tgindex
TIKVAH Airdrop

TIKVAH Airdrop

Статистика

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። ማርኬቲንግ 📞 0979333111 @TikvahEthMarketingBot መረጃና መልዕክት ፦ 0998999899 ​@tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna

Последний пост
3 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
8 403
−7 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
453
23 постов
Вовлечённость
5,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • ወደ ካናዳ ሰራተኛ መላክ ተጀምሯል ? " ገንዘብ አስከፍለዋቸው ተበልተው የመጡ ሰዎች አሉ " - ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ኢትዮጵያውያንን ለሥራ እድል ተጠቃሚነት ወደ ካናዳ ለመላክ "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል" ከተሰኘው ድርጅት ጋር የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ ዜጎችን መላክ እንደተጀመረ በማስመሰል በሚያጭረብሩ አካላት ገንዘብ የተጭበረበሩ ሰዎች መኖራቸውን ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ሚኒስቴሩ፣ ከካናዳ "ቀረበልኝ" ባለው ጥያቄ መሰረት ወጣት ባለሙያዎችን ወደ ካናዳ ለሥራ ለመላክ ከድርጅቱ ጋር በቅርቡ ስምምነት መፈራረሙ ይታወቃል። ባለሙያዎቹን ወደ ካናዳ ለማሰማራት በመንግስት ፈቃድ የተሰጠው ብቸኛው ድርጅት "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል" መሆኑንና ከካናዳ ኤምባሲ ውጭ የቪዛ ወኪል እንደሌለ ሚኒስቴሩ በስምምነቱ ወቅት መግለጹ ይታወሳል። ይሁን እንጅ ስምምነቱ ከተፈጸመ በኋላ በርካቶች " ወደ ካናዳ እንልካችኋለን " በሚሉ አካላት የማይገባቸውን ገንዘብ እየከፈሉ እየተጭበረበሩ ናቸው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ወደ ካናዳ መላክ ጀምራለች ? " እንልካችኋለን " በሚል ገንዘብ ስለሚያስከፍሉ አካላት ጥቆማ ደርሷችኋል ? ሲል በሚኒስቴሩ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት የውል ምርመራ እና ማጽደቅ ዴስክ ኃላፊ አቶ በዛወርቅ ከተማን ጠይቋል። አቶ በዛወርቅ " ወደ ካናዳ መላክ አልተጀመረም። ክፍያም የለም " ብለዋል። " ስምምነት ተፈረመ እንጅ ወደ ካናዳ የሚልክ መንግስት የሚያውቀው እውቅና የሰጠው ኤጀንሲ የለም " ያሉት ኃላፊው፣ " ገና የመላክ ስራው አልተጀመረም፤ ሲጀመር መንግስት እከሌ የሚባል ኤጀንሲ ካናዳ ላይ ፈቃድ ወስዷል ብሎ ያሳውቃል " ሲሉ ተናግረዋል። " በዚህ ወቅት መላክ ስላልተጀመረ የሚልከው ህገወጥ ነው፤ ህገወጥ ላይ የሚሳተፍ ማህበረሰብ መኖር የለበትም። ክፍያም የለውም። ግን አብዛኛዎቹ አስከፍለው 'እንልካችኋለን' ብለው ነው ማስታወቂያ የሚያሰሩት። ይሄ ስህተት ነው " ብለዋል። እያጭበረበሩ ያሉ ድርጅቶች፣ የተጭበረበሩ ዜጎች እንዳሉ ፈትሸው እንደሆነ ማብራሪያ የጠየቅናቸው ኃላፊው፣ " ገንዘብ አስከፍለዋቸው ተበልተው ወደዚህ (ወደ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር) የመጡ ሰዎች አሉ። ከፌደራል ፖሊስ ጋር ሆነን ገንዘብ የተቀበሉ ሰዎች ላይ ክትትል እየተደረገበት ነው። ጥቆማዎችም ይመጣሉ " ብለዋል። " ተጭበረበርን " ብለው ያመለከቱት ዜጎች ብዛት ስንት እንደሆኑ ስንጠይቃቸው ግን ቁጥራቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። አቶ በዛወርቅ ከተማ ፥ ስምምነት ተፈረመ ማለት ባለሙያዎችን ወደ ካናዳ መላክ ተጀምሯል ማለት እንዳልሆነና ክፍያም እንደሌለው ገልጸው፣ ማህበረሰቡ ይህን እንዲገነዘብ አሳስበዋል። ከካናዳ መንግሥት " 'ይሄን ስራ እንድትሰሩልኝ ባለሙያ ትልኩልኛላችሁ ወይ?' " የሚል ጥያቄ እንደቀረበላቸው ገልጸው፣ "መንግስትም 'አዎ፤ ባለሙያ አለን፤ እንልካለን የሚል ስምምነት ተፈራርሟል። ያ ማለት ግን መላክ ተጀምሯል ማለት አይደለም " ነው ያሉት። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • የምርጫ ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋገጠ የመጨረሻ ውጤት ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል። ይሁን እንጂ አጠቃላይ ውጤቱ ከመታወቁ በፊት፣ ከዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ላይ ጊዜያዊ ውጤቶች መለጠፍ ይጀምራሉ። በተመሳሳይ ከግንቦት 25 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በምርጫ ክልሎች ደረጃ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ እንደሚደረጉ ተገልጿል። ምርጫ ቦርድ ከየምርጫ ክልሎቹ ውጤቶችን የመረከብ ሒደቱን ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚያከናውን ሲሆን፣ ከምርጫው ዕለት (ግንቦት 24) ጀምሮ እስከ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ቅሬታዎችን የመቀበልና የማስተናገድ ሥራ እንደሚሠራ አመልክቷል።

  • አርሰናል በዚህ ክረምት ምን ያስፈርማል ? አርሰናል በዚህ ክረምት የግራ ክንፍ ተሰላፊ ለማስፈረም ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሸራ ተገልጿል። በተጨማሪም መድፈኞቹ የመሐል ሜዳ እና ተመላላሽ ቦታዎችን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተሰምቷል። ጋብሬል ጄሱስ ሊለቅ የሚችል በመሆኑ የዘጠኝ ቁጥር ቦታንም ሊመለከቱት እንደሚችሉ ተነግሯል። መድፈኞቹ ማንን እየተመለከቱ ነው ? አርሰናል በአሁኑ ሰዓት ሞርጋን ሮጀርስን እየተመለከቱ ከሚገኙ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም ብራድሌይ ባርኮላ ፤ ጁኒየር ክሩፒ እና የአያክሱ ሚካ ጎድትስ የአርሰናልን አይን ስበዋል ተብሏል። በቀኝ መስመር ቦታ አርሰናል ቲኖ ሌቭራሜንቶ እና የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ኢቫን ፍሬስኔዳ እየተመለከቱ ይገኛሉ። በተቃራኒ ቦታ ደግሞ የፍራንክፈርቱን ሁለገብ ተጨዋች ናታኔል ብሮውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተገልጿል። አርሰናልን እነማን ሊለቁ ይችላሉ ? - ጋብሬል ጄሱስ :- ክለቡን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል - ጋብሬል ማርቲኔሊ :- አርሰናል በቀጣይ ስለቆይታው ይወስናል - ትሮሳርድ :- ክለቡ በተመሳሳይ በቀጣይ ይወስናል - ኢታን ንዋኔሪ :- በዚህ ክረምት በቋሚነት ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል - ክርስቲያን ኖርጋርድ :- የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ይቀበላል @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የመድፈኞቹ ደጋፊዎች ሪከርድ ሰበሩ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ድሉን በለንደን ጎዳናዎች እያከበረ ይገኛል። በጎዳና ላይ ክብረበዓሉ የተገኙ ደጋፊዎች ከ 1️⃣ ሚልዮን በላይ እንደሚገመት የለንደን ፖሊስ አስታውቋል። የድል ክብረበዓሉ በለንደን ከተማ ታሪክ በርካታ ህዝብ የተሰበሰበበት በመሆን ሪከርድ መስበሩን ፖሊስ አሳውቋል። የህዝብ ሰልፉ 9.5 ኪሎ ሜትር መሸፈኑ ተዘግቧል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • CHAMPIONS 🏆 የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ሁለተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን በይፋ ተረክቧል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • ፒኤስጂ ሻምፒዮን 🏆 ሆኗል ! የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂን አርሰናልን በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል። ፒኤስጂ አርሰናልን በመለያ ምት 4ለ3 በማሸነፍ የዋንጫው አሸናፊ ሆኗል። ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ነበር ያጠናቀቁት። የአርሰናልን ግብ ካይ ሀቨርትዝ የፒኤስጂን ደግሞ ኡስማን ዴምቤሌ ማስቆጠር ችለዋል። ጋብሬል ማግሀሌስ እና ኢዜ የመለያ ምት መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል። በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የሚመራው ፒኤስጂ የሻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፈዋል። ፒኤስጂ በሁለት ተከታታይ አመት ዋንጫውን በማሸነፍ ከሪያል ማድሪድ ቀጥሎ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • የመለያ ምት ተጀምሯል ! ፒኤስጂ ✅✅❌✅✅ አርሰናል ✅❌✅✅❌ ውጤት በዚሁ ፖስት ላይ " Update " ይደረጋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል ! የአርሰናል እና ፒኤስጂ ጨዋታ ተጨማሪ የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። ይህንንም ተከትሎ ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • 105' ፒኤስጂ 1 - 1 አርሰናል ⚽ ዴምቤሌ              ⚽ ሀቨርትዝ - የጨዋታው ዳኛ ዳንኤል ሴበርት ዴክላን ራይስ እና ሚኬል አርቴታ ተቃውሞ አሰምተዋል በሚል ቢጫ ካርድ አስመልክተዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ደቂቃ አምርቷል ! የአርሰናል እና ፒኤስጂ ጨዋታ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። ይህንንም ተከትሎ ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃ አምርቷል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

  • 90 ' ፒኤስጂ 1 - 1 አርሰናል ⚽ ዴምቤሌ              ⚽ ሀቨርትዝ - ስድስት ደቂቃ ተጨምሯል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe

TIKVAH Airdrop — tgindex