tgindex
AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት

AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት

Статистика

ይህ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ main ካምፓስ ግቢ ጉባዔ የቤተ-መፃህፍት ጥያቄ ና መልስ እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎች የሚተላለፍበት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው ማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ በዚህ @AMUlibrary_bot ያድርሱን።

Последний пост
27 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 477
+2 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
905
29 постов
Вовлечённость
61,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✝✝እንኳን ደስ አላችሁ✝✝✝ ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ... መዝ 118:26 ውድ የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ የ2018 ዓ.ም ተመራቂ እህቶችና ወንድሞች እንኳን ደስ አላችሁ “እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።”   — መዝሙር 128፥4 እግዚአብሔርን መፍራት የተማርንባችሁ ተመራቂዎች እንኳን ለዚህች ለምትናፍቋት ቀን አደረሳችሁ!!.... እዚህ ቀን ለመድረስ ቅድስት ክዳነምህረት ቤተክርስቲያን ግቢ ተደፍታችሁ ያነባችሁት የዕንባ ብዛት ትዝ ይላችኋል?..... "እንደው የነገዋን ፈተና አላጠናሁም፣ እባክሽ አሳልፊኝ" ብላችሁ ስንቴ ነው ቅድስት ክዳነምህረት ያስጨነቃቿት?😁..... አሁን በቅርቡ እንኳን የ exit ነገር አስጨንቋችሁ ስንቴ ነው የቅድስት ክዳነምህረት  የጸሎት Network ያጨናነቃችሁት?🤭..... እዚህ የደረሳችሁት በምትወዷት በእመብርሃን ምልጃ፣ በአቡነ ሀብተማርያም ረዳትነት በአምላካችሁ ፈቃድ መሆኑን መቼም እንዳትረሱ!..... በቃና ዘገሊላ ተገኝታ የጎደለውን ወይን ያስሞላች እመቤታችን እናንተንም የጎደላችሁን ነጥቦች ሞልታ እዚህ እንዳደረሰቻችሁ እንዳትረሱ! በዚህ ቀን ስለእናንተ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ወላጆቻችሁ በደስታ የሚሰክሩበት ዕለት ነው። ከእነርሱ በላይ ደግሞ ፈጥሮ፣ መግቦና አሳድጎ እዚህ ያደረሳችሁ አባታችሁ መድኃኔዓለም የሚደሰትበት ዕለት ነው። ለምን ተደሰቱ ካላችሁ ዋጋ የተከፈለበት ነገር አብቦ ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር ስለሌለ ነው። ስለዚህ አሁንም ዋጋ የከፈሉላችሁን አባትና እናቶቻችሁን (የሥጋ ወላጆቻችሁ፣ አባታችሁ መድኃኔዓለም፣ እናታችሁ እመብርሃን) ልታስደስቷቸው የምትችሉት ራሳችሁን ሰጥታችሁ አገልግሎታችሁን ስትቀጥሉ ነው። አደራችሁን አገልግሎታችሁን እንዳታቋርጡ!!! አይዟችሁ እስካሁን ያሳለፋችሁት አገልግሎት፣ ቤተ ክርስቲያን የተመላለሳችኋት እያንዳንዷ እርምጃ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቆጥራለች። ምክንያቱም “እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።”(ዕብራውያን 6፥10) እግዚአብሔር ደግሞ ዋጋን የሚከፍለው በምድርም፣ በሰማይም ነውና አሁንም ለምትጀምሩት አዲስ የሥራ ሕይወት በበረከት ይጎብኛችሁ!!... በመንገዳችሁ ሁሉ እመብርሃን ከነልጇ ይቅደሙላችሁ! ስለማይነገረው ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። 👉መልካም የሥራና የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ!               ✨ አብርሂ አብርሂ                 ግቢ ጉባኤ ኢየሩሳሌም

  • 8 июн.5922из amumcgg

    "ለችግረኞችና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሄር በክፉ ቀን ያድነዋል" መዝ 40/41፥1-2 ሰላም የግቢ ጉባኤያችን ልጆች እንደምን ቆያችሁ🤗 እንደሚታወቀው ለእናቶች የክረምት አስቤዛ መግዣ መሰብሰብ ስለ ተጀመረ በዶርም፣ በክላስ የሚመጡ ልጆች ስላሉ ለሚመጡት ልጆች ያሏችሁን : የፕላስቲክ ዕቃዎች፣ ልብሶች ለእናቶች ስለሚጠቅማቸው ሲመጡ እንድትተባበሯቸው እንጠይቃለን 1000532546323 Dibora asrat ለበለጠ መረጃ : 0950179351                      : 0963810100                      : 0934926817                      : 0903103803 ሙያ እና ተራድኦ(ቅዱሳን መካናት)

  • 31 мая6991из amumcgg

    🕊️ የዝክር እና የምስጋና መርሐግብር 🙏 “ለእግዚአብሔር ምን እመልሳለሁ? ስላደረገልኝ ውለታ ሁሉ። የመድኃኒትን ጽዋ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።” መዝሙር 116:12-13 📖 “በእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት፣ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት ከሞት ከተረፍን 1 ዓመት ሆነ።” ✨ ያለፈው አመት በዚች ዕለት በግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ድንገተኛ አደጋ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው። ነገር ግን በዚያ ሁሉ ጨለማ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር አልተለየንም፤ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጋሻና መከታነትም ከሞት አፋፍ መልሶናል። 🙌 የተደረገልንን ታላቅ ነገር ወደ ልባችን መልሰን የምናስብበት፣ አምላካችን የምናመስግንበትና ሰማዕቱን የምንዘክርበት ልዩ ቀን ነው። 🔹 ኑ፣ በአንድነት ቆመን የምስጋና መሥዋዕት እንሰዋ! 📍 መርሐ ግብሩ መቼና የት ነው? ዛሬ፦  እሁድ ግንቦት 23 - 2018 ዓ.ም ሰዓት፦ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ቦታ፦ አምዩ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ -ደብረ ሎዛ ቅድስት ኪዳነምህረት “የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና በረከት አይለየን።” ይህንን መልዕክት ለሌሎችም Share ያድርጉ። 📢

  • 21 мая7091из amumcgg

    ‎🔷ውድ የ 2018 ዓ ም pre engineering ተማሪዎች 👪👪 ዛሬ ማለትም በቀን 13/ 09 / 2018 ዓ.ም የ C++ tutorial ስለሚሰጥ ሁላችሁም የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች የሰማችሁ ላልሰሙት እህት ወንድሞቻችሁ እያሰማችሁ እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን ። ‎እህት ወንድሞቻችን እንጋብዝ መቅረት አይታሰብም ። ‎ ‎🕕ሰአት :1፡30 ማታ ‎🏫ቦታ : "J" block ‎ ሙያና ተራድዖ : ነፃ ሙያ ንዑስ ክፍል

  • 6 мая1 0641

    https://vt.tiktok.com/ZS9qv9u8y/

  • 6 мая1 04611

    https://vt.tiktok.com/ZS9qWE1MR/

  • Share ይደረግ

  • 2 мая1 15722

    የግቢ ጉባኤያችን የ2017 የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ክፍል ተጠሪ የነበረው  ወንድማችን ሳሙኤል አውግቸው የውጪ የትምህርት ዕድል እየተወዳደረ ነውና.....ውድድሩ public vote ወይም ምርጫም ስላለው የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች Vote በማድረግ እንድትተባበሩት እያልን ከታች ባለው link እየገባን vote በማድረግ  እናግዘው👇👇 https://bunasm.com/#/voting/69edfb9b319e11614bc9d349?option=69f1e9d0d0ee3cb012160d09

  • 1 мая9503из amumcgg

    👀⏳7 ቀን ብቻ ቀረው ...    #33ኛ...  #ምሥረታ... 🙏መሐረነ አብ...የጸሎት ምሽታችን😍         ✨የእናት ግቢ ጉባኤ✨ ✨፴፫ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል        🗓 ከሚያዚያ 30 - ግንቦት 02 #story    #share ተሳተፉ 📌 የምሥረታ ቲሸርት 📌 ባለ7 ዕጣ ሎተሪ ማብራሪያ፡ እያንዳንዱን ጽሑፍ ይንኩት ወደ ዋናው መግለጫ ይመራል። ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ ©አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ

  • የግቢ ጉባኤያችን የ2017 የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ክፍል ተጠሪ የነበረው  ወንድማችን ሳሙኤል አውግቸው የውጪ የትምህርት ዕድል እየተወዳደረ ነውና.....ውድድሩ public vote ወይም ምርጫም ስላለው የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች Vote በማድረግ እንድትተባበሩት እያልን ከታች ባለው link እየገባን vote በማድረግ  እናግዘው👇👇 https://bunasm.com/#/voting/69edfb9b319e11614bc9d349?option=69f1e9d0d0ee3cb012160d09

  • 13 апр.6371из amumcgg

    ትንሳኤን ከእናቶች  ጋር "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩር ሆኖ ከሙታን ተነስቷል።" (1ኛ ቆሮንቶስ 15:20) እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓልን ከእናቶች ጋር በጋራ ስለምናሳልፍ ሁላችሁም ተጠርታችኋል። በዕለቱም :- የማይጠገበውን የእናቶች ጨዋታ እና ምርቃት በዓል በዓል ከሚሸቱ መንፈሳዊ መርሃግብሮች ጋር አጋፔን ጨምሮ አዘጋጅተን🏠 በእናታችን (ውሃ ምንጠጣበት) ቤት እንጠብቃችኋለን። 🗓 ሚያዝያ 05(ዛሬ) ⏰ 8:00 ⛪️ ውሃ ምንጠጣባቸው  እናት ቤት © አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

  • 13 апр.466из amumcgg

    ትንሳኤን ከእናቶች  ጋር "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩር ሆኖ ከሙታን ተነስቷል።" (1ኛ ቆሮንቶስ 15:20) እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓልን ከእናቶች ጋር በጋራ ስለምናሳልፍ ሁላችሁም ተጠርታችኋል። በዕለቱም :- የማይጠገበውን የእናቶች ጨዋታ እና ምርቃት በዓል በዓል ከሚሸቱ መንፈሳዊ መርሃግብሮች ጋር አጋፔን ጨምሮ አዘጋጅተን🏠 በእናታችን (ውሃ ምንጠጣበት) ቤት እንጠብቃችኋለን። 🗓 ሚያዝያ 05(ዛሬ) ⏰ 8:00 ⛪️ ውሃ ምንጠጣባቸው  እናት ቤት © አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

  • 6 апр.1 370111

    ✍​​በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡- በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግዕዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ ኪርያላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ እብኖዲ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው ታኦስ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ ማስያስ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው ትስቡጣ፦ «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

  • 6 апр.1 2997

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 апр.1 2656

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 апр.1 2906

    መልክዓ ኅማማት.pdf

  • 4 апр.1 16823

    ​​ሆሳዕና ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ሆሼዕናህ የሚል ሲሆን ትርጉሙም እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡ መዝ.117፡25-26 የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ ዕለት የጸበርት እሑድ /Palm Sunday/ ይባላል፡፡ ታሪካዊ አመጣጡ የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት መገለጫ ሆኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ይኸውም ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ጨርሳ ልማደ እንስት ከተቋረጠባት በኋላ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ ድርብ ደስታ በገለጡ ጊዜ፣ እንዲሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ አደባባይ ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን መስቀሉ /ሉቃ.22፤18/ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አእሩግ ነጻ የሚወጡበት ቀን መድረሱን እነርሱ ሳያውቁ እግዚአብሔር ባወቀ ዘንባባ በመያዝ ዘምረዋል፡፡ እስራኤል ዘንባባ በመያዝ እንዳመሰገኑት እኛም አስራኤል ዘነፍስ ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን በየዓመቱ እያስታወስን እናከብራለን፡፡ በዚህ ዕለት ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝቡ ይታደላል፡፡ ሕፃናትና አእሩግ ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል፡፡ እያሉ ዘምረዋል፡፡ ይህ ሁሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲሆን በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ ጸሐፍት ፈሪሳውያን መምህር ሆይ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ ሲል መልሶላቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው ፈሪሳውያንም የዋህ የሆነው ሕዝብ ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው በዕለተ ሆሳዕና እሑድ ዘንባባ ይዘው የዘመሩለትን ጌታ ዓርብ ይሰቀል ዘንድ ይገባል ብለዋል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በዚህም በነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡ ዘካ.9፡9፤ ማቴ.21፡4፤ ማር.11፡1-10፤ሉቃ.19፡28-40፤ ዮሐ.12፤15፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት ሲሆንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም እውነተኛ የኅሊና ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡ መላእክት በዕለተ ልደቱ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል በምድር ሰላም ለሰው ሁሉ ይሁን /ሉቃ.2፡13/ እያሉ የዘመሩለት የሰላም ባለቤት ነው፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም ሰላሜን እሰጣችኋለሁ /ዮሐ.14፡27/ ብሎ እንዳስተማረ ያን ሰላም የሚሰጥበትን ዕለት መቅረቡን ለማመልከት ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፣ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡ በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ ቅርብ ሲሆን በእምነት ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ መሆኑን አስተምሯል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜያችን ሳትጠልቅ በእምነት እንፈልገው፡፡ አሞጽ4፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፣ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅም። ኢሳ.66፡2፤ መዝ.50፡17፡፡ ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የሆነ ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደተቀመጠ ሁሉ ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት ዛሬም ያድራል፤ የኅሊና ሰላምን ይሰጣል። ስለዚህ ንስሐ ገብተን ጌታችንን ሆሳዕና በአርያም እያልን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር *ምንጭ፡ ሐመር ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ መጋቢት/ሚያዝያ 1996 ዓ.*ም

  • 📚ርዕስ:- ሕማማት 📝ደራሲ:- ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 📜ዘውግ፦ ሃይማኖታዊ 📖የገፅ ብዛት:- 460 📅ዓ.ም:- 2010 🔓Password:- @eotc_books_by_pdf

  • 1 апр.693из amumcgg

    ✨ዛሬ 📍 ከመጋቢት 23 - 25(ረቡዕ - አርብ ) 🔷 አስተማሪ መርሐግብሮች ስለተዘጋጁ መቅረት ያስቆጫል 📖 አንብበው ሴሚስተሩን ሙሉ የፈለጉትን መጽሐፍ ይዋሱ ⏰ማታ 12:00 - 1:30 ©️አርባምንጭ ዩንቨርስቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ

  • #story #share

AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት — tgindex