tgindex
ዮሐንስ ጌታቸው

ዮሐንስ ጌታቸው

Статистика

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 137
−7 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 981
20 постов
Вовлечённость
63,1%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
485
1/48двое суток
555
1/72трое суток
599

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://youtu.be/J1og7Pp2rcQ?si=XOTC2WbZ_OJJ7GN6

  • ++++#የእማሆይ_ሲንቅለጢቃ_ምክር#++++ የሰይጣን ብልሃቱ ብዙ ነው። ነፍስን በድህነት ማሸነፍ ካቃተው ብልጽግናን ያመጣባታል፣ በስድብ ማሸነፍ ካቃተው ክብርና ውዳሴ ያስከትልባታል። በጤንነት ድል ማድረግ ካቃተው፣ ሕማምን ያመጣል፣ በምቾት ማባበል ሲሣነው ከፍላጎት ውጭ በኾነ ሥቃይ ይሞክራል። ከዚህም ጋር እጅግ መራር የኾነ ደዌ ያመጣል። ገና ያልጸኑትን ፈሪዎች ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ያቀዘቅዝባቸው ዘንድ፣ ሰውነትን በክፉ ንዳድ ይመታና ያከሳቸዋል፣ ሊቋቋሙት የማይችሉ የውኃ ጥምም ያመጣባቸዋል። ኃጢአተኛ እንደ መኾንህ ይህን ኹሉ ስታልፍ የፈጣሪህን ፍርድ፣ የማይጠፋውን እሳት፣ የሚመጣውን ዘለዓለማዊ መከራ አስብ። ነገር ግን ተስፋ አትቍረጥ። እግዚአብሔር ይጎበኝሃልና ደስ ይበልህ። "መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፣ ለሞት ግን አልሰጠኝም" (መዝ 117፥18) የሚለውን ቃል አስበው። አንተ እንደ ብረት ነህ። እሳቱ ዝገትህን ያጸዳዋል። ጻድቅ ኾነህ በደዌ ብትመታ ከኃይል ወደ ኃይል ያሻግርሃል። ወርቅ ነህን? እሳት ያነጻሃል። የሥጋ መውጊያ ተሰጥቶሃልን? (2ቆሮ 12፥9) በዚህ መልክ የተፈተነ ማን እንደ ኾነ አስብና ተደሰት። ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር አንድ ዓይነት መከራ መቀበል ላንተ ክብር ነውና። በንዳድ ትሠቃያለህን? "በብርድ ተመተሃልን?"በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን ወደ ዕረፍትም አወጣኸን (መዝ 65፥12) ያለውን ቃል አስበው። አንዱን ስትሻገር ሌላውን ጠብቅ፣ በበጎ ሕሊና ውስጥ ኹንና የከንፈርን መሥዋዕት ሠዋ "እኔ ችግረኛ ቍስለኛ ነኝ" (መዝ 68፥29) በል፤ ይህንን የመሰለውን ድካም ከተቀበልክ ወደ ፍጹምነት ትደርሳለህ። እግዚአብሔር በጠራሁት ጊዜ ሰማኝ (መዝ 4፥3) ብሏልና አንደበትህን ክፈት፣ በእነዚህ የነፍስ ውጣ ውረዶች ውስጥ በማለፍ በጠላታችን ዐይን ሥር እያለፍን መኾኑን ትረዳ ዘንድ። (ዳንኤል ክብረት፣ በበረሓው ጉያ ውስጥ፣ 2004 ዓ.ም፣ ገጽ 78)። የሰይጣን ዓላማው ኹል ጊዜም ቢኾን እኛን ከትክክለኛው መንገድ ማስወጣትና በምድር ላይ ያለንን ሕይወት ፍሬ ቢስ እንዲኾን ማድረግ ነው። ይህንም ዓላማውን ለማሳካት በብርቱ ይፈትነናል። ቅዱስ ጳውሎስ "ከኃጢአት ጋር እየታገላችሁ ገና ደምን እስከማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም" ይላል፣ ዕብ 12፥4። ከተፈጠርንለት የሕይወት ዓላማ ውጭ ሊያደርገን የሚመጣብንን ፈተና ኹሉ ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ለማለፍ የራሳችንን ድርሻ እንወጣ። በገጠሙንና ለወደፊትም ሊገጥሙን ባሉ ፈተናዎች ምክንያት የክርስትናን ሕይወት በተሸናፊነት አቋርጠን አንውጣ። ጌታችን "እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል" ብሏልና።

  • 7 авг.1 31713

    #በውዳሴ_ማርያም_ላይ_ለሚነሡ_አንዳንድ_ጥያቄዎች_የተሰጠ_አጠር_ያለ_ማብራሪያ። https://youtu.be/a7fM1N4NG60?si=dvPNduU3_wdYyqb7

  • 31 июл.1 1742

    Mikiyas Berhanu: የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት የዩቲዩብ ቻናል - ”ሠሌዳ ሚዲያ” ሥራ ጀመረ! የሠሌዳ ሚዲያ የስቱዲዮ ምረቃና የቻናሉ ይፋዊ  የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት የሃይማኖት አባቶች፣ መምህራንና የተከበሩ እንግዶች በተገኙበት ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀትና በመንፈሳዊ ክብር ተከናውኗል። የትውልዱን ሕሊና በዕውቀትና በጥበብ የሚያንጹት የተወዳጁ መምህር መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርቶች በ"ሠሌዳ ሚዲያ" መድረክ በኩል ለአድማጮችና ለተመልካቾች መቅረብ መጀመራቸው አገልግሎቱን በስፋት ለማዳረስ ተጨማሪ ዕድል እንደሚሆን ታምኖበታል። ሠሌዳ ሚዲያ በመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የተመሠረተ የዲጂታል ሚዲያ መድረክ ሲሆን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር እውነትን፣ ጥበብንና ኦርቶዶክሳዊ ዕሴቶችን የሚያለመልምና ትውልድን የሚያጎለብት የዕውቀት ምንጭ እንዲሆን ታስቦ ሥራ ጀምሯል። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕያው ቃሉ "ምን እንድትሰሙ፥ ተጠበቁ"(ማርቆስ 4፥24)  እንዳለው፥ ሠሌዳ ሚዲያ አድማጭና ተመልካቾች የሚያዩትንም ሆነ የሚሰሙትን በመጠኑና በጥንቃቄ እንዲመርጡ ለሚያሳስበው የዘመኑ የነፍስ ጥሪ ምላሽ የሚሆኑ የጠሩ እና የተመረጡ ይዘቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡ በሠሌዳ ሚዲያ፡- Ø  መንፈሳዊ ትምህርቶችና ስብከቶች፣ Ø  የማኅበረሰብ ጉዳዮች ዳሰሳዎችና ትንተናዎች፣ Ø  የባህልና የዕሴት አንጸባራቂ አንድምታዎች፣ Ø  ከምሁራን፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ ጥልቅ ውይይቶችና ቆይታዎች Ø  ሌሎችም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ርእሰ ጉዳዮች በሚዛናዊነትና በኃላፊነት ስሜት ይቀርባሉ፦ ይህን የዕውቀትና የጥበብ ማዕድ ለመካፈል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይወዳጁን፤ ለብዙኃኑ ተደራሽ እንዲሆንም አጋር በመሆን ሰብስክራይብና ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! YouTube:ሠሌዳ ሚዲያ TikTok: @seledamedia Instagram: seledamedia Facebook: Seleda Media ሠሌዳ ሚዲያ - ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። ### Youtube https://www.youtube.com/@seledamedia.megabehadiseshetu Tiktok http://www.tiktok.com/@seledamedia Instagram https://www.instagram.com/seledamedia/ Facebook https://web.facebook.com/profile.php?id=61591554360962

  • 22 июл.1 2574

    https://youtu.be/SjVE1qycVm4

  • 17 июл.1 3835

    https://youtu.be/PmXViVq-qqI?si=IrMBHpV4XwrTjMDI

  • 15 июл.1 4024

    https://youtu.be/mYQKPwXhWYU?si=JzYhzTovE3sjEcuk

  • 13 июл.1 9617

    https://youtu.be/OPWYMt8oWfo?si=wK8Uqx-w1cDccYr5

  • 8 июл.2 2583

    видео или голосовое, без подписи

  • 8 июл.1 6522

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 июл.4 51033

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 июл.3 54224

    #ለመጽሐፍ_ምርቃቱ_ቀን_5_ቀናት_ብቻ_ቀሩት_ሐምሌ_4_2018_ከቀኑ_7፡00 ጀምሮ_በቅድስት_ሥላሴ_ዩኒቨርሲቲ_ሕንጻ_አራተኛ_ፎቅ_ላይ_ኹላችሁም_ተጋብዛችኋል። በዚያ ቀን ቀጠሮ ይዛችሁ እንድትገኙልኝ ስል በአክብሮት ጋበዝኋችሁ🙏 ለቅምሻ ያህል ከኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሥላሴ፦ ቅዱስ አትናቴዎስ “የተለያዩ የአካል ክፍሎች ተሰብስበው ሙሉ አካልን እንደሚገነቡ፣ ሙሉ አካልም የተለያዩ ክፍሎች ውሑድ እንደ ኾነው፣ እያንዳንዱ ክፍልም የሙሉ አካሉ ክፍል ነው፡፡ ይህ ግን ስለ አምላክ ካለን ሐሳብ እጅጉን የራቀ ነው፡፡ እግዚአብሔር ምሉዕ ነው፤ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ወይም ልዩ ልዩ የኾኑ ንጥረ ነገሮች ውሑድ አይደለም፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ የዓለምን ሥርዓት የሠራ ነው፡፡ አምላክ የአካል ክፍሎች አለው ሲሉ ምን ዓይነት የማይረባ ነገር አምላክን ተቃርነው እንደሚናገሩ ተመልከቱ፡፡ እርሱ ከአካል ክፍሎች ከተገነባ፣ በእርግጠኝነት እርሱ ራሱን አይመስልም፣ ከማይመሳሰሉ የአካል ክፍሎችም የተገነባ ነው የሚለውን ሐሳብ ያስከትላል፡፡ እርሱ ፀሐይ ከኾነ ጨረቃ አይደለም፤ ጨረቃ ከኾነ ምድር አይደለም፤ ምድር ከኾነ ባሕር መኾን አይችልም፤ ወዘተ፡፡ … ዓይን የመስሚያ አካል አይደለም (ጆሮ)፣ የኋለኛው (የመስሚያ አካል) እጅ አይደለም፣ ሆድም ደረት አይደለም፣ እንደገና አንገትም እግር አይደለም፣ ነገር ግን እያንዳንዱ የራሱ ሥራ አለው፤ አንዱ ነጠላ ሰውነት ከእነዚህ ክፍሎች የተገነባ ነው፡፡ … ይህን ለአምላክ የሚሰጡ ከኾነ የሚከተሉትን ያመጣል፡- አንደኛ ከላይ እንዳየነው እርሱ ራሱን አይመስልም ያሰኛል፤ ኹለተኛ ተፈጥሮአዊ በኾነ ኹኔታ የአካል ክፍሎች እንደሚከፋፈሉት እርሱንም እንደገና እንዲከፋፈል እናደርገዋለን፡፡” ይላል፡፡ በመኾኑም እግዚአብሔር የአካል ክፍሎች አሉት ማለት ተገቢ አለመኾኑን ይህ ሊቅ ያትታል፡፡ እኛ ጋር ያሉ የአካል ክፍሎችን ለእግዚአብሔር ሰጥቶ መናገር ወይም ለእግዚአብሔር አካሉን ከፋፍሎ ዐይኑ የኾነ የአካል ክፍሉ ነው፣ ጆሮውም የኾነ የአካል ክፍሉ ነው፣ እጁም የኾነ የአካል ክፍሉ ነው … እያልን ልንከፋፍል አይገባም ነው ሊቁ የሚለን፡፡ ለቅምሻ ያህል ከዐይነ ልቡና መጽሐፌ፦ ቃል ሥጋ ሲኾን፣ ቃልነቱን ለቆ ሥጋ ወደ መኾን አልተለወጠም፤ ይህማ ቢኾን ፈጣሪ ፈጣሪነቱን ለቆ ፍጡር ኾነ ያሰኛል። እንዲህ ይኾናል ብሎ ማሰብ አእምሮ ካለው ከማንም የሚጠበቅ አይደለም። በመጽሐፍ "እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም" ብሎ ራሱ ባለቤቱ እንደ ተናገረው በአምላክ ዘንድ ውላጤ ፈጽሞ የለም፤ ሊኖርም አይችልም። ፈጣሪን ፍጡር ወደ መኾን ይለወጣል ብሎ የሚያምን ሰው ፈጣሪ የለም ብሎ ከሚያምን ጋር ነው ቍጥሩ ሊኾን የሚችለው። በሌላ በኲል ሥጋም ቃልን ወደ መኾን መለወጥ አይችልም። ምንም እንኳን ለፍጥረት ለውጥ ቢስማማውም በምንም መንገድ ቢኾን ፍጡር በራሱ ፈጣሪ ወደ መኾን ሊለወጥ አይችልም። ፍጡር ፈጣሪ ወደ መኾን ይለወጣል ብሎ ማሰብም ፈጣሪም ፍጡር ወደ መኾን ይለወጣል ብሎ ከማሰብ በላይ ስሕተት ነው። ፍጡር ፈጣሪ ወደ መኾን መለወጥ ከቻለ ለፍጡር የተቻለ ለፈጣሪ አይቻልም ይባል ዘንድ ተገቢ ስላልኾነ ፈጣሪም ይለወጣል ብሎ በተዘዋዋሪ እንደ ማመን ነው። በእርግጥስ ፍጡር ፈጣሪ ወደ መኾን መለወጥ ከቻለ ቀድሞ ፈጣሪ የነበረው አዲስ ከሚመጣው "ፈጣሪ" ጋር እንዴት ሊኾን ኖሯል? ይህን ውዥንብርና የተምታታ አስተሳሰብ ከየልቡናችን ልናስወግድ ይገባል። ቃል ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ቃልነቱን ለቋል፤ ሥጋም ቃልን በተዋሐደ ጊዜ ሥጋነቱን ለቋል የሚል ቢኖር ፈጽሞ የተወገዘ ነው። ከላይ ያነሣነውን መሠረት አድርጎ መቃርስ እንዲህ ይላል፦ "ሰውም ቢኾን አምላክነቱን አልለቀቀም፤ አምላክነቱን ለቀቀ ማለት አይገባም፤ በተዋሕዶ አንድ በኾኑት (በመለኮትና በትስብእት) መለወጥ፣ ባሕርይን መልቀቅ የለም፤ በአለበት በተዋሕዶ ጸንቶ ይኖራል እንጂ።" እንዲል። ሃይ. አበ.ዘመቃርስ 98፥15። Share በማድረግ ወደ ብዙኀን አድርሱልኝ🙏

  • 27 июн.3 38919

    видео или голосовое, без подписи

  • 27 июн.1 8675

    #እንደ_እግዚአብሔር_ፈቃድ_ሐምሌ_04፣ 2018 ዓ.ም_ከቀኑ_7፡00 ጀምሮ ኹለት መጻሕፍትን አስመርቃለሁኝ። #ውድ_ኦርቶዶክሳውያን_በዚያ_ቀን_እንድትገኙ_በአክብሮት_ጥሪዬይን_አቅርቤላችኋለሁ🙏 #ማስታወቂያውን_Share_በማድረግ_ብዙኀን_እንዲመለከቱት_ታደርጉልኝ_ዘንድ_በአክብሮት_እጠይቃችኋለሁ🙏

  • 19 июн.2 8659

    +++#የባሕራን_ደብዳቤ#+++ ባሕራን መመጽወትና መዘከር ጽኑዕ አገልግሎቱ ከኾነ አባት የተወለደ ነው። እናቱም በዚያ መልካም ግብር ተጸምዳ ትኖር የነበረች ናት። አባትና እናት በአስተሳሰባቸው አንድ ኾነው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሲሠሩ ፡ ጎረቤታቸው ያለው ክፉ ባለ ጸጋ የመልካምነት ክንፉን በቅምጥልነት ሕይወቱ ስላጣው፡ በአስተሳሰብ ልዕልና ከመገኘት ይልቅ መሬታዊ በኾነ ክፋት ቆሳስሏል። የቅዱስ ሚካኤልን መክበር በፍጹም አካሉ፣ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ልቡናው ተጸይፏል። ይህ ሰው ከቤቱ ደጅ ያለውን የመልካምነት ትምህርት ቤት (የባሕራንን ቤተሰብ ሕይወት) ለመማር ባለመፈለግ ደንቁሯል! ይህ በእጅጉ አሳዛኝ የኾነ ሕይወት ነው። የተሰጠውን ሀብት አለመጠቀሙ! ያሳዝናል፤ ያስቆጫልም! ምናልባትም የእኛ ምሳሌ ኾኖ እርሱ ራሱ በአኗኗሩ እንዳይገስጸን እንመርምር! ባሕራን ስሙን የወረሰው ከተገኘበት ባሕር የተነሣ ነው። ከባሕር ተገኝቶ የተገኘባትን ባሕር በስሙ ተሸክሟት ኖረ። ተወዳጅች ሆይ የተገኘንባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተሸክመናት ይኾን? ወይስ አኹንም በላዩአ ተንሳፈን እየተጓዝን። ማለትም ተኝተንባት! ንስሓ ላይ ተኝተን፤ ቅድስና ላይ ተኝተን፤ ምጽዋዕት ላይ ተኝተን፤ ክብረ መላእክት ላይ ተኝተን፤ ፈቃደ እግዚአብሔርና ሕገ እግዚአብሔር ላይ ተኝተን የምንጓዘው እስከ መቼ?! ባሕራንን ባሕራን ብሎ የሰየመው የበጎች ጠባቂ እረኛ የነበረው አሳዳጊው ነው። ክርስቲያኖች የኾነውን እኛንም ክርስቲያን ያሰኘን ስለ እኛ የቅድስት ድንግል ማርያምን ፍጹም ሥጋና ነፍስ ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከእርሱ ፈቃድ መውጣት ክርስትናን ማጣት መኾኑን ልብ ይሏል። ከዕለታት አንድ ቀን ባሕራን የጨካኙ ጎረቤታቸውን ሀብት ንብረት የሚወርስ መኾኑ በእግዚአብሔር መልአክ ተነገረ። ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ የባሕራን አባት ሞተ። ባሕራንም የባለ ጸጋውን ሀብት የሚረከብ መኾኑን ባለጸጋው እንዲያውቅ እግዚአብሔር ፈቀደ። ሀብቱ የተሰጠው እንዲጠቀምበት ነበራ! በእጃችን ያለው ገንዘብ እንደ እውነቱ ከኾነ እኛ ጋር ያስቀመጠው የእግዚአብሔር ነው። የተሰጠንን ቍሳዊ ሀብት በፍትሐዊነትና እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ ካልተጠቀምን የሚወሰድብን መኾኑን ልብ እንበል! አስተውሉ!እኛ ራሳችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መኾናችን ከገባን ሀብት ንብረታችንማ እንዴት የእርሱ አይኾን! አብርሃምን ባለ ጸጋ ያደረገው በተሰጠው ነገር ኹሉ በቅንነት እግዚአብሔርን ማገልገሉ መኾኑን አንድም ከባለ ጸጋው ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ መኖሩ መኾኑን ልብ ይሏል። ባለ ጸጋው ከባሕራን እናት ልጇን የሚንከባከብ መስሎ ተረከበው፤ ወደ ባሕርም በሳጥን አድርጎ አስወረወረው። ከዚያን ባሕራንን ባሕራን ባለው በግ ጠባቂ ባሕራን ባሕር ዳር ላይ ተገኘ። ባሕራንም ተባለ! ከ20 ዓመት በኋላ ባለጸጋው መንገድ ሲሄድ ባሕራን ካለበት ድንገት ደረሰ። ከአሳዳጊው ታሪኩን ሲሰማ ቀድሞ ያስጣለው መኾኑን ተረዳ፤ የሞት ደብዳቤ አስይዞ ባሕራንን ላከው። የራሱን የሞት ደብዳቤ ይዞ የሚጓዘው ባሕራን ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ወደ ሕይወት ደብዳቤ ገለበጠለት። ብዙዎቻችን ባለማወቃችን ምክንያት የሞት ደብዳቤ ይዘን ወደ ሲዖል እንፈጥናለን። በጭካኔ፣ በጥላቻ፣ ባልተገባ ትችት፣ በሐሜት፣ በሌሎች ሰዎች ውድቀት በመደሰትና በመሳሰሉት የሞት ደብዳቤ ወደ ጥፋት እንፈጥናለን። የዕለት ዕለት የሕይወት መርሐችን ወደ ሞት የሚወስድ እንጂ ወደ ሕይወት የሚያደርስ አይመስልም። ምክንያቱም ዕለት ዕለት እንደ ምግብ ኃጢአትን እየደጋገምን እንፈጽማለንና። እንግዲህ መልአኩ የልቡናችንን ሐሳብ በምልጃው ባያቀናልን ኖሮ እየገሠገሠን ያለነው ወደ ዘረኝነት ሞት፣ ወደ ድንቁርናና ስንፍና ሞት፣ ወደ ቅናትና ትዕቢት ሞት መኾኑን ልብ እንበል! ቅዱስ ሚካኤል በኃጢአታችን ምክንያት ወደ ተስፋ መቍረጥ የምንጓዘውን ከመንገድ ያግኘን። ከሞት አፋፍ በምልጃው ይታደገን። ወደ ሕይወት የምንገባበትን መልካም ሥራ በሰውነታችን ውስጥ ያለምልምልን። እንግዲህ ያ የባሕራንን ደብዳቤ የሚቀለበስልን በምንሠራው ሥራ አማካኝነት መኾኑን እንረዳ፤ ወደ ጽድቅ እንሩጥ፤ ከጥላቻ ሰውነታችንን እናላቅቅ! ጣዕሙ እጅግ ደስ የሚያሰኘውን የፍቅር ደብዳቤ ከልቡናችን መዝገብ አጽፈን፤ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንገሥግስ። በሕይወታችን ሊገጥሙን የሚችሉትን መሰናክሎች እኛ ባናያቸውም እንኳን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ይለውጥልናል። ሕይወታችንን በለመለመ የውኃ መስክ አጠገብ የበቀለች ተክል አድርጎ ያሳምረዋል። እንግዲህ የባሕራን ደብዳቤ መነሻዋ ጥፋት መድረሻዋ ግን ሕይወት ኾኗል። አምላካችን እግዚአብሔርም በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ምልጃ የኃጢአት ደብዳቤያችንን ሰርዞ የጽድቅ ያድርግልን አሜን!

  • 12 июн.1 6952

    https://youtu.be/4GNEMjTBx-k?si=vbjfe2bHlguisvv5

  • 9 июн.1 6976

    https://youtu.be/-JIC5lqv4U0?si=0ElGaq9uNBXjjITP

  • 3 июн.2 81017

    +++#ለመንጋው_የማይጨነቁ_እረኞች#++++ ከእግዚአብሔር የተሰጠችው ሃይማኖት ንጹሕ ልቡናን ትፈልጋለች። ልቡና በዚህ ዓለም ክርፋት ከተያዘች ሃይማኖትን መያዝ አትችልም። በዚህ ዘመን ትልቁ ፈተና ያለው እቤታችን ውስጥ ነው። ኹሉ የደፈረንና ያቀለለን ሃይማኖትን ከዚህ ዓለም ክርፋት ጋር ቀይጠው በያዙ እረኞች ምክንያት ነው። ብዙዎቹ በዚህ ዘመን ያሉ እረኞቻችን ለምን እረኛ እንደ ኾኑ ኹሉ የሚያውቁ አይመስሉም። የሚኖሩት በጎቻቸውን ጠብቀው የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያወርሱ ሳይኾን በዚህ ዓለም ተቀማጥለው ለመኖር ነው። መሠረታዊውን የእረኝነት ግብር ከተውት ቆይተዋል። ስለዚህ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የኾኑ አካላት ቢያቃጥሉን፣ ቢያርዱን፣ በድንጋይ ቢቀጠቅጡን፣ በመጋዝ ቢተረትሩን፣ አንገታችንን ቢያርዱት ብዙም ስሜት የሚሰማቸው አይመስልም። እነርሱ ያሉት በራሳቸው የምቾት ዞን ላይ ስለ ኾነ የእኛ ጩኸት አይሰማቸውም። እግዚአብሔር ይጠብቀን እንጂ እረኞቻችን ተስፋ አስቆራጮች ናቸው። እረኞቻችን ቍስላችን የማይጠዘጥዛቸው፣ መከራችን የማይሰማቸው፣ በየዕለቱ የክርስቲያኖች መገደል፣ መሰደድ ብዙም የማይረብሻቸው፣ ከልብ በጥብዓት ኾነው ልጆቼን አትንኩ ብለው ከፊት ለፊት የማይቆሙ መኾን ከጀመሩ ቆዩ። ስለዚህም እንደ ዘመነ ሰማዕታት ዕለት ዕለት እንገደላለን። እረኞቻችን ምቾት ያለበት ቦታ ሲኾን ሰብሰብ ብለው ይገኛሉ፤ መከራና ሥቃይ ሲኾን በሩቁ ባልሰማና ባላወቀ ለማለፍ ይሞክራሉ። መንግሥትንም ፊት ለፊት ለምን ብለው ለመጠየቅ ይፈራሉ፣ እኛንም ያስፈራራሉ። መንግሥትም በሞታችን ኹሌም ሌላ ፖለቲካዊ ስም እየሰጠ ይቀልድብናል። ለመኾኑ ይህ በገዛ ሀገራችን ባዕድ ኾኖ መኖር እስከ መቼ ይቀጥላል? በዚህ ሰዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን የማይገደሉበትና የማይሰደዱበት የማይታፈኑበት ቦታ የት ነው? በእርግጠኝነት ከእረኞች አንዱን ምእመን በሚገደሉበት አሠቃቂ መንገድ ገዳዮቻችን ቢገድሏቸው ይፈሩና አብረው መጮኸ ይጀምሩ ነበር ብለን እስክናስብ ድረስ አድርገውናል። እንዲህ እስክናስብ ድረስ እጅግ በጣም ፈትነውናል። እረኞቻችን እንኳን እኛን ሊጠብቁን ገና ለገና እኛን ሊያገዳድሉን የዘር ፍጭታቸውን ቀምመው ይስጡናል። ለምን? የሚሾሙት እግዚአብሔር የሰጣቸውን አደራ ለመጠበቅ ሳይኾን፤ ሊቀማጠሉብን፣ ብር ሊሰበስቡ፣ የየግል ቤት ሊሠሩ፣ ሊዝናኑና ዘና ፈካ ሊሉብን ነውና። የሚሾሙትም ቢኾን ወይ በዘር ወይም በገንዘብ ወይም በመንግሥት ነው። የቀኖና መጻሕፍት ላይ የተቀመጠው ሕግ ቆይቷል ከተሻረ፣ ቢጠቀስ ይቀልዱብናል፣ እንደ ጅልም ይቆጥሩናል። "እኛ ቀድመን እንገደላለን እናንተ መግለጫ ብቻ እያወጣችሁ ቀልዱብን፤ ተራችሁ ሲደርስ በጎቹን ያጠፋ እረኞችን የሚተው አይምሰላችሁ" አኹን ላይ ያለው ቤተ ክህነት በሙሰኛ፣ በዘረኛ፣ በከሐዲ፣ በአረመኔ የተሞላ፣ ኦርቶዶክሳዊነት የራቀው ፍጹም ዓለማዊ ስለ ኾነ በይፋ ከእነዚህ አካላት ጋር መጋፈጥ ያስፈልጋል። እየገለጹ ያሉት በይፋ ኦርቶዶክሳዊነትን እንደ ካዱ ነው። ትልቍ የሃይማኖታችን ጠላት የአረመኔ ስብስብ የኾነው ቤተ ክህነት ነው። የመንግሥት አካላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማጥፋት አቅደው ስለሚሠሩ ምንም ዓይነት ነገር አይሰማቸውም። እነርሱም የፈለጓትን ኢትዮጵያ ለመገንባት ተግተው መሥራታቸውን እየገለጹ ነው። ለዚያ ነው ለዓለም ኹሉ ጮኸን በዓለም ኹሉ መነጋገሪያ የኾነው የአርሲ ክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ ቀለል ተደርጎ የተወሰደውና ምንም እንዳልተፈጠ እየታየ ያለው። ኦርቶዶክሳውያንን እያስገደሉ እና እየገዱ እየጨረሱ ያሉት የመንግሥት አካል ነን የሚሉ አረመኔዎች ናቸው። አረመኔው ቤተ ክህነትም በዝምታና በማድበስበስ እያበረታታ ያለው ይህን ጨካኝ መንግሥት ነው። ይህ ዘመን በኢትዮጵያ ላለን ኦርቶዶክሳውያን የሰማዕትነት ዘመን ነው። ከየአቅጣቸው ወይ በዘር ወይም በፖለቲካ ወይም በአክራሪ ጽንፈኛ ኃይል የምንገደልበት ዘመን ነው። ስለዚህ ለራሳችን ኹላችንም አንድ ኾነን መፍትሔ ለማበጀት ብናስብ መልካም ነው። ይህን ዘመን የምንሻገርበትን መንገድ እስካልቀየስን ድረስ በልቅሶና በይሉኝታ፣ ወይም በልመናና በፍርሓት የምናመጣው ለውጥ አይኖርም። ይህን ልብ ማለት ይገባል። ሌላው ደግሞ እባካችሁ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ቢያንስ እንደዚህ ዐይነቱ ጊዜ ወደ ንስሐ እንድንመለስ ከዳንኪራ እንድንላቀቅ፣ እግዚአብሔርን በዕለት ዕለት ሕይወታችን እያሳዘነው መኾኑን ወደ መረዳት ልንመጣ ይገባናል። እንዴት በዚህ ዘመን ከኦርቶዶክሳዊ አኗኗር ውጭ ኾነን፣ በስካር፣ በጭፈራ፣ በግብረ ዝሙት፣ በኢክርስቲያናዊ አኗኗር ተጠምደን እንገኛለን? የሃይማኖታችንስ ነገር እንዴት ከጥልቅ ልቡናችን አልሰማ አለን? አኹን እንግዲህ እያንዳንዳችን በአንብዓ ንስሓ ኾነን ወደ አምላካችን ልንመለስ ይገባናል።

  • 2 июн.1 402

    https://youtu.be/lTvZTatSA2U?si=s7a-rZUKxUiAeY-g

  • 2 июн.2 33718

    የዮሴፍን ትጋት እና ለማንኛውም ክፉ ነገር በወጣትነቱ አልገዛ ማለቱን አባ ዳውድ ላሜ ሲገልጹ፦ "...በእውነት ያቺ ጊዜ በዚያ ዕድሜ ላይ (19 ወይም 20) ላለ ወጣት እጅግ ፈታኝ ሰዓት ነበረች። ነገር ግን በጥበብና በክብር ጊዜዋን ተቆጣጠራት። ... ከምንም አንጻር ቢታይ ሁኔታዎቹ ለመፈጸም ምቹ በኾኑበት ኀጢአቱም በቀረበበት ጊዜ ለመፈጸም እጅግ ጋባዥ ነበርና። የዮሴፍ ታሪክ የንጽሕናን ሕይወት ለመጠበቅ ለሚሹ ወጣቶች የሚያነሣሣ ነው። በወጣትነት ለፀፀት የሚያበቁ ነገሮችን ከመፈጸም በፊት ሁለቴ ማሰብ የሚያስቸግር ነውና። ወደ ኀጢአት እንድንገባ በምንገፋፋ ጊዜ የዮሴፍን ጥበብና ራስን መግዛት እኛም ለመያዝ መጣር ይገባናል። እጅግ በአስፈሪ ጊዜ ውስጥ እየኖረ የነበረ ቢኾንም በእምነቱ ጽናት ግን የተጠበቀ ነበር። ... ዮሴፍ የዚህችን ሴት ፈቃደኝነት ታማኝ ያለመኾን ባየ ጊዜ ልብሱን ትቶላት ሸሽቷል። ... ዮሴፍ ይሄን ኀጢአት ለመሥራት ብዙ ምክንያት ነበረው፡ እግዚአብሔር በዚህ ጭንቅ የመከራ ሕይወት ውስጥ ፍቅርና ረድኤት ባጣበት ኹኔታ ውስጥ እንደ ተወውም ተናግሮ ሊከራከር፣ ወንድሞቹ እንደ ተውት፣ አባቱ እንደ ሞተ ባሰበበት ባመነበት ኹኔታ ውስጥ መኾኑን፣ በከነአን ቀርቶ ቢኾን አግብቶ ቀላልና የተለመደ ሕይወትን በንጽሕና ይኖር እንደ ነበር አስቦ ምክንያት ሊዘረዝር ይችል ነበር። ነገር ግን ዮሴፍ ንጹሕ ልብ የነበረው ስለ ነበር ይሄንን ኀጢአት ተቃወመ።" በማለት ዘርዘር አድርገው ያስረዳሉ። (ኤራቅሊስ ዘተዋሕዶ (ተርጓሚ)፣ በዮሴፍ ሕይወት መመሰጥ፣ 2008 ዓ.ም፣ ገጽ 18-19)። ከላይ በተዘረዘሩት ማብራሪያዎች ውስጥ የዮሴፍን ታላቅነትና የግብጻዊቷን ሴት ውርደት በግልጽ እንረዳለን። ፍቅር በስሜታዊነት የሚያዝ ነገር አይደለም። በፍቅር ውስጥ ያለ ሰው የሚመራው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ለሰዎች በምንም ምክንያት ክፉን አያስብም። ፍቅር ከእነዚህ ክፉ ሐሳቦች በአጠቃላይ የምታላቅቅ ረቂቅ ኀይል ናትና። ኾኖም ስሜታዊ ሰው ስሜቱን መቆጣጠር አይችልም፤ አፈቅረዋለው የሚለውንም አካል በእርሱ ስሜት ብቻ እንዲመራለት ይፈልጋል፤ ይህ የማይኾን ከኾነ አፈቅረዋለው ያለውን አካል ያጠቃዋል፥ ልክ የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍ እንዲታሰር እንዳደረገችው ማለት ነው። በዚህ ዘመን በስሜታቸው መሠረት ላይ ብቻ የቆሙ አፍቃሪ ነን ባዮች የወደዷቸውን አካላት አደጋ ሲያደርሱባቸው ወይም እነርሱ የፈለጉት ለማግኘት ብቻ ሲሉ ሌሎችን ሲገድሉ ማየት የተለመደ እየኾነ መጥቷል። አሲድ መድፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ በመርዝ መግደልና የመሳሰሉት አስነዋሪ ድርጊቶች እየተተገበሩ ያሉት በስሜታዊ አፍቃሪዎች ምክንያት ነው። ስሜት ላይ ብቻ የተመሠረተውን ፍቅር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ "በአንድ ወቅት ፍቅርን እና ከፍተኛ ጉጉትን እንድለያቸው ተጠይቄ እንደ ነበር አስታውሳለሁ። እኔም ስመልስ "ፍቅር ሁል ጊዜ መስጠትን ይፈልጋል ምኞት ደግሞ ሁል ጊዜ መውሰድን ይፈልጋል። ፍላጎት ሁል ጊዜ መውሰድን መመኘቱን የራስ ወዳድነት መለያ ነው። ምንም እንኳ ፍቅር ቢመስልም ለሌላው ወገን ግን ጥፋት ነው። ለራሱ ሲል ሌላውን ወገን ይከለክላል። ራሱንም ከሌሎች ይከለክላል። ይህ ምናልባትም አንዳንድ ጊዜ ወደ አጥፊ ቀናተኛነት ሊለወጥ ይችላል።" በማለት ያስረዳሉ። (ቀሲስ ተስፋ እንዳለ እና ዲያቆን ማለደ ዋስይሁን (ተርጓሚያን)፣ ዐሥሩ መንፈሳዊ ግንዛቤዎች፣ 2008 ዓ.ም፣ ገጽ 20)። ስለዚህ ስሜታዊ ፍቅር የራስን ስሜት ለማርካት ብቻ የሚፈልግ እና የሌሎችን ፍላጎት ከግምት ውስጥ የማያስገባ ነው። ለዚህም ነው በእኛ ትርጓሜ ይህቺ ግብጻዊት ሴት "ብእሲተ ጲጥፋራ የኀጢአት፣ ዮሴፍ የንጽሕና፣ ወረሰዮ አምሳለ ለንጽሕ (የንጽሕና አምሳያ አደረገው) እንዲል አንድም ብእሲተ ጲጥፋራ የዚህ ዓለም፣ ዮሴፍ የመናንያን አምሳል ነው፣ ብእሲተ ጲጥፋራ እይዝኅ እይዝኅ ስትለው ዮሴፍ ነጥቋት ጥሏት ወጥቶ እንደ ሄደ፣ ይህቺም ዓለም በከብት፣ በንብረት፣ በሹመት፣ በሽልማት፣ በልጅ፣ በቤት፣ በሚስት፣ ሳታባብላቸው መናንያን ጥለዋት የመሔዳቸው ምሳሌ።" በማለት የሚገልጸው። (ትንሣኤ ማተሚያ ድርጅት፣ ትርጓሚ ኦሪት ዘፍጥረት ወኦሪት ዘፀአት፣ 1999 ዓ.ም፣ ገጽ 255)። እንግዲህ የጲጥፋራ ሚስት በተሳሳተ ፍቅር ውስጥ በመኾኗ የኀጢአትና የዚህ ዓለም ምሳሌ ኾና ቀርባለች። ፍቅር በስሜት መሠረት ላይ ብቻ ሲታነጽ የሚኾነው እንዲህ ነው። ሲዛርየስ (Fr. Ceasarius) "እኔ እንደማምነው እርሷ ራሷንም ኾነ ዮሴፍን አትወድም። ዮሴፍን ብትወደው ኖሮ እንዴት እንዲጠፋ ትፈልጋለች? ራሷንስ ብትወድ ኖሮ እንዴት ራሷን ታዋርዳለች? እርሷ በፍቅር ውስጥ አልነበረችም፤ በፍትወት በተመረዘ እሳት እየተቃጠለች ነበር እንጂ። እርሷ በእውነት ነበልባል እያንጸባረቀች አልነበረችም።" በማለት የጲጥፋራ ሚስት የነበረችበትን ውድቀት ይጠቁመናል። (Fr. Ceasarius, Sermon 98፡1)። እንግዲህ ይህ ሁሉ የስሜታዊነት መዳረሻ ነው። በስሜት ውስጥ ብቻ የሚጓዝ ሰው ከማንም በላይ ቀድሞ ራሱን ነው በእጅጉ የሚጎዳው። እንዲህ ዓይነት ሰዎች ቢመክሯቸው አይሰሙም፡ የሚሠሩትን ሁሉ የሚሠሩት በስሜታቸው ስለ ኾነ ራሳቸውን ብቻ ትክክል እንደ ኾኑ አድርገው ያስባሉ። ፍቅር በእንዲህ ዓይነት መርዛማ መንገድ አይቀመስም። ይህቺ ሴት እንኳን ዮሴፍን ልታፈቅር ራሷን ራሱ የማትወድ ማለትም ለራሷ የሚጠቅማትን መለየት ያቃታት ደካማ ሴት ናት። የስሜታውያን ችግር በዋናነት ይህ ነው።

ዮሐንስ ጌታቸው — tgindex