tgindex
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church.

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church.

Статистика

❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል። ❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/share/14c56nVbmLJ/

Последний пост
7 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
67
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
6 967
+3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
556
40 постов
Вовлечённость
8,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 67
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
418
1/48двое суток
479
1/72трое суток
516

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church. pinned «✝️ ውድ የቴሌግራሜ ቻናል ተከታታዮች ተወዳጅ ቤተሰቦቼ እንዴት ሰነበታችን ቸር አላችሁ #የሆልቤ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ወንድሜ፣ ለፍልሰታ ለማርያም እረዳታ የጠየኳችሁ፣ አንድ ወንድሜ ከአሜሪካ ሀገር፣ ከቤሩት ሊባኖስ የሚኖሩ እኅቶች አስተባብረው፣ በተለያዩ ባሕር ማዶ ሀገር የሚኖሩ ወንድሟች እና እኅቶች በላኩት ገንዘብ እናተንም በማስተባበር የተገዙት ሙሉ የማይክ ሲስተም፣ አንድ አነስተኛ የድምጽ…»

  • ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church. pinned «✝️ #ስለ_በኣታ_ለማርያም_በየዓመቱ_የምታደርጉት የተለመደው ትብብር እንድታደርጉል እንጠይቃለን። #ሼር_ሼር_ሼር በማድረግ ከበረከቱም ተካፋይ እንሁ። ✝️ አሁን ላይ የጾመ ፍልሰታ የበረከት ቀናት ደርሰዋል የእመቤታችንን ቤት እንዳይዘጋ የካህናቱ ያሬዳዊ ዜማ የኪዳኑ ጸሎት፣ ቅዳሴ እንዲሰማ እንተባበር። ✝️ ይች በምስሉ የምትመለከቷት በከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የምትገኘው…»

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤ ውድ የቴሌግራሜ ቻናል ተከታታዮች ተወዳጅ ቤተቦቼ እንዴት ሰነበታችሁ ቸር አላችሁ ኔትወርክ ወደ ማይሠራቦት ቦታ ወጣ ስላልኩ #ከነሐሴ_2_እስከ_ነሐሴ_18 ያለው ቀድሜ Post አድጌዋለሁ ወደኋላ እያላችሁ የየቀኑን ተመልከቱ  አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ጾሙን በሰላም አስጀምሮ በሰላም አስጨርሶ ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለብርሃነ ትንሣኤዋና ዕረገቷ ያድርሰን። ለሁላችንም የበረከት ጾምና መልካም ሱባኤ ይሁንልን።                  @Teamihokidusan

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ ነሐሴ ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን #ለእስክንድርያ_ዐሥራ_ዘጠነኛ ሊቃነ ጳጳሳት በኒቅያ ጉባኤ #በ325 ዓ.ም  አርዮስ #ከአባ_አትናቴዎስ ጋር በመሆን ተከራክሮ ላወገዘው ለታላቁ አባት #ለአባ_እለእስክድሮስ ለመታሰቢያው በዓሉና ለእመቤታችን ለትንሣኤዋና ለዕርገቷ ሦስተኛ ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚች ቀንከሚታሰበው፦ #ከዲያቆን_እንድራኒቆስ ከመታሰቢያው በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለእለእስክንድሮስ ዘደለዎ ጵጵስና ስርግው በቅድስና"። ትርጉም፦ ጵጵስና የተገባው ለኾነ በቅድስና ላጌጠ (ለተሸለመ) #ለአባ_እለእስክንድሮስ ሰላምታ ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_እለእስክንድሮስ፦ እርሱም ቊጥሩ ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ነው። ይህም አባት ከአርዮስ ወገኖች ብዙ ችግር ደርሶበታል እርሱ ከወገኖቹ ጋር ሁኖ አርዮስን አውግዞ ከቤተክርስቲያን አሳዶት ነበርና። ❤ በታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘመን በኒቅያ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ሊቃውንት አርዮስን በጉባኤ አውግዘው ከቤተ ክርስቲያን ለይተው በአሳደዱት ጊዜ ወደ ንጉሡ ቈስጠንጢኖስ ጓደኞቹን ይዞ ገብቶ በእለእስክንድሮስና በአትናቴዎስ ላይ ነገር ሠራ ሁለተኛም እለእስክንድሮስ ከካህናቱ ጋር ይቀበለው ዘንድ እንዲያዝለት ንጉሡን ለመነው። ❤ ንጉሡም ልመናውን ተቀብሎ መልእክተኞችን ልኮ አባት እለእስክንድሮስን አስመጥቶ እንዲህ አለው "አትናቴዎስ ትእዛዛችንን በመተላለፍ አርዮስን አልቀበልም ብሏል፤ እኛም አንተን እንዳከበርንህ አንተ ታውቃለህ አሁንም ትእዛዛችንን አትተላለፍ አርዮስንም ከውግዘቱ ፈትተህ ልባችንን ደስ አሰኝ" አለው ። ቅዱስ እለእስክንድሮስም ለንጉሥ እንዲህ ብሎ መለሰለት "አርዮስን እኮን ቤተክርስቲያን አልተቀበለችውም። ልዩ ሦስትነትን አያመልክምና" ንጉሡም "አይደለም እርሱ በሥሉስ ቅዱስ ያምናል እንጂ" አለው ቅዱስ እለእስክንድሮስም "ወልድ በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ትክክል እንደሆነ የሚያምን ከሆነ በእጁ ይጻፍ" ብሎ መለሰለት። ❤ ንጉሥም አርዮስን አስቀርቦ "ትክክለኛ ሃይማኖትህን ጻፍ" አለው አርዮስም በልቡ ሳያምን "ወልድ ከአብ ጋራ በመለኮቱ ትክክል ነው" ብሎ ጻፈ በሐሰትም የከበረ ወንጌልን ይዞ ማለ። ንጉሡም ቅዱስ እለእስክንድሮስን "አሁን በአርዮስ ላይ ምክንያት አልቀረህም ትክክለኛ ሃይማኖቱን ጽፎአልና በከበረ ወንጌልም ምሎአልና" አለው ። ❤ አባ እለእስክንድሮስም ንጉሡን እንዲህ አለው "በአባትህ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እጅ የተጻፈ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ አባቶች በእጆቻቸው የጻፉትን እርሱንና ወገኖቹን ከቤተ ክርስቲያን እንዳሳደዷቸው የአርዮስን ክህደቱንና ውግዘቱን አትናቴዎስ አንብቦታል። ነገር ግን አንድ ሱባዔ በእኔ ላይ ታገሥ በዚህ ሱባዔ በአርዮስ ላይ አንዳች ነገር ካልደረሰ ይህ ካልሆነ ሃይማኖቱ መሐላውም እውነት ነው እኔም ተቀብዬ ከካህናቱ ጋር እቀላቅለዋለሁ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም ከእሳቸው ጋራ አንድ ይሆናል"። ❤ ንጉሡም አባት እለእስክንድሮስን እንዲህ አለው "እወቅ እኔ ስምንቱን ቀኖች እታገሥሃለሁ አርዮስን ካልተቀበልከው በአንተ ላይ የፈለግሁትን አደርጋለሁ።" ከዚህም በኋላ ከንጉሡ ዘንድ ወጥቶ ወደ ማደሪያው ሔደ ቤተክርስቲያንን ከአርዮስ መርዝ ያድናት ዘንድ በዚያ ሱባዔ እየጾመና እየጸለየ ወደ እግዚአብሔር ሲለምን ሰነበተ። ❤ ከዚያም ሱባዔ በኋላ አርዮስ መልካም ልብስን ለበሰ ወደ ቤተክርስቲያንም ገብቶ በመሠዊያው ፊት ከካህናቱ ጋራ ተቀመጠ። ከዚህም በኋላ አባ እለእስክንድሮስ እያዘነና እየተከዘ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ የሚሠራውን አላወቀም የቅዳሴውንም ሥርዓት ሊጀምር ቆመ። ያን ጊዜ የአርዮስ ሆዱ ተበጠበጠና "ወጥቼ ልመለስ" አለ ይህንንም ብሎ ወደ መጸዳጃ ቦታ ወጣ። ሊጸዳዳም በተቀመጠ ጊዜ አንጀቱና የሆድ ዕቃው ሁሉ ወጣ በዚያውም ላይ ሞተ። በዘገየም ጊዜ ሊፈልጉት ወጡ በመጸዳጃውም ቦታ ሬሳውን ወድቆ አገኙት። ለዚህም ለአባት እለእስክንድሮስ ነገሩት እርሱም አደነቀ የከበረች ቤተክርስቲያኑን ያልጣላት ምስጉን የሆነ ክርስቶስንም አመሰገነው። ❤ ንጉሡም በሰማ ጊዜ አደነቀ ከሀዲ አርዮስም በሐሰት እንደማለና በሽንገላ እንደጻፈ አወቀ። የዚህንም አባት የእለእስክንድሮስን ቅድስናውን ዕውነተኛነቱ ሃይማኖቱም የቀናች መሆኗን የአርዮስንም ሐሰተኛነቱንና ከሀዲነቱን ተረዳ። ❤ አንድ የሆነ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስንም አመሰገነው መለኮታቸውም አንድ እንደሆነ ታመነ። ይህም አባት በበጎ ሥራ ጸንቶ ኖረ ለምለም ወደ ሆነ እርግናም ደርሶ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ የሕይወት አክሊልንም አገኘ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ እለስክንድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 18 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለከ_እለእስክንድሮስ ሥዩም። በዕብረሬት ዘወረደ ኃይለ አርያም። ለአርዮስ ውቁይ በሰይፈ መርገም። እስከ ኢተርፈ ሎቱ እንበለ አነዳ ወዐፅም። ንዋየ ውስጡ ተክዕወ ከመ ዐፍዕ ዘላህም"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_18።                 @Teamihokidusan

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ነሐሴ ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_ጻድቅ_ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት አባት ለአባታች #ለካህኑ_ቅዱስ_ጸጋ_ዘአብና ለእናታቸው ለቅድስት እግዚእ ኃረያ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የካህኑ_ቅዱስ_ጸጋ_ዘአብ_ዕረፍት፦ በዚያም ወራት ከሦስት መቶ ሠላሳ ሦስት ዘመን በኋላ በሐምሌ ሰባት ቀን እግዚአብሔር መንግሥትን ከዛጌ ወገን የእስራኤል ወገለሚሆን ለይኵኖ አምላክ መለሰ። በየሀገሩ ሁሉ ጸጥታ ፍቅር አንድነት ሆነ። ከጥቂት ቀን በኋላ እናቱ እግዚእ ኃረያ በነሐሴ 12 ቀን ዐረፈች እርሷም ባረፈች በአምስተኛው ቀን በነሐሴ 17 ቀን አባቱ ጸጋ ዘአብ ዐረፈ። የሁለቱ ቅዱሳን በረከት ብልህ አዋቂ የሚሆን የልጃቸውም በረከት በእኛ ላይ ትደር ለዘለዓለሙ በእውነት። ፍሰሓ ጽዮንም እናት አባቱ ስላረፉበት አዘነ ነገር ግን ፈቃደ እግዚአብሔር አጸናው። በሚናገረው ነገር በሚመራው ሥራ የሚቻለው ሆነ እግዚአብሔርንም የሚያገለግል ሆነ..."። ከአባታች ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 28፥1-3።                  @Teamihokidusan

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                                                 ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለጊጋር_ሰማዕት_መስፍነ_ሶርያ፤ ዘተጋደለ በቅድመ ሄሮድስ ረሲዕ በእንተ ማርያም ወሕፃና ኢየሱስ ኬንያ፤ እምድኅረ ተቀትለ በሰይፍ መጺኦ በፈረሰ እሳት ጸዐዳ፤ ዘጸፍኦ ለሄሮድስ ፫ተ ጽፍአተ ኵሎን አባላቲሁ እስከ ይርዕዳ ወእስከ ይውኅዝ ደም ወመግል እምአዕናፊሁ በኵሉ መዋዕሊሁ"። ትርጉም፦ ስለ ማርያምና ጠቢብ ስለኾነው ስለ ልጇ ኢየሱስ በከሓዲው ሄሮድስ ፊት የተጋደለ፤ በሰይፍ ከተገደለ በኋላም በነጭ የእሳት ፈረስ መጥቶ መላዎች፡ ውነቶቹን ኹሉ እስኪርዱ ድረስ ሄሮድስን ሦስት ጊዜ በጥፊ የተመታውና በዘመኖቹ ኹሉ ባፍንጮቹ ደምና መግል እንዲፈስስ ያደረገው ለኾነ ለሶርያው መስፍን ለሰማዕቱ ጌጋር ሰላምታ ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን ላይ።                @Teamihokidusan

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምልጣን_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "በኃይለ አጥናን ዘሞዖ ለሰይጣን አሐዱ ቅዱስ እምቅዱሳን ጊዮርጊስ ረባን ሰባኬ ትንሣኤሃ ለእመ ብርሃን አማን ምዑዝ ከመ ዕጣን"። ትርጉም፡- በቅድስት ሥላሴ ኃይል (በሰባቱ ሀብታት ኃይል ሰይጣንን ያሸነፈው) ከቅዱሳን አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ መኰንን (የነገሥታት ዘር) ለብርሃን እናት ትንሣኤዋን የሚመሰክር በእውነት እንደ ዕጣን መዓዛው ያማረ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።                 @Teamihokidusan

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለፍልሰተ_ሥጋኪ ደባትረ ብርሀን ኀበ ተተክሉ። ለገነተ ጽባሕ በማእከሉ ውድስት አንቲ ወስብሕት በአፈ ኵሉ። እምነ ጻድቃን ዘታሕቱ ወእምትጉሃን ዘላዕሉ። #ማርያም_ለኪ_ስብሐተ አደሉ"። ትርጉም፦ #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ በምሥራቃዊ ተክለ ገነት መካከል የብርሃን ድንኳኖች ወደ ተተከሉበት #ለዐረገ_ሥጋሽ_ሰላምታ_ይገባል። ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ። በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም። ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል። #መልክአ_ማርያም።               @Teamihokidusan

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምልጣን_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "በኃይለ አጥናን ዘሞዖ ለሰይጣን አሐዱ ቅዱስ እምቅዱሳን ጊዮርጊስ ረባን ሰባኬ ትንሣኤሃ ለእመ ብርሃን አማን ምዑዝ ከመ ዕጣን"። ትርጉም፡- በቅድስት ሥላሴ ኃይል (በሰባቱ ሀብታት ኃይል ሰይጣንን ያሸነፈው) ከቅዱሳን አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ መኰንን (የነገሥታት ዘር) ለብርሃን እናት ትንሣኤዋን የሚመሰክር በእውነት እንደ ዕጣን መዓዛው ያማረ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለጊዮርጊስ_ተውላጠ_ፃማሁ ወሕማሙ። እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። በፍልሰትኪ ድንግል (ዮም) ተቶስሐ ፍልሰተ ዓፅሙ። እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ አሜሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ"። #መልክአ_ፍልሰታ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ16።                 @Teamihokidusan

  • видео или голосовое, без подписи

  • ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ።  በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል። እግዚአብሔር ውስተ ማእከላ ኢትትሀወክ። ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ"። መዝ4፥4-5 ወይም መዝ 121፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት የሚነበበው ሮሜ 8፥31-ፍ.ም 2ኛ ዮሐ 1፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። ወንጌል ማቴ 26፥26-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤዋና የዕረገቷ በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።                  @Teamihokidusan

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church. — tgindex