tgindex
አንኳር መረጃ- ETH

አንኳር መረጃ- ETH

Статистика

ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት 👇👇👇👇 @Melka_promo አንኳር መረጃ በዚህ ቻናል ለኢትዮጵያ ፍቅር ሰላም አንድነት ስለ ፍትህ የምናወራበት ድምፅ ላጡ ድምፅ የምንሆንበት ቻናል ነው። ''We testify about the Truth ''

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
15 362
−79 за 4 дн.
Сутки
−18
−0,12%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
7 021
28 постов
Вовлечённость
45,7%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 28
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
3 198
1/48двое суток
3 664
1/72трое суток
3 952

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.2 832163

    መንግሥት በዚህ አመራር ላይ አፋጣኝ እርምጃ መዉሰድ አለበት ፣ ህዝብ በመንግስት ላይ ያለዉን አመኔታ እንዲሸረሸር ከማድረጉም ባለፈ ሰዎች ያለ በቂ የህግ ሂደት እንዲረሸኑ ያደረገ እና እዉቅና የሰጠ ግለሰብ ነዉ ፡፡

  • 11 авг.3 606261

    ሶስት አሠልጣኞችና አራት አትሌቶች አሜሪካ ፖርትላንድ ላይ ኮበለሉ! 🔴 ቡድኑ በቺካጎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ 7 የቡድኑ አባላት ከልዑካን ቡድኑ ጋር የሉም 🔴 የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ብቻ ሳትሆን በርካቶች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማም ሆና ተመዝግባለች ✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት) በአሜሪካ ኦሪገን ዩጂን ሲካሄድ የነበረው ከ20 ዓመት በታች 21ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቁ ይታወሳል። ወደ ውድድሩ ስፍራ የተጓዘችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣3 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 6 ሜዳሊያ ማግኘቷም ይታወቃል። ከወደ ኦሪገን ከደቂቃዎች በፊት የደረሠን አስደንጓጭ ዜና ለሻምፒዮናው ከተጓዙት የልዑኳን ቡድን አባላት መካከል ሰባቱ ፖሬትላንድ ላይ መኮብለላቸው ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን በአሁን ሠዓት ከፖርትላንድ ተነስቶ ወደ ቺካጎ አየር ማረፊያ እየተጓዘ ሲሆን እነዚሁ ሰባቱ የቡድኑ አባላት ከልዑኳን ቡድኑ ተለይተው መቅረታቸውን ነው ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ያረጋገጠችው። እንደ ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ከሄዱት አራት አሠልጣኞች ሶስቱ ከቡድኑ ጋር ባለመመለሳቸው በአሁን ሠዓት ወደ ኢትዮጵያ በመገስገስ ላይ በሚገኘው አውሮፕላን ውስጥ አንድ አሠልጣኝ ማለትም አሠልጣኝ መሠረት  ብቻ እንደሚገኝ ነው ምንጮቻችን የገለፁልን። አትሌቶቻችን በተመለከተ አራት አትሌቶች እንደኮበለሉ የገለፁልን የመረጃ ምንጮቻችን በወኪንግ፣በ800፣በ5ሺ እና በ3ሺ መሠናክል ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ከቡድኑ ጋር አብረው እንዳልተመለሱና እንደኮበለሉ ነው የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው የገለፁልን። የአትሌቶቹና የአሠልጣኞቹ ሙሉ ስም የደረሳት ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ለቤተሠቦቻቸውና ለደህንነታቸው ስትል የሁሉንም ስም ይፋ ከማድረግ ተቆጥባለች። የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ቤቻ ሳትሆን በርካታ አትሌቶች፣አሠልጣኞችና  አመራሮች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማ ሆና ተመዝግባለች።

  • 11 авг.3 793315

    በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው   በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ።   ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል።   ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል።   በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ  ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል።   በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል።   የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ በሰጡት አስተያየት፣ እነዚህ አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።   ሆኖም መንግሥት አገራዊ ገቢውን ለማሳደግ ሲል ውሳኔዎቹን በቁርጠኝነት እንደሚተገብራቸው ይጠበቃል ብለዋል።  ethio fm

  • 7 авг.5 875607

    ባሻዬ! ብዙ ሰዎች በህብረት በሚኖሩበት መንደር ውስጥ የሚኖር አንዱ ሰው በሌሊት ተነስቶ ለሥራ ከቤቱ ሲወጣ ጎረቤቱ አንዱን ሰው ሲደበድበው ተመለከተ። ደብዳቢው በያዘው ዱላ ሌላውን ሰው ጭንቅላቱን ሲመታው ተመቺው ወድቆ ሞተ። ገዳዩ ወዲያውኑ ወደ ቤቱ ሄዶ አካፋና ዶማ አምጥቶ ሟቹን እየጎተተ ከወሰደው በኋላ በያዘው ዶማ ጉድጓድ ቆፍሮ ቀበረውና በአካፋው አፈሩን ደፍኖ ማንም ያላየው መስሎት አካፋና ዶማውን ይዞ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ሰውዬው ባየው ነገር ደንግጦ ወደ ቤቱ ተመለሰና እየተንቀጠቀጠ ወደ መኝታ ቤቱ ሲገባ ሚስቱ አየችውና ጠየቀችው፣ "ምን ሆነህ ነው የምትንቀጠቀጠው?" "ያየሁትን ነገር ብነግርሽ አታምኝኝም" "ምን አየህ?" "ይሄ ክፉው ጎረቤታችን እነዚያ የጠፉብንን አካፋና ዶማ እሱ ነው ለካ የሰረቃቸው" ባሻዬ! ስንት ከባድና አስጨናቂ ጉዳይ ባለበት አገር ላይ ስለ አካፋና ዶማ ከሚያስብ ሰው ጋር እንዴት ተግባብቶ መኖር ይቻላል? ለመሆኑ የአገራዊ ምክክሩ ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ ደርሶ ይሆን?

  • 5 авг.6 26645

    ቱርክ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ታሪካዊውን አል-ነጃሺ መስጂድ ዕድሳት አጠናቀቀች የቱርክ ዓለም አቀፍ ትብብር እና ቅንጅት ኤጀንሲ (ቲካ) በኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል የሚገኘውን ታሪካዊውን አል-ነጃሺ መስጂድ እና በቅጥሩ የሚገኙ መቃብራት ዕድሳት ማጠናቀቁን አስታውቋል። የቱርክ ኤጀንሲ በመግለጫው እንዳመላከተው ፕሮጀክቱ፦ የጋራ ባህላዊ እሴቶችን ለማስፋፋት እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ተከናውኗል፡፡ ወደ መስጂዱ የሚያመራውን እና "የሶሃባዎች መንገድ" የሚባለውን የእግር መንገድ ማሻሻያ አካቷል። ታሪካዊ ስፍራውን ለጎብኚዎች ምቹ ያደርጋል፡፡ አካባቢውን የሆቴል፣ የንግድ እና የሙዚየም መሠረተ ልማቶችን በማሳደግ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ያጠናክራል። ውቅሮ አቅራቢያ የሚገኘው አል-ነጃሺ መስጂድ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው መስጂድ እንደሆነ ይነገራል፡፡

  • 4 авг.6 68826

    ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ መታሰራቸው ተሰማ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ በመስጠት እና በፓርቲ ፖለቲካ የሚታወቁት አቶ አበበ በትናንትናው ዕለት መታሰራቸውን የቤተሰብ ምንጮች ለአንዳፍታ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ ፖለቲከኛው በምን ምክንያት እንደታሰሩ ያልታወቀ ሲሆን፤ ባሁኑ ሰአት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ እንደሚገኙም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡ @Ankuar_mereja @Ankuar_mereja

  • 2 авг.6 465142

    በአማራ ክልል የ 8 ኛ ክፍል ዉጤት ተለቆል፡፡ እየተመለከታችሁ ነዉ

  • 1 авг.8 290489

    በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በትግራይ ሀይሎች መካከል በሜካናይዝድ የተደገ ከባድ ዉጊያ ተቀስቅሷል ፡፡ ዝርዝር አለን

  • 1 авг.8 3121044

    #ኢትዮጵያ_ምትባለው_ሀገር_የታለች??? ይሄ ጎብኚ ከአዘርባጃን የመጣ ቱሪሥት ነው!! በጣም ብዙ ሀገር ጎብኝቻለሁ ኢትዮጵያ መጥቼ በጣም የተገረምኩበት ነገር ትግራይ ስሄድ በየቦታው የትግራይ ባንድራ ብቻ ነው ሚውለበለበው አንድም ቦታ የኢትዮጵያ ባንድራ አላየሁም ፣ አፋር ስሄድ የአፋር ባንድሬ ነው ሚውለበለበው በእኔ ሀገር አዘርባጃን ከአገሪቱ ዋናው ባንድራ ውጭ መሥቀል በፍፁም የተከለከለ ነው! ብሎ ሁሉም ክልሎች የራሣቸው ባንድራ ከሰቀሉ ኢትዮጵያ ምትባለው ሀገር የት አለች ብሎ እየጠየቀ ነው!! እስኪ መልሱለት!!!

  • 30 июл.7 480164

    🔶ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነው በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነው ተብሏል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዋሲሁን በላይ ይህ ግብር በተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ የሚጣል ሲሆን፥ተሽከርካሪዎቹ በመንግስት በተገነቡ መንገዶች ላይ ስለሚንቀሳቀሱ በየዓመቱ የሚከፈል ይሆናል ብለዋል። ይህም ከመደበኛው የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ወይም ቦሎ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ግዴታ ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ እንደገለፁት፥ግብር አጣጣሉም እንደ ተሽከርካሪዎቹ ዓይነትና እንደሚያመነጩት ጭስ (ካርቦን) ሊለያይ እንደሚችል ተናግረዋል። ይህ ማለት ብዙ ጭስ የሚለቁ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ አዳዲሶች ደግሞ ዝቅተኛ እንዲከፍሉ ሊደረግ ይችላል ተብሏል። ይህ አሰራር በሌሎች አገራት ለምሳሌ በኬንያ፣ በሩዋንዳና በአውሮፓ አገራት የተለመደ ሲሆን፥መንግስት ለመንገድ ጥገና የሚውል ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ያስችለዋል። ግብሩ በከተሞችና በክልሎች የሚሰበሰብ በመሆኑ የአካባቢ መስተዳድሮች የራሳቸውን የልማት በጀት እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕድል ስለሚፈጥርላቸው በፌዴራል መንግስት ላይ ያለውን የገንዘብ ጫና ይቀንሳል። ይህ የታክስ ፕሮፖዛል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ  ለምክር ቤቱ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ አቶ ዋሲሁን አክለዉም ዝርዝር ደንቦችና መመሪያዎች ወጥተውለት ወደ ተግባር እንደሚገባና የኢኮኖሚው የገቢ ምንጭ እንደሚሆን እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ከዚህ ግብር የሚገኘው ገቢ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት 0.2 በመቶ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል። ©️Ethio fm 107.8

  • 27 июл.8 20391

    ሰበር:ከኤርትራ የተሰማዉ ጥብቅ መረጃ https://youtu.be/FF5yH7KGkXU?si=Nl7HPtW7DD21arnI

  • 25 июл.9 5312

    በአሁኑ ሰዓት በመዲናችን አዲስ አበባ አሪፍ ና ጥሩ ኑሮ ለመኖር የወር ገቢ ቢያንስ ስንት መሆን አለበት ብላችሁ ታስባላችሁ ግን ?

  • 25 июл.10,8 тыс545

    ምክክሩ ቀጥሏል። የምክክሩ አንድ ተወያይ የአስተዳደር ክልሎች የወንዞች ተፋሰስን መሠረት አድርገው ከታች በምስሉ ባለው መልክ ቢካለሉስ? ብለው ሃሳብ አቅርበዋል። እናንተስ ምን ትላላችሁ?

  • 23 июл.9 442141

    ጄነራል ታደሰ ወረደ ወዴት ተሰወሩ? የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በመቀሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መሰወራቸው ተሰማ። እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ መኖሪያ ቤታቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቅና በጥበቃ ተሽከርካሪዎች የተከበበ የነበረ ቢሆንም፣ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ ግን አብረዋቸው የነበሩ ጥበቃዎችና ሰራተኞች ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል። ጄነራሉ ከጥቂት ቀናት በፊት ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር እንዳይገናኙ በትግራይ ጸጥታ ቢሮ ተከልክለው እንደነበርና ቤተሰቦቻቸውም ስለ ደህንነታቸው ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ይታወቃል። ጄነራል ታደሰ ወረደ በፌደራል መንግሥት ዳግም በተሾሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሕወሓት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የሚታወስ ነው። ከኃላፊነታቸው ከመነሳታቸው በፊትም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ለመገልበጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ክልሉን ወደ አዲስ ጦርነት እንደሚያስገባ አስጠንቅቀው ነበር። በአሁኑ ወቅት በሕወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው የፖለቲካ ውጥረት በጨመረበት ሁኔታ፣ የጄነራሉ ከአካባቢው መሰወር በትግራይ ክልል አዲስ የጸጥታ ስጋት ደቅኗል።

  • 23 июл.7 08926

    ጎበዝ የ አይኤሜፍ ኢኮኖሚያዊ አገዛዝ እንዴት እያደረጋችሁ ነው ግብርስ እንዴት ነው

  • 22 июл.8 397101

    ጄ ኤፍ ኤም ከስርጭት ታገደ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጄኤፍኤም (JFM) 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ በሚደረግ ስልጣን ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ከስርጭት ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ መወሰኑን ኖር ሬድዮ ሰምቷል። ባለሥልጣኑ ውሳኔውን ያሳለፈው በጣቢያው ላይ ባደረገው የይዘት ክትትልና በአካል ተገኝቶ ባከናወነው የኢንስፔክሽን ምልከታ በርካታ የሕግና የፈቃድ ውል ጥሰቶችን በመለየቱ እንደሆነ ገልጻል። የሀገራዊ ይዘት ግዴታን አለመወጣትና የብሮድካስት አዋጅ ጥሰቶች እንዲሁም በፈቃድ ውሉ መሠረት አለመስራቱ እና በተደጋጋሚ የተሰጡ የቃልና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያዎችን አስተካክሎ አለመገኘቱ ተጠቅሰዋል። በዚህም መሠረት በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ጣቢያው በፈቃድ ውሉ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች አሟልቶ እስኪገኝ ድረስ ለ6 ወራት ከስርጭት እንዲታገድ ተወስኗል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለእግድ ጊዜው ለጣቢያው የተመደበውን 106.7 ኤፍ ኤም ፍሪኩዌንሲ (Frequency) ጥቅም ላይ ማዋል እንደማይቻል ማሳሰቢያ የሰጠ ሲሆን፣ የሬዲዮ ጣቢያው ለሕግ ተገዢ በመሆን ስርጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

  • 22 июл.6 81110

    ከ9ሺህ 490 በላይ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት አሰራር ስርዓት አተገባበር እና አፈጻጸም ውጤታማነት ላይ ባከናወነው የኦዲት ሪፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 9ሺህ497 የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ያሉበትን ሁኔታ እንደማያውቅ ገልጿል። አሐዱ በተመለከተው የኦዲት ሪፖርት ሰነድ ላይ እንደሰፈረው ከ 2015 እስከ 2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 165 ሺህ 852 የሽያጭ መመዝገቢያዎች ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ 147 ሺህ 963 የሚሰሩ፣ 10 ሺህ 145 የተበላሹ ሲሆን ቀሪዎቹ 9ሺህ 497 የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ግን ያሉበት ሁኔታም ሆነ አድራሻቸው የማይታወቅ መሆኑ ተጠቅሷል። የትኞቹ ማሽኖች ስራ ላይ እንዳሉ፣ ከሲስተም እንደወጡ እና የማሽኖቹም አድራሻ ምን እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ለማወቅ የሚያስችል በቴክኖሎጂ የተደገፈ መቆጣጠሪያ የአሰራር ስርዓት አለመኖሩ ለችግሩ አንዱ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። በኦዲት ግኝቱ ላይ በጽሑፍ ምላሽ የሰጠው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግብር ከፋዪች ከ 3 ዓመት በላይ ግብር ሳያሳውቁ ሲቀሩ በተደረገ ክትትል በተመዘገቡበት አድራሻ ሊገኙ እንዳልቻሉ ገልጾ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራቸው ወደ ዘላቂ ማቆያ ወይም አርካይቭ እንዲገባ መደረጉን አስታውቋል። ገቢዎች ሚኒስቴር አክሎ ማሽኖቹ ያሉበትን ቦታ በጂ ፒ ኤስ ለማወቅ የሚያስችል አሰራር ባለመኖሩ አድራሻቸው የጠፋ ማሽኖች ህገ ወጥ ደረሰኝ እንዳያትሙ ለማድረግ ሲስተም ላይ እንዲዘጉ መደረጉን ገልጿል። በተጨማሪም ከእነዚህ ማሽኖች የሚወጡ ደረሰኞች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ለሁሉም ቅርንጫፎች ፣ ክልሎች እና ከተማ መስተዳደሮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በደብዳቤ ማሳወቁን ጠቁሟል። በገቢዎች ሚኒስቴር ምላሽ ላይ አስተያየት የሰጠው የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች ህገ ወጥ ደረሰኝ የሚጠቀሙ ፣ ያለደረሰኝ የሚሸጡ እና ዜሮ ሪፖርት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን ለመከላከል የሚያስችል ዘመናዊ የቁጥጥርና አሰራር ስርዓት አለመዘርጋቱ በኦዲት ለታዩ ክፍተቶች ምክንያት መሆኑን ጠቅሷል። በዚህም የግብር ከፋዮችን የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ የሚሰበሰቡ መረጃዎች በተቀናጀ መልኩ ለግብር አወሳሰን በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጥቅም ላይ እንዲውል አለመደረጉ እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖች ዕለታዊ የግብይት መረጃዎች ወደ መረጃ ቋት የማይላኩ በመሆኑ የገቢ ስወራ እንዲበራከት ሊያደርግ ይችላል ሲል ማሳሰቡ በሪፖርቱ ተገልጿል። አሃዱ ሬዲዮ

  • 21 июл.6 47020

    ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ፌዴራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ጥሎታል ያሉትን "ከበባ" ለመስበር የሚያስችሉን አስተማማኝ "የውጭ አጋሮች" አሉን በማለት ተናገሩ፡፡ በኃይል ሥልጣን የያዘውን የክልሉን አስተዳደር የሚመሩት ደረጽዮን ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ክልሉ የተጣሉበትን "ዘርፈ ብዙ ክልከላዎች" ለመስበር "በስትራቴጂክ ደረጃ" የሚሠሩ "የውጭ አጋሮች" አሉት ብለዋል፡፡ ደብረጽዮን "የውጭ አጋሮች" ያሏቸውን አካላት ግን በስም አልጠቀሱም፡፡ ትግራይ አሁን ባለው ሁኔታ መቀጠል ስለማትችል ራስን የመከላከል አቅምን ማጠናከር ላይ ትኩረት ለማድረግ ተገደናል ያሉት ደብረጽዮን፣ የክልሉን ታጣቂ ሃይል በማጠናከር የዓለማቀፉን ኅብረተሰብ ትኩረት ማግኘት ችለናል በማለትም አክለዋል፡፡

  • 20 июл.6 688241

    ‹‹በኤሌክትሪክ ክፍያ ላይ የታየው ለውጥ አዲስ ጭማሪ ሳይሆን ቀድሞ የተወሰነ ማስተካከያ ሂደት ነው››-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ በደንበኞች ላይ የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ ክፍያ ቀደም ሲል በስትራቴጂው መሠረት የተወሰነ መሆኑን አስታዉቋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሽያጭና ደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ይኸይስ ስዩም ለኢትዮ ኤፍኤም 107.8 እንደገለጹት፤ በ2017 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ የተጀመረው የታሪፍ ማሻሻያ የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ በ24 የሩብ ዓመታት ተከፋፍሎ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ይህ የታሪፍ ማስተካከያ ተቋሙ ከአራት ዓመት በኋላ የሚሰበሰበውን አጠቃላይ ክፍያ በመስከረም 2017 ዓ.ም ላይ በአንድ ጊዜ ማስከፈል የነበረበት ቢሆንም፣ የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅም ታሳቢ በማድረግ በጥቂት በጥቂቱ ከፋፍሎ እንዲከፍል የተዘረጋ ስትራቴጂ ነው በማለት ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያለው ታሪፍ ዝቅተኛውን የኅብረተሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ ለመደገፍ የመንግሥት ድጎማ የሚደረግበት ነው ያሉ ሲሆን፣ እስከ 50 ኪሎ ዋት ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት 96 ሳንቲም ብቻ እንዲከፍሉ እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል። ዶ/ር ይኸይስ አክለውም፤ እስከ 2መቶ ኪሎ ዋት የሚጠቀም ማንኛውም ደንበኛ በትክክለኛው የታሪፍ ዋጋ ሳይሆን በድጎማ እንዲከፍል እየተደረገ ነው ብለዋል። ደንበኞች በአንድ ወር ውስጥ በተደጋጋሚ ኃይል ሲገዙ ስለሚገጥማቸው የዋጋ ልዩነት ሲያብራሩም፤ የዋጋ አተማመን ሥርዓቱ በ30 ቀናት ውስጥ የተጠቀሙትን አጠቃላይ የኃይል መጠን በአንድ ላይ ደምሮ ስለሚያሰላው የኪሎ ዋት መጠኑ ሲጨምር ታሪፉም አብሮ እንደሚጨምር አስገንዝበዋል። ይህንን ሁኔታ ተከትሎ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ተቋሙ በየክፍለ ከተማው ከነዋሪዎች ጋር ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን እያደረገ ሲሆን፣ ባለፉት 15 ቀናት ውስጥም ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለሚዲያ አካላት ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል። ኢትዮ ኤፍ ኤም

  • 18 июл.7 39635

    ጎጃም ደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው፡፡