tgindex
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት

Статистика

ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ቻናል ነው

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
855
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
440
21 постов
Вовлечённость
51,5%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
100
1/48двое суток
114
1/72трое суток
123

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እንዴት  አደራችሁ  ተወዳጆች ?♡♡ ድክመቶቼን  ማወቄ  ምንድነው  የሚጠቆመኝ ?   ካልን አንድ ሰው ድክመቶቹን ካወቀ እግዚአብሔርን ያውቃል። ''ስደክም ያንጊዜ ኃይለኛ ነኝና'' 2ቆሮ 12፡10። ኃጢአቴ ምን ያህል አስነዋሪ እንደሆነ ሳረጋግጥ የእግዚአብሔርን ፀጋ እሻለሁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል "ጌታ ሆይ  እኔ  ኃጢያተኛ  ነኝ  ከእኔ  ተለይ " ሉቃ 5፡8። ቅዱስ ጴጥሮስ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንዳለ ተሰምቶታል። ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አለው ''አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ'' ሉቃ 5፡10 ቅዱስ ጴጥሮስ ለታላቅ ተልእኮ እና አገልግሎት የበቃው መቼ ነበር? ይህ የሆነው ራሱን ባወቀ ቅጽበትና "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" ብሎ በተናገረ ጊዜ ነበር። የሰው ልጅ በእንዲህ ዓይነት ስሜት ውስጥ በሆነ ጊዜ እግዜአብሔር እንዲህ ይላል። "አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ"። ስለዚህ ራሳችንን ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው። "ከአቡነ  ሺኖዳ  የሕይወት መዓዛ  ከሚለው  መጽሐፍ  የተወሰደ" መልካም  ቀን  ይሁንልን  ❤️❤️❤️ https://t.me/ardssu

  • “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ https://t.me/ardssu

  • ​"የሰውን ጉድና ድክመት ይዞ መሮጥ የባሪያ ነፍስ ምልክት ነው። ሐሜተኛ ሰው የራሱን ቆሻሻ ቤት ረስተው የሌሎችን መስኮት በመጥረግ ይጠመዳል። የሌሎችን ስም የሚያጠፋ ሰው፣ የራሱን ክብር ከሰማይ ወደ ታች እየወረወረ መሆኑን ልቡ አያውቅም። ንጹሕ ሕሊና ያለው ሰው የሰውን ድክመት በዝምታ ይሸፍናል እንጂ በገበያ ውሎ አያወራም።" ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ፣ የተቀደሰ  መልካም  ቀን  ይሁንልን 🙏🥰 https://t.me/ardssu

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 29 июл.330из eotcgssu21

    видео или голосовое, без подписи

  • 29 июл.2531из eotcgssu21

    4ኛው የአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ተከናወነ። የሰ/ት/ቤቶች አንድነት (ሐምሌ 22 / 11 / 2018 ዓ.ም) 4ኛው የአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር በትላንትናው ዕለት በቅድስ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ተከናወናውኗል። በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዌሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰሜን ሸዋ እና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሐላፊ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ሐላፊዎች ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አመራሮች እንዲሁም ከ37 አህጉረ ስብከት ተወጣጥተው ከሐምሌ 06 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተመራቂ ሰልጣኝ መምህራን በተገኙበት ተከናውኗል። የዕለቱን ቃለ እግዚአብሔር በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ መልካም ፈቃድና በመምሪያው ሊቀ ጳጳስ ጋባዥነት ያስተማሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሲሆኑ በ1ኛ ቆሮ 8፡2 ላይ "ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስን ቃል አንስተው ልናውቀው የሚገባውን ምሥጢር እግዚአብሔርን መውደድና መፍራት መሆኑን አስተምረዋል። በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የማደራጃ መምሪያ ሐላፊ መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ "በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል። በአምላካችን አደባባይ ይበቅላሉ።" መዝ 91፡13 የሚለውን የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትን ቃል መነሻ በማድረግ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን እንዲሁም ለሥልጠናው መሳካት አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ አጠቃላይ የሥልጠናውን ሒደት የተመለከተ ሪፖርት በዲ/ን ስንታየሁ ምስጋና የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ በኩል የቀረበ ሲሆን ሠልጣኞቹ የነበራቸውንም ቆይታ የተመለከተ ሪፖርት በተወካያቸው በኩል አቅርበዋል። በመጨረሻም አባታዊ ቡራኬ ቃለ ምዕዳን እና መመሪያ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተሰጥቶ የምርቃቱ ፍጻሜ ሆኗል። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

  • እንኳን ለገናናው መልአክ ቅዱስ ኡራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ https://t.me/ardssu

  • ምክረ አበው ከወድሞች አንዱ ወደ አረጋዊ መጣና " አባ ፣ ደካማ ነኝና ጸልዩልኝ " አለው፡፡ አረጋዊም እንዲህ አለው " በሸተኛን ይቀባ ዘንድ በእጁ ቅባት የሚይዝና ሌላውን የሚቀባ ሰው እርሱም ደኀና ሆኖ ይቀባል፡፡ እንዲሁም እኛም ለሌላው ስንጸልይ ለራሳችን መድኃኒትና ፍስሐ ይሆነናል፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይና እርስ በርሳችን በጸሎት ልንተሳሰብ ይገባናል፤ ሐዋርያው " ትድኑ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ ጸልዩ " ብሎ እንዳዘዘን፡፡ #ከበረሐውያን_ሕይወትና_አንደበት https://t.me/ardssu

  • видео или голосовое, без подписи

  • 27 июл.1 00034

    አስቸኳይ የእርዳታ ተማፅዕኖ😭😭 "እነሆ አገልጋይን ማዳን አገልግሎትን ማዳን ነው" 🙏🙏🙏አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ🙏🙏🙏 በመላው ዓለም የምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ከታች በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን ዘማሪት ሰርክ አዲስ ኃ/መስቀል (ዘማሪት ሐና) ትባላለች። በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴደራል ፍኖተ ወንጌል ስንበት ት/ቤት አገልጋይ ስትሆን ባጋጠማት ከፍተኛ የልብ ሕመም ምክንያት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል ስታደርግ የቆየች ቢሆንም አሁን ላይ ህክምናው ከአቅም በላይ በመሆኑ ምክንያት ለቀዶ ጥገና ከ 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ስለተጠየቅን ይህችን ዘማሪት እህታችንን በማሳከም ወደ አገልግሎት እንመልሳት ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ከታች ባሉት አካውንቶች የቻላቹህትን የአቅማቹን አግዙን🙏🙏 👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(CBE) 1000783587487 👉አቢሲኒያ ባንክ(BOA)  13339538 👇👇👇👇👇 ለበለጠ መረጃ                              👉09 23 31 40 15                            👉09 12 62 12 20

  • [ሐምሌ 19 የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል] ✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ዶሮዳስ ታደሰ ❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው። ❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡ ❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡ ❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡ ❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል። ❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ዐምስት መቶ ሦስት በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡ ✔ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡- “እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ ወስምዖ መጥበቤ ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ ለአባልከ ሰላም እቤ” (እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ)  እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦ “ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ በልደት ንዑስ፤ ንጹሕ ከመ ዕጣን ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡ (በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል) ❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡ (ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨ [የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨ [ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ https://t.me/ardssu

  • видео или голосовое, без подписи

  • "በመናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቅዱስነታቸው በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ አባታዊ መልእክት አስተላላፉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! "ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦ እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።" (መዝሙር ፻፪፥፮) ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት። በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው። መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን! በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው። በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ። በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን። እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን። አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ © የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

  • 24 июл.1 22014

    *<<ወዳጄ ሆይ>>* _«ስለ *ምሕረትና ፍቅር* »_ _«ልብህ ለፍጥረታት ሁሉ የሚራራ ይሁን፤ ልብህ ሰፊ ይሁን።_ ለአራዊት፣ ለአእዋፍ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ—እንዲያውም ለአሳዳጆችህና ጠላቶችህ እንኳ ሳይቀር በፍቅርና በዕንባ ጸልይ። ቅዱስ ልብ ማለት ስለ ፍጥረት ሁሉ እያሰበ በፍቅር የሚቃጠል ልብ ነው። ኃጢአተኛውን ስታይ አትናቀው፤ ይልቁንም 'እኔ ከእሱ የባስኩ ነኝ' ብለህ አስብ። እግዚአብሔር ለዓለም ያለው ፍቅር ከባሕር አሸዋ ይበልጣል። የሰው ልጅ ኃጢአት ወደ እግዚአብሔር ምሕረት ሲጣል፣ ወደ ባሕር እንደተወረወረ አንድ ጠብታ ውኃ ነው—ይጠፋል! ስለዚህ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ አትደቅ፤ ምሕረቱ ከኃጢአትህ በላይ ነውና።» *ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ💙🦋* መልካም ቀን🙏🙏🙏🙏 https://t.me/ardssu

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት — tgindex