ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄
Статистикаእንኳን ደህና መጡ ወደዚህ ቻናል የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥምና ስነፅሁፎች ከእራሳችንና ከገጣምያን ተሰብስበው የምናደርስበት ስሜታችንን የምንገልፅበት አውድ ነው። ግጥማቹን ሌላ ችሎታቹን ለማጋራት የምትፈልጉ ላኩልን✍️
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 456
- 1/48двое суток
- 522
- 1/72трое суток
- 563
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://vt.tiktok.com/ZS4nCewBf/
ትንሣኤሽን ልየዉ ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣ በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ። ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣ ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ። ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣ አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ። ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣ ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ። ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣ በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ። እንኳን አደረሳችሁ🙏 ✍ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
ብታጭ ለምስራች ታበስረኝ ብትመጣ ስለ አለማመኔ እንደ ዘካርያስ ዲዳነት ነው የኔ ዕጣ ይኩነኒ አላልኩም እንደ እመአምላክ ከአምላክ ፊት የሚቆም ቢላክልኝ መልዓክ ታንኳ ተሰዶልኝ ማህበሉን ማለፊያ እኔን ሚያሳስበኝ ወጀቡን መቅዘፊያ ገብርኤል ገብርኤል መልዓከ ራማ ለደረቀ ልቤ ቃሉን ለተጠማ ላላመነ ነፍሴ ገድሉን እየሰማ ድረስለት ፈጥነህ! እርዳው አለማመኔን ለውጥልኝ ስሜን ! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
Check Out! 👇👇👇👇 https://vt.tiktok.com/ZSXDGbJQk/
t.me/milkoret
t.me/milkoret
ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ ገላሽን ይንካና ወዮለት ሰማዩ ወዮለት ደመና ። ወፍ አይዘምርልሽ ዛፍ አያስጠልልሽ በቃ እኔ አለሁልሽ ። ደግሞ ይሄን እወቂ ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ እንቅልፍ እንደማጣ በፀሐይ ስትፈኪ ምራቄ እንደሚመር በእግዜር ስትመኪ ። እኔ ጠባቂሽ እኔ ነኝ ደስታሽ እኔ ነኝ ፈገግታሽ ሁሉንም የምሆን እግዜር አላህ ሰማይ ንፋስ ውሃ ድንጋይ ያንቺ ብቻ አገልጋይ ያንቺ ብቻ ታጋይ ። ክነፍ በዪኝ ልክነፍ እረፍ በዪኝ ልረፍ ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ። By Hab Hd @topazionnn @topazionnn
<< ስትሞት ቀድመህ ምታደርገው ምንድነው >> ስትል ጠየቀችኝ ! መጨረሻዬ ምንም ሆነ ምን ለአምላኬ የማቀርበው አንድ ተማፅኖ ይኖረኛል! << ምን የሚል ? >> በማርያም አንድ ጊዜ መታቀፍን ! በማርያም አንድ ጊዜ መነካትን ! በማርያም አንድ ጊዜ ልጄ መባልን ! በማርያም አንድ ጊዜ መዳሰስን ! ተማፅኖዬ ይሄ ነው ! << መንግሥትህን አውርሰኝ ትላለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር ! >> አቅፋ ለገሃነም እንደማትሰጠኝ አውቃለሁ! በእሷ ተዳስሼ ሲዖልም ብገባ ጠረኗ ገነት ሆኖ ያቆየኛል! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄 pinned a photo
ዛሬ የ ስሜትን በግጥም Channel Owner የሆነችው አ....ፊት ቤዛ......ድ......ማ.... ልደት ነው 😁😁😁 አንቺ የግጥም አርበኛ አንቺ የስንኝ ጦረኛ እሰይ እልልል እንኳን ተወለድሽ 😁😂😂 መወለድሽን ብጠራጠርም መልካም ልደት . . የዕድሜሽ ጉዳይ እየተጣራ ነው 🙏 ✨ መልካም ልደት በሏት ✨ @semetnbegtm
Check out this TikTok I posted! https://vt.tiktok.com/ZSQKKP8tt/
#ከተውሽኝ_ቦታ_ላይ እኔ እዚያው ነኝ ! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
ሰላም ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ።በቶጳዝዮን መወያያ ግሩፓችን ላይ የግጥም ወጋችን ለረጅም ጊዜያት ተቋርጦ እና ተቀዛቅዞ እንደነበር ይታወቃል። ዛሬም እንደተለመደዉ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ የግጥም ወጋችን ይጀመራል።ሀሳባችንን በግጥም መልክ እንገልፃለን። ያልተቀላቀላችሁ ገባ ገባ እያላችሁ።የተቀላቀላችሁ ወዳጅ ጓደኞቻችሁን Add እያደረጋችሁ ጠብቁን።😊😊🙏 https://t.me/topazionnn_gp
@topazionnn @topazionnn @topazionnn
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨ እንዳበባ~ቅጠል እንደ ክረምት~ጠል እንዳለቀ~ከሰል እንደ ጢሰ~ሰንደል ክፍተት እያበጁ በተስፋ እያጃጁ የካብናቸው ሁሉ ቀስ ቀስ እያሉ በዝምታ በደል ተነጠሉን አይደል?!:፧: [ዓለም]
Check out this TikTok I posted! https://www.tiktok.com/@edi_0095/video/7646012989866364168?_r=1&u_code=ddgcfediik36k4&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=f2glie1jll9mi4&share_item_id=7646012989866364168&source=h5_m×tamp=1780226616&user_id=6853133057744110597&sec_user_id=MS4wLjABAAAA28kmgAByne5Yke8n8nkfj8TtnuZ45k5DWoAARpttNuTwOR_lV3Rx5UUTyzyMPPUI&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7644508074707158804&share_link_id=8543a057-a9f2-43cd-b6c4-7d5466bc3fc8&share_app_id=1233&ugbiz_name=MAIN&ug_btm=b8727%2Cb2878&sp_root_share_link_id=8543a057-a9f2-43cd-b6c4-7d5466bc3fc8&link_reflow_popup_iteration_sharer=%7B%22click_empty_to_play%22%3A1%2C%22dynamic_cover%22%3A1%2C%22follow_to_play_duration%22%3A-1.0%2C%22profile_clickable%22%3A1%7D&panel_source_v2=share_panel&share_enter_from=personal_homepage&item_author_type=1&enable_checksum=1&sp_level=1&sp_root_u=ddgcfediik36k4&sp_root_d=f2glie1jll9mi4
#አፍሬ_አላውቅም ከዳቢሎስ በቀር ያፈረብሽ የለም ! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
ፊትሽን አሳይኝ . . . በልቤ የያዝኩትን የሰቀቀን ጭንቄን፤ አያልፍ የሚመስል እልፍ መከራዬን፤ ቃላት ያጣሁለት የዘወትር ሀዘኔን፤ ማንም ያልሰማዉን ያዘልኩት ብሶቴን፤ እንድነግርሽ ዘንዳ ፊትሽን አሳይኝ፤ የምወድሽ ማርያም አንዴ ግለጪልኝ፤ እማዋይሽ እማ ብዙ ምስጢር አለኝ። 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰 "ዘወትር የሚያበራ ፀሐይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤ ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ የምወድሽ ማርያም ሌላ የማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ (አሳይኝ))" (መልክአ ማርያም) ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ በዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
Check out this TikTok I posted! 👇👇👇👇👇👇 https://vt.tiktok.com/ZSx8uAgwF/
አጃኢብ ሰው መዉደድ አጃኢብ ትዝታ........ እንደምን ይቻላል..... ......ናፍቆትን መላመድ የተለዩ ለታ.......... ✍✍ [ ዔደን ታደሰ ] @Edi2_4 @topazionnn @topazionnn