Hruy News
Статистикаአጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን በTelegram በYouTube በFacebook በInstagram በTwitter በTiktok እናቀርባለን። Follow like,share እያደረጉ ይከታተሉ።
- Последний пост
- 19 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በአሁኑ ወቅት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨና የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ የሚገኝ አዲስ ምስል በአማራ ክልል ያለውን የትምህርት ሁኔታ እና የጦርነቱን መዘዝ በጉልህ የሚያሳይ ሆኗል። በምስሉ ላይ እንደሚታየው የፋኖ ታጣቂዎች በትምህርት ቤት ግቢዎች ውስጥ በቀጥታ በመገኘት፣ ከጥቂት የትምህርት ቢሮ ሠራተኞች ጋር በመሆን የ6ኛ ክፍል የአማራ ክልላዊ ፈተናን ሲቆጣጠሩና ተማሪዎችን ሲፈትኑ ይስተዋላል። ይህ ክስተት በክልሉ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የደረሰውን ከፍተኛ መስተጓጎል በይፋ ያጋለጠ ሆኖ ተገኝቷል። ለዚህ ታጣቂዎች በፈተና አዳራሽ ውስጥ የመገኘታቸው ዋና ምክንያት በክልሉ ገጠራማ ክጽል የሚገኙ መምህራን ከደሞዝ ክፍያ መቋረጥና ከጦርነቱ ዘርፈ ብዙ መዘዞች የተነሳ ከአብዛኞቹ አካባቢዎች ሥራቸውን ለማቋረጥ መገደዳቸው ነው። በዚህም ምክንያት በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተፈጠረውን ሰፊ የሰው ኃይል ክፍተት ለመሙላት፣ በክልሉ ገጠራማ አካባቢዎች በስፋት እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የአማራ ኃይሎች ታጣቂ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በመገኘት ክፍሎቹን ተረክቦ ፈተና ሲቆጣጠር ታይቷል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል በአብዛኛው የክልሉ ገጠራማ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች አሁንም ድረስ ዝግ መሆናቸውን መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ አዲሱ ትዕይንት ግን በግጭቱ መሃል ሆነውም ፈተናዎችን ለማስቀጠል እየተደረገ ያለውን አስገራሚ ጥረትና የደረሰውን ማኅበራዊ ቀውስ በግልጽ ያሳያል።
😭
😭
ሰሜ ባላገሩ አንጋፋው የባህል ሙዚቃ ተጫዋች ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም። ከባህል ድምጻዊነቱ በተጨማሪ የዜማና ግጥም ደራሲ የሆነው የሰማኸኝ ስርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል። ሰሜ ከመደበኛ በላይ የሆነ ውፍረቱ ይህ ነው የተባለ የጤና ችግር እንዳልፈጠረበት (ስኳር፣ ግፊት ... የመሳሰሉ) ከአንድ አመት በፊት ተናግሮ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ውፍረቱን ለመቀነስ የተለያዩ የህክምና ዘዴዎችን ሲከታተል የቆየ ሲሆን ጥሩ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እራሱ ሲገልጽ ነበር። ሰኞ ሰኔ 8 ጥዋት ላይ በርካቶችን ባስደነገጠና ባልተጠበቀ ሁኔታ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። የመጨረሻ ሰዓታቱን በተመለከተ ልጆቹን ዋቢ አድርጎ የገለጸው አቻሬ ሚዲያ ፤ ሰኞ ሰኔ 8 ጥዋት የድካም ስሜት ተሰምቶት በልጆቹ አማካኝነት ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ነበር። ወደ ሆስፒታል በሚወሰድበት ወቅት ግን ወንበር ላይ ዘንበል ያለ ሲሆን ሆስፒታል ደርሶ ከገባ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ህይወቱ አልፏል። በአማራ መዲና፣ ባህር ዳር ተወልዶ ያደገው ድምጻዊ ሰሜ፣ ገና በ14 ዓመት ታዳጊነቱ በባህር ዳር ሕጻናት ክፍል ፣ በመቀጠል በአዮማ እና በግሽ አባይ ኪነጥበብ ቡድኖች ውስጥ በመሳተፍ የጥበብ ጅማሮውን አድርጓል፤ በዚህም ረጅም ዓመታትን ለዘለቀው ስኬታማ የጥበብ ጉዞው ጠንካራ መሠረት ጥሏል። ሰሜ ባላገሩ በረጅም ዓመታት የጥበብ ስራዎቹ በተለይ የሀገር ባህል የሙዚቃ ዘርፍን ወጉን እና ስርዓቱን ጠብቆ በከፍተኛ ደረጃ ያስተዋወቀ ሲሆን በተለያዩ ክለቦችም ዘመናዊ ሙዚቃዎችን በመጫወት ልዩ ብቃቱን ያሳየና በርካታ የባህል ሥራዎችን ለአድማጭ ያበረከተ የጥበብ ባለውለታ ነው። ከተወዳጅ የባህል ስራዎቹ መካከል ፦ - ባላገር - ደቦት እንስራ - ዘገኛ - አለሽ ነገር - ዝናቡ - አለምን እንደምነሽ .... የሚሉት ይጠቀሳሉ። ከተሰጥዎው ባሻገር በተገኘበት ቦታ ሁሉ ሳቅን የሚፈጥር ፣ እጅግ ተጫዋች ፣ ቀልድ አዋቂ እንዲሁም በመልካም ስብዕናው ይታወቅ የነበረው ሰማኸኝ፤ በአንድ ወቅት " ሦስት ነገር እወዳለሁ፤ ሀገሬን፣ ትዳሬን እና ሥራዬን " በማለት መርሁን ገልጾ ነበር። ከ35 ዓመታት በላይ በዘለቀው የትዳር ህይወቱ የአራት ልጆች አባት የነበረው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) በሠራቸው ውብ የሙዚቃ ሥራዎቹ ሁልጊዜም ይታወሳል። የሰሜ ባላገሩ ስርዓተ ቀብር ማክሰኞ ሰኔ 9 ቀን 2018 በቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል። ነፍስ ይማር ! @Hruynews
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የረዥም ዘመን የባህል ሙዚቃ አምባሳደሩ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በሀገራችን የባህል ሙዚቃ ዘርፍ ታዋቂነትን ያተረፈውና በብዙሃን ዘንድ ሰሜ ባላገሩ"እየተባለ በሚጠራው ተወዳጁ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በህሩይ ሚዲስም እንገልፃለን ። ባደረበት የድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ የቆየው ድምጻዊው፣ በተወለደ በዛሬው ዕለት (ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም) በተደረገለት የህክምና ክትትል ህይወቱ ማለፉን የቅርብ ቤተሰቦቹ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግና ታሪክ የሚያንጸባርቁ በርካታ የሙዚቃ ስራዎችን ለአድማጮች ያበረከተው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው፣ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ውስጥ በተለይ የኔ አለም ማረአለሽ; ዳቦት እንስራ በሚሉ ተወዳጅ ባህላዊ ዘፈኖች የራሱን ደማቅ አሻራ ጥሎ ማለፍ የቻለ ከያኒ ነበር። ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት እንደነበር ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው የኪነ-ጥበብ አድናቂዎቹ በሙሉ መጽናናትንና ብርታትን ይመኛል። ፈጣሪ ነፍሱን በገነት ያኑራት! https://www.facebook.com/share/r/1EYafh9LQF/
(Hruy ዜና) በ2022ቱ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ቁልፍ ተደራዳሪ የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ እና አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ "ጽንፈኛ" ያሉት የህወሓት ክንፍ ከኤርትራ መንግሥት ጋር በማበር ዳግም ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በማጋለጥ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቀረቡ። ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሰሞኑን በአልጀዚራ ሚዲያ ላይ በጋራ ባወጡት ጽሑፍ እንዳስታወቁት፣ ይህ የህወሓት አክራሪ ቡድን የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በማፍረስ የራሱን ህገ-ወጥ አስተዳደር የመሰረተ ሲሆን፣ በኤርትራ መንግሥት ቀጥተኛ ድጋፍ ወጣቶችን በግዴታ እየመለመለ፣ እያሰለጠነ እና እያስታጠቀ ይገኛል። ባለስልጣናቱ በጽሑፋቸው የኤርትራን ጣልቃ ገብነት በስፋት የኮነኑ ሲሆን፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያ ደካማ እና የተከፋፈለች ሆና እንድትቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። በመሆኑም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማፍረስ፣ በህወሓት ውስጥ ካሉ ጽንፈኛ አካላት እንዲሁም ከአማራ ፋኖ ሚሊሻ አክራሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር «ጽምዶ» የተሰኘ አዲስ ጥምረት በአስመራ አደራጅተዋል ሲሉ ከሰዋል። ይህ በአስመራ፣ በመቐለ እና በሱዳን በሚስጥርም ሆነ በግልጽ ስብሰባዎች የተዋቀረው ጥምረት፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት በአደባባይ በመጣስ በሚቀጥሉት ቀናት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ግልጽ ጥቃት ለመሰንዘር መወሰኑን አቶ ጌታቸው እና አምባሳደር ሬድዋን አጋልጠዋል። በተጨማሪም ይህ ቡድን ለሰላም እና ለስምምነቱ መከበር የቆሙትን አመራሮች ከመዋቅሩ እያባረረ መሆኑን ጠቁመዋል። የትግራይ ህዝብ የጦርነት አጀንዳን በግልጽ ውድቅ ማድረጉን ያነሱት ሁለቱ ባለስልጣናት፣ አክራሪው የህወሓት ቡድን ግን የኤርትራን አስገዳጅ የወታደራዊ ምልመላ ስልት በመጠቀም ትግራይን ወደ ሌላ ምስቅልቅል እየቀየራት መሆኑን አስጠንቅቀዋል። "የፕሪቶሪያው ስምምነት ፍጹም ባይሆንም.. ጠመንጃዎችን ዝም ያሰኘ እና በጦርነት ለፈረሰው ክልል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መደበኛ ህይወት እንዲመለስ ያስቻለ ነው" ያሉት ጸሐፊዎቹ፣ የሙሉ ትውልድን ህይወት ለፖለቲካቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት ቀጠናውን ዳግም ወደ ጦርነት ቅዠት እንዲጎትቱት መፍቀድ እንደማይገባ አሳስበዋል። በማጠቃለያቸውም፣ በህወሓት እና በአስመራ በሚገኙ ደጋፊዎቹ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችል ማንኛውም ዓለም አቀፍ አካል፣ የሰላም ስምምነቱን ለማፍረስ የሚወስዷቸው እርምጃዎች ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌላቸው ግልጽ እና የማያወላዳ ጠንካራ ጫና እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። #share Join👇 @Hruy News
#SaudiArabia በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1,655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። " ይህ ስኬት የተገኘው በሪያድ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በጂዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በማስተባበር ባደረግነእ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ነው። ይህም መንግሥት ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተመዘገበ ውጤት ነው " ብሏል። ሚኒስቴሩ በሳዑዲ አረቢያ ቀሪ የዲፕሎማሲ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን በመጠቆም፤ ሕብረተሰቡ ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ መንገዶች ከሚያሰራጯቸው የሐሰት ማታለያዎች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል። የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ከዚህ ቀደም ከዚህ ቀደም አደንዛዥ እፅ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን 65 ኢትዮጵያውያንን ያካትት እንደሆነ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። በሌላ በኩል ፥ ሳዑዲ አረቢያ በዚህ ሳምንት አራት ኢትዮጵያውያንን በሞት መቅጣቷን አሳውቃለች። የሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኔ 1 ሁለት እንዲሁም ሰኔ 3/2018 ዓ.ም. ሁለት ኢትዮጵያውያን በስቅላት መገደላቸውን ከስም ዝርዝር ጋር ገልጿል። የሞት ቅጣቶቹ የተፈጸሙት ሰኔ 1/2018 ዓ.ም. በናጅራን ግዛት እንዲሁም ሰኔ 3/2018 ዓ.ም. ደግሞ በአሲር ግዛት መሆኑን አመልክቷል። አራቱም ኢትዮጵያውያን በሞት የተቀጡት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሃሺሽ ይዘው በመግባታቸው መሆኑን የሚኒስቴሩን መግለጫ ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል። ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም @Hruynews
без подписи
без подписи
በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱ የተሽከርካሪዎች መለያ ሰሌዳ (ታርጋ) ዋጋ ስንት ነው ? ዛሬ በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ለተመዘገቡና ወረፋ እየጠበቁ ላሉ አዲስ መኪና ለገዙ ተገልጋዮች አዲሱ ታርጋ መሰጠት ተጀምሯል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአዲሱ ታርጋ የተተመነውን ታሪፍ ዶክመንት ተመልክቷል። የነዳጅ (የፊትና የኋላ ታርጋዎችን ጨምሮ) እንዲሁም የኤሌክትሪክ እና የተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎች ታሪፍ በየደረጃው በዝርዝር ተቀምጧል። በዚህም ፥ - የከተማና የሃገር አቋራጭ አውቶቡሶች፣ - የአካል ጉዳተኞች (PD) ተሽከርካሪዎች፣ - የመንግሥት ተሽከርካሪዎች፣ - ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) የሰሌዳ ዋጋ ለነዳጅ 9,400 ብር ሲሆን፣ ለኤሌክትሪክና ተፈጥሮ ጋዝ ደግሞ 7,100 ብር ሆኖ ታሪፍ ወጥቶለታል። ለሕዝብ ታክሲ ትራንስፖርት ለነዳጅ 11,700 ብር ለኤሌክትሪክ ደግሞ 9,400 ብር ክፍያ ተቆርጦለታል። በከፍተኛው የዋጋ ተመን የተመደቡት ፦ - የግል መገልገያ፣ - የንግድ፣ - የዲፕሎማቶች፣ - የዕርዳታ ድርጅቶች፣ - ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም የልዩ ተንቀሳቃሽ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳዎች ሲሆኑ ለእነዚህ ዘርፎች ለነዳጅ ታርጋ ዋጋ 56,000 ብር፣ ለኤሌክትሪክና ተፈጥሮ ጋዝ ታርጋ ዋጋ ደግሞ 44,500 ብር ተቆርጧል። በተጨማሪም የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ሰሌዳ 28,500 ብር ፣ የኤሌክትሪክ ሰሌዳ 15,200 ብር ታሪፍ ተቆርጦላቸዋል። ዝቅተኛው የዋጋ ተመን የተቆረጠው ለባለ ሁለት እግር (ሞተር ሳይክል) ተሽከርካሪዎች ሲሆን ዋጋውም ለነዳጅ 4,700 ብር እንዲሁም ለኤሌክትሪክ 3,550 ብር መሆኑ ታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም @Hruynews
https://vm.tiktok.com/ZTBHPgB6F/
Channel name was changed to «Hruy News»
Channel photo updated
የአማራ ህዝብ ለፋኖ ምን ያድርግ? የአማራ ሕዝብ ለፋኖ ታጣቂ ኃይሎች የሚያደርገው ድጋፍ የትግሉ የጀርባ አጥንትና የህልውናው መሠረት ነው። ታሪካዊው ሽምቅ ውጊያም ሆነ ወቅታዊው ሕዝባዊ ንቅናቄ ያለ ማኅበረሰብ ሙሉ ተሳትፎና ጥበቃ ግቡን ሊመታ አይችልም። ሕዝቡ ለታጣቂ ኃይሎቹ ሊያደርጋቸው የሚገቡ ዋና ዋና ስልታዊና ተግባራዊ ድጋፎች ናቸው፦ 1. አስተማማኝና ወጥ የሆነ የደኅንነት መረጃ መስጠት (Intelligence). በጦርነት ውስጥ መረጃ ከትጥቅ በላይ ዋጋ አለው። ማኅበረሰቡ የአካባቢውን መልክዓ-ምድርና የሰው እንቅስቃሴ ጠንቅለው እንደማወቁ መጠን የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅበታል፦ • የጠላትን ስምሪት፣ አቅጣጫ፣ የጦር መሣሪያ ዓይነትና ቁጥርን አስቀድሞ ለታጣቂዎች በጥንቃቄ ማሳወቅ። • በሕዝብ መሃል የሚሸጎጡ የውስጥ አርበኞችን (ሰላዮችን) በመከታተልና በማጋለጥ የፋኖን ደኅንነት መጠበቅ። 2. ስንቅና መሠረታዊ ቁሳቁሶችን ማደራጀት (Logistics). የታጠቀው ኃይል በጫካና በዱር ውስጥ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ የዕለት ጉርስና የሕክምና አቅርቦት ያስፈልጋል። • የተደራጀ ስንቅ ማቅረብ፦ የአካባቢውን ገበሬና ነዋሪ በማያደኸይ መልኩ፣ በየቀበሌውና በየጎጡ በፈራረቃ ደረቅ ስንቅ (ቆሎ፣ በሶ፣ ዳቦ) ማዘጋጀት። • የሕክምናና የአልባሳት ድጋፍ፦ የቆሰሉና የታመሙ ታጣቂዎችን በሚስጥር ማከም፣ መድኃኒቶችን ማቅረብና ቅዝቃዜን የሚቋቋሙ አልባሳትን (ብርድ ልብስ፣ ጃኬት) ማሰባሰብ። 3. የሞራል ጋሻ መሆንና በሐሰት ፕሮፓጋንዳ አለመሸበር. ጠላት የሕዝብንና የታጣቂውን ትስስር ለመበጠስ የተለያዩ የስነ-ልቦና ጦርነቶችንና የሐሰት ወሬዎችን ይነዛል። • ሕዝቡ በፋኖ ጀግነትና ፍትሐዊነት ላይ ያለው እምነት መጽናት አለበት። ታጣቂዎች በሚገጥሟቸው ጊዜያዊ መሰናክሎች ሳይደናገጡ የሞራል ስንቅ መሆን ይገባል። • የፋኖን ስም ለማጠልሸት የሚለቀቁ የቪዲዮና የድምፅ ቅንብሮችን ባለማመንና ባለማሰራጨት የንቅናቄውን ስም መጠበቅ። 4. የዲሲፕሊንና የፍትሕ ጠባቂ (ገራፊ) መሆን. ሕዝብ ለፋኖ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ማስተካከያም መሆን አለበት። ፋኖ ሕዝባዊ ኃይል ስለሆነ ከሕዝብ የሚሰነዘርን ገንቢ ትችት ሊቀበል ይገባል። • ከተግባር ማናጋት መከላከል፦ ታጣቂዎች ከውትድርና ሥነ-ምግባር ውጭ የንጹኃንን መብት ሲጋፉ፣ በሕዝብ ንብረት ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ወይም የውስጥ አለመግባባቶችን ሲፈጥሩ፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጣልቃ በመግባት ታጣቂዎቹን መገሰጽና ወደ መስመር መመለስ አለባቸው። • ሽፍታን መለየት፦ የፋኖን ስም ይዘው የግል ጥቅም ለማሳደድ የሚንቀሳቀሱ ወንበዴዎችንና ታጣቂዎችን ለይቶ ለዕዙ ማሳወቅ። 5. የውስጥ ሰላምና ኢኮኖሚን ማስቀጠል. ትግሉ ረጅም ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል፣ የክልሉ ማኅበረሰብ የውስጥ ሕይወቱና ኢኮኖሚው መፈራረስ የለበትም። • ግብርናና ንግድን አለማቋረጥ፦ ገበሬው መሬቱን በወቅቱ ማረስና ማምረት አለበት፤ ምክንያቱም የነገው የትግል ስንቅ የሚገኘው ከዚሁ ምርት ነው። • የእርስ በርስ ትብብር፦ ታጣቂ የሆኑ ወጣቶች የእርሻ መሬቶችና ቤተሰቦች እንዳይበደሉ፣ የቀረው ማኅበረሰብ ተባብሮ የታጣቂዎችን ቤተሰብ ማረስና ማገዝ ይኖርበታል። 6. ለአንድነትና ለተማከለ ዕዝ ግፊት ማድረግ. ሕዝቡ በየአካባቢው ራሳቸውን ችለው ለሚንቀሳቀሱ የፋኖ መሪዎች የሚሰጠውን ድጋፍ ከማዋሃድ አጀንዳ ጋር ማያያዝ አለበት። • መሪዎቹ የቡድንና የአካባቢ ስሜትን ትተው በአንድ ወጥ የጦር ዕዝ ስር እንዲሰባሰቡ ሕዝቡ የሞራልና የማኅበራዊ ጫና (ግፊት) ማድረግ ይኖርበታል። “የማትሰበሰቡ ከሆነ አንደግፋችሁም” የሚል ጠንካራ አቋም መያዝ መሪዎቹ ለአንድነት እንዲፋጠኑ ያደርጋል። የአማራ ሕዝብ ለፋኖ ማድረግ ያለበት “መረጃ መሆን፣ ስንቅ ማደራጀት፣ የሞራል ከለላ መስጠት እና ባልተገቡ ተግባራት ላይ ደግሞ የዕርምት መስመር መሆን” ነው። ሕዝብና ታጣቂው በአንድ ልብ ሲቆሙ ትግሉ በአጭር ጊዜ ፍሬ ያፈራል። አማራ ሲያሸንፍ ኢትዮጵያም ታሸንፋለች
https://youtube.com/shorts/QDmzA6YkKY4?si=of3ugWd-nDrN08C1
без подписи