tgindex
ኦርቶዶክሳዊ ስብከት | ORTHODOX SIBKET

ኦርቶዶክሳዊ ስብከት | ORTHODOX SIBKET

Статистика

በዚህ ቻናል የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶችን በሥርዓተ ቤተከርስቲያን ለማነጽ ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው

Последний пост
10 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
17 263
+39 за 4 дн.
Сутки
+13
+0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 929
24 постов
Вовлечённость
34,3%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 341
1/48двое суток
1 536
1/72трое суток
1 657

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 авг.1 5123

    አዳምጡ https://vt.tiktok.com/ZS4764FhQ/

  • 10 авг.2 086696

    በጾመ ፍልሰታ የምንችል ሰዎች፣ ሌሊት ሰዓታቱን እንቁም። ካልቻልን ኪዳን እናድርስ፤ ካልቻልንም ቅዳሴ እናስቀድስ። እሱንም ካልቻልን ደግሞ በሰርክ ጉባኤ ላይ ተገኝተን በጸሎትና በምስጋና እንቀጥል። የምንችለውን በትጋት እናድርግ፤ እግዚአብሔር የልባችንን ፍላጎትና ጥረት ይመልከት። 💚 @Orthodox_sibket 💚 💛  @Orthodox_sibket 💛 ❤️  @Orthodox_sibket ❤️

  • 8 авг.2 314512

    እግዘብሔር ለእኛ ሲል ክብሩን ትቶ ሰው ሆኖ አዳነን። እኛ ለእግዚአብሔር ስንል ምን የተውነው ነገር አለ? 💚 @Orthodox_sibket 💚 💛  @Orthodox_sibket 💛 ❤️  @Orthodox_sibket ❤️

  • 8 авг.2 111262

    እግዚአብሔር ሆይ፣ ውሸትን ከልቤ አርቅ። እውነትን በፍቅር እንድናገር አስተምረኝ። ስህተት ስሠራ ለመቀበል ትሕትና ስጠኝ። ሰውን ለማስደሰት ሳይሆን እውነትን በፍቅር እንድኖር እርዳኝ። አሜን። 💚 @Orthodox_sibket 💚 💛  @Orthodox_sibket 💛 ❤️  @Orthodox_sibket ❤️

  • 8 авг.2 4764612

    📌 ብልግናን Normalize ለማድረግ በዘዴ የሚጠቀሙባት ጥቅስ👉 "አትፍረድ....ይፈረድብሃል" ከዕምነታችን/ ከ አስተሳሰባችን/ ከተማርነው ነገር በመነሳት በቀን ውስጥ ደጋግመን ይህ ልክ አይደለም፣ ይህ መጥፎ ነው ፣ ይህ አይደረግም ስንል ነው የምንውለው አይደል?? ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንዶች ምነው ለምትፈልጉት ጉዳይ ብቻ ሲሆን "አትፍረድ" ለማለት ተሽቀዳደማችሁ? ፍርድ ይህ ልክ አይደለም ማለት ከሆነ ....ቅዱሳት መፅሀፍት በጠቅላላ የቱ ልክ የቱ ልክ እንዳልሆነ አይደል የሚጠቅሱት? ፈጣሪ የጠላውን መጥላት የወደደውን መውደድ የቱ ነው ክፋቱ? መጥምቁ ዩሀንስስ ንጉሱን የወንድምህ ሚስት ላንተ ማድረግ አይገባህም ሲለው ....እውነት መናገሩ እስከ ሞት እንዳስቀጣው ረሳችሁት? አያችሁ እውነትን ሳያመቻምቹ መናገር ለአለም ሲስተም የሚጎረብጥ ስለሆነ ...ከመኖርም ሊያሰናብት ይችላል። ------------- ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤ ዮሐንስ እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም ይለው ነበርና። ------ማቴ 14:3 ------------ አንዳንዴ ሳስበው አመፃን እያየን "አትፍረድ" እያልን ደጋግመን የምንጮኸው  ምንአልባት የራሳችንን ውድቀት/የሀጢያት ልምምድ ለመሸፈን ለሰዎች የተሟገትን እየመሰልን ራሳችንን እየደበቅን ይሆን እላለሁ?? ሌላ ልጨምርላችሁ ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን ላለችው ቤተክርስትያን በፃፈው መልዕክቱ -------------- "ፍሬ ከሌለው ከጨለማ ስራ ጋር አትተባበሩ ይልቁን ግለጡት እንጂ"  ኤፌ 5:11---በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል። ግለጡት እንጂ ክደኑት እንዳላለ ልብ በሉልኝ። --------------- ስጋቴ አሁን ብዙዎች በያዙት" አትፍረድ" አያያዝ 📌እገሌ ግብረሰዶማዊነትን በቲክቶክ ሲያሳይ---- አትፍረድ ልትሉ...እኛም ዝም ልንል? 📌አንዲት እርቃን እየሄደች በኢንስታግራም የምትፖስት ሴት----ኧረ ይሄ ነገር ሲባል.....አትፍረድ ልትሉ....እኛም ዝም ልንል?(ብላችኋል ለነገሩ...እኛም ዝም ብለናል🙄 በመዝሙር ወሲብ ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ሲደረግ---ኧረ ይሄ ልክ አይደለም ብንል...አትፍረድ.....እኛም ዝም ልንል?(ተብሏል) አንዱ ተነስቶ ሀይማኖትን ሲያጠለሽ ፈጣሪን ሲሳደብ.....አትፍረድ.....እኛም ዝም ልንል???(ብለናልም) ከዛስ?? ህግ የለ...የማህበረሰብ እሴት የለ፣ የሞራል ልዕልና የለ ሁሉ እንደ ወደደው ይሄዳል:: በዘመናዊነት መጠሪያ ዘማዊነት ይጨበጨብለታል።  በመብት ስም በነፃነት ሽፉን ሁሉ የስሜቱ ባሪያ ይሆናል። ከልካይ የለውም።  በምዕራቡ እያየነው እንዳለው ማለት ነው። 🙄 እርም የሆነን ነገር ቆሻሻ ስንል በራሳችን ፀድተን ሳይሆን እርሱ ሁሌ እያጠበን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ተስማምተን ነው። ቃሉ በቁንፅል ሳይሆን ሙሉ ሀሳቡ ተወስዶ ነው መፈታት ያለበት።  የተዳሁት ይህን ነው!! የመጨረሻ ይህቺን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክትን ጀባ ልበላችሁ "ትክክለኛ ፍርድ ፍረዱ እንጂ የሰውን ፊት አይታችሁ በማዳላት አትፍረዱ።"-------የዮሐንስ ወንጌል 7:24 ጌታ ሆይ፣ እውነትን በፍቅር እንድናገር እርዳኝ። 💚 @Orthodox_sibket 💚 💛  @Orthodox_sibket 💛 ❤️  @Orthodox_sibket ❤️

  • 28 июл.4 4678716

    እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከዛሬ ጀምሮ በየቀኑ አንድ የበረሃ አባት ታሪክ እናያለን። አባ ሙሴ ጥቁር አባ ሙሴ ጥቁር በመጀመሪያ ኃይለኛና ጨካኝ ሰው ነበሩ። ዝርፊያና ወንጀል ይፈጽሙ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ይፈሯቸው ነበር። አንድ ቀን ግን የበረሃ አባቶችን ሕይወት አዩ። የእነርሱ ትሕትናና ቅድስና ልባቸውን ነካው። ከዚያም ንስሐ ገብተው ወደ ገዳም ገቡ። መጀመሪያ መንፈሳዊ ትግል ከባድ ነበር፤ ግን ጸሎትን፣ ጾምን እና ትሕትናን አልተዉም። በጊዜ ሂደት ታላቅ ቅዱስ ሆኑ። የሚታወቅበት ታሪክ አንድ ጊዜ አንድ ወንድም በኃጢአት ስለወደቀ እንዲፈርዱበት ጠሩት። አባ ሙሴ በጀርባቸው ቀዳዳ ያለውን ከረጢት በአሸዋ ሞልተው ይዘው መጡ። ሰዎቹ "ይህ ምንድን ነው?" ሲሉ ጠየቋቸው፣ እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "ኃጢአቴ ከኋላዬ እየፈሰሰ ነው፤ እኔ ግን አላየውም። እንዴት የወንድሜን ኃጢአት እፈርዳለሁ?" ይህን ሲሰሙ ሁሉም በፍቅር ወንድማቸውን ተቀበሉት። ከአባ ሙሴ የምንማረው ማንም ሰው በንስሐ ሊለወጥ ይችላል። ሌሎችን ከመፍረድ ይልቅ ራሳችንን መመርመር ይገባል። የእግዚአብሔር ምሕረት ከሰው ኃጢአት ይበልጣል። 💚 @Orthodox_sibket 💚 💛  @Orthodox_sibket 💛 ❤️  @Orthodox_sibket ❤️

  • 26 июл.4 6628011

    እንኳን አደረሰን !!!

  • 19 июл.6 495299

    без подписи

  • 19 июл.5 793296

    без подписи

  • 15 июл.6 488103

    አይነስወር ልጁን ያጋባው አባት ተከታይ ፣ልብ አንጠልጣይ ፣ በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ። መከታተል ትችላላችሁ በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ላይ https://t.me/+69KPpZzPUQljYjY0

  • 11 июл.6 75111415

    ለመፀለይ ሲደክምህ ስንት ጊዜ ሳይደክምህ ኃጢያት እንደሰራህ አስብ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

  • 10 июл.6 72972

    ጥሩ መንፈሳዊ ምክር ነው https://vt.tiktok.com/ZSXdf82Wr/ ተጠቀሙበት

  • 6 июл.8 697483

    አቤቱ፥ በመልካሙ ጊዜ ጸሎቴ ወደ አንተ ነው፤ አቤቱ፥ በምሕረትህ ብዛት በማዳንህም እውነት አድምጠኝ። መዝሙረ ዳዊት 69:13

  • 30 июн.10,5 тыс192

    ከዚህ ውስጥ ማድረግ የምትችሉት ነገር ከአለ በሙሴ ጸሊም ስም እጠይቃለሁ በዚህ ስልክ በመደወል ማናገር ይችላሉ። አስራት በኩራት ያለው የደብሩ አስተዳደር ስልክ +251941448030 አድራሻ : ሃያት 49 ማዞሪያ ኤርፖርት ከሚያሰራው  ህንጻ ወረድ ሲሉ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አዲሰ ከሚሰራው ባጃጅ በመያዝ ወደ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ወደ ሚወስደው  መንገድ  ልክ እግዚአብሔር አብ  ቤተክርስቲያን ሳደረሱ  ወደ  ግራ  መታጠፍ (ልዩ ምልከት ድልድዩን መሻገር ) በባጃጅ  ለምትሄድ  50 ብር  ነው በነገራችን ላይ ሕጋዊ የቤተክርስቲያን አካውንት  ነው  1000707004561  ለማንኛውም ጥያቄ +251941448030

  • 30 июн.6 22218

    ሰኔ 24

  • 19 июн.8 616916

    без подписи

  • 19 июн.7 4606211

    🪽🤍❤🤲 ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ለሰው ልጆች ይቅርታን ለማስገኝት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልድ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል። ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! መሬትና ውኃ ያልተቀላቀለበት ከነፍስና ከእሳት ብቻ ለተፈጠረው መልአካዊ ገጽታህ ሰላም እላለሁ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ። የቅዱስ ሚካኤል እረድኤት በረከት ጥበቃና ምልጃው አይለየን አሜን

  • 16 июн.7 927114

    без подписи

  • 15 июн.8 3314538

    በሂወቴ ውስጥ ብዙ ፈተናዎች ብዙ ስቃዮች ብዙ መሰናክሎች ብዙ አለመሳካቶች አጋጠሙኝ። ሁሉንም ግን አንተን አባቴን ሳስብ ከፊቴ ገለል አሉልኝ። በተጎዳሁ ጊዜ እንኳን አባቴን እግዚአብሔርን ሳስብ ግዙፍ የመሰሉኝ ችግሮቼ ሁሉ ትንሽ ይሆኑና ከስሬ ይወድቃሉ። እኔም በእግሮቼ እረግጫቸው እቆምና አባቴን ይበልጥ አመሰግናለሁ። በሂወቴ ውስጥ ያለፍኳቸውንም ፈተናዎች ሁሉ ብቻዬን አላለፍኳቸውም። በእግዚአብሔር እርዳታ ግን ሁሉን አልፌ እዚህ ደረስኩኝ። እግዚአብሔር ሆይ ፀሎቴን ሰምተህ ሁሉንም ምቹ ሁሉንም የሚያስደስት ሁሉንም የሚጥም ስላደረክልኝ ሁሌ አመሰግንሀለሁ። ባለፍኳቸውም ፈተናዎች ይበልጥ ስላጠነከርከኝ ይበልጥ ስላጀከንከኝ ተመስገን እላለሁኝ! ችግሮቼንም በድል እንድወጣ አደረከኝና ሁልጊዜ ደስተኛ አደረከኝ፤አፌንም በምስጋና ሞላኸው! በስቃይ ውስጥም ሆኜ አንተ ንጉሴ ነህ! በችግር ውስጥም ሆኜ አንተ የሂወቴ መሪ ነህ! በማይመረመረው ጥበብህ እኔነቴንም ወደ ተሻለው ማንነቴ አሸጋገርክልኝ። ሁሌ አመሰግንሀለሁ! በሆነልኝም እየሆነልኝ ባለውና ወደፊትም በሚሆንልኝ ሁሉ ተመስገን እልሀለሁ! በሰዎች ፊት የጎደለ የመሰለውንም ህይወቴ አንተ ሙሉ ስላደረከው ሁሌ እወድሀለሁ! አሜን ! ልዩ ማስታወሻ ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሳህበት ተመልስህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ ካሰብክበት ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ። በሰላም ወታቹ በሰላም ግቡ መልካም ቀን Bini Girmachew ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን 💚 @Orthodox_sibket 💚 💛  @Orthodox_sibket 💛 ❤️  @Orthodox_sibket ❤️

  • 12 июн.8 9094965

    1. እግዚአብሔር በተለየ መንገድ እየመለሰልክ መሆኑን መርምር። ኢሳይያስ 55:8-9 "ሀሳቤ እንደ ሀሳባችሁ መንገዴም እንደ መንገዳችሁ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥እንዲሁ መንገዴና ከመንገዳቹ ሀሳቤም ከሃሳባቹ ከፍ ያለ ነው"።አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር እኛን እንዲለውጠን ከመፀለይ ይልቅ ሁኔታውን እንዲለውጥልን እንጸልያለን።ነገር ግን እግዚአብሔር የሚጀምረው ባህሪን፣ ጥበብን፣ ትዕግስትን ወይም መንፈሳዊ ብስለትን በመገንባት ነው። በዙሪያችን ባለወጠው ነገር ላይ ብቻ አናተኩር።እግዚአብሔር በውስጣችን ምን እየለወጠ እንደሆነ በጥንቃቄ እንመልከት። ማድረግ ያለባቹ>> እግዚአብሔርን በምትጠባበቁበት ወቅት ባህሪያቹን፣ ቅድሚያ የምሰጧቸውን ነገሮች እና መንፈሳዊ ህይወታቹን እንዴት እየቀረጸ እንዳለ ማስተዋል። 2. ወደ እግዚአብሔር ቃል ተመለሱ። ሮሜ 10:17 "እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው"።የእግዚአብሔርን ቃል ችላ ብለን ረጅም ጊዜ መጠበቅ እምነታችንን ሊያዳክም ይችላል።ጸሎትና ቅዱሳት መጻሕፍት አብረው ይሰራሉ። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ሲሆን ቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር እንዲናገርህ ይፈቅዳሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ሳይመገብ የሚጸልይ አማኝ ተስፋ ሊቆርጥ ይችላል ምክንያቱም እምነት በመለኮታዊ እውነት ነው የሚያድገው። ማድረግ ያለብህ፦ በተለይም በእግዚአብሔር ተስፋዎች ላይ በየቀኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህንና ማሰላሰልህን ጨምር። 3. እግዚአብሔር አስቀድሞ እንድትተው የጠየቀህን ማንኛውንም ነገር አስወግድ። ኢሳይያስ 59:1-2 "እነሆ የእግዚአብሄር እጅ ከማዳን አላጠረችም፥ጆሮውም ከመስማት አልደነቆረችም"። አንዳንድ ጊዜ ጉዳዩ መልስ ያላገኘንበት ጸሎት ሳይሆን ያልፈታነው አለመታዘዝ ነው። እግዚአብሔር እርማት የሚፈልግ ልማድን፣ ግንኙነትን፣ አመለካከትን ወይም ውሳኔን አስቀድሞ ተናግሮህ ሊሆን ይችላል። ማድረግ ያለብህ፦ እግዚአብሔር ማንኛውንም ያልታዘዝክበትን ቦታ እንዲገልጽልህ እና ለሰጠህ እርማት ደሞ በፍጥነት መልስ ስጠው። 4. የእግዚአብሔርን ታማኝነት አሁን ባለህበት ሁኔታ መለካት አቁም። ዕንባቆም 3:17-18 "ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ"። እምነት በሚታይ ማስረጃ ላይ ብቻ የተመሠረተ አይደለም። ዕንባቆም መልሱን ከማየቱ በፊት በእግዚአብሔር ላይ መታመንን መርጧል። እምነትህ ከሁኔታዎች ጋር የሚወጣና የሚወርድ ከሆነ ተስፋ መቁረጥ ብዙውን ጊዜ ይከተልሃል። የእግዚአብሔር ታማኝነት የተመሠረተው አሁን ባለህበት ሁኔታ ሳይሆን በእሱ ባሕርይ ላይ ነው። ማድረግ ያለብህ፦ በየቀኑ ምስጋናን ተለማመድ፤ የእግዚአብሔርን ያለፈ ታማኝነቱን አስታውስ። 5. ጸሎታችሁን ከመተው ይልቅ አጠናክሩ። ሉቃስ 18:1 "ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሁልጊዜ መጸለይ እንዳለባቸውና ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማስተማር አንድ ምሳሌ ነገራቸው"። ኢየሱስ በጸሎት ስለመፅናት አጥብቆ አስተምሯል ምክንያቱም መዘግየት እንደሚመጣ ያውቅ ነበር። ሰዎች ቀደም ብለው ፀሎት ስለሚያቆሙ ብዙ መልሶች ዘግይተዋል። የማያቋርጥ ጸሎት ማለት እግዚአብሔርን ለማሳመን መሞከር ማለት አይደለም።በእርሱ ላይ መታመን እና ጥገኛ መሆን ማለት ነው። ማድረግ ያለብህ፦ ወጥ የሆነ የጸሎት መርሃ ግብር ፍጠር። ውጤቶቹን በማታይበት ጊዜም እንኳ ታማኝ ሆነህ ቀጥል። 6. ጥበበኛ የሆነ መንፈሳዊ ምክር ፈልግ። ምሳሌ 15:22"ምክር ከሌለች ዘንድ የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል፤ መካሮች በበዙበት ዘንድ ግን ይጸናል"። አንዳንድ ጊዜ በሁኔታችን ላይ በጣም ስለምናተኩር አስፈላጊ ግንዛቤዎችን እናጣለን።እግዚአብሔር ጥበብን፣ እርማትንና ማበረታቻን ለማምጣት የጎለመሱ አማኞችን፣ አማካሪዎችን እና መንፈሳዊ መሪዎችን ይጠቀማል። ማድረግ ያለብህ፦ ወቅትህን እንድትለይ ሊረዱህ ከሚችሉ ታማኝ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ አማኞች ጋር ተነጋገር። 7. እየጠበክ እግዚአብሔርን ማገልገልህን ቀጥል። ገላትያ 6:9"ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት"። በመጠባበቂያችን ጊዜ ከጠላት ግቦች አንዱ አማኞች ማገልገል እንዲያቆሙ፣ ማደግ እንዲያቆሙ እና መታመን እንዲያቆሙ ማድረግ ነው።የተሰጠህ ሥራ መልስህ ገና ስላልደረሰ አይቆምም። እሱን እየጠበቅክ እግዚአብሔርን መታዘዝህን ቀጥል።ከእግዚአብሔር ጋር በታማኝነት ስትመላለስ የጥበቃው ወቅት አይባክንም። ማድረግ ያለብህ፦ ማገልገልህን ቀጥል፣ ማደግህን ቀጥል፣ መጸለይህን ቀጥል እና የእግዚአብሔርን ጊዜ መታመንህን ቀጥል። 💚 @Orthodox_sibket 💚 💛  @Orthodox_sibket 💛 ❤️  @Orthodox_sibket ❤️