- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 55
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 823
- 1/48двое суток
- 943
- 1/72трое суток
- 1 017
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በቃለ ጉባኤዎቹ ላይ ሳንስማማ አንፈርምም - ተመካካሪዎች አዲስአበባ የኦሮሚያ ክልል መቀጫ ትሁን የሚለው አማራጭ በግድ በቃለ ጉባኤ ላይ እንዲካተት መደረጉን ምንጮች ተናግረዋል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አራት የሥራ ቡድኖች ተጠናቅረው በቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ዙሪያ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በተዘጋጁ የቃለ ጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈረም አረጋግጠዋል ቢልም፤ በአራቱ የሥራ ቡድኖች ውስጥ የሚገኙ “በርካታ” ተመካካሪዎች በቃለ ጉባኤዎቹ ላይ አለመፈረማቸው ተሰምቷል። በምክክር ሂደቱ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነው የፌደራል ከተሞች ጉዳይ አጀንዳ ላይ ከስምምነት ሳይደረስ በቃለ ጉባኤ ላይ አንፈርምም ያሉ ተመካካሪዎች በርካታ መሆናቸውን የገለጡልን ምንጮች፤ ቃለ ጉባኤ ባልሰፈረበት ባዶ መዝገብ ላይ ፈርሙ የተባሉ ሌሎች ተመካካሪዎችም “በባዶ መዝገብ ላይ አንፈርምም” በሚል ለቃለ ጉባኤ መመዝገቢያ በተዘጋጀው ቅጽ ላይ ሳይፈርሙ መቅረታቸውን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ለተመካካሪዎች ባቀረበው “የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት” ሰነድ መሰረት፣ በሥራ ቡድን ደረጃ የውሳኔ ስምምነት አለ ለማለት የተመካካሪዎችን 75 በመቶ ድጋፍ ማግኘት ያስፈልጋል። በማንኛውም የምክክር ደረጃ ውሳኔ የሚሻ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ ደግሞ ቢያንስ 75 በመቶ ተመካካሪዎች መገኘት እንዳለባቸውም ሰነዱ ያመላክታል። ይሁንና ኮሚሽኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል ሲል ይፋ ባደረገባቸው የሥራ ቡድኖች፣ ሁለቱም ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው በቆጠራ አለመረጋገጡን፣ የምክክር ሂደቱን የሚመሩ የኮሚሽኑ ባለሙያዎችና የምክረ ሀሳብ አጠናቃሪ ቡድን አባላትም ስለ ቅድመ ሁኔታው አለማንሳታቸውን ምንጮች ገልፀዋል። የፌደራል ከተሞች ጉዳይን እየተመካከረበት የሚገኘው የሥራ ቡድን 7፣ የምክክር ሂደቱን አጠናቅቋል በሚል ቃለ ጉባኤ ላይ እንዲፈረም መወሰኑን
ሰበር ዜና በአዲስአበባ ጉዳይ ተወሰነ አከራካሪ የነበረው የአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት እንደተደረሰበት ተገለጸ በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ ከነበሩ አጀንዳዎች መካከል የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ ዋነኛው ሲሆን፣ በዛሬው የምክክር ውሎ በአጀንዳው ላይ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተገልጿል። ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ በተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 4 ሺህ ተመካካሪዎች በተመረጡ 8 አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ መቆየታቸው ይታወቃል። በዛሬው የምክክር ጉባኤ ውሎ በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ የነበረው የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ አጀንዳ ስምምነት እንደተደረሰበት ታውቋል። በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን 500 አባላት ያሉት የተመካካሪዎች ቡድን ተስማምተዋል። ልዩ ጥቅምን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይ በሰፊው እንደሚመከርባቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ጉዳይ በተመካካሪዎች ዘንድ በሁለት ጎራ፤ «የኦሮሚያ ክልል አካል እና ዋና መቀመጫ ትሁን» በሚል እና «የፌደራል ከተማ ዋና መቀመጫ ትሁን» በሚል በተመካካሪዎች ዘንድ ለቀናት ሲያጨቃጭቅ መቆየቱ የሚታወስ ነው። ዘገባው የመናኀሪያ ራድዮ ነው!
#ሰበር_ዜና መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ ደርሷታል መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ የደረሳት ሲሆን በዚህ መዘርዝር ውስጥ በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡ ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡- 1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው 2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም 3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው 4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ 5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ 6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው 7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ 8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው 9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው 10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ 11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 12. አቶ አለልኝ ምህረት 13. አቶ መንበር አለሙ 14. አቶ ማይክ መላክ 15. አቶ አሳምነው ታደሠ 16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ 17. አቶ እሱባለው በለጠ 18. አቶ እስክንድር ሽፈራው 19. አቶ መሰለ ቸሩ 20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ 21. አቶ ጫኔ ዘየደ 22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ 23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ 24. አቶ ሲሳይ መልካሙ 25. አቶ ታደሰ ወዳይነው 26. አቶ በላይ ሲሳይ 27. አቶ ያሬድ ግርማ 28. አቶ ማረው ስለሺ 29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ 30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ ለአዲስ ማለዳ የደረሳት ደብዳቤ እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡- “በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ” በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ያመላክታል፡፡ ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡ አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡ አዲስ ማለዳ
видео или голосовое, без подписи
አሁን መከላከያ ሰራዊት ወደ ኤርትራ አቅጣጫ #ኡሙሓጀር ላይም ድብደባ መጀመሩም ተሰምቷል።
በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በትግራይ ሀይሎች መካከል በሜካናይዝድ የተደገ ከባድ ዉጊያ ተቀስቅሷል ፡፡
የ«እግረኛው» የበይነ መረብ ሚዲያ ባለቤትና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ። እንደ መረጃዎች ገለፃ፣ ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው ትናንት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ እስካሁን በይፋ የታወቀ የእስር ምክንያት አልተገለጸም። ተክለሃይማኖት በበይነ መረብ ሚዲያው ላይ አነጋጋሪና የበርካታ ሰዎችን ትኩረት የሚስቡ ልዩ ልዩ ማህበራዊና ባህላዊ ጉዳዮችን በማቅረብ የሚታወቅ የይዘት አዘጋጅ ነው። ምንም እንኳን በቁጥጥር ስር የዋለበት ምክንያት በህግ አስከባሪ አካላት በኩል በይፋ ባይብራራም፣ ከቅርብ ጊዜ የነበሩ የቪዲዮ ስራዎቹ ጋር ተያይዞ ሊሆን እንደሚችል በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ይገመታል። በተለይም በቅርቡ በፍርድ ቤት ንቁ የህግ ክስ ሂደት ላይ ከሚገኙና ስማቸው ከተነሳ ታዋቂ አርቲስቶች ጋር ያደረገውን ስብስብ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለተመልካች ማቅረቡ ይታወሳል። ይህ ክስተት የበርካታ ተከታታዮቹን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በመንግስት በተገነቡ መንገዶች ላይ በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ አዲስ ዓመታዊ የመንገድ ግብር ለመጣል የሚያስችል የፖሊሲ ፕሮፖዛል መዘጋጀቱ ታወቀ። ይህ አዲስ አሰራር ተሽከርካሪዎች ከሚያደርጉት መደበኛ የዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ (ቦሎ) ጋር ተያይዞ የሚከፈል ሲሆን፣ የታክስ ተመኑም በተሽከርካሪዎቹ ዓይነት እና ወደ አየር ላይ በሚለቁት የካርቦን ጢስ መጠን ላይ ተመስርቶ እንደሚወሰን ተገልጿል። በዚህ ረቂቅ መመሪያ መሠረት ከፍተኛ መጠን ያለው ጢስ የሚያወጡና ያረጁ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የመንገድ ግብር እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን፣ በአንጻሩ አዳዲስና አነስተኛ በካይ ጋዝ የሚያመነጩት ደግሞ ዝቅተኛ ታክስ እንዲከፍሉ ይደረጋል። በበርካታ ሀገራት የተለመደው ይህ አሰራር፣ መንግስት ለመንገድ ጥገናና እንክብካቤ የሚሆን ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በላይ የአካባቢ መስተዳድሮች የልማት በጀታቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመልክቷል። በአሁኑ ወቅት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደረጃ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ለመቅረብ በዝግጅት ላይ የሚገኘው ይህ የታክስ ፕሮፖዛል፣ ፀድቆ ወደ ትግበራ ሲገባ ከሚሰበሰበው ገቢ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 0.2 በመቶ ያህል ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል።
"የአሸናፊዎች አሸናፊ ፍልሚያ ለማድረግ እየተዘጋጀን ነው"ወ/ሮ ፈትለወርቅ ህውሃት ገዥው ብልፅግናን ካሸነፈ በኋላም ስለቀጠዩ ፍልሚያ እየገለፀ ይገኛል። የህወሓት ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፈትለወርቅ(ሞንጆሪኖ) "ዋናው ነገር ብልፅግናን ለመጣል ፍላግት ያሳይ እንጂ የትኛውም ስብስብ እርስ በራሱ እሳትና ጭድ ቢሆንም እንኳን አብረን እንሰራለን። ብልፅግናን ከጣልን በኃላ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመለየት ሌላ ዙር ፍልሚያ ይኖረናል።ለዚህም እየተዘጋጀን ነው።"በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል። መጨረሻ ላይም"ከድል በኋላ" ፍልሚ እንደሚጠብቀው እያወቀ ፅምዶን የሚቀላቀል አለወይ የሚለው ጥያቄ ተዘንግቷል በሚል አስተያየት ሲሰጥ ተመልክተናል።
ሰበር ዜና 📍ጀነራል ታደሰ ወረደ የቁም እስረኛ ከተደረጉበት ቦታ መሰወራቸው ተሰማ፡፡ ጀነራሉ ካለፈው ማክሰኞ አንስቶ የቁም እስር ከተደረጉበት ስፍራ በህወሃት ታጣቂዎች እንዲሰወሩ መደረጋቸው UMD Media ዘግቧል፡፡
"አባቴ ጥሪ ሲኖርበት ልብስ የለኝም ይላል ፤ ሕልሜ ለአባቴ ቆንጆ ሱፍ መግዛት ነው" ❤️ አንዲት ታዳጊ በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ተከታዮቿ ጥያቄ ጠይቀዋል መልስ ትሰጣለች። ከቀረቡላት ጥያቄዎችም አንዱ "ህልምሽን ንገሪን" የሚል ነበር። የእሷ ምላሽ ግን ብዙሃንን አሳዝኗል። አባቷ ጥሩ ልብስ እንዲኖረው ትሻለች። "ለእሷ ሲል" አያቶቿ ቤት ለመኖር ተገዷል። እንዲህ ትላለች፦ "ህልምሽ ምንድን ነው ተብያለሁ። ህልሜ ለአባቴ ሱፍ መግዛት ነው። ጥሪ ሲኖርበት ልብስ የለኝም ይላል። ደግሞም ለአባቴ ከዚህ ተሻለ ቤት መሥራት። ለእኔ ብሎ አይደል አያቶቼ ጋር የሚኖረው? በቃ ለእሱ ትልቅ ቤት መሥራት" ይህ ምላሿ ብዙሃኑን አሳዝኗል። የእንርዳሽም ጥያቄ እየቀረበላት ይገኛል። (ዶች ኤችዲ)
📍ሀገራዊው የምክክር ጉባኤ በሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና ቡራኬ ተጀመረ📍 ላለፉት 4 ዓመታት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ሲያካሂደው የቆየው ምክክር በመጨረሻ ምዕራፉ የሚከናወነው ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። በጉባኤውም የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምሕረት እና ሌሎችም በተገኙበት በሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና ቡራኬ ተጀምሯል።
በአሜሪካ በሚኒሶታ ግዛት ገና ተገዝቶና ተመርቆ አገልግሎት መሥጠት ከጀመረ ሦስት ወር እንኳን ያላለፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደረሰበት የእሳት አደጋ መቃጠሉ ተሰምቷል። ይህ ድንገተኛና አሳዛኝ ክስተት በካህናቱ፣ በምዕመናኑና በአካባቢው በሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ጥልቅ የሐዘን ስሜትን የፈጠረ ሲሆን፣ ማኅበረሰቡ ለብዙ ዓመታት በከፍተኛ ጥረትና በጉጉት የገነባውን ቅዱስ ሥፍራ እንዲህ ባለ አጭር ጊዜ ውስጥ በቅጽበት ማጣት የብዙዎችን ልብ የሰበረ ክስተት ሆኗል። ይሁን እንጂ በደረሰው ከባድ ጉዳትና ሐዘን ሳይበገሩ፣ የወደመውን የእምነት ተቋም በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሶ ለመገንባትና ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችና የገቢ ማሰባሰቢያ ጥረቶች በምዕመናኑና በበጎ አድራጊዎች አስተባባሪነት ወዲያውኑ መጀመራቸው ታውቋል። ይህ ፈጣን ማኅበረሰባዊ ምላሽና የመልሶ ግንባታ ተነሳሽነት፣ በችግርና በፈተና ወቅት የሚታየውን የጸደቀ ጥንካሬና የአንድነት እሴት የሚያሳይ እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል።
ሰበር ዜና በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየው ዓመታዊ የብድር ገደብ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። የብድር ገደቡ መነሳት የፖሊሲ አቋም ለውጥ ተደርጎ መታየት የለበትም ያለው ብሔራዊ ባንክ ፣ ከዛ ይልቅ በገንዘብ ፖሊሲ መሳሪያ ላይ የተደረገ ለውጥ ብቻ እንደሆነ አስታውቋል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ሲሆን ዝርዝሩን እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።
የደቡብ ሱዳን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሌው አዪኒ አሌው፣ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ደሊል ካዲር ጋር በነበራቸው ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን “የደቡብ ሱዳን አባት” ሲሉ መግለጻቸውን ሱዳንስ ፖስት (Sudans Post) ዘግቧል። ሚኒስትሩ ይህንን ታሪካዊ ንግግር ያደረጉት ሁለቱ ወገኖች በድንበር ደኅንነት እና በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ሲሆን፣ አዲስ አበባ ደቡብ ሱዳን በነፃነት ትግል ወቅት ላበረከተችው የማይተካ ሚና እና ላደረገችው ሁለንተናዊ ድጋፍ ትልቅ ምስጋና አቅርበዋል። ይህ ዲፕሎማሲያዊ መግለጫ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን የገለጹት የፖለቲካ ተንታኞች፣ በተለይም የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነት በጋራ ለመጠበቅና የቀጣናውን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ፍልስጤም ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፓርላማ ምርጫ ልታካሂድ መሆኑ ተገለጠ ፍልስጤም ላለፉት ሃያ ዓመታት ያላካሄደችውን የመጀመሪያውን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (የፓርላማ) ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገች ነው። ሀገሪቱ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረውን አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ መወሰኗ፣ በቀጣናው የፖለቲካ ምህዳር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ተገምቷል። ይህ የታቀደው ምርጫ በተለይም በተለያዩ የፍልስጤም የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያለውን መከፋፈል ለማጥበብና አዲስ ሕጋዊ አመራር ለመምረጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ሲል አልጀዚራ አስነብቧል።
በዛላምበሳ ዓዲ ሓቂ በሚባለው ዋና አስፓልት ላይ ኬላ በመጣል፣ ወጪና ገቢውን እንዲሁም የአካባቢውን ማኅበረሰብ ለዓመታት ሲቆጣጠሩ የቆዩት የኤርትራ ሰራዊት አባላት ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ኤርትራ መስመር መጓዛቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ ይህ ወታደራዊ የማፈግፈግ እንቅስቃሴ የተጀመረው ከትላንት ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ማታ ጀምሮ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች ከረጅም ዓመታት ወታደራዊ ገደብና ጫና በኋላ፣ አሁን ላይ ትልቅ የነፃነትና የሰላም ስሜት እየተሰማቸው መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የአካባቢው አስተያየት ሰጪዎች ሰራዊቱ በድጋሚ ተመልሶ ኬላ እንደማይዘረጋ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻልና ሙሉ ዋስትና እንደሌለ ቢገልጹም፣ አሁን ያለው አንጻራዊ መረጋጋትና ነፃነት ግን ከቀደመው በእጅጉ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ኋላ የመመለስ አዲስ ሒደት ላይ እስካሁን ድረስ ከትግራይ ክልል አስተዳደርም ሆነ ከአካባቢው የአስተዳደር ባለሥልጣናት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫም ሆነ የተባለ ነገር የለም። ኢትዮ ሊድ
"የሰሜኑ ጦርነት ኢትዮጵያን ለIMF ቅድመ ሁኔታዎች እንድትገዛ አስገድዷታል" ማሞ ምህረቱ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ቮክስዴቭ፤ ከተባለ የውጭ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ውይይት በሰጡት ሰፊ ማብራሪያ፣ የሰሜን ኢትዮጵያው የትግራይ ጦርነት በአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ያሳደረውን ከባድና አውዳሚ ጫና በዝርዝር አስገንዝበዋል። በአገሪቱ የኢኮኖሚ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የተሃድሶ እርምጃዎችን ሲመሩ የነበሩት ማሞ ምህረቱ፣ በወቅቱ የነበረውን አጣዳፊ የኢኮኖሚ ውጥረት እንዲሁም ቀደም ሲል የነበረው በብድር ላይ የተመሠረተ የሕዝብ መሠረተ ልማት እና የዕድገት ጉዞ የደረሰበትን ገደብ አንስተዋል። ጦርነቱ አገሪቱን አማራጭ ወደሌለው የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በመክተት፣ ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ቅድመ ሁኔታዎች እንድትገዛ አስገድዷታል ብለዋል። በተለይም የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ዕድገት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ አገሪቱ በከፍተኛ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጫና ውስጥ ሆና የብርን ዋጋ በገበያ እንዲወሰን (floating) ማድረግን ጨምሮ በIMF የሚመሩ የለውጥ እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መገደዷ ያስከተለውን ተጽዕኖ በማንሳት የተሰማቸውን ጥልቅ ነጸብራቅና ፀፀት ገልጸዋል። ይህ ውሳኔ በሀገር ውስጥ የታቀዱ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን መሠረት ያደረገ ቢሆንም፣ የጦርነቱ መዘዝ ግን አገሪቱ ለውጭ የገንዘብ ተቋማት እጅ እንድትሰጥ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ህውሃት ከትግራይ ሰው እንዳይወጣ አላማጣ ላይ አገደ‼️ ከትግራይ የተለያዩ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ አላማጣ የደረሱ አውቶቦሶች ተሳፋሪዎችን አውርደው በባዶ አላማጣን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል።ድጋሜ እንዳይመለሱም እንደተነገራቸው ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ወቅታዊው የክረምት ዝናብ መግባቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚገርሙ የፈጠራ የሥራ ዕድሎችና ማኅበራዊ ታሪኮች መከሰታቸውን ቀጥለዋል። በቅርቡ በሰፊው መነጋገሪያ በሆነው ቪዲዮ ላይ በግልጽ እንደሚታየው፣ አንድ ንቁና ብልህ ወጣት በጎርፍ የተጥለቀለቁ የከተማዋን መንገዶች መሻገር የከበዳቸውን እግረኞች በጀርባው አዝሎ ማሻገር ጀምሯል። ይህ ወጣት እግረኞች ውድ ጫማቸውና ልብሳቸው በጭቃና በጎርፍ ውሃ ሳይበላሽ ወደ ፈለጉበት ቦታ እንዲሻገሩ በማድረግ በምላሹ ተመጣጣኝ የገንዘብ ክፍያ የሚቀበል ሲሆን፣ ይህ የቢዝነስ አስተሳሰቡ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ አድናቆትንና መደነቅን ፈጥሯል። የክረምቱ ወቅት በመጣ ቁጥር የከተማዋ የመሰረተ ልማት ክፍተት የራሱን ፈተና ይዞ ቢመጣም፣ ወጣቶች ችግሩን ወደ መልካም የገቢ ምንጭነት የሚቀይሩባቸው እንዲህ ያሉ አስገራሚና ስራ ፈጣሪ ታሪኮች መደመጣቸውን ይቀጥላሉ።