ነገረሕግ NegereHig
СтатистикаAbout laws Ethiopia.......ስለ ኢትዮጵያ ህግጋት.... ስለህጎችና ህግ ጉዳዮች ብቻ.......የህግ ነገሮችን It is All About Laws....Only Law Matters...... It is about law. ስለህጎች....... ጠበቃና የህግ አማካሪ ቢሮ አዲስ አበባ @AboutLaws_bot
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 07:26
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 192
- 1/48двое суток
- 220
- 1/72трое суток
- 237
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
"በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል። 👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የማይገመገሙ መሆኑ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። 👉 ህጎች በወጡ በሳምንት እና በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸውም እንዳሉም ተገልጿል። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና መጣረሶች እየታዩ መሆኑን፣ ይህንንም መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ፖሊሲም ሆነ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በሀገሪቱ አለመኖሩን ፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ። ጥናቱ "የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም በሀገሪቱ ያለውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የአተገባበር ስርዓት ከረጅምና ከአጭር ጊዜ እቅዶች እንዲሁም ከቦትስዋና፣ ከጋናና ከደቡብ አፍሪካ ተሞክሮዎች አንጻር በመመርመር የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ነው። ህግ የማህበረሰብንና የመንግስትን መስተጋብር የሚመራ መሳሪያ እንደመሆኑ ተለዋዋጭነት ባህሪው ቢሆንም፣ የሚወጡ ህጎች ጥራት፣ ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተገማችነትና ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጥናቱ ያስቀምጣል። ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተካሄደው የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በርካታ ህጎች የመውጣታቸውን ያህል፣ በችኮላና በጥድፊያ የሚወጡ ህጎች የህግ አወጣጥ ስርዓቱ የተረጋጋ እንዳይሆን፣ በህዝብና በባለሙያዎች ያልተመከረበት እንዲሆን እንዳደረጉት ጥናቱ ጠቁሟል። ይህም ባለሀብቶች የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዳይወስኑ፣ ዜጎችም ስለ መብትና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ አናሳ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተመላክቷል። ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ መመርመሩን ገልጿል። ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት፣ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በስድስት ተያያዥ ተቋማዊ ምሶሶዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን የለየው ጥናቱ እነሱም የህገ መንግስት የበላይነት በተግባር መረጋገጥ፣ ውጤታማ የስልጣን ክፍፍልና ሚዛን፣ ጠንካራ የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓት፣ በሙያ የታገዘ የረቂቅ ዝግጅት ተቋም፣ ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎ፣ እና ገለልተኛ የዳኝነት ቁጥጥር ናቸው። ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን ሀገሪቱ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋትን የተመለከተ ፖሊሲ እንደሌላት፤ ጠቅላላ የህግ አወጣጥ ስርዓትን የሚመራ ፖሊሲም እንደሌለ፤ የሚወጡ ህጎችም በአብዛኛው በጸደቁ ፖሊሲዎች ላይ ከመመስረት ይልቅ የአስፈጻሚውን ጊዜያዊ ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ሆነው መገኘታቸውን ለይቷል። በህግ ማዕቀፍ ረገድም ኢፌዲሪ ህገ መንግስት፣ ደንብ ቁጥር 6/2008፣ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና ሌሎች ሰነዶች ቢኖሩም፣ ከማርቀቅ እስከ አፈጻጸምና ክትትል ድረስ ያለውን ሂደት በአንድ ወጥነት የሚገዛ ማዕቀፍ አለመኖሩ ተጠቁሟል፤ ያለው አሰራርም በተበታተኑና በተበጣጠሱ መመሪያዎች ላይ የተመሰረተ ነው። በአተገባበር ደረጃም ከተለዩ ክፍተቶችም ውስጥ :- - ተደጋጋሚ የአዋጅ ማሻሻያዎች (ለምሳሌ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኤክሳይዝ ታክስ አዋጆች በወጡ በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑ) ፣ - ሰፊ የአዋጅ መሻሮች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ብቻውን 18 አዋጆችንና 35 ደንቦችን መሻሩ)፣ - ተደራሽ ያልሆኑ መመሪያዎች ፣ - ተቃራኒ ይዘት ያላቸው አዋጆች መውጣት፣ - ከበላይ ህጎችና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች መኖር (በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰልን በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የያዘ ድንጋጌ በመሆኑ ማክሰኞ ወጥቶ በሳምንቱ ማክሰኞ ማሻሻያ የተደረገበት ሂደት መኖሩ) - የበታች ህጎች ያለ ተገቢ ግምገማ መውጣት ( በተለይ ታክስ አካባቢ ይሄ ችግር በአደገኛ ሁኔታ መስተዋሉ) - አዋጆች በተግባር ያለመፈጸም ይገኙበታል። ከጥንካሬ አኳያም የተለያዩ ግኝቶችን ያስቀመጠው ጥናቱ ባለ ሶስት ደረጃ የምርመራና የንባብ ሂደት፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማጣራት ሚና፣ የህግ ማዕከልና አማካሪዎች መኖር፣ እንዲሁም በቅርቡ የተቋቋመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ማሻሻያና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ እንደ አዎንታዊ እርምጃዎች ተጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የባለሙያ እጥረት፣ የተቋማት አለመናበብ፣ የአመራር ትኩረት ማነስ እና ወጥ የህግ ይረቀቅልኝ ስርዓት አለመኖር እንደ ዋና ዋና ድክመቶች ተለይተዋል። ጥናቱ ከጋና፣ ከደቡብ አፍሪካና ከቦትስዋና ተሞክሮ በመነሳት ፦ ° ፍርድ ቤቶች ግልጽ የህገ መንግስት ተጣጣሚነት የመተርጎም ስልጣን እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ° የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓትን ማጠናከር፣ ° ሙያዊ የረቂቅ ዝግጅት አቅምን ማጎልበት፣ ° የህዝብና የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ተወካዮች ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ፣ ° ህግ ማውጣትን ከፖለቲካ ፍጥጫ ነጻ ማድረግ፣ ° የተጠቃለለ ፖሊሲና ሁሉን አቀፍ ህግ ማዘጋጀት፣ ° ገለልተኛ የህግ ኮሚሽን ማቋቋም፣ ° በዩኒቨርሲቲዎች የሌጂስሌቲቭ ድራፍቲንግ ስልጠናና ካሪኩለም ማዘጋጀት፣ ° የህግ አወጣጥ ሉዓላዊነትን ከውጭ ተጽእኖ መጠበቅ፣ እንዲሁም የበታች ህጎችን ከአዋጅ ጋር ተጣጥመው መውጣታቸውን የሚከታተል ስርዓት መዘርጋት የሚሉ ምክረሃሳቦችን አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#የግብር_ጉዳይ የኢትዮጵያ የፌደራል #ጠበቆች ማህበር ዝማኔ ኩነት ወይም Update on Current Affairs በሚል ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መደብዳቤ ማህበሩ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር የጠበቆች ግብር አከፋፈልና ከሙያው ልዩ ባህርይ ጋርየተጣጣመ የግብር ማዕቀፍ እንዲኖር በተከታታይ ውይይቶች ማድረጉን አስታውቋል። በእነዚህ ውይይቶች በተደረሰው መግባባት እና በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 በተደነገገው መሰረት ሊዘጋጅ የሚገባውን እና የባለሙያዎች የተቀናሽ ወጪ መመሪያ ለማዘጋጀት የሚረዳውን የፖሊሲ ግብዓት ሰነድ ማህበሩ የጥናት ቡድን በመመደብ ባለፉት አራት ወራት ሲሰራ ቆይቶ ስራውን አጠናቆ ሰነዱን ለገንዘብ ሚኒስቴር አስረክቧል ብሏል። ከዚያም በላይ ማህበራችን ጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ክትትል እያደረገ ይገኛል ብሏል። በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአዋጁ መሰረት የተቀናሽ ወጪ መመሪያው ጸድቆ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ ጠበቆች አመታዊ ገቢያቸውን በህጉ መሰረት በሚያሳውቁበት ወቅት ወጪያቸው ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንዲያዝላቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ በማስገባት ውጤቱን በመከታተል ላይ ይገኛል ብሏል። ማህበሩ የጠበቆችን ሙያ ልዩ ባህርይ የሚያንጸባርቅ ፣ ፍትሃዊ ፣ ግልጽ እና ተገማች የግብር ማዕቀፍ እንዲኖር ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የጀመረውን ስራ በቀጣይነት አጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ፣ እንዲሁም የመመሪያውን ዝግጅትና አፈጻጸም በቅርብ በመከታተል ለአባላቱ ተገቢውን መረጃ በየጊዜው ያደርሳል ብሏል። የሚበረታታና የሚደገፍ ጥረት ሲሆን ውጤቱ ደግሞ በጉጉት የሚጠበቅ ነው🙏🙏🙏 የሕግ ቤት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን አዲሱን የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር FVD/01/2026) ማንበብ ለምትፈልጉ ከላይ ሙሉ ሰነዱ ተቀምጧል!
видео или голосовое, без подписи
#የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪዎች የ Externship ክፍያ ስሌት! 2018 ዓ.ም ለሶስት ወር 34,500 ብር የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በ2013 ዓ.ም የመጨረሻ ዓመት የሕግ ተማሪዎች የኤክስተርንሽፕ ክፍያ እና ደረጃን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ በመለሰው መልስ ላይ የሕግ ተማሪዎች Exernship በሚወጡበት ጊዜ ከአንድ አመት ላልበለጠ ጊዜ በልምምድ ስለሚቆዩ የደረጃ VIII(8) ደሞዝ ሳይከፋፈል በየወሩ መሉ ደመውዙ እንዲከፈላቸው በማለት አሳውቋል። 2017 ላይ Extrnship የወጡ ተማሪዎች በወቅቱ የነበረውን የደረጃ 8(VIII) መነሻ ደሞዝ 6940 ብር ሲከፈላቸው ቆይቷል። 6940*3ወር= 20,820 ብር አጠቃላይ ክፍያ 2018 መንግስት የደሞዝ ማሻሻያ አድርጎ የደረጃ 8(VIII) መነሻ ደሞዝ ከ6940 ብር ወደ 11,500 ብር ከፍ ብሏል። በመሆኑም የፌድራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሸን የተለየ ሴርኩላር እና ማሻሻያ ካላደረገ በቀር የዘንድሮ የሕግ ተማሪዎች የእክስተርሺፕ ክፍያ በወር 11,500 11,500*3ወር= 34,500 ብር የደሞዝ ማሻሻያው እና የፌድራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል። https://t.me/AleHig ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service Website: alehig.com https://linktr.ee/alehig WhatsApp👉 #+251920666595 Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи