁለቱንም የሚያወግዙ በሚል የተፈጠረ ክርክር ነበር፣ቅዱስ ሳዊሮስ ተገንጣዊነትን (Separatism) ደጋፊ አልነበረም ይህ ማለት ግን ኬልቄዶንን ተቀብሏል ማለት አይደለም፣ንጉሥ ዜይኑን ያወጣው ሄኖቲኮን በአንዳንድ ኬልቄዶናውያን ኾነ በኢ-ኬልቄዶናውያን ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ሄኖቲካውያን ጳጳሳት በሁለቱም ዘንድ ፈጥሯል። ለምሳሌ እነ ጴጥሮስ ሞንጎስ(የእስክንድርያ ፓትርያሪክ) ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል። በማዮማ-ጋዛ ጳጳስ በቅዱስ ጴጥሮስ ሮሀዊ¹ እና በተማሪው በቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንፆኪያ ያሉ የተዋሕዶ አርበኛ ግን በምልአት አልተቀበሉትም ነበር ምክንያቱም የንጉሥ ዜይኑን ሄኖቲኮን እውነት ነው "ሁለት ባህርይ"(In Two Natures) የሚል ነገረ-ክርስቶስን ቢያወግዝም እና የኬልቄዶንን ጉባኤ ውሳኔ ቅቡልነት ቢቃወምም በግልጽ(Explicitly) በሆነ መንገድ ጉባኤውን አላወገዘም። በዚህ ምክንያት ቅዱስ ሳዊሮስ ከአባቶቹ ከእነ ቅዱስ ጴጥሮስ ሮሀዊ ጎን ቆሞ እነ ጴጥሮስ ሞንጎስን ተቃውሟል። በዚያው ልክ ግን በኢ-ኬልቄዶናውያን ዘንድ ተገንጣዎች እና ወግ አጥባቂ የሆኑ፣ለአንድነት የማይቀኑ ሰዎች እንደ የጆፓ ጳጳስ ቴዎዶጦስ፣ዮልያኖስ ፈረሳዊ እና ተከታዮቹ እንዲሁም የቴላ ጳጳስ ዮሐንስ፣ኢሳይያስ አርመንያዊ እና ጎርጎርዮስ ዘጳንጦስ ያሉ ሰዎችም ነበሩ። ቅዱስ ሳዊሮስ ሁለቱንም አካላት ተቃውሟል እነ ጴጥሮስ ሞንጎስንም ሆነ ኬልቄዶናውያንን ዳግም ጥምቀት አጥምቀው ከኅብረት የሚጨምሩትንም ሆነ በዳግም-ቅብአተ ሜሮን (Re-Anointing) የሚቀበሉ ኢ-ኬልቄዶናውያንን ተቃውሟል። እነርሱን በሚቃወመው ደብዳቤውም² በቅዱስ ሜሮን ኬልቄዶናውያንን ወደ ኅብረት ማግባትን ኬልቄዶኖውያንን በዚህ መልኩ መቀበል ከመንፈስቅዱስ ፀጋ የተነጠሉ እና ፀጋ መንፈስቅዱስ ያልተቀበሉ ስለሚያስብላቸው፣ የምንከተለው የቀደሙን አበው ባስቀመጡት ነው ይላል፤ይህም ማለት በቀደሙት አበው ዘንድ በቅዱስ ቆጵርያኖስ እና በሮሙ ፖፕ እስጢፋኖስ መካከል የተነሳውን ክርክር ያነሳዋል፣በቅዱስ ቆጵርያኖስ እና በአፍሪካውያን ጉባኤያት የተቀነነው "ከማንኛውም ምንፍቅና የሚመጣ ሰው ምንም አይነት ጥምቀት ካልተጠመቀ፣ በቤተክርስቲያን ጥምቀት ፍጽምናን ማግኘት አለበት" የሚል ቢሆንም የማንኛውም አይነት መናፍቃን እንደሆኑ አለዩም ነገርግን ሁሉንም በአንድ አይነት ተቀጽላ አመጡት እንጂ³ ይህን አቋም የያዙት ግን ለእግዚአብሔር ከመቅናት እና ለእርሱ ካላቸው ፍቅር ነው ይለናል ቅዱስ ሳዊሮስ⁴ ነገርግን በወቅቱ የነበረ ታላቁ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘእስክንድርያ የምንፍቅናዎቹን አይነት እና ቀመረ-ጥምቀቱን (Formula of baptism) ይለያያል ማለትም ጥምቀቱ በስመ-ሥላሴ ከሆነ እና ጥምቀቱ የተፈጸመው በመናፍቃን ቢኾንም እንኳ የሦሥቱን የሥላሴ አካላቶችን የሚያምኑ ከሆነ ድጋሜ አይጠመቁም የሚል መካከለኛ አቋም የቤተክርስቲያን ነው ይለናል ቅዱሱ⁵ የአፍሪካውያን እና የቅዱስ ቆጵርያኖስ አቋም መናፍቃንን በአንድ መገለጫ ቢጠቅሱም በዘመነኛቸው በቅዱስ ዲዮናስዮስ ግን ተለያይቷል ይህን አስመልክቶ ቅዱስ ሳዊሮስ ሲያጠቃልለው እንዲህ ይለናል፦ "በሥጋዊ ሕመም ጊዜ እያንዳንዱ ደካማነት በጥቅሉ በሽታ ተብሎ እንደሚጠራና ይህ አጠቃላይ ስምም እንደ ትኩሳት፣ የሆድ እብጠት እና የዝሆኔ በሽታ (Elephantiasis) ያሉ ብዙ የተለያዩ በሽታዎችን እንደሚያጠቃልል ሁሉ፤ በእምነት ድክመት ረገድም ከጤናማው ቃል (ከቀጥተኛው እምነት) ዘወር ማለት ሁሉ በጥቅሉ ምንፍቅና⁶ ይባላል። ነገር ግን በዚህ ጥቅል ስም ስር የሚካተቱት እያንዳንዱ መንፈሳዊ በሽታዎች ተመሳሳይ ባህርይ የላቸውም፤ በክፋታቸውም (በክህደት ደረጃቸው) እኩል አይደሉም። ነገር ግን፣ አንድ የተዋጣለት ሐኪም ትኩሳት ያለበትን ሰው በአንድ መንገድ፣ ብርድ ብርድ የሚለውን ወይም የሆድ እብጠት ያለበትን ወይም የጣፊያ ክፍል ያበጠበትን ሰው ደግሞ በሌላ መንገድ እንደሚያክም ሁሉ፤ በተመሳሳይ መልኩ አብያተ ክርስቲያናትን ከተራ መንፈሳዊነትና ማስተዋል በላይ በሆነ ጥበብ የመገቡና የፈወሱ አባቶችም የእያንዳንዱን ክህደት ባህርይ መለየት ትክክል እንደሆነ ፈረዱ። በብናጥስ⁷ እና በፎጢኖስ⁸ በሽታ የተያዙትን ሰዎች ለማከም የሚሆን ፈውስ፣ በጳውሎስ ሳምሳጢ⁹ የክህደት ዝቅጠትና ረግረግ ከቆሸሹት ሰዎች ጋር እኩል መሆን የለበትም ብለው አሰቡ። የሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ (የኒቂያ) አባቶች አሥራ ዘጠነኛው ቀኖና ከጳውሎስ ሳምሳጢ ወገን የሚመጡት እንደገና እንዲጠመቁ (Re-Baptized) ያዝዛል፤ ነገር ግን ከፎጢኖስና ከብናጥስ ወገን ወደ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለሚመለሱት ደግሞ በፍርግያ ሎዶቅያ በተሰበሰበው ሲኖዶስ የተደነገገው መቶ አሥረኛው ቀኖና በቅብአ ሜሮን (Chrism) ብቻ ፍጹማን እንዲሆኑ ወሰነ፤ ምንም እንኳን የሳምሳጢው ጳውሎስንና የፎጢኖስን አሳዛኝ ክህደት የወለደቻቸው በአብዛኛው ያችው አንዲት ስንፍና ብትሆንም፣ እርስ በርሳቸውም የሚለያዩት በጥቂቱ ብቻ ቢሆንም።"¹⁰ ስለዚህ በቅዱስ ሳዊሮስ ዓይን የኬልቄዶናውያን ሚስጥራት እንዴት መታየት አለባቸው? በንስጥሮሳውያን ላይም ቢኾን በቤተክርስቲያን ዘንድ አንዳንዶች በዳግም-ጥምቀት አንዳንዶች በቅብአ ሜሮን እንደሚቀበሏቸው፣በኋላ ላይ ግን ንስጥሮሳውያን ወደ ቤተክርስቲያን ኅብረት ሲመጡ ንስጥሮሳዊነትን በመካድ (By confession) ብቻ እንዲሆን ተወስኗል ስለሆነም የኬልቄዶናውያን ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይሆንም።የቅዱስ ሳዊሮስን ሀሳብ እንዲህ መረዳት እንችላለን፦ 1.ንስጥሮሳውያን ሆኑ ኬልቄዶናውያን በተዋሕዶ ካለው ልዩነት በቀር በክርስቶስ ዘልዓለማዊነት፣ከአብ ጋር ዕሩይ እና የተካከለ መኾኑን ያምናሉ። ይህ ማለት ልክ እንደ ፎጢኖስ ኾነ እንደ ጳውሎስ ሳምሳጢ ሊታዩ አይገቡም ይህም ማለት የንስጥሮሳውያን ክህደት በተዋሕዶው ነበር የጳውሎስ ሳምሳጢ እና የፎጢኖስ ክህደት ግን ከክርስቶስ መለኮታዊ ባህርይ ጋር የሚገናኝ ምንፍቅና በመናገራቸው፣የንሰጥሮሳውያን ግን ከዚህ በተለየ በመኾኑ ነው ቅዱስ ሳዊሮስ ሁለቱን ያወዳደረው። 2.ቀመረ-ጥምቀታቸው(Baptism Formula) በሥላሴ ስም የተከወነ መኾኑ እና በሥላሴ ላይ ያላቸው እምነት ልከኛ መኾኑ። 3.በቀደሙት አበው ዘንድ ይህ እንደ መተዳደሪያ ያገለገለ እና እንደ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእስክንድርያ እና ቅዱስ ጴጥሮስ ዘሮሀ ያሉ ኬልቄዶንን የተቃወሙ የተዋሕዶ አርበኞች የቴዎዶጦስ ዘጆፓን ሀሳብ ሳይሆን የቅዱስ ሳዊሮስን ሀሳብ መቀበላቸው ሲኾን ይህንን ትምህርታዊ ቅብብሎሽ ቅዱስ ሳዊሮስን ያጠናው Iain R.Torrance እንዲህ ይገልጠዋል፦ "እርሱ የዳግም ቅብአትን(Re-Anointing) ሥርዓት በግልጽ አውግዟል። በዚህም ምክንያት፣ ከቄርሎስ ተነሥቶ፣ በጢሞቴዎስ በኩል አልፎ፣ እስከ ሳዊሮስ ድረስ የዘለቀውን የማይለወጥና ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት በግልጽ ማየት እንችላለን።"¹¹ @pan_oriental_orthodox6
አንድ ረዘም ያለ ጽሑፍ ጻፍኩኝ ቅዱስ ሳዊሮስ በኬልቄዶናውያን ምስጢረ ጥምቀት እና ክህነት ላይ ያለውን እሳቤ የሚያሳይ ታነባላችሁ ወይስ ልተወው🙄? እናንተ NGL ብቻ ነው የተመቻችሁ አየኋችሁኮ...
https://www.youtube.com/live/Mcwb2WeXeWc?si=AimNyYrVwtro6QWs
https://www.youtube.com/live/Mcwb2WeXeWc?si=AimNyYrVwtro6QWs
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ይሄው ከአርመን ካለችው ቤተክርስቲያናችን ከየረቫን አርመንያ በአንድ ወንድም የተላኩልኝ መጽሃፍት፣ pan oriental orthodox ይለመልማል ስላችሁ 😅
በፍራንሺስኩ አልቫርሽ የተጻፈው "ኢትዮጵያ ፖርቹጊዞች እንዳይዋት" የሚለው መጽሐፍ ፖርቹጋላዊውያን ከ1520-1526 ዓ/ም ድረስ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ የተጻፈበት መጽሐፍ ሲሆን ከባህረነጋሽ(ከአሁኗ ኤርትራ) ጀምሮ እስከ ንጉሡ ከተማ እና ሌሎች ግዛቶች ድረስ የነበረውን ጉዞ የሚተርክ መጽሐፍ ነው። በመኾኑም ይህ መጽሐፍ በወቅቱ የነበሩትን ኢትዮጵያዊያን ባህላዊ መስተጋብር በጣም የሚያሳየን መጽሐፍ ነው። ታዲያ በወቅቱ የነበሩትን ክርስቲያኖች በቅዳሴ ሰዓት ሁላቸውም እንደሚቆርቡ ይነግረናል፣እንዳውም ሁሉንም የማያቆርብ ስርአት አለን የሚሉትን እነ አልቫርሽን ኹሉ ሲቃወሙ እናያለን። ታዲያ ይኽ አሁን ያለመቁረባችን ልማድ ከመቼ ጀምሮ ነው የመጣብን🙄 ወይስ አፄ ዘርአያዕቆብ ቢመጣ ይሻለናል😂? አፄ ዘርአያዕቆብ በመንግሥት ዘመኑ ቤተክርስቲያን ለማይመጡ 15 የአለንጋ/የጅራፍ ግርፍ እንዲገረፉ እንዳዘዘ፣በዚህ ዘመን ቢኾን ስንት ጅራፍ ያዝብን ይኾን?😀