tgindex
Dn Abel Kassahun Mekuria

Dn Abel Kassahun Mekuria

Статистика

ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው። ይወዳጁን ለፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL ለyoutube https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_ ለInstagram https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
18 522
−7 за 3 дн.
Сутки
−1
−0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 894
19 постов
Вовлечённость
37,2%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
6
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
2 106
1/48двое суток
2 413
1/72трое суток
2 603

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12 авг.2 37521426

    ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ግን ወንድሞቻችን ላይ በመጨከን ስንት ጊዜ በክርስቶስ የፍርዱ ዙፋን ላይ ተቀመጥን? የሰውን ድካም ሳንረዳ ፈጥነን በመፍረድ ስንት ጊዜ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቦታ አስገባን? እስኪ ዮሴፍን እናስበው፡፡ ወደ ግብጽ ባሪያ አድርገው በግፍ የሸጡት ወንድሞቹ ከአባታቸው ሞት በኋላ እርሱ ወደ ተሾመበት ግብጽ መምጣት በፈለጉ ጊዜ፣ የክፋታችንን ብድራት ያስከፍለናል ብለው ስለፈሩ ‹‹በደላችንን ተውልን›› ሲሉ መልእክተኛ ልከውበት ነበር፡፡ የዋሁ ዮሴፍም ይህንን ሲሰማ እያለቀሰ እንዲህ አላቸው ‹‹አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?››፤ አይደለም ሳታውቀው ዐውቀኸው እንኳን በበደለህ ወገንህ ላይ ለመፍረድ ልብህ በከጀለህ ጊዜ ለራስህ የዮሴፍን ጥያቄ ጠይቀው፡፡ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?›› (ዘፍ 50፡19) ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelmekuria2@gmail.com

  • 9 авг.3 84813626

    “የእግዚአብሔር ጆሮዎች ለመስማት ድምፅን የሚጠባበቁ ይመስላቸዋልን? እንዲህስ ካልሆነ ታዲያ የእነርሱ ጮኾ መጸለይ ጎረቤቶቻቸውን የሚያበሳጭ ነገር ከመሆን በቀር ሌላ ምን ጥቅም አለው?” ሊቁ ጠርጠሉስ፣ በእንተ ጸሎት https://t.me/Dnabel

  • 8 авг.4 34119316

    የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናት ፍሬ በትውልድ እንግሊዛዊው እና ለብዙ ዘመናት የፕሮቴስታንቲዝም አንዱ ቅርንጫፍ በሆነው የአንግሊካን እምነት ውስጥ የቆየው ዕውቁ ሊቅ ሰባስትያን ብሮክ ቅዳሜ ግንቦት 18 (May 25)፣ 2024 ዓ. እ.የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን በቅብዓ ሜሮን ከብሮ ዋለ። ሰባስትያን በኦርቶዶክሱ ዓለም በሶርያ የሚገኙ ጥንታዊ የሆኑ የነ ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናትን ከጥልቅ ሐተታዎች ጋር በመተርጎም እና የሶርያን ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት በማጥናት በሰፊው ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ የሠራቸው እና ያሳተማቸው የጥናት እንዲሁም ትርጉም መጻሕፍት ዝርዝር ብቻ ወደ ሠላሳ ገጽ ይሆናሉ። የሶርያም ቤተ ክርስቲያንም ለዚህ ድካሙ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሜዳልያ (Medal of St. Ephrem the Syrian) የተባለውን በክብር አበርክታለታለች። እነዚያን ወርቅ የሆኑ አጥንት ድረስ ዘልቀው የሚወጉ የማር ኤፍሬምን ድርሳናት ከውጭ (በሃይማኖት) ሆኖ መተርጎሙ ሁሌ ያሳዝነኝ ነበር። ታምሞ ግን የሚድንበትን መድኃኒት ተሸክሞ እንደሚቸገር ምስኪን ሰው አድርጌም አስበው ነበር። ድርሳናቱ መቼ ነው ወደሚድንበት መርከብ እየመሩ የሚያስገቡት ብዬ ብዙ ጊዜ እጠይቅ ነበር። ያለፈው ቅዳሜ ግን ይህን ኀዘን የሚሽር የምሥራች ሰማሁ። ለካስ ቅዱሱ የቀጠረለት ቀን ነበር?! ይኸው የኤፍሬም ቀለም የበላውን (ያቃጠለውን) ምሁር ከኦርቶዶክሳዊው ካህን ስር በትሕትና በርከክ ብሎ አየሁት። ይህ መመለስ የቅዱሱ ምልጃ እና በቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ያለቀሱ የብዙ የዋሃን ምእመናን እንባ ውጤት ነው። የአበው ድርሳን አሁንም በሥራ ላይ ነው!!! ዲያቆን አቤል ካሣሁን selam@dnabel.com

  • 8 авг.3 590387

    “ጉባኤ ኒቅያ” የመጨረሻ ክፍል https://youtu.be/pQOrLH_Jch0?si=EoDaeY0tNO0yHUZY

  • 7 авг.4 69617737

    +++ "እግዚአብሔር የጣላት እሳት" +++ በደብተራ ኦሪት በመሠዊያው ላይ የሚነደውና መሥዋዕቱ ይቃጠልበት የነበረው እሳት ከሰማይ የወረደ ነበር። ይህም እሳት ዘወትር እንዳይጠፋ የአሮን ልጆች (ካህናቱ) ማለዳ ማለዳ እንጨት እየጨመሩ እንዲያቀጣጥሉና እንዲያነዱት እግዚአብሔር አዝዟቸዋል።(ዘሌዋ 6፥12) ከማዕጠንት ጀምሮ እስከ እንስሳት በድንኳኑ የሚቀርቡ ማናቸውም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሁሉ የሚበሉት ከሰማይ በወረደው በዚህ "የእግዚአብሔር እሳት" ነው። ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እንዲህ አደረጉ። ለእግዚአብሔር የእጣን መሥዋዕት ማቅረብ ፈልገው ለየራሳው ጥናውን (ማዕጠንት) አነሡ። ነገር ግን በጥናው ውስጥ ያደረጉት ከሰማይ የወረደውን "የእግዚአብሔር እሳት" ሳይሆን፣ ከመንደር ጭረው ያመጡትን ወይም ራሳቸው ያቀጣጠሉትን "ሌላ እሳት" ነበር። በዚህም እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት ስላቀረቡ አምላክ ተቆጣ። በፊቱም እሳት ወጥቶ እንዲበላቸው አደረገ። እነርሱም ወዲያው ሞቱ።(ዘሌ 10፥1-3) ሊቀ ካህናቱ አሮንን እየተከተሉ እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ልጆቹ ገና አገልግሎታቸውን በቅጡ ሳይጀምሩ ተቀሰፋ። ለመሆኑ እነዚህ ሁለት የኦሪት ወጣት ካህናት የተቀጡበት "የሌላ እሳት" ታሪክ ለሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ምን ምሳሌ ይኖረው ይሆን? እግዚአብሔር በኦሪቱ ድንኳን እሳትን እንዳወረደ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ሲወርድ ይዞልን የመጣው እሳት አለ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር፤ ወምንተ እፈቅድ ዘእንበለ አንድዶታ" - "በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?" እንዳለን።(ሉቃ 12፥49) ይህ መድኃኒታችን በምድር ላይ የጣለው እሳት ምንድር ነው? አገልግሎቱስ እንዴት ነው? ጌታችን በምድር የጣላት እሳት "ወንጌል" ትባላለች። ሰው ሰውነቱን ንጹሕና የተቀደሰ ሕያውም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብባት "የእግዚአብሔር እሳት" ወንጌል ነች። ይህች ወንጌል ጌታ አንድ ጊዜ በምድር የጣላት፣ እኛ ደግሞ ለዘወትር እንዳትጠፉ የምናቀጣጥላትና የምናነዳት እሳት ነች። የማቀጣጠያው እንጨቶችም ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እና ማንበብ ናቸው። ያለ ወንጌል እሳትነት ምንም መሥዋዕት እንድናቀርብ አልተፈቀደልንም። ነገር ግን እንደ አሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ ከመንደር ቆስቁሰን ወይም ራሳችን አቀጣጥለን የምናመጣቸው "ሌላ እሳት" የተባሉ ከንቱ ፍልስፍናዎችና እንግዳ ትምህርቶች የእግዚአብሔርን ቁጣ ይቀሰቅሱብናል። ዳግመኛም እሳት የተባለው በጥምቀት ጊዜ በሁላችንም ላይ የወረደው ጸጋ እግዚአብሔር ነው። ይህም ጸጋ ለመዳናችን ዓይነተኛ ሚና አለው። ይሁን እንጂ ልክ በደብተራ ኦሪት እንደ ወረደው እሳት ካልተንከባከብነው እና ካላቀጣጠልነው ሊዳፈን እና የሌለ ሊመስል ይችላል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ "እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው...በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ" በማለት የሚመክረው።(2ኛ ጢሞ 1፥6) እግዚአብሔር ለሰጠን ጸጋ ማቀጣጠያዎቹ ደግሞ ጾም፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ትሩፋት ሁሉ ናቸው። እርሱ የሰጠህን የጸጋ እሳት ከማቀጣጠል ይልቅ "ሌላ እሳት" ላምጣ ያልህ ቀን ግን ታላቅ ጥፋት ያገኝሃል። ዲያቆን አቤል ካሳሁን abelzebahiran@gmail.com

  • 5 авг.4 5505326

    ለሚያገለግል ሁሉ! https://youtu.be/h9KbjezF8Wc?si=QwL777PsYQfN0HKk

  • 1 авг.5 6794612

    https://youtu.be/vWsA5Jmg-2E?si=AVmV9lDdaUJpU_O2

  • 30 июл.7 005919

    የትውልዱን ሕሊና በዕውቀትና በጥበብ የሚያንጹት የተወዳጁ መምህር መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርቶች በ"ሠሌዳ ሚዲያ" መድረክ በኩል ለአድማጮችና ለተመልካቾች ማቅረብ ሊጀምሩ ነው። ሠሌዳ ሚዲያ በመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የተመሠረተ የዲጂታል ሚዲያ መድረክ ሲሆን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር እውነትን፣ ጥበብንና ኦርቶዶክሳዊ ዕሴቶችን የሚያለመልምና ትውልድን የሚያጎለብት የዕውቀት ምንጭ እንዲሆን ታስቦ ሥራ ጀምሯል። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕያው ቃሉ "ምን እንድትሰሙ፥ ተጠበቁ"(ማርቆስ 4፥24)  እንዳለው፥ ሠሌዳ ሚዲያ አድማጭና ተመልካቾች የሚያዩትንም ሆነ የሚሰሙትን በመጠኑና በጥንቃቄ እንዲመርጡ ለሚያሳስበው የዘመኑ የነፍስ ጥሪ ምላሽ የሚሆኑ የጠሩ እና የተመረጡ ይዘቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡ በሠሌዳ ሚዲያ፡- Ø  መንፈሳዊ ትምህርቶችና ስብከቶች፣ Ø  የማኅበረሰብ ጉዳዮች ዳሰሳዎችና ትንተናዎች፣ Ø  የባህልና የዕሴት አንጸባራቂ አንድምታዎች፣ Ø  ከምሁራን፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ ጥልቅ ውይይቶችና ቆይታዎች Ø  ሌሎችም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ርእሰ ጉዳዮች በሚዛናዊነትና በኃላፊነት ስሜት ይቀርባሉ፦ ይህን የዕውቀትና የጥበብ ማዕድ ለመካፈል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይወዳጁን፤ ለብዙኃኑ ተደራሽ እንዲሆንም አጋር በመሆን ሰብስክራይብና ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! YouTube:ሠሌዳ ሚዲያ TikTok: @seledamedia Instagram: seledamedia Facebook: Seleda Media ሠሌዳ ሚዲያ - ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። ### Youtube https://www.youtube.com/@seledamedia.megabehadiseshetu Tiktok http://www.tiktok.com/@seledamedia Instagram https://www.instagram.com/seledamedia/ Facebook https://web.facebook.com/profile.php?id=61591554360962

  • 29 июл.6 83120936

    +++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++ ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ። ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከአንድ ሳምንት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ። አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ። የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!! (*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።) ዲያቆን አቤል ካሣሁን ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም. (የብፁዕነታቸው የዕረፍት ቀን) ዝዋይ (ብፁዕነታቸው ብዙ ሥራ በሠሩበት ክፍለ አገር ሆኜ)

  • 26 июл.6 70833227

    በእኛ ላይ ሊደርሱ ካሉ ክፉ አደጋዎች የዳንባቸውን ጊዜያቶች እስኪ እናስተውል። ከእነዚያ አስከፊ ሁኔታዎች ተአምር በሚመስል መንገድ የተረፍንባቸውንና ‹ለጥቂት እኮ ነው…› እያልን የምናስታውሳቸውን ሰዓታት እስኪ ለአፍታ ደግመን እናስባቸው። በእነዚያ የጭንቅ ጊዜያቶች ሁሉ የታደገንን የጠባቂ መልአካችንን የተዘረጋች ክንድ እናያለን፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ ፖሊካርፐስ በጠባቂ መልአኩ አማካኝነት እንዴት ከሞት በተአምር ሊተርፍ እንደ ቻለ ይናገራል፡፡ ቅዱሱ አብሮት በአገልግሎት ከሚረዳው ዲያቆን ጋር በጉዞ ሳሉ ቀኑ ስለመሸባቸው መንገድ ዳር ካለ አንድ ትንሽ ቤት ገብተው ይተኛሉ፡፡ በእኩለ ሌሊትም የፖሊካርፐስ ጠባቂ መልአክ በሕልሙ ተገልጦ ‹ፖሊካርፐስ ሆይ ሊፈርስ ነውና ፈጥነህ ይህንን ቤት ለቅቀህ ውጣ› እያለ ሶስት ጊዜ አስጠነቀቀው፡፡ ፖሊካርፐስ ራእዩን እንዳየ ያንን ቤት ለቆ በፍጥነት ወጣ፡፡ ወዲያውም ቤቱን እያየው በፊቱ ፈራርሶ ወደቀ፡፡ እርሱም ሊመጣበት ከነበረው ሞት በጠባቂ መልአኩ አማካኝነት ዳነ፡፡ እንኳን ለጠባቂያችን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን! መልካም በዓል ይሁንልን! ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelzebahiran@gmail.com

  • 24 июл.7 5259531

    የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እና ሥርዓት እንዴት አሁን ያለበትን ዓይነት ቅርጽ ሊይዝ ቻለ? በዚህ ሂደት ውስጥስ በቤተ ክርስቲያን የተካሄዱ ዓለማቀፉዊ ጉባኤያት (Ecumenical Councils) ድርሻቸው ምን ነበር? ይህን አጠር ባለ መንገድ ለመረዳት “ጉባኤ ኒቅያ” የተሰኘውን ሦስት ክፍሎች ያሉትን ተከታታይ ትምህርት ከማስታወሻ ጋር እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ። https://youtu.be/Epd_EC5diLI?si=JlViJ7yVxsPkpyHA

  • 20 июл.8 70719238

    https://t.me/Dnabel

  • 18 июл.8 7725

    видео или голосовое, без подписи

  • 18 июл.9 4774345

    የልደት ቀኔን አስመልክቶ በጎ ምኞታችሁን እና ምርቃቶቻችሁን እንደ ወንዝ ላፈሰሳችሁልኝ ሁሉ፣ እግዚአብሔር እንደ ወንዝ የሚፈስ ሰላሙን ይስጣችሁ። አምላከ ጳውሎስ ያክብርልኝ!

  • 14 июл.11,4 тыс30751

    ፀሐይ ናላ በምታዞርበት እና ሁሉም ለማረፍ ወደ አልጋው በሚሽቀዳደምበት በቀትር ሰዓት አብርሃም ግን በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ እንግዳ በተስፋ ይጠባበቅ ነበር።(ዘፍ 18) በዚህ የቃጠሎ ጊዜ (ስድስት ሰዓት) መንገድ ላይ የሚገኝ ሰው ወይ ምንም ማረፊያ የሌለው ምስኪን ነው፣ አለዚያ ደግሞ እንደዚያች ሳምራዊት ሴት ከሰው የተገለለ ብቸኛ ነው።(ዮሐ 4፥6) አብርሃም ድንኳኑን ያሰናዳው ያማረ ለለበሱ፣ ብድር ለሚመልሱ፣ በመልክም በገንዘብም ዓይን ውስጥ ለሚገቡ ሰዎች ሳይሆን፣ ሰው ለሸሻቸው መጠጊያ ለሌላቸው እና በፀሐይ ንዳድ እየተንገበገቡ ማረፊያ ፈልገው ለሚዞሩ አስታዋሽ አልባ ምስኪኖች ነበር። አብርሃም በደጁ የሚያልፉ ምስኪን እንግዶቹን “ና እስኪ” ብሎ በማቃለል ቃል አይጠራቸውም። እየሮጠ ወደ እነርሱ ሄዶ “ጌቶች (እመቤት) እባካችሁ ወደ ቤቴ ግቡልኝ” ብሎ በትሕትና ይለምናቸዋል እንጂ። ይህንን ግን በምን አወቅን? በሦስት ሰዎች ተመስለው ወደ ቤቱ ቅድስት ሥላሴ በመጡ ጊዜ አብርሃም እነርሱን ያስተናገደበትን መንገድ አይተን ተረዳን። አብርሃም በዚህች ቀን ተዘጋጅቶ ይጠብቅ የነበረው ሰውን እንጂ እግዚአብሔርን አልነበረም። እግዚአብሔር ግን አብርሃም ለምስኪናኑ ያሳይ የነበረው ቸርነቱን አይቶ በቤቱ ሊስተናገድ ወደደ። አብርሃም ለድሆች ሲል በከፈተው በር በኩል በመካንነት ምክንያት የተዘጋውን የሣራን ማኅፀን የሚከፍት የሠራዊት ጌታ ገባለት። የአንተን የብዙ ዓመታት ጥያቄ ለመመለስ እግዚአብሔር ወደ ሕይወትህ የሚገባው፣ ለሌሎች ሰዎች ብለህ በከፈትኸው የመልካምነት እና የቅንነት በር በኩል ነው። ዲያቆን አቤል ካሳሁን ሐምሌ ቅድስት ሥላሴ -2017 ዓ.ም. https://t.me/Dnabel እንኳን አደረሳችሁ!

  • 12 июл.10,2 тыс24638

    “ቅዱሱ በሰይፍ ወደሚቀላበት አደባባይ ከደረሰ በኋላ የሞት ጥላ ዙሪያውን ቢከበውም ‹‹የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል›› ብሎ የተነገረውን የጌታን ቃል አምኖ የልብሱን ኮሌታ ከፍ በማድረግ አንገቱን ለሰያፊው አመቻቸ፡፡(ዮሐ 11:25) ወታደሩም በያዘው ሰይፍ የጳውሎስን አንገት ከሰውነቱ ለየው፡፡ በቃሉ ትምህርት ምድርን ወደ ገነት የቀየረው፣ የብዙዎችን ስብራት የጠገነው፣ ሙት ያስነሣው፣ ሽባ የተረተረው የጳውሎስ አፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ታተመ፡፡ ይህ እንኳን ሰውን ሰማይና ምድርንም የሚያስደነግጥ ክስተት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሊቁ በመልክእ ነገሩን ሲያደንቅ ‹‹ጳውልስ ወጴጥሮስ አመ አፉክሙ ተኀትመ፣ ዘበሰማያት ወዘበምድር እስከ ንፍቀ ሰዓት አርመመ ››/‹‹ጳውሎስ እና ጴጥሮስ ሆይ፣ አንደበታችሁ በተዘጋ ጊዜ፤ በሰማይም በምድርም እስከ ግማሽ ሰዓት ዝምታ ሆነ ›› የሚለው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕትነትን በሚቀበልበት ጊዜ በቦታው ላይ የነበሩ የዓይን ምስክሮች እንዳሉት ሞቱም በተአምራት የተከበበ ነበር፡፡ እነዚህም ሰዎች በሰይፍ ከተቆረጠው ከቅዱሱ አንገት ደም እና ውኃ ፈልቋል ያሉ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ራሱ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት እንደ ነጠረችና በእነዚያም ቦታዎች ላይ ውኃ (ጠበል) መፍለቁን ተናግረዋል፡፡” ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ፡ 410 ቅዱሱ ሰማዕት ጳውሎስ ሆይ፣ እንደ ኤፌሶን ሽማግሎች ስለ ክርስቶስ የተሰየፈች አንገትህን አንድ ጊዜ አቅፈን እንስመው ዘንድ ብታድለን ምን ነበር?! #ኃምሌ 5 ሮም አደባባይ ላይ!

  • Dn Abel Kassahun Mekuria pinned a video

  • 11 июл.8 79721220

    #ጉዞ ወደ ሮም አደባባይ!

  • 11 июл.9 40414021

    በሁሉ ጎዳና ምሳሌ የሚሆን፣ በተለይ ለዚህኛው ትውልድ ቅርብ የሆነ እና ወድቆ በመነሣት ውስጥ ያለውን ተስፋ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አንድ ቅዱስ ወደ ሕይወታችሁ የምትጨምሩበትን መጽሐፍ ልጋብዛችሁ? ይኸው “ራእየ ኒፎን” በቀሲስ ታምራት ውቤ። ቀሲስ ታምራ ውቤ ይህን ድንቅ መጽሐፍ በመተርጎማቸው፣ ቅድስና ርቆ እንደ ተሰቀለ ውብ ፍሬ እያጓጓ የማይደረስበት ለሚመስለን ለዛሬ ክርስቲያኖች፣ ዛፉን ዘንበል አድርጎ ፍሬውን የማቅረብ ያህል ነው ድርሻቸውን ተወጥተዋል። ደግሞ የአተረጓጎም ለዛው፣ እና የቋንቋው ውበት ደግሞ አስደናቂ ነው። አንዴ ካነሡት አስቀምጡኝ አይልም። የነገ ሰንበት ሐምሌ 5 - 8:00 ሰዓት ቀጠሯችሁ “ከቅዱስ ኒፎን” ጋር ካልሆነ በቀር ሌላ ከማንም ጋር አይሁን። ቀሲስ ታምራት ውቤ ጥሩ ነፍስ የሚያጠግብ ድግስ ደግሰው እየጠሩን ነው። ብንገኝ ብዙ እናተርፋለን። ቦታ: ቦሌ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ትልቁ አዳራሽ

  • 9 июл.7 08321412

    #ጉዞ ወደ ሮም አደባባይ!

Dn Abel Kassahun Mekuria — tgindex