አምዩ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ
Статистика➣ ይህ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። 📞 ለበለጠ መረጃ በዚህ ይደውሉ +251941628237 ✨ አብርሂ አብርሂ ግቢ ጉባኤ ኢየሩሳሌም
- Последний пост
- 4 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 277
- 1/48двое суток
- 1 463
- 1/72трое суток
- 1 578
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ግቢ ጉባኤ የሚለው(በAudio የተለቀቀው) ዝማሪያችን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ 50k እይታን አግኝቷል ።እናመሰግናለን🙏 አሁንም ሰሞኑን የተለቀቀው የመዝሙሩ ቪዲዮ ከፍ ያለ እይታን ያገኝ ዘንድ ሁላችንም ከታች የተቀመጠውን ሊንክ ሼር እናድርግ። አብርሂ አብርሂ ግቢ ጉባኤ https://youtu.be/z6l_t4O4EzE?si=gGIDwwv5xOueJibx
видео или голосовое, без подписи
https://youtu.be/z6l_t4O4EzE?si=teMxJGo0tV1CfMhh ተለቋል🔥🙏🏻
ሁላችንም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ''ግቢ ጉባኤ'' የተሰኘው የመዝሙር ቪዲዮአችን ዛሬ ቀን 10:30 ላይ፤ በዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን youtube channel ላይ ይለቀቃል። አብርሂ አብርሂ አብርሂ ግቢ ጉባኤ ኢየሩሳሌም። http://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
#story #share #repost
видео или голосовое, без подписи
በሀገራችን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ካስነሳቸው ብፁዓን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ለቅድስት ቤተክርስቲያን ካላቸው አበርክቶት አንፃር በዘመኑ የተነሱ አጽራረ ቤተክርስቲያንን ለመመከት በሰሯቸው ሐዋርያዊ አገልግሎቶች ፣ በጻፏቸው መጻሕፍት ፣ በሰሯቸው ታላላቅ ስራዎች እንዲሁም በጥዑም ትምህርቶቻቸው ከምዕመኑ ጋር በተለይም ከወጣቱ ጋር የጠበቀ ልዩ ግንኙነት የነበራቸው ፣ ዛሬም በብዙኃኑ ልብ ውስጥ እንደ ታላቅ ትውስታ ተጽፈው የሚኖሩ ፣ ለማኅበረ ቅዱሳን ብሎም ለግቢ ጉባኤ መመስረት መሰረት የጣሉ ፣ ዛሬም ቤተክርስቲያንን በብዙ የሚያገለግሉ እንደሳቸው ያሉ በርካታ ሊቃነ ጳጳሳትን ያፈሩልን ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ አንዱ እና ዋነኛው እንደሆኑ አይዘነጋም። ብፁዕ አባታችን ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም ለአገልግሎት ሲሄዱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፉ የሚዘነጋ አይደለም። ✨እኛም ያዘጋጀነውን ዝማሬ ለእኝህ ታላቅ አባት መታሰቢያ ይሆንልን ዘንድ የፊታችን ሐምሌ ፳፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን ዜማ ወጥበብ የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል።✨ youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉 ‘’ፍሬያማነት በፈተናዎች ውስጥ ያልፋል፤ ውበትም በቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት ይገለጣል!’’ ✨ የዋና ግቢ ጉባኤያችን ሁሌም በክህሎታቸውና በትጋታቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ ፍሬያማ ወጣቶችን በማፍራት 🌱 ይታወቃል ። ዛሬም፣ የግቢ ጉባኤያችንን በመወከል ፣በማኅበረ ቅዱሳን ሙያዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ዘርፍ (የምሕንድስና አገልግሎት ክፍል) ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሕንፃ አርክቴክቸር ተማሪዎች ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ንድፍ (Church Design Competition) ውድድር ላይ ተሳትፎ የነበረው ወንድማችን ምንተስኖት ፀጋዬ አስደናቂ ውጤት አስመዝግቦ ውድድሩን በስኬት በማጠናቀቅ 🥉ኛ ደረጃን በመያዝ የ30,000 (ሠላሳ ሺህ) ብር ተሸላሚና የክብር ምስክር ወረቀት ተቀባይ ሆኗል! ለመላው የዋና ግቢ ጉባኤ አባላት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! 🙌 ለተወዳዳሪው ወንድማችን ምንተስኖት ፀጋዬ በበኩሉ ፈታኝ የሆኑ የምሕንድስና ፈጠራዎችን አልፎ ይሄንን ያማረ ፕሮግራም ስላሳካ እና ለግቢ ጉባኤያችን ኩራት ስለሆነ ታላቅ ምስጋና እያቀረብን፤ የአገልግሎት ዘመኑን እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ እንዲባርክለት እንመኛለን 🙏✨። «ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን» ©️የአምዩ ዋና ግቢ ጉባኤ መዝሙር እናሥነ ጥበባት ክፍል ሥነ-ስዕል ንዑስ ክፍል
✨‟ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር — ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።”✨ መዝሙር ፻፲፯ ፥ ፳፮ 🎓🎓ውድ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂዎች እንኳን በጉጉት ለምትጠብቋት ለዚች ልዩ ቀን እግዚአብሔር በሰላም አደረሳችሁ!! የዓመታት ድካምና ልፋታችሁ ፍሬ አፍርቶ ለዝች ቀን በመድረሳችሁ ግቢ ጉባኤያችን በእናንተ ትኮራለች። ግቢ ጉባኤያችንም እናንተን ውድ ልጆቿን ለመሸኘትና አደራ ለመስጠት ነገ እሁድ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ትጠብቃችኋለች፣ ሁላችሁም ተመራቂዎች ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን በሰዓቱ እንድትገኙ ይሁን!! 🔹 ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ 🔹 ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ!!!🎓🎓
🙏መሐረነ አብ +++ ወበከመ ዐቀብከነ እምነግህ እስከ ሠርክ ዕቀበነ እግዚኦ እምሠርክ እስከ ነግህ፤ ከጧት ጀምሮ እስከማታ እንደጠበቅከን ከማታ እሰከ ጧት ጠብቀን። ⏳12:00
ሰላም እንዴት ናችሁ?? ✍ዛሬ ወረብ ጥናት ይኖረናል 🔹ከዚህ በፊት ስታጠኑ የነበራችሁ ተመራቂ ተማሪዎች ጓደኞቻችሁን እየቀሰቀሳችሁ እንድትገኙ። 👉ማንም ሰው እንዳይቀር ⌛️ 12:00
ሰላም 🤝 ወድ 🎓🎓🎓 ተመራቂ (GC) ተማሪዎች እንደምን ከረማችሁ🙏: Exit exam መልካም እንደ ነበር ተስፋ እናደርጋለን : ለልፋታችሁ መልካም ውጤት ለምርቃታችሁ ደግሞ በሰላም ያድርሳችሁ ብለን ምኞታችንን እየገለጽን : ምናልባት ለግቢ ጉባኤ ልጆቻችን ቅርስ እናስቀምጣለን ብላችሁ ከአሁን በፊት ያነበባችኋቸውን 🔷 መንፈሳዊ መጻሕፍት 📚📚ለቤተ መጽሐፍ ማበርከት የምትፈልጉ ካላችሁ እና 🔷ከአሁን በፊት ከቤት መጻሕፍት ተውሳችሁ በእጃችሁ ያለ ያልመለሳችሁት መጽሐፍ ካለ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐሙስ ማለትም ከቀን 15 -18 ባሉት ቀናት ውስጥ እንድታስረክቡ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን። ተጨማሪ ከአሁን በፊት እንደምታውቁት የተለያዩ አልባሳት : መጠቀሚያ እቃዎች እና ሌሎችም አበርክታችሁ የምትሔደት ነገር ካለ በዚህ ስልክ 0911959989 0901234850 0934926817 ማስረከብ ትችላላችሁ መልካም ዝግጅት ይሁንላችሁ ለምርቃት ቀን 🙏🙏🙏 👨👦👦 ሙያና ተራድኦ👨👦👦
ሰላም እንዴት ናችሁ?? ዛሬ ወረብ ጥናት ይቀጥላል 12:00 ተመራቂ ተማሪዎች ጓደኞቻችሁን እየቀሰቀሳችሁ ከኪዳነምህረት ደጅ እንገናኝ!! መልካም ውሎ🙏
✨እንኳን ለገናናው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል በዓል በሰላም በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ። ✍ተናፋቂው የዓርብ መሐረነ አብ🙏 ጸሎታችን እነሆ ዛሬ 12፡00 ስለሚጀምር ሁላችንም ጓደኞቻችንን በመቀስቀስ በጸሎቱ እንድንሳተፍ ይሁን። 🔹ስመር እግዚኦ ከመ ታድኅነነ ኢታርምም እግዚኦ ወኢትጸምመነ ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንኅነ መልአኩ ሚካኤል ካልታሰበ መከራ እና ፈተና ይሰውረን 🙏
✍ ውድ GC እና የ2018 ዓም pre engineering ተማሪዎች ሁላችሁም እንደምን አላችሁ እንደሚታወቀው በየሳምንት እሁድ እሁድ የእናቶች ዳቦ ማውጣት ነገም ማለትም እሁድ ስለሚወጣ ሁላችንም GC እና Pre engineering ተማሪዎች ዳቦ እንድናወጣ ይሁን! ✨ በተጨማሪ ነገ የሚመቻችሁ ሁላችሁም እየሄዳችሁ እናቶችን እንድትጠይቁ ስንል እናሳስባለን 🙏 © ሙያና ተራድኦ ክፍል
✍ወርኃዊ የእናታችን የቅድስት አርሴማ ዝክር 🔹ዛሬ 12:00 ሰዓት ይቀጥላል 📍ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ✨ከዝክር በኃላ የGC ወረብ ጥናታችን ይቀጥላል ✨አብርሂ አብርሂ ግቢ ጉባኤ✨ © አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ
🙏መሐረነ አብ +++ ወበከመ ዐቀብከነ እምነግህ እስከ ሠርክ ዕቀበነ እግዚኦ እምሠርክ እስከ ነግህ፤ ከጧት ጀምሮ እስከማታ እንደጠበቅከን ከማታ እሰከ ጧት ጠብቀን፤ ✨ የህብረት ጸሎታችን 4ኛ ቀን ስለሚቀጥል ሁላችንም በሰዓቱ እንገኝ። ✍exit ተፈታኝ ተመራቂዎችም በቤቱ ሄደን ልንማጸን ስለሚያስፈልግ እስከ አርብ በሚቀጥለው በዚህ የጋራ ጸሎት ላይ እንድንሳተፍ ይሁን። ⏳12:00
ዛሬ ከመሀረነ አብ በኃላ ወረብ ጥናት እንጀምራለን🙏🙏