tgindex
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

Статистика

+251915955656 @Binigirmachew16

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
27
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
88 229
−262 за 2 дн.
Сутки
−108
−0,12%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 632
27 постов
Вовлечённость
7,5%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 27
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
2 347
1/48двое суток
2 689
1/72трое суток
2 900

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.1 798173

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.2 6466520

    ሶፊ“ከእኔ ተማሩ፤ ትዳራችሁን በጊዜያዊ ደስታ አትለውጡ” “በትዳር ውስጥ ላላችሁ ሴቶች ሁሉ አንድ መልዕክት አለኝ። የእኔ ታሪክ ለእናንተ ትምህርት እንዲሆን ላካፍላችሁ” ትላለች ሶፊያ። “ሶፊያ እባላለሁ። 39 ዓመቴ ነው። ከ13 ዓመታት የትዳር ሕይወት በኋላ የተፋታች፣ የሦስት ልጆች እናት ነኝ። ሁለት ወንድ ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ አሉኝ። በ23 ዓመቴ ነበር ያገባሁት። በዚያን ጊዜ ወጣት ነበርኩ፣ የትዳር ሕይወትንም በበቂ ሁኔታ አልተረዳሁም። ባለቤቴ አሳቢ፣ ቤተሰቡን የሚወድና ኃላፊነቱን የሚወጣ ሰው ነበር። እኔ ግን በወጣትነት እና በልምድ ማነስ ምክንያት ትዳር ብስለትን፣ ትዕግሥትንና መተማመንን እንደሚፈልግ በትክክል አልተረዳሁም። 31 ዓመቴ ላይ የሦስት ልጆች እናት ሆኜ ነበር። ትኩረቴ ቤተሰቤን መንከባከብ፣ ልጆቼን ማሳደግና ቤቱን ማስተዳደር ላይ ነበር። ልጆቼ እያደጉ ሲሄዱ ግን ከቤት ወጥቼ ለመንቀሳቀስና ለራሴ ጊዜ ለመስጠት ትንሽ ነፃነት አገኘሁ። ከዚያም አንድ ምሽት ገበያ ወጥቼ ሳለሁ ሕይወቴን የለወጠ ነገር ተፈጠረ። አንድ ዕቃ ለማንሳት መደርደሪያ አጠገብ ቆሜ ሳለሁ ከኋላዬ አንድ ሰው እንደነካኝ ተሰማኝ። ዞር ስል ፈገግ ያለ አንድ ወንድ ተመለከትኩ። በትህትና ሰላምታ ሰጠኝ፣ ጥቂትም ተጫወትን። የሚያምር፣ በራሱ የሚተማመንና ንግግር የሚችል ሰው ነበር። ግብይቱን እንደጨረስኩ ሂሳቤን እንድከፍል ረዳኝ፣ እስከ መኪናዬም ሸኘኝ። ስልክ ቁጥራችንንም ተለዋወጥን። ከእሱ ከተለየሁ በኋላ ግን ስለእሱ ማሰብ አልቻልኩም። ያሳየኝ ትኩረትና ደግነት በትዳሬ ውስጥ የጎደለኝ ነገር መስሎ ተሰማኝ። ከሁለት ቀን በኋላ ደውሎልኝ ቡና ለመጠጣት እንድንገናኝ ጠየቀኝ። ተስማማሁ። ተገናኝተን ለሰዓታት ተነጋገርን። እኔ ስናገር በትኩረት ያዳምጠኝ ነበር። በእያንዳንዱ ንግግሩ ውስጥ አስተዋይነት ይታይበት ነበር። ክብርና ትኩረትም ያሳየኝ ነበር። እኔም በዚያ ወቅት መስማት የምፈልገውን ሁሉ ከእሱ እያገኘሁ መሰለኝ። በውይይታችን መጨረሻ “ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል፤ ሌላ ቀን ብቻችንን ሆነን ጨዋታችንን እንቀጥል” አለኝ። እኔም አልተቃወምኩም። ሌላ ቀን ተገናኘን። ወደ አንድ የተዋበ ሆቴል ይዞኝ ሄደ። በዚያ ቀን የሚከሰተውን ነገር እያወቅኩም ሆነ ሳላውቅ በስሜት ተከተልኩት። ክፍል አስያዝን፤ እናም ያ ምሽት የሕይወቴ መለወጫ ሆነ። በመካከላችን የተፈጠረው ቅርርብ እንደገና የምኖር ሰው እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ። ግን ያኔ ያላስተዋልኩት ነገር ነበር። ያ የአጭር ጊዜ ደስታ ለዓመታት የገነባሁትን ቤተሰብ ሊያሳጣኝ እንደሚችል አላሰብኩም። ወደ ቤት ከተመለስኩ በኋላ ያንን ሰው ከባለቤቴ ጋር ማወዳደር ጀመርኩ። ንግግሩ፣ ትኩረቱ፣ አድናቆቱና እንክብካቤው ሁሉ በዓይኔ ከባለቤቴ የተሻለ መስሎ ታየኝ። ቀስ በቀስ ከባለቤቴ በስሜት መራቅ ጀመርኩ። በቤት ውስጥ ጠብ መፍጠር ጀመርኩ። በመጨረሻም ያገኘሁት ሰው ከባለቤቴ በመለየት አዲስ ሕይወት እንድንጀምር ጠየቀኝ። በዚያ ጊዜ ስሜትና ፍትወት አሳውረውኝ ነበር። እውነታውን በግልጽ ማየት ተስኖኝ ትዳሬን ትቼ ወጣሁ። ዛሬ ከቤቴ ከወጣሁ ሦስት ዓመት ሆኖኛል። እውነቱን ግን አሁን በግልጽ ተረድቻለሁ። ከቤት ውጭ ያገኘሁት ያን ታላቅ ደስታ አላገኘሁም። ባለቤቴን ትቼ የመረጥኩት ሰው ከባለቤቴ በተለየ መልኩ እንደሚኖርልኝ አስቤ ነበር። ግን አብረን መኖር ከጀመርን ከሦስት ወራት በኋላ ያ የመጀመሪያው ደስታ ጠፋ። አምሽቶ መምጣት ጀመረ። ከእኔ ርቆ ሌሎች ሴቶችን ማዝናናት ጀመረ። ስናገረውም ያለፈውን ሕይወቴን እያስታወሰ ያስወቅሰኝ ጀመር። በአንድ ወቅት እንደልቤ እንዲሆንልኝ የምፈልገው ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዋጋ እንደሌለኝ እንዲሰማኝ አደረገኝ። ያኔ ነው የተሳሳትኩትን በግልጽ የተረዳሁት። ቤቴን አጣሁ። ባለቤቴን አጣሁ። የልጆቼን የቤተሰብ ሕይወት አፈረስኩ። ከሁሉም በላይ የአእምሮ ሰላሜን አጣሁ። ዛሬ ለትዳር ውስጥ ላላችሁ ሴቶች አንድ ነገር ብቻ ልንገራችሁ። ትዳራችሁን በጊዜያዊ ደስታ አትለውጡ። በትዳራችሁ ውስጥ የማይመቻችሁ ነገር ካለ በውይይት ፍቱት። የሚጎዳችሁን ነገር በግልጽ ተናገሩ። የጎደለውን ነገር ከሌላ ሰው ለመፈለግ ከመቸኮል ይልቅ መጀመሪያ በቤታችሁ ያለውን ችግር ለመፍታት ሞክሩ። ከሌላ ሰው ያገኛችሁት የሚመስላችሁ ትኩረት፣ ፍቅርና አድናቆት ብዙ ጊዜ በመጀመሪያ የሚታየው የአዲስ ግንኙነት ስሜት ብቻ ሊሆን ይችላል። ከጊዜ በኋላ የሰው እውነተኛ ባህሪ ሊገለጥ ይችላል። እኔ ግን ይህን በልምድ ተማርኩት። አሁን ከባለቤቴ ይቅርታ እንደማገኝ አላውቅም። ነገር ግን የጀመርኩትን ግንኙነት ትቻለሁ፤ ከራሴ ጋርም እርቅ ለመፍጠር ጀምሬያለሁ። የእኔ ታሪክ ለማሳዘን አይደለም። እኔ በቆምኩበት ቦታ ዛሬ ለቆማችሁ ሰዎች ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ነው። ከእኔ ተማሩ። ትዳራችሁን ጠብቁ።ለባለቤታችሁ ዋጋ ስጡ።የሚጎድላችሁን በውይይት ለመፍታት ሞክሩ።ከሁሉም በላይ ደግሞ ልባችሁን ከችኮላ፣ ከስሜታዊ ውሳኔና ከጊዜያዊ ፍላጎት ጠብቁ። አንድ ጊዜ የምትፈጽሙት ስህተት፣ ለዓመታት የገነባችሁትን ሕይወት ሊያፈርስ ይችላል። ማስታወሻ፦ ይህ ታሪክ ከፌስቡክ የተገኘ ሲሆን የቃላት አገላለጹ ተስተካክሎ ቀርቧል። @binigirmachew @binigirmachew @binigirmachew

  • 11 авг.3 016376

    በንግዱ ኪሳራ ያጋጠመው አባት ቤተሰቡን ገደሎ ራሱን አጠፋ ​ይህ በሀገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤንና ጥልቅ ሀዘንን የፈጠረ አሰቃቂ አጋጣሚ ነው። አንድ አባት ሚስቱንና ሶስት ልጆቹን ህይወት ካጠፋ በኋላ፣ በራሱ ላይም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። ​እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ለዚህ አሰቃቂ ድርጊት እንደ ምክንያት የተጠቀሰው ግለሰቡ በንግድ ስራው ላይ የደረሰበት ከፍተኛ የፋይናንስ ኪሳራ ነው። ክስተቱ በግብፅ የተፈጸመ ሲሆን፣ በሥርዓተ ቀብሩ ዕለትም በርካታ ህዝብ ተገኝቶ ጥልቅ ሀዘኑን ገልጿል። ​ይህ አጋጣሚ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ውድቀት የሚያስከትለው አእምሮአዊና ስነ-ልቦናዊ ጫና ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው። ያም ሆኖ የቱንም ያህል ከባድ ፈተና ቢገጥም ህይወትን ማጣት ወይም የሌሎችን ህይወት ማጠፋት በፍጹም መፍትሄ ሊሆን አይችልም።

  • 10 авг.3 46441

    ጥሩ ምክር ነው በተለይ ... https://vt.tiktok.com/ZS9hohtVWgBjg-HjwKM/

  • 4 авг.7 0199220

    የዛሬን ውድ ስጦታ፣ ይህችን ቅጽበት በከንቱ አታባክን! እያንዳንዷን እስትንፋስ፣ እያንዳንዷን የልብ ምት እንደ ውድ ሀብት ቁጠራት። ምክንያቱም የምትባል ነገ ላይኖር፣ ላታገኛት ትችላለህና! የምንወዳቸውን ሰዎች በሞት አጥተን፣ በሀዘን ተውጠን "ነፍስ ይማር" ከማለታችንና እንባችንን ከማፍሰሳችን በፊት፣ ዛሬ ፍቅራችንን እንግለጽላቸው፤ ዛሬ ከልብ እንደምንወዳቸው እንንገራቸው። ዛሬን በሙሉ ልባችን እንኑርበት፤ በደስታ፣ በፍቅር፣ በርህራሄ፣ በይቅርታና በምስጋና እንሙላበት። እያንዳንዷን ቀን እንደ መጨረሻ ቀንህ ቁጠራት፤ ምክንያቱም ምናልባት ልትሆን ትችላለችና። @binigirmachew ጌታ ሆይ፣ እውነትን በፍቅር እንድናገር እርዳኝ።

  • 28 июл.8 9811027

    በትዳር ውስጥ ሁለታችሁም እየተጎዳችሁ ከሆነ፣ ዓላማው መሆን ያለበት "ማን ትክክል ነው?" ሳይሆን "እንዴት ትዳራችንን እናድን?" መሆን አለበት። መልካም ምሽት @binigirmachew ጌታ ሆይ፣ እውነትን በፍቅር እንድናገር እርዳኝ።

  • 28 июл.8 2597256

    እውነታዎች   • ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ...በሰፈርከዉ ማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ   • ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም፡፡ 20 ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ (እነሱም የቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ) 80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80 ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና! የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል   • ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን አትደገፍ   • ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ   • የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደኋላ አይልም   • 98 ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም(2 ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም)፡፡ ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!   • የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም! አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ   • ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላስን ሰዉ ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ   • ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡   • አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ   • ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ፡፡   • ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡   • የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ   • ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት   • ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በኣጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ፡፡   • ህይወት እኩል አይደለችም፡፡በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰዉ አለ...እኩልነት ዉሸት ነዉ፡ ስለዚህ በመኖርህ ብቻ ተደሰት፡፡ @binigirmachew

  • 28 июл.5 58127

    ከዚህ በዋላ ተመልሰናል መልካም ቀን https://vt.tiktok.com/ZS4eouBEu/ ሁሉም የሶሻል ሚዲያ Active ይሆናል ከዛሬ ጀምሮ። ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን @BiniGirmachew

  • 26 июл.6 5839514

    በየዕለቱ ልባችን ከሚደማበት ነገር አንዱ በሰዎች መካከል ልዩነት ሲደረግ ማየት ነው፡፡ አንዱን ማክበር መልካም ቢሆንም ሌላውን መናቅ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ደግሞ ከገረዴ ጋር እኩል በአንድ ወንበር ልቀመጥ እንዴ? ደግሞ ከማንም የድሀ ልጅ ጋር ልዋል እንዴ? የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን የአእምሮ ድሆች ናቸው፡፡ ከገንዘብ ድህነት የአስተሳሰብ ድህነት ይከፋል፡፡ ካጠቡት ሁሉም ንጹሕ፣ ካስተማሩት ሁሉም አዋቂ፣ ከደገፉት ሁሉም ጎበዝ ነው፡፡ እውነተኛ ክብር ከእውነተኛ ፍቅር ይገኛል። @binigirmachew

  • 25 июл.7 0255630

    በሥራ ቦታ ላይ ብቃት የሌለው ሰራተኛ ባህርያት፦ ​1. ስም ማጥፋት እና ሐሜት (Character Assassination) ​2. ስራን ማደናቀፍ (Sabotage) ​3. የሌሎችን ስኬት ማሳነስ (Downplaying Achievements) ​4. የሌሎችን ስራ ለራስ መውሰድ (Taking Credit) ​5. ትናንሽ ስህተቶችን ማጉላት (Micromanaging/Magnifying Errors) ​6. ቡድን መፍጠር እና ማግለል (Creating Cliques & Isolation) ​በአጠቃላይ ሥራ የማይችል ሰው በጎበዝ ሰራተኛ ላይ ሲቀና፣ ትግሉ ከስራ ጥራት ወደ ግለሰብ ጥቃት ይዞራል። ትኩረቱ ራሱን ማሳደግ ላይ ሳይሆን፣ ጎበዙን ሰራተኛ ወደ እሱ ዝቅተኛ ደረጃ ማውረድ ላይ ይሆናል:: በሥራ ብቻ! ብርቱ ሰው ያድረገን!

  • 21 июл.8 318253

    አይነስወር ልጁን ያጋባው አባት ተከታይ ፣ልብ አንጠልጣይ ፣ በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ።  መከታተል ትችላላችሁ በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ላይ https://t.me/+69KPpZzPUQljYjY0 ክፍል 1,2,3 እና 4 ተለቋል

  • 19 июл.8 8438148

    በትዳር ውስጥ ለመፍታት ከባድ የሆኑ ችግሮች በትዳር ውስጥ አንዳንድ ችግሮች በቀላሉ ሊፈቱ ይችላሉ፤ አንዳንዶቹ ግን በጣም ከባድ ሆነው ለመፍታት ጊዜ፣ ጥበብ እና ትዕግስት ይፈልጋሉ። ትዳር ሁለት ሰዎች ብቻ በአንድ ቤት መኖር አይደለም፤ ልብ፣ ሐሳብ፣ ተስፋ እና ህይወት አብሮ መጋራት ነው። ስለዚህ በዚህ ጉዞ ውስጥ አንዳንድ ግጭቶች መኖራቸው የሚጠበቅ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ችግሮች ከሌሎች ይልቅ በጣም ከባድ ሆነው ትዳርን ሊፈትኑ ይችላሉ። ከእነዚህ ውስጥ በትዳር ውስጥ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ የባልና ሚስት ችግሮች እነዚህ ናቸው፦ 1. የእምነት መጥፋት (Trust Issue) እምነት በትዳር ውስጥ እንደ መሠረት ያለ ነገር ነው። ቤት በመሠረት እንደሚቆም ትዳርም በእምነት ይቆማል። አንድ ጊዜ እምነት ከተሰበረ መመለሱ እጅግ ከባድ ነው። ለምሳሌ፦ • ውሸት መናገር • ነገሮችን መደበቅ • ምስጢር መኖር እነዚህ ነገሮች በትዳር ውስጥ ሲኖሩ የልብ ጉዳት ይፈጥራሉ። እምነት ከጠፋ በኋላ መመለሱ ጊዜ፣ ትዕግስት እና እውነተኛ መለወጥ ይፈልጋል። 2. የመግባባት እጥረት (Poor Communication) ብዙ ትዳሮች የሚፈርሱት በመግባባት እጥረት ነው። ባልና ሚስት ሐሳባቸውን፣ ስሜታቸውን እና ችግሮቻቸውን በግልጽ ሳይነጋገሩ ሲቀሩ ችግር ይፈጠራል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ነገር በልባቸው ይዘውት ይቆያሉ፤ ከዚያ በኋላ ቁጣ፣ መከፋት እና መለያየትን ያመጣል :: መግባባት ያለ ትዳር እንደ ነፋስ የተነካ ጀልባ ነው፤ መድረሻው አይታወቅም። 3. ክህደት (Infidelity / Adultery) ክህደት በትዳር ውስጥ ከሚያጠፋ ነገሮች መካከል ትልቁ ነው። አንድ ሰው የትዳሩን ታማኝነት ሲሰብር የልብ ጉዳት እጅግ ትልቅ ይሆናል። ይህ ብቻ አይደለም፤ • እምነት ይፈርሳል • ቤተሰብ ይበተናል • ልጆች ይጎዳሉ ክህደት በአንድ ትዳር ውስጥ እጅግ ከባድ ፈተና ነው። 4. የገንዘብ ጉዳይ (Financial Problems) ገንዘብ በብዙ ትዳሮች ውስጥ የክርክር ምክንያት ይሆናል። ለምሳሌ፦ • የገቢ እጥረት • የገንዘብ አጠቃቀም ልዩነት • ዕዳ አንዳንድ ጊዜ አንዱ መቆጠብ ይፈልጋል፤ ሌላው መውጣት ይፈልጋል። ይህ ካልተነጋገሩበት ችግር ይፈጥራል። 5. የባህርይ እና የስብዕና ግጭት ሁለት ሰዎች በተለያዩ ቤተሰቦች፣ ባህሎች እና ልምዶች ውስጥ አድገው ወደ ትዳር ይገባሉ። ስለዚህ አመለካከታቸው የተለየ መሆን የተለመደ ነው። አንዱ ፈጣን ይሆናል፤ ሌላው ዝግተኛ ይሆናል። አንዱ ተናጋሪ ይሆናል፤ ሌላው ጸጥ ያለ ይሆናል። ይህ ልዩነት ካልተቀበሉት ግጭት ይፈጥራል። 6. የቤተሰብ ግፊት (Family Interference) ወላጆች፣ ዘመዶች ወይም ጓደኞች በትዳር ውስጥ ሲገቡ ችግር ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የትዳር ጉዳይ ውስጥ በጣም ሲገቡ ባልና ሚስት መካከል ግጭት ይፈጠራል። ትዳር ሁለት ሰዎች መጀመሪያ የሚጠብቁት መሆን አለበት። 7. ክብር መጥፋት በትዳር ውስጥ ክብር ከጠፋ ፍቅር ደግሞ ይቀንሳል። • ስድብ • ንቀት • ማዋረድ እነዚህ ነገሮች ትዳርን በጣም ይጎዳሉ። ክብር የሌለበት ቤት ሰላም አይኖረውም። 8. መንፈሳዊ ልዩነት አንዳንድ ጊዜ ባልና ሚስት በእምነት ወይም በመንፈሳዊ አመለካከት የተለያዩ ሲሆኑ ይህ ደግሞ ግጭት ሊያመጣ ይችላል። አንዱ መንፈሳዊ ህይወትን በጥልቀት ሲኖር ሌላው ግን ካልተገናኘ በአመለካከት ልዩነት ሊኖር ይችላል። ✅ ማጠቃለያ ብዙ የትዳር ችግሮች ምክንያታቸው • እምነት መጥፋት • መግባባት እጥረት • ክብር መጥፋት ናቸው። እነዚህ ነገሮች ካሉ ትዳር በቀላሉ ይፈርሳል ። ነገር ግን ትዳርን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ነገሮች፦ • ትዕግስት • ይቅርታ • ፍቅር • ግልጽ መነጋገር ናቸው። ባልና ሚስት እነዚህን ነገሮች ካጠናከሩ ብዙ ችግሮች ሊፈቱ ይችላሉ። Bini Girmachew ቴሌግራም @BiniGirmachew

  • 14 июл.7 850346

    🚨 "ለምን ሁልጊዜ ራሴን እወቅሳለሁ?" 🚨 "ለምንስ ሁልጊዜ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማኛል?" 🚨 "ለምን ከአንድ ሰው ጋር ከቆየሁ በኋላ ራሴን እጠላለሁ?" እነዚህን ጥያቄዎች በአእምሯችሁ እየተመላለሱ ከሆነ ወይም በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለፈ ያለ ሰው የምታውቁ ከሆነ፣ ይህ ተከታታይ ትምህርት ለእናንተ ነው። በስነ-ልቦና ሙያዬ ውስጥ ከብዙ ተጎጂዎች ጋር ሰርቻለሁ። ከእነዚህም ውስጥ ናርሲሲስት ባህሪ ካላቸው ሰዎች ጋር ለረጅም ጊዜ ኖረው ነገር ግን የሚደርስባቸውን ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ያልተረዱ ብዙዎች ናቸው። እውነቱ ግን ይህ ነው፦ መሳሳትና ማጥፋት ሰዋዊ ባህርይ ነው። ይህ ማለት ግን ሁልጊዜ ችግሩ እናንተ ናችሁ ማለት አይደለም። ችግሩ ካላችሁበት ግንኙነት የመጣ ሊሆን ይችላል። በዚህ ዙርያ ሰፋ ያለ ግንዛቤን ለመፍጠር ከዛሬ ጀምሮ ስለ ናርሲሲዝም በሳይንሳዊና በተግባራዊ መንገድ የሚያስተምር ተከታታይ ትምህርት እጀምራለሁ። በዚህ ተከታታይ ትምህርት፦ ✅ ናርሲሲስት ባህርይ ምንድነው? እንዴትስ መለየት እንችላለን? ✅ የእነዚህ ሰዎች ስነ-ልቦና ማታለያ ዘዴዎቻቸው ምን ይመስላሉ? ✅ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን? ✅ ከግንኙነቱ በኋላ እንዴት መፈወስ እንችላለን? ✅ እነዚህን እና ሌሎች ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችን እንማራለን። 📌 ይህ መረጃ የአንድን ሰው ሕይወት ሊያድን ይችላል። 🔄 Share በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ። ❤️ Like በማድረግ ድጋፍዎን ያሳዩ። ✅ Follow በማድረግ ቀጣዮቹን ትምህርቶች ይከታተሉ። Bini Girmachew የስነ-ልቦና ባለሙያ 📞 +251 915 955 656 📲 በቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ። @BiniGirmachew @BiniGirmachew @BiniGirmachew እዚህ ላይ በመግባት Add ማድረግ ትችላላችሁ https://t.me/binigirmachew2

  • 14 июл.6 62192

    🎉 የክረምት ልዩ ቅናሽ! 🎉 ፔዲ ኬር የህፃናት ህክምና እና የህፃናት ቀዶ ህክምና ማዕከል በዚህ ክረምት በሁሉም የህፃናት ቀዶ ህክምናዎች 10% ቅናሽ መስጠቱን በደስታ ያሳውቃል! 📅 ከሐምሌ 8 እስከ ነሐሴ 24, 2018 ዓ.ም. (July 15 – August 30, 2026) ይህ ልዩ እድል ልጆቻችሁ የሚያስፈልጋቸውን የቀዶ ህክምና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ እና በከፍተኛ ጥራት እንዲያገኙ ያስችላል። 👨‍⚕️ ለረጅም አመታት ልምድ ባካበቱ የህፃናት ቀዶ ህክምና ሐኪሞች ይከናወናል 1. ዶ/ር ማሩ ጋማ 2. ዶ/ር ወርቅዬ ጥጋቤ 3. ዶ/ር ዚነዲን በከር 4. ዶ/ር አሻግሬ ገ/ሚካኤል 5. ዶ/ር ሳለመላክ ጥጋቤ 💉 የህፃናት ማደንዘዣ ስፔሻሊስቶች (Pediatric Anesthetologist ) 🏥 ለህፃናት ምቹና ዘመናዊ የህክምና አካባቢ የቀዶ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ህፃናት ካሉዎት ወይም የቀዶ ህክምና ምክር የሚፈልጉ ከሆነ፣ ይህን ልዩ እድል ይጠቀሙ። 📍 ዛሬውኑ ፔዲ ኬርን ይጎብኙ ወይም ቀጠሮ ይያዙ! አስተማማኝ እጆችን ፣ ለለጋ ህይወቶች ! 💙 Telegram | TikTok | Facebook | Instagram 📍 አድራሻ - ለቡ መብራት ሃይል ወደ ላፍቶ ቪዉ በሚወስደው መንገድ ሠነዶች ማረጋገጫ ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር : 0978213403                     0978176504 Safe Hands for Young Lives!

  • 11 июл.7 988154

    видео или голосовое, без подписи

  • 11 июл.9 30110081

    ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በ94 ዓመታቸው፣ ለናይጄሪያውያን የጻፉት ልብ የሚነካ #መልእክት ውድ የአገሬ ልጆች፣ ሰዎች ሕይወት ረጅም ናት ይላሉ። “አትቸኩል፤ ጊዜ ብዙ አለ” ይላሉ። እኔ ግን አሁን 94 ዓመት ሆኜ፣ ይህ እውነት እንዳልሆነ በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እችላለሁ። ሕይወት ረጅም አይደለችም፤ በዓይን ጥቅሻ ታልፋለች። ከዚህ ዓለም ለመለየት እየቀረብኩ ስሄድ፣ ልቤ ጥቂት ትምህርቶችን ትቶላችሁ ለመሄድ ይፈልጋል። ሀብት ሰበሰብኩ፣ ተጽዕኖ አገኘሁ፣ ክብርና እውቅናም አተረፍኩ። ነገር ግን ዛሬ እነዚህ ሁሉ በክፍሌ ጥግ ላይ እንደተከማቸ አቧራ ይመስሉኛል። አሁን እጄን ብዘረጋ፣ ከእነሱ አንዳቸውም ከእኔ ጋር ሊሄዱ አይችሉም። #ትምህርት_አንድ፡ ሕይወትን እየጠበቅክ አትኑር የሕይወቴን ትልቅ ክፍል በመጠበቅ አሳለፍኩ። ተማሪ ሳለሁ፣ “ከተመረቅሁ በኋላ ነው ሕይወት የሚጀምረው” ብዬ አሰብኩ። ወታደር ሆኜ ስሠራ፣ የሳምንቱን መጨረሻ እጠብቅ ነበር። ካገባሁ በኋላ፣ ልጆቼ እስኪያድጉ ጠበቅሁ። እነሱ ካደጉ በኋላ፣ ጡረታን መጠበቅ ጀመርኩ። እያንዳንዱን ቀን ወደ ፊት የሚወስደኝ እርምጃ ብቻ አድርጌ ነበር የማየው፤ እውነተኛው ሕይወት ወደፊት የሆነ ቦታ እንዳለ አስብ ነበር። ዛሬ ግን የመጨረሻ መድረሻ የለም ብዬ ተረድቻለሁ፤ ጉዞው ራሱ ሕይወት ነው። #ትምህርት_ሁለት፡ ወርቅ ምግብ አይደለም ለ50 ዓመታት ሀብት በማከማቸት ተጠምጄ ኖርኩ። በጣም ጠንክሬ ስሠራ፣ ከቤተሰቤ ጋር ማሳለፍ የነበረብኝን ውድ ጊዜዎች አጣሁ። ትላልቅ ቤቶችን፣ ውድ መኪናዎችን እና የቅንጦት ንብረቶችን ገዛሁ። ነገር ግን አሁን የሕይወቴ መጨረሻ እየቀረበ ሲመጣ፣ ከእኔ ጋር ሊሄድ የሚችል አንድም ነገር እንደሌለ ተረድቻለሁ። አንድ ቀን ልጄ በአትክልት ስፍራ ያገኘችውን ትንሽ ነፍሳት እንዳሳየኝ ስትጠራኝ አስታውሳለሁ። እኔ ግን “አሁን አይደለም፤ ሥራ ላይ ነኝ” አልኳት። እስከዛሬ ድረስ ያን ጊዜ ማጣቴ ያማል። #ትምህርት_ሶስት፡ በልብህ ያለውን ግድግዳ አፍርስ በወጣትነቴ፣ ርኅራኄ ማሳየት ወይም ይቅርታ መጠየቅ ድክመት እንደሆነ አምን ነበር። ከእኔ ጋር ያደገ ወንድም ነበረኝ። አንድ ቀን በትንሽ ጉዳይ ተጣላን። ዛሬ ላይ ያንን ጠብ ምን እንዳስነሳው እንኳ አላስታውስም። እሱ መጀመሪያ ወደ እኔ እንዲመጣ ጠበቅሁ። ዓመታት አለፉ። ከዚያም አንድ ቀን እንደሞተ የሚነግረኝ ስልክ ተደወለልኝ። በዚያን ጊዜ ተረዳሁ፤ ምናልባት ትክክል ነበርኩ፣ ነገር ግን ወንድሜን አጣሁ። አንድን ሰው የምትወድ ከሆነ፣ ዛሬ ንገረው። ስህተት ከሠራህ፣ ዛሬ ይቅርታ ጠይቅ። ነገ እንደሚኖር ማንም ዋስትና አይሰጥም። #ትምህርት_አራት፡ ፍርሃት ጥላ ብቻ ነው 22 ዓመት ሲሆነኝ ጸሐፊ የመሆን ሕልም ነበረኝ። በሕልሞችና ታሪኮች የተሞሉ ማስታወሻ ደብተሮች ነበሩኝ። ነገር ግን ሰዎች ይስቁብኛል ወይም እወድቃለሁ ብዬ ስለፈራሁ፣ ያንን መጽሐፍ ፈጽሞ አልጻፍኩም። ዛሬ እጆቼ ይንቀጠቀጣሉ፣ ዓይኖቼም ደክመዋል። ያ መጽሐፍ ግን አሁንም በውስጤ አለ። በሕይወት ውስጥ ትልቁ አሳዛኝ ነገር ሞት አይደለም፤ በሕይወት እያለን የምንቀብራቸው ሕልሞቻችን ናቸው። ልብህ የሚፈልገውን ነገር ማዘግየት አትቀጥል። ዛሬ ጀምር። ብትወድቅም እንኳ፣ “ሞክሬ ነበር” ማለት ትችላለህ። #መደምደሚያ የሰዓቴ ቲክታክ ድምፅ አሁን በጆሮዬ ይበልጥ እየተሰማ ነው። ጭንቀትን፣ ትዕቢትን እና ፍርሃትን ትቻለሁ። እናንተ ግን አሁንም በሕይወት ናችሁ። አዲስ ቀን አላችሁ። እሱን አታባክኑት። እጆቻችሁን ተመልከቱ። ጣቶቻችሁን አንቀሳቅሱ። እስትንፋሳችሁን ይሰማችሁ። ይህ ሁሉ በረከት ነው። Bini Girmachew - ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን @BiniGirmachew @BiniGirmachew @BiniGirmachew

  • 6 июл.8 7306114

    ሰዎች ከትዳራቸው ከተለያዩ በኋላ ለምን የቀድሞ አጋራቸውን በሚዲያ ሲያመሰግኑ ይታያሉ? (ከስነ-ልቦና አንጻር) “ባለቤቴ በጣም ጥሩ ሰው ነበር/ነበረች። እኔ ነበርኩ የተሳሳትኩት” ይህን ዓይነት ንግግር በተለይ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ ወይም በተለያዩ ቃለ ምልልሶች ላይ ብዙ ጊዜ እንሰማለን። በተለይም ታዋቂ ሰዎች ትዳራቸውን ከፈቱ በኋላ ስለ ቀድሞ ባለቤታቸው ሲጠየቁ “እሱ/እሷ ጥሩ ሰው ነበር” ሲሉ ይናገራሉ። ጥያቄው፦ እንደዚያ ከሆነ ለምን አብረው አልቆዩም? ከሥነ-ልቦና አንጻር ይህ ባህሪ 3 ዋና ዋና መነሻዎች አሉት፦ 1. ፀፀት እና ያለፈ ትውስታን ማሳመር (Rosy Retrospection) የስነ-ልቦና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች ፀፀት ሲሰማቸው ያለፈውን ጊዜ እያስታወሱ መልካም ጎኑን ያጉላሉ። በወቅቱ ትዳራቸውን ያበላሸው ጉዳይ ምናልባትም የእነርሱ ስህተት ባይሆንም እንኳን ፀፀት ሲኖር ግን “ምናልባት እንዲህ ባላደርግ ኖሮ እኮ..." ብለው ማሰብና ራሳቸውን መውቀስ ይጀምራሉ። 2. ማህበራዊ ግፊት (Social Pressure) በተለይ በህዝብ የሚታወቁ ሰዎች “ስለ ቀድሞ አጋሬ መጥፎ ብናገር ተከታዮቼ ይወቅሱኛል” ብለው ይፈራሉ። ስለዚህም መሸፋፈንን ሊመርጡ ይችላሉ። 3. ራስን ለመጠበቅ (Self-Justification) ሰዎች በሕዝብ ፊት መጥፎ ሰው ሆነው መታየት አይፈልጉም። ስለዚህ የቀድሞ የትዳራቸውን “ጥሩ” አድርገው በማቅረብ፣ “መረዳት ያልቻልኩት እኔ ነበርኩ” በማለት ራሳቸውን በጥፋተኝነት በመውቀስ እና ዛሬ ላይ ግን የተሻሉ ሰው እንደሆኑ በመግለፅ የህዝብን ርህራሄ ለማግኘት ይሞክራሉ። ታዲያ የቀድሞ አጋራቸው ጥሩ ሰው ከሆነ ለምን አብረው አልኖሩም? መልሱ ቀላል ነው፦ “ጥሩ ሰው” መሆን እና “ተስማሚ የትዳር አጋር” መሆን ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ሰዎች ሊስማሙ ይችላሉ፣ ሊዋደዱ ይችላሉ። ግን ለረጅም ጊዜ አብረው ለመኖር የሚያስችል ፍቅር፣ መቻቻል፣ ግንዛቤ፣ የጋራ ራዕይ ካጡ መለያየት የማይቀር ነው። ማጠቃለያ፦ በሚዲያ ላይ የቀድሞ አጋራቸውን የሚያመሰግኑ ሰዎች ሁሉ በእነዚህ ምክንያቶች ነው ማለት አይደለም። በእርግጥም በወቅቱ ካለመብሰል እና ካለማስተዋል የተነሳ የሚፈርሱ ትዳሮች ብዙ ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ ነገሮች ከሆኑ እና ከተለያዩ በኋላ በተረጋጋ አእምሮ ራስን ሲመለከቱ ምናልባትም እንኳንስ ለፍቺ ለፀብ እንኳን የማያደርሱ ጥቃቅን ምክንያቶች መደራረብ የወለደው ፍቺ መሆኑን ተገንዝበው መለያየታቸው ትክክል እንዳልነበረ የሚረዱ ብዙ ሰዎች አሉ። ከተለያዩ በኋላ የሚታረቁ ሰዎችን የምናየውም ለዚህ ነው። ነገር ግን ሁሉም ሰው በሚዲያ የሚናገረው ነገር ሁሉ የእውነት ነው ማለትም አንችልም። ፀፀታቸውን ለመደበቅ አልያም ራሳቸውን ከህዝብ ፍርድ ለማዳን ብለው የሚያደርጉትም እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል። “ጥሩ ሰው” መሆን ብቻ ትዳርን አያስቀጥልም። ዘላቂ ትዳር ከጥሩነት ባሻገር መስማማት፣ መቻቻል እና መረዳዳትን ይጠይቃል። እናንተስ? ይህን ዓይነት ንግግር ስትሰሙ ምን ይሰማችኋል? ሀሳባችሁን ከዚህ በታች ፃፉልኝ 👇 📢 በተመጣጣኝ ዋጋ የስነ-ልቦና ድጋፍ ማግኘት ከፈለጉ በዚህ ቁጥር በቴሌግራም ያግኙኝ፦ +251915955656 Bini Girmachew - ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን @BiniGirmachew @BiniGirmachew @BiniGirmachew

  • 28 июн.10,4 тыс5255

    ሼር በማድረግ የ1 ሰው ትዳር ያድኑ በባልና ሚስት መካከል መባል የሌለባቸው ዋና ዋና ነገሮች ====================================== በትዳር ውስጥ ጤናማ ግንኙነት እንዲኖር የቃላት አጠቃቀም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በንዴትም ሆነ ባለማወቅ በባልና ሚስት መካከል መነገር የሌለባቸው ጎጂ ቃላት እና ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው፦ 🙏1. የፍቺ ዛቻ ማቅረብ "ከዚህ በኋላ አብረን መቀጠል አንችልም" ወይም "እንፋታ" የሚሉ ቃላት። ጉዳቱ፦ በትዳሩ ላይ ያለውን የመተማመን ስሜት እና ደህንነት ያጠፋል። ምንም እንኳን በንዴት ቢነገርም፣ የትዳር አጋርን ሁልጊዜ በስጋት ውስጥ እንዲኖር ያደርጋል። 🙏🏼2. ከሌሎች ጋር ማወዳደር "ለምን እንደ እገሌ ባል/ሚስት አትሆንም?" ወይም የሰዎችን ኑሮ አምጥቶ ማነጻጸር። ጉዳቱ፦ የትዳር አጋር የዝቅተኝነት ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል። ትዳር የሁለት ሰዎች ልዩ ጉዞ በመሆኑ የሌላውን ሰው ህይወት መመዘኛ ማድረግ ቂምን ይወልዳል። 🙏3. "ሁልጊዜ" እና "በፍጹም" የሚሉ ቃላትን መጠቀም "ሁልጊዜ ችላ ትለኛለህ/ትይኛለሽ" ወይም "በፍጹም አትረዳኝም/አትረጂኝም"። ጉዳቱ፦ እነዚህ ቃላት የትዳር አጋርን ጥሩ ጎን ሙሉ በሙሉ የሚክዱ እና የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግ ለመከላከል (defensiveness) የሚያነሳሱ ናቸው። በምትኩ "ይሄን ስታደርግ ቅር ይለኛል" ማለት ይመረጣል። 🙏4. ያለፈን ስህተት ደጋግሞ ማንሳት ይቅርታ የተደረገበትን ወይም ያለፈን የድሮ ስህተት አሁን በተፈጠረ ጠብ ውስጥ መልሶ ማምጣት። ጉዳቱ፦ ይቅርታው ከልብ እንዳልነበረ ያሳያል፤ እንዲሁም የትዳር አጋር ወደፊት እንዳይራመድ እና መተማመን እንዳይኖር ያደርጋል። 🙏5. ማንጓጠጥ፣ ንቀት እና ስድብ መሳደብ፣ የማሰብ ችሎታን፣ ቤተሰብን ወይም አካላዊ ገጽታን ማንቋሸሽ። ጉዳቱ፦ በራስ መተማመንን የሚጎዳ እና ጥልቅ የስነ-ልቦና ጠባሳ የሚተው ተግባር ነው። ንቀት (Contempt) ለትዳር መፍረስ ትልቁ መንስኤ እንደሆነ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ። 🙏6. ስሜትን ማጣጣል "ለምን ታካብዳለህ/ታካብጃለሽ?" ወይም "ይሄ እኮ ምንም የሚያስከፋ ነገር የለውም" ብሎ መገምገም። ጉዳቱ፦ የትዳር አጋር ስሜቱ ቦታ እንደሌለውና ሀሳቡ እንደማይከበር እንዲሰማው ያደርጋል። ጤናማ ትዳር ለመገንባት መግባባት፣ መከባበር እና ግልጽነት ወሳኝ ናቸው። አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በችግሩ ላይ እንጂ በግለሰቡ ላይ ትኩረት አለማድረግ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። ከእነዚህ ከተጠቀሱት ነጥቦች ውስጥ በተለይ የቱ ጉዳይ በትዳር ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ተጽዕኖ ይፈጥራል ብለው ያስባሉ? @BiniGirmachew @BiniGirmachew @BiniGirmachew ሼር በማድረግ የ1 ሰው ትዳር ያድኑ

  • 28 июн.9 2964728

    አስተሳሰብህን ህይወትህን ቀይር (change your thinking change your life) የስነልቦና ባለሞያ ቢኒ ግርማቸው አንድ ነገር ለማድረግ አስብ ያሰብከውን ለማሳካት አልችለውም የምትለውን ነጥብ አስተወል። ወደ ተግባር ከመሄድህ በፊት አልችለውም የሚለውን ሀሳብህን ከአእምሮህ ውስጥ በቅድሚያ ለማጥፋት ስራ። አእምሮህ ጥሩ ጓደኛህም መጥፎ ጠላትህም መሆን ይችላል። አእምሮህን በፈለግከው አቅጣጫ ለመምራት ስልጡንና ታዛዥ ነው።ይህን የሰላ አእርምሮህን በመጠቀም ሕይወትህ በእውቀት የመጠቀ በሀብት የበለጸገ ማድረግ አልያም ለጥፋት በማጀገን ለእርኩሰት በማመቻቸት ድንዙዝና መናኛ በማድረግ ርባናቢስ ሕይወት እንዲኖርህ ልታደርግ ትችላለህ። ማልዶ ከእንቅልፍ መነሳት የስኬት ልምድ ነው።ስኬታማ ሰዎች ማልደው በመነሳት ያነባሉ የእለታዊ ስራዎቻቸው ያዘጋጃሉ፣ያደራጃሉ በወረቀት ላይም ቀድመው ያሰፍራሉ ያቅዳሉ። ብዙዎቹ ይህን በአብዛኛው ለማድረግ ሲቸገሩ ይስተዋላል።ቶማስ ጅፈርሰን "ፀሀይ አልጋዬ ውስጥ እያለሁ አትወጣም"።ይል ነበር። በሕይወት ውስጥ ሁለት ጊዜያቶች አሉ።ትናንትና እና ነገ። ዛሬ አሁናዊ ሁነታዎቻችን ይማዳምጥበት ሲሆን ትናንት እንዴት እንደነበርም የማሰብ አልያም ነጋችን ምን ሊሆን እንደሚችል በመገመት መካከል ራሳችንን ልናገኝ የምንችልበት ነው። ዛሬ ልንቀይረው በማንችለው ትናትናችን ላይ በመቆም ወይም በእኛ ቁጥጥር ውስጥ ስላለው ነጋችን በመገመት ላይ ወሳኝ ሆኖ እናገኛታለን። ብዙ ሰዎች ነጋቸው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ትላንታቸው ላይ በተፈጠሩ ጠባሳዎች ዛሬ ላይ ቆመን በንዴት ሲበሽቁ ይገኛሉ።ይህ ከትናንት የወረሱት አሉታዊ ስሜታቸው ዛሬያቸውን ጨምሮ እንደነጠቃቸው በፍጹም አይገነዘቡም። ዛሬ ላይ ትናትናቸውን ሲያማርሩና ሲወቅሱ ሲገረሙ ነጋቸው ላይ ልዩነት መፍጠር የሚችለውን የዛሬ ማንነታቸውን በቅሬታ ገመድ ጠፍረው እንደያዙት አይረዱም። በህይወትህ ስኬታማ ያልሆንክበት ነገር ምንድነው? ለአለመሳካቱ ተጠያቂ የደረግከው በየጊዜውስ የምትወቅሰው ማንን ነው? መልስህ ምንም ይሁን ምን ከዛሬ ጀምሮ ችግሩ የኔ ነበር ብለህ ሃላፊነቱን ውሰድና የስኬት መንገድህን ጀምር። ባለፈ ሕይወትህ ላይ እክል ለገጠሙህ ሰዎች ሁሉ ይቅርታ የምታደርገው ዛሬ ነው። እነሱም ይሂዱ አንተም ወደፊት ተጓዝ!። @BiniGirmachew @BiniGirmachew @BiniGirmachew ወጥ የሆነ ትምህርት ለማግኘት በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ። https://t.me/+kKDSPxKL7iNlNmM0 መልካም ሰንበት

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን — tgindex