ዓምደ ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት | Amde Silase Sunday School
Статистикаይኽ የካራሎ ደ/ታቦር ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የዓምደ ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የዓምደ ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያደርሳል። https://linktr.ee/amdesilase
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 13
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 319
- 1/48двое суток
- 365
- 1/72трое суток
- 394
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#የአብነት_አዳራሽ_ምርቃት “የእግዚአብሔርም ቤት ስለ ተመሠረተ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ።” ዕዝራ 3፥11 የአብነት አዳራሹን ምርቃት ምክንያት በማድረግ ልዩ ጉባኤ ተዘጋጅቷል፤ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት መምህር መልዓከ ታቦር ኃ/ኢየሱስ ትምህርተ ወንጌል ያስተምራሉ፣ ቅኔ፣ ወረብ፣ መዝሙር በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ እናንተን እንጠብቃለን። #ዝክረ_ቅዱስ_ያሬድ #ወጉባኤ_እስጢፋኖስ #ሱባኤ_ጉባኤ #ዓምደ_ሥላሴ #ደብረ_ታቦር #ካራሎ_ቅድስት_ሥላሴ
እንኳን ለጽንሰተ ማርያም በሰላም አደረሳችው🙏 " ድንግል ሆይ ከምልጃሽ በቀር ሊጠብቀኝ የሚችል እንደሌለ አወኩኝ ያለ ማህጸንሽም ፍሬ ሊራራልኝ የሚችል እንደሌለ ይህንንም አውቄ ወደ አንቺ ተጠጋሁ በልጅሽም አመንኩ እርሱንም አመለኩ ቸርነቱንም ተስፋ አደረኩ " ❤️ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጅ አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን ለመግራት እንጂ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው ። ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም። ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ። ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ። ጾም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙን የሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነ እግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳ ለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታ የሚሠራበት ጊዜ ይሆናል። ጾም ማለት ነፍስና ሥጋ በኀብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናውን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው። በጾም ወቅት ነፍስና ሥጋ የነፍስን ሥራ ለመሥራት ይተባበራሉ። ይህም ማለት ለጸሎት ለተመስጦ ለክብርና ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው። ❤️ ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ https://t.me/amdasilase07
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ዘዳዊት_በገና_ዘዓምደ_ሥላሴ #ልዩ_የበገና_መርሃግብር #መጋቤ_ስብሐት_አለሙ_አጋ #መልዓከ_ሰላም_ዘውዱ_ንጉሤ #ነሃሴ_3_2018 #ዓምደ_ሥላሴ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት #ካራሎ_ደብረ_ታቦር_ቅድስት_ሥላሴ
#ታላቅ_የበገና_ምሽት 🌙✨ "ዘዳዊት በገና ዘዓምደ ሥላሴ" 🙏 🗓️ እሑድ ነሃሴ 3 ❤️ ታላቁን አባታችን መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ በገናን ከ65 ዓመት በላይ የደረደሩት ከሰፊ የሕይወት ልምዳቸው ጥቂቱን ያጋራሉ 📜🗣️። ⏰ ከ9:00 ሰዓት ጀምሮ መቅረት ያስቆጫል 🚶♂️። በገና ትምህርት ለመመዝገብ፡👇👇 https://forms.gle/c8SG8jrtE4B3rcgV8 ለበለጠ መረጃ፡ 📞 0929010479 📞 0948685897 📍 በዓምደ ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት አብነት አዳራሽ 🏛️🎶 https://t.me/amdasilase07
"በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ፣ ከነቢያት ማኅበር ሁሉ ጋራ ወደኔ ነይ፡፡ ካንደበታቸው የወጣውን የምስጋናሽን ኃይለ ቃል ልብ ታስደርጊልኝ ዘንድ፡፡ ድንግል ሆይ፣ የቃልን ካንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአስተማሩ፣ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ሐዋርያት ጋራ ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ፣ በሥጋቸው የልጅሽን መከራ ከተሸከሙ የሰማዕትነታቸውን ደም ከተቀቡ ሰማዕታት፣ እርሳቸው ሁለት ልሳን ያለው ሰይፍ የሚታጠቁ ድል የሚነሱ የንጉሥ ሠራዊት ናቸው፡፡ ከርሳቸው ማኅበር ጋራ ደግሞ በረድኤት ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ በማመንዘር እድፍ ልብሳቸውን ካላሳደፉ፣ ለመንፈስም ማደሪያ ከሆኑ ንጹሓን ደናግል ማኅበር ጋራ ወደኔ ነዪ" ❤️ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!
፯ተኛ ዙር ሱባኤ ጉባኤ ዘዓምደ ሥላሴ ልዩ የመክፈቻ መርሃ ግብር፡ 🗓 አርብ ነሃሴ 1 ⏱ ምሽት ከ12:30 ጀምሮ ✝ መምህር፡ መልዓከ ታቦር ኃ/ኢየሱስ ፋንታሁን በአካል ለመማር ውስን ቦታዎች ይኖሩናል፡ ለመመዝገብ👇👇👇👇 https://forms.gle/MLQDJYaCrxW1AZCw7 👆👆👆👆👆👆👆👆 የርቀት ለመመዝገብ፡ 👇👇👇👇👇👇👇 https://forms.gle/b6uoedCp6yp9BMp16 👆👆👆👆👆👆👆👆 📍 በካራሎ ደብረ ታቦር ቅድስት ሥላሴ ሰንበቴ አዳራሽ ይኼ ልዩ ዕድል እንዳያመልጣችው። https://t.me/amdasilase07
የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል የሆነዉ የወንድማችን ሃብታሙ ሹሚ #ሮቡ አባቱ ስላረፉ የቀብር ስነስርአታቸዉ ዛሬ 28/11/2018 ዓ/ም ከቀኑ 08:00 ሰዓት በደብራችን በካራሎ ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ስለሚከናወን በስርዓተ ቀበሩ ላይ መገኘት የምንችል አባላት እንድንገኝ ይሁን። የማጽናኛ መርሃ ግብር ምሽት ከ12:30 ጀምሮ በመኖሪያ ቤታቸው ስለተዘጋጀ በሠዓቱ ተገኝተን ቤተሰቡን እናጽናና። የአባታችንን ነፍስ በአፀደ ገነት ያኑርልን እመ አምላክ የልባቸዉን ሀዘን ታቅልልን። ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ያድልልን ዓምደ ሥላሴ ሰ/ት/ቤት
የርቀት ትምህርት (ሱባኤ ጉባኤ) ምዝገባ ጀምረናል፡ ለመመዝገብ፡ 👇👇👇👇👇👇👇 https://forms.gle/b6uoedCp6yp9BMp16
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው። 1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ !! 2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ !! ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ። የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ። " ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ ። +++ ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ+++ ሥራህን ሥራ፦ ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰቶታል፤ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነው። በርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፤ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል። የሃሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን እንዲጠይቁህ፣ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገርብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ፣ ሔሮድስ፣ ሐናንያ፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ። ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሰላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል። ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዝብ አትችልምን? ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ ይጨቃጨቅ፡፡ አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል። የሰይጣን ውሻዎችን ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎቹን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ። ሥራህን ሥራ፦ ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ። አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈፀም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ። ሥራህን ሥራ፦ ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልተነገረህም፤ ሰይጣን አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም። እነኚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሠራ አትችልም፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለጌታ አልሠራህም። ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ዐለት የፀና ይሁን፣ ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፤ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል። አንተ ግን በጸና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት እስከ መጨረሻ ጸንተህ “የሰጠኽኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ” ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል። " ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ !!! https://t.me/amdasilase07
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 "እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ✨️️️️️️ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው "የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ "እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል" ✨️️️️️️ አባ አርሳኒ ✨️️️️️️✨️️️️️️❇️ "ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ" ✨️️️️️️አባ ስምዖን "ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል" ✨️️️️️️ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ "እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው" ✨️️️️️️ባሕታዊ ቴዎፋን ✨️️️️️️✨️️️️️️❇️ "ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" ✨️️️️️️አባ ቴዎዶር "አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል" ✨️️️️️️ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው "ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት" ✨️️️️️️ ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ ✨️️️️️️✨️️️️️️❇️ "ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" ✨️️️️️️አባ ኤፍሬም አረጋዊ "በሃይማኖታችሁ የሚስቅ እና ሚሳለቅ ቢኖር ጸልዩለት። በፍርድ ቀን የሚያስቅ ነገር አይኖርም።" ✨️️️️️️ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟