tgindex
Последний пост
15 мая
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 000
−3 за 3 дн.
Сутки
−1
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 010
20 постов
Вовлечённость
50,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 15 мая517из Theo_Sophia_apology

    ይህንን story በማድረግ እና share በማድረግ ተባበሩን ። እንደሁል ጊዜው መልካም ፈቃዳችሁ እና ቀና ልቡናችሁ ያስፈልገናል ። ያልሰማ ሰው እንዳይኖር ሰምቶም ቸላ ያለ እናም ለመስጠት የሰሰተ እንዳይኖር የሰማ ሁሉ የአቅሙን እንዲያደርግ እና የነዳያንን ረሃብ እንድናስታግስ እንለምናችኋለን።

  • 19 мар.840из Theo_Sophia_apology

    без подписи

  • 19 мар.7411из Theo_Sophia_apology

    ስላረፈድን በእውነቱ በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን ። ይህ ፖል ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው ፤ ምክንያቱም በዚህ ምርጫችሁ መሠረት ነው ቀጣይ የሚታተሙት መጻሕፍት ቁጥር የሚወሰውነው ። እና ደግሞ አሁን እዚህ ላይ  ያላችሁ ሁላችሁም ቅድሚያ እንዲደርሳችሁ፣ እዚህ ያለውን ሰው ብዛት እና መግዛት የምትፈልጉትን መጠን ማወቅ ያስፈልገናል ። መጽሐፉ እንደሰማችሁት ለጥቂት ሰው ስለሆነ የሚታተመው የጀርባ ዋጋ አልወጣለትም ከዚህ የሚሸጠው ግን ለ አንድ መጽሐፍ 1200 ብር ነው በብዛት ለሚገዙ (በተለይ ናዝሬት ብዙ ሰው ጠይቆናል) እና እዚው ለምናቃቸው ተማሪዎች ምን አልባት ይቀንሳል ።

  • 17 мар.6078из Theo_Sophia_apology

    እነሆ እገዛችሁ የሚስፈልግበት ቀን መጥቷል። ከመቼውም ጊዜ በላይ ለእኛ የምትተጉበት ጊዜ እና አገልግሎታችንም እንዲቀጥል የምታደርጉበት ጊዜ መጥቷል። ይህንን በምትችሉት ሁሉ Share አድርጉ፦ በፌስቡክ (Facebook)፣ በቴሌግራም ስቶሪ በግሩፖችና ቻናሎች፣ በኢንስታግራም ስቶሪ ፣ በቲክቶክ (TikTok)፣ በግል መልእክቶች ልባቸው ክፍት ለሆኑ ሰዎች ሊደርስ በሚችልበት በማንኛውም ስፍራ አድርሱ ዜናው በሁሉ ዘንድ እንዲሰማ እና እንዲወራ የሁሉንም ሰው ጆሮ ልንወር ይገባናል። የአባቶችን ጽሁፍ ሁሉም ሰው ሊያነበው ይገባል!።

  • 31 янв.90014из Theo_Sophia_apology

    ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን በቅርቡ "ነገረ አበው ኢትዮጲያውያን" በሚል ስም የወጣ የመምህር በኃይሉ መጽሐፍ ላይ የተሰጠ ክርስቲያናዊ አስተያየት ነው ። ብዙ ነገሮችን ዳሰንበታል ፤ እናም አንብባችሁ ለሌሎችም አድርሱ ርቱዓን አባቶቻችን አማላጅነታቸው የሃይማኖታቸው ቅንነት አይለየን ። አሜን ። @theo_sophia_apology

  • 27 дек.1 04081

    ክፍት ኦርቶዶክሳዊ የመወያያ መድረክ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን። የፊታችን እሁድ የምናደርገው መርኃ ግብር እስከዛሬ በነበሩን ርእሶች ለይ ክፍት የመወያያ መድረክ ሲሆን፣ ያላችሁን የመከራከርያ ጥያቄ እና ሌሎች መናገር የምትፈልጉትን ሁሉ ተዘጋጅታችሁ የምንወያይበት ቀን ነው። ማነኛውም የሚገኝ ሰው አንድ ሰው ይዞ መገኘት ይኖርበታል! ለጌታ ቃል ልባቹ የተሰበረ ስለሆነ እና ስለምትታዘዙ ስለእናንተ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። ባመጣችሁት ሰው መጠን እና እንደ ትጋታችሁ ጌታ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ። አሜን!

  • 20 нояб.1 1306из Theo_Sophia_apology

    የዓለም ሃይማኖት ክርስትና በነበረበት ጊዜ ክርስቲያኖች ውስጥ ለውስጥ የሚለያዩበት እና የሚጣሉበት ብዙ ምክንያቶች አሏቸው የክርስቶስን ሃይማኖት የሚዋጉ የሰይጣን ተላላኪዎች በመጡ ጊዜ ግን ሁሉም በአንድነት ይነሳሉ የምንለያይበት ብዙ ነገር ሊኖር ይችላል ክርስቲያን ስለሆንክ የሚገድልህ ሴቶችን ወስዶ ወንዶችን የሚገድል ክርስቶስን ትተን ገዳይ ሃይማኖት እንድናመልክ የሚፈልግ የሚዋጋን የኢስላም ጦር እየመጣ ነው ። Orthodox protestant እና ለጌታ ሃይማኖት የምትቀኑ በሙሉ ሌሎች ኃይሎችን ሳንጠብቅ በፍጥነት አንድ ሆነን ለክርስትና እንተባበር በግብፅ እና በሶርያ የገደሉትን እልፍ ክርስቲያኖች ደም በኢትዮጵያ አይደገምም። ይሄ ከመሆኑ በፊት በእውነት ዓለም ትጥፋ ! የተኙ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም ተስፋ ቆርጠን አንተዋቸውም የክርሰቲያኖች ሞት ጥላውን እያየን ነው። በፍጥነት ተዘጋጅተን እንድንጠብቃቸው .......በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መከራ እና ሞት እንለምናቹሃለን

  • 20 нояб.1 00312из tsegayekifluchannel

    ይህ ቪዲዮ በጥንቃቄ ይመልከቱት፡፡ ህጻናት ባለበት አይከፈት፡፡ ይህ አራጆቻችን እየደገሱት ያለው ድግስ ነው

  • 26 окт.1 12310из Theo_Sophia_apology

    ሰላመ እግዚአበሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን ዛሬ ሁለት ጥያቄዎችን በመመለስ መጥተናል የመጀመሪያው ጥያቄ ጌታ አብን በስጋው ወራት አምልኳል የሚል ነው ሁለተኛው ደግሞ ቅዱስ ቁርባን ይመለካል ወይ የሚል ነው አንብባችሁ እንወያይበት

  • የጌታ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን ዛሬ ማታ 3 ሰዓት ጆን(ባለፈው በጽሁፍ ስንቀጣቀጥ የነበረው😁) ይመጣል ። እና ጆ philosophy masters paperኡን አሁን ላይ አዲስ አበባ university እየሰራ ነው ።እናም አንዳንድ ነገሮች ስለ paperኡ እና ልቅ ስሜት ከምን ይመነጫል በሚል ርዕስ ከጆን ጋር እንማማራለን በዚህ ላይ ያላቹን ጥያቄ ይዛቹ ኑ እና አትቅሩ

  • https://t.me/+PNBVNLMqrf8yMDc0

  • https://t.me/Theo_Sophia_apology?livestream=bc4d48a94a1d9b8377

  • 29 авг. 2025 г.1 1643из Theo_Sophia_apology

    без подписи

  • 29 авг. 2025 г.1 0601из Theo_Sophia_apology

    без подписи

  • 29 авг. 2025 г.9646из Theo_Sophia_apology

    እግዚአብሔር ቢገለጥለትም አብረሃም የተመለከተው ግን 3 ሰዎችን ነው፡፡ አብረሃም ያየውን ነው የሣለው እንዳንል ሰዎች ነው የተገለጡት ይለናል ፡፡ በሰው ምሳሌ መላእክት ስለተገለጡለት ነውም እንዳንል የተገለጠው እግዚአብሔር ነው ይለናል ። ዘፍ 19፡2 ላይ እንዳለው ሁለቱ እንኳን መላእክት ናቸው ብንል የዘፍ 18 ታሪክ ቢያንስ አንዱ እግዚአብሔር ነው ብሎ ይመስክርብናል፡፡ ዘፍጥረት ብቻ አይደለም መጻሕፍት የሰዶምን ታሪክ ሲጠቅሱ እግዚአብሔርን በሩቅ መድበው ጠርተው እግዚአብሔር መሆኑን ሳይጠቅሱ አያልፉም፡፡ ትንቢተ አሞጽ 11: ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። ትንቢተ ኤርምያስ 50፡ 40: ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም። ይህንን ስትሏቸው የእግዚአብሔር መልአክ የተባለው በብሉይ ኪዳን የተገለጠው እግዚአብሔር የተገለጠበት በእርሱ ላይ እግዚአብሔር ስለሚያወራ ነው ይላሉ(ምሥራቅ ኦርቶዶክሶች እንኳን አይሉም የእኛው ጉዶች ናቸው ይህን ባዮች) ፡፡ ይህ ደግሞ ፈጽሞ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ እና እንደውም ምዕራባዊ ቶሚስቲክ ትርጓሜ እንጂ የአባቶች አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ የተባለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለተላከ ነው፡፡ እግዚአብሔርም የተባለው ወልድ ስለሆነ ነው፡፡ ይህንን የማይመስክር የቤተክርስቲያን አባት ማግኘት አይቻልም፡፡ ስለዚህ በዚህም ትርጓሜ ቢሆን ፈጽሞ ልክ አይደለም፡፡ ልክ አለመሆን ብቻ አይደለም እንደውም በቤተክርስቲያን ታሪክ በነበረው የምሥጢረ ሥላሴ ክርክር ከአባቶች ይልቅ ለመናፍቃን ያደላ ነው፡፡ ታላቁ አባት ሰማዕቱ ቅዱስ ዮስጢኖስ ሰማዕት ከአይሁዳዊው ጥሪፎን ጋር የነበረው ክርክር ይህ ነበር (Justin Martyr, Dialogue with Trypho, 56)፡፡ ስለዚህ ይህ ሥዕል ዘፍጥረት 18 ላይ ያለውን ታሪክ አለመውከሉ ብቻ ሳይሆን እውነተኛውን የቤተክርስቲያንን የዘፍጥረት 18ን ትርጓሜ የሚሸፍን ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት ሊሰጡት የፈለጉትን ትኩረት ችላ ያለ ነው፡፡ እንዲሁ በቸልተኝነት ውበቱን እና ቀለም አቀባቡን አይተን ልናስገባው አይገባም፡፡ እና ተጠንቀቁ፡፡ ለጊዜው እንደዚህ አሳጠርኩት፡፡ በሌላ ጊዜ ዘፍ 18ን ማየታችን አይቀርም፡፡ የሰማዕቱ ዮስጦስ እና የጥሪፎን ክርክር በኮምንት መስጫ ውስጥ ለቀዋለው ። ይቆየን !

  • 29 авг. 2025 г.82616из Theo_Sophia_apology

    + የቅድስት ሥላሴ ስዕል+ “የትኛውንም ቃለ እግዚአብሔር በየትኛውንም ሰው ቢነገር ከተራ ቃላት ስብስብ በላይ ከፍ ያለ ትርጉም ይኖራዋል። ተናጋሪው ሰው ምንም እንኳን አንደበቱ ርቱዕ እና ቀልጣፋ ምላስ ባይኖረውም የሚናገረው ነገር የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ብቻ ትልቅ ክብር ይሰጠዋል፡፡ አባቶች እና መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ሲሆኑ ደግሞ ከአንደበታቸው መጣፈጥ በላይ ከሰውነታቸው ቅድስና የሚፈሱት ዐረፍተ ነገሮች ልብ ይስባሉ ጆሮ ይይዛሉ፡፡ የነፍሳቸው ቅድስና እና የሰውነታቸው ንፅሕና የልባቸውን ብርሃን የሚሰማቸውን ሰው ደንዳና ልቡና ይሰብራሉ፡፡ ልክ እንደዚህ ሁሉ ሥዕላትም ከማንኛውም የቀለም ክምር የተለዩ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ጠቢባን ከሚባሉ ሰዎች ዓለማዊ ሥዕል ፤ መንፈሳዊው ሥዕል ስለ መንፈሳዊነቱ ሲባል ብቻ ክብር ይሰጠዋል ፡፡ ከእነዚህ መንፈሳውያን ሥዕሎች ደግሞ ብዙ ምሳሌ እና ምስጢር ያላቸው ሥዕላት ዓይንን ያፈዛሉ ቀልብ ይስባሉ፡፡ እቅዴ ስለ ሥዕል ትውፊት ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊነት እና በቤተክርስቲያን ታሪክ እሙንነት ለማሳየት አይደለም ፤ እነዚህ ከላይ የነገርኳችሁ የንግግር ጥበብ እና የሥዕል ጥበብ ልክ እንደ መልካም ነገራቸው ሁሉ ደካማ እና መጥፎ ጎን ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ዛሬ አሁን አሁን ላይ በእኛ ምእመናን ዘንድ የሚስተዋል፣ ጭራሹኑ ደግሞ መምህራንም ላይ የሚታይ፣ ከኛ ትውፊት ውጪ የሆነ እንዲያውም በተቃራኒ የሆነ ሥዕል በብዛት ለሚጠቀሙ ወንድሞች እና እህቶች አጠር ያለ ማሳሰቢያ ለመስጠት ወደድኩ፡፡ ምንም እንኳን ሥዕላት የተሠሩበትን ቁስ እና ቀለም ባንስግድላቸውም በሥዕላቱ የተወከለውን ቅዱስ በሥዕል ፊት ቆመን እንሰግዳለን፡፡ ይህማ ሌላ አምላክ ማምለክ ነው ለሚለው ፕሮቴስታንታዊ ጥያቄ ሌላ ቀን እመለሳለሁ፡፡ ይህንን ግን እኛ ምን ያህል ሥዕላትን እንደምናከብር ልነግራችሁ ብቻ አንሳሁት ፡፡ በቤተመቅደሶቻችን ሞልተዋል ፤ በጸሎት ክፍላችንም አሉ ፤ ከክርስትና ሕይወታችን እና ታሪካችን ጋር ፈጽሞ ተጣብቀዋል፡፡ ይህ ፍቅራችን ግን የተሳሳቱ እና ከኛ ትውፊት ውጪ የሆኑ ሥዕሎችንም እንደዚሁ እንድንቀበል እንዳያደርገን መጠንቀቅ ይገባል በተለይ ከአባቶች ቀዳሚው ትምህርት ጋር፡፡ ሥዕላት የሚሳሉት ትክክለኛ ትርጉም እንዲኖራቸው ተደርጎ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እንደየ ሥዕላዊ ጥበብ እና መንፈሳዊ ዕውቀት ይለያያል፡፡ ከዚህም የተነሳ በንድፍ ጥበብ፣ በቀለም አጠቃቀም፣ በአሳሳል ዓይነት ብዙ ትውፊቶች አሉ፡፡ በኢትዮጲያ ፣ በቅብጥ፣ በሶርያ ፣ በምዕራቡ እና በምሥራቃ አብያተ ክርስትያናት የተለያየ አይነት የአሳሳል ትውፊት እናገኛለን፡፡ አንዳንዴ በሥዕል ትውፊት ላይ ከአሳሳል ትውፊት ልዩነት በዘለለ ደግሞ ትምህርታዊ የሆኑ ልዩነቶች አሉ ፡፡ አንዳንዶቹ ቀለል ያሉ ልዩነቶች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ጠንከር ይላሉ ፡፡ በዚህ ጊዜ የትኛው ልክ እንደሆነ በቤተክርስቲያን ትምህርት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ከአሳሳል ትውፊት ያለፈ ልዩነት ላስታውሳችሁ፡፡ የቅድስት ሥላሴን ሥዕል በተመለከተ ብዙ ልዩነቶች አሉ፡፡ ከአሳሳል ልዩነቶች በመጀመሪያ አንዳንዱ የሥላሴን ሥዕል አብን በአረጋዊ፣ ወልድን መስቀል ይዞ መንፈስ ቅዱስን በርግብ ሲሥሉ እናገኛለን፡፡ በሌላ ቦታ አብና ወልድ በዙፋን ተቀምጠው መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ይሳላል፡፡ በሌላ ቦታ አብን በአረጋዊ፣ ወልድን በሕፃን፣ መንፈስ ቅዱስን በርግብ ይስላሉ፡፡ እነዚህ ሥዕሎች አብን በዳንኤል ራዕይ መሠረት ይስሉታል፡፡ ሌላው ደግሞ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አብን ዓይኑን ሸፍነው ይስላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በፍጹም አንሥለውም ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት የአብን አለመታየት ምክንያት አድርገው ነው፡፡ በእነዚህ ላይ የምናየው ልዩነት 2 አስተያየት ልሰጥበት እችላለሁ፡፡ የመጀመሪያው አብን በሥዕል ማስፈር በምንም ሁኔታ ፈጽሞ የተከለከለ ነው የሚሉ አንዳንድ ትውፊቶች ቢኖሩ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ሆነ ትውፊታዊም አይደለም፡፡ ምክንያቱም አብን የሳሉ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ በመጻሕፍትም አብ ለዓይን መስል እንዲገባ ሆኖ በአምሳለ አረጋዊ ተገልጧል፡፡ በዚህም ቅዱሳት መጻሕፍት አብን በህሊና በሰው አምሳል መሳል አለመከለላቸውን እናቃለን፡፡ ነገር ግን ይህንን ስል እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ትውፊታቸው ይታረም ልክ አይደለም እያልኩ አይደለም፡፡ አብ በምድር ተገልጦ ስላልተመላለሰ እና መጻሕፍት ስለእርሱ የሚናገሩትን ያለመታየቱን ነገር ትኩረት ለመስጠት ከሆነ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሥላሴን ሥዕል የሚሥሉ አብያተ ክርስቲያናት በሥላሴ ላይ እነዚህ አካል ክፍሎች አሏቸው ለማለት ከሆነ ይህ በፍጹም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በቤተክርስቲያን ታሪክ እንዲህ ሆኖ አያውቅም፡፡ ሆኖም ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ እግዚአብሔር የተገለጠባቸውን ክፍሎች ምክንያት በማድረግ ከሆነ ትውፊታዊም መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው፡፡ (በነገራችን ላይ እያንዳንዱን የሥላሴ ሥዕል ሕጹጽ መሆኑ የታወቀ ነው ፡፡ ልክ ቃላት በምልዐት እንደማይገልጹት ቀለሞችም ጌታን ሊገልጹት አይችሉም፡፡) ስለዚህ በዚህ የተነሳ እነዚህ ትውፊቶች ያለ መቃራን አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ በአንድሬ ሩብሌቭ (በምሥራቃውያን ዘንድ ቅዱስ ነው፡፡) በሶስት መላዕክት አምሳል የተሳለው የቅድስት ሥላሴ ስዕል ከእኛ ትውፊት አብዝቶ የራቀ ብቻ ሳይሆን የቀድሞውን የአባቶች ትምህርት የሚቃረን(እዚህ ጋር እያልኩት ያለሁት ሥዕሉ ለተሳሳተ ትምህርት ክፍት የሆነ እና አሳሳች ምንም እንኳን ለሥዕሉ የሚሰጠው ትርጉም ልክ መሆን የሚችል ቢሆንም) ነው ። አንዳንድ ምዕመናን እና መምህራን ሲጠቀሙበት አያለው ። አንድሬ ሩብሌቭ ለምን በሶስት መላእክት ሥላሴን ሣለ ስትሏቸው የመጀመሪያው እግዚአብሔር አይታይም በዘፍጥረት 18 ላይ ያለውን ታሪክ ነው የሣለው ይሉናል፡፡ በዘፍጥረት ግን የትኛውም ክፍል ቅድስት ሥላሴን በሶስት መላእክት አምሳል ለመሳል ጥሩ ምክንያት አይሆንም፡፡ በዘፍ 18 ላይ ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፡- "በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት ፤ ዓይኑንም አነሣና እነሆ ፡ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆእመው አየ ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሦቶ ሮጠ ፡ ወደ ምድርም ሰገደ ..." [ዘፍ 18 ፡ 1 - 2]

  • 29 авг. 2025 г.6662из Theo_Sophia_apology

    የአንድሬ ሩብሌቭ የቅድስት ሥላሴ ሥዕል ይሄ ነው

  • 15 авг. 2025 г.856из Theo_Sophia_apology

    ከ 10 min በኋላ እንገናኝ epistemology

  • 12 авг. 2025 г.975212из Theo_Sophia_apology

    без подписи

  • 12 авг. 2025 г.1 0623из Theo_Sophia_apology

    ሰላም ሰዎች ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁም ጋር ይሁን ሰለ መልክአ እግዚአብሔር ደብተራ በአማን ነጸረ ተኀሥሦ በተባለ መጽሐፋቸው ላይ አንድ ረጅም ጽሁፍ አጥናቀናል እና ረዘም ስለሚል pdfኡን እና እንደገና ደግሞ ዝርው አድርገን እንፖስተዋለን ንጹህ እና ቅዱስ ጌታችን ሆይ አንተን ብቻ እንወድ ዘንድ እንለምንሃለን ለአባቶቻችን የተረፈላቸው ፍቅርህን አድለን አቤቱ እስከመጨረሻይቱ ህቅታ ድረስ እንወድህ ዘንድ ፍቅርህ በልቡናችን ይሙላ አሜን