tgindex
የሆሄያት ህብር📝📝

የሆሄያት ህብር📝📝

Статистика

ውድ የሆሄያት ህብር ቻናል ቤተሰቦች ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።👍👍 ቻናላችን፦ 👉በግጥም 📔📰📼📼 👉በድርሰት📚📚 👉በትረካ📀🎼 👉በስዕል🃏🃏 👉ወጎች📜📜 👉በአጫጭር ልብ ወለዶች ወደ እናንተ እንደርሳለን። ለሀሳብ እና አስተያየት ፦ሊዮ ማክ፦ @Leoyri ፦ዮሲ ማን፦ @yosikeman ፦የሪ፦ @yerijo ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል 👉 @gGetem

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
868
+1 за 2 дн.
Сутки
+2
+0,23%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
276
23 постов
Вовлечённость
31,8%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
73
1/48двое суток
83
1/72трое суток
90

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • ረሳኋት (ሚካኤል አ) ጤዛ እኮ ነው ገጽዋ በማለዳ ረጥቦ ፣ ቀትር የሚሰዋ። ጉም ነው የሷ መውደድ ጋርዳዋለች ሲሉ ፣ እኔ አለው ስራመድ። ጣሟን ዘነጋሁት ፣ እንደ በዓል ዶሮ ዛሬ እንኳ ብቀምሳት ፣ እኩል ነች ከሽሮ። ጠረኗ ጠፍቶኛል ፣ አዲስ ነኝ ለራሴ እሰይ ከስማ ቀረች ፣ ያቺ የሰው ከሴ ! ጆሮዬን አልሰጥም ስሟን እየጠሩ ፣ ተቀምጠው ጎኔ እዛው ጨፈርኩበት ፣ በአምና ድንኳኔ። ፡ እያየኋት ከሳች ፡ እያየኋት ጠፋች ፡ እንደ አየር ጢያራ፣ ደመናማው ሰማይ ይብላኝ ለሷ ፣ ጠራ። : እያልኩኝ ደንፍቼ ላገኘሁት ሁሉ ፣ ጉራዬን ስነፋ “ረሳኋት “ በሚል አንድ ከንቱ ግጥም ፣ ብቅ አለች ተጽፋ። ኡፋ 🥹 @gGetem @gGetem @leoyri

  • 11 авг.8331из gGetem

    👩‍💼ከሚላ 3✍ (መምጫሽ ነው መሰለኝ...) #ገጣሚ_ሊዮ_ማክ 🎤🗣 #ግራፊክስ_ሲፈን_አባተ 🤷‍♀🎑 #ማጀቢያ_ነቢያት_ፊሊሞን 🙍‍♀🎼 #ኤዲቲንግ_አዲስአለም_ኪዳኔ 💇‍♀🎬 #ግብዐተ_ድምፅ_ማክዳ_ሀይለ 🙋‍♀🎧 የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋 #የጥበብ_ማዕድ @gGetem 4 Join @leoyri 4comment... መታሰቢያ ዘመነ ህዳር 19/2011ዓ.ም የሳምንቱ ምርጥ_🫡

  • [በላይ በቀለ ወያ] . እኖር ብዬ ብታረድም ፣ ለመኖር ስል ብሰደድም እኖር ብዬ ብጨነቅም ፣ እኖር ብዬ ብዋረድም ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው… አንዴ እንደመኖር አይከብድም! መኖር ከመምት አይልቅም ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡ . የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል… በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡ ያልኖረ አያውቅም ሞቶ። . መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ መኖር እንጂ የሚያስከፋኝ መኖር እንጂ የገደለኝ መኖር እንጂ የበደለኝ ሞት አያምም ካቆሰለኝ ምት አያምም ከገደለኝ! . @gGetem @gGetem @gGetem

  • ላንዱ ጥቅስ ፣ላንዱ ጥብስ ላንዱ ዕምባ፣ ላንዱ ጥርስ ፤ ለአንደኛው መረቅ ለሌላኛው መብረቅ፤ ለአንደኛው መርዟን ለሌላኛው ብርዟን፤ ትሰጣለች ዓለም … በጎዶሎ ሚዛን ። ሆኖም ብንከፋም! እኩል እያደለን ጸሀይና ዝናብ እኩል ቀኑን ከፍሎ ያለ ምንም ሂሳብ ለቺስታ እና ሀብታም፤ እኩል አጽናፍ ሰማይ አየሩን እንደማይ ሳይሸራርፍ ሰ’ቶ ግራ አጋባን ከቶ ! በመርዝ እና ብርዙ እ’ሱን ለመሳደብ አፉችን ተከፍቶ … ደግሞ በአድናቆት ቀረ ሳይዘጋ … : እኩል እየመሸ እኩል ስለነጋ። (ሚካኤል አ) @leoyri @gGetem

  • =እኔ ነኝ የማውቀው = አንዴ ብቻ ይድላኝ አንዴ ብቻ ልረፍ አንዴ ብቻ ልኑር አንዴ ብቻ ልትረፍ ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገው እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማውቀው። ሀብታሙ ሀደራ (እንዲህ ያለም የለ) @gGetem @getem

  • 27 июл.2473из gGetem

    የሀና ሀይሉ ግጥም - #ደረስንልሽ_ሀገሬ አንቺን ማቃጠሉ ስለሚቀል እንጂ ጭስ በጭስ የሆነው እሳቱን ለማጥፋት ስላንቺ ሚማገድ ከአመዱ መሀል ብዙ ሰው ነው ያለው @gGetem @gGetem @hanahailu ለአስተያየት @Leoyri

  • (በላይ በቀለ ወያ) በሰው አእምሮ ልክ በሰው እውቀት መጠን፤ ያለሁ ተወስኜ የአሁንን ብቻ ነው... ልነግርሽ ምችለው ፤ እርግጠኛ ሆኜ በኋላ ምን ቢሆን ፤ ነገ ምን ቢፈጠር መገመት ነው እንጂ ፣ ተስፋ መድረግ እንጂ ፣ እርግጠኛ ሆኜ አልችልም በናገር፡፡ እናም አሁን ላይ ነው ! ከራስ አስበልጦ ፣ የኔ አንቺን መውደድ ፣ የኔ አንቺን ማፍቀር፡፡ ።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ በኋላ ብርቅሽ ፣ ነገ ላይ ብጠላሽ ፣ ‹‹አይወደኝም ነበር›› ዋሽቷል እንዳትይኝ የአሁን እውነቴን ፤ ዘላለም እመኚኝ፡፡ ምክንያቱም የኔ ውድ በኋላን ያለፈ ፤ ነገን የሚሻገር አሁን ነው ሰው መጥላት፤ አሁን ነው ሰው ማፍቀር ቅፅበት ነው መለየት ፤ ቅፅበት ነው መጣመር፡፡ ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ እናም አሁኔ ላይ….. ከራሴ አስበልጬ ፣ አንቺን ያፈቀርኩሽ እናም አሁኔ ላይ….. የዘልዓለሜ ነሽ ፣ ብዬ እንደነገርኩሽ ቀናቶች ወራቶች ፥ አመታቶች ሁሉ እኔ አንቺን ሳፈቅርሽ የእድሜ ዘመናቶች ፣ አሁኔ ላይ አሉ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ በኋላ ብርቅሽ ነገ ላይ ብጠላሽ "አይወደኝም ነበር " ፣ዋሽቷል እንዳትይኝ የአሁን እውነቴን ፤ ዘላለም እመኚኝ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ @gGetem @gGetem @gGetem

  • የእግረ መንገድ ኑሮ... ሊዮ ማ° ብዙ ቀናቶቼን እንዲሁም ህልሞችን በመሳቀቅ አዚም በይሉኝታ ልማድ ስሰርዝ ስደልዝ  ከራሴ ላይ ሳወርድ ህይወቴን ዘንግቼ በሰው እንድወደድ እኔው ሆኜ ሳለ የእኔው ተጠያቂ ግን አድርጌ ሾሜ ሰዎችን አዋቂ ሲሻቸው ሲያቆሙኝ ሲያሻቸው ሲጥሉኝ ይሄም ልክ መሰሎኝ ድንገት ግን ስነቃ የመሞት ያክል ነው ይሄ ሁሉ በቃ!!! ማንም ያሻውን ቢል ከፀጉርህ ቅንጣት አንዲቷ ለማትጎል ለምን በ'ፍረት ወጥመድ ተይዤ ልታጎል ትናንት ዛሬ ሆኖ ቦታውን ለማይለቅ መደሰት ነው ዛሬን ያላንዳች መጨነቅ። "እንዲህ ልክ አደለም!!! Truth Story🙄 @leoyri @gGetem

  • видео или голосовое, без подписи

  • #ጠብቄሽ_ነበረ . ገጣሚ ደበበ ሰይፉ አንባቢ ሲራክ @gGetem

  • ጥያቄ አልባ ሟቾች! (ሚካኤል አስጨናቂ) ።።። የኤልሻዳዩን ንጉስ ~ ስልጣን ተገዳድሮ 'ንጉስ ነኝ' ሲላቸው ~ ሳጥናኤል ፎክሮ መግዘፉን ያዩቱ ትልቀቱን ያዩቱ ጥቂት መላዕክቶች አምነው ስለነበር ጦር ይዘው ገጠሙ.. የንጉስ ክብሩ  ቅጥሩ እንዳይደፈር ። ።።። እነዛ የዋሆች! በርግጥ አማች ናቸው.. ጥያቄ አንስተው መጠርጠር አያውቁም የገዘፈን ሁሉ የተለቀን ሁሉ ንጉስ ነው ከማለት ከቶ አይቦዝኑም። ።።። እነዛም መላዕክት! ንጉስ ነው ላሉቱ ቀድመው ላመኑቱ . 'ጦር ያዙ' ሲላቸው! 'ግጠሙ' ሲላቸው! 'ግደሉ'   ሲላቸው! . መጠየቅ አይደለም... ጦር ይዘው መግደል ነው ጦር ይዘው መግጠም ነው የእሺታ መልሳቸው። ።።። እነዛም ወታደር! አገልጋይ መላዕክት ጦር ይዘው ሲሮጡ ጦር ይዘው ሲገድሉ ጥያቄ አንስተው 'ለምን?' ስለማይሉ ተሸንፈው እንኳ.. ከሰማይ ከተሞች ወደ ታች ሲጣሉ . ያመኑቱ ንጉስ! "ተረታችሁ ሳይሆን እግዜሩ ፈርቷችሁ ወደ ላይ ሸሽቶ ነው" ብሎ ሲነግራቸው.... . 'ሀሰት ይሆን?' ብለው ሳይጠረጥሩ ነው... የሲኦል ወላፈን ፥ እሳት  የበላቸው። @gGetem @sirak6 Join&share🍎

  • ሲኖር የሚገርመኝ አይደለም እንደ ሟች ይሄ ሁሉ ተጓዥ ፣ ይሄ ሁሉ ዘማች ፤ ሁሉም ጥሬ አሳሽ ፣ ስብስብ ነው የዶሮ አነር ያድነዋል ፣ እንደ ዱር መንጥሮ። ከስብስቡ መኃል ፣ ባለቀን ሲነጠቅ ሌላው ዶሮ ይጮኃል ፣ ፈርቶ በመሳቀቅ። ሲሞላ ግን አፍታ እየው አበክረህ ወንድሙን የሸኘ ያን አልቃሻ ዶሮ ጥሬ ይናጠቃል ዛሬም እንደ ዱሮ። አይገርምም ? አይደንቅም? የሞት ማግስት ወጉ አነርን ይረሳል የዶሮ ዝንጉ። 🐓 (ሚካኤል አ) @gGetem @gGetem @gGetem

  • ሰብለ ንዳድ ሊዮ ማ° የእሳት መንገድ በበዛበት ፍቅርሽ ገሎኝ እንደ ዘበት ሳሰላስል ሳወላዳ እኔው ሆንኩኝ የእኔው እንግዳ:: @gGetem @leoyri @gGetem

  • 18 июл.32633из sirak6

    ገድለ ፍቅር ሊዮ ማ° ብዙ አሜኬላ በመንገድ ላይ ወድቆ እግራችን ሲደማ ከልባችን ዘልቆ እኔ እና አንቺ ሆነን የእኛው ተጠያቂ ሰው ገብቶብን መሀል ሲሆን እንዳዋቂ ይሁን ብለን ስንተው ንትርክ ጥላቻ ፍርሀት ሆኖብን ሆንን መጫወቻ። ∞∞∞∞∞∞ እንታገል ወይስ ዝምምምምም እንበል እቱ?🙋 @gGetem @gGetem

  • ነጠብጣብ ሀሳቦች (በእውቀቱ ስዩም) በዘመን አየር ፤ ጫጫታው ከብሮ በጩኸት መሀል፤ ዜማ ተቀብሮ ጆሮ ግንባር ላይ፥ ቤቱን ለመስራት እንዳልፈለገ ወደ ማጅራት አፈገፈገ:: **** የሞሰቡን ወግ፥ ፌስታሉ ወርሶት ለምለሙ እንጀራ ፥ ረድኤት አንሶት ቢጎርሱት እንባ ፥ ቢውጡት ብሶት ! **** ምንገዱ ሁሉ ፥የሚያሰናክል ቁልቁለት ሲያዝል ፥ የዳገት ያክል ስኬት በስኒ፥ ላባችን በጋን በወግ ለመሞት ሁሌ እየተጋን መኖር ዘነጋን:: By Bewuketu seyum @gGetem @gGetem @leoyri

  • ለአንድ ጀግና (በእውቀቱ ስዩም) የጠብህን ጠበል፤ ለሁሉ አታዳርሰው ክንድህን አትዘዝ ሠይፍህን አትምዘዝ ሞቶ ለመጣ ሰው፤ የድመቶች ክብር በሞታቸው ሰዓት በነብር ወጥመድ ውስጥ ተንደርድሮ መግባት፤ ለሐሳዊ ነብር፤ ክንድህን አትነቅንቅ በወጉ አያከብርም፤ በወጉ የማይንቅ (ከስብስብ ግጥሞች) @gGetem

  • ገድለ ፍቅር ሊዮ ማ° ብዙ አሜኬላ በመንገድ ላይ ወድቆ እግራችን ሲደማ ከልባችን ዘልቆ እኔ እና አንቺ ሆነን የእኛው ተጠያቂ ሰው ገብቶብን መሀል ሲሆን እንዳዋቂ ይሁን ብለን ስንተው ንትርክ ጥላቻ ፍርሀት ሆኖብን ሆንን መጫወቻ። ∞∞∞∞∞∞ እንታገል ወይስ ዝምምምምም እንበል እቱ?🙋 @gGetem @gGetem

  • (ምን መሰለሽ? ) ሌላን ሴት ጠይቀው ‘እሺ’ የተባሉ … በርግጥ ለአንዲት ቀን ፈክተው ይስቃሉ። ፡ ሆኖም የገረመን ፡ አንቺን ተለማምጠው ‘እንቢ’ ብለሽ እንኳን ድግስ ደግሰዋል.. ዳስ ጥለዋል ድንኳን። ፡ ‘እርሷን ሞክሪያለሁ’ ብለው ስላወሩ ስንቱን ሰው አየነው ኮርተው ሲከበሩ። (ሚካኤል አ) @gGetem @gGetem

  • ፀደይን በመስኮት . ( በእውቀቱ ስዩም) . . ክረምቱ ሲወጣ ርጥብ ዳሱን ነቅሎ አዳሜ ከተሜ ጃንጣላውን ሰቅሎ ካቦርታውን ጥሎ አዳም ከሄዋኑ (ድስት ከነክዳኑ) ላጤውም ለብቻው ወንዱ ደረት ሊያሳይ በባህር ዳርቻው ሴቱም እንደልቡ፤ ቂጡን እየጣለ በሙቅ አሸዋ ላይ እየተንጋለለ ቅብጠት ድርያ፤ ሲያምረው፤ ማጭድ ታጥቆ ገባ ሁሉን የማይምረው፤ ፊት ያለውን ሁሉ በብረት መዳፉ፤ የሚያጠናግረው ፤ እምቢልታ ተነፋ ደወል ተደወለ ያልታደለው ጠፋ ቀሪው እቤት ዋለ ሰው ቤቱ መሸገ መስኮት እንደጋሻ፤ አየወለወለ፤ በየአደባባዩ እዩኝ እዩኝ ባዩ እንዳልተጀነነ ሰው ለመኖር ብሎ፤ ከኑሮ መነነ! እኔም እንዳገሬው፤ ለነፍሴ ብሳሳ ለብሻት ሰነበትኩ፤ ቤቴን እንደገሳ፤ አምና እንዳልነበርኩኝ የተፈጥሮ ሚዜ፤ የፀጋው ተካፋይ የእልፍኝ እስረኛ ነኝ ፤ አጮልቄ የማይ ያውና እዚያ ማዶ፤ጥርት ያለ ሰማይ ያቻት እዚያ ማዶ፤ ያልተሞቀች ፀሀይ! በየልምላሜው በየዛፍ ቅጠሉ ንቡ ወፉ ትሉ ሲቦርቅ ሲራኮት! እኔ ግን ሸኘሁት! ፀደይን በመስኮት @gGetem

የሆሄያት ህብር📝📝 — tgindex