tgindex
✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

Статистика

ይህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ታላላቅ የድሮና አዳዲስ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቁ መጽሐፍት በPDF ያቀርባል

Последний пост
9 мая
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
125 532
−176 за 3 дн.
Сутки
−68
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
30,5 тыс
19 постов
Вовлечённость
24,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 9 мая27,1 тыс52678

    #ግንቦት_ልደታ_ለማርያም ግንቦት ልደታ ለምን ይከበራል? ግንቦት ልደታ (ግንቦት 1) የሚከበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት ለማሰብ ነው። በዓሉ የሰው ልጅ የመዳን ተስፋ መጀመሪያ የሆነችው ማርያም ከአባቷ ከኢያቄም እና ከእናቷ ከሐና በአድባረ ሊባኖስ የተወለደችበትን ዕለት የሚያከብር ታላቅ በዓል ነው።  የበዓሉ ዋና ዋና ምክንያቶች፦…

  • 8 мая24,7 тыс12980

    #ግንቦት_ልደታ_ለማርያም ግንቦት ልደታ ለምን ይከበራል? ግንቦት ልደታ (ግንቦት 1) የሚከበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት ለማሰብ ነው። በዓሉ የሰው ልጅ የመዳን ተስፋ መጀመሪያ የሆነችው ማርያም ከአባቷ ከኢያቄም እና ከእናቷ ከሐና በአድባረ ሊባኖስ የተወለደችበትን ዕለት የሚያከብር ታላቅ በዓል ነው።  የበዓሉ ዋና ዋና ምክንያቶች፦ የድንግል ማርያም ልደት፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በግንቦት 1 ቀን መወለዷን ለማሰብ። የትንቢት መፈጸምያ፦  በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነቢያት ስለ መሲሁ መምጣት የተነበዩት ትንቢት መፈጸሚያ የሆነችው የጌታ እናት የተወለደችበት ቀን በመሆኑ። የመዳን ምስራች፦  የሰው ልጅ ሁሉ መዳን ምክንያት የሆነችውና የሰማይ እና ምድር ፈጣሪን የማኅፀኗ ፍሬ ያደረገችው ድንግል ማርያም መወለዷን ለማብሰር። ደስታና ምስጋና፦  ቅዱስ ያሬድ “ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም” (በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ) ብሎ እንደዘመረው፣ ይህ ዕለት የዓለም ሁሉ የደስታ ቀን ተደርጎ ይወሰዳል።  በአጠቃላይ፣ ግንቦት ልደታ የድንግል ማርያምን በጎ ስብዕና እና ለሰው ልጅ ያላትን ትልቅ ቦታ የምናስብበትና የምናመሰግንበት በዓል ነው። @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 12 апр.30,7 тыс42377

    † እንኳን ለጌታችን እና መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሰን † ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡” መልካም በዓል ! @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 8 апр.32,5 тыс33752

    #ህማማት በህማማት ሳምንት (Holy Week) የየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ እና ቅዱስ ሳምንት ነው ፤ የኢየሱስ ክርስቶስ መከራ፣ ሞት እና ትንሣኤ ይዘከራል። በዚህ ሳምንት የሚደረጉ ነገሮች እነዚህ ናቸው፦ 1. ጾም (ጾመ ህማማት) ከሌሎች ጾሞች የበለጠ ጠንካራ ነው ምግብ እስከ ማታ ይቆያል (አንዳንድ ሰዎች ሙሉ ቀን ይጾማሉ) ስጋ እና የእንስሳ ምርቶች ፈጽሞ ይከለከላሉ ። 2. ጸሎት እና ስግደት ቤተክርስቲያን ብዙ ጊዜ መገኘት ረጅም ጸሎቶች እና ስግደት (መስገድ) መጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ። 3. የቀናት ልዩ ትርጓሜ ሰኞ  ፣ ማክሰኞ ፣ ረቡዕ :  የተለመዱ ጸሎቶች እና ጾም ይከናወናል። ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ): የመጨረሻ እራት ዝክር ዓርብ (ስቅለት): የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ መሞት የሚዘከር ቀን (እጅግ ጥልቅ ጾም) ቅዳሜ (ቀዳም ስድስት): የ ዝምታ እና አርምሞ ቀን 4. መንፈሳዊ ሥነ ምግባር ርህራሄ ማድረግ (ለድሆች መርዳት) ጥላቻ መተው እና ይቅር መባባል ፤ ንጹሕ የንሰሀ ሕይወት መኖር ። 5. ዝምታ እና ሀዘን የጌታን ህመሙን እና ስቃዩን እያሰቡ የደስታ ነገሮችን (ከመዝናኛ፣ ድምፅ ያለውን ዜማ ሳቅ ከመሳሰሉት መቆጠብ! ) ራስን መመርመር እና መንፈሳዊ ህይወትን ማደስ። በ አጠቃላይ ይህ ሳምንት የንስሐ፣ የጸሎት እና የመንፈሳዊ ትኩረት ጊዜ ነው! @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 28 мар.34 тыс32566

    የዐቢይ ጾም ሳምንታት ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስሙ ጐልቶ ከሚነሳባቸው ጉዳዮች አንዱ በዐቢይ ጾም ውስጥ ለሚገኙ ሳምንታት የየራሳቸው መጠሪያ በመስጠቱ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለሳምንታቱ ስያሜዎችን ሲሰጥ ጌታችን የሠራቸውን የቸርነት ሥራዎችን፣ ያስተማራቸው ትምህርቶችን፣ ተጠቅሟል፡፡ በአጠቃላይ በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙ ሳምንታት ስያሜያቸው . . . 1/ ዘወረደ 2/ ቅድስት 3/ ምኩራብ 4/ መፃጉ 5/ ደብረ ዘይት 6/ ገብር ኄር 7/ ኒቆዲሞስ 8/  ሆሣዕና @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 14 февр.48,5 тыс321176

    #ቅድስት_ሥላሴ "ሥላሴን " " ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው ? አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም ። አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር # ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ። አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ። ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ " በማለት ያመሰጥራል ። ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና ፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን ። አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም #ቅድስት ይባላሉ ። አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም ። ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ። ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ #ቅድስት እንላቸዋለን ። አኔድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ #ቅድስት ይባላሉ ። @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 6 февр.42,6 тыс23968

    #ጸሎተ_ሃይማኖት (የሃይማኖት ጸሎት) ነአምን በ፩ዱ፡ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኲሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።  ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።  መቅድም  ሀ. ስሙ  1. ጸሎተ ሃይማኖት  2. የኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ (ውሳኔ ሃይማኖት፤ አንቀጸ ሃይማኖት) Nicene Creed  3. የኒቅያ ቁስጥንጥንያ ውሳኔ ሃይማኖት Nicene-Constantinopolitan Creed ለ.  ለምን አስፈለገ? 1. « መለኮታዊውንና ሐዋርያዊውን እምነት ጠቅልሎ ያስቀመጠ ስለሆነ።» ቅዱስ አትናቴዎስ   2. ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ግልጥ በማድረግ ከክህደት ምእመናን ለመጠበቅ ነው።  3. እያንዳንዱ ቃልና ሐረግ የክርስቲያንን እምነት የሚያጠነክር ስለሆነ ነው።  4. ቤተ ክርስቲያን ልትሆነውና ልታደርገው የሚገባትን ነገር የሚያመለክት ነው።  ሐ. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ያለው ልዩ ቦታ  1. በመላው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ተቀባይነት ያለው አንቀጸ ሃይማኖት ነው።  2 የክርስቶስን አምላክነት የመንፈስ ቅዱስ አምላክነት  በማብራራት ቤተ ክርስቲያንን ከታላቅ አደጋ የታደገ ነው።    3. በኒቅያ በ325 ዓ.ም ላይ   እንደገና በ381 ዓ.ም ላይ በቁስጥንጥንያ በተከናወነው ኢኩሜኒካል ጉባኤ ላይ ተጨማሪ አንቀጾች ( መንፈስ ቅዱስን የሚመለከቱ) ገብቶለት ቤተ ክርስቲያንን በቀጥተኛ ሃይማኖት (ኦርቶዶክስ) የመራ ነው።  መ. በቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ሕይወት ያለው ቦታ 1. በጸሎት ማለትም በቅዳሴ ጊዜ በካህናትና በምእመናን ይደገማል።  2. የሚጠመቁ ሰዎች እምነታቸውን የሚገልጡት ጸሎተ ሃይማኖትን አሰምተው በመድገም ነው። (የክርስትና አባትና እናት ስለሕፃኑ ፈንታ ሁነው በጸሎተ ሃይማኖት እምነታቸውን መመስከር አለባቸው።   3. የክርስትና መለያ ምልክት ስለሆነ በምኩራብ የእምነት መግለጫ የሆነው « እስራኤል ሆይ ስማ (ሼማ)በሚለው የአይሁድ አንቀጸ ሃይማኖት ትይዩ ሊታይ የሚችል ነው።  መ. ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያለው ግንኙነት  1. ጸሎተ ሃይማኖት በተደነገገ ወቅት ገና የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ገና አልተቋጨም ነበር።  2. ጸሎተ ሃይማኖት ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን የያዘ ስለሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ለመወሰን ማለትም የትኞቹ መጻሕፍት በቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር መግባት እንዳለባቸው ለመወሰን አገልግሎአል።  @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 4 февр.32,3 тыс243108

    #ፀሎት ፀሎት ማለት ምን ማለት ነው? #ጸሎት ማለት ፦ጸለየ፣ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እግዚአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ “ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር፡፡” አባታችን አዳምም ከመላእክት ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዜ ጸሎት እያደረገ ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ዘርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡ ጸሎት ሰማእታት ከነደደ እሳት፣ ከተሳለ ስለት፣ ከአላውያን መኳንንት፣ ከአሕዛብ ነገሥታት ከዲያብሎስ ተንኮል እና ሽንገላ ዲያብሎስ በእነርሱ ላይ ከአጠመደው አሽከላ የዳኑበት ጋሻ ነው፡፡ ኤፌ.6፥10 21 ጸሎት፣ ሰው አሳቡን ለእግዚአብሔር የሚገልጥበት እግዚአብሔርም የሰውን ልመና ተቀብሎ ፈቃዱን የሚፈጽምበት ረቂቅ ምስጢር ነው፡፡ የጸሎት መሠረቱ “ዕሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኋል ደጁ ምቱ ይከፈትላችኋል” የሚለው የጌታችን ትምህርት ነው።/ማቴ: 7፥7/ @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 2 февр.32,5 тыс10561

    #በእንተ_ፆም ጾም ‹‹ጾመ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም መተው፣ መጠበቅ፣ መከልከል ማለት ነው፡፡ ጾም ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይኾን ከክፉ ተግባር ዅሉ መቆጠብ ጭምር ነው፡፡ ሠለስቱ ምዕትም፡- ‹‹ጾምሰ ተከልኦተ ብእሲ እመብልዕ በጊዜ ዕውቅ በውስተ ሕግ፤ ጾምስ በታወቀው ሰዓት፣ በታወቀው ዕለት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው›› በማለት የጾምን ትርጕም ያስረዳሉ /ፍትሐ ነገሥት፣ አንቀጽ ፲፭/፡፡ ጾም በብሉይ ኪዳንም ኾነ በሐዲስ ኪዳን የታወቀ፣ በነቢያት የነበረ፣ በክርስቶስ የጸና፣ በሐዋርያት የተሰበከ እና የተረጋገጠ መንፈሳዊ ሕግ፤ ፈጣሪን መለመኛ መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡ ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይኾን ልዑል እግዚአብሔር የመሠረተው፣ ከእግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተሰጠ የመጀመሪያው ትእዛዝ ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒችን ኢየሱስ ክርስቶስም እከብር አይል ክቡር፣ እነግሥ አይል ንጉሥ፣ እጸድቅ አይል ጽድቅ የባሕርዩ የኾነ አምላክ ነው፡፡ ለእኛ አርአያ ቤዛ ሊኾነን፣ እናንተም ብትጾሙ ብትጸልዩ አጋንንትን ድል ትነሳላችሁ ሲለን፣ ጾምን ለመባረክ ለመቀደስ፤ በመብል ምክንያት ስተን ስለ ነበር ስለ እኛ ኀጢአት እና በደል ሲል ዐርባ ቀንና ሌሊት ጾሟል፡፡ ጌታችን ሲጾም ዐርባውን መዓልት እና ሌሊት ሙሉ ምንም እኽል ውኃ አልቀመሰም፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴም እንደዚሁ ጽላተ ሕጉን ከእግዚአብሔር ሲቀበል እኽል ውኃ አልቀመሰም ነበር፡፡ ምክንያቱም አምላካችን ‹‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል፤ ከእኔ የበለጠም ያደርጋል›› ብሏልና፡፡ አባቶቻችን ጻድቃንም ከዐሥረኛው ማዕረግ (ከዊነ እሳት) ላይ ሲደርሱ በእርሱ መንፈስ (በመንፈስ ቅዱስ) ኃይል ታግዘው ከእኽል ውኃ ተከልክለው ይጾማሉ፡፡ ይህም በሥጋዊ ዓይን ሲመዘን ፈጽሞ የሚከብድ ነው፡፡ ሃይማኖት ከሳይንስና ከአእምሮ በላይ ነውና፡፡ በዚህም  ሃይማኖት የሚቀበሉት እንጅ የሚጠራጠሩት የሚፈላሰፉት እንዳልኾነ እንረዳለን፡፡ @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 1 февр.32,8 тыс223128

    #ጾመ_ሰብአ_ነነዌ ‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡ በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው (ሉቃ.፲፩፥፴)፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፤ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናገረ (፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩)፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል (፩ኛነገ.፲፯፥፲፱)፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል (ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪)፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብናአ እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አስረድቶታል፡፡ ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል (ትንቢተ ዮናስ)፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡ ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ነው፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ሁሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች (አስ.፬፥፲፭-፲፮)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች (ሉቃ.፪፥፵፮)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል (ሉቃ.፲፫፥፴፪)፡፡ ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ  ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኃጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ሆነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡ ስለሆነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡ ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 pinned a photo

  • 29 янв.33,7 тыс11863

    #ጥር_21_የእመቤታችን_በዓለ_ዕረፍት ! ” አስተርእዮ ማርያም “ አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል። ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ”  የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል። ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል። ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው ። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ። የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት። ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው አግችተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል። በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች። ሰአሊ ለነ ቅድስት የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን። አሜን! @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • 29 янв.24,3 тыс18420

    እንኳን አደረሳችሁ! " አስተርእዮ ማርያም " Eotc_Books_By_Pdf

  • 26 янв.31 тыс31159

    #በስመአም_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን !                                                                   የጊዜያት ባለቤት እግዚአብሔር አምላክ ሆይ የጨለማውን ግርማ ገፈህ ብርሃንህን እንድንመለከት ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ። በመኝታዬም ስለጠበከኝ ከሞት ስለሰወርከኝ እጅ መንሳቴን አቀርባለሁ ። ቸር አረኛዬ ትጉህ የማታንቀላፋ ነህና ሌሊቱን ከእኔ ጋር ሆነህ እንደጠበኸን ይህንን ማለዳ  ባርከህ ቀድሰህ የሰላም ውሎ እንድንውል ቀኝህ ትርዳኝ ። መንገዴን  ሁሉ ከፊት እያሆንክ ምራኝ ። መንገዴን ሁሉ ከፈት እየሆንክ ምራኝ ። ከደካማ ፍጡርነቴ የተነሳ በኋላዬም ምን እንዳለ አላውቅምና አንተ ጠብቀኝ ። በዙራያዬ ሁሉ ጠላት ያስቀመጠብኝን እንቅፋትና መሰናክል አስወግድልኝ ። በመልካም እሳቶች አስስጊጠኝ ከፈተና ያተነሣ እንኳን  ብወድቅ አንሳኝ እንጅ አትተወኝ ። በዚህች ብሩክት እለትም በስራዬ ፤ በንግዴ ፤ በመንገዴ ፤ በክብራ ፤ በአገልግሎቴ ሁሉ የጥፋት መረብን ዘርግቶ ሰላሜንና በረከቴን ሊያሳጣኝ የተዘጋጀውንና ያሚያሴርብኝን ጠላት(ዲያብሎስን )እቅዱንና ሥራውን ሁሉ አፍርስህ ሰላምን አጎናጽፈኝ ።  በዚህ እለት ኀጢያትን እቅጄ በድፍረት እንዳልፈጽም ፤ በመዘንጋትም እንዳልተገብር አድርገኝ ።ደም ከሚፈስበት ፤ ፍርድ ከሚዛባበት ፤ ደሀ ከሚበደልበት ፤ በማታለልና በማጭበርበር ከሚከበርበት ፤ ጣዖትና ስይጣን ከሚመለክበት ሥራና ባታ ሁሉ ፈጽመህ ጠብቀኝ ። ደካማው ልጅህ እጆቼን ዘርግቼ መንገዴን እንድትመራኝ በቀረብሁ ጊዜ ኅጢያቴንና በደሌን አይተህ ሳትጠያፈኝ ተቀብለህ ምራኝ ። እለቱን ሁሉ ፈቃድህን ማድረግ እንድችል በቃልህ አስተምረኝ ።መንፈስ ቅዱስ ሕይወቴን ይቆጣጠር ።ትናንትን  እንደጠበኸኝ  እንደመገብከኝ  ከክፉም እንደሰወርከኝና እንደሰወርከኝ ዛሬም እንደፍቃድህ ጠብቀኝ ። አንተ ያልከው ይሆን ዘንድ ግድ ነውና በከንቱ ከመጨነቅና ከመተከዝ ተስፋም ከመቁረጥ ሰውረኝ                     ለዘላለሙ አሜን ! @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf

  • ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 pinned a photo

  • 19 янв.30,8 тыс24214

    እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!❤️ መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

  • 17 янв.31,5 тыс7369

    ድኅነት ፦ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር. 16፡16)           የድኅነት ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጽ እንደተናገረው ዘላለማዊ ድኅነትን ለማግኘት የሚሻ ሁሉ ወልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት አምኖ መጠመቅ ግድ ይለዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን ከሙታን ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ‹‹ያመነ የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል›› (ማር 16፡16) በማለት በጥምቀት ድኅነት እንደሚገኝ…

  • 15 янв.23,9 тыс19179

    የጥምቀት አመሠራረት            #የምሥጢረ_ጥምቀት መሥራች ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ነገር ግን ከጌታችን ጥምቀት በፊት አይሁድ ለመንጻትና ለኃጢአት ሥርየት (ይቅርታ) የሚጠመቁት “ጥምቀት” ነበራቸው፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥባቸው የተቀደሱ ዕለታትና ቦታዎች ሁሉ ሰውነትንና ልብስን ማጠብ የእግዚአብሔር ቤት ማገልገያ የሆኑ ዕቃዎችን ሁሉ ማጠብ ማንጻት ሥርዓትና…

  • 13 янв.25,1 тыс19577

    #ምስጢረ_ጥምቀት፡ የክርስትና መግቢያ በር               #ጥምቀት (Mystery of Baptism) የሚለው ቃል “አጥመቀ” (አጠመቀ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው።                             ምስጢረ ጥምቀት በምስጢራዊ (በሃይማኖታዊ) ፍቺው በተጸለየበት ውሃ (ማየ ኅይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ…

  • 12 янв.26 тыс20275

    #ምስጢረ_ጥምቀት፡ የክርስትና መግቢያ በር               #ጥምቀት (Mystery of Baptism) የሚለው ቃል “አጥመቀ” (አጠመቀ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው።                             ምስጢረ ጥምቀት በምስጢራዊ (በሃይማኖታዊ) ፍቺው በተጸለየበት ውሃ (ማየ ኅይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ የመውጣት ሂደት ነው (ማቴ 28፡19)። ጥምቀት “የክርስትና መግቢያ በር” ናት፡፡ ምክንያቱም ከሌሎች ምስጢራት ስለሚቀድምና ለእነርሱም መፈጸም ቅድመ ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡ ጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት (ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና) ምሥጢር ነው።             ሰው  ከሌሎች ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ለመካፈል አስቀድሞ መጠመቅና ከማኅበረ ክርስቲያን መደመር አለበት፡፡ ስለዚህም ምስጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት እንዲሁም ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የእምነታችን መሠረትም፣ የጸጋ ልጅነት የሚገኝበትም ምስጢር ነውና ከሁለቱም ይመደባል፡፡ በቀጣይ ፦ የጥምቀት አመሠራረት ❤️ @Eotc_Books_By_Pdf @Eotc_Books_By_Pdf