መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
Статистикаትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 4 357
- 1/48двое суток
- 4 993
- 1/72трое суток
- 5 385
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
https://www.youtube.com/live/wFKQlG6y83o?si=XCgk8UZpxMqFrW87
https://www.youtube.com/live/uM9l9DcN9uQ?si=ffWs5YIx2Qiav5yX
https://www.youtube.com/live/DyhhpkSEf9s?si=YuLjw7zWC-yu4mUM
https://youtu.be/42nL8RlJ8MY?si=qn0baQSHty4PXuml
https://www.youtube.com/live/mfdVdZTbDfM?si=MLL8bKjXxk2qO4mB
https://www.youtube.com/live/joqVEM2oDNY?si=56R3MZv-H1RuLbGF
https://www.youtube.com/live/RqslEofIb-4?si=8HkRWZ3oaIGFsJx8
https://www.youtube.com/live/mLPp6j4HXSA?si=tNaJXt9bFBZJOfFp
https://youtu.be/GMWvfHrqQpA?si=WXsMt-ascpvW_PsB
✠🌿✠ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሠላም አደረሳችሁ። ✠🌿✠ ⛪ በቀበና ምሥራቀ ፀሐይ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል 📖 የውዳሴ ማርያም እና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ 🗓️ ከሰኞ - ዐርብ 🕟 ከቀኑ 4:30 - 6:00 🗓️ ቅዳሜና እሑድ ⛪ ከቅዳሴ በመቀጠል 🕑 ጠዋት 2:00 ጀምሮ 🎙️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ይተረጎማል። 📡 የቀጥታ ሥርጭት የምታስተላልፉ ሚዲያዎች በተጠቀሰው ሰዓት ተገኝታችሁ ማስተላለፍ የምትችሉ መኾናችኹን እንገልጻለን። ✠🌹 በእመቤታችን ፍቅርና በረከት በሁላችንም ይደር። 🌹✠
ንባብ ለሕይወት ለ8ኛ ዙር ያዘጋጀው የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ላይ የዶክተር ሮዳስ ታደሰ መጻሕፍት የሚገኙ ሲኾን ከ30-50 % ቅናሽ አላቸው። በኤግዚቢሽን ማዕከል በአዳራሹ ዉስጥ ታገኙናላችሁ። ወይም በስልክ ቁጥር +251925354271 ይደውሉ።
видео или голосовое, без подписи
https://youtu.be/GJPzlnLjt_E?si=S7x1DKugEEzOKuhw
[ሐምሌ 19 የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል] ✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ዶሮዳስ ታደሰ ❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው። ❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡ ❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ ❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡ ❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡ ❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡ ❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል። ❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ዐምስት መቶ ሦስት በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡ ✔ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡- “እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ ወስምዖ መጥበቤ ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ ለአባልከ ሰላም እቤ” (እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦ “ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ በልደት ንዑስ፤ ንጹሕ ከመ ዕጣን ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡ (በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል) ❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡ (ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨ [የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨ [ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
https://youtu.be/LtixFdwNLBI?si=1GzfA7CphY5El2QJ
видео или голосовое, без подписи
✨ በሙሽራዋ ዕርገት የሙሽሪት ቤተ ክርስቲያን ደስታ 📖 በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ 📚 ነገረ ክርስቶስ መጽሐፌ ገጽ 209-212 ☁️ ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ሐዋርያት ወደ ሰማይ በናፍቆት ሽቅብ ሽቅብ ትኲር ብለው ሲመለከቱ ነጫጭ ልብስ ለብሰው መላእክት ተገልጠውላቸዋል። 📖 የሐዋ ፩፥፲ 🤍 ነጫጭ ልብስ ለብሰው መታየታቸው በትንሣኤው እንደተገለጡት “ወርኀ ፍሥሐ፣ ወርኀ ተድላ” ነው ሲሉ ነው። 🕊️ ከዚያም፦ “የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችኊ ስለ ምን ቆማችኋል? ይኽ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲኼድ እንዳያችኹት እንዲኹ ይመጣል” ብለው በናፍቆት ሲያዩት ለነበሩት ለሐዋርያት ጉባኤ ዳግመኛ ለፍርድ ተመልሶ የመምጣቱን ነገር ነግረዋቸዋል፡፡ ⛪ በጌታችን ዕርገት የተደረገው የመላእክትና የሐዋርያት ጉባኤ፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት፣ የሰጠውን ፍጹም ደስታና ሐሴት ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ የቤተ ክርስቲያንን የምእመናንን አንደበቷን አንደበት አድርጎ አምልቶና አስፍቶ እንዲኽ ይተነትነዋል፦ ☞ “የገነነው ሙሽራ በአባቱ ቤት ይመሰገናል፤ የብርሃን ልጆች ጉባኤም በርሱ መኼድ ተቀሰቀሱ፤ ሙሽሪት፣ የሐዋርያት ጉባኤ፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ሙሽራዋ በታላቅ ክብር ሲያርግ ተመለከተች፤ መከራ ሲቀበል አይታ አጐንብሶ የነበረውን ራሷን ቀና አደረገች፤ በኀይል ተነሥቶ ወደ አባቱ ያረገውን ተመለከተች፤ እናም በሞቱ የተነሣ በሐዘን ተቀስፎ የነበረ ልቧ ተጽናና 📖 ዮሐ ፲፬፥፳፰-፳፱። 💒 የሙሽሪት ናፍቆት ☁️ በአየር ላይ ሲኼድ ስታይ በስቅለቱ ጊዜ የደረሰበትን ስድብና ውርጅብኝን ተወች፤ ከርሱ ፊት የሚጋልቡትን ደመናዎችና ጒምን ተመለከተች፤ እናም ርሱን ተከትላ የብርሃን ልጅ እንደመኾኗ ለመኼድ ተመኘች። ❤️ “ወደምትኼድበት ከአንተ ጋር ውሰደኝ፤ የአንተ ኾኜያለኹና፤ ወደ አባትኽ ካንተ ጋር ላርግ ፈቃድኽ ይኹን” አለችው። ✝️ በፍቅርኽ ፈለግኸኝ፤ በመከራኽ ዐጨኸኝ፤ በጦር ተወግተኽ ነጻ አወጣኸኝ፤ እነሆ ገንነኻል፤ አንተን ተከትዬ ወደ አባትኽ ቤት ልሩጥ። 🌹 ወደ ሸንጎው ውስጥ የአንተን መከራ ለማየት ገባኊ፤ በአንተ የተነሣ ከአይሁድ ኀፍረትን ተቀብዬያለኊ፤ በመስቀል ላይ ሲዘባበቱብኽም እሞት ይኾን ብዬ ፈርቼ ነበር፤ በኀጢአተኞች ስትደበደብ ሸሽቼ ተደብቄ ነበር። 📖 መሓ ፭፥፯ 🪦 በወንበዴዎች መኻከልም ሲሰቅሉኽ ከአንተ ጋር ተዘባብተውብኝ ነበር፤ እንደገናም እንደ ሙታን በመቃብር ውስጥ ሲያኖሩኽ አሞኝ ነበር፤ ዕጹብ ድንቅ በኾንኸው ባንተ የተነሣ ተጽናንቼ ሐዘኔን ረሳኹት። 🕊️ በአንተ የተነሣ መሳደድ ደርሶብኛልና ከአንተ ጋር ልኺድ፤ ስምኽ ለእኔ የሚያስደስተኝ የከርቤ ዘይት ይኹንልኝ። 📖 መሓ ፩፥፫ 🍷 ምሕረትኽ ከወይን የተሻለ ነውና በአንተ ልጽናና፤ ከአንተ ከሙሽራው ከምወድድኽ ጋር ወደ ቦታኽ ልኺድ፤ ጠፍቼ እንዳልቀር በአንተ እሰበሰብ ዘንድ በመንጋኽ ውስጥ ዐስበኝ። 📖 መሓ ፩፥፯ 👑 በፍቅሩ የታመመች ሙሽሪት 🌸 የኢየሩሳሌም ቆነጃጅት ሆይ ንጉሡን ሙሽራ ወዴት አያችኹት? በጣም አብዝቼ ብፈልገውም ወደ ቦታው በማረጉ ፈጽሞ ላገኘው አልቻልኩም። 📖 መሓ ፫፥፪ 💘 እነሆ በሙሽራው ፍቅር ታምሜያለኊ ርሱንም እፈልገዋለኊ፤ ከኹሉም ውቦች በላይ ውብ የኾነውን እወድደዋለኊ፤ ሲናገር ከናፍሮቹ መውደድን ያዘንባሉ፤ ለሚመለከቱት ኹሉ ርሱ ከኹሉም በላይ ውብ ነው። 📖 መዝ ፵፬፥፪ 🌿 ልብሶቹም ልክ እንደ አሮን ጣፋጭ የዕጣን መዐዛን ይረጫሉ፤ ከርሱ የሚፈስሰውም ነጭና ቀይ፤ ውሃና ደም ነው። 📖 መሓ ፭፥፲፤ ዮሐ ፲፱፥፴፬ 🌺 ለሚመለከተው ጉንጮቹ የሽቱ ብልቃጥ ናቸው፤ አባቱ በርሱ ምክንያት ዓለምን በመታረቁ ሙሉ በሙሉ ሽቱ ነው። ☁️ ወደ ሰማይ ያረገው ሙሽራ 👣 በመንገድ ላይ አግኝቶኝ ነበር ባለማወቄ የተነሣ አላወቅኹትም ነበር። 📖 ሉቃ ፳፬፥፲፮ ☁️ ወደ ሰማያቱ ዐርጓል፤ ርሱን አየው ዘንድ ርሱ ወዳለበት ማን ያሳርገኛል? አለች። ⛰️ የሐዋርያት ጉባኤ በደብረ ዘይት ቆመዋል፤ ድንግል ሙሽሪት፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ምእመን፣ ከምድር ያረገውን ሙሽራ አተኲራ ትመለከተዋለች። 📖 የሐዋ ፩፥፲ 🕊️ እነሆ ርሱ ትቷት በማረጉ የተነሣ ልታነባ ስትል መላእክት “እነሆ እንደገና ይመጣል” ብለው ሊያጽናኗት ቀረቧት። 📖 የሐዋ ፩፥፲፩ 👑 ንግሥቲቱ ሙሽሪት፣ ቤተ ክርስቲያንን፣ ምእመንን፣ የንጉሡ አገልጋዮች (መላእክት) ሲያጽናኗት ነበር። ✨ “ከቶ ማዘን የለብሽም ምክንያቱም ይኸው ሙሽራ ይመጣልና በርግጠኛነት ታይዋለሽ፤ የኼደው የከበሩ ነገሮችን ይዞልሽ ሊመለስ ነው፤ ፈጽሞ አይተውሽም፤ ወደ አንቺም ይመለሳል።” 🕊️ “የሚመጣውን ተመልከቺው፤ በአካሉ ተሸከመሽ እነሆ በርሱ የተቀደሰ ስፍራ ከርሱ ጋር ነሽ፤ መንፈሱን ሰጠሽ።” 📖 ዮሐ ፳፥፳፪ 💛 “እነሆ ርሱ እዚኹ ከአንቺ ስፍራ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ራስሽ በርሱ ተፈጠርሽ፤ ርሱ ግን ከአንቺ ጋር ነውና መቼም ብቻሽን አይተውሽም።” 📖 ዮሐ ፲፬፥፲፰ 🌍 ሰማይና ምድር በዕርገቱ ተጣመሩ 🤍 መላእክት ደቀ መዛሙርትን ከብበው አበረታቷቸው፤ “ጌታችኊ ይመጣል፤ ርሱ ምስጉን ነውና ፈጽሞ ዐትዘኑ፤ ወደ ሰማይ ሲኼድ እንዳያችኹት እንዲኹ ሲመጣም ታዩታላችኊ፤ ዳግመኛ በክበበ ትስብእት እያበራ ይመጣልና” አሏቸው። 🕊️ መላእክቱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመደሰት መጡ፤ አንዳቸውን ጉባኤ ከሌላቸው ጋር በታላቅ ሰላም አጣመረ፤ ከደስታቸው የተነሣ መላእክት ራሳቸውን በነጭ ካባዎች አጐናጸፉ። ✨ ምክንያቱም በጠላትነት ከነበሩ ከሰው ዘሮች ጋር አስታርቋቸዋልና፤ በእግዚአብሔር ልጅ ሰማይና ምድር ርስ በርስ ተጣመሩ፤ በርሱ አማካይነት በሰው ዘርና በመላእክት መኻከል ሰላም ሰፈነ። 🔥 የወልድ መገለጥ እና የሰማያውያን ድንቅ 👼 የሰማያዊ ፍጥረታት ነገዶች ርሱን ሊያዩ ፈለጉ፤ ምክንያቱም ወደ እኛ መጥቶ ሥጋን ለብሶ በመኻከላችን እስኪኖር ድረስ አላዩትም ነበር። ☀️ ከአባቱ ጋር እንደነበረና ከርሱም ጋር ኅቡዕ እንደኾነ ያውቁታል፤ ነገር ግን ሰማያዊ ነገዶች ርሱን በባሕርዩ ለማየት ችሎታ አልነበራቸውም። ✝️ ለሰው ልጅ ባለው ፍቅር ሥጋን ተውሕዶ በምድር ላይ ሲገለጽ፤ ርሱ ከመገለጹ የተነሣ እነሆ የሰማይ ጭፍሮች ሊያዩት ፈለጉ፤ ኀይላት ሥልጣናት በየነገዳቸው ተደነቁ። 🌟 ምክንያቱም ስዉር የኾነው ርሱ በፈቃዱ ይመለከቱት ዘንድ ተገልጧልና፤ ወደ ሰማያት ሲያርግ ሥልጣናት ሊያዩት ተሰበሰቡ፤ ምክንያቱም ይዞት በመጣው የምሥራች ተነሳሥተው እና ተቀስቅሰው ለርሱ ምስጋናን አቀረቡለት። 🕯️ ርሱ ራሱ እንዲገለጽ የወደደው ዐዲስ ተአምር፣ ምስጢር ያውም የወልድን መገለጥ በቅንነት ለማየት ፈለጉ፤ በሥጋ ተገለጸ፤ በክብርም ዐረገ፤ ሲያርግም በሰዎችና በመላእክት ታየ። 📖 ፩ኛ ጢሞ ፫፥፲፮ 📚 ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በእንተ ዕርገተ እግዚእ በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ 📚 ነገረ ክርስቶስ መጽሐፌ ገጽ 209-212 [ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በዕርገትኽ ዕርገታችንን የገለጽክልን እንወድኻለን]
https://a.co/d/03gjdiSj
https://a.co/d/01p3d3vw The Sun of Righteousness