tgindex
ነገረ ማርያም( አንድምታ)

ነገረ ማርያም( አንድምታ)

Статистика

በዚህ ቻናል ሃይማኖታዊ ምስጢሮችን ያገኙበታል። " ኪሩቤል አፍራሰ ፌማ፥ ወሱራፌል ዘራማ፥ ክሉላነ ሞገስ ወግርማ ፥ ይሴብሑኪ ማርያም፥ በቃለ ጥዑም ዜማ።"/ ማርያም ሆይ የመንፈስ ቅዱስ አፍራስ ኪሩቤልና በግርማና በክብር የተጋረዱ በራማ የሚኖሩ ሱራፌል ማርያም ሆይ ጥዑም በሚሆን የዜማ ቃል ያመሰግኑሻል።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 133
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
261
23 постов
Вовлечённость
12,2%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
176
1/48двое суток
201
1/72трое суток
217

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • https://www.youtube.com/live/U-TbQPcsesY?si=0_Z-8PGP6R-mnK5q

  • " እመቤቴ ማርያም ምን ሆናለች አንገቷን ደፍታ ታለቅሳለች ብታለቅስ(2) የወልዴ ቀሚስ በሰበሰ ብታነባ አብቅላ አደረች ጽጌ አበባ ያን አበባ አስረው ገረፉት እንደ ሌባ ይግረፉኝ ያዳፉኝ ሐሰት በቃሉ ሳይገኝ። 👉 የኢየሩሳሌም ቆነጃጅት   ንጉሣችንን ወሰዱት፣ ወሰዱት ግንድ አሸክመው ሊያዳፉት፣ ያዳፋኝ ሐሰት በቃሉ ሳይገኝ እሱን ሊሰቅሉት ሐሙሱን ተሰናበታት እናቱን፣ እናትዬ ነገ ታይኛለሽ ተሰቅዬ፣ ይስቀለኝ ሐሰት በቃሉ ሳይገኝ፣ ውሃ ሲለምን ጌታችን ሐሞት አጠጡት የዝሆን፣ አዳም ስሱ (2)  ለዝናብ ጌታ ውሃ አነሱ።

  • ወፌ ሰንብታ ሰንብታ፣ መጣች ለፍልሰታ። አገርሽ የት ነው? ኤፍራታ አሳድሪኝ ማታ። በክንፍሽ ጥላ ጋርደሸ ከልጅሽ ስፍራ ወስደሽ፣ እንዳልቆምብሽ በግራ፣ እንዳያሰቃየኝ መከራ። ወፌ ነፍሴን አደራ ወፌ ነፍሴን አደራ(2) 👉ወዴት አለፈች ከመንደር፣ የእንቦሳው እናት ያች ጊደር በእግዜር አሳዩኝ መንገዱዋን፣ እንድከተላት በኀዘን እሳት አዝላ ወዴት ባከነች ከገሊላ፣ ባረፍሽበት ከዛፍ ጥላ፣ ሽፍቶች ከበቡሽ በዚያ ቆላ፣ ዓይኖችሽ ፈርተው ስለ እነሱ እንባ ክረምትን አፈሰሱ። የኔ የኔ የባሪያሽ ይጥፋ ሁለት ዐይኔ፣ ባንቺ ፈንታ ግብጽ በስደት ልንገላታ ዓለም ይጭነቀኝ ይጥበበኝ እንደ ጠበበሽ ግራ ቀኝ ሽፍቶች ከበቡሽ ሲማከሩ ዓይኖችሽ  ፈዘው እንባ አዘሩ መራቆቱ ስላሳዘነው ጌትነቱ አመነታ ልብሱን መለሰ አንዱ ሽፍታ። ሰላም ሰጊድ❗❗❗

  • https://www.youtube.com/live/5D0rXFnzs-4?si=24dIU181WhXYQOOJ

  • https://www.youtube.com/live/r2SNyQ2ge_U?si=6N3wPNOXW4eLYheC

  • በክንፍሽ ጥላ ጋርደሸ ከልጅሽ ስፍራ ወስደሽ፣ እንዳልቆምብሽ በግራ፣ እንዳያሰቃየኝ መከራ። ወፌ ነፍሴን አደራ ወፌ ነፍሴን አደራ(2)

  • ድንግል ሆይ! ምን ብዬ... (ከማዕበል ፈጠነ) ድንግል ሆይ! በቤተ መቅደስ ሳለሽ መላእክት አረጋጉሽ! ድንግል ሆይ! የሰማይ መና ሊመግብሽ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከልሽ! ድንግል ሆይ ! የጌታችንን መጸነስ ሊያበሥርሽ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተፈሥሒ ተፈሥሒ እያለ ሰገደልሽ! ድንግል ሆይ! በግብጽ በረኃ በተሰደድሽ ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ተከተለሽ! ድንግል ሆይ! በቀራንዮ አደባባይ ስታለቅሽ ወንጌላዊ ዮሐንስ ተከተለሽ። ድንግል ሆይ! የልጅሽን ትንሣኤ ራሱ ክርስቶስ ገለጠልሽ! ድንግል ሆይ! ለግንዘተ ሥጋሽ አበው ሐዋርያት በብሩህ ደመና ተሰበሰቡልሽ! ድንግል ሆይ! ወደሰማይ ስታሪጊ ቅዱስ ቶማስ ከደመናው ውስጥ ሰገደልሽ!! ድንግል ሆይ! ቅዱስ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ቅዱስ ያሬድ በማኅሌቱ ስምሽን ያወድሱሻል!! ድንግል ሆይ! እኔ ባሪያሽ እረ ምን ብዬ ላወድስሽ!? ድንግል ሆይ! ምንም ኀጢአተኛ ብሆን "እንደ አባቶቼ "ሰዓሊ ለነ ቅድስት" እልሻለሁ!! በሱባኤ እማጸንሻለሁ!! መልካም ሱባኤ!!

  • 9 авг.2763из mariam6846

    видео или голосовое, без подписи

  • 9 авг.2711из mariam6846

    видео или голосовое, без подписи

  • 9 авг.2942из mariam6846

    видео или голосовое, без подписи

  • 9 авг.3062из mariam6846

    видео или голосовое, без подписи

  • 9 авг.3011из mariam6846

    видео или голосовое, без подписи

  • ወፌ ሰንብታ ሰንብታ፣ መጣች ለፍልሰታ። አገርሽ የት ነው? ኤፍራታ አሳድሪኝ ማታ። በክንፍሽ ጥላ ጋርደሸ ከልጅሽ ስፍራ ወስደሽ፣ እንዳልቆምብሽ በግራ፣ እንዳያሰቃየኝ መከራ። ወፌ ነፍሴን አደራ ወፌ ነፍሴን አደራ(2) 👉ወዴት አለፈች ከመንደር፣ የእንቦሳው እናት ያች ጊደር በእግዜር አሳዩኝ መንገዱዋን፣ እንድከተላት በኀዘን እሳት አዝላ ወዴት ባከነች ከገሊላ፣ ባረፍሽበት ከዛፍ ጥላ፣ ሽፍቶች ከበቡሽ በዚያ ቆላ፣ ዓይኖችሽ ፈርተው ስለ እነሱ እንባ ክረምትን አፈሰሱ። የኔ የኔ የባሪያሽ ይጥፋ ሁለት ዐይኔ፣ ባንቺ ፈንታ ግብጽ በስደት ልንገላታ ዓለም ይጭነቀኝ ይጥበበኝ እንደ ጠበበሽ ግራ ቀኝ ሽፍቶች ከበቡሽ ሲማከሩ ዓይኖችሽ  ፈዘው እንባ አዘሩ መራቆቱ ስላሳዘነው ጌትነቱ አመነታ ልብሱን መለሰ አንዱ ሽፍታ። ሰላም ሰጊድ❗❗❗

  • ➥  ምልዕተ ክብር ሆይ! ከቅዱሳን ኹሉ ይልቅ ትለምኚልን ዘንድ ላንቺ ይገባል፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳት አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ከመምህራን፣ ከሐዋርያት፣ ከ፸ አርድእትም አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ይልቅ የሚበልጥ የመወደድ የመፈራት ግርማ አለሽ፡፡ ሊቁ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡- “ኦ ሙኃዘ ፍስሐ! ፈድፋደ ብኪ ግርማ ራዕይ ዘየዐቢ እም ኪሩቤል እለ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ ወሱራፌል ፮ ክነፊሆሙ - የደስታ (የጌታ) መገኛ የምትኾኚ እምቤታችን ሆይ! ዐይናቸው ብዙ ከሚኾን ከኪሩቤል፣ ክንፋቸው ስድስት ከሚኾን ከሱራፌል ይልቅ በምእመናን ዘንድ የመወደድ፣ በአጋንንት በአይሁድ በመናፍ*ቃን ዘንድ የመፈራት፣ በሥላሴ ዘንድም የባለሟልነት መልክ አለሽ” ይላል /ቁ.፳፪/፡፡ በእውነት የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ፡፡ ለሰውነታችን ሕይወትን የምታማልጅን አንቺ ነሽ፡፡ አንድነቱን ሦስተነቱን በማመን አጽንቶ ሥጋዌውን በማመን ያፀናን ዘንድ፣  “ጸጋሰ ሥርየተ ኃጢአት ይእቲ” እንዲል በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ለአባ ሕርያቆስ ፤ ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን፤ ሃገራችንን ኢትዮጵያ ከጥፋት፣ ቤተክርስቲያንን ከመናፍ*ቃን፣ ህዝቦቿን ከስደት ትጠብቅልን። ጾሙን ጾመ ሥርየት፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግልን። ልመናዋ ክብሯ የልጅዋም ቸርነት ከኹላቸን ጋራ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር አሜን፡፡ ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ለሕዝበ ክርስትያን ይዕቀቦም እመዓተ ወልዳ። ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ይዕቀባ እመዓተ ወልዳ። https://www.youtube.com/live/uAsErGtI8CI?si=mZNned_EFqAaI-pB

  • ዳግመኛም አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫ፡- ኦ መሶብ ቤተ ልሔማዊት ዘወለደቶ ለኅብስተ ሰማይ ዘኢያብቌልዎ ዝናማት ወዘኢሐፀንዎ አየራት - ዝናማት ያላበቀሉትን አየራት ያላሳደጉትን የሰማዩን እንጀራ የወለድሽው ቤተ ልሔማዊት መሶብ ሆይ” በማለት መስክሯል /አርጋኖን ዘረቡዕ/፡፡ ከአባቶች አንዱም፡- “ድንግል ሆይ! በእውነቱ አንቺ ከታላላቅ ይልቅ ታላቅ ነሽ፡፡ ማኅደረ ቃለ አብ ሆይ! አንቺን ሊተካከል የሚችል ታላቅ ማን ነው? ድንግል ሆይ! ከየትኛው ፍጥረት ጋር አወዳድርሻለሁ? አንቺ ቀድሞ በወርቅ ካጌጠችው የሕጉ ታቦት ይልቅ በንጽሕና ያጌጥሽ ታላቅ ነሽ! እውነተኛውን መና የተሸከምሽ መሶበ ወርቅ አንቺ ነሽ፡፡ መና የተባለውም መለኮት የተዋሐደው ሥጋው ነው” ብሏል፡፡ ኅብስተ ሕይወት ከሚባል ልጅሽ ጸንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡         ✍️ተቅዋም ፭.      እንቲ ውእቱ ተቅዋም ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ማኅቶተ ፀዳል ኩሎ ጊዜ። ዘውእቱ ብርሃኑ ለዓለም። ብርሃን ዘእምብርሃን ዘአልቦ ጥንት። አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን። ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ። ወበምጽአቱ አብርሃ ላዕሌነ ለእለ ንነብር ዉስተ ጽልመት ወጽላሎቱ ሞት። ወአርአትዐ እገሪነ ዉስተ ፍኖተ ሰላም በምሥጢረ ጥበቡ ቅዱስ። ሰአሊ ለነ ቅድስት።          ➥ ብርሃንነት ያለውን ፋና የተሸከምሽ የወርቅ ተቅዋም (መቅረዝ) አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፭፡፴፩-፵/፡፡ ይኸውም ፋና ለሰው ኹሉ ዕውቀትን የሚገልጽ ብርሃን ነው፡፡ ጥንት ከሌለው ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው፡፡ ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ ሳይለወጥ ካንቺ ሰው የኾነው ነው፡፡ ሰውም በመኾኑም በድንቁርና በቀቢጸ ተስፋ ለምንኖር ለኛ አበራልን (ዕውቀትን ገልጸልን)፡፡ በጥበቡ ባደረገው ሥጋዌ እግረ ልቡናችንን ወደ ሕገ ወንጌል ጎዳና አቀናልን /ኢሳ.፱፡፩-፪፣ ማቴ.፬፡፲፬-፲፮/፡፡ ታላቁ የዜማ አባት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም፡- “አንቲ ውእቱ ተቅዋም ዘወርቅ ዘኢገብራ እደ ኬንያ ዘሰብእ… - የብልሐተኛ እጅ ያልሠራት በውስጧም መብራት የሚያበሩባት የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ፤ ራሱ የአብ ብርሃን ያበራባታል እንጂ፡፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ወደ አንቺ መጥቶ አደረ፡፡ አምላክነቱም በዓለም ኹሉ አበራ፡፡ ጨለማን ከሰዎች ላይ አራቀ፡፡ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ በብርሃኔ እመኑ፤ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ ብሎ በሚያድን ቃሉ አዳነን” ብሏል /ቁ.፰፣ ዮሐ.፲፪፡፴፭፣ ፩ኛ ዮሐ.፩፡፭/፡፡ በጥበቡ ባደረገው ሥጋዌ እግረ ልቡናችንን ወደ ሕገ ወንጌል ጎዳና ከአቀናልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡    ✍️ማዕጠንት ፮. አንቲ ውእቱ ማዕጠንት ዘወርቅ። እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳት። ብሩክ ዘነሥአ እመቅደስ ዘይሠሪ ኃጢአተ ወይደመሰስ ጌጋየ። ዝ ውእቱ ዘእግዚአብሔር ቃል ዘተሰብአ እምነኪ ዘአዕረገ ለአቡሁ ርእሶ ዕጣነ ወመሥዋዕተ ሥሙረ። ሰአሊ ለነ ቅድስት።          ➥  ቡሩክ አሮን ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍሕም የተሸከምሽ ማዕጠንተ ወርቅ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፴፡፩-፰/፡፡ ፍሕም የተባለውም በአፍኣ በውስጥ በሥጋ በነፍስ ኃጢአትን የሚያስተሠርይ ነው፡፡ ይኸውም ከአንቺ ሰው የኾነውና “ወአንከረ አብ እምዝንቱ መሥዋዕት - ከዚህ መሥዋዕት የተነሣ አብ አደነቀ” እንዲል /ሃይ.አበ.፷፰፡፳፫/ ለአባቱ ራሱን ያማረ የተወደደ መሥዋዕት አድረጎ ያቀረበ አካላዊ ቃል ነው /ኤፌ.፭፡፪/፡፡ ራሱን ያማረ የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ካቀረበ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡        ✍️ተፈሥሒ ፯. ተፈሥሒ ኦ ማርያም ርግብ ሠናይት። ዘወለድኪ ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ። አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ እንተ ሠረፀት እምሥርወ ዕሤይ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት። አካላዊ ቃልን የወልድሽልን መልካም ርግብ ማርያም ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ከእሴይ ሥር የወጣሽ መዓዛ ሠናይ አበባ አንቺ ነሽ፡፡ መዐዛ ሰናይ የተባለውም የቅዱሳን መዐዛ የሚኾን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /መጽሐፈ ድጓ፣ ገጽ.፻፺፱/፡፡ መዐዛ ሠናይ ከተባለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡     ✍️በትረ አሮን ፰. በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ዘኢንበለ ተክል ወኢሠቀይዋ ማየ። ከማሃ አንቲኒ ኦ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክነ ዘበአማን ዘእንበለ ዘርእ መጽአ ወአድኅነነ። ሰአሊ ለነ ቅድስት። ሳይተክሏት የበቀለች፣ ውሃ ሳያጠጧትም የለመለመች ያበበች ፲፪ በኵረ ሎሚ ያፈራች የአሮን በትር ነበረች /ዘኁ.፲፯፡፩-፲/፡፡ ከቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት ኑረሽ፣ ዘር ምክንያት ሳይኾነው ሰው ኾኖ ያዳነን እውነተኛ አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን አንቺም እንደርሷ ነሽ /ኢሳ.፯፡፲፬/፡፡ አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫም በአርጋኖን ዘሰኑይ ላይ፡- “ዕፀ ከርካዕ እንከ እሰምየኪ እስመ ከርካዕ ሠናየ ይጸጊ፤ ወሠናየ ይፈሪ፤ ወሠናየ ይጼኑ፤ ወከመ በትር ይቡስ ዘቦ ላዕሌሁ ወፅአ ዑፃዌ ክህነት አሥረጸ አዕጹቀ ወአቊጸለ ከርካዕ ምዑዘ፤ ወከማሁ አንቲኒ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ዐሠርተ ወክልኤተ ክራማተ ወፀነስኪዮ ለኢሱስ ዘእንበለ ዘርዐ ብእሲ - እንግዲህ የሎሚ ዕንጨት ብዬ እጠራሻለሁ፡፡ ሎሚ መልካሙን ያብባል፤ መልካሙን ፍሬ ያፈራል፡፡ በጐ በጐ ይሸታልና ዕጣ እንደ ወጣበት ደረቅ በትር ሳይተከል በቤተ መቅደስ ለምልሞ፣ ቅንጣት አውጥቶ፣ አብቦ ተገኘ፡፡ ሽታው ያማረ የተወደደውን ሎሚ አፈራ፡፡ እንዲሁም አንቺ በቤተ መቅደስ ዐሥራ ኹለት ዓመት ተቀምጠሸ ያለ ወንድ ዘር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀነስሺው” በማለት አብራርቶታል፡፡ ዳግመኛም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፡- “ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር በቤተ መቅደስ ነበረች፡፡ ለካህናት ዝግጁ ያደረጋት ነበረች፡፡ አንቺም በቅድስናና በንጽሕና ጸንተሸ እንደ እርሷ በቤተ መቅደስ ኖርሽ፡፡ ከቤተ መቅደስም በክብር በታላቅ ደስታ ወጣሽ፡፡ በእውነት የሕይወት ፍሬ የኾነ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከአንቺ ተገኘ፡፡ ቅድስት ሆይ! ከመልአኩ እንደተረዳሽው ከወንድ ያለመገናኘት ልጅን አገኘሽ፡፡ መልአኩ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጸልልሻል ብሎ ነግሮሽ ነበርና” በማለት አማናዊቷ የአሮን በትር እርሷ መኾኗን አስተምሯል /ቁ.፲፩/፡፡ ሰው ኾኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡    ✍️ለኪ ይደሉ ፱. ለኪ ይደሉ ዘእምኩሎሙ ቅዱሳን ተስአሊ ለነ ኦ ምልእተ ጸጋ አንቲ ተዐብዮ እምሊቃነ ጳጳሳት ወፈድፍደ ትከብሪ እምነቢያት ብኪ ግርማ ራእይ ዘየዐቢ እምግርማ ሱራፌል ወኪሩቤል። አንቲ በአማን ምክሐ ዘመድነ ወሰአሊት ሕይወተ ለነፍሳቲነ ሰአሊ ለነ ኅበ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ያፅንዐነ በርትዕት ሃይማኖት ዉስተ አሚነ ዚአሁ። ይጽግወነ ሣህሎ ወምሕረቶ። ይሥረይ ኃጢአተነ በብዝኅ ምሕረቱ። ሰአሊ ለነ ቅድስት።

  • የእሑድ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ        ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት በዚህ ዕለት እመቤታችን ከወትሮው ይልቅ ቀደም ብላ መጥታለች፡፡ “ዛቲ ዕለት ተዓቢ እምኩሎን ዕለታት፤ ወውዳሲያቲሃኒ የዓብያ እምኵሉ ውዳሴያት - ከዕለታት ኹሉ ይህቺ ዕለት ታላቅ ናት፤ ከውዳሲያቱም ኹሉ የዚች ዕለት ውዳሴ ታላቅ ነው” አለችውና ባረከችው፡፡ እርሱም በቤተ መቅደስ ባሉ ንዋያት ማለትም፡- በመሶበ ወርቅ፣ በተቅዋመ ወርቅ፣ በማዕጠንተ ወርቅ፣ በበትረ አሮን እየመሰለ ሲያመሰግናት አድሯል፡፡ ✍️ተሰመይኪ ፩.  ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምእንስት አንቲ ውእቱ ዳግሚት ቀመር እንተ ተሰመይ ቅድስተ ቅዱሳን ወዉስቴታ ጽላተ ኪዳን። ፲ቱ ቃላት እለ ተጽሕፍ በአፃብዒሁ ለእግዚአብሔር ቀዲሙ ዜነወነ በየዉጣ እንተ ይእቲ ቀዳሜ ስሙ ለመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ። ወኮነ ዓራቄ ለሐዲስ ኪዳን። በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሐሙ ለማሃይማን ወለሕዝብ ንጹሐን። ሰአሊ ለነ ቅድስት።          ➥ ንዕድ ክብርት ሆይ! ከሴቶች ተለይተሽ የሥላሴ ባለሟል ተባልሽ፡፡ ከተለዩ የተለየሽ፣ ከከበሩ የከበርሽ፣ ቅዱሳን ኪሩቤል የተሣሉብሽ፣ ቅዱሳን ካህናት የሚያመሰግኑሽ ኹለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፮፡፩-፴/፡፡ ሕግ የተጻፈባት ጽላት ያለብሽ የምትባዪ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፴፪፡፲፭-፲፱/፡፡ ኪዳንም ያልኹት በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ (በግብር አምላካዊ የተገኙ) ዐሥሩ ቃላት ናቸው፡፡ ዐሥርቱ ቃላትን በጽላቱ ጽፎ እንዳኖረ ኹሉ ዋሕድ ቃለ እግዚአብሔርም በአፃብዐ መንፈስ ቅዱስ (ያለ ወንድ ዘር፣ በግብረ መንፈስ ቅዱስ) በማኅፀንሽ እንዲቀረጽ ኾኗልና የሙሴ ጽላት አንቺ ነሽ /ቅዳ.ማር. ቁ.፴፫/፡፡ ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብም በነገረ ማርያም መጽሐፉ፡- “… ወማኅፀናሰ ለማርያም ድንግል በክልኤ ይትሜሰል በጽላት ዘተጽሕፈ ውስቴታ ዐሠርተ ቃላት፡፡ ወዐሠርተ ቃላት ቀዳሜ ስሙ ለወልዳ ውእቱ ዘውእቱ የውጣ ዘተሰምየ በኈልቄ ዐሠርተ ቃላት - … በኹለት ወገን ድንግል የምትኾን የማርያም ማኅፀንስ ዐሥሩ ቃላት በውስጧ በተጻፈ ጽላት ይመሰላል፡፡ ዐሥሩ ቃላትም የልጇ የኢየሱስ ክርስቶስ የመዠመርያ ስሙ ነው፤ ያውም የውጣ በዐሥሩ ቃላት የተጠራ ነው” ብሏል /ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን፣ ክፍል ፩፣ ገጽ ፻፳፰፣ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ/፡፡   ከአንቺ ሳይለወጥ ሰው ኾነን፡፡ ለኦሪት ሳይኾን ለወንጌል ሊቀ ካህናት ኾነን፡፡ ለምድረ ርስት ሳይኾን ለመንግሥተ ሰማያት አስታራቂ ኾነን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን፤ እርሱም የበደላችን ስርየት ነው” እንዲል በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን አዳናቸው /ኤፌ.፩፡፯/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የኤፌሶንን መልእክት በተረጐመበት በአንደኛው ድርሳኑ ላይ፡- “ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘነው ሥርየተ ኃጢአት በርግጥ ታላቅ ነው፡፡ ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው በልጁ ደም መኾኑ ግን ከምንም በላይ ታላቅ ነው” በማለት የእግዚአብሔር ከኅሊናት የሚያልፈውን የማዳን ምሥጢር (ፍቅር) በመደነቅ ተናግሯል፡፡ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን ካዳነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ✍️ታቦት ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይትቅዝ ይትሜሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ ዘኮነ ሰብአ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢዉላጤ መለኮት ንጹሕ ዘአልቦ ሙስና ዘዕሩይ ምስለ አብ ወቦቱ አብሠራ ለንጽሕት፡ ዘእንበለ ዘርእ ኮነ ከማነ በኪነ ጥበቡ ቅዱስ፡ ዘተሰብአ እምነኪ ዘንበለ ርኩስ፡ ደመረ መለኮቶ። ሰአሊ ለነ ቅድስት።                                                             ፪. ኹል ጊዜ ንጽሕት የምትኾኚ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ስለዚህ ነገር ኹላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለንም፡፡ ሰውን ከሚወድ ሰው ከሚወደው ከርሱ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ ኹል ጊዜ ዓይነ ልቦናችንን ወዳንቺ እንሰቅላለን፡፡ ሸምሸር ሰጢን ከሚባል ከማይነቅዝ (በአምልኮተ ጣዖት ከማይለወጥ) እንጨት የተቀረጸ በአፍአ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት አካላዊ ቃልን ይመስልልናል /ዘጸ.፳፭፡፱-፳/፡፡ ይህ ንጹሕ የሚኾን፣ መለወጥ የሌለበት እርሱ ባለመለወጡ አለመለወጧን ነገራት፤ ከአብ ዕሪና ባለመለየቱም አለማለየቷን ነገራት (አምላክ ወሰብእ ኾኖ እርሷም እም ወድንግል መኾኗን ነገራት)፡፡ ከጥበብ በሚበልጥ ጥበብም ዘር ምክንያት ሳይኾነው እንደ እኛ ሰው ኾነ፡፡ አበው፡- “ዓለሙን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ ሰው ኾኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል” የሚሉትም ስለዚሁ ነው፡፡ አደፍ ጉድፍ ሳያገኝሽ መለኮቱን አዋሕዶ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ መለኮቱን አዋሕዶ ሰው ከኾነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ ✍️ መቅደስ መቅደስ ዘይኬልልዋ ኪሩቤል እለ ሥዑላን በሥዕለ እግዚአብሔር፡ ቃል ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ዉላጤ ኮነ ሠራዮ ኃጥአትነ ወደ ምሳሴ አበሳነ። ሰአሊ ለነ ቅድስት። ፫.  እግዚአብሔር በፈጠራቸው በኪሩቤል አምሳል፤ ሙሴ የሣላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደሰ ሙሴ አንቺ ነሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በፈጠራቸው በኪሩቤል አምሳል፣ ሰሎሞን የሣላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደሰ ሰሎሞን አንቺ ነሽ፡፡ ጌታ በማኅፀንሽ ያደረብሽ አማናዊቷ መቅደስ አንቺ ነሽ፡፡ ሳይለወጥ ካንቺ ሰው የኾነው አካላዊ ቃል በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይልን ኾነ፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ ✍️ መሶበ ወርቅ አንቲ ዉእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ እንተ ዉስቴታ መና ኅቡእ፡ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወሀቤ ሕይወት ለኩሉ ዓለም። ሰአሊ ለነ ቅድስት። ፬. መና ያለብሽ መሶበ ወርቅ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፲፮፡፴፫-፴፬/፡፡ ይኸውም መና የተባለው ከሰማይ የወረደና ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀንሽ የተሸከምሽው ነው፡፡ እርሱም “አበዊክሙሰ መና በልዑ በገዳም ወሞቱ - አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ፤ ሞቱም” እንዳለው ያይደለ፤ ይልቁንም ለሰው ኹሉ ሕይወት የሚያድል ኅብስት ነው /ዮሐ.፮፡፶/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን ላይ፡- “አስተማሰልናኪ ቅድስት ወብፅዕት ስብሕት ወቡርክት ክብርት ወልዕልት በመሶበ ወርቅ ዘውስቴታ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት ወሃቤ ሕይወት ለኵሉ ዘየአምን ኪያሁ ወይበልዕ እምኔሁ በአሚን ወበልብ ሥሙር ምስለ እለ በየማኑ - የተለየሽና ደግ የኾንሽ የተመሰገንሽና የተባረክሽ የከበርሽና ከፍ ከፍ ያልሽ ሆይ! የሕይወት ኅብስት ባለበት በወርቅ መሶብ መሰልንሽ፡፡ የሕይወት ኅብስትም በቀኙ ካሉ ጻድቃን ጋር እርሱን ለሚያምን በሃይማኖትና ፈቃደኛ በኾነ ልብ ከእርሱ ለሚበላም ኹሉ ሕይወትን የሚሰጥ ከሰማይ የወረደ ነው” ብሏል /ቁ.፯/፡፡

  • https://www.youtube.com/live/R0MY9CCTtjs?si=3UNkFWyVvq73jK1O

  • ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሓ ወኑዛዜ ኀበ ይረስእዎ ለላህ ወኢየሐልይዎ ለትካዜ ማርያም ህሉት ውስተ ልበ አምላክ እምቅድመ ጊዜ ትፍሥሕተሰ ተፈሣሕኩ በፍልሰትኪ ይእዜ ገጸ ዚአኪ እሬኢ ማዕዜ ። ሰላም ለሥጋሽ መፍለስ ወደ መረጋጋት እና ደስታ ኀዘንን እና ትካዜን ከማያስታውሱበት ቦታ ዘመን ቈጠራ ሳይታወቅ ዓለም ሳታምር ለምታ ማርያም በልበ አምላክ ታስበሽ የኖርሽ በጌታ። መደሰትንስ ተደስቻለኹ በፍልሰትሽ ቀን በእልልታ "ፊትሽን መች ዐየው ይኾን?" እላለኹ ጧት ማታ። መልክዐ ፍልሰታ (ትርጒም፥  ኤፍሬም የኔሰው  ) https://www.youtube.com/live/r2SNyQ2ge_U?si=cjER6FN6M0ZZhiOz

ነገረ ማርያም( አንድምታ) — tgindex