ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
Статистикаየዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/ በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
- Последний пост
- 10:21
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 26
- Всего постов
- 617
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Видео
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 139
- 1/48двое суток
- 159
- 1/72трое суток
- 171
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
✞✞✞✝ እንኳን ለታላቁ ክርስቲያናዊ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞✝ ✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞✝ ✞✞✞✝ ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ✝ ✞✞✞ ✞✞✞ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒ እና ከአባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የመከራ ጊዜ) ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በተደረገው የአርባ ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ:: ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ:: የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ: ቀርነ ሃይማኖት የቆመው: ብዙ ሥርዓት የተሠራው: ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና:: ይህች ዕለት ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የነገሠባት ናት:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በ312 ዓ/ም ዓለምን አስጨንቀው ሲገዙ ከነበሩ ነገሥታት አንዱ የሮሙ ቄሣር መክስምያኖስ ነበር:: ክርስቲያኖችን ከግዛቱ ያጠፋ ዘንድ ብዙ ጊዜ ሞክሯል:: በሰይጣን ምክር አብያተ ክርስቲያናትን ዘግቷል: መጻሕፍትን አቃጥሏል: ምዕመናንንም ጨፍጭፏል:: ነገር ግን ሰማዕታት አንዱ ሲሰዋ አንድ ሺውን እየተካ (በእምነት እየወለደ) ነውና እንኳን ሊጠፉ በየቀኑ ይበዙ ነበር:: ምንም የሚሊየኖችን ደም ቢያፈስም ክርስቲያኖች ከጽናታቸው የሚነቃነቁ አልሆኑም:: በዚህም ስለ ተበሳጨ ከክርስቲያኖች አልፎ በአሕዛብም ላይ ግፍን ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ደግሞ የበራንጥያው ንጉሥ ቁንስጣ ዐርፎ ልጁ ቆስጠንጢኖስ ነግሦ ነበርና የሮም ሰዎች ዝናውን ሰሙ:: በእርሱ መንግስት ፍርድ አይጓደልም: ደሃ አይበደልም: ግፍም አይፈጸምም ነበርና ይህንን ያወቁ የሮም ሰዎች መልዕክተኛ ልከው ከአውሬው መክስምያኖስ እንዲያድናቸው ተማጸኑት:: እርሱም ነገሩን ሲሰማ አዝኖ: ከመከራ ሊታደጋቸውም ወዶ: ሠራዊቱን አስከትቶ ተነሳ:: ወደ ጦርነት እየሔደ ካረፈበት ወንዝ ዳር በመንፈቀ መዓልት (ስድስት ሰዓት ላይ) ድንገት ከሰማይ ግሩም ተአምርን ተመለከተ:: የብርሃን መስቀል በከዋክብት አጊጦ: ሰማይንም ሞልቶ: ብርሃኑ ፀሐይን ሲበዘብዛት: በላዩ ላይም "ኒኮስጣጣን" የሚል ጽሑፍ ተስሎበት አየ:: "ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ አንድ ደፋር ክርስቲያን ወታደር (አውስግንዮስ ይባላል:: አርጅቶ በመቶ አሥር ዓመቱ ሰማዕት ሆኗል::) ወደ ንጉሡ ቀርቦ "ይሔማ አዳኝ ሕይወት የሆነ መስቀለ ክርስቶስ ነው::" ብሎታል:: ይሕንን እያደነቀ ሳለም በሌሊት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ መጥቶ ነገሩን ገለጠለት: ምሥጢሩንም ተረጐመለት:: "ኒኮስጣጣን ማለት 'በዝየ ትመውዕ ጸረከ-በዚህ መስቀል ጠላትህን ድል ታደርጋለህ' ማለት ነው::" አለው:: በነጋ ጊዜም ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ በሁሉም የጦር እቃ (በወታደሩ: በጦሩ: በፈረሱ: በጋሻው . . .) ላይ የመስቀል ምልክትን ሠርቶ መክስምያኖስን ገጠመው:: በኃይለ መስቀሉም ድል አድርጐ ማረከው:: የተረፈው የአሕዛብ ሠራዊትም እሸሻለሁ ሲል ድልድይ ተሰብሮበት ወንዝ ውስጥ ገብቶ አለቀ:: ✞✞✞ ቅዱሱ ንጉሥም በኃይለ መስቀሉ ሮሜን እጅ አደረጋት:: "ሃይማኖተ ክርስቶስ ነሢኦ ወዘመስቀሉ ትርጓሜ: ቆስጠንጢኖስ ዮም ነግሠ በሮሜ: ዘመክስምያኖስ ዕልው ድኅረ ኀልቀ ዕድሜ::" እንዲል:: ቅዱሱ ንጉሥ ድል አድርጐ በዚህች ቀን ወደ ሮም ሲገባ ከመከራና ሞት የተረፉ ክርስቲያኖች ዕፀ መስቀሉን ይዘው በዝማሬ ተቀብለውታል:: እርሱም በዚህች ቀን በ312 ዓ/ም በሮም ግዛት ሁሉ ላይ ነግሦ ለሰባት ቀናት በዓለ መስቀልን በድምቀት አክብሯል:: በዘመኑ ሁሉም ቅዱስ ሚካኤል አልተለየውምና ወዳጁ ሲባልም ይኖራል:: ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት: ሐዋርያት እና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት: በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ አርፏል:: "ቆስጠንጢኖስ" ማለት "ሐመልማል" ማለት ነው:: ✞✞✞ ጌትነት ያለው አምላካችን በይቅርታው ይጐብኘን:: ደግ መሪ: መልካም አስተዳዳሪን ያድለን:: ከቅዱሱ ንጉሥም በረከትን ያሳትፈን:: ✞✞✞ ነሐሴ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (ጻድቅ ንጉሥ) 2.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ✞✞✞ ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ) 3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ድሜጥሮስ 5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት) 7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ✞✞✞ "እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው::" ✞✞✞ (፩ጢሞ. ፪፥፩-፬) ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
ምስባክ ዘነሐሴ ፲፪ ዘሠርክ ፍልሰታ
ምስባክ ዘነሐሴ ፲፪ ዘቅዳሴ ፍልሰታ
ምስባክ ዘነሐሴ ፲፪ ዘነግህ ፍልሰታ
ግጻዌ ዘነሐሴ ፲፪ ፍልሰታ
без подписи
ምስባክ ዘቅዳሴ አመ ፲ወ፩ ለነሐሴ
ምስባክ ዘነሐሴ ፲ ዘቅዳሴ ፍልሰታ(ሰንበተ ክርስቲያን)
ግጻዌ ዘነሐሴ ፲ ዘቅዳሴ ፍልሰታ(ሰንበተ ክርስቲያን)
ምስባክ ዘነሐሴ ፱ ዘቅዳሴ ፍልሰታ
ግጻዌ ዘነሐሴ ፱ ፍልሰታ
††† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት ቅዱስ አልዓዛር እና ለቅዱሳን ቤተሰቡ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ አልዓዛር ካህን ††† ††† ይህ ቅዱስ #የብሉይ_ኪዳን_ሰማዕታትተብለው ከሚታወቁት ዋነኛው ነው:: የነበረበት ዘመንም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲሆን " #ዓመተ_መቃብያን/ #ዘመነ_ካህናት" ይባላል:: በወቅቱ ሰሎሜ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ ይኖር የነበረው ቅዱስ አልዓዛር በኢየሩሳሌም ተወዳጅ ነበር:: ሐረገ ትውልዱ ከአሮን ወገን ነውና በክህነቱ ተግቶ ያገለግል ነበር:: በዚያ ላይ ሊቀ ካህንነትን በመመረጡ ሕዝቡን ይሠራ: ያስተምር: ያስተዳድር ነበር:: ቅዱስ አልዓዛር ከተባረከች ሚስቱ ሰሎሜ 7 ወንዶች ልጆችን አፍርቷል:: እነርሱንም በሥርዓት አሳድጐ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጐ ነበር:: በዚያው ዘመን በኢየሩሳሌም አካባቢ የሚኖሩ 3 እኩያን (ክፉ) ካህናት ነበሩ:: እነዚሁም ሕዝቡን ከማስቸገር: ፈጣሪን ከማሳዘን ቦዝነው አያውቁም ነበር:: የክፋታቸው መጨረሻ ግን የገዛ ሃገራቸውን ማጥፋት ሆነ:: ነገሩ እንዲህ ነው:- 3ቱም ተመካክረው የአልዓዛርን የሊቀ ካህንነት ቦታ ሊቀሙ ወስነው ወደ እርሱ ሔዱና እንዲህ አሉት:: "ሹመት በተርታ: ሥጋ በገበታ" ሲሆን ያምራልና እኛ በተራችን በወንበሩ ላይ እንቀመጥ::" እርሱ ግን "ሕዝቡን ጠይቃችሁ ተሾሙ" አላቸው:: እነርሱም ሕዝቡን ጠርተው "ሹመት ይገባናል" ቢሏቸው ሕዝቡ መልሶ "አልዓዛርን የሾመው እግዚአብሔር ነውና እናንተም ከፈጣሪ ጠይቃችሁ ተሾሙ" አሏቸው:: በዚህ ጊዜ 3ቱ እኩያን ተቆጡ:: ምክንያቱም እግዚአብሔር እንደ ማይሰጣቸው ያውቃሉና:: ወዲያው ግን 3ቱም ከአካባቢው ጠፉ:: ከኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ጨካኙ የግሪክ ንጉሥ አንጥያኮስ ሔዱ:: አንጥያኮስ ማለት "ቀኝ ዐይናችሁን ገብሩልኝ" የሚል ንጉሥ ነው:: እርሱን " #ኢየሩሳሌም ባለቤት የላትምና ሒደህ ውረራት" አሉት:: "አጥሩ ጥብቅ ነው:: በምን እገባለሁ?" ቢላቸው "እኛ በመላ እናስገባሃለን" አሉት:: እርሱም 240,000 ሠራዊት አስከትቶ ወረደ:: እነርሱ ቀድመው ወደ ኢየሩሳሌም ገብተው ያስወሩ ጀመር:: "እናንተ ሹመት ብትነሱንም እኛ ግን አንጥያኮስን ያህል ንጉሥ በእሥራኤል አምላክ አሳምነን መጣን" እያሉ ይሰብኩ ገቡ:: ቅዱስ አልዓዛር "አትስሟቸው:: በዚያም ላይ አሕዛብ የተቀደሰውን ምድር መርገጥ የለባቸውም" ብሎ ነበር:: ነገር ግን አንዳንድ ችኩሎች አይጠፉምና ፈጥነው የከተማዋን በር ከፈቱት:: ሠራዊቱን ደብቆ ትንሽ ራሱን የቆመ የመሰለው አንጥያኮስ በምክንያት: በክፋትና በመላ ሁሉን ሠራዊቱን አስገባ:: የሚገርመው በጊዜው የከተማዋ ሕዝብ 12 እልፍ (120,000) ሲሆን ንጉሡ ያስገባው ሠራዊት ግን 24 እልፍ (240,000) ሆኖ ተገኘ:: ወዲያው አንጥያኮስ ሕዝቡን ሰበሰበና አልዓዛርን ለብቻው ጠርቶ ተናገረው:: "አንተ አምላክህን እንደምትወድ ሰምቻለሁ:: አንተ የበጉን መስዋዕት በልተህ: #ለስዕለ_ኪሩብ ሰግደህ: ሕዝቡን ግን እሪያ (አሳማ) እንዲበላና ለጸፀሐይ እንዲሰግድ አድርግልኝ" አለው:: ቅዱስ አልዓዛር መለሰለት:- "እግዚአብሔር የሾመኝኮ በጐ ሃይማኖትን ላስተምር እንጂ ለክፋት አይደለም:: ለሕዝቤ የክፋት አብነት ፈጽሞ አልሆንም" አለው:: ያን ጊዜ ንጉሡ በቅዱሱ ላይ ተቆጣ:: "የምልህን ካላደረግህ ብዙ ግፍ ይደርስብሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የፈለግኸውን አድርግ" አለው:: በዚያን ጊዜ ንጉሡ የቅዱሱን ሚስትና 7 ልጆች እንዲያመጡለት አዘዘ:: ቅዱሱ እያየ ከፊቱ ላይ 7ቱንም ልጆቹን በሰይፍ አስመታቸውና 7ቱም ወደቁ:: ለአንድ አባት ይህ የመጨረሻው መራራ ፈተና ነው:: #አልዓዛር ግን ምን አንጀቱ በኀዘን ቢቃጠልም ከልጆቹ ለእግዚአብሔር አድልቷልና ቻለው ታገሠው:: በዚህ ለውጥ እንዳልመጣ ያየው ንጉሡ ሌላ ፍርድ ተናገረ:: ቅዱሱንና ሚስቱን ( #ሰሎሜን) በፈትል ጠቅልለው በሠም ነከሯቸው:: (ጧፍ እንደሚሠራበት መንገድ ማለት ነው:: ) አሁንም ግን ከአምልኮታቸው ፈቀቅ ባለማለታቸው ትልቅ ብረት ምጣድ ተጥዶ: 2ቱም ከነነፍሳቸው እንዲቃጠሉ ተደረገ:: ቀጥሎም ሕዝቡን እንዲፈጁ አዋጅ ወጣ:: በከተማዋ ከነበረው ሕዝብ 40,000 ያህሉ ተገደሉ:: 40,000 ያህሉ ሲማረኩ 40,000 ያህሉን ደግሞ #ይሁዳ የሚባል አርበኛ በር ሰብሮ ይዟቸው ሸሸ:: "እንሾማለን: እንሸለማለን" ብለው ሕዝባቸውን ያስፈጁ እነዚያ ካህናትም #እግዚአብሔር ፈርዶባቸው እነርሱም ተገደሉ:: ቅዱሱ የአልዓዛር ቤተሰብ ግን የክብርን አክሊል አግኝተዋል:: ††† #የእሥራኤል_አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር እንዲህ ካለው መከራ በኪነ ጥበቡ ይሰውረን:: ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን:: ††† ነሐሴ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (ሰማዕት) 2.ቅድስት ሰሎሜ ሰማዕት (ሚስቱ) 3."7ቱ" ቅዱሳን ሰማዕታት (ልጆቹ) 4.ቅዱስ አሞን ሰማዕት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ብሶይ (ቢሾይ) 4.አቡነ ኪሮስ 5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ††† "አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ:: የቅድስናህንም #መቅደስ አረከሱ:: #ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት:: የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ:: የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት:: ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ:: የሚቀብራቸውም አጡ::" ††† (መዝ. 78:1) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/zikirekdusn
ምስባክ ዘነሐሴ ፰ ዘቅዳሴ ፍልሰታ
ምስባክ ዘነሐሴ ፰ ዘቅዳሴ ፍልሰታ
ምስባክ ዘነሐሴ ፰ ዘነግህ ፍልሰታ
ግጻዌ ዘነሐሴ ፰ ፍልሰታ
без подписи
без подписи