- Последний пост
- 22:10
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 21
- Всего постов
- 37
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 295
- 1/48двое суток
- 338
- 1/72трое суток
- 364
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ እና 5ኛ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ለአምስት ወር በጋራ ሲስለጥኑ የነበሩ ምልምል የሰራዊት አባላት በዛሬዉ ዕለት ተመረቁ! በአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ (15ኛ ኮር 45ኛ መብረቅ ክፍለጦር) እና በ5ኛ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ (1ኛ አፄ ዘርያቆብ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለጦር) አዘጋጅነት ለተከታታይ አምስት ወራት የቆየውን ወታደራዊ ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ምልምል የፋኖ አባላት በዛሬው ዕለት ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመርቀዋል። በዚሁ የምረቃ መርሐግብር ላይ የምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር አርበኛ አማረ አያሌው፣ የዕዙ ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሐጅ ኑረዲን አበበ ሐሰን፣ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርያቆብ ኮር ሎጀስቲክስ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ጌታሁን ቦጋለ፣ በፍቃዱ በላይ ክፍለጦር ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ በላቸው እሸቴ፣ የ45ኛ መብረቅ ክፍለጦር አዛዥ አርበኛ ሃጂ ንጉሴ ሃሚድ፣ የ45ኛ ክፍለጦር ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ በቃሉ አስማማው (ቼኩቬራ) ጨምሮ ሌሎች የኮርና የክፍለጦር አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል። በመርሐግብሩ ወቅት ንግግር ያደረጉት ተጋባዥ እንግዶች ተመራቂዎች የተሸከሙትን የትግል አደራ እና የተሰው ጓዶቻቸውን መስመር ጠብቀው፣ በቀጣይ ለሚገጥሟቸው ማንኛውም ዓይነት ተግዳሮቶች ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል። ተመራቂዎቹ በበኩላቸው ላለፉት አምስት ወራት ከቀሰሙት ተግባራዊና ፅንሰ-ሀሳባዊ ወታደራዊ ትምህርት በመነሳት ለክብር እንግዶቹ የሚመጥን ወታደራዊ ትርኢት አቅርበዋል። በተጨማሪም የተሰው ጓዶቻቸውን አደራ በመጠበቅ፣ ለአማራ ሕዝብ ሕልውና መከበርና ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ የተጣለባቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት ቃል-መሐላ በመፈጸም መርሐግብሩ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ወሎ ቤተአማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ! ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም
без подписи
ከቀኜ የውስጥ አርበኞች ንቅናቄ፤ አዲስ አበባን አስመልክቶ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ! ነሐሴ 10/ 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ በታሪክ፣ በሕግም ሆነ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የኗዋሪዎቿና የአማራ ነባር ርስት መሆኗ ይታዎቃል። ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካዊያን መሰባሰቢያና የዓለም ሀገራት የዲፕሎማሲ ማዕከል ናት። ይሁን እንጂ፣ እኛ የቀኜ የውስጥ አርበኞች ንቅናቄ አባላት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጋር አብሮ ለመኖር ባለን ፅኑ ፍላጎት የተነሳ አዲስ አበባ የሁላችንም ናት በሚል እጅግ ለዘብተኛ አቋም፣ ኦህዴድ ብልጽግና የተሸከመውን የ "ኬኛ" መንፈስ ትቶ፣ እንዲሁም ሌሎች በአዲስ አበባ ጉዳይ ቅሬታ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የአዲስ አበባን የጋራ መኖሪያነት እንዲቀበሉና ከሁሉም ጋር ወደ ስምምነት ለመምጣት ብርቱ ጥረት አድርገናል። በዚሁ መሰረትም፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሚባል መልኩ ሐሳባችንን በመደገፍ ለእኩልነት፣ ለአንድነትና ለጋራ ተጠቃሚነት ያላቸውን ፍላጎትና አቋም አሳይተዋል። አገዛዙ እያካሄደ ባለው የይስሙላ ምክክር እንኳን አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊያንና የኗዋሪወቿ የአንድነት ከተማ እንጂ የአንድ ወገን እንዳልሆነች ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡና በይስሙላው ምክክር የሚሳተፉት ተስማምተው እንደነበረ ንቅናቄያችን በውስጥ አርበኞቹ በኩል ለማወቅ ችሏል። ይሁንም እንጅ፣ በምክክሩ የሚሳተፉ አካላት ውሳኔያቸው ከላይ የጠቀስነው ቢሆንም፣ ይህ የስምምነት ውሳኔ በማን አህሎኝነት ከአገዛዙ አለቃ፣ አብይ አህመድ በወረደ ትዕዛዝ ተሽሮ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ ሆና፤ በክልሉ ፍቃድ ተመስርቶ ልዩ ጥቅም እየከፈለ፣ የፌደራል መንግስቱም ዋና መቀመጫ እንዲያደርጋት የሚል ውሳኔ ተላልፏል። ይህንን ውሳኔ በማይቀበሉት የአገዛዙ የይስሙላ ምክክር ተሳታፊዎችና ታዛቢዎች ላይ የአብይ አህመድ ቡድን እጅግ ከፍተኛ ወከባ፣ እንግልትና ማስፈራሪያ እያደረሰባቸው መሆኑንን ንቅናቄያችን ባደረገው ማጣራት ለማወቅ ችሏል። ቀኜ የውስጥ አርበኞች ንቅናቄ፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የአገዛዙን የማጭበርበር፣ የክህደት፣ የስግብግብነት፣ የጠቅላይ አስተሳሰብ ዕቅድና አውዳሚ አካሄዶችን ይበልጥ ያጋለጠበትና የተገነዘበበት ወሳኝ መድረክ መሆኑን አረጋግጧል። በተመሳሳይ ንቅናቄያችን የኦህዴድ ብልፅግናን አውዳሚ ትዕዛዝና ውሳኔን አልቀበልም በማለት ለአንድነት፣ ለእውነትና ለእኩልነት የቆሙ የሌሎች ነገዶች (ብሔሮች) ተወካዮችን፣ ዛቻና ማስፈራሪያዎችን እያደረሰባቸው መሆኑን አጣርተናል። እንደ አዲስ አበባ ጉዳይ ያሉ ግዙፍና ውስብስብ የፖለቲካ ቁምነገሮችን የመረዳት አቅም የሌላቸው ተላላኪ አማራዎች፤ ከኦህዴድ ብልፅግና ጉምቱ ባለስልጣናት እኩል፣ በይስሙላ ምክክሩ የሚሳተፉ አካላትን አቋማቸውን ለማስቀየር ሲያንገራግሩና ሲያዋክቡ እንደቆዩ ንቅናቄያችን ባደረገው ማጣራት ለመለየት ችሏል። በማረፊያ ቦታቸው ሁሉ ሳይቀር የታጠቁ የደኀንነትና የጸጥታ አካላትን እየላኩ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲፈጽሙ እንደቆዩ በውስጥ አርበኞቻችን በኩል ለማወቅ ችለናል። በአዲስ አበባ ጉዳይ የእነ አብይ አህመድን ውሳኔ የማይቀበሉ ተብለው የተለዩ አካላትን ሁሉ በተለያየ ሰበብ ለማሰርና በህይዎታቸው ላይ ሁሉ ሳይቀር እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅታቸውን እንደጨረሱ ቀኜ የውስጥ አርበኞች ንቅናቄ መረጃው ደርሶታል። በመሆኑም፣ ቀኜ የውስጥ አርበኞች ንቅናቄ፣ በአዲስ አበባ ጉዳዩ የአገዛዙን ሰልቃጭ እንቅስቃሴ ከገመገመ በኋላ የሚከተለውን አቋም ወስዷል፦ 1) የአዲስ አበባን ጉዳይ፣ አንዱ የህልውና ትግሉ አስኳል ክፍል በማድረግ ተቀብለነዋል። አዲስ አበባ በታሪክ፣ በህዝብ ስብጥርና በሕግ የአማራ ህዝብ ርስት ብትሆንም በብዙ ታሪካዊ ሂደቶች የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ከተማ እየሆነች መጥታለች። በመሆኑም፣ ከዚህ ሀቅ በተቃራኒ ከኗዋሪዎቿና ከመላው ኢትዮጵያውያን ፈቃድና ፍላጎት ውጭ በኃይል የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ናት ተብሎ የተላለፈውን ውሳኔ በጽኑ እናወግዛለን። 2) "ብሔራዊ ምክክር" ተብሎ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ግርግር፣ በሂደቱም ሆነ በውጤቱ በአብይ አህመድ የሚዘወርና የይስሙላ ጉባዔ መሆኑን በተጨባጭ ንቅናቄያችን በውስጥ አርበኞቹ በኩል ስላረጋገጠ ተቀባይነት የሌለውና እንዳልተደረገ የሚቆጠር ፈራሽ ነው ብለናል። 3) የአገዛዙን የይስሙላ "ምክክር" ለማጋለጥ ንቅናቄያችን በውስጥ አባሎቻችን በኩል ያደረገውን ተጋድሎና ሌሎች ነገዶች (ብሔሮች) ያደረጉት ተጋድሎ፤ በዝርዝር ተሰንዶ ለታሪክ እንዲቀመጥና በተገቢው ጊዜ ደግሞ ይፋ እንዲደረግ ወስነናል። 4) የኦህዴድ ብልፅግናን ጠቅላይ አካሄድ ንቅናቄያችን ውስጥ ድረስ ሰርጎ በመግባት በማጋለጡና ላልተረዱት አካላት ግልፅ ማድረጉን ተከትሎ፣ ሁሉም በአገዛዙ ስር የሚገኙ አመራሮችና አባላት ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ለንቅናቄያችን በርካታ የአባልነት ጥያቄዎችን እያቀረቡ በመሆኑ የትግላችንን ቀጣይ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከአፋብን በቅርቡ ለሚወርድልን ትዕዛዝ ዝግጁ ሆነን እንድንጠብቅ ወስነናል። 5) በኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ ስር በኃይል ታፍናችሁም ሆነ በፈቃዳችሁ በየደረጃው የምትገኙ የንቅናቄያችን ደጋፊ ፣የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አመራርና አባላት፣ የአገዛዙን ፀረ-አማራነት ተገንዝባችሁ በያላችሁበት ሆናችሁ ትግሉን እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርባለን። 6) መላው ህዝባችን፣ የአዲስ አበባ ናዋሪዎችና ሁለም ኢትዮጵያውያን የኦህዴድ ብልፅግናን አረመኔያዊ አገዛዝ ተረድታችሁ በተባበረ ትግል በጋራ እንድናስወግደው ንቅናቄያችን ጥሪ ያቀርባል። 7) የአዲስ አበባን የጋራ ከተማነት ጉዳይ አስመልክቶ ናዝሬት ከተማ ላይ በሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች (ብሔሮች) የብልፅግና አመራሮች የተላለፈውን የጋራ ውሳኔ አብይ አህመድ በራሱ ስልጣን ሽሮ፤ በኦሮሚያ ክልል ስር እንድትካተት የሰጠው ትዕዛዝ የአገዛዙን ዓያን ያወጣ አጭበርባሪነት የሚያሳይ መሆኑን ተረድታችሁ የቀኜ የውስጥ አርበኞች ንቅናቄን በህቡዕ የውስጥ አደረጃጀት በኩል በፍጥነት እንድትቀላቀሉ ጥሪ እያቀረብን ለዚህ ደግሞ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እናደርጋለን። ቀኜ የውስጥ አርበኞች ንቅናቄ!!!
без подписи
без подписи
"በአዲስ አበባ ከተማ እና ነዋሪወቿ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል" ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ! ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም ዘረ ፈጁ የብልፅግና አገዛዝ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል ስም በኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂደው የድራማ መድረክ የህዝብ ውክልና የሌለበት፣ ተጨማሪ ቀውስ የሚያዋልድ እና የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የተነደፈ የአረመኔው አገዛዝ የፖለቲካ አሻጥር መሆኑን ከዚህ በፊት ባወጣነው መግለጫ አቋም መውሰዳችን ይታወቃል። ሆኖም ግን አገዛዙና አጋሮቹ ይህንን ከጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ ያቀረብንላቸውን ጥሪ በመተው ''በምክክር'' ስም የከተሞችንና አካባቢዎቻቸውን የታሪክ፣ የዴሞግራፊ፣ መልክአምድራዊና የይዞታ ቅርፃቸውን ለማዛባትና በተለይም ነባር የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችንና የአማራን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የጥፋት መንገድ ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል። አዲስ አበባ ከተማ እንደገና ከመቆርቆሯና ከአሁኑ መጠሪያዋ ቀደም ብሎ ''በራራ'' በመባል የምትታወቅ፣ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በጦርነት ሳቢያ እስከወደመችበት ጊዜ ድረስ የአማራ ነገስታት መቀመጫና የአማራ ህዝብ ጥንተ-ርስት እንደሆነች የታሪክ መዛግብትና አርኪዮሎጂያዊ ማስረጃዎች በግልፅ ያረጋግጣሉ። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል አዲስ አበባ ከተማን በድጋሚ ሲቆረቁሯት፣ ባዶ መሬት ላይ ሳይሆን የአባቶቻቸውን ታሪካዊ ይዞታ፣ ርስትና ውርስ መነሻ በማድረግ ነው። ይህ ታሪካዊ እውነት ሊሸረሸርም ሆነ ማንም አምባገነናዊ አገዛዝ በጊዜያዊ ስልጣን ህዝብ ባላመነበት ፖለቲካዊ ውሳኔ ሊሰርዘው የማይችለው ፅኑ የታሪካችን አንድ አካል ነው። ከተማዋ የአማራ ጥንተ-ርስት መሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሂደት የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ መኖሪያ፣ የባህልና የኢኮኖሚ ማዕከል፣ እንዲሁም የአንድነት ተምሳሌት ሆና ተገንብታለች። ከዚህ አኳያ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መናገሻና የዓለም አገራት የዲፕሎማሲ ማዕክል መሆኗን ሙሉ በሙሉ ያምናል፤ ይቀበላልም። በዚህ መነሻ፣ ከተማዋ የብዝኃነትና የጋራ እድገት ማዕከል እንጂ የአንድ ዘረ ፈጅ አገዛዝ ብቸኛ መጫወቻ ስፍራ ልትሆን እንደማትችልም ድርጅታችን ያረጋግጣል። የአማራ ህዝብ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገሪቱ በስፋት በሚኖርባቸው አካባቢዎች፤ ፍትሐዊ የስልጣንና የሀብት ተጠቃሚነቱ መረጋገጥ እንዳለበት ድርጅታችን ያምናል። በአሁኑ ወቅት፣ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ አዲስ አበባን በብቸኝነት የአንድ ወገንና ብሔር በበላይነት እንዲቆጣጠራት ለማስቻል የሚሰራው ሕግን የጣሰ፣ የዴሞግራፊና የጂኦግራፊ ለውጥ በምንም መልኩ ሕጋዊ፣ ሞራላዊ፣ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን። አገዛዙ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል የፖለቲካ ሽፋን በከተማዋ ላይ የሚያካሄደው ሴራና አሻጥር የከተማዋን ነባር ኗዋሪዎች መብት የሚጥስ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያነቷን የሚክድና ታሪካዊ እውነታውን ለማዛባት የተሸረበና የአንድ ቡድን የበላይነትን በህዝባችን ላይ በኃይል ለመጫን ያለመ በመሆኑ፣ የዚህን አምባገነን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር መላው የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንዲያወግዙት፣ እንዲቃወሙትና እንዲታገሉት በድርጅታችን አፋብን ስም ጥሪ እናቀርባለን። እንዲሁም በከተማዋ ቀደም ብለው ይኖሩ የነበሩትም ይሁን አሁንም የሚኖሩት 80 በመቶ ( በ1999 ዓ.ም በተካሄደው ህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት) የሚሆኑት ነባር ኗዋሪዎች አማራዎች ናቸው። በመሆኑም የህዝብ ስብጥርንም ሆነ ታሪካዊ እውነታን በኃይልና በተሳሳተ ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመቀየር የሚደረገውን ማንኛውም የአገዛዙን ሴራ አጥብቀን የምንታገለው መሆኑን እንገልፃለን። የአማራ ህዝብ በገዛ አገሩ ከገጠመው ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ ባሻገር ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የትጥቅ ትግል ውስጥ ለመግባት ካስገደዱት ምክንያቶች መካከል፦ በአዲስ አበባ ከተማ በአገዛዙ የተደቀነው የዴሞግራፊ ለውጥ አደጋ፣ የከተማዋን ቀደምት ባለቤቶችና ነባር ኗዋሪዎች በማፈናቀልና ማንነታቸውን በማጥፋት፣ የአማራ ህዝብ ከከተማዋ ጋር ያለውን ታሪካዊ እና ማህበራዊ ትስስር በመበጣጠስ ከህዝቦች ተፈጥሯዊ መስተጋብር ውጭ በሆነ መልኩ የባህል፣ የቋንቋና የተለያዩ አመለካከቶችን በኃይል ለመጫን የሚደረገው ሩጫ ይገኝበታል። በመሆኑም፣ ድርጅታችን አፋብን ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ውስጣዊ አንድነቱንና አደረጃጀቱን ጠብቆ በመጓዝ፣ አምባገነኑና ከፋፋዩን አገዛዝ በጀመርነው ትግል ከስሩ ነቅለን በመጣል፣ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚስማማ፣ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያከብር ሥርዓተ መንግስት በመገንባት ፍትህ፣ እኩልነትና የሕግ የበላይነትን ከመትከል ባሻገር አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያና ዋና ከተማ፤ የአንድነትና የእድገት ማዕከል ሆና እንድትቀጥል ይታገላል። አገሪቱ ከገባችበት ጥልቅ የህልውና፣ የፍትህና የእኩልነት ቀውስ መውጣት የምትችለው የህዝቧን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በኃይል በማፈን፣ አገሪቱን የማያቋርጥ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በማስገባት ወደ ገደል እየመራት ያለውን ዘረ ፈጁን የብልፅግና አገዛዝ፤ በሕዝባዊ ትግል ሙሉ በሙሉ መገርሰስ ሲቻል ብቻ መሆኑን አፋብን በፅኑ ያምናል። በስተመጨረሻ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ በአዲስ አበባ ከተማና በህዝባችን ላይ በምክክር ስም የጠነሰሰው ዓይን ያወጣ የፖለቲካ አሻጥር የፈጠረው የህልውና በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
የአገዛዙ ጦር በመፍረስ የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ እና ጀኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦርን እየተቀላቀለ ይገኛል ! ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም የአማራን ህዝብ ማህበረ ፖለቲካ ስሪትን ለማጥፋት ቀን ከሌት የሚሰራው የብልጽግናው ስርዓት ባለፉት ሶስት ዓመታት ሁሉንም ፀረ ህዝብ ስራዎችን ሰርቷል። ስለሆነም እራሱን በታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ለማቆየት በስርዓቱ ላይ ያነጣጠረ ትግል ላይ እሚገኘው የአማራ ህዝብ ከውጊያ ባሻገር ስቦ በማስከዳት የዕዝ ሰንሰለቱን በማፍረስ ላይ ነው። ስለሆነም በተከታታይ ሁለት ቀናት የአገዛዙ መከላከያ እና አድማ ብተና አባላት አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር እና ጀኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። 1.ማሩ ይግዛው 2.አሻግረው ፈንታ 3.ዝናቤ መልኬ 4.ወርቁ ሲሳይ 5. ብሩክ አዝመራው ሲሆኑ ክፍለ ጦሮቹም ወታደራዊ ሥነ-ምግባርን የተከተለ መንገድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
የአደረጃጀት ዜና አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክፍለ ጦር ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ጥልቅ ወታደራዊና ፖለቲካዊ የግምገማ መድረክ በስኬት በማጠናቀቅ አጠቃላይ የመዋቅርና የአደረጃጀት ሪፎርም ማድረጉን ይፋ አድርጓል። ከታሪካዊው የጎንደር አንድነት ማግስት ጀምሮ የሰራዊቱን ወታደራዊ ዝግጁነት ከማሳደግ ባሻገር ህዝባዊ ደጋፍ መሰረቱን በማጠናከር ረገድ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየው ኮሩ ፣ የአሁኑ አደረጃጀታዊ ሽግግር የትግል ጉዞውን ወደ ላቀ የስልታዊና የተግባር ብቃት ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ስራ ሰርቷል ። ይህ ከፍተኛ የግምገማና የስራ አመራር መድረክ የዕዝ፣ የኮርና የክፍለ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን፣ በቆይታውም የሰራዊቱን ያለፉት ጊዜያት ኦፐሬሽናል እንቅስቃሴዎች፣ የውጊያ ብቃት፣ የአመራር ድክመቶችና ጥንካሬዎች በዝርዝርና በግልጽነት ተገምግሟል። በመድረኩ በተካሄደው ጥልቅ ሂስና ግለ-ሂስ መሰረት፣ ክፍለ ጦሩን በቀጣይነት ለላቀ ወታደራዊ ድል የሚያዘጋጁና የትግሉን ህዝባዊ አላማ በጽናት የሚያስፈጽሙ ብቁ አመራሮችን በጥብቅ መስፈርት በማወዳደር የመለየትና አዲስ የስራ ኃላፊነት የመስጠት ስራ ተከናውኗል። በዚሁ የመዋቅር ማሻሻያ መሰረት ባለፉት የትግል ዓመታት በወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ልምዳቸው፣ በፖለቲካዊ ብስለታቸው፣ በውጊያ ሜዳ መሪነታቸው፣ በከፍተኛ የስነ-ምግባር አርአያነታቸውና በትግል ጽናታቸው የላቀ አፈጻጸም ያሳዩ አመራሮች ወደ ፊት እንዲመጡና ክፍለ ጦሩን በበላይነት እንዲመሩ መድቧል። በመሆኑም:- 1) አርበኛ ክንዳለም መለሰ …… ዋና ሰብሳቢ 2) አርበኛ ዘመኑ ገብሬ (ባበይ ) …… ምክትል ሰብሳቢ 3) አርበኛ ሙሉቀን ሲሳይ …… ዋና ወታደራዊ አዛዥ 4) አርበኛ ፀዳሉ አበበ …… ምክትል ወታደራዊ አዛዥ 5) አርበኛ ፈለቀ ካሳሁን …… ዋና ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 6) አርበኛ ውበቱ ሞላ …… ምክትል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 7) አርበኛ አዳነ ማተቤ …… ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ 8) አርበኛ ፍቅሩ ባየ …… ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ 9) አርበኛ አሳፈው ሞሀበው …… ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ 10) አርበኛ አብርሃም አምበሉ …… ጽህፈት ቤት ኃላፊ 11) አርበኛ አንሙት ዋለልኝ …… ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ 12) አርበኛ በላይ አማረ …… ሎጂስቲክስ መምሪያ ኃላፊ 13) አርበኛ ታደለ ምሬ …… ስልጠና መምሪያ ኃላፊ 14) አርበኛ ጌታቸው ባየ …… አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ 15) አርበኛ መብሬ ደጀን …… ህዝብ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ 16) አርበኛ በቀለ በላይ …… ቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ኃላፊ 17) አርበኛ መምህር ፈንታሁን ገብሬ …… ግዥ መምሪያ ኃላፊ 18) አርበኛ ንጉስ ገላው …… የሰው ኃይል መምሪያ ኃላፊ 19) አርበኛ ደፋሩ አረጋ …… ኦርዲናንስ መምሪያ ኃላፊ 20) አርበኛ ቴዎድሮስ አስፋው …… ኦዲትና ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ 21.) አርበኛ አማን ዋሴ …… ጤና መምሪያ ኃላፊ 22) አርበኛ መልኬ ደስታ …… ** 23) አርበኛ ውብድል ካሴ …… ህግ እና ስነ-ምግባር መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተወድበዋል ሲል መረጃውን ያደረሰን የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ነው። ምንጭ፦በአፋብን በላይ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ዱርቤቴ ከተማ ታላቅ ድል ነሀሴ 9/2018ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር ቃኝ እና መሀንዲስ ወደ ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ሰርጎ በመግባት ልዩ ስሙ ጁፊ ባታ ላይ በእንቅስቃሴ ላይ በነበረ የአረጋ ከበደ መንበር አርጠባቂ ሚኒሻ እና አድማ ብተና ላይ በወሰደው የደፈጣ እርምጃ በአንድ ሲኖ ትራክ መኪና ተጭነው ሲንቀሳሱ የነበሩ የmላት አባት ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ። በዚህም አንድ ብሬን ከ 20 በላይ ክላሽ እና የቃታ መሳሪያ መማረክ የተቻለ ሲሆን ዱርቤቴ ሆስፒታል በዚህ ሰአት በkuስለኛ ተጥለቅልቋል ። ውጊያውን የ55ተኛ ክ/ጦር ዘመቻ ሀላፊ አርበኛ ስላባት አቤ በታላቅ ጀግንነት መርቶታል ።
የአውሮፓ ህብረት (EU) በኢትዮጵያ ያለውን አጠቃላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እክል እና የሽግግር ፍትሕ ሁኔታዎችን በጥብቅ እንዳሳሰበው ገለጸ! የአውሮፓ ህብረት (EU) እ.ኤ.አ በ2025 በዓለም ዙሪያ የነበረውን የሰብዓዊ መብቶች እና ዲሞክራሲ ሁኔታ አስመልክቶ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ ያለውን አጠቃላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የእርዳታ አቅርቦት እክል እና የተጠያቂነት ሁኔታዎችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል። በሪፖርቱ መሠረት፣ እ.ኤ.አ በ2025 በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱት ግጭቶች የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ሕግ (IHL) ጥሰቶች እንዲባባሱ ማድረጋቸውንና የሰብዓዊ ሁኔታው አሁንም እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ፣ የተከሰቱት ግጭቶች የተቸገሩ ማኅበረሰቦች ዘንድ ደርሶ አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት አደናቅፈውታል። በዚሁ ዓመት ውስጥ ከ90 በላይ የእርዳታ ሰራተኞች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን፣ አብዛኞቹ እገታዎች የተፈጸሙት በአማራ ክልል እንደሆነና ከእነዚህም መካከል ቢያንስ የአንድ እርዳታ ሰራተኛ ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። የአውሮፓ ህብረት የሀገሪቱን አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እና የጥበቃ ፍላጎቶች ለማሟላት ወደ 80 ሚሊዮን ዩሮ የሚጠጋ በጀት መመደቡንም አስታውቋል። በሌላ በኩል፣ በመስከረም 2025 በተካሄደው 60ኛው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት (HRC60) ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረት በ42 ሀገራት የተፈረመ የጋራ መግለጫ ያቀረበ ሲሆን፣ በመግለጫውም በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብቶች እና የሽግግር ፍትሕ ሂደት ላይ ያለውን ጥልቅ ስጋት መግለጹን አስታውሷል። የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛም በተጠያቂነት እና በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካላት፣ ከቀጠናዊ ድርጅቶች እና ከሲቪል ማኅበራት ጋር ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተጠቅሷል። ©ኢትዮ 251 ሚዲያ
የብልፅግና ባለስልጣናት በጋዜጠኞች ላይ የከፈተውን ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት እንዲያቆም ተጠየቀ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ)፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሽብር የተከሰሱ አምስት ጋዜጠኞች በይቅርታ ከእስር ለመውጣት በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስና ለጠፋው የሰው ሕይወት "ይቅርታ" እንዲጠይቁና "ኃላፊነት" እንዲወስዱ ግፊት እያደረጉ ነው በማለት ወቀሠ። ▪️ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ ▪️መምህርት መስከረም አበራ፣ ▪️ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፣ ▪️ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ▪️ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ “ራሳችን ጥፋተኛ አድርገን የይቅርታ ደብዳቤ አንጽፍም” ማለታቸውን ከጠበቃቸው መስማቱን ዓለምቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (CPJ) አሳውቀኧል። ጋዜጠኞቹ ፍርድ ቤት ውስጥ የካዱትን የወንጀል ክስ አሁን እንዲያምኑ ባለሥልጣናት እያስፈራሯቸው ነው ያሉት የቡድኑ የአፍሪካ ኃላፊ ሙቶኪ ሙሞ፣ ባለሥልጣናት ጋዜጠኞቹን ከማዋረድና እጃቸውን ከመጠምዘዝ እንዲቆጠቡ፣ ክሱን እንዲያነሱና ከእስር እንዲለቋቸው ጠይቀዋል።
አዲስ አበባ-የምክር ሒደቱ ሥጋት እንዳሳደረባቸዉ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ። አዲስ አበባ ዉስጥ በተያዘዉ አገራዊ ምክር ላይ የሚሳተፉ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክር ሒደቱ ቅሬታ፣ ጥርጣሬና ሥጋት እንደተሰማቸዉ አስታወቁ።እናት ፓርቲ (እፓ) ፣የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በየፊናቸዉ ባወጧቸዉ መግለጫዎችና ደብዳቤ እንዳሉት ምክክሩ እንዲሳካ ሒደቱ ሊታረም ይገባል። እናት ፓርቲና የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ቅሬታና ማሳሰቢያቸዉን በየፊናቸዉ ባወጡት መግለጫ ሲያስታዉቁ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በምክክር ሒደቱ ላይ ያለዉን ቅሬታ ለምክክር ኮሚሽን ለሶስተኛ ጊዜ በፃፈዉ ደብዳቤ መግለፁን አስታዉቋል። እናት ፓርቲ በመግለጫዉ የምንመካከረው "አዲስ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማዋለድ አይደለም" ሲል ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ሥጋት እንዳለው ገልጿል።በምክር ሒደቱ የአዲስ አበባ ከተማን ለአንድ ቡድን ለማስረከብ እና "አዲስ የፀብ ግንባር ለመቀስቀስ" ጥረት እንዳለ መታዘባቸውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሠይፈ ሥላሴ አያሌው ገልፀዋል።ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫ ደግሞ ሐገራዊ ምክክሩ እንዲሳካ «ሁሉም የበኩሉን ያበርክት" የሚል ጥሪ አድርጓል። የፓርቲው መግለጫ አክሎም "የምክክር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ የአንድ ወገንን ፍላጎትን በሌሎች ላይ ለመጫን ከሚደረግ ሙከራ መራቅ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በምክክር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከሚያደርጉ አፍራሽ ተግባራት መቆጠብ ያስፈልጋል።" በማለት አሳስቧል።
7/70 ክፍለ ጦር ወታደራዊ ቁመናውን በማዘመን ለሁለንተናዊ ድልና ለግዳጅ ራሱን በተሃድሶ አዘጋጀ!! ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም ጀብደኛው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ 7/70 ክፍለ ጦር ተቋማዊና ወታደራዊ ብቃቱን ይበልጥ የሚያጠናክርበትን ሰፊ የተሐድሶ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ አካሄደ። በሃይማኖት አባቶች ጸሎትና ቡራኬ የተከፈተው ይህ የተሀድሶ መርሃ ግብር የድርጅት፣ የዕዝ፣ የኮር እንዲሁም የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዕዙ ባህልና መዝናኛ ቡድን ያሸበረቁ አማራዊ ተውኔቶች ታጅቦ ተከናውኗል። ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል የዘነበበትን የመከራና የጭቆና ዶፍ ለመመከት የአማራ ህዝብ አምጦ የወለዳቸው እንቁ የዘመናችን የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል አንዱ የሆነው 7/70 ክፍለ ጦር፣ ህዝቡን ከመጥፋትና ከውርደት ታድጎ ወደ ታሪካዊ የክብር ማማ ለማሸጋገር ራሱን ለህዝባዊ አላማ አሳልፎ የሰጠ የትግል ግንባር ቀደም ኃይል ነው። ለ13ኛ ጊዜ በጠላት ወረራና በእሳት ከተቃጠለው የደም ምድርና ጽኑ ማህበረሰብ ተሰባስቦ የተደራጀ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል። በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ምድር በጀግንነት ታሪኩ የሚታወቀው፤ በመከራ ቀን እንደ ንብ የሚናደፍ ለመጣበት ጠላት የማይበገር የታሪካዊቷ የአጣዬ ምድር ፍሬና የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ጠበቃ ነው። ክፍለ ጦሩ በሂደት ያጋጠሙትን ውስጣዊ ክፍተቶች በመሙላት፣ በአዳዲስ አመራሮች ወታደራዊ ቁመናውን ለማዘመንና ለቀጣይ ድርጅታዊ ግዳጆች ራሱን በከፍተኛ ዝግጁነት አድሶ ተከስቷል። በዚሕ የተሐድሶ መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአፋብን ተ/ምክትል ሊቀመንበርና የፖሊት ቢሮ አባል አርበኛ መከታው ማሞ ባስተላለፉት መልዕክት፦ የትግሉን ቁርጠኝነት ገልጸው፤ "ሶፍት ላኩላቸው" ላሉን መንጋዎች፡ እኛ ደግሞ "ዳይፐር ላኩላቸው" ነው መልሳችን ሲሉ ገልፀዋል። በሌላ በኩል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሰብሳቢና የአፋብን ስራ አስፈጻሚ አባል አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ፦ "ትግላችን ግብን እንዲመታ መሰረታዊ ሀዲዱን ዘርግተን እየተጓዝን ነው" ሲሉ ገልጸዋል። እዲሁም የአሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ አማን እሸቱ በበኩላቸው የወታደራዊ ዝግጅትን ደረጃ በማጎላት "ራሳችሁን ለቀበሌና ለወረዳ ሳይሆን፣ ለመጨረሻው ታላቅ ግዳጅ አዘጋጁ" ሲሉ ለሰራዊቱ ወታደራዊ መመሪያ አስተላልፈዋል። በመጨረሻም የተሐድሶ መርሃ ግብሩ ባሕልና መዝናኛ ክፍል ባዘጋጃቸው ህዝባዊና ወታደራዊ ኪነት ደምቆ ውሏል። ክፍለ ጦሩ አዳዲስ አመራሮችን በመመደብ፣ ሕዝባቸውንና ሠራዊታቸውን በተጣለባቸው ኃላፊነት አመራሮቹ፡ በታማኝነት፣ በቁርጠኝነት፣ በቅንነት እዲያገለግሉ ቃለ-መሀላ በመፈፀም መርሃ ግብሩ ተጠናቋል። " ክብር ለትግሉ ሰማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የአምባገነኑና ዘረኛው ስርዓት ሠራዊት ያለውጊያ መበተኑን ቀጥሎበታል! ነሃሴ 07/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ያለ ምንም ጦርነትና መስዋዕትነት የአገዛዙን ጦር በመረጃና ደሕንነት እዲፈርስ ማድረጉ ታወቀ። የአማራን ሕዝብ ከዘር መጥፋት ለመታደግ ዋስ ይሆነው ዘንድ ድርጅት መስርቶ በአራቱም አቅጣጫ እየተዋደቀ የሚገኘው "የአፋብን" ሠራዊት የጠላትን ኃይልን በመቀበል ወደ ፋኖ እዲቀላቀሉ እያደረገ ይገኛል። በዚሕም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝን በጥቂት ቀናቶች በርካታ የስርዓቱ ጠባቂ ኃይሎች ከድተው እዲቀላቀሉ ለማድረግ ተችሏል። 1.ሀብታሙ ብርሀኑ--የሻለቃ መሪ አጃቢ 2.በለጠ አዳነ--ዶሽቃ ተኳሽ ➠2 ጥርጥር ክላሽ ➠230 ተተኳሽ ➠2ቦንብ ➠ 2 ትጥቅ 👉 ከ112ኛ አየር ወለድ ክ/ር --ወደ አፄ ምኒልክ ክ/ር 3.ም/፲ አለቃ ስመኝ ሙላቱ--መሰናክል አስወጋጅ 4.ም/፲ አለቃ ኤሊያስ ዳምጤ-- '' '' '' '' ➠2 ጥቁር ክላሽ ➠2 የደረት ትጥቅ ➠2ቦንብ ➠180 ተተኳሽ 👉 ከ605ኛ ኮር ኮማዶ ክ/ር--ወደ ራስ አበበ አረጋይ ክ/ር 5.ክንዱ ቸሩ ስናይፐር ተኳሽ 6.ይሳቅ ፈቃዱ ዶሽቃ ተኳሽ ➠3F1 ቦንብ ➠1 ሳንጃ(ጩቤ) 👉 ከ101ኛ አየር ወለድ ክ/ር 5ኛ ሻለቃ-ወደ አፄ ዳዊት ክ/ር 7.መሠረታዊ ወ/ር ኤልያስ ፀጋዬ(RSF) 8." " " ጊዜው የማታ(RSF) ➠2 ጥርጥር ክላሽ ➠ 4ቦንብ ➠2ትጥቅ ➠440 ተተኳሽ 👉 ከ112ኛ አየር ወለድ ክ/ር--ወደ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ክ/ር 9. ሁለት(2) ለደሕንነታቸው ስማቸው ያልተጠቀሱ ➠2ክላሽ ➠2ትጥቅ ➠3 ቦንብ ➠175 ተተኳሽ 👉 ከ111ኛ ኮማዶ ክ/ር--ወደ ሀ/ማርያም ማሞ ክ/ር ✔ በጠቅላላ፦ 10 =የሠራዊት አባል 8=ትጥቅ 14=ቦንብ 1025= ተተኳሽ 8= ክላሽኮቭ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አምደ ጽዮን ኮር ገቢ ማድረግ መቻሉን የኮሩ ሚዳያና ኮሙኒኬሽን አስታውቋል። " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ዙሪያ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ ሀገራችን እያለፈችበት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት በምክክር ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አገር ልትጸና ይገባል በሚል ጽኑ እምነት ፓርቲያችን የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምሥረታው፣ በኮሚሽነሮች አመራረጥና በኮሚሽኑ የአሠራር ሂደት፣ የአካታችነት ችግሮች፣ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች በሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖና መሰል አስቻይ ባልሆኑ ሁኔታዎች ላይ ጠንካራ ሀሳቦችንና የመፍትሔ ጥቆማዎችን ፓርቲያችን ሲያቀርብ መቆየቱም ይታወቃል። ፓርቲያችን በምክክሩ ሂደት እና ከምክክሩ አስቀድሞ ስኬታማ ምክክር ለማካሄድ ሊተገበሩ ይገባቸዋል ብሎ የሚያምንባቸውን ሃሳቦችና ቅድመ ሁኔታዎች በግልጽ አስቀምጦ ያለመታከት ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም ሰሚ ጆሮ በመጥፋቱ አገር ባለችበት ሁኔታ ወደ ምክክር እንድትገባ ተደርጓል። እናት ፓርቲ ይህን በትክክለኛው ጎዳና ተጉዞ በስኬታማ መልኩ ሊጠናቀቅ ቢችል የአገራችን መፃኢ ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችልን ሂደት ቅድመ ሁኔታዎች ስላልተሟሉ በማለት በቸልታ ሊመለከተው ያልፈለገ ሲሆን ይልቁን ሂደቱ ውስጥ በማሳተፍ ትክክለኛነቱን ካረጋገጠ ለአገር የሚበጁ ሀሳቦችን በማንሳት ለመሞገት ብሎም በተመካካሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ በጎ ተጽዕኖ መፍጠርን በማሰብ በምክክሩ እየተሳተፈ ይገኛል። አገር የገባችበት ችግር ከምንጊዜውም ይልቅ በተወሳሰበበት ሁኔታ ውስጥ የምክክሩ ሂደት ከነችግሮቹ እያነከሰ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ያለ ቢሆንም በሂደቱ የጎሉ ችግሮች እየተስተዋሉበት ይገኛል። ለአብነትም በወረዳ ደረጃ ተደረጉ ከተባሉ ምክክሮች ጀምሮ የምክክር ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና የሥርዓቱ ደጋፊዎች መሆናቸው ሲገለጽ የነበረ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ባለው በዚህ ምክክርም አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ተሳታፊዎች የገዥው ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች መሆናቸውን መረዳት ችለናል። በምክክሩ ሂደት ድምጾች እንዳይሰሙ መገደብ፣ የአካታችነት ችግሮች፣ የተሳታፊዎች ምርጫና ምደባ፣ የፍትሓዊነት፣ የገለልተኝነት፣ የግልጽነት ማነስ፣ በጸጥታ አካላት ታጅቦ መወያየት፣ የውይይት ተሳትፎውን ለማጥበብ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ ጫናና ወከባዎች፣ የምክክሩ አጠቃላይ ወለል ወይም ቀይ መሥመር ያለመኖር እና የመሳሰሉ ጉልህ ችግሮች የተስተዋሉበትን እውነታ ታዝበናል። ምክክሩ ኢትዮጵያን ለማጽናት ሳይሆን እንዳለፈው ጊዜ ስሑት ትርክትና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት ያለው የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ብሎም ሁሉ ለእኔ ብቻ ፍላጎት በአጠቃላይ ኢትዮጵያን አንደ ሀገር እና ዋና መገለጫ ጌጦቿን ኹሉ ለድርድር ያቀረበ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በዚኽም የምክክሩን ፍትሓዊነትና ቅቡልነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አግኝተነዋል። ይኽ ደግሞ ፓርቲያችንና ሌሎች ተሳታፊዎች ከሂደቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ እያስገደደ ይገኛል። ምክክር የቅንጦት ጊዜ ኹነት ሳይኾን የቀውስ ጊዜ መፍትሔ ማመንጫ ውጥን ነው። ቀዳሚው ዘርና ጎሳ ላይ የተመሠረተው ፌዴራሊዝም ሀገራችንን ሊያጠፋት ከጫፍ ደርሶ እያለ ይህን ያፈጠጠ አደጋ ሊያስቀር ወይም ሊያለዝብ የሚችል መፍትሔ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልክቱ እንኳ አለመታየቱ እጅግ የሚያስቆጭ ነው። እንዲያውም ገና ምክክሩ ሳይጠናቀቅ አንዳንድ ክልሎችን በስም ተጠርተው ሌላ ክልል ለማዋለድ ምክረ ሀሳብ ሲነሳ ብቻ በደስታ ይጨበጨባል፤ ሌላው ደግሞ ማን ነክቶን እያለ በማን አለብኝነት መግለጫ ይሰጣል። ይህም በዘርና በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ለሀገር አንድነትና ሕልውና ሥጋት መሆኑን አንዱ ማሳያ ነበር። በሌላ በኩል ይህ ምክክር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ሦስት ክልሎች ላይ ጦርነቶች እየተካሄዱ ነው፤ ሌላውም መጣሁ እያለ ነው። የርስ በርስ ጦርነቱን ጉዳይ ብልጽግናን ጨምሮ ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ እውነተኛ፣ ጥልቅ ውይይትና ደፋር ምክረ ሀሳብ ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሂደቱ ግን እከከኝ ልከክህ ሆኖ የአንድን ወገን ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ ቀድሞ የተወሰነን ውሳኔ በሀገራዊ ምክክር ስም ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ እየተከናወነ ነው። የታሪክና የትርክት መፋለሶች በናኙበት በዚህ ዘመን ቢያንስ እውነት አፈላላጊ ቡድኖችን አዋቅሮ ግማሽ መንገድ እንኳን ማቀራረብ ይገባ ነበር። እነዚኽንና መሰል አንኳር ጉዳዮች እንጂ የኢትዮጵያ መሪ (ከፕሮቶኮል አንጻር ነው አመክንዮው) ጠቅላይ ሚንስትር ሳይሆን ፕሬዝዳንት መኾን ነው ያለበት ላይ አልነበረም የችግሮቹ ቋጠሮ ያለው። ዙሪያ ዙሪያዋን ሲሏት የነበረችውን አዲስ አበባ በወከባ ብዛት ለአንድ ቡድን ሆ ብሎ ለማሳቀፍና አዲስ የፀብ ግንባር ለመቀስቀስም አልነበረም ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ ድሬዳዋ ከየት ወገን ትሑን የሚለው ሀገር ሊያፈርስ ደርሶም አልነበረም በሚሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት አባክነን ለምክክር የተቀመጥነው፡፡ በዓለም በልዩነት የምንታወቅበት ዘመን አቆጣጠር አሥሮ ይዞንም አልነበረም ምክክር ያስፈለገን፡፡ በአጠቃላይ የተጠቀሱና መሰል የተስተዋሉ ሳንካዎች ምክክሩ ከታለመለት ዓላማና በሀገሪቱ ያለውን ችግር ከሥሩ ከመፍታት ይልቅ ጠግኖ ለማስቀጠል፣ ለይምሰል የተደረገ፣ የአገዛዝ እና ቡድን(ኖች) ጠባብ ጊዜያዊ ፍላጎት ለማሳካት በሚመስል ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ ይሰማናል። በዚህም በመሠረታዊ የሀገር ሕልውና ጉዳዮች በዋናነት የርስ በርስ ጦርነትን በማስቆም፣ የዘርና ጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስቀረት/ማለዘብ እንደ ዋና ግብ መያዝና መሰል የተጋረጡ ፈተናዎች በአግባቡ ተረድቶ እልባት የሚበጅበትን አቅጣጫ ሊያስቀምጥ ያልቻለ ሀገራዊ ምክክር ከመነሻው እንደከሸፈ ለመረዳት ነቢይ መሆን አይጠይቅም። እናት ፓርቲ ከዚህ በመለስ ባሉ የምክክር አጀንዳዎች እና በምክክር ስም ተላለፉ በሚባሉ ስምምነቶች ላይ ፊርማውን የማያሰፍር መሆኑን ሕዝባችን እንዲያውቅ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ በዚህም፤ 1. ገዥው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክሩ ስም ለማሳካት ከሚፈለግ ማንኛውም ፍላጎትና ሀገርን አስይዞ ከሚደረግ የፖለቲካ ቁማር እንዲታቀብ እናሳስባለን። 2. ተመካካሪዎች ለጊዜያዊ ጥቅምና የፖለቲካ ውሳኔዎች ሽፋን ከመስጠት እና በታሪክ ተወቃሽ ከሚያደርጉ ድርጊቶች በመቆጠብ ለሀገርና ለሕዝብ መቆምን በቀረችው አጭር ጊዜም ቢሆን በድፍረት እንዲያሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 3. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገራዊ ምክክሩ የጥቂት አካላትን ፍላጎት ማስፈጸሚያና ለአዲስ ቁርሾ የሚያዘጋጅ እንዳይሆን ሂደቱን በንቃትና በትኩረት እንዲከታተል እናሳስባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
без подписи
без подписи
ከአፋብን አባት አርበኞች ምክር ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚያደርገው የህልውና ተጋድሎ የአገዛዙን ሰራዊት አከርካሪ በመስበር ላይ ይገኛል። ይህ ትግል ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ይደርስ ዘንድ በእሳት የታጠሩ መሰናክሎችን በማለፍ መስዋዕትነት እየከፈሉ ፋኖነትን ያቆዩ አርበኞች በታሪክ ፊት ልዩ ክብር ይገባቸዋል። ይህንን የተገነዘበው ድርጅታችን አፋብን የአባት አርበኞች ምክር ቤትን አቋቁሞ አርበኞች የትግሉ አካል የምንሆንበትን አደረጃጀት በመፍጠሩም የሚያስመሰግነው ተግባር ነው። የአፋብን አባት አርበኞች ምክር ቤት አባላት ወቅታዊ የሀገራችንን ሁለንተናዊና ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ በተለይም የአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ስርዓታዊ ጭቆና፣ የህልውና አደጋና የዘር ማጥፋት ወንጀል በመገንዘብ ህዝብን ከእልቂት ለመታደግ ሲባል ይህንን ወገናዊ ጥሪ የያዘ መግለጫ አውጥተናል። በመሆኑም ይህ ጥሪ የሚመለከታችሁ መላው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፤ የአማራ ክልል አድማ ብተና፣ ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በሙሉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሠረት ጥሪ ተግባራዊ ስለሚደረግ ጥሪውን ተቀብላችሁ አገራዊ እና ሰብአዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ የአፋብን አባት አርበኞች ምክር ቤት ያሳስባል። 1ኛ. ማንኛውም የመከላከያ ሰራዊት አመራርና አባል በሙሉ፡ ይህ ስርዓት የሃገርን ዳር ድንበር ዘብ እንዲሆን የተቋቋመን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ለራሱ የስልጣን ማራዘሚያ አድርጎ በገዛ ህዝቡ ላይ በማስተኮስና ነጻነት ፈላጊ ህዝብ በሰራዊቱ ላይ መልሶ እንዲተኩስ በማድረግ አመታትን ያስቆጠረ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የተከበርከው የሃገር መከላከያ ሰራዊት በየቀኑ እየተኮስክበትና እየገደልከው ያለው ህዝብ የራስህ ህዝብ ነው፡፡ ባልና ልጆቻቸው ተሰውተውባቸው የሚያለቅሱ እናቶች፣ ሴቶችና ህጻናት ሃገርህ ኢትዮጵያ እንድትጠብቃቸው አደራ የወጣህባቸው መሆናቸውን ፈፅሞ መዘንጋት የለብህም፡፡ በመሆኑም ይህን የአፋብን አባት አርበኞች ምክር ቤት የምህረት ጥሪን በመቀበል ከስነ ስርዓት አልባው የብልፅግና ስርአት ከነመሳሪያችሁና ሙሉ ትጥቃችሁ በመውጣት የአፋብን ሠራዊትን እንድትቀላቀሉ ስንል የአፋብን አባት አርበኞች ምክር ቤት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ 2ኛ. ማንኛውም የልዩ ሀይል: የአድማብተና: የፖሊስና የሚሊሻ አመራርና አባላት በሙሉ፡ ለማያዛልቅ ደሞዝ ፣ ቤት መስሪያ ቦታ እና ርካሽ ጥቅማጥቅም ብላችሁ በአማራ ህዝብ እየደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ችላ በማለት አሁንም ድረስ ህዝብን እንደ ይሁዳ በሰላሳ ዲናር መሸጡ የይሁዳን እጣፋንታ ከማድረግ ባለፈ ዘላቂ ምቾትን አያስገኛችሁም፡፡ በመጨረሻም ጨፍጫፊው ስርዓት ይፈርሳል፣ አለቆቻችሁ በዘረፋ ባከማቹት ገንዘብ ራሳችውን ያሸሻሉ፣ እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ግን ከማህበረሰቡ ትቀራላችሁ፡፡ ይህን ጉዳይ ግንዛቤ በማስገባት መሳሪያና ሙሉ ትጥቃችሁን በመያዝ አፋብንን እንድትቀላቀሉ የአፋብን አባት አርበኞ ምክር ቤት ጥሪ እናቀርባለን፡፡ 3ኛ. ማንኛውም የአማራ ክልል የብልፅግና ስርዓት አመራር ፣ ካድሬና ካቢኔ አባላት በሙሉ፡ የዚህን ደም አፋሳሽ ስርዓት ተልዕኮን ተቀብላችሁ በተለያዬ መልኩ በመፈጸምና በማስፈፀም በአማራና በመላ የሀገሪቱ ህዝብ ላይ እየደረሰ ባለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ያላችሁን ሚና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማቆም ለአማራ ብሎም ለአሁኗና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሰላም ማምጣት አማራዊ; አገራዊ እና ሰብአዊ ግዴታችሁ በመሆኑ አፋብንን በመቀላቀል የበኩላችሁን እንድትወጡ ስንል የአፋብን አባት አርበኞች ምክር ቤት ጥሪ እናቀርባለን:: ድል ለፋኖ !!! ድል ለአማራ!!! ድል ለኢትዮጵያ!!! 1 ኛ ኮማንደር አረጋ አለባቸው ጎንደር ............ 2 ኛሻለቃ አብነው ታደሰ ቤተአማራ ወሎ 3 ኛ አሺኔ ዘመዱ ሸወ/ጠቅላይ ግዛት 4 ኛቢያዝን በዜ ጎጃም 5 ኛአርበኛ እሸቴ በዬ ጎንደር 6 ኛ አረበኛ ሠፈር መለስ ሰሜን ጎንደር 7 ኛ ሻምበል ገብሩ ልይህ ሰሜን ጎንደር 8ኛ አርበኛ ደስታው ደመላሽ ደቡብ ጎንደር 9ኛ ሻምበል መሠረት አለሙ ሰሜን ጎንደር
አፄ ምኒልክ ክፍለ ጦር የአፋብን ሸዋ ጠቅለይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር አካል የሆነው የአፄ ምኒልክ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለት ነሃሴ 04 ቀን 2018ዓ.ም ባተካሔደው መድረክ ላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ሲያደርግ፣ በመድረኩም በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ለሰራዊቱ የፖለቲካ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ማድረጉን የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል። "ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ነሃሴ 04/2018 ዓ.ም የአፄ ምኒልክ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
የጄኔራሎችን ዘመቻ ድባቅ የመታው የሉማሜ ከተማ ጀብድ! ነሐሴ 4/ 2018 ዓ.ም ======================= ጅባራው ብርሃኑ ጥላሁን የ6ኛ ዕዝ አዛዥ፣ ጄኔራል ሶፊያ በክሪ የ602ኛ ኮር አዛዥ፣ ኮሎኔል አለምሰገድ ተስፋየ የ32ኛ ክ/ጦር አዛዥ በአለፍቱ ቀናት የጎጃምን ታጋይ ወደ ተራ ሽፍትነት ቀይረነዋል የሚል ትልቅ ዘመቻ በጮቄ ተራራ አድርገናል እያሉ ሲያቅራሩ የተመለከተው 34ኛ ክ/ጦር ሉማሜ ከተማን በመቆጣጠር ጀብድ ሰርቷል። ሉማሜ ከተማን ካርታ ላይ በማስፈር የተጠና እቅድ በማቀድ የተጀመረው ልዩ ኦፕሬሽ የጦር አመራሩ ሰራዊቱን የግዳጅ አፈፃፀሙን በሚገባ እንዲረዳ አድርገዋል። ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በጀግኖች የተመራው 34ኛ ክ/ጦር ሉማሜን በመቆጣጠር የጠላትን ሰራዊት ድባቅ መምታት ጀምረዋል። የጠላት የሰራዊት አቀማመጥ ቤተ ክርስቲያንን ከለላ ያደረገ ቢሆንም የወገን ኃይል በተጠና መልኩ ሰራዊቱን በማናጠል ደምስሰዋል። የሉማሜ ከተማ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ተመስገን ምስክር በብልፅግና ቢሮ በር ላይ በ34ኛ ክ/ጦር ተደምስሷል። አቶ ናቃቸው ጫኔ በሉማሜ ከተማ የገቢዮች ጽ/ቤት ግብር ሰብሳቢ ቡድን መሪ የነበረው ህዝብን በከፍተኛ ግብር በማሰቃየት እንዲሰደዱ ያደረገ ዋና የብልፅግና ጨካኝ ሰው በማህበረሰቡ ጥቆማ ተማርኳል። በሉማሜ ከተማ የመሸገውን የጠላት ኃይል በመደምሰስ የጄኔራሎች ጩኸት ባዶ ያስቀረው 34ኛ ክ/ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ ድል አስመዝግቧል ። በነበረው ውጊያ 4 ፓትሮል፣3 አምቡላንስ የጠላት ኃይል ቁስለኛ ሁኗል ከ25 በላይ ተደምስሷል፤ ክላሾች ተማርከዋል። ከቀናት በፊት አስደማሚ የኮማንዶ ሰራዊት ያስመረቀው 34ኛ ክ/ጦር በተከታታይ አቅዶ በተዋጋባቸው ውጊያዎች ድል ማስመዝገቡ ቀጥሏል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት