የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
Статистика- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 3 401
- 1/48двое суток
- 3 897
- 1/72трое суток
- 4 203
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የ2019 ዓ.ም የሥርዓተ ትምህርት ማስተግበሪያ የጊዜ ሰሌዳ በተመለከተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ተልዕኮ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ጎልማሶችን በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት የጸኑ፣ ሥነ ምግባራቸው ያማረ፣ ቀደምት አባቶቻቸውን በመምሰል ቤተ ክርስቲያንን የሚረከቡ እና ሀገርን የሚጠብቁ ትውልድን የማፍራት ሥራውን በመሥራት ላይ ይገኛል። ይህንንም ከተዥጎረጎረ እና ወጥነት ከጎደለው፣ ለአንድ ዓላማና ግብ የተናጠል ሩጫ ከበዛበት አሠራር ሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ተላቀው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በአንድ ሐሳብና በአንድ ቃል እንዲጓዙ የሚያስችል ሥራን በመሥራት ላይ ይገኛል። ከነዚህም አንዱና ዋነኛው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ነው። ይህም ሥርዓተ ትምህርት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት በትግበራ ላይ ይገኛል። ሰንበት ትምህርት ቤቶችም ለአተገባበር ያመቻቸው ዘንድ ዓመታዊ የትምህርት መርሐ ግብር የሚያስፈልግ በመሆኑ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ይህን ማስተገበሪያ ሰነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል። ይህም ዓመታዊ የትምህርት ማስተግበርያ ሰነድ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል። በዚህ ማስተግበርያ ሰነድ ውስጥ የዓመቱን የትምህርት መርሐ ግብር መጀመርያ እና መጨረሻ ጊዜ፣ የፈተና መርሐ ግብራት፣ የሴሚስተር የሪፖርት ጊዜያትን፣ የመርጃ መሣርያ ዝግጅትን ወዘተ በዝርዝር የያዘ ነው። ለዚህም የትምህርት መርሐ ግብር የየአህጉረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እንዲሁም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሓላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ሰፊውን ድርሻ መያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ የትግበራ ሰነድ ወይም የትምህርት መርሐ ግብር በተቀመጠለት ጊዜና ሰዓት ተፈጻሚ መደረግ ይኖርበታል። ሰነዱንም በአንድነቱ የዌብሳይት ገጽ ላይ ከስር ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://eotc-gssu.org/a/የ2019-ዓ-ም-የሥርዓተ-ትምህርት-ማስተግበሪያ/ መንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሐምሌ 2018 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉 Website
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደ/ጎንደር ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍልና በሰ/ት/ቤቶች አንድነት ሲሰጥ የቆየው የመምህራን ስልጠና ተጠናቀቀ። ሐምሌ 29/11/2018ዓ.ም የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ስልጠናው የተሰጠው ከሐምሌ 12-26/ 2018 ዓ.ም ሲሆን ከወረዳዎች የተውጣጡ 71 የሚደርሱ የአሰልጣኞች ሥልጠና ተሳታፊዎች በ15 ቀናት ለ200 ሰዓታት የተሰጠውን ሥልጠና ጨርሰው ተመርቀዋል። በምርቃት መርሐ ግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አሰኪያጅ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምሕረት ሞላ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊ መላከ ብርሐን ቀሲስ ዘውዱ አበጀ፣ የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ሓላፊ ሊቀ ጉባኤ ሳሙኤል እንየው እንዲሁም የየመምሪያ ሓላፊዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሰ/ት/ቤት አባላት ተገኝተዋል። በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል በሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ሓላፊ ሊቀ ጉባኤ ሳሙኤል እንየው የተሰጠ ሲሆን በተመራቂ መምህራን ለዕለቱ የሚስማማ ወረብ ቀርቧል። የዚህ ስልጠና ዋናው ዓላማው በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ሕፃናት ከልጅነታቸው ነገረ እግዚአብሔርን አውቀው ለቤተክርስቲያናቸው እና ለሀገራቸው ዘብ የሚቆሙና የሚጠቅሙ ትውልድ ማፍራት ነው። በመጨረሻም ለተመራቂዎች የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ሥልጠናው የተሳካ እና ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል ። መረጃው፦ የደ/ጎ/ሀ/ስ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉 Website
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ለ3ኛ ጊዜ የሀገረ ስብከት አቀፍ ፈተና ለ4ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ10ኛ ክፍል ከ2500 በላይ የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ሐምሌ 26/2018 ዓ/ም መስጠቱን አስታወቀ፡፡ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በ2018 ዓ/ም ለ3ኛ ጊዜ የሀገረ ስብከት አቀፍ ፈተና ለ4ኛ፣ ለ8ኛ እና ለ10ኛ ክፍል የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች 6 ፈተናዎች በየትምህርት ዓይነቱ በ2ቱም ቋንቋ (በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ) በትላንትናው ዕለት ጠዋትና ከሰዓት እንዲሰጥ አድርጓል፡፡ በመንበረ ጵጵስና፣ በቢሾፍቱ አካባቢውና በአድአ፣ በአዳሚ ቱሉ፣ በሉሜ፣ በዱግዳ፣ በቦሰት እና በፈንታሌ በድምሩ በ8 የወረዳ ቤተክህነት ሥር በሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች በተመረጡ ማዕከላዊ የምዘና ጣቢያዎች ምዘናው ተሰጥቷል፡፡ መረጃው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉 Website
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи