tgindex
አለ ሕግ

ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service Website: alehig.com https://linktr.ee/alehig WhatsApp👉 #+251920666595 Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
8
Всего постов
50
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
16 019
+37 за 3 дн.
Сутки
+13
+0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 420
40 постов
Вовлечённость
21,3%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 50
Упоминаний
6
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
2 432
1/48двое суток
2 787
1/72трое суток
3 005

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.1 443537

    ⚜አዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ቁጥር 1425/2018 ⚜New _ Customs Amendment Proclamation No. 1425/2026 ⚠This New Proclamation is Effective from 23rd July; 2026

  • 14 авг.2 14913

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.2 142313

    የአማራ ክልል የጠበቆች ግብር (VAT) 🙏

  • 12 авг.2 699387

    የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት (arbitration) የምስለ-ችሎት ውድድር (FDI Moot) የዞኑ አሸናፊ በመሆን አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት በዚህ ፈታኝ ውድድር ከናይጄሪያ፣ ከኬንያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 14 ቡድኖችን በመበለጥ ከሰብ-ሳሃራን አፍሪካ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል። በዚህ ውድድር ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ወክለው የተሳተፉት ፦ ➡ ባምላክስራ ፋሲል (የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡ ቃልኪዳን ሰብስቤ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡ ዲቦራ ታደሰ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) እና ➡ ናሆት ግርማ (የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ናቸው። ለዚህ አህጉራዊ ውጤት ያበቃቸው ዋና ምክንያት ምንድን ነው ? " ለዚህ ውጤት ያበቃን ቀደም ሲል በቪስ ሙት (Vis Moot) የነበረን ልምድ ነው። ከቡድናችን አራት አባላት መካከል ሦስቱ በዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ውድድር ላይ ለአንድ አመት ተወዳድረዋል። ይህ ልምድ በጣም ጠቅሞናል። አሁን ላይ የተወዳደርንበት ጉዳይ ከአለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት ጋር የተያያዙ ውስብስብ ጥያቄዎችን ያካተተ ነበር። ከዋና ዋናዎቹ የስነ-ስርዓት ክርክሮች መካከል ከሳሹ ቀደም ሲል አቤቱታውን ለሌላ አካል አቅርቦ ስለነበር አሁን እንዳይከለከል የሚለው እና የክስ ማገጃ ትእዛዝ መሰጠት አለበት ወይ ? የሚሉት ይገኙበታል። የፍሬ-ነገር ክርክሩ በበኩሉ ፍትሃዊ እና እኩል እንክብካቤ እንዲሁም ንብረት መውረስን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን አካቷል። በውድድሩ ወቅት የገጠመን ትልቁ ፈተና ከዳኞቹ ለሚቀርቡ ዝርዝር እና ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ነው " ብለዋል። የተወዳዳሪዎቹ መሪ የሆኑትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው የህግ ተማሪ፣ የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳ፥ ተማሪዎቹ እስካሁን ያለምንም ድጋፍ ለዚህ ድል የበቁ ቢሆንም፣ በመጪው ኦክቶበር (October) ወር በቻይና በሚካሄደው የመጨረሻ ፍጻሜ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ የገንዘብ እና የተቋማት ድጋፍ ይፈልጋሉ ብለዋል። በተለይም ፦ - ለዓለም አቀፍ ጉዞ፣ - ለእንግዳ ማረፊያ፣ - ለቪዛ፣ - ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ወጪዎች እና ለዝግጅት ድጋፍ የሚያስፈልግ በመሆኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት (በተለይም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን) የሕግ እና የንግዱ ማኅበረሰብ፣ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች ትብብር እንዲያደርጉላቸውና እውቅና እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል። ይህ እድል የነዚህ አራት ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን፣ ኢትዮጵያን እና የአፍሪካን የሕግ ትምህርት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለመወከል የሚሰጥ ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል። ​ተወዳዳሪዎቹን ማግኘት የምትፈልጉ፣ የቡድኑ መሪ የሆኑትን የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳን በስልክ ቁጥር +251925494142 ማግኘት ትችላላችሁ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ/ም

  • 11 авг.3 1352730

    በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ። ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል። በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል። በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል። Source: Ethio FM 107.8 #Ethiopianbusinessdaily

  • 11 авг.2 78634

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.3 08010

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.3 2282010

    "በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል። 👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የማይገመገሙ መሆኑ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። 👉 ህጎች በወጡ በሳምንት እና በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸውም እንዳሉም ተገልጿል። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና መጣረሶች እየታዩ መሆኑን፣ ይህንንም መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ፖሊሲም ሆነ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በሀገሪቱ አለመኖሩን ፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ። ጥናቱ "የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም በሀገሪቱ ያለውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የአተገባበር ስርዓት ከረጅምና ከአጭር ጊዜ እቅዶች እንዲሁም ከቦትስዋና፣ ከጋናና ከደቡብ አፍሪካ ተሞክሮዎች አንጻር በመመርመር የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ነው። ህግ የማህበረሰብንና የመንግስትን መስተጋብር የሚመራ መሳሪያ እንደመሆኑ ተለዋዋጭነት ባህሪው ቢሆንም፣ የሚወጡ ህጎች ጥራት፣ ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተገማችነትና ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጥናቱ ያስቀምጣል። ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተካሄደው የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በርካታ ህጎች የመውጣታቸውን ያህል፣ በችኮላና በጥድፊያ የሚወጡ ህጎች የህግ አወጣጥ ስርዓቱ የተረጋጋ እንዳይሆን፣ በህዝብና በባለሙያዎች ያልተመከረበት እንዲሆን እንዳደረጉት ጥናቱ ጠቁሟል። ይህም ባለሀብቶች የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዳይወስኑ፣ ዜጎችም ስለ መብትና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ አናሳ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተመላክቷል። ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ መመርመሩን ገልጿል። ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት፣ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በስድስት ተያያዥ ተቋማዊ ምሶሶዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን የለየው ጥናቱ እነሱም የህገ መንግስት የበላይነት በተግባር መረጋገጥ፣ ውጤታማ የስልጣን ክፍፍልና ሚዛን፣ ጠንካራ የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓት፣ በሙያ የታገዘ የረቂቅ ዝግጅት ተቋም፣ ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎ፣ እና ገለልተኛ የዳኝነት ቁጥጥር ናቸው። ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን ሀገሪቱ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋትን የተመለከተ ፖሊሲ እንደሌላት፤ ጠቅላላ የህግ አወጣጥ ስርዓትን የሚመራ ፖሊሲም እንደሌለ፤ የሚወጡ ህጎችም በአብዛኛው በጸደቁ ፖሊሲዎች ላይ ከመመስረት ይልቅ የአስፈጻሚውን ጊዜያዊ ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ሆነው መገኘታቸውን ለይቷል። በህግ ማዕቀፍ ረገድም ኢፌዲሪ ህገ መንግስት፣ ደንብ ቁጥር 6/2008፣ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና ሌሎች ሰነዶች ቢኖሩም፣ ከማርቀቅ እስከ አፈጻጸምና ክትትል ድረስ ያለውን ሂደት በአንድ ወጥነት የሚገዛ ማዕቀፍ አለመኖሩ ተጠቁሟል፤ ያለው አሰራርም በተበታተኑና በተበጣጠሱ መመሪያዎች ላይ የተመሰረተ ነው። በአተገባበር ደረጃም ከተለዩ ክፍተቶችም ውስጥ :- - ተደጋጋሚ የአዋጅ ማሻሻያዎች (ለምሳሌ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኤክሳይዝ ታክስ አዋጆች በወጡ በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑ) ፣ - ሰፊ የአዋጅ መሻሮች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ብቻውን 18 አዋጆችንና 35 ደንቦችን መሻሩ)፣ - ተደራሽ ያልሆኑ መመሪያዎች ፣ - ተቃራኒ ይዘት ያላቸው አዋጆች መውጣት፣ - ከበላይ ህጎችና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች መኖር (በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰልን በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የያዘ ድንጋጌ በመሆኑ ማክሰኞ ወጥቶ በሳምንቱ ማክሰኞ ማሻሻያ የተደረገበት ሂደት መኖሩ) - የበታች ህጎች ያለ ተገቢ ግምገማ መውጣት ( በተለይ ታክስ አካባቢ ይሄ ችግር በአደገኛ ሁኔታ መስተዋሉ) - አዋጆች በተግባር ያለመፈጸም ይገኙበታል። ከጥንካሬ አኳያም የተለያዩ ግኝቶችን ያስቀመጠው ጥናቱ ባለ ሶስት ደረጃ የምርመራና የንባብ ሂደት፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማጣራት ሚና፣ የህግ ማዕከልና አማካሪዎች መኖር፣ እንዲሁም በቅርቡ የተቋቋመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ማሻሻያና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ እንደ አዎንታዊ እርምጃዎች ተጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የባለሙያ እጥረት፣ የተቋማት አለመናበብ፣ የአመራር ትኩረት ማነስ እና ወጥ የህግ ይረቀቅልኝ ስርዓት አለመኖር እንደ ዋና ዋና ድክመቶች ተለይተዋል። ጥናቱ ከጋና፣ ከደቡብ አፍሪካና ከቦትስዋና ተሞክሮ በመነሳት ፦ ° ፍርድ ቤቶች ግልጽ የህገ መንግስት ተጣጣሚነት የመተርጎም ስልጣን እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ° የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓትን ማጠናከር፣ ° ሙያዊ የረቂቅ ዝግጅት አቅምን ማጎልበት፣ ° የህዝብና የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ተወካዮች ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ፣ ° ህግ ማውጣትን ከፖለቲካ ፍጥጫ ነጻ ማድረግ፣ ° የተጠቃለለ ፖሊሲና ሁሉን አቀፍ ህግ ማዘጋጀት፣ ° ገለልተኛ የህግ ኮሚሽን ማቋቋም፣ ° በዩኒቨርሲቲዎች የሌጂስሌቲቭ ድራፍቲንግ ስልጠናና ካሪኩለም ማዘጋጀት፣ ° የህግ አወጣጥ ሉዓላዊነትን ከውጭ ተጽእኖ መጠበቅ፣ እንዲሁም የበታች ህጎችን ከአዋጅ ጋር ተጣጥመው መውጣታቸውን የሚከታተል ስርዓት መዘርጋት የሚሉ ምክረሃሳቦችን አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • 8 авг.3 294918

    ስለ ነጻ የጥብቅና አገልግሎት ክፍለ ከተማ ምርጫ ማሳወቂያ ውድ የማህበራችን አባላት፣ ከፍትህ ሚኒስቴር ለማህበሩ በተላከ ደብዳቤ (ቁጥር 409-28/0521/19፣ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም.) የተላለፈውን መረጃ ለአባላት እናደርሳለን። የፍትህ ሚኒስቴር ነጻ የህግ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ጠበቃ የመመደብ ስልጣን በህግ የተሰጠው ሲሆን፣ እስካሁን ጉዳዮች ለጠበቆች ሲመደቡ የሚደረገው በተመዘገበው አድራሻ መሰረት ነው። ይህ አሰራር በጠበቆች ዘንድ ቅሬታ ሲያስነሳ የቆየ ከመሆኑም በላይ፣ ነጻ የህግ ድጋፍ ተጠቃሚዎች ላይም አላስፈላጊ መጓተት እያስከተለ ይገኛል። በመሆኑም ጠበቆች ነጻ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉበትን ክፍለ ከተማ (Subcity) አስቀድመው መርጠው እንዲያስመዘግቡ ሚኒስቴሩ ጠይቋል። የክፍለ ከተማ ምርጫ ምዝገባ ሊንክ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfKR2tHgvj8AaD5o0nwUjYw9XbkFZcrQDd96OavsujXUx0rRA/viewform የጊዜ ገደብ የክፍለ ከተማ ምርጫውን ከደብዳቤው ቀን (ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም.) ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ያስፈልጋል። እባክዎ ልብ ይበሉ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ምርጫቸውን ያላስመዘገቡ ጠበቆች፣ ወደፊት ለነጻ የጥብቅና አገልግሎት በሚመደቡበት ክፍለ ከተማ ላይ የሚያነሱትን ቅሬታ ሚኒስቴሩ እንደማይቀበል በግልጽ አስታውቋል። ማህበሩ ይህንን አስፈላጊ የጊዜ ገደብ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ አባላት በተቻለ ፍጥነት ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ በአጽንኦት ያሳስባል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም.

  • 8 авг.3 1638

    видео или голосовое, без подписи

  • 8 авг.3 14128

    በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ ሥርዓት ውስጥ ወንጀል ፈጽመው የታረሙ ግለሰቦች በድጋሚ ወደ ወንጀል ድርጊት የመመለሳቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥናት አመልክቷል። 👉 በጥናቱ ከተካተቱና ወንጀል ፈጽመው ታርመው ከወጡት ታራሚዎች ውስጥ 94 በመቶዎቹ ከ5 አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሌላ ወንጀል በድጋሚ ወደማረሚያ ቤት የተመለሱ ናቸው። በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ ሥርዓት ውስጥ ወንጀል ፈጽመው የታረሙ ግለሰቦች በድጋሚ ወደ ወንጀል ድርጊት የመመለሳቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ይህንን ለመግታት የተቀናጀ የመረጃ አያያዝና የህግ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያከናወነው ጥናት አመልክቷል። ኢንስቲትዩቱ አመታዊ የጥናትና ምርምር ማጽደቂያ መርሃ ግብሩን ያከናወነ ሲሆን በመድረኩ "የወንጀል ደጋጋሚነት እና የማረሚያ ቤት ሚና በኢትዮጵያ፣ የሕግ ማዕቀፍ እና አተገባበር ስርዓት" የተሰኘ ጥናቱን ይፋ አድርጓል። በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የቀረበው ይህ ጥናት፣ ወንጀለኞች ታርመውና ታንጸው ሰላማዊ ዜጋ እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር አሁንም ሰፊ ክፍተቶች መኖራቸውን አመልክቷል። ቀደም ሲል በተፈጸመ ወንጀል፣ ቅጣት በተሰጠ ወይም በይቅርታ ቀሪ እንዲሆን በተደረገ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ስድስት ወር የሚያስቀጣ አዲስ ወንጀል ሰርቶ መገኘት የወንጀል ደጋጋሚነት የሚባል ሲሆን በወንጀል ፍትህ ስርዓት ውስጥ ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎችን እያረሙ ስለመሆን ወይም አለመሆናቸው የሚለይበት ዋናኛ መለኪያ ነው። ይሁን እንጂ በጥናቱ ከተካተቱት 127 የወንጀል ድጋሚ ፈጻሚዎች መካከል ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ  በወንጀል ድርጊት የተገኙት 5.6 በመቶዎቹ ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ማለትም 94.4 በመቶ የሚሆኑት ከአምስት ዓመት በታች በሆነ ጊዜ ወደ ማረሚያ ቤት ተመልሰዋል ይህም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎችን የማረም ሂደት ላይ ውጤታማነት እንደማይታይበት አመላካች ሆኗል። የጥናቱ ውጤት በዝርዝር ሲታይ 57.9 በመቶ የሚሆኑት ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ማረሚያ ቤት የተመለሱ ሲሆኑ፣ 31 በመቶዎቹ ደግሞ ለሦስተኛ ጊዜ የተፈረደባቸው ናቸው። ከእስር ከተፈቱ በኋላ ወደ ወንጀል ለመመለስ የሚወስድባቸውን ጊዜ በተመለከተ፣ 36.5 በመቶ የሚሆኑት ከ2 እስከ 5 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሲመለሱ፣ 23 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ በድጋሚ ወንጀል ፈጽመው ይገኛሉ። 17.5 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከ6 ወር በታች በሆነ ጊዜ ወደ ወንጀል መመለሳቸውን ውጤቱ ያሳያል። በተጨማሪም፣ ታራሚዎቹ ቀደም ሲል ተከሰው ከተቀጡበት ወንጀል (52 በመቶ ዝርፊያ/ስርቆት) ጀምሮ፣ በአሁኑ ጊዜ ተይዘው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገቡ ካደረጋቸው አዲስ ወንጀል (53.6 በመቶ ዝርፊያ/ስርቆት) ድረስ ተመሳሳይ የወንጀል ዓይነት ደጋግመው መፈጸማቸው በጥናቱ ተመዝግቧል። የተቀሩት አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም እና ማዘዋወር ፣ውንብድና ፣ የግብር ስወራና ማጭበርበር ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ፣የሙስና ወንጀሎች እና ሌሌችም ወንጀሎች ይገኙበታል። በጥናቱ በድጋሚ ወንጀል እንዲፈጽሙ ካደረጓቸው ምክንያቶች መካከል 13.4 በመቶ የሚሆኑት ስራ ባለማግኘታቸው ምክንያት ተመልሰው ወንጀል ውስጥ መገኘታቸውን ተናግረዋል። ገንዘብ ለማግኘት አለመቻል እንዲሁም ከማረሚያ ቤት ከወጡ በኋላ ክትትልና ድጋፍ አለመኖርም ተመልሰው በወንጀል ውስጥ እንዲገኙ ማድረጉን የጥናቱ ውጤት ያመለክታል። በተጨማሪም ከእስር የወጡ ግለሰቦች በማህበረሰቡና በቤተሰቦቻቸው ዘንድ ተቀባይነት ማጣታቸው፣ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ በቂ የሙያና የስነ-ልቦና ስልጠና አለመስጠት እንዲሁም በእስር ላይ እያሉ አዳዲስ የወንጀል ስልቶችን መማር በድጋሚ ወንጀል እንዲሰሩ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። ሌላው በጥናቱ የተጠቀሰው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ወንጀለኞችን በዘመናዊ መንገድ ለመለየት የሚያስችል ወጥና የተደራጀ የዲጂታል መረጃ አያያዝ (Database) ስርዓት አለመኖሩ ሲሆን በተለይም በአዲስ አበባ የፖሊስ ደረጃ የጣት አሻራ ምርመራ በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ የማይደረግ በመሆኑ፣ ድጋሚ ወንጀል ፈጻሚዎችን ማንነት እና እንደሃገር ያለውን የወንጀል ደጋጋሚነት ምጣኔ በትክክል ለመለየት አስቸጋሪ አድርጎታል ተብሏል። ጥናቱ ይህንን የፍትህ ስርዓቱን ክፍተት ለማረም የወንጀል ደጋጋሚዎች ከሌሎች ታራሚዎች ተነጥለው ለብቻ የሚያዙበት ራሱን የቻለ የተለየ የተሃድሶ ፕሮግራሞች እንዲኖሩ እንዲሁም የእርምት ጊዜያቸውን ጨርሰው ከማረሚያ ቤት የሚወጡ ታራሚዎች ወደ ማህበረሰቡ መልሶ መቀላቀልን በተመለከተ የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጸድቅና ተግባራዊ እንዲሆን ምክረሃሳብ አቅርቧል። በመድረኩ የተገኙት የፍትህ ሚኒስቴር ተወካይ ጥናቱ የወሰዳቸው የናሙናዎች መጠን (Sample size) አነስተኛ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን በምክረ ሃሳብ ደረጃ ለተነሱት ሃሳቦች ግን ረቂቁ ተጠናቅቆ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን እና በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • 6 авг.3 98889

    መንግሥት 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ መታገዳቸውን ዛሬ በይፋ አሳውቋል። መተግበሪያዎቹ ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ እንደነበር አመልክቷል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ የክሪፕቶ ከረንሲ መተገበሪያዎች የኢትዮጵያን ብር ከP2P መድረክ ላይ ማስወጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል። በሌላ በኩል፤ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን አሳውቋል። በተጨማሪ በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓልም ብሏል። Source: Tikvah Ethiopia #Ethiopianbusinessdaily

  • 6 авг.3 2992

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.3 3582

    የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው ስለሚቆዩባቸው ጊዜያት የተሰጠ መግለጫ

  • 5 авг.5 07883

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.5 34581

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.5 13783

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.3 91783

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.4 18083

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.3 83283

    видео или голосовое, без подписи