EOTC TV (በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት)
Статистика- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 43
- Всего постов
- 50
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 728
- 1/48двое суток
- 1 980
- 1/72трое суток
- 2 135
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
https://youtu.be/zmw9odKWryQ?si=ReSbmlwNrpJLwEG_
ማስታወቂየ
የአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ልማት
ጾምና ስግደት ለጤና ያላቸው አስተዋፅዖ
የቀሲስ እሸቱ ዳምጠው ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቀባበል ተደረገላቸው
ቤተ ክርስቲያኗ አሠራሯን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ልታሸጋግር ነው
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከግሪክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ፲፬ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ መ/ር ጌታቸው በቀለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፭ኛ ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፲፬ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ በዓል እሑድ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎት ታስቦ ይውላል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም ነበር። እነሆ ፲፬ ዓመታት ተቆጠሩ። ቅዱስነታቸው በጥቂቱ ሲታወሱ፡- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ወንጌልን በማስፋፋት የቤተክርስቲያንን አስተዳደር ለማጠናከርና የቤተክርስቲያኒቱን ዓለም አቀፍ ግንኙነት ለማስፋት ያላሰለሰ ጥረትን አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከውጭው ክፍለ ዓለም ጋር በመገናኘት ከኦርየንታልና ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲጠነክር አድርገዋል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ያላት ተሰሚነትና ተቀባይነት አንዲያድግ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመላው ዓለም እንድትስፋፋ ያደረጉ ታላቅ ዓለም አቀፋዊ አባት ነበሩ፡፡ ቤተክርስቲያናችን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘመነ ክህነት የሀገርና የዓለም አቀፍ ይዘቷን እያጠናከረችና እያሰፋች በመጣችበት ወቅት፤የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ፣ የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኰሌጅ፣ የፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኰሌጅ እንዲከፈቱ አድርገዋል፤ በደርግ መንግሥት ተወርሰው የነበሩትን የቤተክርስቲያን ሕንፃዎችንና ንብረቶችን አስመልሰዋል፡፡በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲታነጽ አድርገዋል፡፡ ወደ የአህጉረ ስብከቱ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ በየገዳማቱና አድባራቱ እንዲሁም በገጠር በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በመገኘት ከቤተ መቅደሱ ክህነታዊ አገልግሎት ጀምሮ በሚሰጡት ቀኖናዊ መመሪያ፤ አባታዊ ቡራኬ፣ ቃለ ምዕዳንና ትምህርተ ወንጌል፤ካህናት በቤተክርስቲያን አገልግሎታቸው፤ምእመናንም በእምነታቸውና በአንድነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ አድርገዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ሰብሳቢ ያጡ ዕጓለ ማውታ ሕፃናት፣ በአንድነት ተሰባስበው እየተማሩ እንዲያድጉ በማድረግ፤ የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታደስ፣ በተለያዩ ቦታዎች አዳዲስም አብያተ ክርስቲያናት እንዲሠሩ ማድረግ የቅዱስነታቸው የዘወትር ተግባር ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ጠንካራ ሥራ ከሀገር፣ ከአህጉርና ከወገን አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝቶ ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የናንሰን ሜዳይ ተሸልመዋል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስነታቸው በፕትርክና ዘመናቸው የቤተክርስቲያንን ሉዓላዊነት ያስከበሩ፣ የቋንቋ ባለቤትና የባለ ምጡቅ አእምሮ ባለቤት ሲሆኑ፤ በመስቀል ደመራና በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት በሚያስተምሯቸው ትምህርቶችና በሚያስተላልፏቸው ዓለማቀፋዊ መልእክቶች የብዙ ቱሪስቶችን ቀልብ የሳቡ ነበሩ፡፡ የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization( UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ ያደረጉና በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ሲታወሱ የሚኖሩ አባት ናቸው፡፡ በዓለ ዕረፍት እሑድ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም የቅዱስነታቸው ክቡር ሥጋቸው ባረፈበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት፣ ምእመናንን የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ያሳደጓቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው፣ በተገኙበት ከጧቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከታቸው ይድረሰን፡፡ አሜን!!!
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ቅዱስ ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር ሚስተር አንቶንዮስ ስጉሮፖሎስን (Antonios Sgouropoulos) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። መ/ር ጌታቸው በቀለ (#EOTC_TV ግንቦት ፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ የግሪክ ኤምባሲ አምባሳደር አንቶኒዮስ ስጉሮፖሎስን (Antonios Sgouropoulos) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት በግሪክ አቴንስ ከተማ በምትገኘው ምክሐ ደናግል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በምእመናንና በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ጋር በነበረው አለመግባባት የተነሣ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከ40 ዓመታት በላይ አገልግሎት ስትሰጥ የነበረችው ቤተክርስቲያን አገልግሎቷ ሊቋረጥ ችሏል፤ በዚህም የተነሣ በሀገሪቱ ሕግ መሠረት በግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር ትእዛዝ መሠረት ተዘግታለች። ይህች ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናንን በአቴንስ አገልግሎት ስትሰጥ የነበረ ታሪካዊ ማዕከል መሆኗ ይታወቃል። ይህን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ቅዱስነታቸው በኢትዮጵያ የግሪክ ኤምባሲ አምባሳደር ከሆኑት አንቶኒዮስ ስጉሮፖሎስ ጋር ቤተክርስቲያኗ ስለምትከፈትበትና አገልግሎቱ የሚጀመርበትን አካሄድ በተመለከተ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በውጩ ሀገራት ለሚገኙ ምእመናን መንፈሳዊ አገልግሎት የምትሰጥ ብቻ ሳይሆን ትውልዱ በመልካም ሥነ ምግባር ተኮትኩቶ እንዲያድግ የምታደርግ ናት፡፡ ቤተክርስቲያኗ ባህላዊ ማዕከል (በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው ባህላቸውንና እምነታቸውን እንዲይዙ የምታደርግ)፣ በማኅበራዊ ጉዳይም (በስደት ዓለም ለሚኖሩ ምእመናን መጠጊያና መጠለያ) በመሆን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ የምትሰጥ ተቋም መሆኗ ይታወቃል፡፡ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/