tgindex
THIQAH

ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በ @tikvahethiopia (ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ) ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው። ማንኛውንም ጥቆማና አስተያየት @EyobTikuye ማድረስ ይቻላል።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
26
Всего постов
529
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
9 340
−9 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 267
40 постов
Вовлечённость
24,3%
к подписчикам
Постов в день
3,7
всего 529
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
2 167
1/48двое суток
2 483
1/72трое суток
2 678

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 43820

    እስራኤል 12 ሺሕ 360 ዜጎችን የፍልስጤም ግዛት በሆነው በዌስት ባንክ ማስፈሯ ተገልጿል። በአንፃሩ ደግሞ 7,000 ፍልስጤማውያን መፈናቀላቸውን የፍልስጤም መሬት ባለስልጣን (PLA) አሳውቋል። በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተወካይ አላ አልታሚ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በእየሩሳሌም "ወንጀል እየፈፀመች" መሆኑን ገልጸዋል። አልታሚ በጋዛም የእስራኤል ጦር ከባድ ወንጀሎችን ከመፈፀም አልተቆጠበም ብለዋል።…

  • 14 авг.1 44671

    አሜሪካ የኢራንን ድሮን መትታ ጣለች። አንድ የኢራን ድሮን በገልፍ ወደሚገኘው የአሜሪካ አየር ሀይል ሲበር ነው ጥቃቱ የተፈፀመው ተብሏል። ኢራን ኢላማ ያደረገችው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ ያሰማሩት  ዩኤስኤስ አብረሃም ሊንከን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላይ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ስለተፈፀመው ጥቃት የአሜሪካም ይሁን የኢራን ባለስልጣናት የሰጡት ማረጋገጫ የለም ነው የተባለው። የአሜሪካ ባህር…

  • 14 авг.1 48261

    90 ሺሕ የሚጠጉ እስረኞች ጉዳይ በግብጽ በፈረንጆቹ 2013 ከነበረው አመጽ በኋላ በተለያየ ጊዜ የታሰሩ ከ90 ሺሕ በላይ እስረኞች በማረሚያ ቤት እንደሚገኙ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ያሳያል፡፡ ታዲያ #ማህበር ጭምር ያቋቋሙ የታሳሪ ቤተሰቦች የፖለቲካ እስረኞቹ እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው። ለዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ተቋማት ባቀረቡት ጥሪ እስረኞቹ  ከእስር እንዲለቀቁ፤ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡና የተሻለ የእስር አያያዝ እንዲኖር ጠይቀዋል፡፡ የታሳሪ ቤተሰቦች ማህበር በማቋቋም የእስረኞች መብት እንዲከበርና በመንግስት የሚፈጸሙ አፈናዎች እንዲቆሙ አሳስበዋል፡፡ የግብጽ መንግስት የሀገሪቱ ህግና አለማቀፍ መመሪያዎችን እዲያከብር ጠይቀዋል፡፡ #thenewarab @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 12 авг.2 402334

    ኔታንያሁ በዌስት ባንክ አዲስ ጥቃት እንዲፈጸም አዘዙ። የእስራኤል ጦር በተቆጣጠራቸው ግዛቶች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ ይህን ትዕዛዝ ካክተላለፉ በኋላ በኒንቡስ ከተማ አራት ፍልስጤማውያን ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፣ የሀገሪቱ ጦር ሰፊ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ተመድ እስራዔል ሕገወጥ…

  • 12 авг.2 40721

    "ሩሲያ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን በጦርነቱ አሰልፋለች" - ዩክሬን ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ የተረከበቻቸውን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች "ዩክሬን ላይ እየተጠቀመች ነው" ሲሉ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ወነጀሉ። "ሩሲያ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን በጦርነቱ አሰልፋለች" ብለዋል።    ዘለንስኪ የሰሜን ኮሪያ ጦር በዩክሬን ምድር የሚያደሬገው ጦርነት ወታደራዊ አቅሙን በማሳደግ ለጃፓን እና ለሌሎች የፓስፊክ ቀጠና…

  • видео или голосовое, без подписи

  • 12 авг.2 25210

    የጋና ብሄራዊ ፔትሮትሌም ምክትል ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ድራማኒ ቡካሪ በለንደን የስራ ጉብኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ህይወታቸው አልፎ ተገኘ። ቡካሪ መሞታቸው የተሰማው የልደት በዓላቸውን ባከበሩ ማግስት መሆኑ ተገልጿል። ቡካሪ በጋና የነዳጅ ሀብት ምርት እና ግብይት ላይ ግንባር ቀደም ሚና ነበራቸው ተብሏል። የህልፈታቸው ምክንያት እስካሁን በብሪታንያም ይሁን በጋና በኩል አልተገለጸም። #msn @EyobTikuye @ThiqahEth

  • 12 авг.2 517112

    ዩክሬን ሁለት የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ ጥቃት አደረሰች። ሩሲያ 93 ሰው አልባ አልባ አውሮፕላን አከሸፍኩ አለች። አንዱ የነዳጅ ማጣሪያ ብቻ በአመት 15 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን፣ በቀን 300,000 በርሚል ነዳጅ የሚያመርት እንደነበር ተገልጿል። ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ኪቭ የረዥም ርቀት ሚሳዔሎችን መጠቀሟን ተናግረዋል። ዘለንስኪ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ ጥቃቱ ሩሲያ…

  • 12 авг.2 3529

    በኮሎምቢያ በተከሰተ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 132 ሰዎች ሲሞቱ 480 ተጎዱ። በበርካታ ሕንጻዎች ፍርስራሽ ሥር ሰዎች ተቀብረዋል የሚል ስጋት በመኖሩ የሟቾች ብዛት ከ132 ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል። በኮሎምቢያ ከባድ መሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፣ ይህም በሬክተር ስኬል 7.4 ሆኖ ተመዝግቧል። በቾኮ ግዛት የተከሰተው አደጋው ከመሬት በ103 ኪሎሜትር በታች የተከሰተ እንደሆነ የአገሪቱ…

  • 11 авг.3 03442

    በታይላንድ የቀድሞ የፓርላማ አባል ባደረሱት ጥቃት የግዛት አስተዳደር ተገደሉ። በታይላንድ በቀናት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት መፈጸሙ ተመላክቷል። የኖኔታቡሪ ግዛት አስተዳደር ሊቀመንበር ቶንጋቺ ዮንብራሰርት በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸው ተገልጿል። ዮንብራሰርት ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸው ማትረፍ አልተቻለም። ጥቃቱን ያደረሰው የቀድሞው የፓርላማ አባል ቻሎንግ ሪውራንግ የተባለ ግለሰብ ነው። ፖሊስ…

  • 11 авг.2 545202

    የሶሪያ ፍርድቤት በቀድሞው ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ላይ የሞት ፍርድ ወሰነ። ፍርድ ቤቱ አል አል አሳድን ሰብዓዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ነው የሞት ፍርድ ያስተላለፈባቸው። በፕሬዝዳንቱ የወንጀል ዝርዝር ግድያ፣ ስቃይ እና ድብደባ ተካተዋል። አላሳድ "ወንጀሉን የፈጸሙት" በ2011 በነበረው የአረብ አብዮት ወቅት መሆኑን የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል። ደማስቆ የሚገኘው አራተኛው የወንጀል ችሎት በቀድሞው የደህንነት ባለስልጣን አቴፍ ናጂብ፣ በአልአሳድ እና በወንድማቸው ማሄር አልአሳድና በሌሎች ሶሪያውያን ላይ ወንጀል ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰቦች ውሳኔ ሰጥቷል። #iranintl @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 11 авг.2 465172

    በኮሎምቢያ በተከሰተ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 132 ሰዎች ሲሞቱ 480 ተጎዱ። በበርካታ ሕንጻዎች ፍርስራሽ ሥር ሰዎች ተቀብረዋል የሚል ስጋት በመኖሩ የሟቾች ብዛት ከ132 ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል። በኮሎምቢያ ከባድ መሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፣ ይህም በሬክተር ስኬል 7.4 ሆኖ ተመዝግቧል። በቾኮ ግዛት የተከሰተው አደጋው ከመሬት በ103 ኪሎሜትር በታች የተከሰተ እንደሆነ የአገሪቱ የጂኦሎጂካል አገልግሎት አሳውቋል። በመሬት መንቀጥቀጥ ከ480 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። ከመሬት መንቀጥቀጥ መነሻ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፒሬራ ከተማ የከፋው ጉዳት ተመዝግቧል። ቢቢሲ ትክክለኛነቱን አረጋገጥኩት ያለው አንድ ቪዲዮ፣ 'ፕላዛ ቦሊቫር' በተባለው የከተማው ዋና አደባባይ የሚገኝ አንድ ሕንፃ ሲደርመስ አሳይቷል። በርካታ ሰዎች ተሰብስበውበት የነበረ ስፍራ በፍርስራሽ እና አቧራ ሲሞላም ይታያል። በከተማው 40 ሰዎች መሞታቸውን እና 65 ሕንፃዎች መፍረሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በ15ቱ ሕንፃዎች ፍርስራሽ ስር ሰዎች ተቀብረው ሊሆን እንደሚችልም ይታመናል። ከመሬት መንቀጥቀጡ መነሻ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ካሊ ከተማ ውስጥ ደግሞ 32 ሕንፃዎች ፈርሰዋል። በቾኮ እና ቫሌ ዴል ካውካ ግዛቶች በሚገኙት ማኒዛሌስ፣ ኪብዶ እና ሜዴሊን ከተሞችም የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል። ንዝረቱ በጎረቤት አገራት ቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር እና ፓናማም ደርሶባቸዋል። የአሁኑ አደጋ የተከሰተበት ኮሎምቢያ አጎራባች በሆነችው ቬንዙዌላ ከ6 ሺሕ በላይ ሰዎች በተመሳሳይ አደጋ መሞታቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። #Bbc @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 11 авг.2 311141

    በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ቡርሃካባን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። በቤይ ክልል የምትገኘው ቡርሃካባ በአልሸባብ ሀይሎች መከበቧን ተከትሎ ነው ኢትዮጵያ ጦሯን ያስወጣችው ተብሏል። በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የአረጋጊ ተልዕኮ (AUSSOM) ስር የተሰማራው የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ለሶማሊያ ጦር አስረክቦ መውጣቱ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ወታደሮች በዚህ ስትራቴጂካዊ ስፍራ ላለፉት 12 አመታት መቆየቱ ተመላክቷል። ቡርሃካባ በሰሜን ምዕራብ ከሞቃዲሾ 187 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ስትራቴጂካዊ ስፍራ ናት። #somaliguardian @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 11 авг.2 388118

    የውጭ ሀገር ዜጋ በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት ለመሆን ከ100 እስከ 150 ሺሕ ዶላር እንደሚያስፈልገው የሚደነግግ መመሪያ ወጣ። መመሪያውን ያወጣው የኢትዮጵያ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ነው። ሐምሌ 2018 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ጸድቋል። በመመሪያው መሠረት የውጭ አገር ዜጋ ማለት፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋን ሳይጨምር ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው ወይም የሌላ አገር ዜግነት ያለው ማንኛውም ሰው ማለት ነው። በዚህም መመሪያው ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ ላይ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን 150 ሺህ ዶላር እንደሚያስፈልገው ደንግጓል። በመመሪያው ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟላ የሚገባው ለአንድ መኖሪያ ቤት የሚያስፈልግ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ተቀምጧል። ሸገር ከተማን ሳይጨምር በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በሶማሌ ክልል፣ በሐረሪ ክልል ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ደግሞ ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን 120 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማቅረብን ይጠይቃል። ከሌሎቹ ክልሎች የውጭ አገር ዜጋ የቤት ባለቤት ለመሆን ዝቅተኛ ገንዘብ የሚጠየቀው በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልል ሲሆን የገንዘቡ መጠን ደግሞ 100 ሺህ ዶላር እንደሆነ ተደንግጓል። አንድ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ ሊኖረው የሚችለው የቤት መጠን አንድ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፈቃድ ወስዶ እያለማ ያለ ባለሀብት ግን ይህ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ሳይገድበው የአንድ ቤት ባለቤት መሆን ይችላል። #ShegerFm ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ https://t.me/ShegerFMRadio102_1/26179 @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 11 авг.2 6491415

    #YouTube እስካሁን 4 ሺሕ የነበረው የዩትዩብ የWatch Hours መስፈርት ወደ 8 ሺሕ ከፍ ተደረገ። ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ ከፍ እንዲል መደረጉን የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም መስፈርት በሁለት እጥፍ ማሳደጉን አሳውቋል። እ.ኤ.አ Feb 1, 2027 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው በዚህ አዲስ መመሪያ መሰረት፣ አዳዲስ ፈጣሪዎች በዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም ተቀብለው ገቢ ማግኘት ለመጀመር፦ -ረጃጅም ቪዲዮዎች ላለፉት 12 ወራት 8,000 የታዩ ሰዓታት /Watch Hours/ ማሟላት አለባቸው። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 4,000 ሰዓታት በሁለት እጥፍ ያደገ ነው። -በአጭር ቪዲዮዎች በኩል ማመልከት የሚፈልጉ ደግሞ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊየን የታዩ ዕይታዎች ማሳካት ይኖርባቸዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ሚሊየን እይታ በሁለት እጥፍ ጨምሯል። ለውጡ ከፈረንጆች 2018 ወዲህ በዩቲዩብ የገቢ አስተዳደር ደንብ ላይ የተደረገ ትልቁ ማሻሻያ ሆኗል። በተጨማሪ፣ ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉ የአጭር ይዘት ፈጣሪዎች የገቢ ክፍያቸውን ለማስቀጠል በየ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊየን ዕይታዎችን ጠብቀው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል። የ1,000 ተከታዮች መስፈርት ለውጥ አልተደረገበትም። @tikvahethmagazine @TechCrunch @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 10 авг.2 444413

    #Ethiopia #Oromia በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች ጥቃት 12 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ። በዞኑ አንገር ጉትን ወረዳ መንደር 1፣ መንደር መንደር 3፣ መንደር 4 በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ከትላንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ያልተቋረጠ በጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃት እየተፈጸመ እንደሚገኝ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተገኙ መረጃዎች አመላክተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከትላንት ጀምሮ በደረሰው ጥቃት ከ12 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ገልጸዋል። የዛሬው የጉዳት መጠንና የሟቾች ቁጥር እስካሁን በውል አልታወቀም። "ጥቃቱን እየፈጸሙ ያሉት የኦሮሚያ የፀጥታ ኃይል፣ የገዳ ኮማንዶ እና ጋቸና ሲርና" በሚል መጠሪያ የሚታወቁ አካላት በጋራ መሆኑ ተጠቅሷል። በአካባቢው የሚገኘው ህዝብ ለከፍተኛ አደጋ መጋለጡ ተገልጻል። አቅም ያላቸው ነዋሪዎች ህይወታቸውን ለማዳን ወደ ጫካ እየሸሹ እንደሚገኙና አቅም የሌላቸው ደግሞ በየመንገዱ እና በየቤታቸው ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑ ተነግሯል። ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሕፃናት አዛውንቶች ለከፍ ችግር የተዳረጉ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ "አንገር" በተባለ ወንዝ ውሃ ሙላት ተወስደዋል፤ አስከሬናቸው አልተገኘም ተብሏል። ቀደም ሲል በተደረጉ ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የነበሩት እነዚህ መንደሮች፣ አሁንም በድጋሚ ለከፍተኛ አለመረጋጋትና ውጥረት መጋለጣቸው ታውቋል። #BeleteKassa @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 10 авг.2 39191

    "ኢራን ላይ ጥቃት ከመፈጸም ኢኮኖሚያዊ ጫና መጠቀም መርጫለሁ" - ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገው "የትግል ሰልት መቀየራቸውን" ገለጹ። "በኢራን ላይ ማዕቀብ መጣል እና ወደብ መዝጋት የተሻለ አማራጭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። "ኢራን ላይ ጥቃት ከመፈጸም ኢኮኖሚያዊ ጫና መጠቀም መርጫለሁ" እያሉ ናቸው። ፕሬዝዳንቱ "ኢራን ወደ ድርድር እንድትመጣ ይህን ስትራቴጂ መከተል ስላለብን፤ አድርገነዋል" ብለዋል። "ኢራን በመጥፎ ሁኔታ ላይ ትገኛለች" ያሉት ትራምፕ "ገንዘቧ ወድቋል፣ ለወታደሮቿ የምትከፍለው ገንዘብ የላትም" ሲሉ ገልጸዋል። በዚህ ጉዳይ ኢራን ምላሽ ከሰጠች ሀሳቧ ይካተታል። #aljazeera #axios @EyobTikuye  @ThiqahEth

  • 10 авг.2 44413

    በሳዑዲ አረቢያ በሶፋ ፋብሪካ ውስጥ በተከሰተ ቃጠሎ 16 ሰዎች ሞቱ። ሁሉም ሟቾች የባንግላዴሽ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። የእሳት አደጋው የተከሰተው በሪያድ ከተማ በሚገኝ የሶፋ ፋብሪካ ነው። የአደጋውን መንስኤ ማጣራት መጀመሩን የሪያድ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል። የባንግላዴሽ እና የሳውዲአረቢያ ባለስልጣናት የሟቾችን አስክሬን ወደ ትውልድ ሀገር ለመላክ ውይይት መጀመራቸው ተገልጿል።  #outlook @EyobTikuye @ThiqahEth

  • 10 авг.2 6312

    በታይላንድ የቀድሞ የፓርላማ አባል ባደረሱት ጥቃት የግዛት አስተዳደር ተገደሉ። በታይላንድ በቀናት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት መፈጸሙ ተመላክቷል። የኖኔታቡሪ ግዛት አስተዳደር ሊቀመንበር ቶንጋቺ ዮንብራሰርት በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸው ተገልጿል። ዮንብራሰርት ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸው ማትረፍ አልተቻለም። ጥቃቱን ያደረሰው የቀድሞው የፓርላማ አባል ቻሎንግ ሪውራንግ የተባለ ግለሰብ ነው። ፖሊስ የግድያው መንስኤ በመካከላቸው የነበረ አለመግባባት መሆኑን አስታውቋል። ሪውራንግ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። #aljazeera @EyobTikuye  @ThiqahEth

THIQAH — tgindex