tgindex
⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye)

⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye)

Статистика
@ethiolawtipsInstagramангНиКскиК

@lawyerhenoktaye (LL.B LL.M) 0953758395 ☎️ Youtube👇 https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1 Facebook 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100071372553654&mibextid=ZbWKwL

Последний пост
9 авг.
Последнее чтение
12:23
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ангНиКскиК
Категория
Instagram
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
13 192
+5 Са 3 дн.
Сутки
+1
+0,01%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
3 927
22 постов
Вовлечённость
29,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 22
УпОПинаниК
1
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
3 330
1/48двое суток
3 816
1/72трое суток
4 115

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 9 авг.1 8631216

    በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ  በተሰጣቸዉ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዉክልና ስልጣናቸዉ በቀጥታ ያዩዋቸዉን የፈዴራል ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ስልጣን ያላቸዉ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑ በክልሉ እንዲደራጁ  የተደረጉት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ናቸው ተብሎ ተወስኗል፡፡👇 https://t.me/ethiolawtips

  • 2 авг.3 7793479

    በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1196(1) መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ሰው የንብረቱ ባለቤት ለመሆኑ የሕግ ግምት የሚወሰድ በመሆኑ፣ ይህ ግምት ሊፈርስ የሚችለው ካርታው ከሕግ ውጪ መሰጠቱ ወይም ሰነዱን የመስጠት ሥልጣን በሌለው አካል የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ በሰው ምስክርነት ወይም ገንዘብ አውጥቻለሁ በሚል ክርክር ብቻ ሊፈርስ አይችልም። ​በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 (1 እና 2) መሠረትም የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጠበቀው በሕጋዊ መንገድ በተያዘ ይዞታ ላይ ሲሆን ብቻ ነው። በመሆኑም በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስት በወላጅ ስም በተመዘገበ ይዞታ ላይ ገንዘብና ጉልበት በማፍሰስ ቤት ቢገነቡ እንኳ፣ ይዞታውም ሆነ በይዞታው ላይ የተገነባው ቤት የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ሊሆን አይችልም። ​በቤቱ ግንባታ ላይ በትዳር ዘመን በባልና ሚስት የተደረገ የገንዘብ ወጪ ወይም አስተዋጽኦ ካለ፣ ግምቱን ከመጠየቅ ውጪ በሌላ ሰው ስም ባለው ይዞታ ላይ ያረፈውን ቤት የጋራ ንብረታችን ነው ብለው የክፍፍል ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም። ​ስለሆነም፣ በጋብቻ ውስጥ በወላጆች ስም ባለው መሬት ላይ የሚገነባ ቤት የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ሳይሆን የባለይዞታው ንብረት እንደሆነ የሚቆጠር ሲሆን፣ በፍቺ ጊዜ የትዳር አጋሮች መብት የሚጠበቀው ያወጡትን ገንዘብ በድርሻቸው ተመላሽ እንዲደረግላቸው በመጠየቅ እንጂ የንብረቱን/የቤቱን ክፍፍል በመጠየቅ አይደለም። ​የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ አቶ ብርሃኑ ከበደ እና ም/ኢ/ር ጥሩነሽ ዱባለ፣ መዝገብ ቁጥር 132 (ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም)

  • 30 июл.4 3191929

    ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም። ማጠቃለያ የወንጀል ክስ በአንድ በኩል ተጎጂዎች ፍትሕ የሚያገኙበት የሕግ ሂደት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በወንጀል የተጠረጠሩ ወይንም የተከሰሱ ግለሰቦች ነፃነት በሕግ የሚገደብበት ነው። በዚሁ መሠረት የወንጀል ክስ መመስረቻ ጊዜ ገደብ በሕግ ወስኖ ማስቀመት በሁለቱ ተፃራሪ መብቶች መካከል ሚዛን ለመጠበቅ የሚያስችል ነው። ስለሆነም ማንኛውም ክስ በሕግ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ ይገባል፡፡ ምንጭ ፍትሕ ሚኒስቴር ገፅ

  • 30 июл.3 8521149

    የወንጀል ክስ ይርጋ በኢትዮጵያ ******** ወንጀል ፈፃሚዎች ለፈፀሙት ጥፋት በሕግ ፊት መጠየቃቸውና ተገቢውን ቅጣት መቀበላቸው ተገቢና አስፈላጊም ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ አንድ እንደተመለከተው በወንጀል ሕጉ መሰረት ወንጀል የተደረጉ ድርጊቶች እና የሚያስከትሉትን ቅጣት በመደንገግ ሰዎች ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ አሰቀድሞ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ቢሆንም ቅድመ-ማስጠንቀቂዎች በቂ ባልሆኑ ጊዜ ወንጀል ፈፃሚዎች ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲታቀቡና ለሌሎችም ማስተማሪያ እንዲሆኑ ማድረግን ግቡ ያደረገ ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ግን በወንጀል ሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ ሊመሠረት እና አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብ የሚገባ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ክሱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ የወንጀል ክስ ይርጋን ምንነት፣ በሕግ የተመለከተውን የክስ ይርጋ ዘመን እናአቆጣጠር እንዲሁም የክስ ይርጋ ዘመን መቋረጥና መታገድ በአጭሩ እንመለከታለን፡፡ የወንጀል ክስ ይርጋ ምንነት የወንጀል ሕጉ የወንጀል ክስ ይርጋን ምንነት በተመለከተ ቀጥተኛ ትርጓሜ ባይሰጥም ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 217 በመነሳት የወንጀል ክስ ይርጋ ማለት በማናቸውም ወንጀል ጉዳይ በግል አቤቱታ ወይም በወንጀል ክስ አቅራቢነት ጉዳዩ በዳኝነት ከመታየት የሚታገድበት በሕግ የተመለከተ ጊዜ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ የመደበኛ ክስ ይርጋ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 217 መደበኛ የክስ ማቅረቢያ ጊዜን የደነገገ ሲሆን • የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በሃያ አምስት ዓመት • ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችሉ ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በሃያ አመት • ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት ለመድረስ የሚችል ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በአስራ አምስት አመት • ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በአስር ዓመት • ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በአምስት ዓመት • እስከ አንድ ዓመት ቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወይም በመቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል በሦስት ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ ክሱ በይርጋ ይታገዳል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው ሲገኙ የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች ተመሳሳይ በሚሆኑበት ጊዜ የአንዱ ወንጀል የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በሁለቱም ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆንና የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች የተለያዩ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ከሁሉም ከባድ የሆነው ወንጀል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን በሌሎች ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 217(2) ይደነግጋል፡፡ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ይርጋ በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል ወይም በሌላ ማሟያ የወንጀል ሕግ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ብቻ እንደሚያስቀጡ የተደነገጉ ወንጀሎች የግል ተበዳዩ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ የግል አቤቱታ ካላቀረበ በስተቀር ክስ እንደማይመሰረት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 212 ተደንግጓል ፡፡ ለአንብነትም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 560 የእጅ እልፊት ወንጀል በግል አቤቱታ ሲቀርብ የሚስቀጣ ወንጀል መሆኑ ተደንግጓል፡፡ መሰል በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ወንጀሎች የተፈፀመበት የግል ተበዳይ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 213 መሠረት አቤቱታውን ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን የእነዚህ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ብቻ የሚያስቀጡ ወንጀሎች የክስ ይርጋ ዘመን ሁለት አመት እንደሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 218 ተደንግጓል፡፡ ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 222 ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን የተደነገገ ሲሆን በማናቸውም ምክንያት ከላይ የተመለከትነው መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን እጥፍ ጊዜ ካለፈ ወይም በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች ሲሆኑ ደግሞ ከላይ ከተመለከትነው በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎችን የይርጋ ዘመን በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ ካለፈ በወንጀሎቹ ላይ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡ የክስ ይርጋ አቆጣጠር በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 219 መሠረት የክስ የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይገቡ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ ሲሆን የተፈፀመው ወንጀል በተለዋጭ ወይም በተደራራቢ ተፈፃሚነት በሚኖራቸውም ቅጣቶች የሚያስቀጣ ሲሆን የይርጋ ዘመኑ የሚታሰበው ከሁሉም ከባድ ለሆነው ወንጀል በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረውም ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱ እየተደጋገመ የተፈፀመ ከሆነም የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ የወንጀል ድርጊቱ ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ ከሆነ ደግሞ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀል ድርጊቱ ካቆመበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡ የክስ ይርጋ መታገድ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 220 የወንጀል ክስ ይርጋ የሚታገድበትን ሁኔታ የደነገገ ሲሆን ይኸውም  በሕግ ወይም በፍሬ ነገር ክሱ እንዳይጀመር ወይም እንዳይቀጥል የሚያግድ መሰናክል ካለ መሰናክሉ እስካለ ድረስ  ክስ ቀርቦ ነገሩ በዳኝነት በመታየት ላይ ከሆነ ወይም በሌላ ችሎት የቀረበ ክስ ሳይፈፀም ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ የማይገባ በሆነ ጊዜ የይርጋ ዘመኑ ታግዶ ይቆያል፡፡ መታገዱን ያስከተለው መሰናክል ሲወገድ ግን የይርጋ ዘመኑ ወዲያውኑ መቆጠር ይጀምራል፡፡ የይርጋ ዘመን መቋረጥ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 221 እንደሚያመለክተው ከወንጀሉ ወይም ከወንጀለኞቹ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርመራ እንዲካሄድ፣ ብርበራ እንዲደረግ፣ መጥሪያ እንዲሰጥ ወይም ክስ እንዲቀርብ የሚሰጥ ትዕዛዝ፣ የሚፈፀም ድርጊት ወይም የሚሰጥ ውሳኔ የይርጋ ዘመኑን መቆጠር ያቋርጣል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ የይርጋ ዘመን እንደገና እንደ አዲስ መቆጠር ይጀምራል፡፡ በድንጋጌው መሠረት የይርጋ ዘመኑ መቋረጥ ፍፁም የሆነ ውጤት የሚኖረው ሲሆን በወንጀሉ ተካፋይ መሆናቸው ለታወቀውም ሆነ ላልታወቀው ሁሉ መቋረጡ ይፀናባቸዋል፡፡ ይህ ማለት የወንጀል ተካፋይ መሆናቸው ወንጀሉ በተከሰተበት ጊዜ ያልታወቁ ሰዎች ያኔ ባለመታወቃቸው ምክንያት የይረጋ መቋረጥ አስመልክቶ ሊኖር የሚችል ልዩነት እንደሌለ መረዳት ይቻላል፡፡ በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች በመርህ ደረጃ የወንጀል ድርጊቶች ከተፈፀሙ በኋላ ክስ ለማቅረብ የሚቻልበት የጊዜ ገደብ በግልፅ ሰፍሮ ያለ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ በሌላ ሕግ ከተደነገገ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎች እንዳሉ ከወንጀል ሕጉ እንቀጽ 216(1) መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ መንግሥት ቀዳሚው ሲሆን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 28(1) መሠረት ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶችና በሌሎች የአገራችን ሕጎች የሰው ልጅ ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑ ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር ወይም የኢሰብዓዊ ድብደባ ድርጊቶችን በፈፀሙ ሰዎች ላይ

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • 29 июл.3 2861868

    #ዓቃቤ_ህግ_በቂ_ማስረጃ_ስላቀረበ_ብቻ_ተከሳሹን_ጥፋተኛ_ማድረግ_አይገባም!!! ___ #ታሪክ_ቀያሪ_የፌዴሬሽን_ምክር_ቤት__ውሳኔ_"ብየዋለሁ! የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀን 03/11/2018ዓ/ም በመዝገብ ቁጥር 151/2018 ላይ ታሪካዊ ዉሳኔ ሰጥቷል። የዉሳኔው ይዘት በሁለት ጭብጥ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን 👉1ኛዉ ጭብጥ የተከሰሰ ሰዉ ነፃ ሁኖ የመገመት መብት በዓቃቤ ህግ ላይ የሚጥለዉ የማስረዳት ሸክም በህገ መንግስቱ ተቀባይነት ያለዉ አነስተኛ መመዘኛ ምንድን ነው?? የሚል ሲሆን በመጨረሻም የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ዓቃቤ ህግ ተከሳሹ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ #ከምክኒያታዊ_ጥርጣሬ_በፀዳ_መልኩ(beyond reseaonable doubt) የማስረዳት ግዴታ አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህም ከዚህ በፊት የነበረዉን በቂና አሳማኝ የሆነ የማስረዳት ሸክም የሚለውን አሰራር የሚቀይር ነዉ!!! ስለዚህ ዓቃቤ ህግ በቂ ማስረጃ ስላቀረበ ብቻ ተከሳሹን ጥፋተኛ ማድረግ አይገባም ማስረጃው ከምክኒያታዊ ጥርጣሬ የፀዳ መሆኑ ሊረጋገጥ ግድ ነው ማለት ነዉ!!! 👉2ኛዉ ጭብጥ ፍርድ ቤቶች የጥፋተኝነት ፍርድ ከዓቃቤ ህግ የማስረዳት ሸክም አነስተኛ መመዘኛ እና ከተከሳሹ ነፃ ሁኖ የመገመት መብት አንፃር ያለዉን ህገ መንግስታዊነት እንዴት ይታያል?? የሚል ሲሆን የተከሳሽ ንፁህ ሁኖ የመገመት መብት ተከሳሽ #ከጥርጣሬዎች_ሁሉ_ተጠቃሚ እንዲሆን ጭምር የሚያደርግ ነዉ። በመሆኑም ከተከሳሽ የሚጠበቀዉ ዓቃቤ ህግ ያቀረበዉ ማስረጃ #ከምክኒያታዊ_ጥርጣሬ_ያልፀዳ_መሆኑንና በዚህ ማስረጃ የማስረዳት አቅም መተማመን እንደማይገባ ማሳየት የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ስለዚህ ከዚህ በሗላ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች የተሻለ አስረድተዋል: ተከሳሹ የዓቃቤ ህግን ማስረጃ አላስተባበለም: ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል ስለመፈፀሙ ዓቃቤ ህግ በበቂ ያስረዳ(የተመሰከረበት) ስለሆነ.....በሚሉ ምክኒያቶች ብቻ ተከሳሹን ጥፋተኛ ማለት እንደማይገባ እና ከማናቸውም ጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ ዓቃቤ ህግ የማስረዳት ግዴታ ያለበት መሆኑን በሙሉ ድምፅ አቋም ተይዞ ዉሳኔ ተሰጥቶበታል።Baye T page 👇👇👇👇 https://t.me/ethiolawtips

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • видоО иНи гОНОсОвОо, йоС пОдписи

  • 25 июл.4 3101696

    #ተተኪ_ወራሽ ለመሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥስ 110040 በሆነው በቅፅ 19 ላይ የተሰጠ አስገዳጅ ውሳኔ። ልጆች ተተኪ ወራሽ ለመሆን አባታቸው ከአያታቸው ቀድሞ የሞቱ መሆን ይገባል በማለት በአብላጫ የተሰጠ ውሳኔ ነው። https://t.me/ethiolawtips

  • 18 июл.5 5022964

    መ/ቁ. 107/15 ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ፌዴሬሽን ም/ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔ በተከራካሪ ወገኖች መካከል ያለ ጉዳይ በቃል በተደረገ የእርቅ ስምምነት ተፈጽሞ እንዳለቀ በችሎት በዳኞች ፊት ተረጋግጦ መዝገቡ ቢዘጋም የእርቅ ስምምነቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 274-277 በተደነገገው መሠረት በጽሑፍ ተደርጎ በተከራካሪዎቹ ተፈርሞና ስምምነቱም ሕግንና ሞራልን የማይቃረን መሆኑ በዳኞች ተመርምሮ ጸድቆ የመዝገቡ አካል ተደርጎ እስካልተያያዘ ድረስ የእርቅ ስምምነቱ ተፈጻሚነት የለውም። 👇 https://t.me/ethiolawtips

  • 18 июл.4 678836

    ባለዕዳው የውል ግዴታውን መፈጸም ባለበት ወቅት ሳይፈጽም አዘግይቶ፣ በኋላ ላይ ለተከሰቱ ችግሮች "ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት" (Force Majeure) በማለት የሚያቀርበው መከላከያ በሕግ ተቀባይነት የለውም። በአሁኑ ወቅት ባለዕዳው ምርቱን እያመረተ ያለ ፋብሪካ በመሆኑና ውሉ በተገባበት ወቅት የነበረው የምርት ዋጋ አሁን ካለው የገበያ ዋጋ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ መራራቁ እየታወቀ፣ ግዴታው በዓይነት እንዳይፈጸም መከልከል ባለመብቱን ለከፍተኛ ኪሣራ የሚዳርግና ባለዕዳውን ደግሞ ያለአግባብ የሚያበለጽግ ይሆናል። በመሆኑም ባለመብቱ በፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 1776 እና 2329 መሠረት ውሉ በዓይነት እንዲፈጸም (ምርቱ እንዲሰጥ) የመጠየቅ ሕጋዊ መብት ያለው ሲሆን፣ ባለዕዳውም በዚሁ አግባብ ምርቱን ለባለመብቱ ሊያስረክብ ይገባል። ባለዕዳው አሁንም ምርቱን እያመረተ ያለ በመሆኑ ውሉ በዓይነት እንዲፈጸም መወሰኑ የባለዕዳውን የግል ነፃነት የሚነካ አይደለም። ሰ/መ/ቁ.250756 (ሕዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም)👇👇 https://t.me/ethiolawtips

  • 18 июл.4 1561246

    #ፍርድ_ቤት ከተከራካሪ ወገኖች ውጭ በሥነ-ሥረዓት ህጉ መሠረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ ሳያደርጉ ለ3ተኛ ወገን ንብረት ነው በማለት የሚሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን #የፌደራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_ሰበር_ሰሚ_ችሎት በመዝገብ ቁጥር 162628 በሆነው የሰጠው ውሳኔ። ፍርድ ቤቶች ከተካራካሪ ወገኖች መካከል ጣልቃ ገብ ተከራካሪው በሥነ ሥርዓት ሕጉ መሰረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ እና ክርክሩን እንዲያቀርብ ባልተደረገበት ሁኔታ፣ ዳኝነት ባልተከፈለበት፣ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ንብረት የዉርስ ሀብት ሳይሆን የ3ኛ ወገን ንብረት ነዉ በማለት መወሰን የማይቻል ስለመሆኑ፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.182 (2)፤40 (2)

  • 8 июл.4 1541742иС fscethiopiaPR

    የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል ሕግ ትርጉም ውሳኔዎች ስብስብ (በየጉዳዮች የተደራጀ ልዩ እትም) ታትሞ ወጥቷል። ‎ ‎ይህንን ህትመት 4 ኪሎ በሚገኘው በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ልደታ ፍርድ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የብርሃንና ሰላም ሽያጭ መደብር የሚያገኙ ሲሆን ሶፍት ኮፒውን እዚሁ አያይዘናል። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ 👉ዌብ ሳይት ↠ https://www.fsc.gov.et/ 👉ፌስቡክ ↠ https://web.facebook.com/FSCEthiopia 👉ትዊተር (ኤክስ) ↠ https://x.com/federalsupreme1 ሊንክድኢን ↠ https://tinyurl.com/supereme-court-of-ethiopia 👉ቴሌግራም ↠ https://t.me/fscethiopiaPR 👉ዋትስአፕ ↠ https://tinyurl.com/fscethiopia 👉ዩቲዩብ ↠ https://www.youtube.com/@fscethiopia 👉ቲክቶክ ↠ https://tiktok.com/@federal.supreme.court

  • 11 июн.7 1801868

    በወንጀል የተከሰሰ ሰው የግል ተበዳይን በመከላከያ ምስክርነት ያቀረበና የግል ተበዳይም ድርጊቱ ያለመፈጸሙን በመግለጽ የምስክርነት ቃል የሰጠ ከሆነ ዓ/ህግ የግል ተበዳይ የምስክርነት ቃል በደላላ ወይም በጥቅም የተገኘ መሆኑን ለማረጋገጥ እስከ አልቻለ ድረስ ተከሳሽ ክሱን አልተከላከለም ሊባል የማይገባ ስለመሆኑ፡፡ ሰ.መ.ቁ 137545 ቅፅ 22